The Amhara Beyond

  • Home
  • The Amhara Beyond

The Amhara Beyond Amhara Insights Abroad

15/12/2020
15/06/2020
የሰሜን ሸዋ አማራ ህዝብ ከሁሉም በከፋ የራሱ አምባገነኖች መዳፍ ስር የወደቀ ህዝብ ነው ፣ ብአዴን አማራን ሁሉ ይጠላል ሸዋን ደግሞ እጅግ አምርሮ ይጠላል ። ትንንት በቱባ መሪው በኩል አዲስ...
09/06/2020

የሰሜን ሸዋ አማራ ህዝብ ከሁሉም በከፋ የራሱ አምባገነኖች መዳፍ ስር የወደቀ ህዝብ ነው ፣ ብአዴን አማራን ሁሉ ይጠላል ሸዋን ደግሞ እጅግ አምርሮ ይጠላል ። ትንንት በቱባ መሪው በኩል አዲስ አበባ የኦሮሞ እንድትሆን አምርረን እንታገላለን ብሎናል ፣ ዛሬም በመግለጫው አዲስ አበባም ልክ እንደ አምቦ ሁሉ የኦሮሞ ናት ብሎናል ።

ምክራችን እንደ The Amhara Observer አማራ ሁሉ ይንቃ ይፍጠን : ሸዋ ደግሞ ሌሎቹን ወነድም አማራወችን ይዞ እጅግ ይፍጠን የሚል ነው ።



ደብረ ብረሃን ከተማ 07 ቀበሌ

በዚህ የኮቨድ -19 ቨይረስ እንደሰድድ እሳት በማህበረሰቡ ውስጥ እየተስፋፋና እየተሰራጨ በአለበት ወቅት ድሃውን የህብረተሰብ ክፍል ለዚህ በሽታ የበለጠ ተጋላጭ የሚያደረጉ ጥቃቄ የጎላቸው የመግስትም ሆነ የግል ድርጅቶች አገልግሎት አሠጣጥ በብዙ ቦታዎች አሁንም ድረስ እንደቀጠሉ ናቸው፡፡ ይህ ሁኔታ ማህበረሰቡን የበለጠ ለበሽታው ተጋላጭ አንዲሆን በማድረግ የሚያስከትለው አደጋ በጣም የከፋ በመሆኑ ትልቅ ትኩረት ሊሰጠው የሚገባ ጉዳይ ነው፡፡ ዛሬ ወደ ታዘበሁት ጉዳይ ስመለስ ደብረ ብረሃን ከተማ ከቅረብ ዓመታት ወዲህ በማደግ ላይ ያች ከተማ ናት፡፡ በረከት ያሉ እቨስተሮች ወደ ከተማዋ በመምጣት በኢንቨስትመንት ስራ ላይ ተሰማረተዋል፡፡

በሌላ በኩል ከእንቨስትመት መስፋፋት ጋረ ተያይዘው የመጡ በረካታ ችግሮች በህብረተሰቡ የዕለት ተለዕት ኑሮ ላይ ጫና እያሳደሩ ይገኛለ፡፡ ለአብነትም ያህል የአካባቢ ብክለት፡ የኑሮ ውድነት፤የሙስና መስፋፋትና በመሠረታዊ ሸቀጦች (ስኳር፤ዘይት) ስርጭትና አከፋፈል፤ ወቅቱን ጠብቆ አለመቅረብ ይጠቀሳሉ፡፡ በተይ በተለይ ትልቅ ትኩረት ሊሰጠው የሚገባው ጉዳይ የስኳር አቅረቦትና ስርጭት ነው፡፡ ስኳር ለህብረተሰቡ የሚቀረበው ወቅቱን ጠብቆ በየወሩ ካለመሆኑ በተጨማሪ በመጣ ጊዜ እንኳን በአግባቡ ደሃው ማህበረሰብ ድርሻውን እንዲያገኝ ከማድረግ አንፃር ከፍተኛ ችግር ነው ያለው፡፡ ደብረ ብርሃን ከተማ ካሉት ዘጠኝ ቀበሌዎች ውስጥ በተለይ ከፍተኛ ችግር የሚስተዋለው ቀበሌ 07 ነው፡፡ የቀበሌው ነዋሪ ሶስት ወይም ሁለት ኪሎ ስኳር ለማግት በትንሹ ሁለት ቀን ቀበሌ መመላለስና ተሰልፎ መዋል ይጠበቅበታል፡፡ የዚህ ሰሞኑ ማለትም ከግንቦት 27/2012 ዓ.ም ጀምሮ በዘመነ ኮርና ወቅት ያለው ምልልስ ደግሞ የከፋና ሳምንቱን ሙሉ ነው፡፡

እድለኛ ሆኖ ተራው የደረሰው ሰው እንኳን ለምሳሌ የተመደበለት ኮታ 5 ኪሎ ከሆነ አንድ ኪሎ ፤ተቀንሶ 4 ኪሎ ይሰጠዋል አንደገና ከአራቱ ኪሎ ላይ ደግሞ ቢያንስ የኪሎ ቅሸባ 15 ግራም ተቀንሶ 3፤85 ኪ.ሎ ስኳር ሶሰት ቀን ወይም ሁለት ቀን ተመላልሶ ያገኛል፡፡ ብዙ ሰዎች ደግሞ ተመላልሰውም አለቀ ተብለው ሳያገኙ የሚቀሩ አሉ፡፡ በዚህ ምክንያት ህዝቡ የተመደበለት ስኳር ሳያገኝ በምሬት ጥሎ ይሄዳል፤የተመደበለትን ኪሎ ይቀንሱበታል በመጨረሻም ስኳሩን አውጥተው ለነጋዴ ይሸጡታል፡፡ ቀበሌ 07 ያለው ችግር በተጨባጭ ይህ ነው፡፡ ይባስ ብሎ ሰሞኑን ደግሞ ኮርና አንዲህ በተሰራፋበት ወቅት ህብረተሰቡ ራሱን ለሽታው በሚያጋልጥ ሁኔታ ስኳር ለማግት ሳምንቱን ሙሉ 07 ቀበሌ አንዲህ ከታች አንደምታዩት በመጉላላት ርቀቱን ሳይጠብቅ ከባድ ችግር ላይ ነውና የሚመለከተው አካል ትኩረት ይስጠው እላለሁ፡፡

ሸዋ መድረሻ አጣ !
ከተገልጋዮች አንዱ!!!

The Amhara Observer

Address


Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when The Amhara Beyond posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

  • Address
  • Alerts
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share