01/02/2023
የጠቅላይ ሚኒስተሩ አድሏዊ የንግግር ግድፈቶች
***
ጠቅላይ ሚንስትሩ ቅድስት ቤተክርስትያን ያጋጠማትን ፈተና ላይ ያደረጉትን ንግግር አዳመጥኩኝ።
የጠላይ ሚንስትር ንግግር ህግን የሚያስከብር እንደ ትልቅ ሀገራዊ የመንግስት መሪ ሳይሆን በሁለት ጎን ተወዳጅ ሸንጋይ ቃል ወርዋሪ አካል ተጫውተው አልፈዋል።
"ባለውለታ ሆኜ እንዴት እታማለው" አይነት ልብ የሚያራራ ንግግሮች ረጅሙን ሰዓት ቢወስዱም ለማሳዘን በተኬደው ሆደ ቡቡ ቃላቶች መሃል እነዚህ ግድፈቶች ግን ፈጠው ይታያሉ።
***
ግድፈት ፪
>
ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስተሩ ነካ አድርገው ለማለፍ የሞከሩት ንግግር ከዬትኛው የታሪክ ዶሴ እንደተገኘ ባላውቅም "የነገስታት ሃይማኖት" ተብላ በሐሰት ለማማት በር ላይ ለቆሙ ሰዎች" አይዟችሁ በርቱ " የሚል አይነት ጉልበት ሰጪ የተቀበረ ፈንጅ ንግግር ሆኖ አይቸዋለው።
ይህን መንግስታዊ ማማት ብለኸው ትደመድማለህ።
**
ግድፈት ፪
""የትግራይ ጳጳሳት ከኢ/ኦ/ተ/ቤ ሲገነጠል መግለጫ ሳይወጣ የኦሮሚያው ጉዳይ ላይ ግን ጮኸት በዛ"
ይህ ደግሞ ሊደብቁት ያሰቡትን የወሊሶ ህገወጥ ድርጊት ስውር ድጋፍ ሰጪነት ያመላከተ ይመስለኛል።
ይህን ንግግር ከእሳቸው በፊት የወሊሶ ህገ ወጥ ሹመት ደጋፊዎች ሲያደነቁሩን የወላቱን ቃል ከአንድ ሀገር መሪ መስማት በጣም ያስተዛዝባል።
የትግራይ ሊቃነጳጳሳት ኩርፊያን መሰረት ያደረገ ግንጠላ ለማካሄድ ወሰኑ እንጅ የእራሳቸውን ሲኖዶሳዊ መስመር አልዘረጉም።
የትግራይ ጉዳይ በሁሉም ሃይማኖቶች ላይ ፓለቲካው ያመጣው ጥቁር ጠባሳ እንጅ በኢ/ኦ/ተ/ቤ ላይ ብቻ በተናጠል የተካሄደ ልዩ ዘመቻ አይደለም።
የትግራይ ጳጳሳት ፍትህ ነገስትን ጨፍልቀው ህገወጥ ሲመት እና ቅዱስ ፓትርያርክ ምርጫ እቃቃዎሽ ላይ አልገቡም።
ስለዚህ የወሊሶው እን የትግራይ ጉዳይን ማነጻጸር አኩራፊ እና ወንበዴ ልጅን በእኩል ለመዳኘት እንደሞሞከር ነው።
***
ግድፈት ፫
>
ይህን ንግግር ስስማ በእውነት ድንጋጤ ወሮኛል። የእዚህ ንግግር አወንታዊ መገለጫው ቅድስት ቤተክርስቲያን የቋንቋ አገልግሎትን ታፍናለች ለሚል ትርጉም ይጠጋጋል። ጥላቻ እንዲህ ፈጦ ሲገኝ "እግዚኦ" ብለን እንለፈው።
***
ግድፈት ፬
ቤተክርስቲያን በመንግስት ዘንድ ህጋዊ አካል ናት። ስለዚህ ህጋዊ አካል ለወሰነው ውሳኔ ህግ አስከብርልን ተባልክ እንጅ መቼ የመንግስትን ድጋፍ ሻትን?
የአመጸ አካል ሁሉ መቅደስ እየሰበረ በገባ ቁጥር ተደራደሩ ከተባልን ቤተክርስቲያኒቷ በህግ ፊት ያላት እውቅና ከወረቀት አይዘልም።
የኦሮሚያ ልዩ ኃይል እጀባ የሚሰበሩ የሀገረስብከት ጽ/ቤቶች ግን ለማንም ድጋፍ ሰጪ እንዳልሆነ የሚያሳይ እንደሆነ እንቀበል ዘንድ ህጻን መስለንላችዋል መሰለኝ።
***
ትዝብት ፭
>
ይህ ንግግራቸው ደግሞ የአኃዝ ማጭበርበር ተጠቅመው ህዝቡን ህጻን በማድረግ ለመሸወድ ጥረዋል ።
ሃቁን ስንበረብር ግን ወ/ሮ አዳነች አበቤ ከወራት በፊት ለአዲስ አበባ ምክር ቤት ባደረጉት ሪፓርት
ለእስልምና....................... 260,938 ካሬ
ለወንጌላውያን አማኞች........98,290 ካሬ
ለአድቨንቲስት ቸርች............6812 ካሬ
ለካቶሊክ.......................... 7700 ካሬ
ለኦርቶዶክስ .....................ከአንድ ሚሊዬን በላይ ተብሎ ተገልፆል።
ይህን አሐዝ ስናሰላ ከኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ውጪ 373,740 ካሬ ሲያገኙ በጠቅላይ ሚንስትር ንግግር ግን ፣350,000 ሲሉ ለመቀነስ ሞክረዋል።
በነገራችን ላይ የአዲስ አበባ ህዝብ ሃይማኖታዊ ንጽጽር መንግስት እጅ ላይ ባለው ይፋዊ ሰነድ ስንመለከት
ኦርቶዶክስ...... 74.6℅
ሙስሊም....... 16.2℅
ፕሮቴስታንት.....7.8℅
ካቶሊክ ..........0.5%
እና ሌሎች....... 0.9 ይይዛሉ።
በተነገረልን አሐዝ መሰረት እንኳን ስንመለከት
ለአንድ ፐርሰንት ሙስሊም ተከታይ.....16,107 ካሬ መሬት
ለአንድ ፐርሰንት ካቶሊክ ተከታይ....... 15,400 ካሬ መሬት
ለአንድ ፐርሰንት ኦርቶዶክስ ተከታይ.... 13,405 ካሬ መሬት
መሬት እንደተከፋፈለ ቁጥሮች ያሳያሉ። ስለዚህ በመሬት እድላ በኩል እንኳን ለኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ልታደሉ ቀርቶ ከሌላው ቤተእምነት ጋር እኩል መመልከት እንዳልቻላችሁ ያሳያል እና መሬትን አስታካችሁ የምታራግቡት የድጋፍ መሰብሰቢያ ፊሽካ ቢቆም መልካም ነው
መሬት ሰጥተናል በሚለው ሪፓርት ጋር እነ መስቀል አደባባይን ጨምሮ በ4 ዓመት ውስጥ የተወረሱ ኦርቶዶክሳዊ ርስቶችም ምን ያህል እንደሆነ ቢካታቱ መልካም ነው።
ትዝብት ብቻ!!! ለማይቀረው ሰማዕትነት ተዘጋጅ።
Kune Demelash kassaye -Arba Minch