Ethiopian Christian Media

  • Home
  • Ethiopian Christian Media

Ethiopian Christian Media We Share Gospel!

 በ2015 በ6ተኛ ዙር በሁለተኛው ቀን የመልካም ወጣት ስልጠና ላይ   ተቀብለዋል። ፡፡
23/08/2023



በ2015 በ6ተኛ ዙር በሁለተኛው ቀን የመልካም ወጣት ስልጠና ላይ ተቀብለዋል።

፡፡

     ::   በሰማይ ታላቅ ደስታ ሆነ ክብር ለእግዚአብሔር ይሁን🙏🏼
01/08/2023



::

በሰማይ ታላቅ ደስታ ሆነ ክብር ለእግዚአብሔር ይሁን🙏🏼

ያልኖርክበት ዘመን የለምከአንተ በፊት ዘመን አልነበረምዘላለምን ፈጥረህ ለዘላለም ትኖራለህከምልህ በላይ ካዩህም በላይትልቅ ነህ ጌታ ዘመን ዘምኖ ያለወጠ አንተ ነሀ      ይደረግ!
24/07/2023

ያልኖርክበት ዘመን የለም
ከአንተ በፊት ዘመን አልነበረም
ዘላለምን ፈጥረህ ለዘላለም ትኖራለህ

ከምልህ በላይ ካዩህም በላይ
ትልቅ ነህ ጌታ ዘመን ዘምኖ ያለወጠ አንተ ነሀ

ይደረግ!

~ ከዘላለም ሞት~ ከሐጢያት ባርነት~ ከሕግ ኩነኔ~ ከሰይጣን እስራት~ ከክፉ መርገም~ ከዓለማዊ ምኞት ----------   #ኢየሱስ ያድናል!የዘንድሮ የ2015 ዓ.ም ተመራቂ ተመራዎች እንኳን...
20/07/2023

~ ከዘላለም ሞት
~ ከሐጢያት ባርነት
~ ከሕግ ኩነኔ
~ ከሰይጣን እስራት
~ ከክፉ መርገም
~ ከዓለማዊ ምኞት ---------- #ኢየሱስ ያድናል!

የዘንድሮ የ2015 ዓ.ም ተመራቂ ተመራዎች እንኳን ጌታ ረዳችሁ! በአጋጣሚዎች ሁሉ #ኢየሱስን የሚሰብኩ ጀግኖች ጸጋው ይብዛላችሁ! ቅዱሳን #ሼር አድርጉ!

"ቤተ ክርስቲያን ቴአትር ቤት፣ እኛም ኮሜዲያን ሆነናል!"-------------------------------------------------------------------የዶ/ር ማሙሻ ፈንታ መልዕክ...
20/07/2023

"ቤተ ክርስቲያን ቴአትር ቤት፣ እኛም ኮሜዲያን ሆነናል!"
-------------------------------------------------------------------
የዶ/ር ማሙሻ ፈንታ መልዕክት #ሼር #ሼር አድርጉ!

ብዙ አማኝ ወደ ቤተ ክርስቲያን የሚመጣው ለመዝናናት ነው። ሌላውም ሰው ጆክ ሲያምረው፣ መሳቅ ሲፈልግ የእኛን ቪዲዮዎች ነው የሚያየው። በኢየሱስ ስም፣ በልሳን፣ በጸሎት ከት ከት ብሎ ይስቃል። እኛም አብረን እንስቃለን። ምንም ስለማይመስለን ቪዲዮውን እየተቀባበልን እንስቃለን። የእግዚአብሔር ስም መቀለጃ ስለሆነ የሚያየው አይፈራው፣ የሚሰማን አይፈራው። እኛም አላከበድነው በሚገባ አላሳየነው፣ አልገለጥነው፣ አላመጣነው...።

የአብዛኞቻችን አገልጋዮች ዓላማ ራሱ ሰውን ማዝናናት ነው፤ "ምን ብናገር አዝናናዋለሁ ነው።" የብዙ ምዕመናን የቤተ ክርስቲያን፣ የስብከትና የአገልግሎት ምርጫ "የት ብሄድ ያልተካበደ ነገር እሰማለሁ"፣ "መዝናናት አገኛለሁ" የሚል ነው። ቤተ ክርስቲያን ቴአትር ቤት፣ እኛም ኮሜዲያን ሆነናል።

