መባቻ

መባቻ የመረጃ እና የመዝናኛና ገጽ

መባት: መግባት፣ መጀመር፣ መሠልጠን?

እነሆ "ለሀገሬ" ሰው "ሀገሬን" እንካችሁ ብያለሁ፡፡Henok Seyoume Hagere ሦስተኛዋ መጽሐፋችን ታትማለች፡፡ ገበያ ላይ መዋሏን እናበስራለን። ስሟን "ሀገሬን" ብለናታል፡፡ ወደ ሀገ...
03/03/2021

እነሆ "ለሀገሬ" ሰው "ሀገሬን" እንካችሁ ብያለሁ፡፡
Henok Seyoume Hagere

ሦስተኛዋ መጽሐፋችን ታትማለች፡፡ ገበያ ላይ መዋሏን እናበስራለን። ስሟን "ሀገሬን" ብለናታል፡፡ ወደ ሀገሬ የተደረገ ጉዞ ነው፡፡ አባይ ሸለቆ ውስጥ እንገባለን፤ ጀግኖቹ የጉምዝ ባላባቶችን ለሀገር የተከፈለ ተጋድሎ ባድማቸው ድረስ ሄደን እናያለን፡፡ ደግሞ ወደ ምስጢራዊው ገዳም አብረን ደርሰናል፡፡ ደቅ፤ መተከል ያለው የሥውራን ስፍራ፤
ከእሳት ባህር እስከ ዱሩ-ብዙ ትረካዎችን ይዟል፤ ከዝኆን ጋር የተፋጠጥንባቸው የዱር ሕይወት ትዝታዎችም ተከትበውበታል፡፡ እንስሳቱ የት ገቡ? ብለን የነበረን ነበር ሲሆን አብረን እንሞግታለን፡፡
ስለ ኮማንዶ ምኑን ልንገራችሁ፤ እላያችን ላይ የፈነዳ እሳተ ገሞራን ያስመለጠ አርብቶ አደር እኮ ነው፡፡ እሳት ዳር ቁጭ ብለን ጂኒዎቹ ለምን መጡ? ዛሬም የሚያስፈራ፤ ዛሬም የሚያስቅ ምሽት፤ ጎፋ መርቆኛል፡፡ አህያ ቀንድ እስክታበቅል መስቀልን ኖሬ እመለከት ዘንድ፤ የጎፋው ኢትኖግራፊም፣ ታሪክም፣ ጉዞም ነው፡፡ ጉንዳ ጉንዶ መድረስ ጀግንነት መሆኑን አምኜ ጽፌዋለሁ፡፡ ሌሎቹን ምዕራፎች ባልነካቸው ይሻለኛል። ስትገልፁት ድረሱበት።
ተአምረ ምኒልክ፣ መልከአ ምኒልክ፣ ገድለ አበው ዘ አድዋና ገድለ አበው ዘ ኢትዮጵያ በክብር ከነገረ አንበሳ አንድ ምዕራፍ ጋር ታጅበው ቀርበውበታል፡፡ በቦታው የታየውን ስለቦታው ቀድሞ ከተፃፈው ጋር ተዋህዶ ከብዙ ድካም በኋላ እጃችሁ መግባቱን እነግራችኋለሁ፡፡ በእግርም በእጅም የተጻፈ መጻሕፍ ነውና፡፡

አድዋ"የኩራት መልኩ፣የውሃ ልኩ፤ይሞላል ወንዙ፣የደም ላቭ ወዙ፤ይጸናል ቤቱ፣የነፃነቱ፣ያርበኝነቱ፤አድዋ___!ነፍስ የገበሩ፣ሀገር አኖሩ፤ላገር ያለፉ፣ከሞት ተረፉ፤እየረገፉ፤እየረገፉ፤እየረገፉ፤አድ...
02/03/2021

አድዋ

"የኩራት መልኩ፣
የውሃ ልኩ፤
ይሞላል ወንዙ፣
የደም ላቭ ወዙ፤
ይጸናል ቤቱ፣
የነፃነቱ፣
ያርበኝነቱ፤
አድዋ___!
ነፍስ የገበሩ፣
ሀገር አኖሩ፤
ላገር ያለፉ፣
ከሞት ተረፉ፤
እየረገፉ፤
እየረገፉ፤
እየረገፉ፤
አድዋ___!
የኪዳን ቃሉ፣
የመዳን ውሉ፤
የውሉም ፊርማው፣
ሰንደቅ አላማው!
ሰንደቅ አላማው!
ሰንደቅ አላማዉ!
!!!!!!!!!
አድዋ~የደም ፀሀይ!

(ሃብተ ማርያም መንግስቴ)
🙏🙏🙏

Ethiopian Music : Dagne Walle ዳኜ ዋለ (የደም ፀሐይ) - New Ethiopian Music 2021(Official Video) Ethiopian Music: Check Out Ethiopian New Musics, Comedy and More Et...

“ምነዋ” - “በምነው ሸዋ”!...ከወራት በፊት በቃና ቲቪ በተላለፈ የአውደ አመት የመዝናኛ ፕሮግራም ላይ “ይረገም” እና “በባይተዋር ጎጆ” የተሰኙትን ዘመን ተሻጋሪ ዜማዎች በአስደማሚ ብቃት...
12/02/2021

“ምነዋ” - “በምነው ሸዋ”!...
ከወራት በፊት በቃና ቲቪ በተላለፈ የአውደ አመት የመዝናኛ ፕሮግራም ላይ “ይረገም” እና “በባይተዋር ጎጆ” የተሰኙትን ዘመን ተሻጋሪ ዜማዎች በአስደማሚ ብቃት በማቀንቀን ለመጀመሪያ ጊዜ በህዝብ አይን ውስጥ የገባችው አዲሲቷ ድምጻዊት ተዓምር ግዛው፣ “ምነዋ” የተሰኘውን አዲስ ነጠላ ዜማዋን ከደቂቃዎች በፊት ለህዝብ አድርሳለች፡፡

ግጥሙን ናትናኤል ግርማቸው ከትቦት፣ ዜማውን አንተነህ ወራሽ ቀምሮት፣ ሚካኤል ሃይሉ ያቀናበረው፣ 16 ፊልም ፕሮዳክሽን በኤልሳቤጥ በለጠ ዳይሬክተርነት ቪዲዮውን ያዘጋጀለትና በናትናኤል ግርማ ፕሮዲዩሰርነት የቀረበው “ምነዋ”፣ በምነው ሸዋ የዩቲዩብ ቻነል በኩል እየታዬ ይገኛል፡፡

ናትናኤል ግርማቸው ከዚህ በፊት ለአድማጭ ያበቃቸው ስራዎቹን ለመጥቀስ ያህል፡-

ለዳዊት ጽጌ - “እትቱ” እና “ደሳለኝ” ን ጨምሮ 5 ግጥሞች
ለተመስገን ታፈሰ - “ሳብዬ”
ለአቢ ላቀው - “መሳይ”
ለታረቀኝ ሙሉ - “ስሚያቸው”
ለብስራት ሱራፌል - “የቤት ስራ”፣ “ዛሬም ከኋላ” እና “የጀግና እናት” (ነጠላ ዜማ) ጨምሮ 4 ግጥሞች
ለሃሌሉያ ተክለጻድቅ - “ተጠፋፋን”
ለራሄል ጌቱ - “የአገሬ ሰው”
ለአህመድ ተሾመ - “አይ መሬት ያለ ሰው” እና “ሸገር”
ለጂ መሳይ ከበደ - “አገኘሁዋት"
ለበሃይሉ ታፈሰ (ዚጊዛጋ) - “ብትመጪም ብትሄጅም” እና “ጎዲን”ን ጨምሮ 4 ግጥሞች… የሚጠቀሱ ሲሆን፣ ከሌሎች ገጣሚዎች ጋር በጋራ ከሰራቸው የሙዚቃ ግጥሞች መካከል ደግሞ፤ ለብስራት ሱራፌል የሰጠው “አለና” እንዲሁም አዲስ ሙላት እና አብዱ ኪያር በቅርቡ በጋራ ያቀነቀኑት “የውብዳር” ይጠቀሳሉ፡፡
ብዙዎች በጉጉት ሲጠብቁት የቆዩትን “ምነዋ” አዲስ ነጠላ ዜማ የሙዚቃ ቪዲዮ በሚከተለው ሊንክ ገብታችሁ ትመለከቱት ዘንድ በአክብሮት ተጋብዛችኋል!!!
https://www.youtube.com/watch?v=3PJSmjnVbsE

Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)

JUST 4 DAYS - MORE THAN 333,000 VIEWS🙏
11/02/2021

JUST 4 DAYS - MORE THAN 333,000 VIEWS🙏

Yehunie Belay | Dem Dem | ይሁኔ በላይ - ድም ድም | New Ethiopian Music 2021 #ይሁኔበላይ #ድምድምይህ የይሁኔ በላይ የዩቲብ ቻናል ነው:: በየጊዜው ለሚለቀቁ ስራዎች በቀጥታ እንዲላክ...

