ባህርዳር መረጃ ማዕከል Bahirdar Media

  • Home
  • ባህርዳር መረጃ ማዕከል Bahirdar Media

ባህርዳር መረጃ ማዕከል Bahirdar Media የባህርዳር ከተማ ኢኮኖሚ ፣ማህበራዊ እና ፖለቲካዊ ሁኔታዎች

ልዩነቶችን በግጭትና ጦርነት ለመፍታት የሚደረጉ ሙከራዎች ውጤታቸው የጋራ ጥፋት መሆኑን በአግባቡ መረዳት በክልሉ ዘላቂ ሰላም እንዲጸና ሁሉም ማህበረሰብ በባለቤትነት ሊሰራ ይገባዋል፡፡     ...
05/10/2023

ልዩነቶችን በግጭትና ጦርነት ለመፍታት የሚደረጉ ሙከራዎች ውጤታቸው የጋራ ጥፋት መሆኑን በአግባቡ መረዳት በክልሉ ዘላቂ ሰላም እንዲጸና ሁሉም ማህበረሰብ በባለቤትነት ሊሰራ ይገባዋል፡፡
የአብክመ ርዕሰ መስተዳድር
ክቡር አቶ አረጋ ከበደ

የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት አፈጣጠር ልዩ የሚያደርገው ከህዝቦች አብራክ የወጣ መሆኑ ብቻ ሳይሆን የጭቆና ቀንበር ለመስበር ከህዝብ ጎን በመቆምና በመታገል የህዝብ ትግል ግንባር ቀደም ተዋናይ...
25/07/2023

የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት አፈጣጠር ልዩ የሚያደርገው ከህዝቦች አብራክ የወጣ መሆኑ ብቻ ሳይሆን የጭቆና ቀንበር ለመስበር ከህዝብ ጎን በመቆምና በመታገል የህዝብ ትግል ግንባር ቀደም ተዋናይ ከሆነው ትውልድ ጭምር የተፈጠረ መሆኑ ነው።

ይህ ተፈጥሮው በአገሩ ብቻ ሳይሆን እስካሁን ድረስ በዓለም አቀፍ የሰላም ማስከበር ግዳጅ ላይ በተሰማራባቸው አገሮችም የተረጋገጠ ነው። ህዝባዊነቱ ከሌሎች አገሮች ሰራዊቶች በመሰረቱ የተለየ ሆኖ እንዲታይና የህዝብ ፍቅርና አለኝታነትን እንዲጎናፀፍ አስችሎታል።

የሰራዊታችን መሰረታዊ እሴት በጠንካራ ዲሲፒሊን ከራስ በላይ ለአገርና ለህዝብ ጥቅም ማስከበር ላይ የተመሰረተና የህገመንግስቱ የመጨረሻ ምሽግ እንዲሆን ተደርጎ የተገነባ ነው።

የኢትዮጵያ ዋና ጠላት የሆነውን ድህነት ለማጥፋት አገራችን በምታደርገው ትግልም ሰራዊታችን ለዕድገትና ለዲሞክራሲ ግንባታ መሰረት የሆነውን ሰላምና መረጋጋትን በማረጋገጥ ወደር የማይገኝበት ሚና ሲጫወት ቆይቷል። አገራችን በልማትና በዲሞክራሲ ለምታስመዘግባቸው ዕድገቶችና ለውጦችም ላይ የራሱን ደማቅ አሸራ እያስቀመጠ ይገኛል።

12/07/2023
ድል ለባህርዳር ከነማ🌴🌴
10/06/2023

ድል ለባህርዳር ከነማ🌴🌴

29/09/2022
10/08/2022
05/08/2022

ኑ! የነሐሴ 01/2008 ሰማዕታት ጀግኖች ቀን በጋራ እናስብ!
〰️〰️〰️ 〰️〰️〰️ 〰️〰️〰️
ነሐሴ 01/2008ዓ.ም የባህርዳር ከተማ ወጣቶች የወቅቱን የወያኔን የግፍ አገዛዝ በመቃወም "ወልቃይት ብረሳሽ ቀኜ ትርሳኝ!" በማለት ሰላማዊ ትግል ለኩሰው ትግሉ ህዝባዊ እንዲሆን የተከፈተው ሁለንተናዊ መሰዋእትነት ይታወሳል።

እለቱ ከአራቱም አቅጣጫ ወደ ከተማው አደባባይ በርካቶች ድምፃቸውን ለማሰማት የተመሙበት ነበር።ከከተማው ወጣቶች በተጨማሪ በጎንደርና በጎጃም አቅጣጫ በርካቶች ብዙ ኪሎ ሜትሮችን አቆራርጠው የባህርዳር ከተማን ወጣቶችን በመቀላቀል ሰላማዊና የወያኔን አገዛዝ በመቃዎም ሰልፍ ላይ የተገኙ ብዙዎች ነበሩ።

ህዝባዊ እምቢተኝነቱ እና የስርዓት ይቀየር ለውጥ ፍለጋ ጉዞዉ ያስደነገጠው ወያኔ ለሰላማዊ ጥያቄ አደባባይ የወጡ ንፁሃን ላይ አፈሙዝ በማዞር ብዙዎችን ለመስዋዕትነት አንዳንዶች ለአጋል ጉዳት ዳርጎ አልፏል።

የህዝብ ጥያቄዎችን በአፈናና በአንባገነንነት ማሸነፍ አይቻልምና በ2008 ዓ.ም የተጀመረው የለውጥ እንቅስቃሴ በርካታ ውጣ ውረዶችን አልፎ በ2010ዓ.ም ሀገራዊ ለውጦ በህዝባችን ተጋድሎ፣በጠንካራ መሪዎች መዘውር አባገነኑ፣አፋኙና ከፋፋዩ ወያኔ ከዘዋሪዎቹ ጋር ከህዝብ ጫንቃ ላይ አሽቀንጥሮ ማስወረድ ተችሏል።

ከተማችን ባህርዳር ከተማ አስተዳደር ያን ወቅት ከከተማው ነዋሪዎች፣ከጀግና ወጣቶች ጋር በመሆን በፅናት በመታገል ያሳለፈ ሲሆን ከለውጡ በኋላም በየአመቱ ጀግኖቻችን በማክበር ለሀገራዊ እኩልነት፣ፍትሐዊ ተጠቃሚነትና ተሳታፊነት እየተጋ ይገኛል።በዚህ አመት ጀግኖቻችን በማክበር በከተማ ደረጃ የተለያዩ ኩነቶችን የምናሳልፍ ሲሆን

ሐምሌ 30/2014 ዓ.ም በአይነቱ ለየት ያለ "የህይወት ስጦታ ይስጡ! ደም ይለግሱ!" በሚል መሪ ሀሳብ መሰዋእትነት በከፈሉ ጀግኖች ስም መላ የከተማችን ነዋሪዎች እለቱን ደም በመለገስ እንዲያሳልፉ ይደረጋል።

በዕለት ነሐሴ 01/2014ዓ.ም ሁሉም የከተማችን ነዋሪዎች፣አመራሮች፣ የግልና የመንግስት ሰራተኞች የጋራ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ እና የእግር ጉዞ የሚደረግ ይሆናል።

"ኑ! ነሐሴ 01/2008 የሰማዕታት ጀግኖች ቀን በጋራ እናስብ!"
ማስታወሻነቱ፦ ለነሐሴ 01/2008 ሰማዕታት ጀግኖቻችን ነው!
〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️
◾️የደም ልገሳ ሐምሌ 30/2014: አዝዋ አካባቢ
◾️የአካል ብቃት እንቅስቃሴና የእግር ጉዞ ነሐሴ 01/2014 የድሮው ጊዮን

በእለቱ ማንም ሰው እንዳይቀር!

