Menz mama prosperity/መንዝ ማማ ብልፅግና

  • Home
  • Menz mama prosperity/መንዝ ማማ ብልፅግና

Menz mama prosperity/መንዝ ማማ ብልፅግና የብልፅግና እሳቤዎችና ክዋኔዎች እንዲሁም የወረዳው ሁኔታ ይ?

10/07/2023

የሰሜን ሸዋ ዞን አስተዳደር አስተባባሪ አመራር ለሸዋሮቢት ከተማና ለቀወት ወረዳ አስተዳደር ለተለያዩ የኃላፊነት ቦታዎች ከሐምሌ 3 ጀምሮ ሹመት ሰጠ።

በዚህም መሠረት :-

ለሸዋሮቢት ከተማ አስተዳደር

1. አቶ ውብሸት ዘነበ .... የሸዋሮቢት ከተማ አስተዳደር ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ፅ/ቤት ኃላፊ

2. አቶ ኑራሁሴን ኢብራሒም ... ምክትል ከንቲባና የገቢዎች ፅ/ቤት ኃላፊ

ለቀወት ወረዳ

1. አቶ ወንድማገኝ ትርፌ .... የቀወት ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ

2. አቶ ነሲቡ ሞገስ ... ምክትል አስተዳዳሪና ገንዘብ ፅ/ቤት ኃላፊ

3. አቶ ኃይለማርያም አጥላው ... የቀወት ወረዳ ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ፅ/ቤት ኃላፊ

ሆነው መሾማቸውን አሳውቋል።

10/07/2023
10/07/2023

ሰላም የሁሉን ተሳትፎ የሚጠይቅ፣በሰከነ ንግግርና ትምምን የሚፀና፣የመልካም ነገሮች ሁሉ መሰረት የሆነ፣የህብረተሰብ የወል ሀብት ነው።

ለሰላማችን በጋራ እንትጋ።

~~~
"የጎሃ ቃልኪዳናችን የከፍታችን ልክ -ቃላችንን ፈፅመን ከፍታው ላይ እንገናኝ"
~~~
ለወቅታዊ ፣ ትክክለኛና አዳዲስ መረጃዎች የፓርቲያችንን የማህበራዊ ገፆች ይወዳጁ።

ቴሌግራም፦

https://t.me/shewaprosperity

ፌስቡክ

https://www.facebook.com/profile.php?id=100064788996103

ቲዊተር፦
https://twitter.com/ShewaNorth?s=09

ቲክቶክ
https://www.tiktok.com/?_t=8dEh8MoumH7&_r=1

ዩቲዩብ
https://youtube.com/

"  ሁለተኛ  ትዉልድ ጤና ኤክስቴንሽ መፍጠር በሚል ሀሳብ ላይ   ለሴት ልማት ቡድን አመራሮች ለ14 ቀን ሲሰጥ የነበረዉስልጠና ተጠናቀቀ::       የመንዝ ማማ ምድር ወረዳ ጤና ጥበቃ ፅ/...
09/07/2023

" ሁለተኛ ትዉልድ ጤና ኤክስቴንሽ መፍጠር በሚል ሀሳብ ላይ
ለሴት ልማት ቡድን አመራሮች ለ14 ቀን ሲሰጥ የነበረዉ
ስልጠና ተጠናቀቀ::
የመንዝ ማማ ምድር ወረዳ ጤና ጥበቃ ፅ/ቤት በ19 የገጠር ቀበሌ ያሉ የሴት ልማት ቡድን አመራሮችን ለተከታታይ 14 ቀን በጤናዉ ዘርፍ በቀበሌ ጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያና በክላሰተር ባሉ የጤና ባለሙያዎች ሲሰለጥኑ ቆይተዋል:: የሰለጠኑትም "ሁለተኛ ትዉልድ ጤና እክስቴንሽን መፍጠር በሚል ሲሆን ይህን ስልጠና ቀድመዉ የጀመሩ ቀበሌዎች ማለትም በጤናዉ ዘርፍ ሰልጠናቸዉን ያጠናቀቁት ከ018;017;02; 020;ከ019 ;014ቀበሌ በመቀጠል ያጠናቀቀዉ 011 ቀበሌ ሲሆን እነዚህ የሰለጠኑ ሴት ልማት ቡድን አመራሮች ራሳቸዉ ሞዴል በመሆን ለሌሎቹ ግንባር ቀደም ተዋናይዎች መሆናቸዉን በመግለፅ ምርቃቱየተጠናቀቀ ቢሆንም በዚህ ምርቃት ላይ የተገኙት አቶ በሻህ ገ/እግዚያብሔርጰየመንዝ ማማ ምድር የወረዳዉ ም/አስተዳዳሪና የሰራና ስልጠና ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ በረደድ በላይሁን የወረዳዉ ጤና ኤክስቴንሽን አስተባባሪ አቶ በኩራት አስራት የባሽ ጤና ጣቢያ ሀላፊ አቶ ዱባለ ጌታነህ የቀበሌዉ ደጋፊና የወረዳዉ ወጣት ሊግ ም/ሀላፊ በመገኘት ያስመረቁ ሲሆን በዚህ የስልጠና ማጠቃለያ ቀን የተገኙት አቶ በሻህ ገ/እግዚያብሔር ጤናዉ የተጠበቀ ማህበረሰብ ለመፍጠር ሴቶች አመራሮቻችን ግንባር ቀደም ተዋናዮች ናቸዉ በማለት እና ለሰለጠኑት አመራሮች የመፈፀምና አቅማችሁን በማሳደግ ሌሎችን መለወጥ ያሰፈልጋል የሚል ተልዕኮ በመስጠት የምረቃ ሰነ ስረአቱ ተጠናቋል::

የመንዝ ማማ ምድር ወረዳ ብልፅግና ፓርቲ ፅ/ቤት
መንዝ ማማ ዲጂታል ባለሙያ !!

09/07/2023

በአንድ ጀምበር 500 ሚሊዮን ችግኞች እንደ ሀገር-ሀምሌ 10 ቀን 2015 ዓ.ም

ኢትዮጵያዊያን ተባብረን እናለማለን ኢትዮጵያችንም አረንጓዴ ሙሽራ ትሆናለች።

ሀምሌ 10 ቀን 2015 ዓ.ም እንደ ሃገር 500 ሚሊዮን ችግኞች ይተከላሉ።በሰሜን ሸዋ ዞን አስተዳደርም በእለቱ 49 ነጥብ 8 ሚሊዮን ችግኞች ይተከላሉ።

ኢትዮጵያን በተባበረ ክንድ አረንጓዴ አሻራ እናለብሳታለን።

~~~
"የጎሃ ቃልኪዳናችን የከፍታችን ልክ -ቃላችንን ፈፅመን ከፍታው ላይ እንገናኝ"
~~~
ለወቅታዊ ፣ ትክክለኛና አዳዲስ መረጃዎች የፓርቲያችንን የማህበራዊ ገፆች ይወዳጁ።