ገለል በሉለት!...(በእውቀቱ ስዩም)ገለል በሉለት - አንድ ጊዜ ለሱየወረቀት ዛር - ቀለም ነው ምሱበዱር ሳይሸምቅ - ወጥቶ አደባባይጥይት ሳይተኩስ - በቃል ሲያደባይየሚያንቀጠቅጥ - ጉልበት...
14/10/2020

ገለል በሉለት!...

(በእውቀቱ ስዩም)

ገለል በሉለት - አንድ ጊዜ ለሱ
የወረቀት ዛር - ቀለም ነው ምሱ
በዱር ሳይሸምቅ - ወጥቶ አደባባይ
ጥይት ሳይተኩስ - በቃል ሲያደባይ
የሚያንቀጠቅጥ - ጉልበት አለኝ ባይ::
በዘመን ሰፌድ -እያንጉዋለሉ
ቢያንጠረጥሩት - ዳሩ ማሃሉ!
ፍሬ ብቻ ነው - የለውም አሠር
ልቡ እንደ ገላው የማይታሠር !!

“የፈራ ይመለስ!”

13/10/2020

"መሃይም ነው ተብሎ፣ ሰው እንዴት ይናቃልያልተማረ አዋቂ፣ ሲጠይቅ ይጨንቃል"                                     - የአገሬ ባላገር
09/10/2020

"መሃይም ነው ተብሎ፣ ሰው እንዴት ይናቃል
ያልተማረ አዋቂ፣ ሲጠይቅ ይጨንቃል"
- የአገሬ ባላገር

ማን ይድረስለት?አመት ሙሉ ደፋ ቀና ብሎ ያደረሰውን ሰብል የአንበጣ መንጋ ዶግ አመድ ሲያደርግበት አንገቱን ከመድፋት ውጭ መላ ላጣው የአገሬ ገበሬ ማን ይድረስለት?
08/10/2020

ማን ይድረስለት?
አመት ሙሉ ደፋ ቀና ብሎ ያደረሰውን ሰብል የአንበጣ መንጋ ዶግ አመድ ሲያደርግበት አንገቱን ከመድፋት ውጭ መላ ላጣው የአገሬ ገበሬ ማን ይድረስለት?

ሰውዬው!
08/10/2020

ሰውዬው!

በሚገባ ኖረዋል... ብዙ አበርክተዋል 🙏
30/09/2020

በሚገባ ኖረዋል... ብዙ አበርክተዋል 🙏

አትሌት ደጊቱ አዝመራው ኮሮና ስለተገኘባት ከለንደን ማራቶን ጉዞ ታገደችእሁድ በሚካሄደው የለንደን ማራቶን የወርቅ ሜዳሊያ ታገኛለች ተብላ የተጠበቀችው ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ደጊቱ አዝመራው በኮ...
29/09/2020

አትሌት ደጊቱ አዝመራው ኮሮና ስለተገኘባት ከለንደን ማራቶን ጉዞ ታገደች

እሁድ በሚካሄደው የለንደን ማራቶን የወርቅ ሜዳሊያ ታገኛለች ተብላ የተጠበቀችው ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ደጊቱ አዝመራው በኮሮና ቫይረስ መያዟ መረጋገጡን ተከትሎ ከጉዞው እንድትቀር መደረጉን ስፖርት ስታር ዘግቧል፡፡

ዛሬ ወደ እንግሊዝ ልትበርር ተዘጋጅታ ከነበረችዋና የኮሮና ቫይረስ ተጠቂ በመሆኗ ወደ አውሮፕላኑ እንዳትገባ ታግዳ ከውድድሩ ውጭ ከተደረገችው የ2019 አምስተርዳም ማራቶን አሸናፊዋ አትሌት ደጊቱ በተጨማሪ የአትሌቷ አሰልጣኝ የሆኑት ሃጂ አዴሎም የቫይረሱ ተጠቂ በመሆናቸው ከጉዞው መታገዳቸውንም ዘገባው አመልክቷል፡፡

እሱ: SMS ልኬልሽ ነበርኮ? 🤔🤔እሷ: ሰርቨሬ ቴክስት በዝቶበት መቀበል አልቻለም😉😉
27/09/2020

እሱ: SMS ልኬልሽ ነበርኮ? 🤔🤔

እሷ: ሰርቨሬ ቴክስት በዝቶበት መቀበል አልቻለም😉😉

አሸናፊት!!!🏆🏆🏆
27/09/2020

አሸናፊት!!!🏆🏆🏆

26/09/2020
18/09/2020

"ልቤ ቆላ ወርዶ ይዞ መጣ ንዳድ
ተውት ያንገብግበው ይህ መከራ ወዳድ"
ጋሽ ባህሩ ቃኜ

‹‹ያገባኛል›› የሚል ሁሉ ሐሳብ የሚሰጥበት ጉዳይ...( አሳዬ ደርቤ)ጠላቶቻችን ጥቃታቸውን የሚያለማምዱብን መድረክ ፌስ-ቡክ ይባላል፡፡ የዚህ ሚዲያ ተጠቃሚ ስትሆን ደግሞ የመረጃ ፍሰቱን ተከ...
16/09/2020

‹‹ያገባኛል›› የሚል ሁሉ ሐሳብ የሚሰጥበት ጉዳይ...

( አሳዬ ደርቤ)

