Mormor Media Amharic

  • Home
  • Mormor Media Amharic

Mormor Media Amharic Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Mormor Media Amharic, Media/News Company, .

07/11/2022
07/11/2022
የዛሬ ውሎ ❤ ጎቤ❤ሽኖዬ❤ሸገር ❤ቦሌ❤ስቴዲየም
08/09/2022

የዛሬ ውሎ ❤ ጎቤ❤ሽኖዬ❤ሸገር ❤ቦሌ❤ስቴዲየም

የጎቤ እና ሽኖዬ በዓል ሲከበር በሸገር።በምስል
07/09/2022

የጎቤ እና ሽኖዬ በዓል ሲከበር በሸገር።
በምስል

በአውስትራሊያ የ4 አመት ህፃን በድንገተኛ ህመም ለወደቀች እናቱ አምቡላንስ ደውሎ በመጥራት አድነቆት አተረፈ።ሞንቲ ኩከር የተባለ ህፃን እንዴት ወደ አምቡላንስ እንደሚደወል እናቱ ከመውደቋ አ...
07/09/2022

በአውስትራሊያ የ4 አመት ህፃን በድንገተኛ ህመም ለወደቀች እናቱ አምቡላንስ ደውሎ በመጥራት አድነቆት አተረፈ።

ሞንቲ ኩከር የተባለ ህፃን እንዴት ወደ አምቡላንስ እንደሚደወል እናቱ ከመውደቋ አንድ ቀን አስቀድማ ነው ያስተማረችው።

ህፃኑም ትናንት በተማረው መሰረት አምቡላንስ ጋር ደውሎ እናቴ ወድቃለች ድረሱላት ሲል ጥሪውን እንዳስተላለፈ ነው የተሰማው።

የአደጋ ጊዜ የጤና ሰራተኛ ማርክ እስሞል ስልኩ ከተደወለበት ስፍራ ስንደርስ ይህ ህፃን በመስኮን ቆሞ እጁን ስያውለበልብ ነበር ብሏል።

የአደጋ ጊዜ ቡድኑም እናቱ ካገገመች በኋላ ወደ ቤቷ በመመለስ የአደሰናቆት የምስክር ወረቀት ለህፃን ሞንቲ ኩከር መስጠታቸውን ቢቢሲ ዘግቧል።

ኬንያየኬንያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በሀገርቱ ምርጫ ውጤት ላይ የቀረበውን ክስ ውድቅ አደረገ።ፍርድ ቤቱ ዊሊያም ሩቶ በተገቢ መልኩ ነው የተመረጡት ብሏል።ሩቶ በሀገሪቱ በተደረገው ምርጫ 50.5 በ...
05/09/2022

ኬንያ

የኬንያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በሀገርቱ ምርጫ ውጤት ላይ የቀረበውን ክስ ውድቅ አደረገ።

ፍርድ ቤቱ ዊሊያም ሩቶ በተገቢ መልኩ ነው የተመረጡት ብሏል።

ሩቶ በሀገሪቱ በተደረገው ምርጫ 50.5 በመቶ የሚሆን ድምፅ መግኘታቸውን በመግለፅ የሀገሪቱን ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ማሸነፋቸውን የምርጫ ኮሚሽን መግለፁን ተከትሎ ነው ተቀናቃኛቸው ራይላ ኦዲንጋ የምርጫውን ውጤት በመቃወም ወደ ፍርድ ቤት ጉዳዩን የወሰዱት።

ይሁንና የሀገሪቱ ጠቅላይ ፍርድቤት የምርጫውን ውጤት ትክክለኝነት አረጋግጧል።

ስፖርት የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን አሸንፎ ለቻን ውድድር ማለፉ ለኢትዮጵያ ህዝብ የአዲስ አመት ስጦታ ነው ሲሉ የአትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት አቶ ኢሳያስ ጅራ ተናገሩ፡፡  ርዋንዳን...
05/09/2022

ስፖርት

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን አሸንፎ ለቻን ውድድር ማለፉ ለኢትዮጵያ ህዝብ የአዲስ አመት ስጦታ ነው ሲሉ የአትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት አቶ ኢሳያስ ጅራ ተናገሩ፡፡

