Xayiba Lona- nufi

  • Home
  • Xayiba Lona- nufi

Xayiba Lona- nufi Xayiba Lona-nufi!

የቤላ ልጆች እንኳን ደስ አላችሁ!ቤላ አካባቢ የተገነባውን 3 በ 1 ሁለገብ የስፖርት ማዘውተሪያ ሜዳ በኢትዮጵያ የጣሊያን አምባሳደር ከሆኑት አጉስቲኖ ፓሌስ ጋር በመሆን መርቀን አገልግሎት አ...
10/12/2023

የቤላ ልጆች እንኳን ደስ አላችሁ!

ቤላ አካባቢ የተገነባውን 3 በ 1 ሁለገብ የስፖርት ማዘውተሪያ ሜዳ በኢትዮጵያ የጣሊያን አምባሳደር ከሆኑት አጉስቲኖ ፓሌስ ጋር በመሆን መርቀን አገልግሎት አስጀምረናል።

የጣሊያን ኤምባሲ የትውልድ ግንባታ ስራችን አካል የሆነው የወጣቶችና ህፃናት ስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎችን የማስፋፋት ስራችንን በመደገፍ ዛሬ የመረቅነውን የስፖርት ማዘውተሪያ በመገንባቱ በቤላ ልጆች ስም ማመስገን እወዳለሁ።

አዲስ አበባን ህፃናት ቦርቀው፣ ደስ ብሏቸው፣ በአእምሮ እና በአካል ጎልብተው የሚያድጉባት ከተማ ለማድረግ የጀመርነውን ስራችንን አጠናክረን እንቀጥላለን።
ከንቲባ አዳነች አቤቤ

"ብዝኃነትና እኩልነት ለሀገራዊ አንድነት"በጅግጅጋ በድምቀት እየተከበረ ለሚገኘው 18ኛዉ የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች  ቀን እንኳን በሰላም አደረሳችሁ፣ አደረሰን! ይህ ዕለት በብ...
09/12/2023

"ብዝኃነትና እኩልነት ለሀገራዊ አንድነት"

በጅግጅጋ በድምቀት እየተከበረ ለሚገኘው 18ኛዉ የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን እንኳን በሰላም አደረሳችሁ፣ አደረሰን!

ይህ ዕለት በብዝሀነት ውስጥ አንድነት የሚደምቅበት፣ ሕብረ ብሔራዊ ወንድማማችነትና እህትማማችነት ያስተሳሰረን ህዝቦች በድምቀት በጋራ የምናከብርው፣ በልዩነቶች ውስጥ ያለው አንድነት ጎልቶ የሚታይበት ፣ ኢትዮጵያን ለማበልጸግ የሰነቅነውን ታላቅ ራዕይ ዕውን ለማድረግ የገባነውን ቃል ኪዳን የምናድስበት ቀን ነው።
ኢትዮጵያዊነት አንድ ዓይነትነት አይደለም፤ ኢትዮጵያዊነት መለያየትም አይደለም፤ ኢትዮጵያውያን ከሚለያዩን ጉዳዮች ይልቅ በአንድነት ያጋመዱን ጉዳዮች ይበዛሉ። ኢትዮጵያዊነት መጠሪያችን ብቻ ሳይሆን፣ ማንነታችንም ነው።

መልካም በዓል ይሁንልን
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ!

ከንቲባ አዳነች አቤቤ

"ኢትዮጵያን የማበልጸግ ራዕይ በጋራ የጀመርነው ስለሆነ የሚቆም አይሆንም" ከንቲባ አዳነች አቤቤ--------"ቀጣይ ምዕራፍ ለሁለንተናዊ ለውጥ" በሚል መሪ ቃል በአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች...
05/12/2023

"ኢትዮጵያን የማበልጸግ ራዕይ በጋራ የጀመርነው ስለሆነ የሚቆም አይሆንም" ከንቲባ አዳነች አቤቤ
--------
"ቀጣይ ምዕራፍ ለሁለንተናዊ ለውጥ" በሚል መሪ ቃል በአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት አማክኝነት የተዘጋጀ የምስጋናና የሰላም ኮንፈረንስ በሚሊኒየም አዳራሽ ተካሂዷል።

በኮንፍረንሱ ላይ በክብር እንግድነት የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ባስተላለፉት መልዕክት እያለፍን ያለነው በለውጥ ሂደት እንደመሆኑ በርካታ ፍሬዎችና ድሎችን ከህዝባችን ጋር ሆነን አስመዝግበናል ያሉ ሲሆን ያለ እናንተ ትብብርና ፀሎት አንድም የተገኘ ውጤት የለም ብለዋል።

ከንቲባ አዳነች አክለውም፣ በብዙ ተግዳሮቶች ውስጥ እያለፍን ለውጡን እያስቀጠልን እንደምንገኝ ሁሉ ፈተና በገጠመን ወቅት ሁላችሁም ኃይማኖቶች አገር እንድትቀጥል በተከታታይ ላደረጋችሁት የፀሎት መርሃ-ግብር መንግሥት ዕውቅና ይሰጣልም ብለዋል።

ወደ ሰላም መንገድ ለሚመጣ ኃይል ሁሉ የመንግሥት በር ሁሌም ክፍት መሆኑን ያረጋገጡት ከንቲባ አዳነች፣ ከግጭት ይልቅ ከእርቅ ፣ ከሰላምና አንድነት የምናተርፈው እጅግ ብዙ ነው ሲሉም አሳስበዋ።

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዝደንት ሼኽ ሃጂ ኢብራሂም ቱፋ በሰላምና ምስጋና ኮንፈረንስ ላይባደረጉት ንግግር ሰላም ሲኖር ያቀድነውን ሁሉ ከግብ ማድረስ እንችላለን ያሉ ሲሆን ኢትዮጵያውያን በተገኘንበት ሁሉ በአንድነት ሁሉም ጉዳይ ወደ ወይይት፣ በምክክር ወደ ሚገኝ ሰላማዊ መፍትሔ እንዲመጣ የበኩላችንን ልንወጣ ይገባል ብለዋል።

መርሃ-ግብሩ በዋነኛነት የህዝበ-ሙስሊሙ የዘመናት ጥያቄዎች ከሀገራዊ ለውጡ በኋላ በመንግስት በተገባው ቃል መሰረት በመመለሳቸው በየደረጃው ለህዝበ ሙስሊሙ ጥያቄዎች አስተዋጽኦ ያደረጉ አካላትን የማመስገን ሲሆን በሀገሪቱ ዘላቂ ሰላምን ለማስፈን ህዝበ ሙስሊሙ ሚናውን የበለጠ እንዲወጣም ማድረግን ያለመ ነው።

ከሀገራዊ ለውጡ በኋላ የህዝበ ሙስሊሙ መሪ ተቋም የሆነው የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ጽህፈት ቤት ህጋዊ እውቅና ያለው ተቋም ሆኖ እንዲመሰረት እና ተቋማዊ አደረጃጀቱም እንዲሻሻል መደረጉ ምላሽ ካገኙ ጥያቄዎች መካከሎ አንዱ መሆኑ በመድረኩ ተገልጿል።

በሼሪያ ህግ የሚመሩ ወለድ አልባ ባንኮች መመስረት እና በተለይም በአዲስ አበባ ከተማ ህዝበ ሙስሊሙ የሚያነሳቸው ለአምልኮና ለተለያዩ ማህበራዊ አገልግሎቶች የሚውሉ ቦታዎች ጥያቄ በየደረጃው መመለሳቸውም ሙስሊሙ ማህበረሰብ ካገኛቸው የለውጥ ትሩፋቶች መካከል መሆናቸው ተገልጿል።