ጠላቶቻችን ጥቃታቸውን የሚያለማምዱብን መድረክ ፌስ-ቡክ ይባላል፡፡ የዚህ ሚዲያ ተጠቃሚ ስትሆን ደግሞ የመረጃ ፍሰቱን ተከትለህ መንጎድ እንጂ ወሳኝ ጥያቄ ይዘህ ‹‹ለዚህ ጥያቄዬ መልስ ካልተሰጠኝ በቀር አልንቀሳቀስም›› የምትልበት መድረክ አይደለም፡፡
ስለሆነም ትናንት አንዱ ቦታ ላይ ጥቃት እንዲደርስ ካደረጉ በኋላ በጥቃቱ የተሰማህን ስሜት የምትናዘዝበት አፍታ ይሰጡኻል፡፡ ከዚያ ሌላ አጀንዳ ይወረውሩና ያኛውን አጀንዳ ያስጡልኻል፡፡
➛‹‹ምዕራብ አርሲ የፈጸማችሁትን ጭፍጨፋ በስሙ ጥሩት›› እያልክ ስትጨቀጭቃቸው ሌላ ጮማ ዜና ያቀብሉህና ሥሙን ቀርቶ ጥቃቱን ያስረሱኻል፡፡
➛በአዲስ አበባ ላይ የፈጸሙት ዝርፊያ ይፋ ሆኖ ከባድ ተቃውሞ ሲያስነሳ ‹‹ ይሄን ተቃውሞ ያመጣው የእከሌ መታሰር ነውና መፈታት አለበት›› የሚል ፖስት ይለቀቅብኻል፡፡ የፓርክ ምረቃ እንዲታይ በማድረግ በልምላሜ ያፈዝኻል፡፡
ከዚያም የተለመደው ሕዝብ ላይ የተለመደው ጭፍጨፋ በዙር ይካሄድና ሙሾህን የምታወርድበት አንድ ሁለት ቀን ይሰጥኻል፡፡ በእነዚህ ቀናት ለቅሶህን የማትጨርስ ከሆነም ሐዘንህን የሚያስረሳ ዜና ወይም ደግሞ ሌላ ሐዘን ይግቱኻል፡፡
በብዙ ሰበር ዜናዎች መሃከል ግን በዙር የምትመጣ አንድ ቋሜ ዜና አለች፡፡ እርሷም ‹‹ይሄን ያህል አማራዎች ላይ ጥቃት ደረሰ›› የምትል ናት!
ስለሆነም የአሁን ዘመን ሰበር ዜናዎች ዋነኛ ዓላማቸው አንድም አማራ ላይ የተፈጸመን ጥቃት ማድበስበስ፣ ሁለትም የምናመነዥከው አጀንዳ ሰጥቶ ዝርፊያና ወረራ ማካሄድ ነው፡፡
ስለሆነም ብዙ ጥያቄዎች፣ ብዙ ለቅሶዎች፣ ብዙ ተቃውሞዎች ስናሰማ ከርመን መልስ በማግኘት ፈንታ ሌላ ተቃውሞ የሚያስነሳና ልብ የሚሰብር ዜና እየተሰጠን ሁለት ዓመታት አሳልፈናል፡፡
ከዚህ በኋላ ግን ዓመቱን ሙሉ ተመሳሳይ ጥያቄ ማቅረብ ባንችልም የሚከተሉትን ሁለት ነገሮች በማድረግ ይሄን የተለመደ ወንዛዊ የፌስቡክ ጉዞ መግታት አለብን፡፡
1️⃣….. ከለውጡ ወዲህ በየስፍራው የተፈጸሙብንን ግፎች በዝርዝር የያዘ ወጥ መረጃ ማዘጋጀት❗️
2️⃣…. የተጨፈጨፉ ወገኖቻችንን የምናስብበት፣ ለጠፉ እኅቶቻችንን ድምጻችንን የምናሰማበት፣ የተከማቹ ጥያቄዎቻችንን የምናቀርብበት፣ እንደ አጠቃላይ ከላይ ያደራጀነውን መረጃ የምንቀባበልበት ሁለት? የዘመቻ ቀናቶችን ከሳምንቱ ውስጥ መርጠን በቋሚነት መመደብ❗️
እኒህን ማድረግ ከቻልን ከአጀንዳ ተቀባይነት ባለፈ አጀንዳ ሰጭዎች እንሆናለን፡፡ የቀድሞውን በደል እየጣልን፣ አዲስ የሚወረወርልን እያንጠለጠልን በተዘረጋልን የመረጃ ፍሰት በመጓዝ ፈንታ የተፈጸመብንን ግፍ የምናወራርድበት ወቅትና የሚያስከብረን ድርጅት እስኪመጣ ድረስ የምናከማቸው እንጂ የምንረሳው በደል አለመኖሩን ለጠላቶቻችን ማሳየት እንችላለን፡፡
እኛም ብንሆን በየጊዜው ያንጠባጠብናቸውን የጥቃት ቅርንጫፎች ዛፍ ሆነው ስናያቸው ‹‹እውነት ይህ ሁሉ ግፍ የተፈጸመው በእኛ ላይ ነው?›› ብለን እንዲናስብና በመወዛወዝ ፈንታ አቋም እንዲንይዝ ያደርገናል፡፡
የትግል መጀመሪያው የተፈጸመን ግፍ ጠንቅቆ መረዳት ነውና!
የነጻነት መነሻው የባርነትን ልክ ማወቅ ነውና…
ስለሆነም ይህ ጉዳይ ይመለከተኛል የምትሉ ሁሉ ሕዝባችን ላይ በየስፍራው ከተፈጸሙ ግፎች መሃከል የምታስታውሱትን ኮሜንት ላይ በመጻፍና ይሄን ጽሑፍ ሼር አድርጋችሁ ለሌሎች በማስተላለፍ ኃላፊነታችሁን ትወጡ ዘንድ ትጠየቃላችሁ፡፡

ደራሲ መዓዛ መንግስቴ በታላቁ የቡከርስ ሽልማት ለፍጻሜ ደረሰችትውልደ ኢትዮጵያዊቷ ደራሲ መዓዛ መንግስቴ ቡከርስ ፕራይዝ ለተሰኘው ታላቁ የእንግሊዝ የስነጽሁፍ ሽልማት ለፍጻሜ ከደረሱ 6 ደራሲ...
15/09/2020

ደራሲ መዓዛ መንግስቴ በታላቁ የቡከርስ ሽልማት ለፍጻሜ ደረሰች

ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ ደራሲ መዓዛ መንግስቴ ቡከርስ ፕራይዝ ለተሰኘው ታላቁ የእንግሊዝ የስነጽሁፍ ሽልማት ለፍጻሜ ከደረሱ 6 ደራሲያን አንዷ ለመሆን መቻሏን የሽልማት ድርጅቱ ዛሬ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል፡፡
‘The Shadow King’ በተሰኘው የረጅም ልቦለድ መጽሐፏ ለዘንድሮው ሽልማት በዕጩነት የቀረበችው ደራሲ መዓዛ መንግስቴ፣ አምስቱን ተፎካካሪዎቿን ማሸነፍ ከቻለች የ50 ሺህ ዶላር ሽልማት እንደምታገኝም ዘ ቡከርስ ፕራይዝ ፋውንዴሽን ያወጣው መረጃ ያሳያል፡፡

ላለፉት 50 ያህል አመታት በብሪታንያና በአየርላንድ በእንግሊዘኛ ቋንቋ የታተሙ የልብ ወለድ መፅሐፍትን በማወዳደር ሲሸልም የቆየው ተቋሙ፣ 162 መጽሐፍት በዕጩነት የቀረቡበት የዘንድሮው ቡከርስ ሽልማት አሸናፊ ጥቅምት 17 ቀን 2013 ዓ.ም ይፋ እንደሚደረግም አስታውቋል፡፡

በአዲስ አበባ የተወለደችውና በ1966 ቱ አብዮት ማግሥት ከወላጆችዋ ጋር ወደ ሃገረ አሜሪካ ያቀናችው ደራሲ መዓዛ፣ ከኒዮርክ ሲቲ ዩኒቨርስቲ በሥነ-ጽሑፍ እና የልቦለድ አፃፃፍ የተመረቀች ሲሆን በዩኒቨርሲቲው የሥነ-ጽሑፍ መምህርት ሆና በማገልገል ላይ ትገኛለች፡፡

ቢኔዝ ዘ ላየንስ ገጌዝ የተሰኘው የመጀመሪያ ስራዋ በገርዲያን ምርጥ አፍሪካውያን መጽሐፍት ዝርዝር ውስጥ የተካተተላት ደራሲ መዓዛ፣ የአሜሪካው የሥነ-ጥበብ አካዳሚ የ 2020 ለየት ያለ ስኬት ተሸላሚ ለመሆን የበቃች ዝነኛ ደራሲ ናት፡፡

መባቻ - Anteneh Yigzaw 2

እነ አበጋዙ ከ36 አመታት በፊት…የአድማስ ባንድ አባላት - ከግራ ወደ ቀኝ… ዮሴፍ ተስፋዬ (ድራም)፣ ቴዎድሮስ አክሊሉ (ኪቦርድ)፣ ሄኖክ ተመስገን (ቤዝ ጊታር) እና አበጋዙ ክብረ ወርቅ ሺ...
08/09/2020

እነ አበጋዙ ከ36 አመታት በፊት…

የአድማስ ባንድ አባላት - ከግራ ወደ ቀኝ… ዮሴፍ ተስፋዬ (ድራም)፣ ቴዎድሮስ አክሊሉ (ኪቦርድ)፣ ሄኖክ ተመስገን (ቤዝ ጊታር) እና አበጋዙ ክብረ ወርቅ ሺዎታ፡፡

አድማስ ባንድ እ.ኤ.አ በ1984 ዋሽንግተን ውስጥ ያሳተመው “የኢትዮጵያ ልጆች” የተሰኘ የሙዚቃ አልበም በወቅቱ በእጅጉ ተደማጭ እንደነበረና 7 ሙዚቃዎችን እንዳካተተ የፈረንሳይ አለማቀፍ ሬዲዮ ዛሬ ባወጣው ዘገባ አስታውሷል፡፡

የይቅርታ እርዝመት...ማሪያምን የኔ አለም!...በሰው ልጆች አቅም፣ ከሚሰራው ሁሉ በዚህች ጉደኛ አለምከበደሎች መሃል፣ አንተ በድለኸኝ የማልችለው የለም!...ምንም ይሁን ምንም አንተ ስትፈጽመ...
06/09/2020

የይቅርታ እርዝመት...
ማሪያምን የኔ አለም!...
በሰው ልጆች አቅም፣ ከሚሰራው ሁሉ በዚህች ጉደኛ አለም
ከበደሎች መሃል፣ አንተ በድለኸኝ የማልችለው የለም!...