ርዋንዳን በማሸነፍ በታሪክ ለሶስተኛ ጊዜ ወደ ቻን ውድድር ያለፈው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ትናንት ሌሊት አዲስ አበባ ሲገባ የፌዴሬሽኑ ፕሬዚዳንት፣ ምክትል ፕሬዚዳንት እና የስራ አስፈፃሚ አባላት አቀባበል አድርገውለታል፡፡

በአቀባበሉ ላይ ንግግር ያደረጉት አቶ ኢሳያስ ጅራ በማሸነፋችሁ ለኢትዮጵያ ህዝብ ትልቅ የአዲስ ዓመት ስጦታ አብርክታችኋል ብለዋል።

“ከሶስት ዓመት በፊት ከውድድሩ ያስቀረንን ቡድን ጥለን ማለፋችን ትርጉሙ ብዙ ነው” ያሉት ፕሬዚዳንቱ÷ ለቻን ውድድር ላለፈው ብሄራዊ ቡድን የማበረታቻ ሽልማት እንደሚኖር እና ቀኑ በፌዴሬሽኑ ተወስኖ የሚገለፅ መሆኑን አመላክተዋል፡፡

አልጄሪያ ላይ በሚደረገው ውድድር የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ ከወዲሁ መዘጋጀት ያስፈልጋል ሲሉ አቶ ኢሳያስ ማስገንዘባቸውን ፋና ብሮድካስት ዘግቧል፡፡

ጎቤና ሽኖዬየጎቤና ሽኖዬ ካርኒቫል በፊንፊኔ ሊደረግ መሆኑን የኦሮሚያ መንግሥት ኮሙኒኬሽን ቢሮ አስታወቀ።ቢሮው በፌስቡክ ገፁ እንዳለው፣ ካርኒቫሉ ለአራተኛ ዙር ከጳጉሜ 5 ጀምሮ ይካሄዳል።ጳጉ...
03/09/2022

ጎቤና ሽኖዬ

የጎቤና ሽኖዬ ካርኒቫል በፊንፊኔ ሊደረግ መሆኑን የኦሮሚያ መንግሥት ኮሙኒኬሽን ቢሮ አስታወቀ።

ቢሮው በፌስቡክ ገፁ እንዳለው፣ ካርኒቫሉ ለአራተኛ ዙር ከጳጉሜ 5 ጀምሮ ይካሄዳል።

ጳጉሜ 5 ከጠዋት ጀምሮበኦሮሞ ባህል ማእከል ቀጥሎም ከ7 ሰአት ጀምሮ ደግሞ በፊንፊኔ አውራጎዳናዎች ላይ እንደሚካሄድ ቢሮው አስታውቋል።

የካርኒቫሉ አላማ በፊንፊኔ ውስጥ ተረስቶ የቆየው የኦሮሞ ህዝብ ባህል መልሶ እንዲንሰራራ ማድረግ እንደሆነ ገልጿል።

ይህ የጎቤና ሽኖዬ ካርኒቫል ከጳጉሜ 1 እስከ መስከረም 7 በተለያዩ ትእይንቶች ይከበራል ብሏል የኮሙኒኬሽን ቢሮው።

ሀመር የአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ ልዑክ ማይክ ሐመር በድጋሚ ወደ ኢትዮጵያ እሁድ ሊመጡ ነው ተባለ።ከአንድ ወር በፊት አዲስ ኢትዮጵያ የነበሩት ማይክ ሐመር በድጋሚ የሚመጡት ከሰሜን ኢትዮጵ...
03/09/2022

ሀመር

የአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ ልዑክ ማይክ ሐመር በድጋሚ ወደ ኢትዮጵያ እሁድ ሊመጡ ነው ተባለ።

ከአንድ ወር በፊት አዲስ ኢትዮጵያ የነበሩት ማይክ ሐመር በድጋሚ የሚመጡት ከሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት ጋር በተያያዙ ጉዳዮች ላይ ለመምከር እንደሆነ ተገልጿል።

ልዩ መልእክተኛው የአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ሆነው ባለፈው ግንቦት ወር ከተሾሙ በኃላ ሁለት ጊዜ ወደ ኢትዮጵያ መምጣታቸው ይታወሳል።

