Journalist Jafi Page

  • Home
  • Journalist Jafi Page

Journalist Jafi Page እውነተኛ መረጃን ማድረሰ!!

ቴሌ ደሞዝ እሲከደርሰ አብድራችዋለው አታሰቡ እያለ ነው!!ብቻ መሰሪያ ቤታችሁ በቴሌ ብር ደሞዛችሁን ይከፍል እንጂ አብሸሩ ብሏል!!Ethio telecomውድ ደንበኞቻችንበቅርቡ ሁሉን አካታች የ...
29/08/2022

ቴሌ ደሞዝ እሲከደርሰ አብድራችዋለው አታሰቡ እያለ ነው!!
ብቻ መሰሪያ ቤታችሁ በቴሌ ብር ደሞዛችሁን ይከፍል እንጂ አብሸሩ ብሏል!!
Ethio telecom
ውድ ደንበኞቻችን
በቅርቡ ሁሉን አካታች የፋይናንስ አገልግሎቶችን በማቅረብ ለሕዝባችን ታላቅ የምስራች ማብሰራችን ይታወሳል፤ ዛሬ ደግሞ በቴሌብር ደሞዝ ለሚከፈላቸው ሠራተኞች እስከ ደሞዝ መዳረሻ የብድር አገልግሎት በፈጣን ቀላል ምቹ እና አስተማማኙ ቴሌብር ማቅረባችንን በደስታ እየገለጽን

ድርጅቶች የሠራተኞቻችሁን ደሞዝ በቴሌብር በመክፈል ሠራተኞቻችሁን የአገልግሎቱ ተጠቃሚ ለማድረግ በአቅራቢያችሁ በሚገኙ የኢትዮ ቴሌኮም ኢንተርፕራይዝ አገልግሎት መስጫ ማዕከላት በመቅረብ መስተናገድ እንደምትችሉ በደስታ እንገልጻለን፡፡



ኢትዮ ቴሌኮም ከዳሸን ባንክ ጋር በአጋርነት

25/05/2022

ዶይቼ ቬለ ርዕሰ ጉዳዮችን በፊስ ቡክ ያወያያል።
Telegram : t.me/dw_amharic

Netiquette: http://www.dw.com/en/dws-netiq

20/03/2022
አቡበከር_ለሙከራ_ወደ_ደቡብ_አፍሪካ_አቅና!!የደቡብ አፍሪካን ሊግ እየመራ ለሚገኘው   ክለብ በጥር ወር የዝውውር መስኮት አቡበከር ናስርን ለማስፈረም የድቡብ አፍሪካው ክለብ ለሙከራ መጥራቱን...
25/01/2022

አቡበከር_ለሙከራ_ወደ_ደቡብ_አፍሪካ_አቅና!!

የደቡብ አፍሪካን ሊግ እየመራ ለሚገኘው ክለብ በጥር ወር የዝውውር መስኮት አቡበከር ናስርን ለማስፈረም የድቡብ አፍሪካው ክለብ ለሙከራ መጥራቱን ተሰምቷል!!
ትላንት ማምሻውን ወደ ደቡብ አፍሪካ አቅንቷል።
via ኢትዮጰያ ቡና

ከ80 ደቂቃ በላይ በ10 ተጨዋች የተጫወተች ፤ 3ቱም በረኞቿ በህመም ያልተሰለፉላት ፤ ለመጀመሪያ ጊዜ በአፍሪካ ዋንጫ የተሳተፈችው ኮሞሮሰ አዘጋጅ ሀገሯን ካሜሮን ገጥማ 2ለ1 ብትሸነፍም የአ...
24/01/2022

ከ80 ደቂቃ በላይ በ10 ተጨዋች የተጫወተች ፤ 3ቱም በረኞቿ በህመም ያልተሰለፉላት ፤ ለመጀመሪያ ጊዜ በአፍሪካ ዋንጫ የተሳተፈችው ኮሞሮሰ አዘጋጅ ሀገሯን ካሜሮን ገጥማ 2ለ1 ብትሸነፍም የአጥቂዋ ዮሱፍ ድንቅ ጎል እና የቡድኑ አሰገራሚ ብቃት ከሳቂታው የተጨዋች በረኛ ጋር የአፍሪካው ዋንጫው ድምቀት መሆናቸው አይካድም!!
የጨዋታው ዳኛ ባምላክ ተሰማ ነበር!!