ተዉ እንጂ ብዙም ሩቅ ባልሆኑ ዓመታት፣ የዛሬ ሰልሳ ዓመት ወደ ኃላ "ሪዋይንድ" ብታደርጉ አማኞች የሚፈራ ምገስ ነበራቸው። ሰዎቹ ዛሬም በሕይወት ስላሉ ሄዳችሁ ጠይቋቸው። በቤተ ክርስቲያናቸው ደጃፍ ማለፍ እንኳ ያስፈራ ነበር። ሕይወታቸው ግርማ ነበረው። መልዕክታቸው አስደንጋጭ ነበር። ለማስደንገጥ ብለው ሳይሆን እግዚአብሔር በመካከላቸው ነበር።

እዚያ ለመቀለድ አትሄድም፤ ንሰሐ እንጂ ጆክ ትዝ አይልህም። አጋንንት ይወጣል፣ ሰዎች ይፈወሳሉ። የእግዚአብሔር ቃል፣ የክርስቶስ ወንጌል ይሰበካል። ይኼ ሁሉ የሚሆነው ፐርፌክት [ፍጹማን] ክርስቲያኖች ስለሆኑ አይደለም። ግን የኢየሱስን ስም አስከባሪዎች ነበሩ።

አሁን ቢያንስ ስሙ በሆነ መንገድ ይከበር ዘንድ ብንጸልይስ? ቢያስፈልግ ኮሜዲያኖቹን በጊዜ ቢወስደን፤ ይኼም እኮ አንዱ መንገድ ነው። ወይም ደግሞ ጥግ አስይዞን የሆኑ ሌሎች ሰዎች ቢያመጣ፣ እኛ ዕድሉን አልጠቀም ስላልን ሌላን ትውልድ ቢያስነሳልን፣ ስላላየናቸው እንጂ እግዚአብሔር ስሙን የሚያስከብሩለት ልጆች አሉታ!...

በዚህ ዘመን ወንጌል የምንሰብክበት ብዙ መድረክ አግኝተን፣ ሚዲያ ተመቻችቶልን አልተጠቀምንበትም። በየሰዉ ቤት የጌታን ስም ተሸክመን ለመግባት እንደዚህ ዘመን ዕድል ተሰጥቶን ያውቃል እንዴ? እኛ ግን ጆካችንን ይዘን ገባንበት፤ እግዚአብሔርን መሳለቂያ አደረግነው። ስለዚህ ወገኖቼ በአሕዛብ መካከል የተነቀፈው ማንነቱ የቀለለው ስሙ መልሶ እንዲከብድ በየትኛውም መንገድ ምክንያት ለመሆን መጸለይ አለብን።

ዶ/ር ማሙሻ ፈንታ
Mamusha Fenta

የዘማሪት የምስራች መኮንን "ልጅህ ነኝ!" የሚል የመዝሙር አልበም ሊመረቅ ነው!የመዝሙር አልበሙ የፊታችን እሁድ በሐዋሳ ሪፈራል አካባቢ  ቃለ ሕይወት ቤተክርስትያን የሚመረቅ ሲሆን ፤ ዘማሪዋ...
20/07/2023

የዘማሪት የምስራች መኮንን "ልጅህ ነኝ!" የሚል የመዝሙር አልበም ሊመረቅ ነው!

የመዝሙር አልበሙ የፊታችን እሁድ በሐዋሳ ሪፈራል አካባቢ ቃለ ሕይወት ቤተክርስትያን የሚመረቅ ሲሆን ፤ ዘማሪዋ እጅግ የተወደደችና ጌታ ለዝማሬ የጠራት ድንቅ መልክተኛ ዘማሪ ናት... ስለሆነም በሐዋሳና አካባቢው የምትገኙ ቅዱሳን በዚህ መረሀ ግብር ላይ በመገኘት ይሄን ድንቅ አልበም እንድታስመርቁ በጌታ ፍቅር ተጋብዛችኋል!