01/08/22ጎርባቼቭየመጨረሻው የሶቪየት ህብረት ፕሬዚዳንት ሚካኤል ጎርባቼቭ ስርኣተቀብር እየተደረገ ነው።ጎርባቼቭ በምእራቡ አለምና በምስራቁ መካከል የነበረውን ቀዝቃዛ ጦርነት መቋጫ በመስጠ...
03/09/2022

01/08/22
ጎርባቼቭ

የመጨረሻው የሶቪየት ህብረት ፕሬዚዳንት ሚካኤል ጎርባቼቭ ስርኣተቀብር እየተደረገ ነው።

ጎርባቼቭ በምእራቡ አለምና በምስራቁ መካከል የነበረውን ቀዝቃዛ ጦርነት መቋጫ በመስጠት ነው የሚታወቁት።

በሶቪየት ህብረት ሪፎርም በማድረግና ህብረቱን ለአለም ክፍት አድርገዋል በሚል በምእራቡ አለም ይሞገሳሉ ጎርባቼቭ።

ይሁንና ያወጁት ሪፎርም የኢኮኖሚ ቀውስ አስከትሏል፣ ህብረቱንም ከመበተን አላዳኑም በሚል በሀገራቸው በስፋት ይተቻሉ እኚህ ሰው።

እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ1985 ወደ ስልጣን የመጡት ሚካኤል ጎርባቼቭ በ91 አመታቸው አርፈዋል።

በሞስኮ በሽኝት ፕሮግራማቸው የሀገርቱ ዜጎች የተገኙ ሲሆን ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑትን ግን አልተገኙም ይላል የቢቢሲ ዘገባ።

አሜሪካና ብሪታንያ በሰሜን ኢትዮጵያ የተቀሰቀሰው ጦርነት እንዲቆም ጥሪ አደረጉ።የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን የኢትዮጵያ መንግስትና ህወሃት የጦርነት ዘመቻን በአፋጣኝ እንዲያ...
01/09/2022

አሜሪካና ብሪታንያ በሰሜን ኢትዮጵያ የተቀሰቀሰው ጦርነት እንዲቆም ጥሪ አደረጉ።

የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን የኢትዮጵያ መንግስትና ህወሃት የጦርነት ዘመቻን በአፋጣኝ እንዲያቆሙ ጠይቀዋል።

መንግስትም ሆነ አማፂ ቡድኑ ጦርነቱን በዘላቂነት ለማቆም የሚደረገውን ጥረት እንዲያጠናክሩም ጠይቀዋል።

የብሪታንያ አፍሪካ ጉዳዮች ሚኒስትር ቪኪ ፎርድ በበኩላቸው በወጡት መግለጫ በሰሜን ኢትዮጵያ በኢትዮጵያ መንግስትና በህወሓት መካከል ጦርነት ዳግም መቀስቀሱ ለኢትዮጵያ ህዝብ ትልቅ አደጋ ነው ብለዋል።

ውይይት ከተደረገ ወደሰላም መመለስ እንደሚቻል እምነታቸው መሆኑን ሚኒስትሯ ገልፀዋል።

የራሺያው ግዙፉ የነዳጅ ዘይት ድርጅት ሉኮይል ሊቀመንበር ራቪል ማጋኖቭ በሞስኮ ከሆስፒታል መስኮት ላይ ከወድቁ በኋላ ህይወታቸው ማለፉ ተነገረ።የሚመሩት ድርጅትም መሞታቸውን አረጋግጧል።ነገር ...
01/09/2022

የራሺያው ግዙፉ የነዳጅ ዘይት ድርጅት ሉኮይል ሊቀመንበር ራቪል ማጋኖቭ በሞስኮ ከሆስፒታል መስኮት ላይ ከወድቁ በኋላ ህይወታቸው ማለፉ ተነገረ።

የሚመሩት ድርጅትም መሞታቸውን አረጋግጧል።

ነገር ግን የ67 አመቱ ማጋኖቭ "በከባድ ህመም ምክንያት ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል" ብሏል።