ቴሌግራም፦

https://t.me/shewaprosperity

ፌስቡክ

https://www.facebook.com/profile.php?id=100064788996103

ቲዊተር፦
https://twitter.com/ShewaNorth?s=09

ቲክቶክ
https://www.tiktok.com/?_t=8dEh8MoumH7&_r=1

ዩቲዩብ
https://youtube.com/

የመንዝ ማማ ምድር ወረዳ ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት የ2015 ዓ.ም የክረምት ወራት የወጣቶች በጎ ፈቃድ አገልግሎት ማስፈፀሚያ ዕቅድ ላይ ከስትሪንግ ኮሚቴው ጋር ውይይት አደረገ።በሰሜን ሸዋ ዞ...
08/07/2023

የመንዝ ማማ ምድር ወረዳ ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት የ2015 ዓ.ም የክረምት ወራት የወጣቶች በጎ ፈቃድ አገልግሎት ማስፈፀሚያ ዕቅድ ላይ ከስትሪንግ ኮሚቴው ጋር ውይይት አደረገ።

በሰሜን ሸዋ ዞን መንዝ ማማ ምድር ወረዳ የባለፈው አመት የክረምት በጎ ፍቃድ ስራዎች በጥንካሬና በእጥረት በዝርዝር የገመገመ ሲሆን በያዝነው የክረምት ወራት ከ 23ሺህ በላይ ወጣቶች በበጎ ፈቃድ አገልግሎት ይሰማራሉ ተብሏል።
በውይይቱ የማስፈፀሚያ ዕቅዱ ቀርቦ ውይይት የተደረገበት ሲሆን በአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ፣ የአረጋውያን ቤት ግንባታና እድሳት ፣ የማጠናከሪያ ትምህርት፣ የደም ልገሳና ሌሎች አስራ ሁለት የሚሆኑ አገልግሎቶች ላይ ያተኮረ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት እደታቀደ ተገልጿል።

"መፍጠንና መፍጠር የወል እውነቶችን የማፅናት ቀጣይ የትግል ምዕራፍ " በሚል  መሪ ቃል  በመንዝ ማማ ምድር ወረዳ ስር ባሉ ቀበሌዎች  የብልፅግና ፓርቲ አርሶ አደር አባላት  ስልጠና ተሰጠ።...
07/07/2023

"መፍጠንና መፍጠር የወል እውነቶችን የማፅናት ቀጣይ የትግል ምዕራፍ " በሚል መሪ ቃል በመንዝ ማማ ምድር ወረዳ ስር ባሉ ቀበሌዎች የብልፅግና ፓርቲ አርሶ አደር አባላት ስልጠና ተሰጠ።

ስልጠናው በወረዳዉ በሚገኙ 19 የገጠር ቀበሌዎች ላይ የተካሄደ ሲሆን ስልጠናውን ምድብተኛ አመራሮችና የቀበሌ አስተዳዳሪዎች በጋራ እና መሰል የቀበሌ ኮር አመራሮች አሰልጥነዋል::

በዚህም ስልጠናው በየደረጃው ላሉ የፓርቲያችን አባላት እንዲሁም በመላው ህዝባችን ደረጃ ወጥ የሆነ አመለካከትና አረዳድ እንዲሁም ተቃራራቢ የመፈፀም አቅምን ለማጎልበት አቅምን የፈጠረ እና ከግለስብ ይልቅ የዉል እወነቶች ላይ የተኮረ ስልጠና ነዉ::ስለሆነም በወረዳዉ ስር ያሉ የቀበሌ አ/ አደር አባላት ለራስ አቅምን በመፍጠር ለትዉልድ የምትሻገር ኢትዮጲያን የማፅናት መሰረረትን ተክለዉ እንደሚሄዱ በመገለፅ ስልጠናዉ በሁሉም የገጠር ቀበሌዎቻችን በስኬትና የሚፈለገዉን ግብ በማምጣት ተጠናቋል::


"የጎሃ ቃልኪዳናችን የከፍታችን ልክ - ቃላችንን ፈፅመን ከፍታው ላይ እንገናኝ"
የመንዝ ማማ ምድር ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት
ⓜⓐⓜⓐ ⓟⓡⓞⓢⓟⓔⓡⓣⓘⓨ 𝓹𝓪𝓳𝓽𝓼

05/07/2023
"መፍጠንና መፍጠር የወል እውነቶችን ማፅናት ቀጣይ የትግል ምዕራፍ " በሚል ርዕስ የየመንዝ ማማ ምድር ወረዳ ብልፅግና ፓርቲ አባል ለሆኑ የሴክተር  መንግስት ሰራተኞች  ሲሰጥ የነበረው ስልጠ...
05/07/2023

"መፍጠንና መፍጠር የወል እውነቶችን ማፅናት ቀጣይ የትግል ምዕራፍ " በሚል ርዕስ የየመንዝ ማማ ምድር ወረዳ ብልፅግና ፓርቲ አባል ለሆኑ የሴክተር መንግስት ሰራተኞች ሲሰጥ የነበረው ስልጠና ተጠናቀቀ።
=======================
የስልጠናውን ማጠቃለያ የሰጡት የመንዝ ማማ ምድር ወረዳ ብልፅግና ፓርቲ አደረጃጀት ዘርፍ ሀላፊ አቶ ደመቀ ማሙሻ አቶ መርሻ ሁይሉ የወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ መርሻ ሀይሉ አባሉ ላነሳዉ ጥያቄ ምላሽ በመስጠትና የቀጣይ ስራዎችን ስምሪት ተሰጥቷል::
ይህ ስልጠና አስፈላጊነቱ ሀገራችን የገጠማትን የዉስጥና የዉጪ ችግሮችን በመጋፈጥ መፍትሔ የሚሰጥ ፣የሀገራችንን የፖለቲካ ብልሽት ለመለየት እንዲሁም ብልፅግናን እውን በሚያደርግ በአካባቢያችን የሚታዩ የሰላም ችግሮችን በውይይትና በምክክር አንድ ሆነን ; የዉል እዉነትን በመያዝ እና የህዝባችንን የሰላም እጦት በመቀልበስ የህዝባችንን የመልማት ፍላጎት ማሳካት እንደሚገባ ተገልጿል

የወል እውነት የጋራ ማኀበረሰብ ለመገንባት፣ በህዝቦች መካከል የሚነሱ ዉጪያዊ ና ወስጣዊ ጥያቄዎችን ለመፍታት የሚጠቅም በመሆኑ ዘላቂ ሰላም በማፅናትና የህግ የበላይነትን ለማስከበር የወል እውነትን የሚያፀና የትግል ፖለቲካዊ ባህል መላበስ እንደሚያስፈልግ በመጥቀስ ውይይቱ ተጠናቋል።

"የጎሃ ቃልኪዳናችን የከፍታችን ልክ - ቃላችንን ፈፅመን ከፍታው ላይ እንገናኝ"

መንዝ ማማ ምድር ወረዳ ብልፅግና ፓርቲ ዲጂታል::https://www.facebook.com/profile.php?id=100064478212818