ትላንት ማታ ቡርኪናፋሶ ጋቦን በፍፁም ቅጣት ምት 7ለ6 ካሸነፈች በዋላ ከሰር የምትመለከቷቸው የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት "እንኳን ደሰ አላችሁ" ካሉ ከሰአታት በዋላ በመኖሪያ ቤታቸው ላይ ተደጋጋሚ ...
24/01/2022

ትላንት ማታ ቡርኪናፋሶ ጋቦን በፍፁም ቅጣት ምት 7ለ6 ካሸነፈች በዋላ ከሰር የምትመለከቷቸው የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት "እንኳን ደሰ አላችሁ" ካሉ ከሰአታት በዋላ በመኖሪያ ቤታቸው ላይ ተደጋጋሚ የቶክሰ ሩምታ ተደርጎባችዋል።
ፕሬዝዳንቱ በአሁኑ ሰአት የት እንዳሉ አይታወቅም፤ ምናልባት መንፈቅለ መንግሰት ሳይካሄድባቸው አይቀርም ተብሏል!"
ቡርኪናፋሶን ጨምሮ 14 ሀገራትን በእጅ አዙር ቅኝ ግዛት በማሰተዳደር 700 ቢሊዮን ዶላር በአመት ታገኛለች የምትባለው ፈረንሳይ ዜጎቿ ከቤት እንዳይወጡ እና በከተማው የሚገኙ የፈረንሳይ ትምህርቶች እንዲዘጉ አዛለች!!
ቡርኪናፋሶን ከፈረንሳይ የእጅ አዙር ቅኝ አገዛዝ ለማውጣት ከአመታት በፊት የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት የነበረውን ሳንካራን ፈረንሳይ ማሰገደሏን ይታወሳል!!

በአሜሪካ ኮነክቲከት፤ ሚዞሪና ሌሎች ከተሞች በደረሰ ማዕበል ከ50 በላይ ሰዎች መሞታቸውን ተነገረ!!
11/12/2021

በአሜሪካ ኮነክቲከት፤ ሚዞሪና ሌሎች ከተሞች በደረሰ ማዕበል ከ50 በላይ ሰዎች መሞታቸውን ተነገረ!!

06/12/2021

ሰበር ዜና
ደሴ እና ኮምቦልቻ ከተሞች በጀግኖቹ የጸጥታ ኃይሎች ጥምረት ነጻ ወጥተዋል
***************
ታሪካዊቷ የደሴ ከተማና የንግድና የኢንዱስትሪ ኮሪደር የሆነችው ኮምቦልቻ ከተማ፣ በጀግኖቹ የጸጥታ ኃይሎች ጥምረት ነጻ ወጥተዋል።
በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የተመራው የኢትዮጵያ የጸጥታ ኃይሎች ጥምረት፣ ከደሴና ኮምቦልቻ በተጨማሪ በምሥራቅ ግንባር ባቲን፣ቀርሳን፣ ገርባንና ደጋንን ነጻ ያወጣ ሲሆን በሐርቡ ግንባር ደግሞ ቃሉ ወረዳን ሙሉ በሙሉ ተቆጣጥሯል።

የአፋልጉኝ ማሰታወቂያ!!ነኢማ አብዱቄ ትባላለች!! የ13 አመት ታዳጊ ሰትሆን የአዕምሮ ውሰንነት ያለባት ልጅ ነች!!ከትላንት በሰቲያ ሀሙሰ ጥቅምት 11 ከምትኖርበት አለም ገና ከቤት ሰራተኛ ...
23/10/2021

የአፋልጉኝ ማሰታወቂያ!!
ነኢማ አብዱቄ ትባላለች!! የ13 አመት ታዳጊ ሰትሆን የአዕምሮ ውሰንነት ያለባት ልጅ ነች!!
ከትላንት በሰቲያ ሀሙሰ ጥቅምት 11 ከምትኖርበት አለም ገና ከቤት ሰራተኛ ጋር ጠፍታለች!!
ያያችሁት ወይም ያለችበት የምታውቁ በነዚህ ሰልኮች እንዲደውሉልን በፈጣሪ ሰም እንጠይቃለን።
0911 14 43 41
0911 18 62 79
0911 25 20 03
ሀዋ ወይም አህመድ ብለው ይደውሉልን።
ሼር በማድረግ ልጃችን ለማግኘት ይተባበሩን

ለኒካ (ለቀለበት) ፤ ለብራይዳል እና ለ ሰርግአይዳ ዲኮር አለሎ!!በዚህ ሰልክ 090118 72 26 ቢደውሉ ያገኞችዋል!!
20/10/2021

ለኒካ (ለቀለበት) ፤ ለብራይዳል እና ለ ሰርግ
አይዳ ዲኮር አለሎ!!
በዚህ ሰልክ 090118 72 26 ቢደውሉ ያገኞችዋል!!