ግለሰቡ በሞስኮ ሴንትራል ክሊኒካል ሆስፒታል ህክምና እየተደረገላቸው እንደነበረና በደረሰባቸው ጉዳት ህይወታቸው ማለፉን የራሺያ ሚዲያ ዘግቧል።

ማጋኖቭ ሚስጥራዊ በሆኑ ሁኔታዎች ውስጥ ከሞቱት በርካታ የራሺያ ከፍተኛ የንግድ ሥራ አስፈፃሚዎች ውስጥ የቅርብ ጊዜ ሆነዋል ነው የተባለው።

መርማሪ ባለስልጣናት ራቪል ማጋኖቭ እንዴት እንደሞቱ ለማወቅ በቦታው ላይ እየሰሩ መሆናቸውን ተናግረዋል።

የታስ የዜና ወኪል ምንጮቹን ጠቅሶ ግለሰቡ ከስድስተኛ ፎቅ መስኮት መውደቃቸውን ዘግቧል።

በአሜሪካ ሰሜን ካሮላይና በሚገኘው አውሮፕላን ማረፊያ በአንድ አውሮፕላን ላይ የተለየ ጠረን በመስተዋሉ አምስት የእሳት አደጋ ጊዜ ተሽከርካሪዎች ከተሰማሩ በኋላ ነገሩ የጥፍር ቀለም ሆኖ ተገኘ...
01/09/2022

በአሜሪካ ሰሜን ካሮላይና በሚገኘው አውሮፕላን ማረፊያ በአንድ አውሮፕላን ላይ የተለየ ጠረን በመስተዋሉ አምስት የእሳት አደጋ ጊዜ ተሽከርካሪዎች ከተሰማሩ በኋላ ነገሩ የጥፍር ቀለም ሆኖ ተገኘ።

ጉዳዩ እንዲህ ነው። ንብረትነቱ የአሜሪካ አየር መንገድ የሆነው አውሮፕላን ከፊላዴልፊያ ተነስቶ ትናንት ሸርለት ዳግላስ አለምአቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ያርፋል።

መንገደኞችም እንደወትሮው ይወርዳሉ።

የአውሮፕላን ማረፊያው ሰራተኞችም የመንገደኞችን እቃ ማውረድ ይጀምራሉ።

የአውሮፕላኑ የመንገደኞች እቃ ማስቀመጫ ክፍል ሲከፈት ግን የተለያ ጠረን አፍንጫ ይገባል።

በጉዳዩ የተጠራጠሩ ሰራተኞች ሪፖርት ያደርጋሉ።

የሸርለት የእሳት አደጋ ጊዜ ዲፐርትሜንትም ወዲያው አምስት የእሳት አደጋ ጊዜ ተሽከርካሪዎችን ከነሰራተኞች ያሰማራል።

ሰራተኞቹ ሲፈትሹ የተለያ ጠረን ያስከተለውን ነገር ያገኛሉ።

እሱም የሴቶች ጥፍር ቀለም ብልቃጥ በአንዷ መንገደኛ ቦርሳ ውስጥ ተሰብሮ ቀለሙ በመፍሰሱ የተከሰተ ጠረን ሆኖ ተገኝቷል።

አውሮፕላኑ ከዚያ በኋላ ነው ወደ አገልግሎቱ የተመለሰው።

ዘገባውን ከዩፒኣይ ድረገፅ ነው ያገኘነው።

የዋጋ ግሽበትየኬንያ የዋጋ ግሽበት በነሀሴ ወር ወደ 8.50 በመቶ ማሻቀቡ ተገለፀ።ይህም ከመስከረም 2021 ወዲህ ከፍተኛው ነው ተብሏል።የኬንያ ብሄራዊ ስታትስቲክስ ቢሮ እንዳለው በኬንያ ከየ...
01/09/2022