05/07/2023

ለጋራ ሰላምና ደህንነት የሚሰሩ ጀግኖችን በመግደል ህዝብን የሚያጎሳቁሉ ፅንፈኛ ሀይሎችን በጋራ እንታገል

በዛሬው እለት በሸዋሮቢት ከተማ ለጊዜው ማንነታቸው ባልታወቀ ፅንፈኛ ሀይሎች የከተማዋን የፀጥታ ሀላፊ አቶ አብዱ ሁሴንን ህይወት ተነጥቀናል።አቶ አብዱ ሁሴን ቀንና ሌት ሳይሉ ለሸዋሮቢትና ለአካባቢው ህዝብ ሰላምና ደህንነት ራሳቸውን ሰጥተው የሰሩ ሀቀኛና ሰላም ወዳድ አመራራችን ነበሩ።እኚህን ወጣት ተስፈኛ መሪ በመግደል ለጊዜው የተሰወሩ ፅንፈኛ ሀይሎችን ማንነት ለማወቅና በህግ አግባብም ተጠያቂነታቸውን ለማረጋገጥ በመሰራት ላይ ይገኛል።

የሰላም ጠንቅ የሆኑ ደግሞም ሰውን በመግደል የሚያምኑ እጆቻቸው በደም፣ጭንቅላታቸው በመጥፎ ሀሳብ የጨቀየ የጥፋት አካላትን ለመቆጣጠርና ወደ ሰላም ለመመለስ የሚደረገውን ትግል ህብረተሰቡ እንደ ሁልጊዜው በቅርበት እንዲያግዝም ጥሪ እናቀርባለን።

ህዝባቸውን በማገልገል ላይ እያሉ በጨካኞች ላጣናቸው አቶ አብዱ ሁሴን ነፍስ ጀነትን እንዲሁም ለመላው ቤተሰባቸውና ለስራ ባልደረቦቻቸውና ለህዝባችን መፅናናትን እንመኛለን።

በመንዝ ማማ ምድር ወረዳ ሲሰጥ የነበረው የ8ኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተና በሰላም መጠናቀቁን የወረዳው ትምህርት ጽ/ቤት አስታወቀ ሞላሌ፦ ሰኔ 27/2015 ዓ.ም (መማመኮጉ) በመንዝ ማማ ምድር...
04/07/2023

በመንዝ ማማ ምድር ወረዳ ሲሰጥ የነበረው የ8ኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተና በሰላም መጠናቀቁን የወረዳው ትምህርት ጽ/ቤት አስታወቀ

ሞላሌ፦ ሰኔ 27/2015 ዓ.ም (መማመኮጉ) በመንዝ ማማ ምድር ወረዳ ለ2 ቀናት ሲሰጥ የነበረው የ8ኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተና በሰላም መጠናቀቁን የወረዳው ትምህርት ጽ/ቤት ገለፀ።

በወረዳው በ23 ትምህርት ቤቶች 1461 የ8ኛ ክፍል ተማሪዎችን በሰላም እንዲፈተኑ በማድረግ ማጠናቀቅ መቻላቸውን የመንዝ ማማ ምድር ወረዳ ትምህርት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ጥበቡ ታደሰ ገልፀዋል።

ፈተናው በሰላማዊ መንገድ እንዲጠናቀቅ ላደረጉት የጸጥታ አካላት ፣ መምህራን ፣ ሱፐርይዘሮች ፣ የፈተና ጣቢያ ሀላፊዎች አመራሮችና አጋር አካላትን የመንዝ ማማ ምድር ወረዳ ትምህርት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ጥበቡ ታደሰ የላቀ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

"መፍጠንና መፍጠር የወል እውነቶችን የማፅናት ቀጣይ የትግል ምዕራፍ" በሚል መሪ ሃሳብ ለአባል መ/ሰራተኞች ስልጠና እየተሰጠ ነው።በሰ/ሸዋ ዞን የመንዝ ማማ ምድር ወረዳ  "መፍጠንና መፍጠር፣...
04/07/2023

"መፍጠንና መፍጠር የወል እውነቶችን የማፅናት ቀጣይ የትግል ምዕራፍ" በሚል መሪ ሃሳብ ለአባል መ/ሰራተኞች ስልጠና እየተሰጠ ነው።

በሰ/ሸዋ ዞን የመንዝ ማማ ምድር ወረዳ "መፍጠንና መፍጠር፣ የወል እውነቶችን የማፅናት ቀጣይ የትግል ምዕራፍ" በሚል መሪ ሀሳብ በሚል መሪ ሃሳብ ለአባል መ/ሰራተኞች ስልጠና እየተሰጠ ይገኛል።

በመፍጠርና መፍጠን እንዲሁም ከተናጠል እዉነታ ይልቅ የወል እምነቶች ምንነትና አስፈላጊነት ዙሪያ ግንዛቤ መፍጠር የመድረኩ ዋና ዓላማ ሲሆን በቀጣይም ተሳሳፊዎች ከውይይቱ የሚያገኙትን ግንዛቤ ወደ ተግባር በመቀየር ለለውጥ መስራት እንደሚጠበቅባቸው በስልጠናው መክፈቻ ተገልጿል::

መንዝ ማማ ምድር ወረዳ ብልፅግና ፓርቲ// MAMA pp//

የመንዝ ማማ ምድር ወረዳ ት/ት ፅ/ቤት   የ2015 ዓ/ም የ8ኛ ክፍል ፈተና መሰጠት ጀመረ::       በዚህ የትምህርት ዘመን አመቱን ሙሉ ትምህርታቸዉን ሲከታተሉ ቆይተዉ የአመቱን ትምህርት...
03/07/2023

የመንዝ ማማ ምድር ወረዳ ት/ት ፅ/ቤት የ2015 ዓ/ም የ8ኛ ክፍል ፈተና መሰጠት ጀመረ::
በዚህ የትምህርት ዘመን አመቱን ሙሉ ትምህርታቸዉን ሲከታተሉ ቆይተዉ የአመቱን ትምህርት ማጠናቀቂያ ፈተና በወረዳዉ ባሉ 19 ቀበሌ ዉስጥ 23 ትምህርት ቤቶች ፈተናዉን እየሰጡ ይገኛሉ: በአጠቃላይ በዚህ አመት በወረዳዉ የሚፈተኑ ከተመዘገቡት
ወ 678 ሴ 857 ድ 1535 እየተፈተኑ ያሉ ተማሪዎ ብዛት
ወ 632 ሴ 829 ድ 1461 እያሰፈተኑ ይገኛሉ።
በዚህም የትምህርት ፈተና ወቅት በወረዳዉ ባሉ ቀበሌዎች ፈተናዉ በሰላምና ያለንም ችግር እየተሰጠ መሆኑን የወረዳዉ የት/ት ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ጥበቡ ታደስ ገልፀዋል::
" የትምህርት ተደራሽነት ለሁሉም"

“መፍጠንና መፍጠር የወል እውነቶችን የማጽናት ታሪካዊ የትግል ምዕራፍ " በሚል መሪ ቃል በመንዝ ማማ ምድር ወረዳ  የወረዳና የቀበሌ አመራሮች፣ የሴክተር መሠረታዊ ፓርቲ አመራሮች የተሳተፉበት...
02/07/2023