በመድረኩ የተለያዩ የመንግስት የስራ ሀላፊዎች፣ የፌደራልና የክልል መጅሊስ አመራሮች፣ ኢማሞች፣ አምባሳደሮችና ዲፕሎማቶች፣ የሐይማኖት ተቋማት መሪዎች፣ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት፣ አምባሳደሮች እና የተለያዩ ሀይማኖቶች መሪዎች ተገኝተዋል።

ለበለጠ መረጃ:

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ የ3ኛ ዓመት 5ኛ መደበኛ ስብሰባውን በማካሄድ በሚከተሉት ጉዳዮች ላይ ውሳኔውን አሳልፏል።የአስተዳደሩ አስፈፃሚ አካል በ2015  ዓመታዊ የስራ  ግምገማ ...
20/11/2023

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ የ3ኛ ዓመት 5ኛ መደበኛ ስብሰባውን በማካሄድ በሚከተሉት ጉዳዮች ላይ ውሳኔውን አሳልፏል።

የአስተዳደሩ አስፈፃሚ አካል በ2015 ዓመታዊ የስራ ግምገማ ወቅት የተሻለ አገልግሎት ለመስጠት ሪፎርም መደረግ ያለባቸውን ተቋማት እና አደረጃጀቶች ለይቶ የማሻሻያ ጥናት እንዲደረግ አቅጣጫ ማስቀመጡ ይታወሳል።
በዚህም መሠረት ፦
1ኛ. በማዕከል ደረጃ የሚታየውን የሠራተኛ ክምችት ቁጥር ከተማዋ ከምታመነጨው ገቢ እና ለህብረተሰብ ከሚሰጠው አገልግሎት አንፃር የማይመጣጠን በመሆኑ ፤ ሰራተኛውን ከፍተኛ የሥራ ጫና ወደ አለባቸው ወረዳ እና ተቋማት ስርጭት እንዲደረግ እና ይህንንም ተቋማት ሙያዊ እና ተፈላጊ ችሎታን ታሳቢ አድርገው እንዲያስተገብሩ እንዲደረግ፣
2ኛ. በመንግስት ከሚሰራው ለ3ተኛ ወገን ወጪ አውት ሶርስ ተደርገው ቢሰሩ ጥሩ እና ተፈላጊውን ውጤት ያመጣሉ ተብለው በጥናት በተለዩት አገልግሎቶች በ3ተኛ ወገን እንዲሰሩ እና ሂደቱን በተመለከተ በቂ ቅድመ ዝግጅት እንዲያደርጉ እንዲሁም የአስተዳደር ችግር እንዳያጋጥም የሽግግር ሂደት እቅድ ተዘጋጅቶ በጠንካራ የሥራ ዲሲፕሊን እንዲመራ፤
3ኛ. በተቋቋመው የሙያተኞች ኰሚቴ ጥናት ተደርጎባቸው ተመልሰው ሪፎርም እንዲደረጉ እና በአዲስ መልክ እንዲደራጁ የተደረጉ ተቋማት ጥናት፣ የአሰራር ሂደት እና አደረጃጀት ሁኔታ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል። የቀረቡትን ማሻሻያ ሀሳቦች በማየት እና በመመርመር ለምክር ቤት እንዲቀርብ ዉሳኔ አሳልፏል።
ከንቲባ አዳነች አቤቤ

የከተማችን ተጨማሪ ድምቀት፣ የአብሮነትና የፍቅር መገለጫ ታላቁ ሩጫ!ከንቲባ አዳነች አቤቤ
19/11/2023

የከተማችን ተጨማሪ ድምቀት፣ የአብሮነትና የፍቅር መገለጫ ታላቁ ሩጫ!

ከንቲባ አዳነች አቤቤ

ኢንቨስትመንት የስራ እድል በመፍጠር ለሃገር ኢኮኖሚ ቀጥታ አስተዋፅዖ የሚያደርግ ዘርፍ ነው። ዛሬ ከፌደራል፣ ከክልሎችና ከከተማ አስተዳደሮች ከተውጣጡ የኢንቨስትመንት አመራሮች የጋራ የምክክር...
17/11/2023

ኢንቨስትመንት የስራ እድል በመፍጠር ለሃገር ኢኮኖሚ ቀጥታ አስተዋፅዖ የሚያደርግ ዘርፍ ነው።

ዛሬ ከፌደራል፣ ከክልሎችና ከከተማ አስተዳደሮች ከተውጣጡ የኢንቨስትመንት አመራሮች የጋራ የምክክር መድረክ ተካሂዷል።
ኢንቨስትመንት ሁሉም ባለድርሻ አካላት በጋራ በማቀድ፣ በተናበበ እና በተቀናጀ መንገድ በመፈፀም፣ ፍሰቱን በመጨመር ለኢኮኖሚያዊ ዕድገትና ለስራ ዕድል ፈጠራ የላቀ አስተዋጽዖ እንዲያበረክት ማድረግ ስለሚያስችል ቅድሚያ ተሰጥቶታል።

አገራችን ወደ ብልፅግና ልትጓዝ የምትችለው ባለሀብቶች ኢንቨስት ሲያደርጉ እና ወጣቶች ወደ ሥራ ሲገቡ በመሆኑ ሁሉም የበኩሉን አስተዋጽዖ ማበርከት ይኖርበታል።

ከንቲባ አዳነች አቤቤ

የስራ ላይ ስልጠና ያጠናቀቁ 5193 ወጣቶች ተመረቁ::የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የስራ ኢንተርፕራይዝና ኢንዲስትሪ ልማት ቢሮ ከዓለም ባንክ ጋር በመተባበር "ብቃት የወጣቶች የስራ ላይ ል...
17/11/2023

የስራ ላይ ስልጠና ያጠናቀቁ 5193 ወጣቶች ተመረቁ::

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የስራ ኢንተርፕራይዝና ኢንዲስትሪ ልማት ቢሮ ከዓለም ባንክ ጋር በመተባበር "ብቃት የወጣቶች የስራ ላይ ልምምድ መርሀ ግብር "ተሳታፊ 5193 ወጣቶችን በማስመረቅ የሁለተኛ ዙር ስልጠና አስጀምሯል::

በምረቃ ስነ-ስርዓቱ ላይ የተገኙት ምክትል ከንቲባና የስራ ኢንተርፕራይዝና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ጃንጥራር አባይ ከተማ አስተዳደሩ ለሰው ልጅ ሕይወት የመቀየር ፋይዳ ያላቸው ስራዎች አካል በሆነው የስራ ዕድል ፈጠራ ስራ በርካቶችን ከስራ በማገናኘት ራሳቸውን እንዲችሉና ሀብት እንዲፈጥሩ ማድረጉን ገልጸዋል::

የሰለጠነ የሰው ኃይል ዕጥረት እያለ ብዙዎች ስራ ፈላጊ የሆኑበት ሁኔታ ለማስተካከል ወጣቶችን ከኢንዱስትሪ ጋር በማገናኘት በአስተሳሰብ ተቀይረው በክህሎት በቅተው እጆቻቸውን ከስራ ማገናኘት ያስቻለው ይህ መርሀ ግብር በሁለተኛው ዙር መርሀ ግብር ከ15 ሺህ በላይ ወጣቶችን ተጠቃሚ የሚያደርግ መሆኑን ገልጸዋል::

አቶ ጃንጥራር መርሀ ግብሩ እንዲሳካ ሰልጣኞችን ተቀብለው በማሰልጠን ብቁ በማድረግና በመቅጠር አስተዋፅዖ ያበረከቱ ልበ-ቀና ተቋሞችን አመስግነው ወጣቶች ከተማ አስተዳደሩ በሚፈጥራቸው ዕድሎች በንቃት መሳተፍ እንዳለባቸው አሳስበዋል::

"ኣብረሆት ቤተ መፃህፍት ከኤ2ኤስቪ (A2SV) ጋር በመቀናጀት ባዘጋጀው የአፍሪካን የቴክኖሎጂ ልህቀትና የፈጠራ ስራን በሚያበረታታው የሰው ሰራሽ አስተውሎት( AI) ውድድር ላይ ተገኝተን ወጣ...
12/11/2023