የዋጋ ግሽበት

የኬንያ የዋጋ ግሽበት በነሀሴ ወር ወደ 8.50 በመቶ ማሻቀቡ ተገለፀ።

ይህም ከመስከረም 2021 ወዲህ ከፍተኛው ነው ተብሏል።

የኬንያ ብሄራዊ ስታትስቲክስ ቢሮ እንዳለው በኬንያ ከየካቲት ወር ጀምሮ የዋጋ ግሽበት ለተከታታይ ስድስት ዘራት ተመዝግቧል።

የምግብ እና አልኮሆል ያልሆኑ መጠጦች ዋጋ መጨመር የዋጋ ግሽበቱን አባብሷል ነው ያለው።

በአፍሪካ ቀንድ ሀገራት የዋጋ ግሽበት ዜጎችን ለከፋ ሁኔታ እያጋለጠ መሆኑ ተመላክቷል።

ዘገባውን ከቢዝነስ እንሳደር አፍሪካ ነው ያገኘነው።
https://amharic.mormormedia.com/%e1%8b%a8%e1%8a%ac%e1%8a%95%e1%8b%ab-%e1%8b%a8%e1%8b%8b%e1%8c%8b-%e1%8c%8d%e1%88%bd%e1%89%a0%e1%89%b5-%e1%8a%a0%e1%88%bb%e1%89%80%e1%89%a0/

በምስራቃዊ ኮንጎ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ከሚገኝ እስር ቤት ከመለጡ ከ822 በላይ እስረኞች መካከል ከ250 በላይ በጸጥታ ሃይሎች መያዛቸውን የሀገሪቷ ባለስልጣናት አስታወቁ።የመንግስት ሃይሎች ...
12/08/2022

በምስራቃዊ ኮንጎ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ከሚገኝ እስር ቤት ከመለጡ ከ822 በላይ እስረኞች መካከል ከ250 በላይ በጸጥታ ሃይሎች መያዛቸውን የሀገሪቷ ባለስልጣናት አስታወቁ።

የመንግስት ሃይሎች በቡተምቦ ከሚገኘው የካኩዋንጉራ ማእከላዊ እስር ቤት ያመለጡትን ቀሪ እስረኞችን እያደኑ መሆኑ ተነግሯል።

ታጣቂዎች በእስርቤቱ ላይ ረቡዕ ጥቃት በመፈፀም እስረኞችን ማስመለጣቸውን ነው ቢቢሲ የዘገበው።

80 የሚሆኑ ታጣቂዎች የከፈቱትን ጥቃት እስርቤቱን ስጠብቁ የነበሩ 15 ፖሊሶች መቋቋም ስላልቻሉ ታጣቂዎቹ እስረኞችን ማስመለጥ እንደቻሉ ተዘግቧል።

የመንግሥት ሃይሎች ጥቃቱን የፈፀመው ከኣይኤስ ጋር ግንኙነት ያለው ቡድን መሆኑን ገልፀዋል።

የአይኤስ ቡድንም ከጥቃቱ ጀርባ እጁ እንዳለበት አምኗል።

በማረሚያ ቤቱ ሁለት ፖሊሶች መገደላቸውን እና በኋላም ሶስት የጥቃት አድራሹ ቡድን አባላት ናቸው ተብለው የተጠረጠሩ ሰዎች በአካባቢው ህዝብ መገደላቸውን ባለስልጣናት ተናግረዋል።

በደቡብ አፍሪካ ክሩገር ብሔራዊ ፓርክ ከ100 በላይ ጥንብ አንሳዎች እና ጅብ ሞተው መገኘታቸው ተሰማ።ጥንብ አንሳዎች እና ጅቡ የሞተን ጎሽ በመመገብ ሳይሞቱ እንዳልቀረ ባለሥልጣናት ተናግረዋል...
12/08/2022