ምንም ይሁን ምንም አንተ ስትፈጽመው
የለም አንዳች በደል፣ ጀርባዬን አጽንቼ የማልሸከመው!...
ይሄው ልማልልህ!...
አንዳች በደል የለም፣ ፍቅሬ በድለኸኝ ይቅር የማልልህ!...

ምን ይበጀኝና፣ አስቀየምከኝ ብዬ ልደግስልህ ጠብ?
ይሄው ነው መላዬ፣ ቆሽሸህ ስትመጣ ተቀብዬ ማጠብ
ካኮረፍኩህማ፣ ስተስሰርቀኝ አይቼ ደሞ እንደልማድህ
የታል የማፈቅርህ የታል የምወድህ?...

ቃል እምነት ማጠፉ፣ አንተን ካልደከመህ
አታስብ ስለኔ... ይቅር እልሃለሁ በድለኝ ደጋግመህ!...

ኩርፊያ ምን ሊረባኝ፣ ምን ሊፈይድልኝ ምን መላ ሊፈጥር
ተበደልኩኝ ብዬ፣ ፊቴን ላጥቁርብህ ባንተ ቂም ልቋጥር
ይልቅ እንዳመሌ፣ ይቅር ስልህ ልኑር በበደልከኝ ቁጥር!...

በደለኝ ሰረቀኝ፣ ብዬ ለጎረቤት ለምን አወራለሁ
የሰማ ሲነግርህ፣ አኩርፈህ ብትቀር ምን እጠቀማለሁ!?...

ስትሰርቀኝ ስይዝህ፣ አፍረህ በዚያው ቀርተህ እኔኑ ከሚያመኝ
እንዳላየ ማለፍ፣ በይቅርታ መተው ምንጊዜም አይደክመኝ!

በኔላይ ግፍ መስራት፣ ዘለለት መበደል አንተን ካልደከመህ
ዕድሜ ዘላለሜን ይቅር ስልህ ልኑር አስከፋኝ ደጋግመህ!...

እንኳንስ ላለፈው፣ ንቄ ለረሳሁት ለማይመለሰው
ይቅር ላልኩህ በደል፣ ሲስቅብኝ አገር ሲሳለቅብኝ ሰው
ለሚመጣው በደል፣ ገና ከእጆችህ ላይ ነገ ለምቀምሰው
ቀድሜ የያዝኩት፣ ብዙ ይቅርታ አለኝ ላንተ እምለግሰው!

አንተም እስኪበቃህ፣ እኔኑ መበደል እኔም በቃ እስኪለኝ
እንዳታስብ ፍቅሬ፣ ገና ያልሰጠሁህ ብዙ ይቅርታ አለኝ
አንተም ታውቀኛለህ፣ በደልክን ለመርሳት ወትሮስ መች ለግሜ
ባስቀየምከኝ ቁጥር፣ ይቅር እልሃለሁ ገና ደጋግሜ!...

(ተጻፈ 2008 ዓ.ም)

ቢኒ በጎ ሰው - እንኳን ደስ ያለህ!!!የማይታየው ሰው…( Anteneh Yigzaw ድጋሜ የተለጠፈ)በህይወቴ ካጋጠሙኝ እጅግ ታታሪ ሰዎች አንዱ ነው፡፡ነፍሱ ከሁለት ነገሮች ጋር በጥብቅ የተቆራ...
06/09/2020

ቢኒ በጎ ሰው - እንኳን ደስ ያለህ!!!

የማይታየው ሰው…

( Anteneh Yigzaw ድጋሜ የተለጠፈ)

በህይወቴ ካጋጠሙኝ እጅግ ታታሪ ሰዎች አንዱ ነው፡፡

ነፍሱ ከሁለት ነገሮች ጋር በጥብቅ የተቆራኘች ባተሌ ሰው ነው - ከኪነ-ጥበብ እና ከልጆች፡፡

ለአገርና ለወገን የሚበጁ ብዙ በጎ ነገሮችን ሌት ተቀን ተግቶ ይሰራል ይሰራል እንጂ፣ ስለመስራቱ በአደባባይ ሲደሰኩር አይታይም፡፡

“የኢትዮጵያ ልጆች” የተሰኘውንና ሙሉ ትኩረቱን በህጻናት ላይ አድርጎ ደረጃውን በጠበቀ መልኩ የሚሰራውን በአገራችን የመጀመሪያው የልጆች የቴሌቪዥን ጣቢያ ከአመታት እልህ አስጨራሽ ትግል በኋላ እውን ያደረገ የትውልድ ባለውለታ ነው፡፡

በአዲስ አበባ ኢግዚቢሽን ማዕከል ለአራት ተከታታይ ክረምቶች የተካሄደውን “ንባብ ለሕይወት የመጻሕፍትና የምርምር ተቋማት አውደ ርዕይ” ያዘጋጀው እሱ ነው፡፡

ብዙ ብዙ ለአገር ለወገን የሚበጁ መልካም ነገሮችን ቢሰራም፣ ስራዎቹ እንጂ እሱ በአደባባይ አይታይም፤ ተግባሩ እንጂ ስሙ አይታወቅም፡፡

የሚገባውን ምስጋና ለማቅረብ የከተብኳትን ይህቺን አጭር ጽሁፍ በምስል ለማስደገፍ ሳስብ እንኳን፣ የብዙ ስራዎቹን እንጂ አንድም የእሱን ፎቶ ግራፍ በርብሬ ላገኝ አልቻልኩም!

ቢኒያም ከበደ!

ላመሰግንህ ወደድኩ!

Join our Telegram Channel - https://t.me/mebachaantenehyigzaw

ወይ አዲስ አበባ!...ወርሃዊ መጽሔት የመጀመሪያ ዕትም ቅዳሜ ነሐሴ 30፤ 2012 ዓ.ም ለንባብ ትበቃለች። " በእውነት ለእውቀት እንሰራለን! " የምትወዷቸው፣ የምታከብሯቸው፣ የምታደንቋቸው፣...
03/09/2020

ወይ አዲስ አበባ!...

ወርሃዊ መጽሔት የመጀመሪያ ዕትም ቅዳሜ ነሐሴ 30፤ 2012 ዓ.ም ለንባብ ትበቃለች። " በእውነት ለእውቀት እንሰራለን! " የምትወዷቸው፣ የምታከብሯቸው፣ የምታደንቋቸው፣ ሚዛናዊዎቹ ከወይ አዲስ አበባ ጋር ናቸው። በልዩነት፣ በተሻለ አማራጭ፣ ቁጥር ከመጨመር በላይ እሴትን ለመጨመር ታስቦባት፣ በበቂ ጥናት ላይ ተመስርታ የመጣችውን "ወይ አዲስ አበባ መጽሔት"፤ ቅዳሜ አበባ ይዛችሁ፣ ማኪያቶ ፉት እያላችሁ ተቀበሏት!!!!!!

ልጅ ሚክሎል አንተነህ!...
03/09/2020

ልጅ ሚክሎል አንተነህ!...

አውግቼው ተረፈ እና “የዚህ አገር ድልድየይ”…የሆነ ጊዜ ነው አሉ...አንጋፋው ደራሲና ተርጓሚ አውግቼው ተረፈ (ነፍሱን ይማረውና) ከአንድ ወዳጁ ጋር ወደ አንድ የገጠር መንደር ያቀናል፡፡እነ...
28/08/2020

አውግቼው ተረፈ እና “የዚህ አገር ድልድየይ”…

የሆነ ጊዜ ነው አሉ...

አንጋፋው ደራሲና ተርጓሚ አውግቼው ተረፈ (ነፍሱን ይማረውና) ከአንድ ወዳጁ ጋር ወደ አንድ የገጠር መንደር ያቀናል፡፡

እነአውግቼው ወደ መንደሯ በመቃረብ ላይ ሳሉ፣ በመካከል አንዲት ጅረት ታጋጥማቸዋለች፡፡ ጅረቷን ለመሻገር የሚችሉበት ድልድይ ዙሪያውን ቢፈልጉ ያጣሉ፡፡

ደግነቱ ጅረቷ እምብዛም ፈታኝ አልነበረችምና፤ በዝላይ ተሻገሯት፡፡ ጉዟቸውን ሊቀጥሉ ሲሉ ግን... የአውግቼው አይኖች አንድ ነገር ላይ አረፉ - አለፍ ብሎ ከእንጨት ርብራብ የተሰራ ድልድይ መሬት ላይ ወድቋል፡፡

አውግቼው ድልድዩን በግርምት እያየ፣ ወደ ወዳጁ ዞር ብሎ እንዲህ አለው አሉ...