"ኣብረሆት ቤተ መፃህፍት ከኤ2ኤስቪ (A2SV) ጋር በመቀናጀት ባዘጋጀው የአፍሪካን የቴክኖሎጂ ልህቀትና የፈጠራ ስራን በሚያበረታታው የሰው ሰራሽ አስተውሎት( AI) ውድድር ላይ ተገኝተን ወጣቶችን አበረታተናል።

መድረኩ ከተለያዩ ሃገራት የተውጣጡ ወጣቶች የአፍሪካን የቴክኖሎጂ ለውጥ እውን ለማድረግ ሃሳብ የሚለዋወጡበት ፣ ተቀራርበው በጋራ የሚሰሩበት እና ለአፍሪካ ችግር አፍሪካዊ መፍትሄ ለማበጀት በጋራ የሚሰሩበት ነው።

ወጣቶቻችን የኢትዮጲያን ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን የሚያንፁ የተለያዩ ፕሮጀክቶችን በመንደፍ ሃገራችን ውስጥ ለሚስተዋሉ ክፍተቶች ወቅቱን የሚመጥን መፍትሄ በመፍጠር የበኩላቸውን አስተዋፅዖ እንዲወጡ ጥሪዬን ለማስተላለፍ እወዳለሁ።"

ከንቲባ አዳነች አቤቤ

ዛሬ በሁለተኛ ቀን የፕሮጀክቶች ጉብኝታችን የሁለት ሪፈራል ሆስፒታሎች ፣ የቤቶችን እና የላፍቶ የገበያ ማዕከል ግንባታ ያለበትን ደረጃ ተዘዋውረን ጎብኝተናል::በአዲስ አበባ ከተማ እስከ ዛሬ ...
12/11/2023

ዛሬ በሁለተኛ ቀን የፕሮጀክቶች ጉብኝታችን የሁለት ሪፈራል ሆስፒታሎች ፣ የቤቶችን እና የላፍቶ የገበያ ማዕከል ግንባታ ያለበትን ደረጃ ተዘዋውረን ጎብኝተናል::

በአዲስ አበባ ከተማ እስከ ዛሬ ከገነባናቸው ሆስፒታሎች ሁሉ የሚልቁት የቤተል-መንዲዳ ሪፈራል ሆስፒታል እና የላፍቶ ሪፈራል ሆስፒታል ግንባታቸው በያዝነው በጀት አመት ሲጠናቀቁ ከሚሰጡት ማህበራዊ ፋይዳ በተጨማሪ ከተማችንን የጤና ቱሪዝም ማዕከል የሚያደርጉ ይሆናል::
በከተማችን ያለውን የቤት እጥረት በዘላቂነት ለመቅረፍ በከተማው በጀት ግንባታቸው የተጀመሩ የ5000 ቤቶች ግንባታ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ የሚጠናቀቅ ሲሆን የአቃቂ ተገጣጣሚ ቤቶችን ውስጥ ግንባታቸው ሙሉ በሙሉ የተጠናቀቁ 400 ቤቶችን አይተናል::

በመጨረሻም ለከተማችን 4ኛው የገበያ ማዕከል የሆነው የላፍቶ ምዕራፍ 2 የግብርና ምርቶች የገበያ ማዕከል 144 ሱቆች እና 14 መጋዘኖች የተካተቱበት ሲሆን በቀጣይ 90 ቀናት ውስጥ ግንባታውን በማጠናቀቅ ለአገልግሎት ክፍት በማድረግ የገበያ ሰንሰለቱን በማስተካከል አምራችን በቀጥታ ከሸማች ጋር በማገናኘት የአዲስ አበባን ህዝብ የኑሮ ጫና የማቃለል ስራችንን ውጤታማ የሚያደርግ ይሆናል::

አዲስ አበባን ለመኖር ምቹ የሆነች ከተማ ማድረግ በቃል ብቻ ሳይሆን የገባነው ቃል በተግባር እውን እየሆነ በመምጣቱ እንኳን ደስ አላችሁ::

ከንቲባ አዳነች አቤቤ

አዲስ በፈጣን የለውጥ ጎዳና ላይ ናት!ከንቲባ አዳነች አቤቤ
11/11/2023

አዲስ በፈጣን የለውጥ ጎዳና ላይ ናት!
ከንቲባ አዳነች አቤቤ

ዛሬ ማለዳ የኮልፌ የግብርና ምርት መሸጫ የገበያ ማዕከልን መርቀን ለህዝባችን አገልግሎት ክፍት አድርገናል::ከአምስቱም መግቢያ በሮች 3ኛው የሆየዉ ይህ የግብርና ምርት መሸጫ ማዕከል ሸማችን ...
04/11/2023

ዛሬ ማለዳ የኮልፌ የግብርና ምርት መሸጫ የገበያ ማዕከልን መርቀን ለህዝባችን አገልግሎት ክፍት አድርገናል::

ከአምስቱም መግቢያ በሮች 3ኛው የሆየዉ ይህ የግብርና ምርት መሸጫ ማዕከል ሸማችን ከአምራች ጋር በቀጥታ በማገናኝት በከተማችን የሚስተዋለውን የዋጋ ንረት በዘላቂነት በማረጋጋት ረገድ ጉልህ ሚናን ይጫወታል::

በ2.3 ሄክታር ላይ ያረፈው የገበያ ማዕከሉ በውስጡ 4 ትላልቅ ብሎኮች ፣ በቴክኖሎጂ የተደገፉ ዘመናዊ የምርት ማቀዝቀዣና ማሞቂያ ክፍሎች ፣ ከ90 በላይ የምርት ማከማቻ ፣ ከ12 በላይ የጅምላ መሸጫ ሱቆች ፣ ከ80 በላይ የችርቻሮ ሱቆች ፣ ከ10 በላይ የማጠቢያ ክፍሎች ፣ በአንድ ጊዜ ከ200 በላይ ተሽከርካሪ ማቆሚያ ስፍራ እንዲሁም ለባንክና ለቢሮ ግልጋሎት የሚውሉ ክፍሎችም ተካተውበታል::

ለህዝብ የገባነውን ቃል ወደተግባር እየመነዘርን ለነዋሪዎቿ ምቹ የሆነች ከተማ መገንባታችንን አጠናክረን እንቀጥላለን::

አስጀምሮ ያስጨረሰን ፈጣሪ ይመስገን!

ከንቲባ አዳነች አቤቤ

ኮልፌ የግብርና ምርቶች መሸጫ የገበያ ማዕከል በነገው ዕለት ከንቲባ አዳነች አቤቤ በተገኙበት ይመረቃል::በከተማችን የሚስተዋለውን የዋጋ ንረት ለማረጋጋትና አምራችን ከሸማች ጋር በቀጥታ ለማገ...
03/11/2023

ኮልፌ የግብርና ምርቶች መሸጫ የገበያ ማዕከል በነገው ዕለት ከንቲባ አዳነች አቤቤ በተገኙበት ይመረቃል::

በከተማችን የሚስተዋለውን የዋጋ ንረት ለማረጋጋትና አምራችን ከሸማች ጋር በቀጥታ ለማገናኝት ከተማ አስተደደሩ እያስገነባቸው ካሉ የግብርና ምርት መሸጫ ማዕከላት አንዱ የሆነው የኮልፌ የግብርና ምርቶች መሸጫ በነገው ዕለት ይመረቃል::