የተወደዳችሁ ቅዱሳን የእግዚአብሔር ልጆች በጌታ ዕርዳታ ቁጥር ሦስት የመዝሙር ሲዲዬ ዝግጅቴን ጨርሼ  በቅርቡ ይወጣል። ለእናንተ በረከት ለእግዚአብሔርም ክብር እንዲሆን ጌታን እለምናለሁ። ተባ...
03/05/2023

የተወደዳችሁ ቅዱሳን የእግዚአብሔር ልጆች በጌታ ዕርዳታ ቁጥር ሦስት የመዝሙር ሲዲዬ ዝግጅቴን ጨርሼ በቅርቡ ይወጣል። ለእናንተ በረከት ለእግዚአብሔርም ክብር እንዲሆን ጌታን እለምናለሁ። ተባረኩ!!

ዘማሪ ዮሴፍ አያሌው!

ልዩ የአምልኮ ምሽት ከመስኪ ጋር... በዩጎ ቸርች አርብ ሚያዝያ 27/2015አብራችሁን እንድታመልኩ ሁላችሁም በአክብሮት ተጋብዛችኋል!
03/05/2023

ልዩ የአምልኮ ምሽት ከመስኪ ጋር... በዩጎ ቸርች አርብ ሚያዝያ 27/2015

አብራችሁን እንድታመልኩ ሁላችሁም በአክብሮት ተጋብዛችኋል!

 #ርኆቦት ፦ 63 የድል ዓመታት!የሀዋሳ የሕይወት ብርሃን ቤተክርስቲያን 63ኛ ዓመት የምስረታ ክብረ በዓል በደማቅ ተከብሯል! ጌታ ከፍ ብሏል።"አሁን እግዚአብሔር አሰፋልን፥ በምድርም እንበዛ...
03/05/2023

#ርኆቦት ፦ 63 የድል ዓመታት!
የሀዋሳ የሕይወት ብርሃን ቤተክርስቲያን 63ኛ ዓመት የምስረታ ክብረ በዓል በደማቅ ተከብሯል! ጌታ ከፍ ብሏል።

"አሁን እግዚአብሔር አሰፋልን፥ በምድርም እንበዛለን።” ዘፍ 26፥22


!

ላላገባችሁ...ትዳር የእግዚአብሔር ስጦታ ነው:። በጌታ በኢየሱስ ከእግዚአብሔር የሆነ ትዳር ይዘጋጅላችሁ።መጋቢ ቢኒያም ዋለ እና ባለቤቱን የምትወዱ ባርኳቸው!
03/05/2023

ላላገባችሁ...

ትዳር የእግዚአብሔር ስጦታ ነው:። በጌታ በኢየሱስ ከእግዚአብሔር የሆነ ትዳር ይዘጋጅላችሁ።

መጋቢ ቢኒያም ዋለ እና ባለቤቱን የምትወዱ ባርኳቸው!

የአዲስ አበባና አካባቢው    /ቤት    #መጀመሩን አስመልክቶ የመክፈቻ መርሐ ግብር ተካሄደ።ሰኞ ሚያዝያ 23/15 የአዲስ አበባና አካባቢው ቃለ ሕይወት ቤተክርስቲያን የቀጠና ጽ/ቤት በኮልፌ...
03/05/2023

የአዲስ አበባና አካባቢው /ቤት #መጀመሩን አስመልክቶ የመክፈቻ መርሐ ግብር ተካሄደ።

ሰኞ ሚያዝያ 23/15 የአዲስ አበባና አካባቢው ቃለ ሕይወት ቤተክርስቲያን የቀጠና ጽ/ቤት በኮልፌ ቃለ ሕይወት ቤተክርስቲያን የ52 ቀናት የወንጌል ስርጭት የመክፈቻ መርሐ ግብር የተካሄደ ሲሆን በዶ/ር አለሙ ቢፍቱ በጸሎት ተጀምሮአል።

በመቀጠልም የኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤ/ክን ጸሃፊ በሆኑት በዶ/ር ስሞን ሙላት የመክፈቻ ንግግር ተደርጎል።