“ይገርማል!... እዚህ አገር... ድልድዩን የምታገኘው፣ ወንዙን ከተሻገርክ በኋላ ነው!...”

ሰውዬው!!!....
07/08/2020

ሰውዬው!!!....

“ውሃ እሚያጠፋ እሳት” እየመጣ ነው…ከአመታት በፊት ለህትመት ባበቃው “የአመድ ልጅ እሳት” የተሰኘ የመጀመሪያ የግጥሞች ስብስብ መጽሐፉ የሚታወቀው ገጣሚ እምሻው ገብረ ዮሃንስ፣ እነሆ አሁን ...
05/08/2020

“ውሃ እሚያጠፋ እሳት” እየመጣ ነው…

ከአመታት በፊት ለህትመት ባበቃው “የአመድ ልጅ እሳት” የተሰኘ የመጀመሪያ የግጥሞች ስብስብ መጽሐፉ የሚታወቀው ገጣሚ እምሻው ገብረ ዮሃንስ፣ እነሆ አሁን ደግሞ “ውሃ እሚያጠፋ እሳት” በሚል ርዕስ ሁለተኛ ስራውን ይዞ መጥቷል፡፡

በሌንስ ማተሚያ ቤት አሳታሚነት በቀጣዩ ሳምንት ለገበያ የሚውለው “ውሃ እሚያጠፋ እሳት” የግጥሞች ስብስብ መጽሐፍ፣ በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ የሚያጠነጥኑ 60 ያህል ግጥሞችን ያካተተ ሲሆን፣ በ50 ብር የመሸጫ ዋጋ በአዲስ አበባ እና በክልል ከተሞች በመጽሐፍት መደብሮችና አዟሪዎች ለገበያ እንደሚቀርብ ተነግሯል፡፡

ከመጽሐፉ ሽያጭ ከሚገኘው ገቢ ከፊሉ ጣና ሃይቅን ከእንቦጭ አረም ለማዳን የተጀመሩ ጥረቶችን ለማገዝ እንደሚውል የገለጸው ገጣሚ እምሻው ገብረ ዮሃንስ፣ በቀጣይ “በረከትን ፍለጋ” የሚል ርዕስ ያለው የአጫጭር ልቦለዶች፣ ወጎችና ግጥሞች ስብስብ መጽሐፉን ለአንባብያን ለማብቃት ዝግጅት እያደረገ እንደሚገኝም ተናግሯል፡፡

መንግስት ከጉዳይ ያልጣፈውን የጣና ጉዳይ ጉዳዬ በማለቱና ስንኝ ሽጦ ከሚያገኘው ሳንቲም ለጣና ለመለገስ በመፍቀዱ ገጣሚውን እያመሰገንን፣ ከዚህ ቀደም ለንባብ ካበቃው “የአመድ ልጅ እሳት” የተሰኘ መጽሐፉ የቆነጠርናቸውን ሶስት ግጥሞቹን እነሆ ለቅምሻ እንበላችሁ!...

ከዛፍ ስትጣላ...

የተነሳብህ ለት
የዛፍ ባላንጋራ
ከምትተናነቅ
ከመቶ ቅርንጫፍ
ከሺህ ቅጠል ጋራ
እንደ ጡንቻ ሁሉ
ስልት በማፈርጠም
ወርደህ ከግንዱ ጋር
አንድ ለአንድ ግጠም!... . .

ሠም እና ሠም

አበባው አብቦ ንቡ ገብቶልህ
እንግዲህ ጉብሌ ማር ካላበላህ...
“እንኳንስ ማርና...
አላየሁም ሠፈፍ...”
እያልህ በመራራ፣ ዜማ ከመንሠፍሠፍ...
ያ!... የቀፎው አውራ፣ ማሩን የደበቀው
ንብ ሆኖ ሲመጣ...
ጭስ ሆነህ ጠብቀው! . .

ውሃ መሳይ

ለአጥቂ ባይገለጽ መስሎ ተራ ጥበብ
ከአይን ዳር መንጭቶ
ጉንጮችን በማጠብ
እየገነፈለ ቁልቁል ሲንጠባጠብ፣
ተጠቂ ቢመስል ከንቱ የማይረባ...
በደረት አቋርጦ
ከመሬት ሲገባ...
ብረትን አብቅሎ ጦር ይስላል እምባ!...

ሃይሌ ይናገራል!...“የውጭ ሃይሎች በሠሩት ሴራ ድርጅቶቼ ላይ ጥቃት ተፈፀመ ብዬ ከነበረኝ አቋም ወደ ኋላ አልመለስም፤ ኢትዮጵያ የመጀመሪያም የመጨረሻም አማራጬ ስለሆነች ከሀገሬ ውጭ ሄጄ ማ...
23/07/2020

ሃይሌ ይናገራል!...

“የውጭ ሃይሎች በሠሩት ሴራ ድርጅቶቼ ላይ ጥቃት ተፈፀመ ብዬ ከነበረኝ አቋም ወደ ኋላ አልመለስም፤ ኢትዮጵያ የመጀመሪያም የመጨረሻም አማራጬ ስለሆነች ከሀገሬ ውጭ ሄጄ ማልማትም ሀብት ማፍራትም አልመኝም፤ የምሠራው ለራሴ ቢሆንም ህልሜ ሀገሬን ማሳደግ፤ ለሌሎችም የሥራ ዕድል መፍጠር ነው” - አትሌት ሻለቃ ኃይሌ ገብረሥላሴ

• በሰሞኑ ክስተት ከኔ በላይ አርባ ሃምሳ ዓመት ሠርተው ያፈሩት ንብረት የወደመባቸው ሰዎች እንኳን ቢሆኑ እንዲህ አይነት ጉዳት ደርሶብናል ብለው ወደ ኋላ ይላሉ ብዬ አልገምትም። ምክንያቱም በሀገራቸው ካልሠሩ የት ሊሠሩ ይችላሉ። ግን ደግሞ መንግሥት የተሰበሩ ቅስሞችን መጠገን ይገባዋል ብዬ አስባለሁ።

• የሻሸመኔም ይሁን የዝዋይ ህዝብ የእኛን ድርጅት የሚመካበት ነው። በእርግጠኝነት የሆቴሉን ጥቅምና ለከተማው ያለውን አስተዋጽኦ የተረዱ ነዋሪዎች በዚህ ጥቃት ላይ ይሰማራሉ የሚል እምነት የለኝም።

• እኔ ከሀገሬና ከህዝቤ ጋር ከመኖር ውጭ ያሉ ሌሎች አማራጮችን የምመለከት ሰው አይደለሁም። ሀብት ያፈራሁት በሩጫው ዘርፍ ሀገሬን ወክዬ ባስመዘገብኩት ጥሩ ውጤትና በተሰጠኝ ሽልማት ነው።

• ሀገሬና ህዝቤ ለእኔ እዚህ መድረስ ባለውለታዎቼ ናቸው፤ ኢንቨስት ባደረግኩ ቁጥር ለሀገሬ ዕድገት አስተዋጽኦ እያበረከትኩ እንዳለሁ ይሰማኛል። ለበርካታ ሰዎች የሥራ ዕድል የፈጠርኩ ይመስለኛል። በከተሞች ዕድገትና ዘመናዊነት ላይ አስተዋጽኦ አበረክታለሁ።

• የውጭ ሃይሎች በሠሩት ሴራ ድርጅቶቼ ላይ ጥቃት ተፈፀመ ብዬ ከነበረኝ አቋም ወደ ኋላ አልመለስም። ኢትዮጵያ የመጀመሪያም የመጨረሻም አማራጬ ስለሆነች ከሀገሬ ውጭ ሄጄ ማልማትም ሀብት ማፍራትም አልመኝም። የምሠራው ለራሴ ቢሆንም ህልሜ ሀገሬን ማሳደግ፤ ለሌሎችም የሥራ ዕድል መፍጠር ነው።

• ውድመት የደረሰባቸው ድርጅቶች በእኔ ስም ያሉ ቢሆንም የሥራ ዕድልን በመፍጠር፣ ለከተሞች ዕድገትና ውበት በመስጠት፣ ለመንግሥት ገቢ የሚያስገኙ በመሆናቸው ጉዳቱ የእኔ ብቻ ሳይሆን የሁላችንም ነው። ይህ አገራዊ እንጂ ግላዊ ጉዳት አይደለም።