ቀድሞው የፈረንሳይ ፕሬዝደንት እግር ላይ የሚሄዱበትን ቦታ የሚቆጣጠር መሳሪያ ሊታሰር ነው።ቢቢሲ እንደዘገበው በድጋሚ ለመመረጥ ሲሉ የቀድሞ የፈረንሳይ ፕሬዝዳንት ሳርኮዚ ከሚገባው በላይ ለምር...
01/10/2021

ቀድሞው የፈረንሳይ ፕሬዝደንት እግር ላይ የሚሄዱበትን ቦታ የሚቆጣጠር መሳሪያ ሊታሰር ነው።
ቢቢሲ እንደዘገበው በድጋሚ ለመመረጥ ሲሉ የቀድሞ የፈረንሳይ ፕሬዝዳንት ሳርኮዚ ከሚገባው በላይ ለምርጫ ቅሰቀሳ ገንዘብ አውጥተዋል ተብሏል።
በዚህም ጥፋተኛ ተብለው 1 አመት ተፈርዶባችዋል።
እሰር ቤት መግባት አይጠበቅባቸውም የተባሉት ፕሬዝዳንቱ እግራቸው ላይ መሳሪያው ከታሰረ በኋላ የአንድ ዓመት እስራቸውን በመኖሪያ ቤታቸው ሆነው ማሳለፍ ይችላሉ ሲል ፍርድ ቤቱ ወስኗል።

ሰሜን ሎንደን ደርቢ አርሴናል ከቶተንሀም!!ድንቅ ጨዋታ!! አርሰናል 3 ለ 0 ቶተንሀምን እየመራ ለረዕፈት ወጥተዋል!!
26/09/2021

ሰሜን ሎንደን ደርቢ አርሴናል ከቶተንሀም!!
ድንቅ ጨዋታ!! አርሰናል 3 ለ 0 ቶተንሀምን እየመራ ለረዕፈት ወጥተዋል!!

የመንዙማና ነሺዳ አባት መሀመድ አወል ሳላህ የቀድሞ የኢትዮጵያ የጦር ሰራዊት የጀግና ሜዳላይ ተሸላሚ የ18ኛ ተራራ ክ/ጦር አባልም እንደነበረ የቀድሞ ጓደኛዋ በዚህ መልኩ ፅፎታል!!======...
23/08/2021

የመንዙማና ነሺዳ አባት መሀመድ አወል ሳላህ የቀድሞ የኢትዮጵያ የጦር ሰራዊት የጀግና ሜዳላይ ተሸላሚ የ18ኛ ተራራ ክ/ጦር አባልም እንደነበረ የቀድሞ ጓደኛዋ በዚህ መልኩ ፅፎታል!!
=========================================
መሐመድ አወል ሳላህ ("ነይ ድጌ!") ዐማኝ፣ ጨዋና ትሁት ኢትዮጵያዊ ብቻ አልነበረም።
ጀግና ወታደር! የኪ-ጥበብ ሰው እና የዚያ የብረት አጥር 18ኛ ተራራው ክፍለ ጦር ባልደረባም ነበር።
ዜና ዕረፍቱን ስሰማ ከልብ አዝኜአለሁ።
አይበገሬዎቹ የሳህል ተራራ ጀግኖች
እናንተ በሕይወት ያላችሁ የቀይ ኮከብ ፈርጦች
የእናት ሃገር ኢትዮጵያ የአንድነቷ ዘመን ነብሮች
ይኸው የጀግንነታችሁ አብሳሪ ድምፅ የነበረው ወንድማችሁ ተሰናብቷችኋል።
ፈጣሪ ነብሱን በደጋጎች አጠገብ ያሳርፍ።
ሠሎሞን ለማ ገመቹ

17/08/2021

ኢትዮጰያ በአፍሪካ ዋንጫ ከአዘጋጇ ካሜሮን ጋር ተመደበች።
የመከፈቻ ጨዋታ ካሜሮን ከ ቡርኪናፋሶ ይደረጋል። ተጨማሪ ድልድሎች በታዋቂ ተጨዋቾች እየወጣ ነው!! ኢትዮጰያ የመጀመሪያ ጨዋታዋ ከኬቬርዴ ጋር ሆኗል!!

19/01/2021
18/01/2021
ፕሬዝዳንት ሙሰቪኒ ማሸነፋቸውን አሰታወቁ!! የዩጋንዳው ፕሬዝዳንት በ76 አመታቸው ለተጨማሪ አመታት በሰልጣን እንድቆይ ህዝብ 58 በመቶ ድምፅ በመሰጠት መርጦኛል ብለዋል። በግማሸ ዕድሜ የሚያ...
16/01/2021

ፕሬዝዳንት ሙሰቪኒ ማሸነፋቸውን አሰታወቁ!! የዩጋንዳው ፕሬዝዳንት በ76 አመታቸው ለተጨማሪ አመታት በሰልጣን እንድቆይ ህዝብ 58 በመቶ ድምፅ በመሰጠት መርጦኛል ብለዋል። በግማሸ ዕድሜ የሚያንሰው የ38 አመቱ ተቀናቃኛቸው ቦቢ ዋይን ወታደሮች ቤቱን መውረራቸውና ምርጫው መጭበርበሩን ገልፅዋል። በሙዚቃው አለም ተወዳጅነትን ያተረፈው ቦቢ ዋይን ወደ ፖለቲካው ከገባ ጀምሮ በሀገሪቱ ዜጎች ተቀባይነት ቢያገኝም በፖሊሰ በተደጋጋሚ ለእሰር መዳረጉን ተነግሯል። ዩጋንዳ የመሪ ለውጥ ሳሰተናግድ 6 የሰልጣን አመታትን በማሰቆጠር ላይ መገኘቷ ሙሰቪን እያሰተቻቸው ይገኛል።