በዘማሪ መስፍን ጉቱ ዝማሬ ቀርቦ ጉባኤው ጌታን አምልኮአል።

በመጋቢ መስፈን ሙሉጌታ "የወደቀችውን የዳዊትን ድንኳን አነሳለሁ" በሚል መሪ ሀሳብ የእግዚአብሔር ቃል የቀረበ ሲሆን ቀጣይ ዘመን ኢትዮጵያ እና አፍሪካ ወንጌልን ይዞ በመነሳት ለመላው አለም የመንፈስ ቅዱስ የተሃድሶ ጊዜ እንደሚሆን ተናግረዋል።

52 ቀናት የወንጌል ስርጭት ከማያዝያ 24 እስከ ሰኔ 16 ድረስ የሚቆይና በዚህም ለአንድ ሚልየን ሰዎች ወንጌል ተሰብኮ ሰኔ 17 እና 18 በሚልንየም አዳራሽ የወንጌል ኮንፈረንስ እንደሚካሄድ ከአዘጋጆቹ ለማወቅ ተችሎአል።


ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!!!!!

በአርባ ምንጭ ከተማ ሲካሄድ የነበረው 62ኛው የኢትዮጵያ ቃለ ህይወት ቤተ/ን ጠቅላላ ጉባዔ በስኬት ተጠናቋል።በጉባዔው ላይ የተለያዩ የቤተ ክርስቲያኒቱን ቀጣይ የአገልግሎት አድማስ የሚያሰፉ ...
07/04/2023

በአርባ ምንጭ ከተማ ሲካሄድ የነበረው 62ኛው የኢትዮጵያ ቃለ ህይወት ቤተ/ን ጠቅላላ ጉባዔ በስኬት ተጠናቋል።

በጉባዔው ላይ የተለያዩ የቤተ ክርስቲያኒቱን ቀጣይ የአገልግሎት አድማስ የሚያሰፉ እቅዶች የጸደቁ እና ውሳኔዎች የተላለፉ ሲሆን ፤ ቤተ ክርስቲያኒቱን ላለፉት አራት አመታት በዋና ጸሐፊነት ያገለገሉት ዶ/ር ስምዖን ሙላቱ እንዲሁም ለአራት አመታት በልማት ኮሚሽነርነት ያገለገሉት ዶ/ር ተፈራ ተሎሬ ለቀጣይ አራት አመታት በድጋሚ እንዲያገለግሉ ተመርጠዋል።

እንኳን አደረሳችሁ ~ እንኳን ደስም አለን!የሰመራ ዩኒቨርስቲ ክርስቲያን ተማሪዎች ህብረት የተመሰረተበትን 15ኛ ዓመት ክብረ በዓል ፥ ጌታ ረድቷቸው በዚህ መልኩ በደማቁ አክብረዋል።እግዚአብሔ...
06/04/2023

እንኳን አደረሳችሁ ~ እንኳን ደስም አለን!

የሰመራ ዩኒቨርስቲ ክርስቲያን ተማሪዎች ህብረት የተመሰረተበትን 15ኛ ዓመት ክብረ በዓል ፥ ጌታ ረድቷቸው በዚህ መልኩ በደማቁ አክብረዋል።

እግዚአብሔር በሰመራ ዩኒቨርስቲ እየሰራ ስላለው ሥራ ስሙ ይባረክ!

Sola - ብቻአዲስ መዝሙር ~ በቅርብ ቀን ~ በሐና ተክሌሶላ (Sola) የላቲን ቃል ሲሆን ትርጉሙም "ብቻ" እንደማለት ነው። በውስጡም "ተጨማሪ የሆኑ ነገሮች አያስፈልጉም" የሚልን መልዕክ...
06/04/2023

Sola - ብቻ
አዲስ መዝሙር ~ በቅርብ ቀን ~ በሐና ተክሌ

ሶላ (Sola) የላቲን ቃል ሲሆን ትርጉሙም "ብቻ" እንደማለት ነው። በውስጡም "ተጨማሪ የሆኑ ነገሮች አያስፈልጉም" የሚልን መልዕክት አዝሏል።