@የባህርዳር ከተማ አስተዳደር

ባህርዳር ከተማ የአገልግሎት አሰጣጥ ጉዳይ ትኩረት ያሻል!ሌብነትና እጅ መንሻ ፈተናዎች ሁነዋል።
09/02/2022

ባህርዳር ከተማ የአገልግሎት አሰጣጥ ጉዳይ ትኩረት ያሻል!ሌብነትና እጅ መንሻ ፈተናዎች ሁነዋል።

31/01/2022

ሌብነቱ፣ጎጠኝነቱ፣ስንፈቱ ተባብሶ ቀጥሏል

ደብረብርሐን አሁን
21/01/2022

ደብረብርሐን አሁን

ሌላኛው የጥምቀት ገፅታ በባህርዳር
19/01/2022

ሌላኛው የጥምቀት ገፅታ በባህርዳር

እግዚዮ ሰው መጥፋት ወይኔ ባህርዳሬ
16/01/2022

እግዚዮ ሰው መጥፋት

ወይኔ ባህርዳሬ

በአፄ ቴዎድሮስ ዘመን ታስረው ከነበሩ እንግሊዛዊያን መካከል አንዱ ዶ/ር ሔነሪ ብላንክ የሚባል ነበር ። " ለመጀመሪያ ግዜ በ1852 ዓ.ም አፄ ቴዎድሮስን ሳገኛቸው እድሜያቸው 48 ይሆን ነበ...
14/01/2022

በአፄ ቴዎድሮስ ዘመን ታስረው ከነበሩ እንግሊዛዊያን መካከል አንዱ ዶ/ር ሔነሪ ብላንክ የሚባል ነበር ።

" ለመጀመሪያ ግዜ በ1852 ዓ.ም አፄ ቴዎድሮስን ሳገኛቸው እድሜያቸው 48 ይሆን ነበር ። መልካቸውም ከብዙዎች ሀበሾች ጠቆር ያሉና ጠይም የሚባሉ ናቸው ። ....
በፈረሰኝነታቸው ፣ በጦር አወራወር ስልታቸውና በወታደርነታቸው የተመሰገኑ ፣ ጠንካራ የሆነውን ጠላታቸውን ለማሸነፍ ችሎታ ያላቸው ሰው ነበሩ ። ጎድጎድ ያሉት የጥቋቁር አይኖቻቸው አገላለጥ አስደንጋጭ ሲሆን ፣ በሰላም ጊዜ ለስላሳ ሆነው ደስ የሚያሰኙ ፣ በተቆጡ ጊዜ ደግሞ በርበሬ መስለው የሚያስደነግጡ እና የሚያሸብሩ እሳተ ገሞራ የሚወረውሩ ነበሩ ። በድንገት ሲቆጡ መላ አካላቸው የሰውን ልጅ ከፍ ካለ ድንጋጤ ላይ ይጥላል ። ጠይሙ ገላቸው ሲኮሰኩስ ፣ ስሉ ከንፈራቸው ሲንቀሳቀስና ፀጉራቸው ሲዘናፈል በጠቅላላው ሰውነታቸው የአንበሳነት ፀባይ የያዘ አስደንጋጭ ይሆናል " ብሏል ። (Dr.Henry blank 1886)...

ልጅ ካሳ ጥር 6 1811 ዓ.ም ከቋራው ተወላጅ ከሐይሉ ወልደጊዮርጊና ከእንፍራዛ እመቤት ወ/ሮ አትጠገብ ወንደሰን ነበር የተወለዱት ።

ከፍሰሀ ያዜ ካሣ ከኖህ እስከ ኢህአዴግ መፅሀፍ ገፅ 376 እና 377 የተወሰደ ።

12/01/2022

ኧረ ተው ጎበዝ አንተዛዘብ?
ይች ሀገረ የኛም ናት!

04/01/2022

አመንም አላመንም አሁን ላይ በህይወት የምንኖረው ለእኛ ሲሉ ቀድመው በተሰው ጀግኖች ወንድሞቻችን ላይ ነው...

