ejostaejo2019

  • Home
  • ejostaejo2019

ejostaejo2019 Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from ejostaejo2019, Video Creator, .

11/09/2023

እንኳን አደረሳቹ እንኳን አደረሰን
2016 ዘመነ ዮሐንስ ፍቅር ሰላም ደስታ ተድላ ይቅርታ ቸርነት ምህረት በረከት ረድኤቱ አይለያቹ አይለየን
◦ እንቁጣጣሽ መጣች ለአዲስ አመት አደረሰን
◦ የአደይ አበባ ደምቃ ወጣችልን
◦ መሥኩ ለመለመ ዝናቡም አባራ
◦ ገበሬው ፈራለት አሽቶ አዝመራ
◦ ሠላም ፍቅር ሆነ በየአደባባዩ
◦ በብርሃን ሊምላ አጌጦ ሠማዩ
◦ ውበት እንደ አደይ ከቶ የት ተገኝቶ
◦ ማንስ ሠው ሊከፋ ተስፋዋን ተጋርቶ
◦ የአደይ ፍንጣቂ የአበባዋ ቀለም
◦ አመት ሙሉ ተስፋ የሚያሥመኝ ሠላም
◦ አደይ አበባዬ ትንሿ ብዙዋ
◦ ነብሴ ታደሰብሽ አይቼሽ ስገባ
◦ እስከ ከርሞ ድረስ ዳግም እስክትመጪ
◦ ብዙ እንዳትናፍቂኝ አሁን በደንብ ውጪ
◦ አብቢ ፍኪልኝ ልይሽ በየመስኩ
◦ ነብሴን ልቤን ላድስ ህዋሶቼም ይርኩ
✓ ከባድ ነበርና ያለፈው የሄደው
አዲሱን ግን አመት በተስፋ ልውደደው
አንቺን በተምሳሌት ጌታ ካበቀለሽ
የአደይ አበባዬ እንኳን ደህና መጣሽ

🌼
::::::::::::::::::::::::::::::::::::
እንቁጣጣሽ🌼
የአሮጌ እሳቤ መቃብር የአዲስ ተስፋ ጅማሮ።
አዲስ ለውጥ አዲስ ዘመን የትኩስ ጉልበት ቋጠሮ።
መገፋፋት እንደ ኮሶ ከስሩ ሚነቀልበት።
ዘረኝነት ተመንጥሮ ፍቅር የሚተከልበት።
ሰንጋው ሀረር ቡናው ጅማ
ጠጅ ጠላው ከአማራ ተዙሮ ጀባ ሚባልበት።
ፍቅር እንደ ጤፍ ተሰብስቦ ጥላቻ እንደ አረም ሚጣልበት።
አሮጌ ማንነት ይዞ
ዘመንን ብቻ ቢቆጥሩት መች እውነት ነው መለወጡ።
ከአንገት በላይ ይሆናል
የውሸት ሳቅ የውሸት ደስታ በአዲስ ማንነት ካልመጡ። 🌼🌼ፈጣሪ በአዲሱ አመት🌼🌼
🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻

ታሞ ከመማቀቅ፣
በብድር ከመሳቀቅ፣
ተፈትኖ ከመዉደቅ፣
የምንወዳትን ቺክ ከመነጠቅ፣
ይሰዉረን !✨
🌼
ከሰዉነት አንሶ እንስሳ ከማከል፣
የራስ እያረረ የሰዉ ከማማሰል፣
ለዘር ለጎጠኝነት ዱላ ከማቀበል፣
በቸልተኝነት ጉዞ ሚስኪኑን ከመበደል፣
ይሰዉረን !! ✨✨
🌼
ፈገግ ብለዉ ከሚገሉን፣
ጀነን ብለዉ ከሚያዋርዱን፣
ደንዘዉ ከሚያደነቁሩን፣
እሱ ይሰዉረን! 🙏
🌼
ሀብታም ሆኖ ሰገጤ፣
ድሃ ሆኖ አራዳ፣
አዕምሮ ይዞ ዘረኛ፣
ሀብት ይዞ ጎጠኛ፣
ከመሆን ይሰዉረን!! 🙏
🌼
ከባለሃብት ቋጣሪ፣
ከእነቅልፋም ታታሪ፣
ከበጥባጭ መሪ፣
ከወንድ ፈሪ፣
ከሴት አስነዋሪ፣
ይሰዉረን! 🙏
🌼
ከመሪ ሸረኛ፣
ከሴት ነገረኛ፣
ከወንድ ጉረኛ፣
ከማህፀን በረኛ፣
ይሰዉረን! 🙏 ተስፋ እንደሚያበስር አደይ አበባ
እንደሚታይ ብሩህ እድል
የለበሰ የ ወርቅ ካባ
ሸክሙ ቀላል የሚጣፍጥ
ቢጎረብጥ የማያሰምጥ
ፍክት ያለ አዲስ ዘመን
ፍክት ያለ አዲስ አመት
ጣጣ የለሽ እንቁ ብቻ
የደስታ አመት ይሁንል
ወደር ይጣ አምሳያ አቻ ፡፡ እንቁጣጣሽ ነበር መስከረም ሲጠባ
አውቆ የበቀለ ወፍ ዘራሽ አበባ፡፡
ለምለም አረንጓዴ…
ያልተጠበቀ መስክ ከብት የሚግጥበት
የደመና ግላጭ የሚጫወትበት፡፡
ሌላም ብዙ ነበር
ሌላም… ደግሞ ሌላ
አለብኝ ትዝታ!
ዘመዶቼ ሳሙኝ
ጓደኞቼም ጋብዙኝ
ሊስትሮ ጨብጠኝ
ባለጋሪ ንዳ መንገዴን አሳየኝ
ያገሬ ልጅ ቆንጆ ‹‹ቤት ለእንግዳ›› በይኝ
አለብኝ ትዝታ…ተስፋ እንደሚያበስር አደይ አበባ
እንደሚታይ ብሩህ እድል
የለበሰ የ ወርቅ ካባ
ሸክሙ ቀላል የሚጣፍጥ
ቢጎረብጥ የማያሰምጥ
ፍክት ያለ አዲስ ዘመን
ፍክት ያለ አዲስ አመት
ጣጣ የለሽ እንቁ ብቻ
የደስታ አመት ይሁንል
ወደር ይጣ አምሳያ አቻ ፡፡ የተፈጥሮ ሀብቱን እግዜር እየቸረን
ባጠቃቀም ግድፈት ለምን ይቸግረን
ይልቅ
ባረገዘው ዕንባ በሰማዩ ለቅሶ
ለምልሞ ገላጣው ምድር ፀጋን ለብሶ
ድርቀት የሌላቸው እርጥባን ቢበዙ
ጨልፈው በዘዴ ፈሳሽ ከ'የወንዙ
ከሊቅ
እስከደቂቅ
ሁሉም በ'የጎራው ሁሉም በ'የፈርጁ
ታሪክ ለመፈፀም ከሆነ ዝግጁ
በዚ'ች በ'ኛ ምድር በቅዱሳን ምኩራብ
በተድላ ይኖራል አንድም ሰው ሳይራብ