በፕሮቴስታንት ተሐድሶ ወቅት የተሐድሶ መሪዎች ከመጽሃፍ ቅዱሱ የወንጌል እውነት ፈቀቅ የተባሉባቸውን በርካታ ጉዳዮችን አንስተው ሞግተዋል። "አምስቱ ብቻዎች" | "The five solas" | በመባል የሚታወቁት ሃሳቦችም የተሐድሶውን አጠቃላይ አሳብ በአጭሩ ማንጸባረቅ የቻሉ አንኳር ነጥቦች ነበሩ።

አምስቱ ብቻዎች ("The Five Solas") በመባል የሚታወቁት ነጥቦች አጋዥም ሆነ ጭማሪ የማያስፈልጋቸውን አምስት የክርስትና ዋና ዋና ሃሳቦችን የሚገልጹ ሲሆኑ እንደአንድ አማኝ ሁሉም ሰው ሊያውቃቸው የተገቡ መሰረታዊ የክርስትና እውነቶች ናቸው።

እነርሱም የሚከተሉት ናቸው፡ -

1 -በጸጋ ብቻ | Grace Alone | Sola Gratia.

“በበደላችን ሙታን ሆነን ሳለ፣ በክርስቶስ ሕያዋን አደረገን፤ የዳናችሁት በጸጋ ነው።”
ኤፌሶን 2፥5 (አዲሱ መ.ት)

2. በእምነት ብቻ | Faith Alone | Sola Fide

“ሰው በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን እንጂ፣ ሕግን በመጠበቅ እንደማይጸድቅ እናውቃለን። ስለዚህ ሕግን በመጠበቅ ሳይሆን፣ በክርስቶስ በማመን እንጸድቅ ዘንድ እኛም ደግሞ በክርስቶስ ኢየሱስ አምነናል፤ ሕግን በመጠበቅ ማንም አይጸድቅምና።”
ገላትያ 2፥16 (አዲሱ መ.ት)

3. በእግዚአብሔር ቃል ብቻ/ቃሉ ብቻ| Scripture Alone | Sola Scriptura

“ከሕፃንነትህም ጀምረህ፣ በክርስቶስ ኢየሱስ በማመን መዳን የሚገኝበትን ጥበብ ሊሰጡህ የሚችሉትን ቅዱሳት መጻሕፍትን ዐውቀሃል።”
2ኛ ጢሞቴዎስ 3፥15 (አዲሱ መ.ት)

4. • በክርስቶስ ብቻ/ክርስቶስ ብቻ | Christ Alone | Solus Christus

“ኢየሱስም እንዲህ አለው፤ “መንገዱ እኔ ነኝ፤ እውነትና ሕይወትም እኔው ነኝ፤ በእኔ በኩል ካልሆነ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም።”
ዮሐንስ 14፥6 (አዲሱ መ.ት)

5. ለእግዚአብሔር ክብር ብቻ | For the Glory of GOD Alone| Soli Deo Gloria

“ሁሉም ከእርሱ፣ በእርሱ፣ ለእርሱ ነውና፤ ለእርሱ ለዘላለም ክብር ይሁን፤ አሜን።”
ሮሜ 11፥36 (አዲሱ መ.ት)

• በፀጋ ብቻ
• በእምነት ብቻ
• በክርስቶስ ብቻ
• በእግዚአብሔር ቃል ብቻ
• ለእግዚአብሔር ክብር ብቻ

ይህንን ሀሳብ ለማውሳት ያህል በጣም በጥቂቱ ይህንን ካልን በእያንዳንዱ ነጥብ ውስጥ ሰፋፊ ዝርዝር ሀሳብ ስላለው ከዚህ በተሻለ የመፅሀፍቅዱስ አስተማሪዎች ብዙ ማለት ስለሚችሉ መማማር እንችላለን!

መምህሩ የተሰኘዉ አልበሜ ሰኞ (መጋቢት 1/2015) በ Bereket Tesfaye official YouTube channel ላይ 14 ዝማሬዎች ይለቀቃሉ። ከኔጋ በፀሎትና በተለያየ ነገር ስታግዙኝ...
06/04/2023