ኢትዮጲያዊቷ የእግር ኳስ ተጫዋች ወንድ ነሽ ቢሉኝም እኔ ግን ሴት ነኝ መገለሉ ይቁም ስትል ተናገረችለሀዋሳ ከተማ የምትጫወተዉ መሳይ ተመስገን በተያዘዉ የዉድድር ዓመት የሴቶች ፕርሚየር ሊግ ...
15/01/2021

ኢትዮጲያዊቷ የእግር ኳስ ተጫዋች ወንድ ነሽ ቢሉኝም እኔ ግን ሴት ነኝ መገለሉ ይቁም ስትል ተናገረች
ለሀዋሳ ከተማ የምትጫወተዉ መሳይ ተመስገን በተያዘዉ የዉድድር ዓመት የሴቶች ፕርሚየር ሊግ በኮከብ ግብ አግቢነት እየመራች ትገኛለች፡፡
ጾታዋን በተመለከተ በርካቶች ጥያቄን ያነሳሉ አንዳንዶችም ከፍተኛ የመገለል በደል እንደሚያደርሱባት ከጋዜጠኛ ምህረት ተስፋዬ ጋር በነበራት ቆይታ ተናግራለች፡፡
ተጫዋቿ በ2006 ዓመት ባህር ዳር ላይ ተዘጋጅቶ በነበረ የክልሎች ሻምፒዮና ጨዋታ ላይ በአንድ ጨዋታ አራት ግቦችን ታስቆጥራለች፡፡ይህ ግን መደነቅ አልነበረም ያተረፈላት ይልቁኑ ይህ ተጫዋች ወንድ ነዉ፤አብሮን ሊጫወት አይገባም የሚሉ ዘለፋና የደጋፊዎች ስድብ ከምቆጣጠረዉ በላይ ስሜቴን የጎዳ ክስተት ነበር ስትል መሳይ ተመስገን ተናግራለች፡፡
በእንዲህ ዓይነት ጫና እና ወከባ የተነሳ ከሶስት ዓመታት በላይ ከዉድድር ራሷ እንድታገል አስገድዷታል፡፡በድጋሚ ወደምትመደዉ ስፖርት እንድትመለስ አሰልጣኝ ዮሴፍ ገ/ወልድ ትልቁን ድጋፍ እንዳደረገላትም ታነሳለች፡፡
እግር ኳስ ፌደሬሽኑ በጠየቀዉ መሰረት ምርመራዉን አከናዉና በምርመራዉ ሴት መሆኗ ተረጋግጦላታል፡፡ምም እንኳን መሳይ በምርመራዉ ሴት መሆኗ ቢረጋገጥም አሁንም ድረስ በሜዳና ከሜዳ ዉጪ ስሜቷን የሚጎዱ ዘለፋና መገለል እንደሚደርስባት ተናግራለች፡፡
የሰዉነቴ አቋም እኔ ፈልጌ ያመጣሁት አይደለም፡፡ፈጣሪ የሰዉ ልጆችን ሲፈጥር በምክንያት ነዉ፡፡ ስለ እኔ ብዙ የሚሉ ሰዎች ግጭታቸዉ ከእኔ ጋር ሳይሆን ከፈጣሪ ጋር ነዉ፤በፈጣሪ አምናለሁ፡፡
መሳይ የማንችስተር ዩናይትድ ደጋፊ መሆኗን የምትናገር ሲሆን ከወጪ የክርስቲያኖ ሮናልዶ አድናቂ ከሀገር ዉስጥ ደግሞ የሽታዬ ሲሳይ አድናቂ መሆኗን ከብስራት ሬድዮ ዘጋቢዋ ምህረት ተስፋዬ ጋር በነበራቸዉ ቆይታ ላይ ተናግራለች፡፡

ኤለን መስክ የምድራችን ቀዳሚ ሀብታሙ ሰው ሆነ*****************የቴስላ ኤሌክትሪክ መኪና እና የስፔስ ኤክስ የሕዋ ታክሲ ፈጣሪና ባለቤት ኤለን መስክ ባልተጠበቀ ፍጥነት የየዓለም ሀብ...
12/01/2021

