Biruk

Biruk Information for change

06/06/2024
06/06/2024

ብልፅግና የአስተውሎት እና የማሰላሰል ውጤት ነው።

የመደመር ፍልስፍና መሠረት የሰው ልጆች ነፃ ፍቃድ በየጊዜው እያደገ የሚሄድና በዕድገት ውስጥም የዕውቀትና የሥነልቦና ኃይል እያዳበረ የሚሄድ ነው።

የሰው ልጆች ጉዞም ነጻ ፈቃዳቸውን እያጠነከሩ ከአከባቢና ከተፈጥሮ ባሪያነታቸው ነፃ እየወጡ የሚመጡበት ሂደት ነው።

ስለዚህም የሰው ልጆች ነፃ ፈቃድ ቀደም ብለው በሰሩት ስራ ላይ የሚመሰረት ነው። ይህ ማለት ትናንት የሰሯቸው ስራዎች ለቀጣይ ስራቸው መነሻ ወረት ይሆናቸዋል ማለት ነው።

ብልፅግና እነዚህን የኢትዮጵያን እሴቶች ተረድቶ፤ ማህበራዊ ሃብቶቿን ለይቶ፤ ግሩም ውበቶቿን አድንቆ፤ ስሟን ከፍ አድርጎ፤ ህዝቦቿንና ማንነቶቻቸውን አክብሮ የተነሳ የአስተውሎት እና የማሰላለሰል ውጤት ነው፡፡

ከመደመር ገፅ 9 የተወሰደ
---------
ለበለጠ መረጃ:-

✅ Website = http://www.aaprosperityparty.org.et/
✅ Facebook:- 👉 አማርኛ =https://www.facebook.com/AddisAbabaPP?mibextid=JRoKGi
👉 Afan Oromo= https://www.facebook.com/PBFinfinnee?mibextid=ZbWKwL
👉 ትግርኛ = https://www.facebook.com/aappTigrigna?mibextid=ZbWKwL
✅ Twitter = https://x.com/aa_prosperity?t=TB_E6thmUUxQBsXEibRJbQ&s=09
✅ Tiktok = https://www.tiktok.com/.ababa.prosp?_t=8mfpA1zPvoT&_r=1
✅ Youtube = https://youtube.com/?si=9KuC45zwqmID9aZK
✅ Telegram = https://t.me/prosperityaddis
✅ whatsup = https://whatsapp.com/channel/0029Vagih5HBKfi0UeAEYL2r
✅ Instagram = https://www.instagram.com/addisababaprosperity?igsh=YzljYTk1ODg3Zg==

ላይ ይከታተሉን!
እናመሰግናለን!

06/06/2024

የሰው ተኮር ተግባራት ለሁለንተናዊ የብልፅግና ስኬት መሠረት ናቸው!

የተጀመረውን የሰው ተኮር ተግባራትን አጠናክረን በማስቀጠል የህዝባችንን የመረዳዳት እሴት ማስቀጠል ይገባል።

ቤታቸው የተጎሳቆለባቸውን መጠገንና መልሶ መገንባት፣ የተቸገሩትን መርዳት፣ የደከሙትን መደገፍ የታመሙትን መጠየቅ፣ የተራቡትን ማጉረስ የህዝባችን ነባር እሴት ነው።

የፓርቲያችን እና የመንግስታችን ሰው ተኮር ፕሮግራሞችም ከህዝባችን ነባር እሴት ጋር የተጣጣሙ መሆናቸው እሙን ነው። የመረዳዳት ባህሎቻችን ወቅት ጠብቀው የሚደረጉ ሳይሆኑ ዓመቱን ሙሉ እንዲዘልቁ በተለይም የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ባህላችን እንዲሆን ጥረቶች እየተደረጉ ነው።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ የሚገኙ ዜጎችን ህይወት በማሻሻል ፍትሀዊ ልማትን ለማረጋገጥ በሰው ተኮር የልማት ፕሮግራሞች እያከናወነ ይገኛል።

የአገራችን ሁለንተናዊ ብልፅግና ሲረጋገጥ የህዝባችን የኑሮ ደረጃ ከፍ እንደሚል ፓርቲያችን ያምናል። የአገራችን ብልፅግና እውን የሚሆነው የህዝባችንን ፍትሀዊ ተጠቃሚነት እያረጋገጥን አንገብጋቢ ችግሮችን ደግሞ በሰው ተኮር ፕሮግራሞቻችን እያቃለልን ስንጓዝ ነው።