ስለሆነም በአሉን ስናከበር በምንኖርበት ቀበሌ የተሰው ወንድም እህቶቻችንን ቤተሰቦች አስቀድመን ያለንን አካፍለን መሆን አለበት።
እንደ ባህርዳር እኔ ባለኝ መረጃ ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ሰማእቶች ቤተሰብቻቸው ባህርዳር ነው የሚኖሩት ብለውኛል ( የዘለልኋቸው ካሉ በቅንነት ከታች አስተያየት መስጫው ላይ ጨምሩልኝ)
የተሰው ወንድሞቻችንን
1. አበበ አለሙ
ቤተሰቦች የሰራሽ ጀምበር እና ፍቅር ምስጋን
በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሂሳብ ቁጥር
1000448855337 ነው።
ስልክ ቁጥር የሟች አበበ ወንድም በቁየ ይባላል 0946456262
2. የሻምበል ቤተሰቦች በባለቤቱ በወ/ሮ ንግስቴ ሙሉየ ስም በተከፈተው የንግድ ባንክ አካውንት 1000448735978
የሻምበል ባለቤት ስልክ ቁጥር
0993707059
3. ጀጀው ደጉ ለሀገር ሲል በጋሸና ግንባር የተሰዋ
ዘርፌ ቢያይልኝ ሚስት
ቃልኪዳን ጀጀው ልጅ
አርሴማ ጀጀው ልጅ
ስ/ቁጥር 0938253670
4. የተሰዋው ሞላ ደስየ የራያ ፋኖ - ሚስቱ -ህይወት በላይ ትባላለች ባህርዳር ቀበሌ 14
ንግድ ባንክ -1000224569207
ስልክ -0918134118::
ንግድ ባንክ -1000224569207
5).አቶ ሙሉቀን አዳነ ሰፊው
የባለቤቱ ስም ፦ወ/ሮ ዓለምፀሀይ ሲሳይ
ስልክ ቁጥር =0975102215
የባንክ አካውንት ቁጥር =1000448287436
6).ማንደፍሮ አድማሱ የተሰዋዉ ጓድ ሲሆን (ቤተሰብ)0918020896
7) የፋኖ ስም: ዘመቻ ሞላ
የሚስት ሚስት፡ ምንቴ አለምነው።
አድራሻ፡ ባህርዳር ቆጠጢና።
ስልክ፡0975020826።
1000425399873 ምንቴ አለምነው። ንግድ ባንክ
8).አስናቀ ንጋቱ የተሰዋዉ ጓድ ሲሆን ቤተሰቡ (ባለቤቱ) 0900139659
የተሰው ወንድሞቻችንን
1. አበበ አለሙ
ቤተሰቦች የሰራሽ ጀምበር እና ፍቅር ምስጋን
በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሂሳብ ቁጥር
1000448855337 ነው።
ስልክ ቁጥር የሟች አበበ ወንድም በቁየ ይባላል 0946456262
2. የሻምበል ቤተሰቦች በባለቤቱ በወ/ሮ ንግስቴ ሙሉየ ስም በተከፈተው የንግድ ባንክ አካውንት 1000448735978
የሻምበል ባለቤት ስልክ ቁጥር
0993707059
3. ጀጀው ደጉ ለሀገር ሲል በጋሸና ግንባር የተሰዋ
ዘርፌ ቢያይልኝ ሚስት
ቃልኪዳን ጀጀው ልጅ
አርሴማ ጀጀው ልጅ
ስ/ቁጥር 0938253670
4. የተሰዋው ሞላ ደስየ የራያ ፋኖ - ሚስቱ -ህይወት በላይ ትባላለች ባህርዳር ቀበሌ 14
ንግድ ባንክ -1000224569207
ስልክ -0918134118::
ንግድ ባንክ -1000224569207
5).አቶ ሙሉቀን አዳነ ሰፊው
የባለቤቱ ስም ፦ወ/ሮ ዓለምፀሀይ ሲሳይ
ስልክ ቁጥር =0975102215
የባንክ አካውንት ቁጥር =1000448287436
6).ማንደፍሮ አድማሱ የተሰዋዉ ጓድ ሲሆን (ቤተሰብ)0918020896
7) የፋኖ ስም: ዘመቻ ሞላ
የሚስት ሚስት፡ ምንቴ አለምነው።
አድራሻ፡ ባህርዳር ቆጠጢና።
ስልክ፡0975020826።
1000425399873 ምንቴ አለምነው። ንግድ ባንክ
8).አስናቀ ንጋቱ የተሰዋዉ ጓድ ሲሆን ቤተሰቡ (ባለቤቱ) 0900139659
9). ሙሉቀን አዳነ የተሰዋዉ ጓድ ሲሆን የባለቤቱ ስልክ 0975102215
ከነዘመነ ካሴ አባል የተሰዋ ባህርዳር
10) .፲ አለቃ ኤፍሬም
0912491375 ታዴ
11) .፲ አለቃ ኤፍሬም
12).ቴዎድሮስ-ቀበሌ 13
የጀግናው ሰማእት ቴዲ
ዳንኤል ፀጋው ዜናሚኒችል እና ወርቅየ ፈቃዱ 1000446289989
0912491375 ታዴ

በአማራ ክልል የተጣለው ሰዓት እላፊ የእንቅስቃሴ ገደብበአማራ ክልል ተቋርጦ የነበረው የኢንተርኔት አገልግሎት መጀመሩ ጥሩ ነው። ሌሎች መሰል አገልግሎትም እየተመለሱ ነው። ይሔ መልካም እና ይ...
04/01/2022

በአማራ ክልል የተጣለው ሰዓት እላፊ የእንቅስቃሴ ገደብ

በአማራ ክልል ተቋርጦ የነበረው የኢንተርኔት አገልግሎት መጀመሩ ጥሩ ነው። ሌሎች መሰል አገልግሎትም እየተመለሱ ነው። ይሔ መልካም እና ይበል የሚያሰኝ ነው።

በተመሳሳይ በፊት ተጥሎ የነበረውን ሰዓት እላፊ እንቅስቃሴ ገደብ ላይ ተደርጎ የነበረው ማሻሻያ በበጎ ጎኑ የሚታይ ነው።

ከኢትዮጵያ መንግሥት በኩል የቀረበላቸውን ጥሪ ተቀብለው ወደ አገር ቤት የገቡ የዲያስፖራ አባላትና የገና በዓልን ለመታደም ከተለያዩ የዓለማችን ሀገራት ጎብኝዎች ወደ አማራ ክልል እየገቡ ነው።

በመሆኑ ቀደም ሲል ከጥዋቱ 12:30 እስከ ምሽቱ 4:00 ድረስ ተጥሎ የነበረው ስዓት እላፊ የእንቅስቃሴ ገደብ በተመረጡ ከተሞችና በርካታ እንግዶች በሚታደሙባቸው አካባቢዎች ላይ መሻሻል ይኖርበታል።

በተለይም በክልሉ ርዕሰ መዲና ባህርዳር፣ ጎንደር፣ ደብረ ብርሐን፣ ደብረ ማርቆስ፣ ላልይበላል፣ ደብረ ታቦርና መሰል የጸጥታ ስጋት የሌለባቸው ከተሞች ላይ ያለው የእንቅስቃሴ ሰዓት እላፊ ገደብ ቢሻሻል ለክልሉም ሆነ ለእንግዶች ምቹ ሁኔታ መፍጠር ይችላል።

ተዋቸውደርሶ

ባህርዳርን ይጎብኙ!🌴🌴🌴🌴
02/01/2022

ባህርዳርን ይጎብኙ!
🌴🌴🌴🌴

02/01/2022

ፍትህ ለወለጋ ወገኖቻችን!

የግብዣ ጥሪ ከባህርዳር!አንድ ሚሊዮን ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ወደ አገር ቤት እንዲመጡ በጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ የቀረበውን ጥሪ ተከትሎ እንግዶች የቱሪስት መስህብ...
19/12/2021

የግብዣ ጥሪ ከባህርዳር!

አንድ ሚሊዮን ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ወደ አገር ቤት እንዲመጡ በጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ የቀረበውን ጥሪ ተከትሎ እንግዶች የቱሪስት መስህብ በሆነችው እና ተወዳጇ ከተማ ባህርዳር በመምጣት፦

👉 "ከ 37 ገዳማት በላይ በውስጡ ያቀፈውን ታሪካዊ እና ጥንታዊ የጣና ገዳማትን

👉ውብ የሆነውን የጣናን ሀይቅን።

👉 የዘጌ ገዳማትን

👉 የከተማችን ውብ እና አስደናቂ መዝናኛዎችን።

👉የጢስ ዓባይ ፏፏቴ።

👉በአፄ ሱስንዮስ ዘመነ መንግስት 17 ክ/ዘመን እንደተሰራ የሚነገርለት ጥንታዊውን የአላታ ድልድይ።

👉ታሪካዊ ቦታዎችን እና ሌሎችንም የቱሪስት መስህብ ቦታዎችን በመጎብኘት ውድ ጊዜዎትን ከቤተሰብዎ እና ከሌሎች ወዳጅዎ ጋር ያሳልፉ።

ይምጡ! እየተዝናኑ ስለሀገራችን ይምከሩ!