ኤለን መስክ የምድራችን ቀዳሚ ሀብታሙ ሰው ሆነ
*****************
የቴስላ ኤሌክትሪክ መኪና እና የስፔስ ኤክስ የሕዋ ታክሲ ፈጣሪና ባለቤት ኤለን መስክ ባልተጠበቀ ፍጥነት የየዓለም ሀብታሙ ሰው ሆኗል።
መስክ በድንገት 1ኛ የዓለም ሀብታም ሊሆን የቻለው የቴስላ የአክስዮን ዋጋ ማክሰኞ ዕለት በከፍተኛ ሁኔታ መጨመሩን ተከትሎ ሀብቱ ወደ 185 ቢሊዮን ዶላር በመመንደጉ ነው።
ከፈረንጆቹ 2017 ዓ/ም ጀምሮ የዓለም ቢሊዮነሮች ዝርዝርን ከላይ ሆኖ ሲመራ የነበረው የአማዞኑ ባለቤት ጄፍ ቤዞስ ነበር።
የኤሌክትሪክ መኪና አምራቹ ኩባንያ ቴስላ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የአክስዮን መጠኑ በማይታመን ደረጃ እየጨመረ መጥቶ ትናንት ረቡዕ 700 ቢሊዯን ዶላር እንደደረሰ ተዘግቧል።
ይህ ሁኔታ የኤለን መስክን ሀብት እንዲመነደግ ሳያደርገው አልቀረም። የኤለን መስክ ቴስላ የአክስዮን ፍላጎት ለመጨመሩ በርካታ ምክንያቶች ይጠቀሳሉ። ከነዚህ አንዱ መጪው ዘመን ከአየር ንብረት ለውጥ ጋር ተያይዞ ብዙ አገራት ፖሊሲያቸው ለኤሌክትሪክ መኪና የሚስማማ መሆኑ አይቀሬ እንደሆነ በመታመኑ ነው። bbc Amharic

ትላንት ለሊት የትራምፕ ደጋፊዎች የህዝብ ተወካዮች መሰብሰቢያ አዳራሸን በጉልበት ተቆጣጠሩ!! የዲሞክራሲ ጠበቃና ምሳሌ ነኝ በምትለው አሜሪካ ነውጠኛው የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ባነ...
07/01/2021

ትላንት ለሊት የትራምፕ ደጋፊዎች የህዝብ ተወካዮች መሰብሰቢያ አዳራሸን በጉልበት ተቆጣጠሩ!! የዲሞክራሲ ጠበቃና ምሳሌ ነኝ በምትለው አሜሪካ ነውጠኛው የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ባነሳሱት አመፅ የተመራጩ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን መመረጥ ይፋ እንዳይደረግ ደጋፊዎቻቸው ሂደቱን አሰናክለዋል!! አፈጉባኤዋ ናንሲ እና ጆ ባይደን ጥቃት እንዳይደርሰባቸው በደህንነት ሀይሎች ጥበቃ ተደርጎላችዋል ተብለዋል!! ጆ ባይደን ለትራምፕ ባሰተላለፋት ጥሪ ደጋፊዎቻቸው አካባቢውን እንዲለቁ እንዲነግሮቸው በማሰሰባቸው ትራምፕ"ወደ ቤት ሂዱ፤እንወዳችዋለን"ሲሉ ለደጋፊዎቻቸው ተናግረዋል!! በአሁኑ ሰአት ምክር ቤቱ ሰብሰባውን ቀጥሏል!!

በትግራይ ክልል ተቋርጦ የነበረው የአሮጌ ብር ኖት ቅያሬ በድጋሚ ተጀመረ**************************በትግራይ ክልል ተቋርጦ የነበረው ከ100 ሺህ ብር በታች የአሮጌ ብር ኖት ቅያ...
30/12/2020

በትግራይ ክልል ተቋርጦ የነበረው የአሮጌ ብር ኖት ቅያሬ በድጋሚ ተጀመረ
**************************
በትግራይ ክልል ተቋርጦ የነበረው ከ100 ሺህ ብር በታች የአሮጌ ብር ኖት ቅያሬ ድጋሚ መጀመሩን ኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ አስታወቀ።
ባንኩ ለኢቢሲ በላከው መግለጫ መንግሥት በክልሉ በወሰደው የሕግ ማስከበር ዘመቻ ምክንያት የአሮጌ ብር ኖት ቅያሬው ተቋርጦ እንደነበር አስታውሶ አሁን ላይ በተወሰኑ የክልሉ ከተሞች የመብራት እና የኢንተርኔት አገልግሎት በመጀመሩ በእነዚሁ አካባቢዎች ባንኮች ሥራ እንዲጀምሩ እየተደረገ ይገኛል ብሏል።
በዚሁ መሠረት ተቋርጦ የነበረውን የአሮጌ ብር ኖት ቅያሬ ባንኮች ሥራ ከጀመሩበት ቀን ጀምሮ ቅዳሜና እሁድን ጨምሮ በ14 ቀናት ውስጥ አሮጌ ብር እንዲቀይሩ ከዛሬ ታኅሣሥ 21 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ መወሰኑንም ነው ባንኩ ያስታወቀው።
ባንኮችም ይህንኑ ተከታትለው እንዲያስፈጽሙ እና ተግባራዊ እንዲያደርጉ በመጠቆም በብር መቀየሩ ሂደት የነበሩ መመሪያዎች እና አሠራሮች እንደተጠበቁ መሆናቸውንም ገልጿል።
ከባንክ በጥሬ ገንዘብ የሚወጣው የገንዘብ መጠን ላይ በተሻሻለው መመሪያ ላይ በተቀመጠው መሠረት ተፈፃሚ የሚሆን ሲሆን ከ100 ሺህ እስከ 1.5 ሚሊየን አሮጌ ብር ያላቸው የመቀየሪያው የጊዜ ገደብ የሕግ ማስከበሩ ከመጀመሩ በፊት የተጠናቀቀ በመሆኑ ብር መቀየር የሚችሉት ከ100 ሺህ ብር በታች ያላቸው መሆናቸውን ባንኩ አስታውቋል።