---------
ለበለጠ መረጃ:-

✅ Website = http://www.aaprosperityparty.org.et/
✅ Facebook:- 👉 አማርኛ =https://www.facebook.com/AddisAbabaPP?mibextid=JRoKGi
👉 Afan Oromo= https://www.facebook.com/PBFinfinnee?mibextid=ZbWKwL
👉 ትግርኛ = https://www.facebook.com/aappTigrigna?mibextid=ZbWKwL
✅ Twitter = https://x.com/aa_prosperity?t=TB_E6thmUUxQBsXEibRJbQ&s=09
✅ Tiktok = https://www.tiktok.com/.ababa.prosp?_t=8mfpA1zPvoT&_r=1
✅ Youtube = https://youtube.com/?si=9KuC45zwqmID9aZK
✅ Telegram = https://t.me/prosperityaddis
✅ whatsup = https://whatsapp.com/channel/0029Vagih5HBKfi0UeAEYL2r
✅ Instagram = https://www.instagram.com/addisababaprosperity?igsh=YzljYTk1ODg3Zg==

ላይ ይከታተሉን!
እናመሰግናለን!

04/06/2024
04/06/2024

በመርህ መመራት ዕውነትን ያፀናል፤ ሀገርን ወደፊት ያራምዳል!

ሀገር የምትመራውና አንድነቷን አፅንታ ክብሯን ወደሚመጥን ከፍታ የምትሻገረው የጋራ ግብና የወል ዕውነት ሲኖር ነው። የተናጠል ዕውነት የጋራ ግብን አያመጣም፤ ያለመርህ የሚፀና ፖለቲካዊውም ሆነ ኢኮኖሚያዊ ስኬት አይኖርም።

ብልጽግና ሀገር የወል ዕውነት ላይ ተመርኩዛ ህብረብሔራዊ አንድነቷን ታፀና ዘንድ በመርህ የሚመራ ግብና ተልኮን አንግቦ እየተጋ ይገኛል። በእኔ ብቻና መርህ አልባ የፅንፍ አስተሳሰብ ለጋራ ህልውና እንቅፋት መሆኑን በማመን የመደመር ዕሳቤ ለሁለንተናዊ ብልጽግና ወሳኝ በመሆኑ ፓርቲያችን አበክሮ እየሰራ ይገኛል።

መደመር በህብረብሔራዊ ወንድማማችነትና እህትማማችነት መርህ የሚመራ ሀገራዊ ብልጽግናን ለማረጋገጥ የምንጓዝበት መዳረሻ መንገዳችን ነው። ብልጽግና አሰባሳቢ ትርክትን በማስረጽ በተደማሪ አስተሳሰብ ሁለንተናዊ ከፍታን ለማረጋገጥ የሚተጋ ፓርቲ ነው። ፓርቲያችን ከሁሉም ለሁሉም የሆነ ዘመን ተሻጋሪ ግብን ያነገበ የአዲሱ ትውልድ ዕሳቤ ነው።

ዘመንን የዋጀ ግብና ራዕይ ዘመን ተሻጋሪ ዕሳቤ ላይ ሆኖ በመርህ ከተገራ ለሀገራዊ ብልጽግና ወሳኝ ነው። ለዚህም ነው ብልጽግና ዓላማቢስና መጨረሻ ግብ የሌላቸው ዕሳቤዎች በወል ዕውነት ሀገርን ከማጽናት ይልቅ በዋልታረገጥነት የተናጠል ዕውነትን በማንገብ ብቻ ከፋፋይና ሀገርን የማያሻግር ለጋራ ሀገርና ግብ ፀር መሆናቸውን በማመን አጥብቆ ይታገላል።

በመሆኑም የመደመር ትውልድ የጋራ ግብና ዕሳቤ ላይ በመጽናት ለትውልድ ተሻጋሪ የሆኑ ሁለንተናዊ ብልጽግናን የሚያበስሩ ስራዎችን እየሰራ ይገኛል። ብልጽግና ያስባል፤ ይሳራል፣ ግቡም የሁሉን ተጠቃሚነት ያረጋግጣል። ለዚህም የወል ዕውነትን የሚያፀና ብሔራዊ ገዥ ትርክትን በመትከል ለሁላችን የሆነች የነገ ትውልድ የሚመካባት የበለፀገች ኢትዮጵያን መገንባት ወሳኝ ነው።

03/06/2024

ከተረጂነት ወደ ምርታማነት ለመሸጋገር ያሉንን ፀጋዎች በአግባቡ በመጠቀም የምግብ ዋስትናችንን እናረጋግጥ !