ባህርዳሮች 💪💪ጀግኖች ወደ ግንባር ተሸኝተዋል🙏🙏
06/11/2021

ባህርዳሮች 💪💪
ጀግኖች ወደ ግንባር ተሸኝተዋል🙏🙏

ድላችን ለከተማችን!!ገቢያችን ለወገናችን!!ባህርዳር ከነማ ዛሬ ከመከላከያ ከነማ ጋር በባህርዳር አለም አቀፍ ስታዲየም የአደረገውን ጨዋታ በድል በማጠናቀቅ የአዲስ አበባን City Cup ዋንጫ...
10/10/2021

ድላችን ለከተማችን!!
ገቢያችን ለወገናችን!!

ባህርዳር ከነማ ዛሬ ከመከላከያ ከነማ ጋር በባህርዳር አለም አቀፍ ስታዲየም የአደረገውን ጨዋታ በድል በማጠናቀቅ የአዲስ አበባን City Cup ዋንጫ
ወስዷል።

በድጋሜ እንኳን ደስ አላችሁ!!🏆🏆

  ‼️ጥንታዊቷ መንቆረር የአሁኗ ደብረማርቆስ ለዘመናት እንደ መርገምት ተጭኗት የኖረውን የአቧራ ክምር በጀግና አመራሮቿና በህዝቧ ብርቱ ትግል ንዳ ዛሬ ላይ ደምቃና ፈክታ መታየቷ ባልተዋጠላቸ...
10/10/2021

‼️

ጥንታዊቷ መንቆረር የአሁኗ ደብረማርቆስ ለዘመናት እንደ መርገምት ተጭኗት የኖረውን የአቧራ ክምር በጀግና አመራሮቿና በህዝቧ ብርቱ ትግል ንዳ ዛሬ ላይ ደምቃና ፈክታ መታየቷ ባልተዋጠላቸውና የፌስቡክ አርበኛ ነን በሚሉ የእንግዴ ልጆች ግርሻት ምክንያት አንድ ኢንች እንኳን ከግስጋሴዋ ወደ ሗላ አትልም ።

ከፅንፈኛው ጥላሁን አበጀ እስከ ቀሚስ ስር ቁማርተኛዋ ቤተልሄም ዳኛቸው ድረስ የተዘረጋው ተራ የፌስቡክ ዘመቻም ሆነ በስውር ገፆቻቸው / The Amhara Informer, Debremarkos Info / በየቀኑ በሚለቀቁ እንቶፈንቶ ወሬዎች የሚረበሽ የደብረማርቆስ አመራርም ሆነ ህዝብ ትናንትም አልነበረም ፤ ዛሬም የለም ፤ ነገም አይኖርም ።

ባልተለመደ የዕድገት ፍጥነት የተከሰተችዋን እና ለዘመናት ከተኛችበት ዕንቅልፍ በቁርጥ ልጆቿ የነቃችውን ውብ ከተማ በምርጫ ሰበብ ለማፍረስና የከተማውን ማህበረሰብ በተለይ ነጋዴውን ለመከፋፈል ሞክረው ያልተሳካላቸው እነዚህ የቁራ መልዕክተኞች ዛሬ ላይም በድጋሜና አይናቸውን በጨው አጥበው የቀለብ ሰፋሪዎቻቸውን ስውር ዕቅድ ዕውን ለማድረግ በተራ የፌስቡክ ዲስኩር አመራር የመሾም / የማውረድ የሞኝ መንገዳቸውን ተያይዘውታል ።

እኛም እንላቸዋለን !! እናንተ በፅንፈኝነት ክፉ በሽታ የናወዛችሁ ቆሞ ቀሮች ሆይ በፅኑ መሰረት ላይ የተገነባውን የደብረማርቆስ ከተማ ሰላም ታደፈርሱም ሆነ የአመራር አንድነት ትበትኑ ዘንድ አይቻላችሁም ። በእናንተ የቁራ መልዕክተኞች ድምፅ ተረብሾ ደብረማርቆስን የሁለንተናዊ ለውጥ ባለቤት ከማድረግ ሊያፈገፍግ የሚችል ከንቲባም ሆነ ብልጽግና ሃላፊ ይኖራል ብላችሁ አታስቡ ። በፈሪዎች የፌስቡክ ጠባብ ምሽግ እየተርመሰመሳችሁ በየቀኑ የምታሰሙትን ደረት ድቂና ሙሾ ማውረድ ከአዞ እምባ ለይተን አናየውም ።

እውነት እውነት እንላችሗለን በእናንተ የረከሰ ማንነት ፤ የተበረዘ አስተሳሰብ አፈርን !! በዚህ አስቸጋሪና ድርብርብ ችግሮች በሚፈራረቁበት ወቅት እንደ አንድ የአማራ ክልልም ሆነ የደብረማርቆስ ተወላጅነት አዕምሯችሁን ለቅን ዕሳቤ ማዘጋጀት ዕጃችሁን ለድጋፍ መዘርጋት በሰው ሰዎኛው የሚጠበቅ ጉዳይ ቢሆንም የቀነጨረ አስተሳሰባችሁ ዛሬም ድረስ በከተማችሁ ላይ ጦር ትወረውሩ ለወግ ለማዕረግ ያበቃች ህዝባችሁን ከጀርው ትወጉ ዘንድ እየተቅበዘበዛችሁ ነውና እጃችሁን ከደብረማርቆስ ከተማ ላይ አንሱ የመጨረሻ ምክራችን ነው ።

እንደ ፅንፈኞች ከንቱ ቅዠት ሳይሆን ህዝባችንን ከጎናችን በማሰለፍ የተጀመረውን ሁለንተናዊ የዕድገት ሽግግር ዳር ከማድረስ የሚያቆመን ምንም ሃይል አለመኖሩንም እንገልፅላችሗለን ።

‼️

የጥንቃቄ መልዕክት ለባህርዳር ከተማ ነዋሪዎች፦የፊታችን ዓርብ ነሐሴ 07/2013 ዓ.ም ከሰዓት በኋላ ከጣና የሚወጣው የአባይ ወንዝ ውሃ አንድ ዩኒት ከጨረጨራ ግድብ ስለሚለቀቅ በአባይ ዙሪያ ...
11/08/2021

የጥንቃቄ መልዕክት ለባህርዳር ከተማ ነዋሪዎች፦

የፊታችን ዓርብ ነሐሴ 07/2013 ዓ.ም ከሰዓት በኋላ ከጣና የሚወጣው የአባይ ወንዝ ውሃ አንድ ዩኒት ከጨረጨራ ግድብ ስለሚለቀቅ በአባይ ዙሪያ የሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች በተለይም በግሽ አባይ እና በአፄ ቴዎድሮስ ክፍለ ከተሞች የሚገኙ ነዋሪዎች አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርጉ የክልሉ ውሃ ሐብት ቢሮ መልዕክቱን ያስተላልፋል፡፡