በግምባታ ላይ ከነበሩት የግብርና ምርት መሸጫ ማዕከላት መካከል የለሚ ኩራ ሳይት ግንባታ ተጠናቅቆ ጳጉሜን 4 ቀን 2015 ዓ.ም. በከንቲባ አዳነች አቤቤ በይፋ ተመርቆ አገልግሎት እየሰጠ የሚገኝ ሲሆን ፤ በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ በ2.3 ሔክታር መሬት ላይ የተገነባው 4 ብሎኮች ያሉት የኮልፌ የግብርና ምርቶች መሸጫ የገበያ ማዕከል ፕሮጀክት ግምባታ ተጠናቅቆ በነገው ዕለት ተመርቆ አገልግሎት ይጀምራል::

ታሪካዊ ቀን፤ ጥቅምት 23፣ 1942 ዓ.ም ከ 73 ዓመታት በፊት ልክ በነገው ዕለት በመዲናችን አዲስ አበባ፣ ፒያሳ - አራዳ ተብሎ በሚታወቀው ሰፈር የሚገኘው የከተማዋ ማዘጋጃ ቤት ሕንፃ  የ...
02/11/2023

ታሪካዊ ቀን፤ ጥቅምት 23፣ 1942 ዓ.ም ከ 73 ዓመታት በፊት ልክ በነገው ዕለት በመዲናችን አዲስ አበባ፣ ፒያሳ - አራዳ ተብሎ በሚታወቀው ሰፈር የሚገኘው የከተማዋ ማዘጋጃ ቤት ሕንፃ የመሠረት ድንጋይ በቀዳማዊ አፄ ኃይለሥላሴ ተቀመጠ።

የህንፃ ዲዛይኑ እና ግንባታው የተከናወነውም በጣልያናዊው አርክቴክት አርትሮ ሜዜዲሚ ነበር። ህንጻው 75 ሺህ ካሬ ሜትር ስፋት ላይ ያረፈ ሲሆን ግንባታው ተጠናቆ ለአገልግሎት ክፍት የተደረገው ግንባታው ከተጀመረ ከ 15 ዓመት በኋላ ጥር 27፣ 1957 ዓ.ም ነበር።
ዛሬ ላይ ይህ የማዘጋጃ ቤት ህንፃ ከ58 ዓመታት በኋላ መልሶ ለመጪዎቹ 60 ዓመታት በጥራት እንዲያገለግል ታሪካዊ ቅርፁን ሳይለቅ አድሰንና አስውበን ለዘመኑ ትውልድ አስረክበናል።

ህዝብ እንድናስተዳድረው ፈቃዱን በሰጠን ባለፉት 4 ዓመታት ውስጥ የአድዋ ሙዚየምን ገንብተን ታሪካዊነቱን ጠበቀን ስናስረክብ ደስታ ይሰማናል። የታሪክ መስራት ቅብብሎሽ ይቀጥላል።

ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ!!

ከንቲባ አዳነች አቤቤ

ዛሬ የአዲስአበባ እና የቾንቹን ከተሞች 20ኛ ዓመት የእህትማማችነት ጉዞ ምክንያት በማድረግ የቾንቹን ከተማ ከንቲባ ዮክ ዶንግ ሃን እና የወጣቶች ዲፕሎማሲ ልዑካን እንዲሁም የጣሊያን ቤርጋሞ ...
01/11/2023

ዛሬ የአዲስአበባ እና የቾንቹን ከተሞች 20ኛ ዓመት የእህትማማችነት ጉዞ ምክንያት በማድረግ የቾንቹን ከተማ ከንቲባ ዮክ ዶንግ ሃን እና የወጣቶች ዲፕሎማሲ ልዑካን እንዲሁም የጣሊያን ቤርጋሞ ከተማ ከንቲባ ጆርጂዮ ጎሪ ከቡድናቸው ጋር በተገኙበት የባህል ልውውጥ አድርገናል:: የሰራናቸውንም ትላልቅና ሰው ተኮር ፕሮጀክቶቻችንን ጎብኝተዋል::

የኢትዮጵያ እና የኮሪያ የ20 ዓመት ወዳጅነት በደም የተሳሰሩና ታሪካዊ ግንኙነትን ወደሚመጥን ተጨባጭ ስራ በመቀየር የባህል ትስስር የሚያጠናክር ባህል ጨዋታ ማምሻዉን የሁለቱ ከተማ ወጣቶች አቀርበዋል።

በመጨረሻም የቾንቹን ከንቲባ ለኮሪያ ቃኘዉ ዘማቾች እና ቤተሰቦች ስጦታ አበርክተዋል ።የኮሪያ ዘማች ቤተሰቦች ስለሰጣችሁኝ እዉቅና ከልብ አመሰግናለሁ ።
ከንቲባ አዳነች አቤቤ

የአዲስአበባ እና የቾንቹን ከተሞች 20ኛ ዓመት የእህትማማችነት ምክንያት በማድረግ ከንቲባ አዳነች አቤቤን ጨምሮ የቾንቹን ከተማ ከንቲባ ዮክ ዶንግ ሃን እና ልዑካን ቡድናቸው ፣ የከተማ አስተ...
01/11/2023

የአዲስአበባ እና የቾንቹን ከተሞች 20ኛ ዓመት የእህትማማችነት ምክንያት በማድረግ ከንቲባ አዳነች አቤቤን ጨምሮ የቾንቹን ከተማ ከንቲባ ዮክ ዶንግ ሃን እና ልዑካን ቡድናቸው ፣ የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች እንዲሁም የቃኘው ሻለቃ የኮሪያ ዘማቾች በተገኙበት የሁለቱን ሃገራት የባህል ልውውጥ በመከናወን ላይ ይገኛል::

የደቡብ ኮሪያ ቹንቾን ከተማ ከንቲባ ዮክ ቶንግ ሃን እና ከወጣቶች ዲፕሎማሲ ልዑካን ቡድናቸው ጋር የሁለቱ ከተሞች እህትማማችነት 20ኛ ዓመት አክብረናል ።በቀጣይ በትብብር በምንሰራቸው ጉዳዮች...
31/10/2023

የደቡብ ኮሪያ ቹንቾን ከተማ ከንቲባ ዮክ ቶንግ ሃን እና ከወጣቶች ዲፕሎማሲ ልዑካን ቡድናቸው ጋር የሁለቱ ከተሞች እህትማማችነት 20ኛ ዓመት አክብረናል ።በቀጣይ በትብብር በምንሰራቸው ጉዳዮች ዙሪያ ፍሬያማ ውይይት አካሂደናል፡፡

አዲስ አበባ ከተማ ካሏት 24 እህት ከተሞች አንዷ የሆነችው ከቹንቾን ከተማ ጋር ለ20 ዓመታት የዘለቀው የእህትማማችነት ግንኙነታችንን ይበልጥ በማጠናከርየቹንቾን ከተማ ከንቲባ ዮክ ቶንግ ሃን እና የወጣቶች ዲፕሎማሲ ልዑካን ቡድንን ተቀብለን ስናስተናግድ የአዲስ አበባ ከተማን ዓለም አቀፍ ግንኙነቶችን የሚያልቁ ታላላቅ ስራዎችን ለመስራት የገባነውን ቃል በማደስ ለላቀ ስራ ራሳችንን በማዘጋጀት ጭምር ነው!