• እንዲህ አይነቱ ተግባር በወቅቱ ከሚያወድመው ኢኮኖሚ በተጨማሪ የሀገርን ገጽታ በማበላሸት በመጪው ኢኮኖሚላይም ተጽዕኖ የሚያደርስ ነው።

• ኢንቨስትመንትም ሰላምና መረጋጋት ይፈልጋል። ማንም ሰው ቢሆን መዋዕለ ነዋዩን የሚያፈሰው የነገ ጥቅሙን አስቦ ነው። በነገ ውስጥ ሰላምና መረጋጋት ሲኖሩ ነው ሰው የዘራውን ማጨድ የሚቻለው። ዋስትና በሌለበት ሁኔታ ማንም ተነስቶ መዋዕለ ነዋዩን ያፈሳል ተብሎ አይታሰብም።

• ትልቁ ችግር ነገ እንደዚህ አይነት ውድመት ላለመፈፀሙ ምን ዋስትና አለ የሚለው ነው። ስለዚህ ኢንቨስት ማድረግ በሚፈልጉ የውጭም ይሁን የሀገር ውስጥ ባለ ሀብቶች ላይ ተጽዕኖ መፍጠሩ አያጠራጥርም።

• እንደሰው ስታስብ በተደጋጋሚ እንዲህ አይነት ጥቃት ሲደርስብህ ተስፋ ልትቆርጥ ትችላለህ። በተለይ ደግሞ በራስህ ወገን እንዲህ ዓይነት ጥቃት ሲፈፀምብህ ጉዳዩ የበለጠ ያስከፋል። ግን ደግሞ ኢትዮጵያ ሀገሬ ነች።

• ብዙዎች ንብረት ሳይሆን ህይወት ከፍለው እዚህ አድርሰዋታል፤ እኛም ዋጋ እየከፈልን እናስቀጥላታለን እንጂ ተስፋ አንቆርጥም።

• በእንዲህ አይነት ሁኔታ ውስጥ ሆነን ሥራችንን እንቀጥላለን ስንል ሰዎች እንደ እብድ ሊቆጥሩን ይችላሉ። ድርጅቶቻችን በተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች የሚገኙ በመሆናቸው ጥቃት ከደረሰባቸው ውጭ ያሉት በሙሉ አሁንም በሥራ ላይ ናቸው።

• ለእኔ ዋናው ችግር ትውልዱ ሀገርን ለመገንባት በሚያስችል የትምህርት ሥርዓት ውስጥ አለማለፉ ነው። ዕድገቷን የማይፈልጉና ጥቅማቸውን ማስከበር የሚፈልጉ የውጭ ሃይሎች ደግሞ ይህንን አጋጣሚ እየተጠቀሙበት ነው።

• ህዝብ መንቃት አለበት እላለሁ፤ ህዝብ እስኪ ነቃ ድረስ ግን መንግሥት የድርሻውን መወጣት ይኖርበታል። ቤተሰብ ልጆቹን ቆንጥጦ እንደሚያሳድግ ሁሉ መንግሥትም የሚያስተዳድረውን አካል አስቀድሞ ቆንጠጥ ቢያደርግ እንዲህ አይነቱን ጥፋት ማስቀረት ይቻላል።

• ችግሮችን የሚያባብሱ ሚዲያዎችን ትክክለኛውን መስመር ማስያዝ ከመንግሥት ይጠበቃል። በተለይ ሶሻል ሚዲያው ላይ የሚታየው ልቅነት እንዲህ አይነት ችግሮችን በማባባስ የሚኖረው ሚና ቀላል ባለመሆኑ መታረም ይኖርበታል።

• መንግሥት ሕግን ማስከበር፤ ሕብረተሰቡም ከመንግሥት ጎን መቆም ይኖርበታል። አስተማማኝ ሰላምን በመፍጠር ዜጎች ያለስጋት የሚኖሩባትን ኢትዮጵያ ማረጋገጥ ይኖርበታል። ይህ ሲሆን ነው ባለሀብቱ መዋዕለ ነዋዩን በማፍሰስ በኢትዮጵያ ዕድገት ላይ የድርሻውን መወጣት የሚችለው።

• ከዚህ በፊትም በደቡብ ክልል በተፈጠረ ግርግር እራሳቸው የመንግሥት ተማኞች በተመኑት መሠረት ወደ 28 ሚሊዮን ብር የሚገመት ጉዳት እንደደረሰብኝ አረጋግጠዋል። መንግሥት ለደረሰው ጉዳት ካሳ እንደሚከፍል ቢናገርም እስከ አሁን ተፈፃሚ አልሆነም።

• ይህ እያለ ደግሞ አሁን በሆቴሎቹ ላይ በደረሰው ውድመት ወደ 290 ሚሊዮን ብር ኪሳራ ደርሶብኛል። ሁለቱም ሆቴሎች ባለ ሦስት ኮከብ ደረጃ ያላቸውና የተሟላ ዕቃ ያላቸው ነበሩ።

• ወጪው የሚያጠራጥር ከሆነ አንድ ባለ ሦስት ኮኮብ ሆቴል በምን ያህል ብር መጠናቀቅ ይችላል በሚለው ማወቅ ይቻላል። ከህንፃው በላይ ሆቴሎቹ በየክፍሎቹ የያዟቸው ቁሶች ከሚሊየን ብር በላይ የሚያወጡ ናቸው።

• በአጠቃላይ በተለያዩ ድርጅቶቼ ውስጥ ተቀጥረው የሚሠሩ ሠራተኞች ብዛት ወደ ሦስት ሺህ የሚጠጋ ነው። አሁን በሁለቱ ሆቴሎች ይሠሩ የነበሩ ወደ አራት መቶ ሠራተኞች ከሥራ ውጭ የሆኑበት ሁኔታ ተፈጥሯል። እነዚህን ሠራተኞች ወደሌሎች ቦታዎች ወስደን ተደርበው እንዲሠሩ ለማድረግ አስበን ነበር፤ ግን በኮቪድ 19 ምክንያት ሌሎቹም ቢሆኑ በሚፈለገው ደረጃ እየሠሩ አይደሉም።

• ኢትዮጵያን የገጠማት ውስጣዊ ችግር ነው ብዬ አላምንም። ውጫዊ ችግሮች ተባብሰው በመምጣታቸው ነው ውስጣዊ ችግሮች የተወለዱት። በተለይ ከታላቁ ኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ጋር በተያያዘ ኢትዮጵያ ላይ እያንዣበበ ያለው አደጋ ዛሬ በዚህ ደረጃ የተገለፀ ቢሆንም ለበርካታ ዓመታት የኖረ መሆኑን የሚያስረዱ ታሪኮች አሉ።

• አሁን ግብጾች በህዳሴው ግድብ ላይ ያለንን ተጠቃሚነት በጦርነት መቀልበስ እንደማይችሉ ሲረዱ እርስ በእርሳችን በማጋጨት ሀገሪቱን ማተራመስ መፈለጋቸውን የሚያሳዩ ሁኔታዎች እየተከሰቱ ነው።

• በእኔ ዕይታ በአርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳ ሞት ሀዘናቸውን ለመግለጽ የወጡ ሰዎች የግብጽን አጀዳ ለማስፈፀም ተልዕኮ ባላቸው አካላት ተጠልፈው እንዲህ አይነቱ ውድመት ሊደርስ ቻለ ነው የምለው።

• ለብዙ ዓመታ የተገነቡ ከተሞች በግማሽ ቀን ዶግ አመድ ለመሆን የበቁት በኢትዮጵያ ውስጥ ባለው የፖለቲካ ልዩነት ሳይሆን በውጭ ሃይሎች ጣልቃ ገብነት ነው። አሁን መጠንቀቅ ያለብን በቀጣይ ምን ታስቦ ይሆን በሚለው ላይ ነው።

• የኢትዮጵያ ፖለቲከኞችና አክቲቪስቶች ዓላማቸው ህዝቡን ነፃ ማውጣት ከሆነ መጀመሪያ ህዝቡን ከድህትና ከኢኮኖሚ ችግሩ ነፃ አውጡት ብዬ መምከር እፈልጋለሁ።
• ወጣትነት ሁሉ ነገር ነው። ይህን ወርቃማ ጊዜ ለመልካም ነገር እንዲያውሉት እመክራለሁ። አቅማቸውን ተጠቅመው ጥሪት እንዲቋጥሩ፤ በስሜት ከመነዳት ይልቅ ቆም ብለው ነገሮችን እንዲያስተውሉ እምክራቸዋለው።

• ሀጫሉ እዚህ ቦታ ላይ ለመድረስ ብዙ መስዋዕትነት ከፍሏል። ታስሯል ተገርፏል፤ ያም ሆኖ ወደ የትም ሳይሸሽ ትግሉን አጠናክሯል። መጨረሻም ለሞት ተዳርጓል። ስለዚህ ሀጫሉ ሰማዕት ሆኗል ነው የምለው።

/ምንጭ አዲስ ዘመን ሐምሌ 16 ቀን 2012 ዓ.ም/

ሰውዬው…በ14ኛው ስራው መጥቷል!
23/07/2020

ሰውዬው…
በ14ኛው ስራው መጥቷል!