አርሴናል 2 ቼልሲ 0 እረፍት ወጥተዋል። ጨዋታው በኢትዮ ሳት Horn Sport 2 እየተላለፈ ነው።
26/12/2020

አርሴናል 2 ቼልሲ 0 እረፍት ወጥተዋል። ጨዋታው በኢትዮ ሳት Horn Sport 2 እየተላለፈ ነው።

የመጀመሪያው አርተፊሻል ልብ በአውሮፓ ለገበያ እንዲውል ፈቃድ አገኘ************************************************በአውሮፓ የዘርፉ ተቆጣጣሪዎች የመጀመሪያ የሆነው...
24/12/2020

የመጀመሪያው አርተፊሻል ልብ በአውሮፓ ለገበያ እንዲውል ፈቃድ አገኘ
************************************************
በአውሮፓ የዘርፉ ተቆጣጣሪዎች የመጀመሪያ የሆነውን ሰው ሰራሽ ልብ ለገበያ እንዲውል ፈቃድ መስጠታቸው ተሰምቷል፡፡ ለሀያ ሰባት አመታት ያክል ሲለፋበት የነበረውና ስኬት አግኝቶ ከሰባት አመታት በፊት ፈቃድ የተሰጠው ሰው ሰራሽ ልብ ለአምራቹ ኬርሜት ትልቅ ተስፋን ሰጥቷል፡፡ ኬርሜት በዘርፉ ስቶክ ገበያ ውስጥ 66 በመቶ ድርሻ ያለው ሲሆን ይህም የገበያ ዋጋውን 407 ሚሊዮን ይሮ አድርሶለታል፡፡
ድርጅቱ በያዝነው ሳምንት ምርቱን በአውሮፓ ህብረት አባል ሀገራት ውስጥ መሸጥ የሚያስችለውን ፈቃድ ማግኘቱን የዘገበው ብሉምበርግ ቴክኖሎጂ ነው፡፡ ይህም በልብ በሽታ እየተሰቃዩ ላሉ ህሙማን የልብ ንቅለ ተከላ ማድረግ የሚያስችላቸውን እድል ይፈጥርላቸዋል ተብሏል፡፡
ሰርጅንና የልብ ቱቦ (heart-valve) ፈጠራ ባለቤት ያደረጉት ስምምነት በፈረንሳይ ሰው ሰራሽ ልብ የሚመረትበትን መንገድ በ1993 ከፍቷል፡፡ የድርጅቱንም ድርሻ ኬርሜትና ኬርፔንቴር የተባሉ ባለቤቶች ይዘውታል፡፡ በመሆኑም የሽያጭ ፈቃዱን በማግኘቱ ኬርሜት የፊታችን ጥር የምርት ሂደቱን እንደሚጀምር አሳውቋል፡፡
ይህ አርቲፍሻል ልብ ተመርቶ ለገበያ ከቀረበ በኋላ ለኬርሜት ከ700 ሚሊዮን ዩሮ በላይ አመታዊ ገቢ እስከ 2030 እንደሚያስገኝለት ተገምቷል፡፡ ምርቱንም በፈረንጆቹ 2021 ሁለተኛ ሩብ አመት ለገበያ እንደሚያቀርብ ድጅቱ አሳውቋል፡፡
ምንጭ Bloomberg Technology