ከንቲባ አዳነች አቤቤ

የቤተል ሳይት ግብርና ምርቶች ማከማቻና መሸጫ ማዕከል ግንባታ ፕሮጀክት የምሽት ገፅታ
30/10/2023

የቤተል ሳይት ግብርና ምርቶች ማከማቻና መሸጫ ማዕከል ግንባታ ፕሮጀክት የምሽት ገፅታ

Finfinnee Halkan kanaanየአዲስ አበባ የምሽት ድባብ
29/10/2023

Finfinnee Halkan kanaan

የአዲስ አበባ የምሽት ድባብ

የቀድሞ አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ፣ ፋና ብሮድከስቲንግ ኮርፖሬት እና የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ዋና ስራ አስፈጻሚ በነበሩት አቶ በቀለ ሙለታ ህልፈተ ህይወት ጥልቅ ሃዘን ተሰምቶኛል።ለቤተሰቦቻቸው...
27/10/2023

የቀድሞ አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ፣ ፋና ብሮድከስቲንግ ኮርፖሬት እና የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ዋና ስራ አስፈጻሚ በነበሩት አቶ በቀለ ሙለታ ህልፈተ ህይወት ጥልቅ ሃዘን ተሰምቶኛል።

ለቤተሰቦቻቸው፣ ለወዳጆቻቸው እና ለስራ ባልደረቦቻቸው መጽናናትን እመኛለሁ።
ፈጣሪ ነብሳቸውን በአጸደ ገነት ያኑር

አድዋ ዜሮ ኪሎ ሜትር ፕሮጄክት
26/10/2023

አድዋ ዜሮ ኪሎ ሜትር ፕሮጄክት

ከንቲባ ዶ/ር አዳነች አቤቤ አሜሪካ ጆርጂያ ግዛት ከሚገኘው ትሪኒቲ ኢንተርናሽናል አምባሳደርስ ዩኒቨርሲቲ የክብር ዶክትሬት ዲግሪ እና የጆርጂያ ግዛት የክብር ዜግነት ሽልማትን ተቀብለዋል። ከ...
24/10/2023

ከንቲባ ዶ/ር አዳነች አቤቤ አሜሪካ ጆርጂያ ግዛት ከሚገኘው ትሪኒቲ ኢንተርናሽናል አምባሳደርስ ዩኒቨርሲቲ የክብር ዶክትሬት ዲግሪ እና የጆርጂያ ግዛት የክብር ዜግነት ሽልማትን ተቀብለዋል።

ከንቲባ ዶ/ር አዳነች አቤቤ ለሕዝብ ተጠቃሚነት እና ለሰላም ላበረከቱት ታላቅ አስተዋፅዖ ፣ ያሳዩት በሳል እና ምሳሌያዊ አመራር በዓለም አቀፍ ደረጃ ለሚገኙ መሪዎች ምሳሌ የሚሆንና መነሳሳት የሚፈጥር በመሆኑ ዩኒቨርሲቲው ይህንን Doctorate of Philosophy እንዳበረከተላቸው የትሪኒቲ ኢንተርናሽናል አምባሳደሪስ ዩኒቨርሲቲ ቻንስለር ዶ/ር ዣክሊን ሞሀየር ገልፀዋል::

በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ ነዋሪዎችን ህይወት ለመቀየር እና የነዋሪዎችን ፍትሃዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ከንቲባ ዶ/ር አዳነች አቤቤ ላሳዩት ቁርጠኝነት እና ለሌሎች ሃገራት መሪዎች አርአያ የሚሆን ስራ በመስራታቸው የጆርጂያ ግዛት የክብር ዜግነት ሽልማት እንደተበረከተላቸው የግዛቱ ሴናተር ጋይል ዴቨንፓርት በመድረኩ ላይ ተናግረዋል::

በመድረኩ ላይ ንግግር ያደረጉት ከንቲባ ዶ/ር አዳነች አቤቤ ለዚህ ስኬት የበኩላቸውን አስተዋፅዖ ላበረከቱ አካላት በሙሉ ምስጋናቸውን አቅርበዋል::

https://www.prweb.com/releases/her-excellency-dr-adanech-abiebie-dessa-honored-with-distinguished-accolades-by-trinity-international-university-of-ambassadors-corp-florida-and-the-state-of-georgia-301965708.html

15/10/2023

የመንገድ መሰረተ ልማት በዚህ ልክ ትኩረት ሰጥተነዋል ስንል ቃላችንን በተግባር ለህዝባችን የተገበርንበት እንደሆነ የሚያሳዩ ጭምር ናቸው።

ከንቲባ አዳነች አቤቤ

👉ያሳዝናል  ያማልጋዜጠኛ፣ገጣሚ፣የልብ ወለድ ደራሲ እንዲሁም የህብረ ዜማ ደራሲው የመድረክ አጋፋሪው አበባው ፍሰሀ ከዚህ አለም ድካም አርፏል። ወንድሜ ነብስህ በሰላም ትረፍ!!! 😭😭😭😭
15/10/2023

👉ያሳዝናል ያማል

ጋዜጠኛ፣ገጣሚ፣የልብ ወለድ ደራሲ እንዲሁም የህብረ ዜማ ደራሲው የመድረክ አጋፋሪው አበባው ፍሰሀ ከዚህ አለም ድካም አርፏል። ወንድሜ ነብስህ በሰላም ትረፍ!!!

😭😭😭😭

አርቲስት ሐሎ ዳዌ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየች አርቲስት ሐሎ ዳዌ ባደረባት ሕመም በዛሬው ዕለት ከዚህ ዓለም በሞት ተለይታለች፡፡ ለኦሮሞ ኪነ-ጥበብ እድገት አስተዋጽኦ ካበረከቱ ታዋቂ አርቲስቶ...
14/10/2023

አርቲስት ሐሎ ዳዌ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየች

አርቲስት ሐሎ ዳዌ ባደረባት ሕመም በዛሬው ዕለት ከዚህ ዓለም በሞት ተለይታለች፡፡

ለኦሮሞ ኪነ-ጥበብ እድገት አስተዋጽኦ ካበረከቱ ታዋቂ አርቲስቶች አንዷ የሆነችው አርቲስት ሐሎ ዳዌ ባደረባት ሕመም ለረጅም ጊዜ ሕክምና ስትከታተል ቆይታ ዛሬ በሞት ተለይታናለች፡፡

ለአርቲስት ሐሎ ዳዌ ቤተሰቦች፣ ወዳጅ ዘመዶች፣ የሙያ አጋሮችና አድናቂዎች መጽናናትን እመኛለሁ፡፡

ዓለም አቀፍ የቀዳማዊ ልጅነት የልህቀት ስትራቴጂ  ዓውደ-ጥናት ከንቲባ አዳነች አቤቤን ጨምሮ ወ/ሮ አለምፀሃይ ጳውሎስ ፣ ሚኒስትሮች ፣ የአለምአቀፍ ተቋማት ኃላፊዎች እንዲሁም የከተማ አስተዳ...
08/10/2023

ዓለም አቀፍ የቀዳማዊ ልጅነት የልህቀት ስትራቴጂ ዓውደ-ጥናት ከንቲባ አዳነች አቤቤን ጨምሮ ወ/ሮ አለምፀሃይ ጳውሎስ ፣ ሚኒስትሮች ፣ የአለምአቀፍ ተቋማት ኃላፊዎች እንዲሁም የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች በተገኙበት በመካሄድ ላይ ይገኛል::

የረዳን ፈጣሪ ይመስገን!!እንኳን ደስ ያለን!!በጋራ መሰባሰቢያ ጎጇችን አዲስ አበባ ያከበርነው ሆረ ፊንፊኔ ሚሊዮኖች ታድመውበት ባሕላዊ እሴቱን ጠበቆ በታላቅ በድምቀት ተከብሯል፡፡በአምስቱም ...
07/10/2023

የረዳን ፈጣሪ ይመስገን!!
እንኳን ደስ ያለን!!
በጋራ መሰባሰቢያ ጎጇችን አዲስ አበባ ያከበርነው ሆረ ፊንፊኔ ሚሊዮኖች ታድመውበት ባሕላዊ እሴቱን ጠበቆ በታላቅ በድምቀት ተከብሯል፡፡

በአምስቱም የከተማዋ በሮች በዓሉን ለመታደም የመጡ እንግዶችን በፍቅር ተቀብላችሁ ያስተናገዳችሁ የከተማችን ነዋሪዎች በተለይ ወጣቶች በወንድማማችነትና እህትማማችነት በመቀራረብ ኢትዮጵያዊነትን ከፍ በማድረጋችሁ በከተማ አስተዳደሩ ስም ላመሰግናችሁ እወዳለሁ!
አንዳችን ሌላችንን ቀርበን በማወቅና በመረዳት የጋራ ዕሴቶቻችንን ከፍ በማድረግ አብሮ መድመቅን አይተናል።ሆረ ፊንፊኔ ከሰባት ሚሊዮን በላይ ሕዝብ ወጥቶ ''ኢሬቻ የአንድነት ፣ የወንድማማችነትና እህትማማችነት ዓርማ'' በሚል መሪ ቃል ባሕላዊ ዕሴቱን ጠብቆ በድምቀት አክብሮታል!