መምህሩ የተሰኘዉ አልበሜ ሰኞ (መጋቢት 1/2015) በ Bereket Tesfaye official YouTube channel ላይ 14 ዝማሬዎች ይለቀቃሉ። ከኔጋ በፀሎትና በተለያየ ነገር ስታግዙኝና ስትረዱኝ የነበራቹ ወገኖቼ ጌታ ኢየሱስ ይባርካቹ። እወዳችኋለዉ። ባለቤቴ ሊዱ ጌታ ዘመንሽን ይባርክ በዛሁሉ ከባድ ጊዜአት አብረሺኝ ስለቆምሽ ስላገዝሽኝ እሱ ጌታዬ ይባርክሽ።

Bereket Tesfaye

 #ለአፋር ቤተክርስቲያን እንድረስላት!በአፋር ክልል ዞን 3 አሚበራ ወረዳ የምትገኝ የሰርካሞ መሰረት ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ምዕመናን በሚያሳዝን መልኩ የአምልኮ ስፍራቸው በጎርፍ ፈርሶ ፥ እ...
06/04/2023

#ለአፋር ቤተክርስቲያን እንድረስላት!

በአፋር ክልል ዞን 3 አሚበራ ወረዳ የምትገኝ የሰርካሞ መሰረት ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ምዕመናን በሚያሳዝን መልኩ የአምልኮ ስፍራቸው በጎርፍ ፈርሶ ፥ እንደምታይዋቸው ሜዳ ላይ እያመለኩ ይገኛሉ። ስለሆነም ፥ ይህችን የክርስቶስ ቤተክርስቲያን መልሰን መስራት አለብንና ፤ እባካችሁ ይሄን መልዕክት የምትመለከቱ ቅዱሳን ሁላችንም የአቅማችንን በመለገስ እንድረስላቸው...


ሰርካሞ መሰረት ክርስቶስ ቤተክርስቲያን

ንግድ ባንክ(CBE) 👉 1000141539737
አቢሲንያ Bank 👉 133364517
coop Bank 👉 1018400093528


እባካችሁ የአቅማችንን በማስገባት እናገልግል! ደግሞም መልዕክቱን ለሌሎች #ሼር ያድርጉ!

01/04/2023

በኢየሱስ በኩል ወደ እግዚአብሔር ከተማ ደርሳችኋል! ይህን ድንቅ መልዕክት

 የቄስና የክቡር ዶክተር በሊና ሳርካ ከመሞታቸው በፊት ለቤተሰቦቻቸውና ለቅርብ ሰዎች "እኔ ሽኝት ላይ ማንም ጥቁር እንዳይለብስ ሁሉም ነጭ ልብስ ይልበስ.. ሁሉም ሰው እያለቀሰ ሳይሆን እየዘ...
09/12/2022



የቄስና የክቡር ዶክተር በሊና ሳርካ ከመሞታቸው በፊት ለቤተሰቦቻቸውና ለቅርብ ሰዎች "እኔ ሽኝት ላይ ማንም ጥቁር እንዳይለብስ ሁሉም ነጭ ልብስ ይልበስ.. ሁሉም ሰው እያለቀሰ ሳይሆን እየዘመረ ይሸኘኝ" ብለዋል። በፊታችን ሰኞ በሚደረገው ሽኝት ላይ ሁሉም ሰው ነጭ ልብሱን ለብሶ ይገኝ። እግዚአብሔር ይባርካችሁ!!!

#የወንጌል አርበኛ አባባ ቄስ በሊና ሣርካ ማን ናቸው ?

#ቄስ በሊና ሣርካ በ1934 ዓ.ም በአሙማ ሄና በቦጂ ድርመጂ ወረዳ ተወለዱ በትውልድ ስፍራቸው ቦጂ ከአንደኛ እስከ ሰባተኛ ክፍል ተማሩ የስምንተኛ ክፍል አገር አቀፍ ፈተናን በነጆ ተምረው እዚያው ነጆ የአንደኛ ደረጃ አስተማሪ ሆኑ ማስተማር በጀመሩበት 1954 ገደማ ከወ/ሮ ባጩ አተያ ጋር ትዳር መሰረቱ ስምንተኛ ክፍል አገር አቀፍ ፈተና በወሰዱበት ነጆ ለሦስት አመት ያህል አስተምረው ወደ ትግራይ ለተማሪነት አመሩ ትግራይ በሚገኘው አድዋ ሚሲዮን ት/ቤት ሁለት አመት ያህል በመምህርነት ሰለጠኑ ከሁለት አመቱ የአድዋ ትምህርት በኃላ ወደ ነጆ በመመለስ ከ1959-1961 ዓ/ም በመምህርነት አገለገሉ በ1961 ዓ.ም ወደ ነቀምቴ አመሩ በነቀምቴም እስከ 1965 ዓ.ም ድረስ ወደ ውስጣቸው ሰርፆ በገባው መምህርነት ቀጠሉ ከብላቴንነት ዘመናቸው ጀምሮ በእግዚአብሔር ቤት ያደጉት ቄስ በሊና የቀለም ትምህርት አስተማርነታቸውን በ1965 ዓ.ም እዚያው ነቀምቴ ፍፃሜውን #ቄስ።