"እኛ የዘመኑ ልጆች…'ውሃ ቀጠነ ብሎ ሲቃ ሲያንቀው፣ ንፋስ አፍኖ ገደለው' ፣ ነው ወጋችን…": ሎሬት ፀጋዬ ገ/ መድህን -የከርሞ ሰው
29/06/2020

"እኛ የዘመኑ ልጆች…

'ውሃ ቀጠነ ብሎ ሲቃ ሲያንቀው፣ ንፋስ አፍኖ ገደለው' ፣ ነው ወጋችን…"
:
ሎሬት ፀጋዬ ገ/ መድህን -የከርሞ ሰው

የቃላት ጨዋታ...ቴዲ አፍሮ ነገ ይለቀቃል በተባለው ነጠላ ዜማው ውስጥ ሊያካተታቸው የሚችሉ ቃላትን ይገምቱ እስኪ?እኔ - አባይ  😉😉😉 እና ደግሞ... ሳንጃው!!!!
29/06/2020

የቃላት ጨዋታ...

ቴዲ አፍሮ ነገ ይለቀቃል በተባለው ነጠላ ዜማው ውስጥ ሊያካተታቸው የሚችሉ ቃላትን ይገምቱ እስኪ?
እኔ - አባይ 😉😉😉 እና ደግሞ...

ሳንጃው!!!!

አቶ ክበበው እና ገራሚዎቹ የልጆቻቸው ስሞች(ኤሌክትሮን፣ ፕሮቶን፣ ኒውትሮን፣ ዲዩትሮን፣ ፖሲትሮን…)Anteneh Yigzawእ.ኤ.አ በ2015...በወርሃ መጋቢት አጋማሽ ላይ፣ ኢትዮጵያን ከስም...
29/06/2020

አቶ ክበበው እና ገራሚዎቹ የልጆቻቸው ስሞች

(ኤሌክትሮን፣ ፕሮቶን፣ ኒውትሮን፣ ዲዩትሮን፣ ፖሲትሮን…)

Anteneh Yigzaw

እ.ኤ.አ በ2015...

በወርሃ መጋቢት አጋማሽ ላይ፣ ኢትዮጵያን ከስም ጋር ያቆራኘ ዜና ከወደ አሜሪካ በተለያዩ ድረገጾች ተሰራጨ፡፡

ለየት ያለ ስም ያላቸውን ግለሰቦች እየመረጠ በየአመቱ ደረጃ የሚሰጠው አንድ ታዋቂ የአሜሪካ ድረገጽ፣ በዚያው ሰሞንም ለ33ኛ ጊዜ በዕጩነት ያቀረባቸውን ስሞች ይፋ በማድረግ፣ ህዝቡ ለመረጠው ልዩ ስም ድምጽ እንዲሰጥ ጋበዘ፡፡

ከፍተኛውን ድምጽ ያገኘው ታዲያ፣ ኢትዮጵያዊው አባት አቶ ክበበው ለልጃቸው ያወጡት ስም ሆነ...

ኤሌክትሮን ክበበው!...

ነገሩ እንዲህ ነው...

ኢትዮጵያዊው አባት አቶ ክበበው፣ በሙያቸው የኤሌክትሪካል ኢንጂነር ናቸው፡፡

ልጆቻቸው የእሳቸውን ፈለግ ተከትለው እንዲያድጉና በሳይንሱ ዘርፍ ልቀው እንዲወጡላቸው አጥብቀው ይሻሉ፡፡
ይህን መሻታቸውን እውን ለማድረግ ግን፣ ተግተው በልጆቻቸው ላይ መስራት እንዳለባቸው አላጡትም፡፡ በብላቴና ልጆቻቸው ልቦና፣ “ሳይንስ” የሚል ትልቅ ሃሳብ መትከል እንዳለባቸው ያውቃሉ፡፡

ለልጆቻቸው ደጋግመው ስለ ሳይንሱ መስክ ታላቅነት መተረክ፣ ወደ ሳይንሱ መስክ የሚያመሩበትን መንገድ ማመላከት፣ በሳይንሱ ገፍተው እንዲጓዙ ለሚያስችሏቸው የትምህርት አይነቶች ትኩረት እንዲሰጡ መደገፍ... እንዲህ እና እንዲያ ያለውን ጥረት ሁሉ ማድረግ እንዳለባቸው ያውቃሉ - አባትዬው!

ይሄም ሆኖ...

አቶ ክበበው እንዲህ እና እንዲያ ያለውን የኩትኮታ ስራ ለመጀመር፣ የወለዱት ልጅ ነፍስ እስኪያውቅና ፊደል መቁጠር እስኪጀምር መጠበቅ ይኖርባቸዋል፡፡

እሳቸው ግን፣ የወለዱት ልጅ ነፍስ እስኪያውቅና ፊደል እስኪቆጥር ስራ አይፈቱም...

ገና እንደተወለደ፣ ወሳኝ ያሉትን ሌላ ስራ ይሰሩበታል...
በዘመን በማይላላ፣ በእርጅና በማይበጠስ፣ በጠንካራ የዕድሜ ልክ ክር “ጨቅላውን” ከ“ሳይንስ” ጋር ያስተሳስሩታል...
ወደ ነገው ይመሩታል...

“ስም” ይባላል - ይህ ጠንካራ ክር!...

ኤሌክትሮን ክበበው
ፕሮቶን ክበበው
ኒውትሮን ክበበው
ዲዩትሮን ክበበው
እና
ፖሲትሮን ክበበው
እነዚህ አምስቱ የአቶ ክበበው ልጆች ናቸው፡፡

አቶ ክበበው ለአምስቱ ልጆቻቸው ያወጧቸው ስሞች፣ ግርምትን የሚያጭሩ ቢሆኑም...

ልጆቻቸው ዛሬ የደረሱበት ደረጃ፣ አባትዬው ለስም የሚሰጡትን ዋጋና ልጆቻቸውን በስማቸው በኩል ወደ ሳይንስ ለመጥራት ያደረጉትን ገራሚ ጥረት ልክነት አስመሰከረ...

ይህም ብቻ አይደለም...

ወላጅ ለልጁ የሚሰጠው ስም በልጁ ቀጣይ ዝንባሌ፣ አመለካከትና የህይወት ምርጫ ላይ የራሱን የሆነ ተጽዕኖ ይፈጥራል ብለው ለሚሟገቱ የስነ ልቦና ምሁራንም ምሳሌ ሊሆን የሚችል ነው - የአቶ ክበበው ልጆች አጋጣሚ፡፡

ከኤሌክትሮን ክበበው እንጀምር...

አድጎ ሳይንስን እንዲያጠናላቸው በማሰብ ጨቅላ ሳለ ኤሌክትሮን የሚል ስም ያወጡለት የትናንቱ ብላቴና፣ ዛሬ በስሙ ብቻ ሳይሆን በስኬቱም ብዙዎችን ያስደመመ የህክምናው ዘርፍ ቁንጮ ሆኗል...

እ.ኤ.አ በ2011...

“የአመቱ የአሜሪካ 1000 ከፍተኛ ደመወዝ ተከፋይ የመንግስት ሰራተኞች” በሚል “ዊኪኦርግቻርትስ” ድረገጽ ባወጣው ዝርዝር ውስጥ፣ ዶ/ር ኤሌክትሮን ክበበው ከአሜሪካው ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ ቀጥሎ በሁለተኛነት ተቀምጠዋል!...