በደቡብ አፍሪካ ክሩገር ብሔራዊ ፓርክ ከ100 በላይ ጥንብ አንሳዎች እና ጅብ ሞተው መገኘታቸው ተሰማ።

ጥንብ አንሳዎች እና ጅቡ የሞተን ጎሽ በመመገብ ሳይሞቱ እንዳልቀረ ባለሥልጣናት ተናግረዋል።

በጥበቃ ላይ ያሉ ጠባቂዎች በአቅራቢያው የተመረዘ የሚመስል የጎሽ ሬሳ እንዳገኙ ነው የተነገረው።

ከሞቱት ውጭ 20 ተጨማሪ ጥንብ አንሳዎች በቦታው ታመው የተገኙ ሲሆን ለህክምና ወደማገገሚያ ጣቢያ ተወስደዋል ነው የተባለው።

የደቡብ አፍሪካ ብሄራዊ ፓርኮች ባለስልጣን ጉዳዩ ለምርመራ ወደ ፖሊስ መላኩን አስታውቋል።

የኤሎን ማስክ 6.9 ቢሊየን ዶላር የቴስላ አክሲዮኖችን መሸጥ የኤሌክትሪክ መኪና አምራቹ ካምፓኒ ቴስላ ሃላፊ ኤሎን ማስክ 6.88 ቢሊዮን ዶላር የሚጠጋ 7.92 ሚሊዮን አክሲዮኖችን መሸጡ ተነ...
11/08/2022

የኤሎን ማስክ 6.9 ቢሊየን ዶላር የቴስላ አክሲዮኖችን መሸጥ

የኤሌክትሪክ መኪና አምራቹ ካምፓኒ ቴስላ ሃላፊ ኤሎን ማስክ 6.88 ቢሊዮን ዶላር የሚጠጋ 7.92 ሚሊዮን አክሲዮኖችን መሸጡ ተነግሯል።

ሽያጩ ባለፈው ሳምንት ከድርጅቱ ዓመታዊ የባለአክሲዮኖች ስብሰባ በኋላ መካሄዱን የቁጥጥር ሰነዶች ያሳያሉ።

ቢሊየነሩ ኤሎን መስክ ትዊተርን ለመግዛት ተስማምቶ የነበረ ሲሆን፣ ከስምምነቱ አወጣለሁ ካለ በኋላ ጉዳዩ ፍርድቤት ሆዷል።

ባለሀብቱ ትዊተርን በ44 ቢሊዮን ዶላር ለመግዛት ከተገደደ ገንዘቡ እንደሚያስፈልገው ተናግሯል።

በፈረንሳይ ቦርዶ አካባቢ የተነሳውን ሰደድ እሳት ለማጥፋት የእሳት አደጋ ሰራተኞች እየተረባረቡ መሆኑ ተሰማ።ቢቢሲ እንደዘገበው ከአንድ ሺ በላይ የሚሆኑ የእሳት አደጋ ሰራተኞች የሰደድ እሳቱን...
11/08/2022

በፈረንሳይ ቦርዶ አካባቢ የተነሳውን ሰደድ እሳት ለማጥፋት የእሳት አደጋ ሰራተኞች እየተረባረቡ መሆኑ ተሰማ።

ቢቢሲ እንደዘገበው ከአንድ ሺ በላይ የሚሆኑ የእሳት አደጋ ሰራተኞች የሰደድ እሳቱን ለመቆጣጠር እየጣሩ ነው።

በአካባቢው ያለው ከባድ ንፋስና ሙቀት እሳቱን ለመቆጣጠር የሚደረገውን እንቅስቃሴ እያስተጓጎለ ነው ተብሏል።

በደቡብ ምእራብ ፈረንሳይ የተነሳው የሰደድ እሳት በ7 ሺ ሄክታር መሬት ላይ ጉዳት ማድረሱ ነው የተነገረው።

በቦርዶ ከተማ አካባቢ የተቀሰቀሰው ሰደድ እሳት ከ10 ሺ በላይ የሚሆኑት ነዋሪዎች ከቤታቸው እንዲሸሹ ማድረጉን የአካባቢው ባለስልጣናት ተናግረዋል።

የጉራጌ ዞን ምክርቤት ዞኑን በአዲሱ ክላስተር ከሌሎች ዞን ጋር በክልልነት ለማደራጀት የቀረበውን ረቂቅ ሃሳብ ውድቅ ማድረጉ ተሰማ።ምክርቤቱ በ52 ተቃውሞና 40 የድጋፍ ድምፅ ውድቅ ማድረጉ ነ...
11/08/2022

የጉራጌ ዞን ምክርቤት ዞኑን በአዲሱ ክላስተር ከሌሎች ዞን ጋር በክልልነት ለማደራጀት የቀረበውን ረቂቅ ሃሳብ ውድቅ ማድረጉ ተሰማ።

