03/08/2023
ተጠቃሚዎች
ሰሞኑ የሚባል ማህበራዊ ሚዲያ ፔጅ አዲስ የሚደራጀውን የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ዋና ማዕከልና በሌሎች ጉዳይ ጋር ተያይዞ የህዝቡን ቀልብ በውሸትና የተቀነባበረ መረጃ በማሰራጨት ትኩረት ስቧል።
በገጹ የሚለጥፉ አብዛኛው መረጃዎች አሁን ያለውን ነባራዊ ሁኔታና አዝማሚያውን በመጠቀም ከእውነት የራቀ እና የተቀነባበሩ መረጃዎች እያሰራጨ በመሆኑ ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈልጋል። ምክንያቱም በዚህ ፔጅ የተለጠፉ አብዛኛው መረጃዎች ከሁለትና ሶስት ቀን በኃላ እየጠፋ ነው። በተጨማሪም የቆዩ ፎቶችን በመወሰድ አንድ ቀን በስብሳባም(በውሳኔውም) ላይ ያልተሳተፉ ግለሰቦችን እየሞገሰ ይውላል።
ይህ ፔጅ ከዚህ በፊት በሌላ ሰው ስም ስያሜ ያለና አሁን ወደ የተቀየረ ነው። በዚህ ፔጅ ከዚህ በፊት የወላይታ ህዝብ ስም የሚጠላሹና ውሸት መረጃዎችን ሲያሰራጭ ነበር። ከ4.5 ሺህ ተከታያ ያለው ሲሆን ከ8 ሺህ በላይ ተከታይን በአንድ ወር ውስጥ በማግኘት ከ13 ሺህ በላይ ተከታይ አፍርቷል።
የዚህ ፔጅ ዋና ዓላማው የወላይታ ህዝብ ጥቅም ለማጠልሸት ከወንድም ህዝቦች ጋር ለማሻከርና ከሌሎች አጋሮባች ዞኖች ጋር ያለውን አብሮነትና አንድነትን ለማፋለስ እየሰራ መሆኑን መረጃዎች እያሳዩ ናቸው።
እንዲሁም አምስት ዞኖችና ስድስት ልዩ ወረዳዎች ህዝቦች በየምክር ቤቶቻቸው በአንድ ክልል ተደራጅተው ለመኖር የተስማሙትን መልካም ሀሳባቸውን በተሳሳተ ሁኔታ አደገኛና ስጋት የሚጫሩ መረጃዎችን እያሰራጨ መሆኑን እንመለከታለን።
ለወላይታ ህዝብ ጠቃሚ መረጃዎችን እያሰራጨ በማስመሰል የወላይታ ህዝብን ዳግም ዋጋን ለማስከፈል እየሰራ መሆኑን ህዝቡ ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈልጋል።
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መቀመጫዎች ወላይታ የድርሻውን ማግኘቱ አይቀርም ሌሎችም እንደዛው። እውነታው ይህ ነው ከዚህ ውጪ አዲስ ነገር አንጠብቅ።
በዚህ ፔጅ የተቀነባበረና ውሸት መረጃውን የሚያሰራጨውን ግለሰብ ማንነት እየተጣራ ጫፍ ላይ የደረሰ ሲሆን የግለሰቡን ማንነት በቅርቡ ለህዝቡ ይፋ እናደርጋለን።
በአጠቃላይ በዚህ ፔጅ ላይ የሚሰራጩ
ጨው ምንጩ ያልታወቀና ያልተረጋገጠ መረጃዎችን ላይክ፣ ኮሜንትና ሼር የሚያደርጉ ግለሰቦች እንድትቆጥቡ እናሳስባለን።