የውጭ ቱሪስቶች ፣ ከተለያዩ የሀገራችን ክልሎችና ከተሞች የመጡ ኢትዮጵያውያን በባሕላዊ አልባሳትና ጨዋታዎቻቸው አዲስ አበባ ከተማን አድምቀዋታል፡፡
አዲስ አበባ የኢትዮጵያውያን ሁሉ ከተማ ናትና እንደ ባሕል ወጋቸው ከኦሮሞ ወንድሞቻቸው ጋር በፍቅርና በወንድማማችነት መንፈስ በዓሉን ታድመው ከተማውን በማድመቅ ለቱሪዝም መዳረሻነት ያላትን አቅም አሳይተዋል፡፡

ለበዓሉ በድምቀት መከበር የበዓሉ ታዳሚዎች ፣ አባ ገዳዎች ፣ ሀደ ስንቄዎች ፣ ፎሌዎች ፣ መላው የጸጥታ አባለት ፣ አመራሮችና የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪ በትጋት ፣ በፍቅርና በባለቤትነት ስሜት ላደረጋችሁት አስተዋጽዖ በራሴና በከተማ አስተዳደሩ ስም ከታላቅ አክብሮት ጋር ላመሰግናችሁ እወዳለሁ!

በሆራ አርሰዲ የኢሬቻም በተመሳሳይ እንዲከበር አስተዋፅዖቻችንን አጠናክረን መቀጠል ይጠበቅብናል።

ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ!!

ከንቲባ አዳነች አቤቤ

የሆራ ፊንፊኔ ኢሬቻ በዓል አከባበር
07/10/2023

የሆራ ፊንፊኔ ኢሬቻ በዓል አከባበር

5ኛው የኢሬቻ ፎረም በከተማችን በመከናወን ላይ ይገኛል:: በመርሃ ግብሩ ላይ ከንቲባ አዳነች አቤቤን ጨምሮ የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ፕሬዝዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ ፣ አባገዳና ሃደ...
06/10/2023

5ኛው የኢሬቻ ፎረም በከተማችን በመከናወን ላይ ይገኛል:: በመርሃ ግብሩ ላይ ከንቲባ አዳነች አቤቤን ጨምሮ የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ፕሬዝዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ ፣ አባገዳና ሃደ ሲንቄዎች ፣ ሚኒስትሮች ፣ ባለሃብቶች ፣ ታዋቂ ግለሰቦች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተሳታፊ ሆነዋል::

ከንቲባ አዳነች አቤቤ የአማሊ ተሳታፊዎችን በጽ/ቤታቸው ተቀብለዋል:: ከንቲባ አዳነች አቤቤ የአፍሪካ ከንቲባዎች የሊደርሺፕ ኢኒሼቲቭ (AMALI)የተሰኘው እና የአፍሪካ ከንቲባዎች የእርስ በእ...
05/10/2023

ከንቲባ አዳነች አቤቤ የአማሊ ተሳታፊዎችን በጽ/ቤታቸው ተቀብለዋል::

ከንቲባ አዳነች አቤቤ የአፍሪካ ከንቲባዎች የሊደርሺፕ ኢኒሼቲቭ (AMALI)የተሰኘው እና የአፍሪካ ከንቲባዎች የእርስ በእርስ መማማሪያ መድረክ ተሳታፊዎችን በከንቲባ ጽ/ቤት ደማቅ አቀባበል አድርገውላቸዋል::

በመማማሪያ መድረኩ የአፍሪካ የከተሞች ከንቲባዎች ፣ ከተለያዩ የአለም ሀገራት የሚመጡ የዘረፉ ምሁራን ፣ የአለም አቀፍ ድርጅቶች ኃላፊዎች፣ የፋውንዴሽኖች እና ፊላንትሮፒ ኃላፊዎች እንዲሁም ሌሎች እንግዶች የሚሳተፉ ይሆናል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከመስከረም 24 ጀምሮ ልዩ ልዩ ዓለም አቀፍ፣ አህጉር አቀፍ እና አገር አቀፍ መድረኮችን ያስተናግዳል:- ወ/ሮ እናትአለም መለሰ----የአዲስ አበባ ከተማ አስተ...
04/10/2023

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከመስከረም 24 ጀምሮ ልዩ ልዩ ዓለም አቀፍ፣ አህጉር አቀፍ እና አገር አቀፍ መድረኮችን ያስተናግዳል:- ወ/ሮ እናትአለም መለሰ
----
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ እናትአለም መለሰ ከተማዋ ከነገ ጀምሮ የምታስተናግዳቸው ዓለም አቀፍ፣ አሕጉር አቀፍ እንዲሁም አገር አቀፍ ልዩ ልዩ መድረኮች ከተማችን ለሕጻናት ሁለንተናዊ አስተዳደግ የሚመጥኑ መሠረተ ልማቶችን እውን ለማድረግ በትኩረት እየሰራች መሆኗን ለማሳወቅ ያለመ መሆኑን ዛሬ በሰጡት ጋዜጣዊ በመግለጫ ገልፀዋል።

እንደ ቢሮ ኃላፊዋ ገለፃ ከመስከረም 24 እስከ 25 የአፍሪካ ከንቲባዎች የሊደርሺፕ ኢኒሼቲቭ መድረክ፤ ከመስከረም 28 እስከ 29 የቀዳማይ ልጅነት ልማት ፕሮግራም የልህቀት ማዕከልን ለማቋቋም የሚረዳ ዓለም አቀፍ የምክክር መድረክ እንዲሁም ከመስከረም 28 እስከ ጥቅምት 1/2016 ዓ.ም የሀገር አቀፍ መሪዎች የልምድ ልውውጥ መድረኮችን የምታስተናግድ ሲሆን፣ ለሕጻናት ሁለንተናዊ አስተዳደግ ቀዳሚ ትኩረት በሚሰጥ መልኩ መዲናችን አዲስ አበባ ሦስት ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ያላቸው ትልልቅ መድረኮች ለማከናውን አስፈለጊ ቅድመ ዝግጅት አጠናቃለች ብለዋል።

የቀዳማይ ልጅነት ልማት ፕሮግራም ከጅምሩ አበረታች ውጤቶችን ማስመዝገብ የቻልንበት ነው ያሉት የቢሮ ኃላፊዋ በጭር ጊዜ ውስጥ ያስመዘገብናቸው ውጤቶች ስኬታማነት ሀገራዊ እና አህጉራዊ ተሞኩሮ ለመሆን መቻሉን ጨምሮ ተመራጭ እና ብዙዎች ሊማሩበት የሚያስችል በየደረጃው የሚገለጽ ዝርዝር ውጤቶችን የያዘ መሆኑን አስመልክቶ ለሌሎች ልምድ ለማካፈል በመሻት መድረኮቹ የተዘጋጁ መሆኑን አስታውቀዋል ።

እስካሁን ባለው በቀዳማይ ልጅነት ልማት ፕርግራም 2500 የወላጆች እና አሳዳጊዎች የምክር አገልግሎት ሰራተኞች፤ ከ56 በላይ ጤና ጣቢያዎች የቀዳማይ ልጅነት ተኮር የህጻናት እና ወላጆች ጤና ክብካቤ አግልገሎትን መስጠት፤ 6 የፌዴራል ሆስፒታል ባለሙያዎች በሕጻናትና እናቶች ላይ ብቻ ማዕከል አድርገው እንዲሰሩ የሚያስችል ስልጠና ወስደው አገልግሎት መጀመራቸውን ጨምሮ ከተማ አስተዳደሩ 9500 ለሚሆኑ ህጻናት እና ወላጆች በከተማዋ አልሚ ምግብ በማቅረብ ላይ እንደሚገኝ ይፋ አድርገዋል።