ግና ምን ያደርጋል

ኩሬ ሳያሳጣን
ሐይቆች ሳያሳጣን
ጅረት ሳያሳጣን
ወንዞች ሳያሳጣን
ከፍቅር ብንጎድል በችጋር ተቀጣን

ተካፍለን እንብላ ተካፍለን እንጠጣ
እስቲ እንመካከር ሀሳብ እናዋጣ
ከስሜት እንራቅ ምክንያት ይዋጀን
ማስተዋል የበዛው ፍቅር ነው 'ሚበጀን

አሁን ካረፈድን አሁን ከዘገየን
ከጫፉ ላይ ያለ ብርሃን ካልታየን
ባክነን እንቀራለን እንደተለያየን
ይሄ ሳይሆን ግና
ከ'ንግዲ' አይርፈድ እንማር ካለፈው
በጋራ እንጠቀም እስቲ በተረፈው ። .
ዋ ብለን መጣን ዋ ብለን
እስከመቼ "እህ " ሆ እንላን
ዋ ብለን መጣን ዋ ብለን
አበባየሁሽ
/ለምለም/
ገንቡ በተራ
/ለምለም/
እንጨት ሰባብረን
/ለምለም/
ቤት እስክንሰራ
/ለምለም/
እንኳን ቤትና
/ለምለም/
የለንም አጥር
/ለምለም/
ደጅ እናድራለን
/ለምለም/
ዘር ስንቆጥር
/ለምለም/
ዘርማንዘር ቆጥረን
/ለምለም/
ሥንሰራ ቤት
/ለምለም/
ለውጡን ሚመራው
/ለምለም/
ደጉ መንግስት
/ለምለም/
ያፈርስብናል
/ለምለም/
መዝናኛ ቦታ ለመገንባት ፡፡.......................... ......
አደይ
ያገር ጉዳይ
ውይ ስቃይ፡፡
አደይ
የጋራ ታሪክ ፣ የለንም ባይ
የጋራ ድንጋይ አይደለም ወይ
።።።
እቴ አበሳ አቴ አበሳዬ
"አዬ እቴ አበሳዬ"
አቴ አበሳ ስትለኝ ከርማ
"አዬ እቴ አበሳዬ"
ባንክ ዘርፋ ነፃ አውጪዬማ
ጥላኝ ጠፋሽ ፣ ድምጿን ሳልሰማ
"አዬ እቴ አበሳዬ"
መብራት ሀይል ሁሌ ጨለማ
"አዬ እቴ አበሳዬ"
ውሃ ልማት ውሃ ሚያስጠማ
"አዬ እቴ አበሳዬ"
መንገድ ሞልቶ መጎዝ ነው አድማ
"አዬ አቴ አበሳዬ"
ይሁን ኑሮ ከተባለማ
"አዬ አቴ አበሳዬ"
አዬ
"እቴ አበሳዬ"
አዬ
"እቴ አበሳዬ"..................
እዬዬ
እህ ሁሌ እዬዬ
ገዦች አሉ ብዬ
በገዛ ሀገሬ ላይ በዛብኝ ስቃዬ፡፡.......... ......................
ይሸታል ሽንኩርት ሽንኩርት
የአባብዬ ምኩት
አይሸትም ዶሮ ዶሮ
የእማምዬ ጓሮ
ዶሮ አልሰሩም መሠል ፣ ሽንኩርት ዋጋው ንሮ
።።
ከብረው ይቆዩን ከብረው
ተረኝነትን ጥለው ፣ዘረኝነትን ቀብረው
ሺህ አክቲቪስቶች አስረው
ቅድሚያ ለሰው ልጅ ሰጥተው
ህዝቦችን አቀራርበው
ሜንጫና ዱላ ጥለው
አንዲት ኢትዮጵያን ይዘው
ከብረው ይቆዩን ከብረው።
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡ በአዲስ ፍጥነት
በአዲስ ምቾት
በአዲስ አኗኗር
ወደ አዲስ ዓመት!!!

መልካም አዲስ ዓመት!
ለመላው የአንዲት ኢትዮጵያ እምነት ተከታዮች መልካም አዲስ አመት

21/09/2022
30/08/2022
Mor
30/08/2022

Mor

.




04/08/2022

Address


Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ejostaejo2019 posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

  • Address
  • Alerts
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share