“መፍጠንና መፍጠር የወል እውነቶችን የማጽናት ታሪካዊ የትግል ምዕራፍ " በሚል መሪ ቃል በመንዝ ማማ ምድር ወረዳ የወረዳና የቀበሌ አመራሮች፣ የሴክተር መሠረታዊ ፓርቲ አመራሮች የተሳተፉበት ስልጠና ተጠናቀቀ

“መፍጠንና መፍጠር የወል እውነቶችን የማጽናት ታሪካዊ የትግል ምዕራፍ " በሚል መሪ ቃል በመንዝ ማማ ወረዳ የወረዳና የቀበሌ አመራሮች፣ የሴክተር መሠረታዊ ፓርቲ አመራሮች የተሳተፉበት የስልጠና መድረክ ተጠናቋል ።

በማጠቃለያ ፕሮግራሙ ላይ የተገኙት የሰሜን ሸዋ ዞን ወጣቶችና ስፓርት መምሪያ ኃላፊ አቶ ብርሀን ጨርቆስ እንደ ሀገር የገጠሙን ችግሮችን ለማለፍ
አመራራችን፣ አባላችን እና መላው ህዝባችን የገጠሙን ችግሮችን ማለፍ የሚያስችል ተግባቦት በመፍጠር የመውጫ መንገዶችን እና የወል እውነቶችን በመገንዘብ የወል እውነቶችን በማጽናት ለአገር ግንባታው የሚጠበቅብንን ሃላፊነት ልንወጣ ይገባል ሲሉ አሳስበዋል።
የስልጠናው አላማ የጋራ ባደረጉን እውነቶች ላይ በመስማማት ልዩነቶችን በውይይት በመፍታት የብልፅግና እሳቤዎች ለአገር ግንባታ ያለውን አስተዋጽኦ ማረጋገጥ መቻል ነው ሲሉ ገልጸዋል። የመንዝ ማማ ምድር ወረዳ ም/አስተዳዳሪና የስራናስልጠና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ በሻህ ገ/እግዚአብሔር በበኩላቸው የህዝቦችን ፍትሃዊ ተጠቃሚነት እና እኩልነት የሚያረጋግጥ ስርአተ መንግስት ለመገንባት የወል እውነቶችን በመቀበል ቅብልነት ያለው ጠንካራ ስርአተ መንግስት መገንባት ፣ መረዳትና ማስረጽ ይገባል ሲሉ ተናግረዋል።
ጠንካራ አገረ መንግስት ለመገንባት የዜጎችን ህይወት መቀየር የሚያስችልና ከድህነት የሚያወጣ የኢኮኖሚ ስርአት መዘርጋት እና አገራችንን እየፈተናት ያለውን የጽንፈኝነት መንገድ በጋራ መታገል ይገባል ብለዋል።
የመንዝ ማማ ምድር ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ደመቀ ማሙሻ በበኩላቸውበየደረጃው የገጠሙን ሀገራዊ እና ክልላዊ ተግዳሮቶችን ለማለፍ የወል እውነቶችን በመገንዘብና ከተናጠል ቡድናዊ ፍላጎቶች በላይ ለጋራ ተጠቃሚነት በመስራት አለመግባባቶችን በውይይት መፍታት የሚያስችል ተግባቦት መፈጠር እንዳለበትገልፀዋል።

የመንዝ ማማ ምድር ወረዳ የአዳባይ  ፕሮጀክት ከተወላጆች ጋር ዉይይት ተካሄደ ::         በዚህ ዉይይት ላይ የዞን  አመሬሮች: የወረዳ አመራሮች; ፕሮጀክቱ ያለበት አካባቢ ተዉላዶች; ወ...
02/07/2023

የመንዝ ማማ ምድር ወረዳ የአዳባይ ፕሮጀክት ከተወላጆች ጋር ዉይይት ተካሄደ ::
በዚህ ዉይይት ላይ የዞን አመሬሮች: የወረዳ አመራሮች; ፕሮጀክቱ ያለበት አካባቢ ተዉላዶች; ወረዳዉን በመሪነት ሲያለግሉ የቆዩ መሪዎች እና አረቲስቶች የተሳተፉበት ዉይይት በሸዋ መዲና የብረሀን አንባዋ ደብረብሃን ጌትቫ ሆቴሌ አዳራሽ ተካሂዷል::
በዚህም ላይ ንግግር ያደረጉት የሰሜን ሸዋ ዞን ም/አስተዳዳሪ አቶ ክላል ሳህለማርያም ሲሆኑ" የማይደፈዉን የደፈር የዘመኑ መሪና ትዉልድ በመፈጠሩ የማማን ብሎም የሸዋን የእደገት ቀጣይነትን ያሳየና ለትዉልድ የሚተላለፍ ፕሮጀክት ነዉ ይህ ፕሮጀክት የተዳፈነ ወርቅ ማዉጣት ብቻ ሳይሆን በዚያ አካባቢ ላሉ የህ/ሰብ ክፍሎች የሚያገለግል መንገድ መሰራቱ ለዘመኑ የሚመጥን ስራ ነዉ በማለት ሀሳባቸዉን ገልፀዋል:: በዚህ ዉይይት ላይ ለዘመናት የነበረባቸዉን ቁጭት የአካባቢዉ ተወላጆች በማንሳት እና ለቀጣይ በሀብት;በጉልበት;በሀሳብ ለማገዝ በቆራጥነት እንሰራለን ሲሉ ተናግረዋል:: በአጠቃላይ ለዚህ ፕሮጀክት በገንዘብ 60000000 /ስልሳ / ሚሊዮን ብር የሚያስፈልግ ሲሆን በዕለቱ 120000 አንድ መቶ ህያ ሺ ብር/ ምንም አይነት የገቢ ማሰባሰብ ስራ ሳይሰራ በራስ ሞራል የተሰጠና ቀጣይ ገቢ የማሰባሰብ ስራዉ እንደሚቀጥል በማሳሰብ እና የተለያዩ ኮሚቴዎችን በማቋቋም የጀመርንዉን እንጨርሳለን ለትዉልድ የሚተላለፍ ታሪክን እንሰራለን በማለት ዉይይቱ ተጠናቋል።

የመንዝ ማማ ምድር ወረዳ ለትዉልድ የሚተላለፍ ፕሮደክት ስራን መስራት ጀምሯል::   ይህ ፕሮጀክት ለዘመናት ሲታሰብ የቆየ ና ነገ የማማን  ብሎም የሸዋን ከፍታ የሚያረጋግጠዉ   እንቁ ና ተና...
01/07/2023