ይሕ በንዲሕ እንዳለ 46 የቅድመ አንደኛ ደረጃ ት/ቤቶች ወደ ጨዋታ መር የማስተማር ዘዴ እንዲሸጋገሩ ማስቻል፣ በከተማችን ከ 150 በላይ የመጫዎቻን ማልማት ጨምሮ በአሁኑ ወቅት በቀዳማይ ልጅነት ልማት እሳቤዎች የተቃኙ 9 አዳዲስ የመጫዎች ቦታዎችም በተለያዩ አካባቢዎች ለምተው በቅርቡ አገልግሎት በመስጠት እንደሚጀምሩ ገልፀዋል።

በመግለጫቸው ማጠቃለያ ወቅት ኃላፊዋ በሦስቱም መድረኮች ከለውጡ ማግስት አንስቶ በሁሉም ረገድ የጀመርናቸው ሰው ተኮር የልማት ፕሮገራሞች እውቅና እንዲያገኙ ከማስቻል ባለፈ ተሞክሮውን እንደ ሀገር እና አህጉር በማስፋት አህጉራዊ ተቀባይነትና ምሳሌነታችንን በተጨባጭ ለማጉላት የላቀ አስተዋጽኦ የሚኖረው ነውም ሲሉ በአንክሮ ተናግረዋል።

አዲስ አበባን አንደ ስሟ ውብ እና አበባ ለማድረግ የገባነው ቃል ወደ ተግባር መቀየራችን አሁንም ተጠናክሮ ቀጥሏል።ዛሬ መለዳ በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ የተገነቡ ጠቅላላ ስፋታቸው 546,200 ካ...
04/10/2023

አዲስ አበባን አንደ ስሟ ውብ እና አበባ ለማድረግ የገባነው ቃል ወደ ተግባር መቀየራችን አሁንም ተጠናክሮ ቀጥሏል።

ዛሬ መለዳ በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ የተገነቡ ጠቅላላ ስፋታቸው 546,200 ካሬ ሜትር የሆኑ የመንገድ አካፋይ፣ ዳርቻና አደባባይ፣ አረንጓዴ መሠረተ ልማቶችን እንዲሁም በግለሰብ የለሙ ሞዴል መንደሮችን ጎብኝተን በይፋ ስራ አስጀምረናል::

ለአገልግሎት ክፍት የተደረጉት የአረንጏዴ ልማት ስራዎቹ ከተማዋን ውብ ፣ ማራኪ ፣ ፅዱ እና አረንጓዴ ከማድረግ ባለፈ ከ12,000 በላይ ለሚሆኑ የአካባቢው ነዋሪዎች የስራ እድል ፈጥረዋል::
ማኅበራዊ ኃላፊነታቸውን በመወጣት በበጎ ፈቃደኝነት አብረውን የሰሩ ልበ ቀና ባለሃብቶችንና ያስተባበሩ አመራሮች ላመሰግን እወዳለሁ::
ከንቲባ አዳነች አቤቤ

ከንቲባ አዳነች አቤቤ የኢሬቻ ሳምንት የመክፈቻ መርሃ ግብር ላይ በመገኘት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ-----በፕሮግራሙም ላይ የአዲስ አበባ ከንቲባ አዳነች አቤቤን ጨምሮ የአዲስ...
02/10/2023

ከንቲባ አዳነች አቤቤ የኢሬቻ ሳምንት የመክፈቻ መርሃ ግብር ላይ በመገኘት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ
-----
በፕሮግራሙም ላይ የአዲስ አበባ ከንቲባ አዳነች አቤቤን ጨምሮ የአዲስ አበባ ባህል ኪነጥበባትና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ሂሩት ካሳው እንዲሁም የአዲስ አበባ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ምክትል ኃላፊ አቶ አለማየሁ እጅጉን ጨምሮ በየደረጃው የሚገኙ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች፣ አባ ገዳና ሃደ ሲንቄዎች፣ አርቲስቶች፣ የባህል አምባሳደሮች፣ ታዋቂ ግለሰቦችና ሌሎችም ተጋባዥ እንግዶች ተገኝተዋል።

በመረሃ-ግብሩ ላይ ከንቲባ አዳነች፣ ለኢሬቻ ክብረ-በዓል ከሀገር ውጭና ከአጎራባች አካባቢዎች ወደ ጋራ ከተማችን አዲስ አበባ የሚመጡ እንግዶቻችንን በሙሉ ለመቀበል አስፈላጊው ቅድመ ዝግጅት ተደርጓል ብለዋል።

ኢሬቻ የሰላም፣ የፍቅር፣ የይቅርታና ሕብረ-ብሔራዊ አንድነትን አጉልቶ የሚያሳይ ክብረ-በዓል መሆኑን በተጨባጭ በእያንዳንዱ ድርጊታችን ልናሳይ ይገባልም ብለዋል ከንቲባ አዳነች።

የአዲስ አበባ ባህል ኪነጥበባትና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ሂሩት ካሳው በበኩላቸው ኢትዮጵያ በህብር አጊጠው በአንድ አገር ጥላ ስር በእጅጉ በተሰናሰለ ህብረ-ብሔራዊ አንድነት ህዝቦች በመከባበር፣ በመቻቻልና ዘመናትን በተሻገረ አብሮነት ፈተናዎችን ሁሉ በአንድነት ድል የነሱ ሕዝቦች የሚኖሩባት ብርቂዬ ሀገር ናት ሲሉ ገልጸዋል።

ኢሬቻ የኢትዮጵያውያን የምስጋናና የይቅርታ ክብረ-በዓል ሆኖ በዩኒስኮ የማይዳሰሱ ቅርሶች መዝገብ ላይ መስፈር እንዲችል አካታች ጥረቶች የተጀመሩ መሆኑን ያነሱት ዶ/ር ሂሩት፣ በዚህ ረገድ ሁላችንም የበኩላችንን ድርሻና ኃላፊነት ልንወጣ ይገባልም ሲሉ አሳስበዋል።

በከተማችን የሚገኙ የቱሪዝም መስህቦችን በሀገር በቀል ባህሎችና እሴቶች በማስዋብ የከተማችን እና የሀገራችንን የቱሪዝም ገቢ በሚፈለገው ደረጃ ለማሳደግ በቅንጅት መሥራት ከመቼውም ግዜ በላይ ከሁላችንም ይጠበቃል ሲሉ የቢሮ ኃላፊዋ በአጽንኦት አስታውቀዋል።

30/09/2023

29/09/2023

አብቹ በምሽት በጅማ ከተማ ጎዳና ላይ💖

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በ20ኛው የአዲስ አበባ መስተዳድር የተስፋ ብርሃን የምገባ ማዕከል የምረቃ መርሐ ግብር ላይ ተገኝተው ለዐቅመ ደካሞች ማዕድ አጋርተዋል::Prime Minister...
28/09/2023

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በ20ኛው የአዲስ አበባ መስተዳድር የተስፋ ብርሃን የምገባ ማዕከል የምረቃ መርሐ ግብር ላይ ተገኝተው ለዐቅመ ደካሞች ማዕድ አጋርተዋል::

Prime Minister Abiy Ahmed attended the 20th Addis Ababa City Administration’s launch of the Tesfa Berhan Feeding Center and shared a holiday meal with beneficiaries of the center.

እንኳን 2016 ዓ.ም የደመራ እና የመሰቀል በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን!!መሰቀል ጌታችን መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የሰው ልጆችን ሁሉ ያለምንም ልዩነት እስከ መሰቀልና ሞት ድረስ...
27/09/2023

እንኳን 2016 ዓ.ም የደመራ እና የመሰቀል በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን!!

