East Gojjam Zone Police

  • Home
  • East Gojjam Zone Police

East Gojjam Zone Police Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from East Gojjam Zone Police, Media, .

የሁለት ሰዎች ህይወት አልፏል።«»«»«»««»«»«»«»ሀሜሌ 25 ቀን 2015ዓ/ምበደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር ቀበሌ 12 ልዩ ቦታው ጨሞጋ ድልድይ ላይ አካባቢ ፣ የህዝብ ማመላለሻ ኤፍ ኤ...
01/08/2023

የሁለት ሰዎች ህይወት አልፏል።
«»«»«»««»«»«»«»
ሀሜሌ 25 ቀን 2015ዓ/ም
በደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር ቀበሌ 12 ልዩ ቦታው ጨሞጋ ድልድይ ላይ አካባቢ ፣ የህዝብ ማመላለሻ ኤፍ ኤስ አር ተሽከርካሪ ከጭነት አይሱዙ ጋር በመጋጨቱ ምክንያት ፣

የጭነት አይሱዙው በግምት 10 ሜትር ርቀት ባለው ድልድይ ወንዝ ውስጥ በመግባቱ ወዲያውኑ የሁለት ሰዎች ህይወት ሲያልፍ ፣ ከባድ እና ቀላል የአካል ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች ወደ ደብረ ማርቆስ ሪፈራል ሆስፒታል ለህክምና መላካቸውን የደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ የመንገድ ትራፊክ ደህንነት ማረጋገጫ ዋና ክፍል ሀላፊ ኮማንደር ቢምረው አሰፋ ገልጸዋል ፡፡

በአደጋው ምክንያትም መንገድ በመዘጋቱ በክሬን ለማስከፈት ጥረት እየተደረገ መሆኑንም አስረድው፣
የአደጋውን መንስኤና ሙሉ መረጃውን በቀጣይ አጣርተን እንገልፃለን ብለዋል ።
-------------------------------------
መረጃው የደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ ህዝብ ቅንኙነት ነው ።

በአደጋው 6 ተማሪዎች ከባድ ጉዳት፤ ከ9 ያላነሱ ቀላል ጉዳት ደርሶባቸዋል ።"""""""""""""""""""""""""""""""""በምስራቅ ጎጃም ዞን የ12ኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪዎች ከደብረ ወ...
31/07/2023

በአደጋው 6 ተማሪዎች ከባድ ጉዳት፤ ከ9 ያላነሱ ቀላል ጉዳት ደርሶባቸዋል ።
"""""""""""""""""""""""""""""""""
በምስራቅ ጎጃም ዞን የ12ኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪዎች ከደብረ ወርቅ ወደ ደብረ ማርቆስ ዩንቨርስቲ ሲጓዙ በደረሰባቸው አደጋ ከባድ እና ቀላል ጉዳት ደርሶባቸዋል።

አደጋው የደረሠው ሀምሌ 23/2015 ዓ/ም ከጥዋቱ 4:30 በምስራቅ ጎጃም ዞን አነደድ ወረዳ አምበር ዙሪያ ቀበሌ ልዩ ቦታው " ዚባ " አካባቢ በሚገኝ ወንዝ ላይ ነው።

አደጋ የደረሰበት ከደብረ ወርቅ ከተማ ተነስቶ ወደ ደብረ ማርቆስ ሲጓዝ የነበረ " አባዱላ ሚኒባስ ኮድ 3-አማ 14062 " ሲሆን ወንዙ ውስጥ በመግባቱ ከባድ እና ቀላል ጉዳት ደርሷል።

እንደ አነደድ ፖሊስ መረጃ ስድስት ሠዎች ከባድ ጉዳት ደርሶባቸው ደብረ ማርቆስ ሪፈራል ሆስፒታል ተልከዋል።

ሌሎች ከዘጠኝ ያላነሱ የደረሰባቸው ጉዳት ቀላል በመሆኑ አምበር ጤና ጣቢያ ተረድተው ወደፈተና ቦታው ሄደዋል።

የደረሰውን አደጋ በተመለከተ በፍጥነት አደጋ መርማሪ ፓሊሶች ከቦታው ደርሰው የአደጋውን መንስኤ እያጣሩ መሆኑ የአነደድ ወረዳ ፓሊስ አሳውቋል።
"""""""""""""""""""""""""""""""""
መረጃው አነደድ ወረዳ ፖሊስ ህዝብ ግንኙነት ነው ።