#በ1964 ዓ.ም መንፈሳዊ ሕይወታቸው እንግዳ ክስተትን አሰተናገደ ለብዙዎች እንግዳ የሆነው ነገር ከቤተክርስቲያን እንዲገፉ ሊያደርጋቸው ወደ ሚችልበት ደረጃ ግስጋሴውን ተያያዘው በ1964 ዓ.ም ያጋጠማቸው እንግዳ ክስተት በመንፈስ ቅዱስ ኃይል አዲስ ቋንቋ /ልሳን /መናገራቸው ነበር።

#በ1966 ዓ.ም አዲስ አበባ መጥተው መካነ ኢየሱስ ቲዮሎጅ/Theology /ሴሚነሪ ገቡ የሰሚነሪ ትምህርታቸውን በተለያዩ ፈተና ውስጥ አልፎ በ1970 ዓ.ም ተጠናቀቁ።

#በወንጌል አገልግሎት ምክንያት በደርግ 14 ጊዜ የታሰሩና ስለ ወንጌል እውነት የጨከኑ አባት ናቸው በኢህዴግ ጊዜም ከ4 ጊዜ በላይ የታሰረ የወንጌል አር #በወንጌል።

#በ1973 ዓ.ም ወደ አድሰ አበባ በመምጣት የእንጦጦ ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን መካነ ኢየሱስ ካህን ወይም ቄስ ሆኑ። ታርካቸው ይቀጥላል ...(ከፍታ ዘመን ለኢትዮጵያ በሚል በእርሳቸው መፅሐፍ ተፅፈው ይገኛል አግኝታችሁ አንብቡልኝ #ታሪኩን ማወቅ ጤናማ ትምህርት ነውና እላችኋለሁ ‼️ #ቄስ በሊና ሣርካ ስለ ወንጌል የኖሩና ወንጌልን በሕይወት ያሳዩት ትልቅ የወንጌል አርበኛ ናቸዉ በእግዚአብሔር ጥሬ ምክንያት በ81 ዓመታቸው ወደሚወዱት ጌታ በክብር ተጠሩ

(ወንጌል አሁንም ይቀጥላል ................................)
(የእርሳቸው እንባ ብዙ የወንጌል አርበኞችን ይወለዳል)
(የሕይወት ታሪካቸው በእርሳቸው መፅሐፍ "የከፍታ ዘመን ለኢትዮጵያ "በሚል መፅሐፍ ገፅ ፦4-14 ድረስ ይገኛል ።
😭እግዚአብሔር ለመላው አብያተክርስቲያናት መፅናናትን ይስጠን አሜን ።

ስንኖር መጓጓት እና መጠንቀቅ ያለብን በምንዘራው ዘር አይነት እና ጥራት እንጂ በመጨረሻ በምንሰበስበው ፍሬ አይሁን የመጨረሻው የሚመጣው ከጅማሬው ነው ::ወዳጆቼ ሰብረን አቁስለን እናደን ለራ...
09/12/2022

ስንኖር መጓጓት እና መጠንቀቅ ያለብን በምንዘራው ዘር አይነት እና ጥራት እንጂ በመጨረሻ በምንሰበስበው ፍሬ አይሁን የመጨረሻው የሚመጣው ከጅማሬው ነው ::
ወዳጆቼ ሰብረን አቁስለን እናደን ለራሳችን ብቻ ኖረን ስንጨርስ የሚወዱን የሚሳሱልን የራሳቸውን ረስተው የእኛን የሚኖሩልን ስንጠብቅ ማርፈድ ሞኝነት ነው .....የዘሩ ጊዜ ወሳኝ ነውና እጄ ላይ ላለው :ልሰጠው ለምችለው :ከእኔ ለሚወጣው ሀሳብ ጉልበት አስተያየት ፍቅር እና አብሮነት መጠንቀቁ ጥሩ ነው !
አጨዳው ወይ ያስደንቀናል ወይ ያስደብረናል እና የማንደበርበትን ዘር እንዝራ!