ሁሉም አሻራውን ያስቀምጥ🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴ባህርዳርን የማስዋብ ዘመቻ ቀጥሏል በዛሬው እለት ኩሪፍቱ ሎጂ እና ስፓ ሰራተኞች እና አስተዳዳሪዎች ከቀበሌ 13 ወጣቶች ጋር በመተባበር  ከዲፖ ...
05/07/2021

ሁሉም አሻራውን ያስቀምጥ
🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴

ባህርዳርን የማስዋብ ዘመቻ ቀጥሏል በዛሬው እለት ኩሪፍቱ ሎጂ እና ስፓ ሰራተኞች እና አስተዳዳሪዎች ከቀበሌ 13 ወጣቶች ጋር በመተባበር ከዲፖ እስከ ጎፋ ማዞሪያ ያለውን መንገድ 600 ችግኝ በመግዛት ከባህርዳር የቀበሌ 13 በጎ አሳቢ ወጣቶች ጋር ተክለዋል።

ኩሪፍቱ ሎጂ እና ስፓ እና የቀበሌ 13 ወጣቶችን ከልብ እናመሰግናለን። ሁሉም አገልግሎት ሰጭዎች አሻራቸውን ቢያስቀምጡ መልካም ነው።
Thomas Mekonnen

አስሩ የወልቃይት ጠገዴ የአማራ ባለቤትነት ማረገጫ የታሪክ ሰነዶች አንደኛ፤ 1420ዎቹ እንደተጻፈ የሚታመነው መጽሓፈ አክሱም በግልጽ እንደሚያሰረዳን የትግራይ ግዛቶችና ወሰኖች የሚከተሉት ነበ...
08/06/2021

አስሩ የወልቃይት ጠገዴ የአማራ ባለቤትነት ማረገጫ የታሪክ ሰነዶች

አንደኛ፤

1420ዎቹ እንደተጻፈ የሚታመነው መጽሓፈ አክሱም በግልጽ እንደሚያሰረዳን የትግራይ ግዛቶችና ወሰኖች የሚከተሉት ነበሩ፡- ተምቤን፣ ሽሬ፣ ስራዮ (Seraye) ሐማሴን፣ ቡር (Bur) ሳማ (Sama) አጋሜ፣ አምባ ሰናዕት (Amba Senait) ገራልታ (Geralta) እንደርታ እና ሰሃርት (Sahart) ናቸው:: መጽሓፈ አክሱም ‹‹Ethiopia: the Land, Its People, History and Culture›› በዮሐንስ መኮንን የተጻፈውን እና John R. Short ‹‹The World through Maps: A History of Cartography›› (ገጽ 352 ይመልከቱ) መጽሓፍት እንደዋቢነት ይጠቀሳል፡፡

ሁለተኛ፤

1634 ዓ.ም የተጻፈው የእማኑኤል በሬዳ መጽሓፍ ‹‹Tractatus tres historico-geographici (1634): A seventeenth century historical and geographical account of Tigray, Ethiopia (Aethiopistische Forschungen) 1634» እንደሚያስረዳው የትግራይ ወሰን ተከዜ እንጂ ተከዜን ተሻግረው ያሉት ወልቃይትና ጠገዴ እንዳልሆኑ ብግልጽ ሰፍሯል፡፡

ሦስተኛ፤

በዘመነ መሳፍንት ኢትዮጵያን ጎብኝቶ የነበረው የጀምስ ብሩስ መጽሓፍም በግልጽ የሚናገረው የትግራይ ወሰን ተከዜ እንጂ ተከዜን ተሻግረው ያሉት ወልቃይትና ጠገዴ እንዳልሆኑ ያመላክታል፡፡ ‹‹Travel to discover source of the Nile Volume 3›› ገጽ 582 የሰፈረውን ማብራሪያ ልብ ይሏል፡፡

አራተኛ፤

በአጼ ዮሓንስ ዘመንም የታሪክ ማስረጃዎች የሚያስረግጡት ያንኑ ነው:: የትግራይ ደንበር ተከዜ ነው፡፡ ወልቃይትና ጠገዴ በጎንደር ስር እንደነበሩ በግልጽ ፈረንሳዊው ፕሮፌሰረ ሬክለስ ጽፎታል፡፡

አምስተኛ፤

በአጼ ቴዎድሮስ ዘመንም ወልቃይትም ሆነ ጠግዴ በትግራይ ስር አልነበሩም:: በወቅቱ ወደኢትዮጵያ የመጡ የእንግሊዛዊያኑን የጉዞ ማስታወሻዎች ያጤኗል፡፡

ስድስተኛ፤

በጣልያን ግዜም የትግራይ ወሰን በደቡብ እንዳምሆኒ፣ በደቡብ ምስራቅ አበርገሌ፣ በምዕራብ ሽሬና አዲያቦ ነበሩ እንጂ ወልቃይት ጠገዴ ዋጃ ኮረም እና መሰል ቦታዎች በትግራይ ስር አልነበሩም፡፡

ሰባተኛ፤

‹‹ወልቃይትንና ጠገዴን ወደ ጎንደር የከለሉት አጼ ኃይለሥላሴ ናቸው፡፡ ይህም በነብላታ ኃይለማርያም ረዳ መሪነት የተካሄደውን የቀዳማይ ወያኔን አብዮት ለመበቀልበስና ሕዝቡንም ለመቅጣት ነው›› የሚለው መሰረት የሌለው ማስተባበያ ነው፡፡ ከጣሊያን ወረራ በፊትም ሆነ በጣሊያን ወረረና ድህረ ጣሊያን የትግራይ ወሰን ያው ተከዜ ነበር፡፡

ስምንተኛ፤

የትህነግ መሪዎችና ከታሪክ ጋር የተፋቱ የትግራይ ምሁራን ወልቃይትን በተመለከተ ‹‹የህዝብ ቁጥርና በሚናገሩት ቋንቋ ነው ወልቃይትንና ጠግዴን ወደ ትግራይ የከለልነው›› ሲሉ ይከራከራሉ፡፡ በመሰረቱ ከሆነ የዘርና የቋንቋ ክልልን ለመጀመርያ ግዜ ኢትዮጵያ ላይ የመሰረተው ጣልያን ነው:: ጣልያን ዘርን መሰረት ያደረገ ካርታ ሲሰራ የራሱን የዘርና የቋንቋ ጥናት አድርጎ ነበር:: በዚህም መሰረት ወልቃይትና ጠገዴን ወደ ትግራይ ሳይሆን ያካለላቸው ወደ ጎንደር ነበር:: ይህ የሆነው ወልቃት ጠገዴ አማራ በመሆኑ ነው፡፡ ይሄ ታሪክ ከተፈጸመ አንድ ትውልድ እንኳን አላለፈውም:: ‹‹ጎንደሬው በጋሻው›› በሚለው የገሪማ ታፈረ መጽሓፍ ላይ እንደተመለከተው በጣሊያን ወረራ ጊዜ አርበኛ ሁነው በአካባቢው የተፋለሙት የጎንደር አርበኞች ናቸው፡፡