ኢትዮጵያ ለብዙ አመታት የተረጂነት አስተሳሰብ ፈተና ሆኖባት ቆይታለች በተለይም ያሉንን የመሬት፣ የሰው ሀይል፣ የማእድንና የውሃ ሀብቶቻችን በአግባቡ ባለመጠቀማችን ምክንያት ለረጅም አመታት ከተረጂነት ለመላቀቅ አልተቻለም፤ ከተረጂነት ወደ ምርታማነት ለመሸጋገር ያሉንን እምቅ ሀብቶቻችን በአግባቡ በመጠቀም ተረጂነት አንገት የሚያስደፋ፣ የሚያዋርድ ብሎም የሀገር ሉአላዊነትን የሚያስደፍር ተግባር በመሆኑ በአስተሳሰብም ሆነ በተግባር ለመዋጋት እና የስራ ባህልን ለመቀየር ፓርቲያችን ትኩረት ሰቶ እየሰራ ይገኛል።

በቀጣይ እነዚህ ሀብቶቻችን በአግባቡ ከተጠቀምን በአጭር ጊዜ መለወጥ እንደሚቻልና ለዚህም ወጣቱ ያለው ሚና ከፍተኛ ስለሆነ የስራ ባህሉን በማሻሻል ፓርቲያችን በተለያዩ ጊዜያት በሚያመቻቸዉ የስራ እድል ተጠቃሚ በመሆን በተገኙ አጋጣሚዎች እድልን ወደ ድል መቀየር ይገባል፡፡

የከተማ ግብርናን በማስፋፋት የምግብ ዋስትናችን ለማረጋገጥ በግብርና ዘርፉ በትኩረት መስራት ግድ ይለናል፤ የአደጋ ጊዜ ስጋት ለመቋቋም እና ምላሽ ለመስጠት የሚሆኑ ስራዎቻችን ይበልጥ ለማጠናከር የመረዳዳት፣ የመደጋገፍ የአብሮነት እሴታችን ይበልጥ ማዳበርና ፀጋዎቻችንን በመለየት ወደ ተግባር መግባት ይጠበቅብናል ፡፡

በሌማት ትሩፋት ተግባራቶቻችን ያሳየነው ውጤት የይቻላል አስተሳሰብ በተጨባጭ ያሳየ እንደመሆኑ በቀጣይም በታቀዱ የልማት ስራዎቻችን ላይ አጠናክረን በማስቀጠል የተረጂነት አስተሳሰብ በመቅረፍ የብልጽግና ጉዞ ማረጋገጥ ይገባል ፡፡

03/06/2024

የወል ትርክታችንን እየገነባን የነገ ታሪካችንን በላባችን እውን እናደርጋለን!

የብሔር፣ የሀይማኖት፣ የባህል ወዘተ ብዝሀነቶች ፀጋዎቻችን ናቸው። የራሳችንን ማንነት አክብረን የሌሎችንም ማክበር ብቻ ሳይሆን ማስከበር ሰብአዊ ግዴታችን ነው።

ኢትዮጵያውያን ከውጭ የተቃጡብንን ጦርነቶች በጋራ የመመከት ባህል ቢኖረንም የውስጥ ችግሮቻችንን በውይይት የመፍታት ውስጣዊ መስተጋብር አላዳበርንም።

በታሪካችን ካለፍንባቸው በላይ ችግሮችን የተጋፈጡ ሀገሮች ትርክታቸውን በአዎንታ በመቃኘታቸው ሀገረ-መንግስት ግንባታቸውን አጠናቀዋል። ትርክትን በአሉታዊነት የቃኙት ደግሞ ተበታትነዋል፣ ተገዳድለዋል፣ ከነበሩበት ገናና ታሪክ ቁልቁል ተፈጥፍጠዋል።