 # #ህልውና የሆነውን ሰላም በዘላቂነት ለማስፈን የህብረተሰቡ ድርሻ ወሳኝ መሆኑ ተገለጸ።»»»»»»»»»»»»»»»»»»»»የምስራቅ ጎጃም ዞን የማቻክል ወረዳ  አስተዳድር ምክር ቤት"ህልውናች...
28/07/2023

# #ህልውና የሆነውን ሰላም በዘላቂነት ለማስፈን የህብረተሰቡ ድርሻ ወሳኝ መሆኑ ተገለጸ።
»»»»»»»»»»»»»»»»»»»»
የምስራቅ ጎጃም ዞን የማቻክል ወረዳ አስተዳድር ምክር ቤት"ህልውናችን ለሆነው ሰላም ዘብ እንቆማለን" በሚል መሪ ሃሳብ የወረዳችን ታዳጊ ከተማ ነዋሪዎች፣ወጣቶች፣አመራሮች ፣የሃይማኖት አባቶች እንዲሁም የሃገር ሽማግሌዎች በተገኙበት በወቅታዊ የወረዳችን የሰላም እና ጸጥታ ጉዳዮች ዙርያ ውይይት እየተካሄደ ነው።

በውይይቱ ህልውና ለሆነው ሰላም ዘላቂነት ህብረተሰቡ ከመንግት ጎን ሊቆም ይገባል፣ ሰላም ከሌለ ወጦ መግባት አይቻልም፣ ሰላም የልማታችን መሰረት ነው፣ ሰላምን በዘላቂነት ለማስፈን የሃገር ሽማግሌዎች እና የሃይማኖት የድርሻቸውን ሊወጡ ይገባል በውይይቱ ተሳታፊዎች የተነሱ ሃሳቦች ዋናዋና ሃሳቦች ሲሆኑ በሁሉም ቀጠናዎች ስምሪት የተሰጣቸው አመራሮች እና የጸጥታ አካላት ምላሽ ሰጠዋል።

በወረዳችን ቀጠናዎች የተካሄደውን የሰላም ውይይት አስመልክተው ማብራሪያ የሰጡት የወረዳው አስተዳዳሪ እና የጸጥታ ምክር ቤት ሰብሳቢ አቶ ታምሩ ዘውዴ ውይይቱ በደጋ -ሰኝን ታዳጊ ከተማ እና በሌሎች የወረዳችን ታዳጊ ከተምች ላይ ህልውና በሆነው ሰላም ላይ ከሰላም ወዳድ ወጣቶች፣ነዋሪዎች፣የሃገር-ሽማግሌዎች ፣የሃይማኖት አባቶች ጋር ውይይት መካሄድን በመግለጽ ለመኖር ህልውና የሆነውን ሰላም በዘላቂነት ለማስፈን የወረዳው ህዝብ ከመንግስት ጎን እንዲቆም ጥሪ አቅርበዋል።

አቶ ታምሩ አያይዘው የወረዳችህዝብ ሰላም በዘላቂነት ለማስከበር ከሃገር ሽማግሌዎች እና ወጣቶች የተወጣጣ 13 አባል ያለው የሰላም አምባ አሳደር ኮሜቴ በማቋቋም በወረዳው አስተዳዳድር ምክር ቤት ዕውቅና መሰጠቱን ተናግረዋል።
----------------------------------
via~ ማቻከል ወረዳ ኮሙኒኬሽን ።

የመጀመሪያው የዙር የ12ኛ ክፍል ማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ፈተና በሰላም መጠናቀቁን የምስራቅ ጎጃም ዞን ትምህርት መምሪያ    ገለፀ ። ❞❞❞❞❞❞❞❞❞❞❞❞❞❞❞❞❞❞❞ፈተናው በሰላም እንዲጠ...
28/07/2023