ዘጠነኛ፡-

በዚህ ዘመን ያሉ እውቅ ኢትዮጵያንና ቀጠናውን በተመለከተ በርካታ መጽሃፍትን ያዘጋጁ ፕሮፌሰሮች ምስክርነታቸው ሰጥተዋል፡፡ ለአብነት የካምብሪጅ ዩኒቨርስቲው ክሪስቶፈር ክላፕማን ‹‹Transformation and Continuity in Revolutionary Ethiopia›› በተሰኘ መጽሓፋቸው ላይ የትግራይ ደንበር ተከዜ እንጅ ከዛ ተሻግሮ እንደማያውቅ ገልጸዋል፡፡

አስረኛ፡-

ዛሬም ድረስ በህይወት ያሉት የአጼ ዮሓንስ የልጅ ልጅ ልዑል ራስ መንገሻ ስዩምም እንዳረጋገጡት ‹‹የትግራይ ወሰን ተከዜ እንጂ ተከዜን ተሻግረው ያሉት ወልቃይትና ጠግዴ አይደሉም›› ሲሉ ለእውነትና ለታሪክ ያላቸውን ከፍ ያለ ቦታ በአንደበታቸው መስክረዋል፡፡
ከዚህ በላይ የቀረቡ የታሪክ ማጣቀሻዎች በሙሉ የትግራይ ወሰን ተከዜ እንጅ ከዛ ተሻግሮ እንደማያውቅ ያረጋግጣሉ፡፡
የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ለዘመናት በጎንደር ክፍለ ሀገር ዳባት አውራጃ፤ ቀደም ሲል ደግሞ በበጌምድርና ስሜን ጠቅላይ ግዛት ይተዳደር የነበረ እንጅ አንድም ቀን በትግራይ ተከዜን ተሻግሮ እንደማያውቅ ታሪክ ምስክር ነው፡፡

ከ1983 በፊት የወልቃይት-ጠገዴ ሰቲት ሁመራ የአማራ ርስትና ግዛት ነበሩ፡፡ "ትግሬ እንጅ ትግራይ ተከዜን ተሻግራ እንደማታውቅ" የትግራይ ተወላጆች የግንባታ ስራ፣ ለቤተ-ክርስቲያን አገልግሎት፣ እንዲሁም የግብርና ሥራ ሰርተው ለመመለስ እንጅ ለነዋሪነት ከተከዜ ምላሽ መጥተው እንደማያውቁ ታሪክ ምስክር ነው፡፡

በወታደራዊው የደርግ አገዛዝ ዘመን ወልቃይት-ጠገዴ በመጀመሪያ የኢህአሠ/ፓ ቀጥሎም የትህነግ ጦር ወደ ሱዳን መተላለፊያና የጦርነት ቦታ ሆኖ ቆይቷል፡፡ ትህነግ በሽምቅ ውጊያ በአካባቢው መንቀሳቀስ ከጀመረበት 1971/72ዓ.ም ጀምሮ በነባሩ የወልቃይት ጠገዴ የአማራ ህዝብ ላይ ጥቃት ሲያደርስበት ቆይቷል፡፡ ይህ ጥቃት በይበልጥ መዋቅራዊ ጉልበት ያገኘው የወልቃይት ጠገዴ ግዛት በጉልበት ወደ ትግራይ ከተጠቀለለ በኋላ ነው፡፡

ሕዝባችን በማንነቱ ብቻ ለሠላሳ ዓመታት በወያኔ አገዛዝ የዘር ማጥፋት ታውጆበት ሺህዎች በጅምላ ተገድለዋል፡፡ በርካቶች ወደ መቀሌና ወዳልታወቁ ስፍራዎች ታፍነው ተወስደው በእስር ሲማቅቁ ኑረዋል፡፡ በጥቅሉ በሠላሳ ዓመቱ የወያኔ አፓርታይዳዊ ዘመን አምስት መቶ ሺህ የሚደርስ ወገናችን ከወልቃይት ጠገዴ እንዲሰደድ ተደርጓል፡፡ ለብዙዎቹ ኢትዮጵያውያንና ዓለማቀፉ ማህበረሰብ ወልቃይት ላይ የደረሰው ግፍና በደል እምብዛም አይታወቅም፡፡ ይህ ከወያኔ የአፈና ሥርዓት ጋር የሚያያዝ ቢሆንም፣ ባለፉት ሠላሳ ዓመታት ዓለም ያልሰማው የዘርማጥፋት ወንጀል ተፈጽሞብናል፡፡ በወያኔ ስለመበደላችን ዓለም እንዲያውቅልን እንፈልጋለን፡፡
በቀጣይ ጊዜያት በውጭና በሀገር ውስጥ ልዩ ልዩ ቋንቋዎች ስለወልቃይት ጠገዴ የአማራ ሕዝብ ተጨባጭ ሁኔታዎች መረጃዎችን እናደርሳለን፡፡

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት
የወልቃይት-ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን አስተዳደር

ለባህርዳር ከነማ ስፖርት ክለብ 9 ሚሊየን ብር የሚገመት ባስ ተበረከተለት።የባህርዳር ከነማ ስፖርት ክለብ በ2010 ዓ.ም ወደፕሪሜር ሊግ ሲያልፍ የክልሉ መንግስት እንደ ወልደያ ከነማና ፋሲል...
02/06/2021

ለባህርዳር ከነማ ስፖርት ክለብ 9 ሚሊየን ብር የሚገመት ባስ ተበረከተለት።
የባህርዳር ከነማ ስፖርት ክለብ በ2010 ዓ.ም ወደፕሪሜር ሊግ ሲያልፍ የክልሉ መንግስት እንደ ወልደያ ከነማና ፋሲል ከነማ ሁሉ አንድ ቢሾፍቱ ባስ ለመግዛት ቃል ገብቶ እንደነበር የባህርዳር ከነማ ስፖርት ባህልና ቱሪዝም ስፖርት መምሪያ አስታውቋል።
ሆኖም በክልሉ ተከስቶ በነበረው አለመረጋጋትና በተለያዩ ምክንያቶች ሳይገዛ ቢቆይም የከነማው የሀብት አሰባሳቢ ኮሚቴ ስራ በመጀመሩ የክልሉ መንግስት ቃል በገባው መሰረት ለቢሾፍቱ ባስ መግዣ የሚውል 6.5 ሚሊየን ብር መስጠቱን የባህርዳር ከተማ ባህል ቱሪዝም ስፖርት መምሪያ ሀላፊ አቶ አብረሃም አዳሙ ተናግረዋል።
ነገር ግን የከተማ አስተዳደሩ ዘመናዊ ባስ ለመግዛት በመፈለጉ የክልሉ መንግስት ከሰጠው 6.5 ሚሊየን ብር ወ/ሮ ትልቅ ሰው ገዳሙ ቀሪውን በመጨመር ለህዝብ ማመላለሻ ከገዟቸው ዘመናዊ ባሶች ውስጥ 9 ሚሊየን ብር የሚገመት አንዱን ባስ ለባህርዳር ከነማ ስፖርት ክለብ ማበርከታቸው ተገልጿል።