የመንዝ ማማ ምድር ወረዳ ለትዉልድ የሚተላለፍ ፕሮደክት ስራን መስራት ጀምሯል::
ይህ ፕሮጀክት ለዘመናት ሲታሰብ የቆየ ና ነገ የማማን ብሎም የሸዋን ከፍታ የሚያረጋግጠዉ እንቁ ና ተናፋቂ የነገ ተስፋ የሆነዉ ፕሮጀክም መስራት ከተጀመር ቀናቶችን አስቆጥሯል:: ፕሮጀክቱም ለዘመናት የባከነ የሸዋ እንቁ ሀብት አሸዋ ለማዉጣት የሚሰራ መንገድ ስራ ነዉ ይህን መንገድ የሚሰራዉ በመንዝ ማማ ምድር ወረዳ የሚገኘዉን ወንዝ በሰሜን ሸዋ ዞን ስር የሚገኙ ስድስት ወረዳዎች የሚያዋስኑትን አዳባይ ታላቁ የጀማ ወንዝ፣የበረሳ እና ሌሎች አምስት ወንዞች የሚገናኙበት ቦታ ነው። ይህ ቦታ ለአጎራባች ወረዳዎች እጅግ ቅርብ ቢሆንም እስካሁን ሳይሰራ ቆይቷል በአጠቃላይ ወረዳው መንገድ ባለመሰራቱ ምክንያት እጅግ ግዙፍ ነጭ ወርቅ (አሸዋ) ተዳፍኖ በመቆየቱ የኢኮኖሚ ምንጭ ሳይሆን ቀርቷል። ለዘመናት ለወጪ ወራጅ ቁጭት ሆኖ ተዳፍኖ ቆይቷል። በዚህ አመት ግን አዳባይ ለልማት አርበኞች እጅ ወደላይ ብሏል፣ ሊማረክ ትንሽ ቀርቶታል። የመንዝ ማማ ወረዳና የአካባቢው ተወላጆች ይህን የዘመናት ቁጭት ወዲያ ብለው የመንገድ ስራውን በራሳቸው በጀት እና ከአካባቢው ተወላጆች እያሰባሰቡ አስጀምረውታል። እስካሁን ጥሩ ስራ ላይ የሚገኘዉ የአዳባይ መንገድ ሰራ ለአካባቢው ነዋሪዎች ሌላ እድል ይዞ መጥቷል፣ መንገድ የደምስር እንደመሆኑ መጠን አካባቢው ላይ የሚመረቱ ምርቶችን በቀላሉ ወደ ገበያ ለማድረስ ትልቅ እገዛ አድርጓል። በጥቅሉ ይህን የማማ የልማት ፈር ቀዳጅ ፕሮጀክት መደገፍ ግድ ስለሆነ ሁሉም እጁን እንዲዘረጋና የማማን ህዝብ ዕድግት በላቀ መሰርት ላይ ለማስቀመጥ ደግሞ አጎራባች ወረዳዎች እና ባለሀብቶች ደጋፋችሁና ትብብራችሁ አይለየን::
የዘመናት ስንቅን ለመሰነቅ ባለን ብቻ ሳይሆን በሌለን ሁሉ ነዉና በብርታት የጀመርንዉን በብርታት ከህዝባችንና ከባለሀብቶቻችን ጋር እንጨርሰዋለን::
"ላንጨርስ አንጀምርም ጀምረን አንተዉም"
" Mama pp"

መፍጠንና መፍጠር የወል እውነቶችን የማፅናት ቀጣይ የትግል ምዕራፍ''በሚል መሪ ቃል በመንዝ ማማ ምድር ወረዳ  ለወረዳወ አመራሮች ፣ለቀበሌ ኮር አመራሮች ስልጠና  ተጀምሯል።      የስልጠና...
01/07/2023

መፍጠንና መፍጠር የወል እውነቶችን የማፅናት ቀጣይ የትግል ምዕራፍ''በሚል መሪ ቃል በመንዝ ማማ ምድር ወረዳ ለወረዳወ አመራሮች ፣ለቀበሌ ኮር አመራሮች ስልጠና ተጀምሯል።

የስልጠናውን የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት አቶ መርሻ ሀይሉ የመንዝ ማማ ምድር ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ ሲሆኑ በስልጠናው አቅምን በመፍጠር ከነጠላ አዉነት ይልቅ የዉል እዉነታን በመያዝ በክልላችን እንዲሁም በሀገር የገጠሙንን ነባራዊ ሁኔታዎችን በአግባቡ ተረድቶ ለችግሮቻችን መፍተሔ ለመስጠት እና የአመለካከት ክፍተቶችንም ለማረም ትልቅ አቅም የሚፈጥር ስልጠና መሆኑን የገለፁ ሲሆን::
በዚህም ስልጠና ላይ
አቶ ብረሀን ጨረቆስ የሰሜን ሸዋ ዞን ሰፓርት መምሪያ ሀላፊ የተገኙ ስኬትን ምክነያት በመደረደር አናገኝም ስኬትን የምናገኘዉ ባይኖረንም ባለን ጨርሰን ዉጤት ላይ ስንደርስ ነዉ ለዚህ ደግሞ በባዶ እግሩ ሮጦ ክብር የተቀዳጀ ጀግን ከአበበ በቂላን እንማር በማለት በአንድነት ለሀገር ክብርና እድገት በመቆም ስኬታችንን በማሰቀጠል የቀሩንን ተግባሮች እንስራ::
የመንዝ ማማ ምድር ወረዳ ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ፅ/ቤት አደረጃጀት ዘረፍ ሀላፊ አቶ ደመቀ ማሙሻ ስልጠናውን እየሰጡ ይገኛሉ ።

ስልጠናው 24-25/2015 ድረስ እንደሚቆይም ጭምር ገልፀዋል።

የመንዝ ማማ ምድር ወረዳ ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ፅ/ቤት
"ከህዝባችን ጋር በወል እዉነታን በመያዝ ከዉድቀት እንሻገራለን"

" መፍጠንና መፍጠር የወል እውነቶችን የማፅናት ቀጣይ የትግል ምዕራፍ " በሚል ርዕስ ለሁለት ቀናት ለሚሰጠዉ ስልጠና የቅድመ ዝግጅት ሰራዎች መጠናቀቃቸዉ ተገለፀ::        ከዚህም የቅድመ...
30/06/2023

" መፍጠንና መፍጠር የወል እውነቶችን የማፅናት ቀጣይ የትግል ምዕራፍ " በሚል ርዕስ ለሁለት ቀናት ለሚሰጠዉ ስልጠና የቅድመ ዝግጅት ሰራዎች መጠናቀቃቸዉ ተገለፀ::
ከዚህም የቅድመ ዝግጅት ሰራዎች መካከል የሚሳተፉ ተሳታፊዎችን የመለየት ሰራና የአዳራሽ ዝግጅትና በአጠቃላይ ለስልጠናዉ የሚየስፈልጉ ነገሮች መዘጋጀታቸዉን አቶ ደመቀ ማሙሻ የመንዝ ማማ ምድር ወረዳ የብልፅግና ፓርቲ ፅ/ቤት አደረጃጀት ዘርፍ ሀላፊ ገልፀዋል::

በዚህም የሁለት ቀን ቆይታ ላይ የብልፅግና ፓርቲ ስራ አስፈፃሚና ማዕከላዊ ኮሚቴ ባወረደው አቅጣጫ መሠረት " በክልልና በዞን ደረጃ ስልጠናዉ ቢሰጥም አሁንም በወረዳ ደረጃ " መፍጠን እና መፍጠር ፤ የወል እውነቶችን የማፅናት ቀጣይ የትግል ምዕራፍ " በሚል መሪ ሀሳብ ስልጠናዉ ለሚመለከተዉ አካል እንደሚሰጥ ገልፀዋል::ይህም ስልጠና በ24-25/10/2015 ዓ/ም ይጀመራል ብለዋል::