የኢትዮጵያ ትርክት በአንድ በኩል ፍፁማዊ አንድነትን የሚሰብክ በሌላ በኩል ደግሞ ፍፁማዊ ልዩነትን የሚያቀነቅን ዋልታ ረገጥነት ተጫጭኖት ለዘመናት ዘልቋል። በሚዛናዊነት ላይ ያልቆመው፣ በተንሸዋረረ የታሪክ እይታ የሚባዝነው የአገራችን የተዛባ ትርክት በየጊዜው የሚያጋጥሙ ችግሮቻችን ምንጭ ነው።

ፓርቲያችን ብልፅግና ወንድማማችነትን፣ እህትማማችነትን እና ህብረብሔራዊነትን የሚያጎለብት የብሔራዊነትና የአርበኝነት ክብርን የሚያጎናፅፍ አሰባሳቢውንና ታላቁን አገራዊ ትርክት ለመገንባት እንቅስቃሴ ጀምሯል።

ትርክትን የምንገራው ኢትዮጵያዊ የመተሳሰብ፣ የመረዳዳት እና የመከባበር እሴቶቻችንን በማጎልበት ነው።

ከመጠላለፍ ይልቅ አብሮ መልማትን፣ ከመነቃቀፍ መተባበርን፣ ከመራራቅ መቀራረብን ምርጫችን ስናደርግ የወል ትርክታችን የተነሰነሰበትን አቧራ አራግፎ ይነሳል።

ከስሜታዊነት ይልቅ አስተዋይነትንና ሚዛናዊነትን፣ ከቂም በቀል ይልቅ ይቅር መባባልን፣ ባለፈ ትርክት ከመበላላት ይልቅ የነገን ታሪክ በጋራ መስራትን፣ ጠብመንጃ ከመማዘዝ ይልቅ ለሰላም መንበርከክን ባህል ስናዳብር የህብረ-ብሔራዊነታችንን በረከት እንቋደሳለን።

አሰባሳቢውን ታላቁን አገራዊ ትርክት ከማስረፅ ባለፈ ይህ ትውልድ በላቡ መስዋዕትነት ታሪክ እየሰራ መሆኑን ትናንትን፣ ዛሬን እና ነገአችንን አስተሳስሮ የያዘው የታላቁ ትርክት ውጤት የሆነው የአድዋ ድል መታሰቢያና የታላቁ የህዳሴ ግድባችንን ለአብነት መጥቀስ ይቻላል።

ታላቁ አገራዊ ትርክት በቤተሰብ የምንነጋገረው፣ በትምህርት ቤት የምናስተምረው፣ በየሀይማኖት ተቋሞቻችን የምንሰብከው፣ በየሚዲያው የምናሰራጨው ሀሳብ ውጤት በመሆኑ ለአንድ አካል ብቻ የሚተው ሳይሆን የሁላችንም ርብርብ የሚጠይቅ ነው።

ለበለጠ መረጃ:-

✅ Website = http://www.aaprosperityparty.org.et/
✅ Facebook:- 👉 አማርኛ =https://www.facebook.com/AddisAbabaPP?mibextid=JRoKGi
👉 Afan Oromo= https://www.facebook.com/PBFinfinnee?mibextid=ZbWKwL
👉 ትግርኛ = https://www.facebook.com/aappTigrigna?mibextid=ZbWKwL
✅ Twitter = https://x.com/aa_prosperity?t=TB_E6thmUUxQBsXEibRJbQ&s=09
✅ Tiktok = https://www.tiktok.com/.ababa.prosp?_t=8mfpA1zPvoT&_r=1
✅ Youtube = https://youtube.com/?si=9KuC45zwqmID9aZK
✅ Telegram = https://t.me/prosperityaddis
✅ whatsup = https://whatsapp.com/channel/0029Vagih5HBKfi0UeAEYL2r
✅ Instagram = https://www.instagram.com/addisababaprosperity?igsh=YzljYTk1ODg3Zg==

ላይ ይከታተሉን!
እናመሰግናለን!

Address

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Biruk posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Videos

Shortcuts

  • Address
  • Alerts
  • Videos
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share