በባህርዳር ከተማ በላይዘለቀ ክ/ከተማ ለጊዜው ምክንያቱ ባልታወቅ ባህርዳር ዩንቨርስቲ ፔዳ ግቢ አካባቢ ካሉ ኮንቲነሮች የእሳት አደጋ ተፈጥሮ የሳት አደጋ መኪናዎች እና ወጣቶች ርብርብ እያደረ...
25/05/2021

በባህርዳር ከተማ በላይዘለቀ ክ/ከተማ ለጊዜው ምክንያቱ ባልታወቅ ባህርዳር ዩንቨርስቲ ፔዳ ግቢ አካባቢ ካሉ ኮንቲነሮች የእሳት አደጋ ተፈጥሮ የሳት አደጋ መኪናዎች እና ወጣቶች ርብርብ እያደረጉ እንደሆነ ከአካባቢው የአገኘነው መረጃ ያመላክታል ።

ኢዜማ የተባለው ፓርቲ አዲስ አበባና መላው አማራ ሲመጣ "በዘር አላምንም ሀገራዊ ፓርቲ ነኝ" ሲልህ ይቆይና በጎን ደግሞ "ጉራጌ እራሱን በራሱ እንዲያስተዳድር ኢዜማን ይምረጡ ይላል።አማራ ላይ...
25/05/2021

ኢዜማ የተባለው ፓርቲ አዲስ አበባና መላው አማራ ሲመጣ "በዘር አላምንም ሀገራዊ ፓርቲ ነኝ" ሲልህ ይቆይና በጎን ደግሞ "ጉራጌ እራሱን በራሱ እንዲያስተዳድር ኢዜማን ይምረጡ ይላል።

አማራ ላይ ሲቀሰቅስ ደግሞ "ዘሬ ኢትዮጵያ ነው" ይለናል🤔🤔🤔

የሴካፋ ውድድር በአማራ ክልል አስተናጋጅነት በባሕር ዳር ዓለም አቀፍ ስታዲዬም እንደሚካሄድ ተገለፀ፡፡የምሥራቅ እና መካከለኛው የአህጉሪቱ ቀጠና ላይ የሚገኙ ብሔራዊ ቡድኖችን የሚያሳትፈው የሴ...
30/04/2021

የሴካፋ ውድድር በአማራ ክልል አስተናጋጅነት በባሕር ዳር ዓለም አቀፍ ስታዲዬም እንደሚካሄድ ተገለፀ፡፡

የምሥራቅ እና መካከለኛው የአህጉሪቱ ቀጠና ላይ የሚገኙ ብሔራዊ ቡድኖችን የሚያሳትፈው የሴካፋ ውድድር በየትኛው የኢትዮጵያ ከተማ እና መቼ እንደሚደረግ ታውቋል።

ከ1926 ዓ.ም ጀምሮ መደረግ የጀመረው የምሥራቅ እና መካከለኛው አፍሪካ ዋንጫ ውድድር የ2021 የውድድር ዓመት ፍልሚያውን እድሜያቸው ከ23 ዓመት በታች በሆኑ ተጫዋቾች በኢትዮጵያ አስተናጋጅነት እንዲከናወን መወሰኑ ይታወቃል።

ኢትዮጵያ የውድድሩ አዘጋጅ መሆኗ በተነገረበት ወቅት ደግሞ መቼ እና የት ከተማ እንደሚከናወን ሳይገለፅ አልፎ ነበር። አሁን ግን የውድድሩ አዘጋጆች ከሰኔ 26 እስከ ሐምሌ 11 /2013 ዓ.ም ድረስ ውድድሩ እንዲደረግ ጊዜያዊ ቀን መውጣቱ ታውቋል።

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ባህሩ ጥላሁን ፌዴሬሽኑ ይህንን ውድድር በባሕር ዳር ከተማ ለማድረግ ማሰቡን አስረድተውናል። ኃላፊው በክረምት ወር የሚደረገውን የቀጠናው ውድድር በደማቅ ሁኔታ ለማከናወን የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች እየተሠሩ መሆናቸውን ገልፀዋል።

ኢትዮጵያ ከዚህ ቀደም ይህንን ውድድር ለአራት ጊዜያት (1980፣ 1997፣ 1999 እና 2008) ዓመታት አዘጋጅታ እንደነበር ይታወሳል። ምንጭ:- የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን

AMC

 #ስግብግቡ አሽከርካሪ በባህርዳር ‼️በሀገራችን የተፈጠረውን የነዳጅ ችግርና የዋጋ መሻሻል ተከትሎ መንግስት ለተሳታፊዎች እና ለባለሀብቶች ተመጣጣኝ ዋጋ በማውጣት ወደስራ መግባቱ ይታወቃል ።...
10/03/2021

#ስግብግቡ አሽከርካሪ በባህርዳር ‼️

በሀገራችን የተፈጠረውን የነዳጅ ችግርና የዋጋ መሻሻል ተከትሎ መንግስት ለተሳታፊዎች እና ለባለሀብቶች ተመጣጣኝ ዋጋ በማውጣት ወደስራ መግባቱ ይታወቃል ።

ይህን ተከትሎ አንዳንድ #ስግብግብ የታክሲ አሽከርካሪዎች በህዝባችን ላይ ያለመጫን አድማ ማድረግ ጀምረዋል ።ለነገሩ "አይገርፉት ልጅ ሲቆጡት ያለቅሳል እንዲሉ ነው ነገሩ‼️" 50 ሳንቲም ሲጨመር አሽከርካሪዎች በራሳቸው መብት እጥፍ ይጨምራሉ።በአንድ ዙር 12 ሰው መጫን ሲገባቸው ስግብግቦች ግን ከ18_20 ሰው ይጭናሉ ፣ትራፊክ ፖሊስ ሲያዩ አውርደው መንገድ ላይ ይጥላሉ ።

ስግብግብ የታክሲ አሽከርካሪዎች ጥያቄያቸውን በሰለጠነ መንገድ በተወካያቸው በኩል መጠየቅ ሲችሉ ግዴታቸው የሁነውን ቀርቶ ደንበኛ የሆናቸውን ህዝብ በሰዓቱ ወደ ስራው፣ወደህክምና የሚሄደውን፣የፍርድ ቤት ቀጠሮ ያለበትን፣ወደ ት/ቤት የሚሄደው በማጉላላት ላይ ይገኙ ‼️

ስግብግቦች መብት አድርገው የጠየቁትን ህዝባችን ከታሪፍ ውጭ ሲከፍል፣የከፈለበትን ወንበር እንኳ ሌላ ሰው ደርበው ሲጭኑበት ይስተዋላል ።