የመጀመሪያው የዙር የ12ኛ ክፍል ማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ፈተና በሰላም መጠናቀቁን የምስራቅ ጎጃም ዞን ትምህርት መምሪያ ገለፀ ።
❞❞❞❞❞❞❞❞❞❞❞❞❞❞❞❞❞❞❞
ፈተናው በሰላም እንዲጠናቀቅ የተረባረባችሁ አካላትን በሙሉም ምስጋናችን ይድረሳችሁ ሲሉ የምስራቅ ጎጃም ዞን ትምህርት መምሪያ ሀላፊ አቶ ጌታሁን ፈንቴ ገልጸዋል ።
˝˝˝˝˝˝˝˝˝˝˝˝˝˝˝˝˝˝˝˝˝˝˝
የ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሃገር-አቀፍ የ12ኛ ክፍል ፈተና በሁለት ዙር በዩንቨርስቲዎች እየተሰጠ መሆኑ ይታወቃል።

በዚህም መሰረት ከ14,279 በላይ የሚሆኑት የምስራቅ ጎጃም ዞን የ12ኛ ክፍል ማህበራዊ ሳይንስ ተፈታኝ ተማሪዎች በባህርዳር፤በመካነሰላምና በደብረማርቆስ ዩንቨርስቲዎች ተመድበው ከሀምሌ 19-21/2015 ዓ.ም ለተከታታይ ሶስት ቀናት የተሰጠውን የማህበራዊ ሳይንስ ፈተና በመልካም ስነ-ምግባር አጠናቀዋል።

የባለፈው ዓመት ችግር እንዳይደገምና የፈተና ሂደቱ እንዳይታወክ የተሰራው ጠንካራ የቅድመ-ዝግጅት ስራ እና የባለድርሻ አካላት የትብብርና የቅንጅት ስራ ፈተናው በሰላም እንዲጠናቀቅ ምክንያት ሁኗል ብለዋል መምሪያ ሀላፊው ።

የተማሪዎቻችንን ውጤትና ስነ-ምግባር ለማሻሻል በበጀት ዓመቱ የተከናወኑ ተግባራትም እጅግ መልካም ነበሩ ያሉት አቶ ጌታሁን። የቅድመ ዝግጅት ስራ በአግባቡ መስራት ለተግባር ምዕራፍ ስራው ስኬታማነት ቁልፍ መንደርደሪያ መሆኑንም በዚህ ዓመት በተሰጠው የ12ኛ ክፍል ሃገር አቀፍ ፈተና አፈጻጸም ማረጋገጥ ችለናል ብለዋል ።

የፈተና ሂደቱ እጅግ ሰላማዊና የተረጋጋ እንዲሁም የተሻለ ልምድ የተወሰደበትም ነበር።ተማሪዎቻችንን ከቀለም ትምህርት በዘለለ በስነ-ምግባር ማነጽ ቁልፍ ተልዕኮ ተደርጎ ሲሰራ በመቆየቱ የተሻለና ተደማሪ ስኬት ታይቶበታል። እንደነዚህ አይነት ተግባራት በሃገር አቀፍ ፈተና ብቻ ሳይሆን በክፍል ምዘናዎችና አጠቃላይ በመማር ማስተማር ሂደቱ ተጠናክረው የሚቀጥሉ ይሆናልም ብለዋል ።

የመጀመሪያው ዙር ተፈታኝ ተማሪዎቻችን የፈተና ሂደት ሰላማዊ ሁኖ እንዲጠናቀቅ ሌት ከቀን ያለመታከት የተጋችሁ የፈተና አስፈጻሚዎች፤የዩንቨርስቲ አመራሮችና የግብረሃይል አባላት፤ለፈተና ስራው የተመደባችሁ የጸጥታ አባላትና አመራሮች፤የትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ ተጠሪ መ/ቤት ሰራተኞችና የተሽከርካሪ ባለቤቶች እንዲሁም አሽከርካሪዎች ፤በየደረጃው የምትገኙ አመራሮች፤የተማሪዎችን እውቀትና ስነምግባር ለማስተካከል ሌት ከቀን የደከማችሁ ውድ መምህራንና የትምህርት አመራሮች፤የመልካም ስነ-ምግባር ባለቤት በመሆን አደራችሁን የተወጣችሁ ውድ ተፈታኝ ተማሪዎችና ወላጆች ፤በጥቅሉ የፈተና ሂደቱ ሰላማዊ ሁኖ እንዲጠናቀቅ ድርሻችሁን የተወጣችሁ አካላት በሙሉ በነበራችሁ የስራ ትጋትና የባለቤት ስሜት በእጅጉ ኮርተንባችኋል፤ምስጋናችንም በእጅጉ ከፍ ያለ ነውና በዞናችን የትምህርት ማህበረሰብ ስም ከልብ እናመሰግናችኋለን ብለዋል አቶ ጌታሁን ፈንቴ ።