24/12/2020

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር አዲስ የካቢኔ አባላትን ይፋ አደረገ
በትግራይ ክልል አዲስ የካቢኔ አባላት ተሹመው ወደ ስራ መግባታቸውን የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር አስታወቀ፡፡ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር የጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ገብረመስቀል ካሣ ለኢዜአ እንደገለጹት በክልሉ አዲስ የካቢኔ አባላት ተሹመው ወደ ስራ ገብተዋል፡፡ በክልሉ ከሚያስፈልጉ 16 የካቢኔ አባላት መካከል 11 ተሿሚዎች በይፋ ስራ መጀመራቸውን ገልጸዋል፡፡
በዚሁ መሠረት፡-
ዶክተር ካህሣይ ብርሃኑ …… የክልሉ ፋይናንስ ቢሮ ሃላፊ
ኢንጂነር አሉላ ሃብተአብ …… የኮንስትራክሽን፣ መንገድና ትራንስፖርት ቢሮ ሃላፊ
ዶክተር ፋሲካ አምደ ስላሴ …… የጤና ቢሮ ሃላፊ
አቶ አበራ ንጉሴ ………. የፍትህ ቢሮ ሃላፊ
ወይዘሮ እቴነሽ ንጉሴ ……… የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ሃላፊ
አቶ ዮሴፍ ተስፋይ ………. የንግድ፣ ኢንዱስትሪና ከተማ ልማት ቢሮ ሃላፊ
ዶክተር ተስፋይ ሰለሞን …….. የትምህርት ቢሮ ሃላፊ
ዶክተር ገብረህይወት ለገሠ ……. የውሃ ጥናትና ዲዛይን ቢሮ ሃላፊ
አቶ ሰለሞን አበራ …….. የውሃ ሃብት ቢሮ ሃላፊ
አቶ አብርሃ ደስታ ……. የማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ሃላፊ እና
አቶ ገብረመስቀል ካሣ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር የጽህፈት ቤት ሃላፊ ሆነው መሾማቸው ተገልጿል፡፡
ሌሎች ያልተሟሉ የካቢኔ አባላት በቀጣዮቹ ሳምንታት ተሟልተው ወደ ስራ ይገባሉ ተብሏል።

የሙለር ሪልስቴት ባለቤት አቶ ሙሉጌታ ተስፋኪሮስ የሕወሓት እና የኦነግ ሸኔ የጥፋት ቡድኖች የፋይናንስ ምንጭ ስለመሆናቸው የሚያስረዳ ማስረጃ ማግኘቱን ፖሊስ ለፍርድ ቤት ገለጸ**********...
24/12/2020

የሙለር ሪልስቴት ባለቤት አቶ ሙሉጌታ ተስፋኪሮስ የሕወሓት እና የኦነግ ሸኔ የጥፋት ቡድኖች የፋይናንስ ምንጭ ስለመሆናቸው የሚያስረዳ ማስረጃ ማግኘቱን ፖሊስ ለፍርድ ቤት ገለጸ
******************
ባለሀብቱ የሙለር ሪልስቴት ባለቤት አቶ ሙሉጌታ ተስፋኪሮስ የሕወሓት እና የኦነግ ሸኔ የጥፋት ቡድኖች የፋይናንስ ምንጭ ስለመሆናቸው የሚያስረዳ ማስረጃ ማግኘቱን የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ወንጀል ቢሮ ለፍርድ ቤት ገለጸ።
ተጠርጣሪዎቹ ኃይላይ መዝገበ፣ ሙሉጌታ ተስፋ ኪሮስ እና ሳሙኤል አባዲ ናቸው።
የሙለር ሪልስቴት ባለቤት የሆኑት ሙሉጌታ ተስፋኪሮስ የሕወሓት እና የኦነግ ሸኔ ሎጂስቲክ ክንፍ በመሆን ሲንቀሳቀሱ ነበር ብሏል ፖሊስ የምርመራ መዝገቡን በመጥቀስ።
ከእርሳቸው ጋር በቁጥጥር ስር የዋሉት ሌሎች ተጠርጣሪዎች የሕወሓት የማጠናከሪያ ሪፎርም በሚል በአዲስ አበባ የጥፋት ተልእኮ አንግበው ሲሠሩ እንደነበር የሚያሳይ ማስረጃ ማግኘቱንም ገልጿል የምርመራ ቡድኑ።
የምርመራ ቡድኑ ፍርድ ቤቱ በሰጠው ጊዜ ያከናወናቸውን ተግባራት በመዘርዘር ለቀሪ ሥራዎች 14 ቀን ጠይቋል።
ተጠርጣሪዎች በግላቸውና በጠበቆቻቸው በኩል በቁጥጥር ስር ከዋሉ 60 ቀናት ቢቆጠርም “ጥፋተኝነታችንን የሚያሳይ ማስረጃ አልተገኘብንም” በማለት ተከራክረዋል።
የሪልስቴቱ ባለቤት አቶ ሙሉጌታ በሺዎች የሚቆጠሩ ሠራተኞች የሥራ እድል በመፍጠር ከየትኛውም ፖለቲካ ነፃ በመሆን በንግድ ሥራ የተሰማሩ የውጭ ዜጋ ስለመሆናቸው ገልጸዋል።
ፈፅመሀል የተባለው ወንጀል አይመለከተኝም በማለት ተከራክረው የመብት ጥያቄም አንስተዋል።
ሦስቱም ተጠርጣሪዎች የምርመራ ቡድን ተጠርጣሪዎች ፈፅመውታል የተባሉ የወንጀል ተግባራትን በመዘርዘር አቤቱታቸው ውድቅ እንዲደረግ አመልክቷል።
የግራ ቀኙን ክርክር የተከታተለው ችሎቱ ፖሊስ ያካሄደውን የምርመራ መዝገብ አስቀድሞ በመመልከት ትእዛዝ ለመስጠት ለነገ ታህሳስ 16/2013 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ይዟል።
በጥላሁን ካሳ