መሰቀል ጌታችን መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የሰው ልጆችን ሁሉ ያለምንም ልዩነት እስከ መሰቀልና ሞት ድረስ እራሱን አሳልፎ የሰጠበት ተወዳዳሪ የማይገኝለት ፍቅር መገለጫ ነው፡፡

እኛም በመስቀሉ ላይ የተገለጠው የክርስቶስ የቤዛነት፣ የፍቅር እና እውነት መጠን ፣ እርስ በእርስ በመዋደድ በመትጋት ከማይረቡ ጉዳዮች፣ እርስ በእርሳችን ከሚጋጩና ከሚያጠራጥሩን ሃሳቦችና ድርጊቶች ርቀን በፍቅር፣ በአንድነት በመኖር እንደ ደመራ አሰባሳቢ ጥበብን እየገበየን ፣ በአመት አንዴ ደመራን ስናከብር ብቻ ሳይሆን በእለት ተእለት ህይወታችን ውስጥ በተግባር እውነተኛ የመስቀሉ ወዳጆች መሆናችን በፍቅራችን እየገለፅን መኖር ይገባናል፡፡

ሁላችንም ለከተማችን እና ለሀገራችን ሰላም እና ልማት ደመራችንን እንደምር እላለሁ።
በድጋሚ እንኳን 2016 ዓ.ም የደመራ እና የመሰቀል በዓል በሰላም አደረሳችሁ፣ አደረሰን እያልኩ በዓሉ የፍቅር ፣ የሰላም፣ የጤና እና የብልጽግና እንዲሆንልን እመኛለሁ።

ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን ይባርክ!!!
ከንቲባ አዳነች አቤቤ

ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለ1498ኛው የመዉሊድ በዓል በሰላም አደረሳችሁ።በዓሉ የሰላም ፣የፍቅር ፣የደሰታ ፣ የመረዳዳትና የአብሮነት እንዲሆንላችሁ እመኛለሁ።መልካም ...
26/09/2023

ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለ1498ኛው የመዉሊድ በዓል በሰላም አደረሳችሁ።

በዓሉ የሰላም ፣የፍቅር ፣የደሰታ ፣ የመረዳዳትና የአብሮነት እንዲሆንላችሁ እመኛለሁ።
መልካም በዓል !

ከንቲባ አዳነች አቤቤ

"የኢትዮጵያዊያን ብርቱ እጆች በጽናት ታሪክ መስራት ቀጥለዋል። ዛሬ በተጠናቀቀው የክረምት የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ካቀድነው በላይ አሳክተን 7.5 ቢሊየን ችግኞችን መትከል ችለናል። ህዝ...
18/09/2023

"የኢትዮጵያዊያን ብርቱ እጆች በጽናት ታሪክ መስራት ቀጥለዋል። ዛሬ በተጠናቀቀው የክረምት የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ካቀድነው በላይ አሳክተን 7.5 ቢሊየን ችግኞችን መትከል ችለናል። ህዝባችን ያሳየውን ትጋትና እና ብርታት መንግስት በእጅጉ ያከብራል።"

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕድ

በአዲስ አበባ ከተማ የ2016 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በሁሉም ትምህርት ቤቶች ዛሬ ትምህርት መሰጠት ጀምሯል::በከተማ አስተዳደሩ በዛሬው እለት የ2016 የትምህርት ዘመን የተማሪ ወላጆች፣ መም...
18/09/2023

በአዲስ አበባ ከተማ የ2016 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በሁሉም ትምህርት ቤቶች ዛሬ ትምህርት መሰጠት ጀምሯል::

በከተማ አስተዳደሩ በዛሬው እለት የ2016 የትምህርት ዘመን የተማሪ ወላጆች፣ መምህራን እንዲሁም የስራ ሀላፊዎች በተገኙበት ትምህርት መሰጠት ጀምሯል።

በትምህርት ማስጀመሪያ መርሃ ግብሩ ላይ የትምህርት ቁሳቁሶች ለተማሪዎች ተሰራጭተዋል::

06/11/2021

ቀፎው እንደተናካበት ንብ ተነሱ!!
እውነትና ፍትህ የሉዓላዊነት ክብር በእብሪትና በግፍ ተነጥቆ መሰነት የማያስችለው ህዝብ የግፈኞች ጽዋ ሞልቶ ሲፈስ መነሳት የዚህ ጨዋ ህዝብ የታሪኩ አካል ነው::
በአሁኑ ሰአት መላው ኢትዮጵያዊ ከሰሜን እስከ ደቡብ ፤ከምስራቅ እስከ ምእራብ ከየአቅጣጫው በእልህና በቁጭት እንደ ሚንቀለቀል ነበልባል ቱግ ብሎ የተነሳው ለዚህ ነው::ቁጣው ከአካባቢ አካባቢ እንደ ሰደድ እሳት ተቀጣጥሏል፡፡ እልህ ቁጭትና የዘመናት በደል የወለደው የልብ ለልብ መገናኘትና የሃገር ፍቅር ከውስጡ አዝሏል፡፡ ይህ ህዝባዊ ማእበል አይደለም የአሸባሪ ቅጥረኛ ቀርቶ የትኛውንም ፈተና የሚያሻግር እውነተኛው የኢትዮጵያ ክንድ ነው፡፡
ኢትዮጵያ በልጆቿ አፍራ አታውቅም፤ ኢትዮጵያ በልጆቿ አንገቷን ደፍታ አታውቅም፤ ለጊዜው ትተክዝ ይሆናል፤ ለጊዜው ህመሟ በርትቶ ይሆናል፤ ኢትዮጵያ ከጀርባዋ የሚወጋት ፤ከውስጥዋ ወጥቶ የሚያደማት ባንዳ ላይጠፋ ይችላል፤ ጥንትም ባንዳዎችና አገር ሻጮች ነበሩ ዛሬም በታሪክ ፊት አስነዋሪ ክህደት የፈፀሙ ባንዳወች ተከስተዋል::
ነገር ግን ባንዳነት መቼም ቢሆን ኢትዮጵያዊነትን አሸንፎ አያውቅም!
የእናት ሆድ ዥንጉርጉር እንደሚባለው ከሚያደሟት ይልቅ የሚሞቱላት ይበልጣሉና ፤ እንደ ይሁዳ በዲናር ከሚቀይሯት ፤ያላቸውን ሰውተው የሚታገሉት ይልቃሉና፤ ጀግኖቿ በብዛትም በብርታትም ይበዛሉና ኢትዮጵያ ቀና ማለቷ፤ እንባዋ መታበሱ ፤ህመምዋ መፈወሱ አይቀርም፡፡
ትውልድ ሄዶ ትውልድ ቢተካ ፤ ልጆቿ በደም ስራቸውና በአጥንታቸው ዘልቆ የሚያልፍ የጀግንነት ሚስጥር የወረሱ ጭቆናንና ወራሪነትን እሺ ብለው የማይቀበሉ ፤ልያንበረክካቸው በሚነሱ ላይ ድርድር የማያውቁ ናቸው፡፡
ይህ ታሪክ ለዝንት አለም ይህን ግርማ ሞገሱንና ክብሩን ይዞ ይቀጥላል! ታሪክ ራሱን ይደግማል እንደሚባለው ባንዳ ይሸነፋል :: ኢትዮጵያ ታሸንፋለች:: የማሸነፏ ምስጥር ነጻነት, እኩልነት ፍትህ እውነት ናቸው::
አቶ መለሰ አለሙ የአዲስ አበባ ብልፅግና ፓርቲ ፅ/ቤት ሀላፊ

Address


Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Xayiba Lona- nufi posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Videos

Shortcuts

  • Address
  • Alerts
  • Videos
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share