መረጃው እንደሚለው ዶ/ር ኤሌክትሮን በአመት 350 ሺህ የአሜሪካ ዶላር ይከፈላቸዋል፡፡

በአዲስ አበባው ቅዱስ ዮሴፍ ትምህርት ቤት የተማሩት ዶ/ር ኤሌክትሮን ክበበው፤ በአሜሪካ ሳንፍራንሲስኮ ከሚገኘው ዪኒቨርሲቲ ኦፍ ካሊፎርኒያ በህክምና የተመረቁ ሲሆን የአሜሪካን ቦርድ ኦፍ ሰርጀሪን የቀዶ ህክምና ሰርተፊኬትም አግኝተዋል፡፡

ላለፉት ከ20 በላይ አመታት በሳንፍራንሲስኮ በኢንዶክሪንና ታይሮይድ ካንሰር ዘርፍ የአጠቃላይ ቀዶ ህክምና አገልግሎት በመስጠት ላይ የሚገኙት ዶክተሩ፤ በአሜሪካ ብሄራዊ የካንሰር ኢንስቲትዩት፣ የካንሰር ምርምር ማዕከል የኢንዶክራይን ኦንኮሎጂ ቅርንጫፍ ሃላፊ ሲሆኑ የካንሰር ጄኔቲክስ ክፍሉንም በበላይነት በመምራት ላይ ይገኛሉ፡፡

ዶክተሩ በእስካሁኑ የሙያ ዘመናቸው ከሁለት ሺህ በላይ የተሳኩ ቀዶ ህክምናዎችን ያከናወኑ ሲሆን ከ150 በላይ የጥናት ጽሁፎችንና መጽሃፍትን ለህትመት እንዳበቁ “ብሬኪንግጎቭ” የተሰኘ ድረገፅ አመልክቷል፡፡
ሌላኛዋ የአቶ ክበበው ልጅ...
ፖሲትሮን ክበበው...
ከዩኒቨርሲቲ ኦፍ ሚቺጋን በህክምና ተመርቃ ከ20 አመታት በላይ ያገለገለችና፣ በካሊፎርኒያ ሳንታ ሞኒካ በመስራት ላይ የምትገኝ ዝነኛ ዶክተር ናት፡፡
ደሞ ሌላኛው ልጃቸው...
ዲዩትሮን ክበበው...
ከዩኒቨርሲቲ ኦፍ ካሊፎርኒያ አባቱ በተመረቁበት በኤሌክትሪካል ኢንጂነሪንግ ተመርቆ፣ በዚያው በአሜሪካ እየሰራ ይገኛል...
አቶ ክበበው ተሳክቶላቸዋል...
ሆነ ብለው ሳይንስ ነክ ስም ያወጡላቸው ልጆቻቸው፣ እንዳሰቡት ወደ ሳይንሱ አለም ተስበዋል... ስኬታማም ሆነዋል...

እርግጥ ነው...
አቶ ክበበው ለልጆቻቸው ያወጡት ስም ብቻውን የፈጠረው ተጽዕኖ መሆኑን እርግጠኛ ሆኖ መናገር አይቻልም...

እኔ እና ቤቴ ግን...እየደነገጥንም፣ እየተጨነቅንም፣ እየሰጋንም "ዶ/ር አቢይ የማይደረገውን የመጨረሻው ስህተት አይኑ እያዬ አያደርግም!" ብለን እናምናለን!!!ያም ሆኖ...ግብጽ ታጥቃ በተነ...
26/06/2020

እኔ እና ቤቴ ግን...
እየደነገጥንም፣ እየተጨነቅንም፣ እየሰጋንም "ዶ/ር አቢይ የማይደረገውን የመጨረሻው ስህተት አይኑ እያዬ አያደርግም!" ብለን እናምናለን!!!

ያም ሆኖ...
ግብጽ ታጥቃ በተነሳችበትና ግድቡን ከንቱ ለማስቀረት በምትኳትንበት በዚህ ወሳኝ ወቅት እያንዳንዷ ደቂቃ የሚተኛባት አይደለችምና መንግስት ከመሼም ቢሆን፣ የሚባለውንና የሆነውን አጣቅሶ እውነቴ ያለውን ሊነግረንና ሊያረጋጋን ይገባ ነበር!

አዲስ አበባ..."...አዲስ አበባ ደግሞ ታላቋ ጋለሞታ ናት። ለደፈራት ሁሉ ቀሚሷን ገልባ ትተባበራለች። "በህግ አምላክ" አትልም። ህግም አምላክም ኖሯት አያውቅም..."(ሌሊሳ ግርማ - ነፀብ...
24/06/2020

አዲስ አበባ...

"...አዲስ አበባ ደግሞ ታላቋ ጋለሞታ ናት። ለደፈራት ሁሉ ቀሚሷን ገልባ ትተባበራለች። "በህግ አምላክ" አትልም። ህግም አምላክም ኖሯት አያውቅም..."

(ሌሊሳ ግርማ - ነፀብራቅ)

Via lij eyasu z ethiopia

"የትግራይ ህዝብ ራስን በራስ የማስተዳደር መብት በመስዋእትነት የተረጋገጠ ነው። ይህንን መብት ለአንድ ቡድን ወይም ሌላ ግለሰብ convenience ሲባል መሰዋት ያለበት መብት አይደለም። የም...
24/06/2020

"የትግራይ ህዝብ ራስን በራስ የማስተዳደር መብት በመስዋእትነት የተረጋገጠ ነው። ይህንን መብት ለአንድ ቡድን ወይም ሌላ ግለሰብ convenience ሲባል መሰዋት ያለበት መብት አይደለም። የምርጫ ቦርድ ደግሞ ወረቀት የሚያድል ተቋም ነው። ምርጫ ቦርድ የመምረጥ መብት የሚያረጋግጥ ተቋም ኣይደለም "

- ጌታቸ ወራዳ 😉

እኔ በዓለም ታሪክ... 😝እኔ ባልኖር ኖሮ...ከቢል ክሊንተን ጋር ቃለመጠይቅ ያደረጉ የአለማችን ጋዜጠኞች ቁጥር በአንድ ይቀንስ ነበር!...የቢል ክሊንተን ታሪክ፣ የኔን ያህል ይጎድል ነበር!...
23/06/2020

እኔ በዓለም ታሪክ... 😝
እኔ ባልኖር ኖሮ...

ከቢል ክሊንተን ጋር ቃለመጠይቅ ያደረጉ የአለማችን ጋዜጠኞች ቁጥር በአንድ ይቀንስ ነበር!...

የቢል ክሊንተን ታሪክ፣ የኔን ያህል ይጎድል ነበር!...

ከአሜሪካም ታሪክ ከክሊንተን ታሪክ የጎደለውን ያህል ይጎድል ነበር!...

የአሜሪካን ታሪክ ያካተተው የእስካሁኑ የዓለማችን ታሪክ፣ በእኔ መጠን ይጎድል ነበር!...

ስለዚህ...

እኔን ያላካተተ የዓለም ታሪክ፣ አሁን ባለበት መጠን ሙሉ አይሆንም!... እደግመዋለሁ፤ አይሆንም!!!...
ልሰልሰው እንዴ?... 😝😝😝
(ከ13 አመታት በፊት የተነሳናት ፎቶ ናት)

የአቶ ገዱ ጣት ወደ ሱለይማን ደደፎ እየጠቆመ ነው?የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው የኢትዮጵያን ብሄራዊ ጥቅም ለማስጠበቅ በሙሉ ጊዜያቸው እየሰሩ ካሉ ዲፕሎማቶች በተጻራሪ በእውቀት...
22/06/2020

የአቶ ገዱ ጣት ወደ ሱለይማን ደደፎ እየጠቆመ ነው?

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው የኢትዮጵያን ብሄራዊ ጥቅም ለማስጠበቅ በሙሉ ጊዜያቸው እየሰሩ ካሉ ዲፕሎማቶች በተጻራሪ በእውቀት ማነስና በአመለካከት ችግር ከቆሙለት አላማ ውጭ የሚንቀሳቀሱ ዲፕሎማቶችን የማስተካከል ስራ እንደሚሰራ ተናገሩ ሲል ፋና ከሰአታት በፊት ያወጣውን ዘገባ ሳነብብ፤ የሚኒስትሩ ጣት ያነጣጠረው ወደ ሱለይማን ደደፎ ይሆን ስል ጠረጠርኩ።

Address


Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when መባቻ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Videos

Shortcuts

  • Address
  • Alerts
  • Videos
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share