ለትውልድ ማሰብ፤ለሃገር ግንባታ መጨነቅ፤ለጋራ ተልዕኮ በጋራ መረባረብና ባለቤት ሁኖ ያለድካም መታከት ፤መደማመጥና ተቀናጅቶ መስራት በእጅጉ የታየበት የፈተና አፈጻጸም ነበር ያሉት መምሪያ ሀላፊው ።

ይህ መልካም አፈጻጸም ቀጣይ ከሀምሌ 25-28/2015 ዓ.ም በሚሰጠው ሁለተኛው ዙር የተፈጥሮ ሳይንስ ፈተናም ከመጀመሪያው ዙር ባደገ መልኩ እንደሚፈጸም በመተማመን ለተፈታኝ ተማሪዎቻችን በሙሉ መልካም የፈተናና ጊዜ እንዲሆንላቸው እመኛለሁ ሲሉ የምስራቅ ጎጃም ዞን ትምህርት መምሪያ ሀላፊ አቶ ጌታሁን ፈንቴ በግል የፌስ ቡክ ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት ገልጸዋል ።

ምክትል ኮማንደር ደባሱ በላይ የ4ኛ ዋና ፖሊስ ጣቢያ ሀላፊ ሆነው ተመደቡ ።˝˝˝˝˝˝˝˝˝˝˝˝˝˝˝˝˝˝˝˝˝˝˝ምክትል ኮማንደር   ደባሱ በላይ የደብረ ማርቆስ ከተማ  አስተዳደር ንጉስ ተክ...
27/07/2023

ምክትል ኮማንደር ደባሱ በላይ የ4ኛ ዋና ፖሊስ ጣቢያ ሀላፊ ሆነው ተመደቡ ።
˝˝˝˝˝˝˝˝˝˝˝˝˝˝˝˝˝˝˝˝˝˝˝
ምክትል ኮማንደር ደባሱ በላይ የደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር ንጉስ ተክለሀይማኖት ክፍለ ከተማ የ4ኛ ዋና ፖሊስጣቢያ ሀላፊ ሆነው መመደባቸው ታውቋል ፡፡

ከፍተኛ መኮንኑ በአላቸው የካበተ አመራርነት ልምድ ፣መልካም ስነምግባር ፣የስራ ተነሳሽነት፣ የትምህርት ደረጃ እና ቁርጠኝነት መሠረት አድርገው መመደባቸውን ከተቋሙ ያገኘነው መረጃ ይጠቁማል፡፡

ምክትል ኮማንደር ደባሱ በላይ በምስራቅ ጎጃም ዞን እና በደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር ውስጥ ለበርካታ አመታት በተለያዩ ፖሊሳዊ ሀላፊነቶች ተመድበው በውጤታማነት ሲያገለግሉ የቆዩ ከመሆኑም በላይ፣

እጅግ ስራ ወዳድ የሆኑና ደከመኝ ሰለቸኝ የማያውቁ ፣ ታማኝ ሀቀኛና እውነት ደፋሪ የሆኑ፣ ለህዝብ ሰላምና ደህንነት መከበር ሌት ከቀን ካለ እረፍት በመስራት የሚታወቁ ታታሪ የፖሊስ መኮንን ናቸው ፡፡

በዛሬው ዕለትም በተመደቡበት የ4ኛ ዋና ፖሊስ ጣቢያ በመገኘት ከአመራሩ እና ከአባላት ጋር በመገናኘት ስለ አጠቃላይ የክፍለከተማው ሁኔታ ከዞን አመራሮች ጋር በመሆን ትውውቅ አድርገዋል ፡፡