ከዚህ ስልጠና በኋላም በቀበሌ ደረጃ ስልጠናው ይቀጥላል ያሉት ኃላፊው በየደረጃው የሚገኙ የብልፅግና ፓርቲ አባላት ፖለቲካዊ አቅማቸውን የማሳደግ ተግባሩ በቀጣይነት የሚፈፀም ይሆናል ተብሏል።

የስልጠናው አላማም የተሳካ የብልፅግና ጉዞን የማረጋገጥ ; አመራሩ እና አባላቱ ከነጠላ አዉነት ወደ የዉል እውነትን በማፅናት ለቀጣይ የሀገር እድገትና ሰላም ለማስቀጠል በመሆኑ ለወል እውነት ተገዢ እንዲሆን ያለምንም የሀሳብ ልዩነት ወደ ትግል በመግባት የብልፅግና ጉዟችንን የሚያደናቅፉ ኃይሎችን አምርሮ እንዲታገል ፖለቲካዊ አቅሙን መገንባትና በተስተካከለ አመለካከት አመራሩን መምራት ማስቻል ነው ብለዋል አቶ ደመቀ ማሙሻ በመግለጫቸው።

ዜና ሹመትርእሰ መስተዳድር ይልቃል ከፋለ ( ዶ/ር )  በዛሬዉ እለት ለአንድ ከፍተኛ  የስራ ኃላፊ ሹመት ሰጥተዋል ፡፡በዚህም መሰረት አቶ ይርጋ ሲሳይ ቅጠዉ በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማእረ...
25/06/2023

ዜና ሹመት

ርእሰ መስተዳድር ይልቃል ከፋለ ( ዶ/ር ) በዛሬዉ እለት ለአንድ ከፍተኛ የስራ ኃላፊ ሹመት ሰጥተዋል ፡፡

በዚህም መሰረት አቶ ይርጋ ሲሳይ ቅጠዉ በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማእረግ የርዕሰ መስተዳድሩ የህዝብ ግንኙነት እና አደረጃጀት አማካሪ ሆነዉ ተሾመዋል ፡፡

ከዚህ በፊት የደቡብ ጎንደር ዞን ዋና አስተዳዳሪ የነበሩት የብልፅግና ፓርቲ ስራ አስፈፃሚ አባል አቶ ይርጋ ሲሳይ በተለያዩ የሕዝብ፣ የመንግሥትና የፓርቲ አደረጃጀቶች የረዥም ጊዜ ልምድ ያላቸው ለህዝባችን የልማት ተጠቃሚነት የሚታትሩ አመራር ናቸው።
~~°~~°~~


"ቃላችንን ፈፅመን ከፍታው ላይ እንገናኝ"
ለወቅታዊ ፣ ትክክለኛና አዳዲስ መረጃዎች የፓርቲያችንን የማህበራዊ ገፆች ይወዳጁ።

👉ቴሌግራም፦https://t.me/SouthGonderPP

👉ፌስቡክ
https://www.facebook.com/profile.php?id=100069002116411

👉ቲዊተር፦https://twitter.com/EsubalewMesfin2?t=g3qUvFocF31k8UwuXfDZ9g

በመጪዉ ሀምሌ ወር መሰጠት የሚጀምረዉን የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ከፍተኛ ዉጤት ለማስመዝገብ እየተዘጋጁ መሆናቸዉን ተማሪዎች ተናገሩ፡፡     ሞላሌ; ሰኔ 15/2015ዓ.ም በመንዝ ማማ...
22/06/2023

በመጪዉ ሀምሌ ወር መሰጠት የሚጀምረዉን የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ከፍተኛ ዉጤት ለማስመዝገብ እየተዘጋጁ መሆናቸዉን ተማሪዎች ተናገሩ፡፡
ሞላሌ; ሰኔ 15/2015ዓ.ም በመንዝ ማማ ወረዳ የደጃአዝማች ከፈለዉ ወ/ፃዲቅ ከፍተኛ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች በመጪዉ ሀምሌ ወር የሚሰጠዉን የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ከፍተኛ ዉጤት ለማስመዝገብ እየሰሩ መሆናቸዉን ተናግረዋል፡፡
የት/ቤቱ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪ የሆኑት ተማሪ ሶስና ኪ/ማርያምና ተማሪ እስጢፋኖስ ፈተናዉን ለመዉሰድ በቤትም ሆነ በት/ቤታቸን በቂ ዝግጅት እያደረግን ነዉ ብለዋል፡፡ ከ9-12 ያሉ የክፍል ደረጃዎችን በወርክ ሽት መልኩ እየተሰራልን ነዉ፡፡ ፈተናዉን በድል ለማጠናቀምቅ ወስነናል ሲሉ ተናግረዋል፡፡
የት/ቤቱ ር/መምህር ነብዩ አላጋዉ በበኩላቸው በዘንድሮዉ አመት በት/ቤቱ 150 የማህበራዊና የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ሀገር አቀፍ ፈተናውን ይወስዳሉ ሲሉ ተናግረዋል፡፡ ተማሪዎቹን በተለያየ መልኩ ለማገዝ ከወላጅ እስከ መምህራን ከፍተኛ ርብርብ እያደረግን ነዉ፡፡መምህራን ከለፉት የክፍል ደረጃዎች ጀምሮ የክለሳ ስራ እየሰሩ ነው፡፡ በዘመኑ የተሻለ ዉጤት እንደሚመዘገብም ተስፋ አለን ብለዋል፡፡
አቶ ነብዩ አያይዘዉም የወረዳው መንግስት የተቋሙን እንቅስቃሴ በመመዘን የይዞታ ማረጋገጫ ደብተርና በቂ የሆነ ግንባታ ለመገባት የሚያስችል በጀት መድቦ ሊሰራ ይገባል ሲሉ አሳስበዋል፡፡

የመንዝ ማማ ምድር ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ግምቱ ከ618 ሺህ  ብር በላይ የሚሆን የቢሮ መገልገያ ቁሳቁስ ድጋፍ አገኘ።ሞላሌ; ሰኔ 13 ቀን 2015 ዓ.ም በሰሜን ሸዋ ዞን የመንዝ ማማ ምድር ...
20/06/2023

የመንዝ ማማ ምድር ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ግምቱ ከ618 ሺህ ብር በላይ የሚሆን የቢሮ መገልገያ ቁሳቁስ ድጋፍ አገኘ።

ሞላሌ; ሰኔ 13 ቀን 2015 ዓ.ም በሰሜን ሸዋ ዞን የመንዝ ማማ ምድር ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2013/14 በነበረው ጦርነት በመንዝ ማማ ምድር ወረዳ ንብረቱ ለወደመበት የገንዘብ ጽ/ቤት የሰሜን ሸዋ ዞን ገንዘብ መምሪያ የ618 ሺህ ብር የቢሮ መገልገያ ቁሳቁስ ድጋፍ ማድረጉን የወረዳው ገንዘብ ጽ/ቤት ም/ኃላፊ አቶ መኮንን ገበየሁ ገልፀዋል።