አዲሱ የትግራይ ቲቪ ፍሪኬንሲ በዚህ ማግኘት ይቻላል!!SD 12645/12646 Vertical,Symbol rate 27500 , AutoTigrai Tv (New) HD 12521,Vertical, Sym...
15/12/2020

አዲሱ የትግራይ ቲቪ ፍሪኬንሲ በዚህ ማግኘት ይቻላል!!
SD 12645/12646 Vertical,Symbol rate 27500 , Auto
Tigrai Tv (New) HD 12521,Vertical, Symbol rate 27500, Auto.

ያልተለመደ ስርቆት...“ቁም” የሚል የትራፊክ ምልክት በመንቀል ተሸክሞ ሲሄድ የተገኘው ተከሳሽ በ2 ዓመት ከ9 ወር ፅኑ እስራት እና 1000 ብር ተቀጣ ፦ በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ልዩ ቦታ...
20/11/2020

ያልተለመደ ስርቆት...
“ቁም” የሚል የትራፊክ ምልክት በመንቀል ተሸክሞ ሲሄድ የተገኘው ተከሳሽ በ2 ዓመት ከ9 ወር ፅኑ እስራት እና 1000 ብር ተቀጣ ፦ በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ልዩ ቦታው አመዴ ማዞርያ ተብሎ ከሚጠራው አካባቢ ግዛቸው ሚልክያስ ጌታቸው የተባለው ተከሳሽ ጥቅም 06/2013 ዓ.ም በግምት ከንጋቱ 12 ሰዓት ወንጀሉን ፈፅሟል።
ንብረትነቱ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትራፊክ ማኔጅመንት ኤጀንሲ የሆነ “ቁም” የሚል የትራፊክ ምልክት ከነብረቱ የዋጋ ግምቱ 8‚317.50 የሚያወጣ ንብረት ተሸክሞ ሲሄድ በቁጥጥር ስር ውሏል።
የፌደራሉ የመጀመርያ ደረጃ ፍርድ ቤት አዲስ ከተማ ምድብ ወንጀል ችሎት ህዳር 08 በዋለው ችሎት ተከሳሽ ክሱ ተነቦለት “አውነት ነው ድርጊቱን ፈፅሚያለሁ በዚህም ጥፋተኛ ነኝ” ሲል የእምነት ቃሉን ያሰማ በመሆኑ ፍርድ ቤቱ በ2 ዓመት ከ9 ወር ፅኑ እስራት እና 1000 ብር የገንዘብ ቅጣት እንዲቀጣ ወስኖበታል።

19/11/2020

በአዲስ አበባ ባለቤት ያልተገኘላቸው ህንጻዎች 100 መድረሳቸውን የከተማ አስተዳደሩ ገለጸ
********************
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በወቅታዊ አገራዊ ጉዳይ ላይ ከሁሉም ክፍለ ከተማ ከተውጣጡ የከተማዋ ወጣቶች ጋር በዛሬው ዕለት ውይይት አካሂዷል።
በመድረኩ ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ እንደገለፁት፣ በከተማዋ የሚገኙ ህንጻዎች፣ ታጥረው የሚገኙ መሬቶች እና የቀበሌ ቤቶችን በተመለከተ እየተደረገ ባለው ዳሰሳ እስካሁን 100 ህንጻዎች ባለቤት አልተገኘላቸውም።
ከዚህም በተጨማሪ ታጥሮ የተቀመጠ ከ1 ሺህ ሄክታር መሬት በላይ ባለቤት ሳይገኝለት ቀርቷል።
በህገ ወጥ መንገድ የተያዙ የቀበሌ ቤቶች ላይም ማጣራት እየተደረገ መሆኑን ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ ተናግረዋል።
በውይይቱ ላይ የተሳተፉ የከተማዋ ወጣቶች በትግራይ ክልል እየተደረገ ያለውን የሕግ ማስከበር ዘመቻ እንደሚደግፉ እና ከመከላከያ ሠራዊት ጎን መሆናቸውን ገልጸዋል።
በእዮብ ሞገስ

Address


Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Journalist Jafi Page posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Videos

Shortcuts

  • Address
  • Alerts
  • Videos
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share