Gashaw
#የንጉሱ ሴት ልጆች/The KIng’s Daughter

09/12/2022

Pastor Tesfaye Gabiso blessing song... ያድርጉ

አዕምሮን የሚከፍተው መጽሐፍ ቅዱስ ነው! ምክንያቱም መጽሐፍ እንዲህ ይላልና ፦"የእግዚአብሔር ሕግ ፍጹም ነው፤ ነፍስን ይመልሳል፤ የእግዚአብሔር ምስክር የታመነ ነው፤ ሕፃናትን ጠቢባን ያደርጋ...
02/12/2022

አዕምሮን የሚከፍተው መጽሐፍ ቅዱስ ነው! ምክንያቱም መጽሐፍ እንዲህ ይላልና ፦
"የእግዚአብሔር ሕግ ፍጹም ነው፤ ነፍስን ይመልሳል፤ የእግዚአብሔር ምስክር የታመነ ነው፤ ሕፃናትን ጠቢባን ያደርጋል።" (መዝሙረ ዳዊት 19:7)

እና ያድርጉ

ማዳን የእግዚአብሔር ነው::ሰላም ቅዱሳን ፀጋ እና ሰላም ይብዛላችሁ:: ዛሬ ከእኛ አቅምበላይ የሆነን ነገር ላካፍላችሁ:: የምንወዳት እህታችንዘማሪት መክሊት ግርማ Meklit Girma በደም ...
02/12/2022

ማዳን የእግዚአብሔር ነው::

ሰላም ቅዱሳን ፀጋ እና ሰላም ይብዛላችሁ:: ዛሬ ከእኛ አቅም
በላይ የሆነን ነገር ላካፍላችሁ:: የምንወዳት እህታችን
ዘማሪት መክሊት ግርማ Meklit Girma በደም ካንሰር
ህመም በመታመም ላይ ስትሆን ወደ ጥቁር አንበሳ
ሆስፒታል ገብታ ህክምና ብትጀምርም ወዲያውኑ ህክምና
ማግኘት ባለመቻሏ እና ህመሙ እየካፋ በመምጣቱ
በአስቸኳይ ከሀገር ውጭ መታከም እንዳለባት ተብሏል::
ይህ ደግሞ ከቤተሰቦቿ አቅም በላይ ስለሆነ የእህታችንን
ሕይወት ለመታደግ የእናንተ ድጋፍ አስፈልጎናል ::

ምንችል
በፀሎት
በገንዘብ
Share በማድረግ

Gofundme እስኪከፈት
1, በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
1000229767503 መክሊት ግርማ ጊንጆ (ዘማሪት)

2, በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
1000020061457 ግርማ ጊንጆ ሰጠና ( ወላጅአባት)

3, ብርሃን ባንክ 1000675368220 ግርማ ጊንጆ ሰጠና

ይደረግ

"በወንጌል አላፍርምና ፤ አስቀድሞ ለአይሁዳዊ ደግሞም ለግሪክ ሰው ፥ ለሚያምኑ ሁሉ የእግዚአብሔር ኃይል ለማዳን ነውና።" (ሮሜ 1:16)  እና   ያድርጉ!
27/11/2022

"በወንጌል አላፍርምና ፤ አስቀድሞ ለአይሁዳዊ ደግሞም ለግሪክ ሰው ፥ ለሚያምኑ ሁሉ የእግዚአብሔር ኃይል ለማዳን ነውና።" (ሮሜ 1:16)

እና ያድርጉ!

25/11/2022

Address


Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethiopian Christian Media posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Videos

Shortcuts

  • Address
  • Alerts
  • Videos
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share