የክልሉ ገንዘብ ቢሮ ከፌዲራል ገንዘብ ሚኒስቴር ጋር በመተባበር ስፔስ (ESPES) ከተባለ ፕሮጀክት በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ በወረዳችን በተለያዩ ጊዜያት በጦርነቱ ምክንያት የወደሙናየተጎዱ የቢሮ መገልገያ ቁሳቁስ ድጋፍ መደረጉን ም/ኃላፊ አቶ መኮንን ተናግረዋል።

በተለይም የፋይናንስ ተቋሙ በጦርነቱ ወቅት በርካታ የቢሮ ቁሳቁስ ጉዳት እንደደረሰባቸው ያነሱት ም/ኃላፊው ተቋማቱን መልሶ ለማቋቋምና ወደ ሥራ ለማስገባት ሰፊ ሀብት የሚጠይቅ በመሆኑ ሀብት የክልሉ ገንዘብ ቢሮ ሀብት በማፈላለግ ችግሩን ለማቃለል ስፔስ ከተሰኘ ፕሮጀክት በተገኘ ድጋፍ ወሳኝ የሆኑና ተቋማቱ ሕይወት ዘርተው ኅብረተሰቡን አገልግሎት መስጠት የሚያስችሉ ንብረቶች ድጋፍ ማድረግ ተችሏል ብለዋል፡፡

ካዝና ፣ የባለሙያ ወንበርና ጠረጴዛ ፣ የፋይል መደርደሪያ ሼልፍ እና የጀኔሬተር ድጋፍ መደረጉን አንስተው ድጋፉን ላደረገው ስፔስ ድርጅት እና ለክልሉ ገንዘብ ቢሮ ምሥጋና አቅርበው ይህ ድጋፍ ተቋማቱን ሙሉ በሙሉ ወደ ሥራ ለማስገባት በቂ ነው ባይባልም ሥራ የሚያስጀምር መሆኑን ገልጸው ሌሎች ድርጅቶችም ድጋፍ ያደርጉ ዘንድ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

በጦርነቱ ጉዳት ከደረሰባቸው ወረዳዎች መካከል የመሐል ሜዳ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ወይዘሮ አይንዬ ፋንቱ እና የአንጾኪያ ገምዛ ወረዳ ገንዘብ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ታንኩ በላቸው የተደረገላቸውን ድጋፍ አስመልክተው አስተያየት ሰጥተዋል።

ጦርነቱ የሰው ሕይወት ያጠፋና የአካል ጉዳት ማድረሱን እና በተቋማት ንብረት ላይ ውድመት ማድረሱን ገልጸው የተደረገው ድጋፍ በቂ ነው ማለት ባይቻልም ሥራ ለማስጀመር እንደሚያስችልና በተለይም የካዝናውና የጀኔሬተሩ ድጋፍ ለተቋማቸው ቁልፍ መሆኑን አንስተው ድጋፉን ላደረጉት አካላትም በተመሳሳይ ምሥጋና አቅርበዋል፡፡

18/06/2023

"ስንተባበር ውጤታማነታችን ይረጋገጣል የህዝባችንም ችግሮች ይፈታሉ"

አቶ ግዛቸው ነገሰ
የሰሜን ሸዋ ዞን አስተዳደር ፅህፈት ቤት ሀላፊ

የልማት አቅሞቻችን በተባበረ መንገድ ጥቅም ላይ እንዲውሉ ማድረግ የውጤታማነት ምስጢር መሆኑን ሀላፊው ተናግረዋል።አቶ ግዛቸው የዞኑን አስተዳደር ወክለው በወርልድ ሰርቭ ኢንተርናሽናል በተሰሩ የንፁህ መጠጥ ውሃ ተቋማት ምርቃት ላይ ተገኝተው ባስተላለፉት መልዕክት ነው ይህን ያሉት።

ስንተባበር ውጤታማነታችን ይረጋገጣል የህዝባችንም ችግሮች ይፈታሉ ያሉት አቶ ግዛቸው የዞኑ አስተዳደር ሁሉንም የልማት አቅሞች አቀናጅቶና ደግፎም ለህብረተሰብ ለውጥ እንደሚሰራ ገልፀዋል።ወርልድ ሰርቭ ኢንተርናሽናል ትልልቅ ስራዎችን በአነስተኛ ወጭና በአጠረ ጊዜ በመስራት ለህብረተሰቡ ላደረገው አበርክቶም ምስጋናቸውን አቅርበዋል።በቀጣይም የሲቪክ ማህበረሰብ ድርጅቶች ወደ ዞኑ መጥተው በየትኛውም ዘርፍ ለሚያደርጉልን ድጋፍ አስተዳደሩና ማህበረሰቡ ቀና ትብብራቸውን እንደሚያደርጉ አረጋግጠዋል።

~~~
"የጎሃ ቃልኪዳናችን የከፍታችን ልክ -ቃላችንን ፈፅመን ከፍታው ላይ እንገናኝ"
~~~
ለወቅታዊ ፣ ትክክለኛና አዳዲስ መረጃዎች የፓርቲያችንን የማህበራዊ ገፆች ይወዳጁ።

ቴሌግራም፦

https://t.me/shewaprosperity

ፌስቡክ

https://www.facebook.com/profile.php?id=100064788996103

ቲዊተር፦
https://twitter.com/ShewaNorth?s=09

ቲክቶክ
https://www.tiktok.com/?_t=8dEh8MoumH7&_r=1

ዩቲዩብ
https://youtube.com/

18/06/2023
"  ሁለተኛ  ትዉልድ ጤና ኤክስቴንሽ መፍጠር በሚል ሀሳብ ላይ   ለሴት ልማት ቡድን አመራሮች ለ14 ቀን ሲሰጥ የነበረዉስልጠና ተጠናቀቀ::       የመንዝ ማማ ምድር ወረዳ ጤና ጥበቃ ፅ/...
17/06/2023