ፍትህ ለሁሉም እኩል ነች ለነዋሪዎቿም ለባለአሽከርካሪዎችን‼️

_Thinkers

ላለፉት 30 አመታ የተዘረፍነው ፣የተገደልነው፣ማንነታችን የተነጠቅነው አይበቃም‼️ ማንነታችን ያስመለስነው በሺዎች በሚቆጠር የህይወት መሰዋትነት ነው።አብርሃ  ደስታ ከታች ያለው ህይወት የጠፋ...
03/03/2021

ላለፉት 30 አመታ የተዘረፍነው ፣የተገደልነው፣ማንነታችን የተነጠቅነው አይበቃም‼️ ማንነታችን ያስመለስነው በሺዎች በሚቆጠር የህይወት መሰዋትነት ነው።

አብርሃ ደስታ ከታች ያለው ህይወት የጠፋው እንደአንተ አይነት ወንበዴዎች ነው ለመሆኑ ኢትዮጵያን የት ታውቋትና ነው

27/02/2021

"የወልቃይት ጠገዴ ጠለምትና ራያ የአማራነት ጉዳይ ፋይሉ የተዘጋ ነው"

ክቡር አቶ አገኘሁ ተሻገር
የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳድር
--------

የኔ ፕሬዝዳንት የወልቃይትና ራያ አማራነት ጉዳይ ፋይሉ የተዘጋ እንደሆነ ይህን አጭርና ግልፅ የሆነ አቋም አስቀምጧል። እውነት ነው የወልቃይትና ራያ ጉዳይ ፋይሉ የተዘጋ ነው፤ እኔም የፕሬዝዳንቴን አቋም እደግፋለሁ።

የትህነግ ርዝራዦችና ተላላኪዎች ግን ዛሬም ትናንት ላይ ቆመው በማሰብ በወልቃይትና ራያ አማራነት ጉዳይ ስሁት መረጃና አጀንዳ እየሰጡ ሊያወናብዱን ብሎም አጀንዳ ሊያስቀይሩን ሲዳዳቸው ይስተዋላል።

ዳሩ ግን ወልቃይትና ራያ አማራ ነው! ወልቃይትና ራያ ወደ አማራዊ ማንነቱ እንዲመለስ ደግሞ ክቡር ፕሬዝዳንታችን እና መላ አመራሩ ዘመን የማይሽረው ታላቅ ታሪክ ሰርተዋል። ይህ የጀግንነት ገድላቸውም በአማራና በመላው ኢትዮጵያዊያን ልብ ዘንድ ታትሞ ይኖራል። ምክንያቱም የአማራን ልዩ ሀይልና ሚሊሻ እንዲሁም መላ ህዝባችንን አስተባብረው ጠላት ትህነግን ያሸነፉ ጀግኖች በመሆናቸውና አማራን ብሎም ኢትዮጵያን ከአምባ ገነኑ ስርዓት ነፃ ያወጡ በመሆናቸው ነው።

ስለ አማራ ልዩ ሀይል ገድልና ጀግንነት ስናነሳ ልዩ ሀይሉን እንዲሁም ሚሊሻውን በጥበብና በብስለት መርተው ድል ያደረጉ መሪዎቻችንን ልናስታውስና ልናወድስ የግድ ይለናል። መሪዎቻችን በአማራነት ወኔ እና ስነ ልቦና ውስጥ ሆነው የመሩት ጦር ክልላችንን ብሎም ሀገራችንን ከብተና ታድጓል። ስለሆነም እነዚህን መሪዎች ልናወድስና ልናመሰግን እንገደዳለን። ሩቅ ሳይሄድ የትናንቱን ማስታወስና መገንዘብ የሚችል አዕምሮ ያለው ሰው የሚሪዎችን ሚና በጉልህና በልኩ ማስቀመጥ ይችላል።

ይሁን እንጂ አንዳንድ የዋህ ወገኖቼ ዛሬም እንደ ትናንቱ የትህነግ ርዝራዦች የሚሰጧቸውን አጀንዳዎች እየተቀበሉ አብረው ሲያስተጋቡ ይስተዋላሉ። ትህነጋዊያን በስሁት መረጃና አጀንዳ ህዝብና ሀገር ሲያደናግሩ መቆየታቸው የቅርብ ትውስታ ነው። ዛሬም ርዝራዦችና አጋፋሪዎቻቸው ይሄን እያስቀጠሉ እንደሆነ መገንዘብ ያስፈልጋል።

ስለሆነም በማወቅም ይሁን ባለማወቅ በጠላት አጀንዳ እየተታለላችሁና እየተጠለፋችሁ የጠላትን አጀንዳ በማስተጋባት ዓላማቸውን ለማሳካት የምትደክሙ የኛ ሰዎች ከዚህ ድርጊታችሁ እንድትቆጠቡና በአንፃሩ ደግሞ ከመሪዎቻችን ጎን በመቆም የአማራን አንድነት በማጠናከር ታሪካዊ ሀላፊነታችሁን እንድትወጡ ለመምከር እወዳለሁ።

ቀጣይ ልንሰራው የሚገባ ጉዳይም ከወልቃይትና ራያ ለዘመናት ሲፈናቀል የነበረውን ህዝባችንን መልሶ የማቋቋም እና የማደራጀት ስራ መሆን ይገባል። ለዚህም ከመሪዎቻችን ጎም በአንድነት በመቆም ውጤታማ ማድረግ እንደሚኖርብንም መልዕክቴ ነው።

ዘንድሮ በጀግኖች መሪዎቻችን በአጤ ምኒሊክና በንግስት ዘውዲቱ የጥበብ መሪነት የተገኘውን 125ኛውን የአድዋ የድል በዓል ስናከብር ዛሬም በጀግኖች መሪዎቻችን በክቡር አቶ አገኘሁ ተሻገርና አመራራቸው የተገኘውን ታላቅ የነፃነት ድል ጭምር በማሰብ በድርብ ድል ውስጥ ሆነን ነው።

ለድርብ ድርብርብ የነፃነት በዓላችን እንኳን አደረሳችሁ!

via:

18/02/2021

#በተዘጋ _ቤት_በር ላይ ቁሞ እንዴት ዋላችሁ ማለት ሞኝነት ነው‼️ቴዎድሮስ አዳህኖም እርሙን አላወጣም እንዴ??

16/02/2021
22/01/2021
የባህር ዳር ከተማ ምክር ቤት አስቸኳይ የ1ቀን ስብሰባ ለነገ ጠርቷል የከንቲባ ሹመት ይደረጋል ተብሎ ይጠበቃል
15/10/2020

የባህር ዳር ከተማ ምክር ቤት አስቸኳይ የ1ቀን ስብሰባ ለነገ ጠርቷል የከንቲባ ሹመት ይደረጋል ተብሎ ይጠበቃል

Address


Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ባህርዳር መረጃ ማዕከል Bahirdar Media posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

  • Address
  • Alerts
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share