ምክርቤቱ በ52 ተቃውሞና 40 የድጋፍ ድምፅ ውድቅ ማድረጉ ነው የተሰማው።

የጉራጌ ዞን ለብቻ ሆኖ በክልልነት ለመደራጀት ፊላጎት እንዳለው ሲገለፅ ቆይቷል።

መንግሥት በደቡብ ክልል ያሉትን ራስን በራስ የማስተዳደርና በክልልነት የመደራጀት ጥያቄን ተከትሎ በክላስተር በመከፋፈል በክልልነት የማደራጀት እንቅስቃሴ ላይ እንደሆነ መረጃዎች ያሳያሉ።

በኬንያ ትናንት በተደረገው ምርጫ ሁለቱ ግንባርቀደም ተፎካካሪዎች በተቀራራቢ ድምፅ እየተፎካከሩ መሆኑ ተሰማ።ትናንት የተሰጠው የመራጮች ድምፅ እየተቆጠረ ሲሆን እስከአሁን ከ90 በመቶ በላይ ድ...
11/08/2022

በኬንያ ትናንት በተደረገው ምርጫ ሁለቱ ግንባርቀደም ተፎካካሪዎች በተቀራራቢ ድምፅ እየተፎካከሩ መሆኑ ተሰማ።

ትናንት የተሰጠው የመራጮች ድምፅ እየተቆጠረ ሲሆን እስከአሁን ከ90 በመቶ በላይ ድምፅ ተቆጥሮ ውጤቱ በየምርጫ ጣቢያ መለጠፉ ተዘግቧል።

በዚሁ መሰረት ዊሊያም ሩቶና ራይላ ኦዲንጋ በጠባብ ልዩነት እየተፎካከሩ ነው ተብሏል።

አጠቃላይ የምርጫ ውጤት ለማወቅ ረዥም ቀናት ሊወስድ እንደሚችል ተነግሯል።

ለምርጫ የወጣ ሰው ቁጥር 60 በመቶ እንደነበረ የተገለፀ ሲሆን፣ ይህም በሀገሪቱ ከአምስት አመት በፊት ከተደረገው ምርጫ ያነሰ ነው ተብሏል።

ከአምስት አመት በፊት በተደረገው ምርጫ የመራጮች ቁጥር 80 በመቶ እንደነበረ ቢቢሲ አስታውሷል።

11/08/2022
በአሜሪካ ሚኒሶታ የኦሮሞ ማህበረሰብ ህብረት ሊቀመንበር ሆነው ለረዥም አመታት ያገለገሉ አቶ ተሽቴ ዋቆ የብሩክሊን ፓርክ ከተማ ምክርቤት ሆነው ተመረጡ።አቶ ተሽቴ ዋቆ በሚኒሶታ የሚኖሩ የኦሮሞ...
10/08/2022

በአሜሪካ ሚኒሶታ የኦሮሞ ማህበረሰብ ህብረት ሊቀመንበር ሆነው ለረዥም አመታት ያገለገሉ አቶ ተሽቴ ዋቆ የብሩክሊን ፓርክ ከተማ ምክርቤት ሆነው ተመረጡ።

አቶ ተሽቴ ዋቆ በሚኒሶታ የሚኖሩ የኦሮሞ ተወላጆች ህብረትን ለረዥም አመታት በመምራት ጠንካራ መሰረት እንዳስያዙ ነው የሚነገረው።

አሁን ደግሞ ለብሩክሊን ፓርክ ከተማ ምክርቤት ተወዳድረው አሸናፊ ሆነዋል።

በሌላ ዜና የዴሞክራቶችን ፓርቲ በመወከል ለአሜሪካ ኮንግረስ ስትወዳደር የነበረችው አማኔ በዳሶ ድል እንዳልቀናትም።

ዴሞክራቶቹን በመወከል ተፎካከሪዋ በነበረችው ቤቲ ማክኮለም ተሸንፋ ከውድድሩ ውጭ ሆናለች።

የምርጫው ውጤት ይፋ ከተደረገ በኋላ አማኔ በዳሶ ተፎካካሪዋ ለነበረችው ቤቲ ማክኮለም የእንኳን ደስ አለሽ መልእክት አስተላልፋለች።

Address


Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Mormor Media Amharic posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

  • Address
  • Alerts
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share