" ሁለተኛ ትዉልድ ጤና ኤክስቴንሽ መፍጠር በሚል ሀሳብ ላይ
ለሴት ልማት ቡድን አመራሮች ለ14 ቀን ሲሰጥ የነበረዉ
ስልጠና ተጠናቀቀ::
የመንዝ ማማ ምድር ወረዳ ጤና ጥበቃ ፅ/ቤት በ19 የገጠር ቀበሌ ያሉ የሴት ልማት ቡድን አመራሮችን ለተከታታይ 14 ቀን በጤናዉ ዘርፍ በቀበሌ ጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያና በክላሰተር ባሉ የጤና ባለሙያዎች ሲሰለጥኑ ቆይተዋል:: የሰለጠኑትም "ሁለተኛ ትዉልድ ጤና እክስቴንሽን መፍጠር በሚል ሲሆን ይህን ስልጠና ቀድመዉ የጀመሩ ቀበሌዎች ማለትም በጤናዉ ዘርፍ ሰልጠናቸዉን ያጠናቀቁት 018;017;020;019;02;010;014 ቀበሌ ዎች በመቀጠል ያጠናቀቀዉ 015 ቀበሌ ሲሆን እነዚህ የሰለጠኑ ሴት ልማት ቡድን አመራሮች ራሳቸዉ ሞዴል በመሆን ለሌሎቹ ግንባር ቀደም ተዋናይዎች መሆናቸዉን በመግለፅ ምርቃቱየተጠናቀቀ ቢሆንም በዚህ ምርቃት ላይ የተገኙት አቶ ተክለአብ አስበ የወረዳዉ ጤና ጥበቃ ፅ/ቤት ም/ ሀላፊ አቶ በረደድ በላይነህ የወረዳዉ የጤና ኤክስቴንሽን አስተባባሪ ;አቶ ሙላት የይገም ጤና ጣቢያ ሀላፊ ;አቶ እሸቱ ፋኖስ የይገም ጤና ጣቢያ የክላስተር ጤና ኤክስቴንሽን አስተባባሪና ; አቶ ሀብተወልድ _ _ _ የወረዳዉ የሴቶችናህፃናት ማህበራ ጉዳይ ፅ/ቤት ባለሙያ አቶ ባሳዝን የ015 ቀበሌ ዋና አስተዳዳሪ; እና ወ/ሪት ሂወት በጋሻዉ የቀበሌዉ ጤና ኤክስቴንሽ ባለሙያ በመገኘት ያስመረቁ ሲሆን በዚህ የስልጠና ማጠቃለያ ላይም አቶ ተክለአብ አስበ ጤናዉ የተጠበቀ ማህበረሰብ ለመፍጠር ሴቶች አመራሮቻችን ግንባር ቀደም ተዋናዮች ናቸዉ በማለት እና ለሰለጠኑት አመራሮች የመፈፀምና የማስፈፀም አቅማችሁን በማሳደግ ሌሎችን መለወጥ ያሰፈልጋል የሚል ተልዕኮ በመስጠት ና የተለያዩ ማነቃቂያ ሽልማቶችን በመሸለም የምረቃ ሰነ ስረአቱ ተጠናቋል::

የመንዝ ማማ ምድር ወረዳ ብልፅግና ፓርቲ ፅ/ቤት
መንዝ ማማ ዲጂታል ባለሙያ !!

ሴቶች  2ኛ ዙር የአደረጃጀት ስልጠናቸዉን አጠናቀቁ፡፡     ሴቶችን ማስተማር ብልህነት ነው በሚል መሪቃል በመንዝ ማማ  ወረዳ የወምሶ/010/ ቀበሌ የሴቶች አደረጃጀት የጤና ኤክስቴሽን ፓኬ...
16/06/2023

ሴቶች 2ኛ ዙር የአደረጃጀት ስልጠናቸዉን አጠናቀቁ፡፡
ሴቶችን ማስተማር ብልህነት ነው በሚል መሪቃል በመንዝ ማማ ወረዳ የወምሶ/010/ ቀበሌ የሴቶች አደረጃጀት የጤና ኤክስቴሽን ፓኬጅ ብቃት ማጎልበት ስልጠና ምዘና ሲወስዱ ቆይተዉ ሰኔ 8/2015ዓ.ም ተመረቁ፡፡
ስልጠናው ለተከታታይ 14 ቀን የተሰጠ ሲሆን በምረቃ ስነስርአቱ ላይ የመንዝ ማማ ምድር ወረዳ ጤና ጥበቃ ጽ/ቤት ም/ኃላፊ አቶ ተክለአብ አስበን ጨምሮ የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል፡፡
የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የመንዝ ማማ ምድር ወረዳ ጤና ጥበቃ ጽ/ቤት ም/ኃለፊ ስልጠናዉ የተግባርና ሙያዊ ስልጠና ሲሆን የእናቶች ጤና፣የህፃናት ጤና ፣ተላላፊና ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች ፣የጤና ፓኬጆችና አጠቃላይ የጤና እዉቀት ክህሎትና አመለካከት ማጎልበት ላይ ያተኮረ ነበር፡፡ በስልጠናዉ ከተመለመሉ 22ሴቶችውስጥ 20ዎቹ በጥራት ስልጠናዉን ወስደዉ ተመርቀዋል ብለዋል፡፡
ከተመራቂዎቹም ከስልጠናው ብዙ አይነት ትምህርት አግኝተናል፡፡ ብዙጊዜ ስንናፍቀው የነበረ ስልጠናነው፡፡የወሰድንውን ስልጠና ለሌሎች ሴቶች ማሰልጠን አለብን፡፡ አሁን ላይ ሁሉም እኩል መሆኑን ማሳየት ችለናል ሲሉ ሃሳብ ሰጥተዋል፡፡
የመንዝ ማማ ምድር ወረዳ ጤና ጥበቃ ጽ/ቤት የጤና ኤክስቴንሽን ትብብር ኦፊሰር ባለሙያ የሆኑት አቶ በረደድ በላይነህ በበኩላቸው ስልጠናው እናቶች ላይ ትኩረት ያደረገዉ የእያንዳንዱ ችግር ቀደምት ተጋፋጭ እናት ናት፡፡ስለዚህ እናትን ማስተማር ህ/ሰብን ማስተማር ነዉ ሲሉ ተናግረዋል፡፡አያይዘውም ከስልጠናዉ በኋላ ትልቅ ሀላፊነት እንደሚጠበቅባቸው አሳስበዋል፡፡
የቀበሌው ዋና አስተዳዳሪአቶ ኃይልዬ ባቦለት ለተመራቂዎች እንኳን ደስ አላችሁ ካሉ በኋላ እስከ ዛሬ መስራት እየቻልን ሳንሰራ አልፈናል፡፤አሁን ላይ እናንተን ማፍራታችን መልካም መሆኑን ገልፀው በቀጣይ በቀሪ የቀበሌያችን የሴቶች አደረጃጀት ላይም በትኩረት ይሰራል ብለዋል።

የብሔር ማንነትና የአገር ማንነት ሊጋጩም ሊነጣጠሉም አይችሉም !**************************የአማራ ህዝብ በተለያዩ ወቅቶች ከሌሎች ወንድሞቹ ጋር በጋራ በመሆን ያፈሰሰውን ደም፣ ...
13/06/2023

የብሔር ማንነትና የአገር ማንነት ሊጋጩም ሊነጣጠሉም አይችሉም !
**************************
የአማራ ህዝብ በተለያዩ ወቅቶች ከሌሎች ወንድሞቹ ጋር በጋራ በመሆን ያፈሰሰውን ደም፣ የከሰከሰውን አጥንት፣ እና የከፈለውን ወደር የለሽ መስዋእትነት የሚመጥን ዴሞክራሲ፣ ልማት፣ ፍትህ እና ሰላም እንዲያገኝ ለማድረግ የክልሉ መንግስት በቁርጠኘነት እየሰራ ይገኛል።

ጋሻው አወቀ (ዶ/ር)
የአማራ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ሃላፊ

•~•~•

"የጎሃ ቃልኪዳናችን የከፍታችን ልክ - ቃላችንን ፈፅመን ከፍታው ላይ እንገናኝ"
•~•~•

Address


Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Menz mama prosperity/መንዝ ማማ ብልፅግና posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

  • Address
  • Alerts
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share