ምክትል ኮማንደር ደባሱ በላይ የትግራይ ወራሪ ሀይል ሀገሪቱን በወረረበት ወቅት ሀገራዊ ጥሪውን በመቀበል በአቀስታ ግንባር የጦር መሪ ሆነው በመዝመት ህዝብ እና መንግስት የጣለባቸውን ግዳጅ በቁርጠኝነት እና በብቃት የተወጡ ከፍተኛ መኮነን ናቸው ፡፡
❞❞❞❞❞❞❞❞❞❞❞❞❞❞❞❞❞❞
መልካም የስራ ዘመን ።
----------------------------------
መረጃው ፦ የደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ ህዝብ ግንኙነት ነው

የመጀመሪያ ዙር የማህበራዊ ሳይንስ ተፈታኝ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ወደሚፈተኑበት ዩንቨርስቲ በሰላም ገብተዋል!!»»»»»»»»»»»»»»»»»»»»»»»»14,279 የመጀመሪያ ዙር የ12ኛ  ክፍል...
24/07/2023

የመጀመሪያ ዙር የማህበራዊ ሳይንስ ተፈታኝ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ወደሚፈተኑበት ዩንቨርስቲ በሰላም ገብተዋል!!
»»»»»»»»»»»»»»»»»»»»»»»»
14,279 የመጀመሪያ ዙር የ12ኛ ክፍል የማህበራዊ ሳይንስ ተፈታኝ ተማሪዎች በ4ቱም የፈተና ማዕከላት በሰላም መግባታቸው የምስራቅ ጎጃም ዞን ትምህርት መምሪያ ሀላፊ አቶ ጌታሁን ፈንቴ ገልጸዋል።

ተማሪዎች ከሀምሌ 19_21/2015 ዓ.ም በባህርዳር፤በመካነሰላም እና በደብረማርቆስ ዩንቨርስቲዎች ለተከታታይ 3 ቀናት ፈተናቸውን የሚወስዱ ይሆናል።

መምሪያ ሀላፊው እንደገለጹት ይህን ጉዞ በማስተባበር ሂደት ትልቁን ኃላፊነት የወሰዳችሁ በየደረጃው ያላችሁ አመራሮች፤የጸጥታ መዋቅር አባላትና አመራሮች፤የተሽከርካሪ ባለቤቶችና አሽከርካሪዎች፤ የመንገድ ደህንነት ባለሙያዎች፤የትምህርት ቤተሰብ ፤በየአካባቢው ያላችሁ የዩንቨርሲቲ አመራሮችና ሰራተኞች እንዲሁም ሌሎችም አካላት ሁሉ ልባዊ ምስጋናዬን እያቀረብኩ ይህ የቅንጅት ስራ ቀጣይም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል እምነቴ ጽኑ ነው ብለዋል።

እነዚህ ተማሪዎች ቀጣይ ሀምሌ 22 እና 23 ወደ አካባቢያቸው ስለሚመለሱና የሁለተኛ ዙር ተፈታኞችም በተመሳሳይ ቀናት ወደ ዩንቨርስቲ ስለሚገቡ ይህንን ሊመጥን የሚችል ቅድመ ዝግጅት እንዲደረግ ከአደራ ጋር አሳስበዋል !!

ሁላችንም ዓመቱን ሙሉ የደከምንበትን ውጤት እንደምናስመዘግብ ተስፋ በማድረግ ለተፈታኝ ተማሪዎቻችን መልካም የፈተናና የስኬት ጊዜ እንዲገጥማቸው ከልብ እመኛለሁ ሲሉ አቶ ጌታሁን ፈንቴ ገልጸዋል !!

23/07/2023
የ12ኛ ክፍል ሃገር-ዓቀፍ ፈተና ቅድመ ዝግጅት መጠናቀቁ ተገለጸ !!»»»»»»»»»»»»»»»»»»» የምስራቅ ጎጃም ዞን ትምህርት መምሪያ የ12ኛ ክፍል ሃገር-ዓቀፍ ፈተና ለማስፈተን ቅድመ-ዝ...
23/07/2023

የ12ኛ ክፍል ሃገር-ዓቀፍ ፈተና ቅድመ ዝግጅት መጠናቀቁ ተገለጸ !!
»»»»»»»»»»»»»»»»»»»
የምስራቅ ጎጃም ዞን ትምህርት መምሪያ የ12ኛ ክፍል ሃገር-ዓቀፍ ፈተና ለማስፈተን ቅድመ-ዝግጅቱን ያጠናቀቀ መሆኑን ገልጿል።

በበጀት ዓመቱ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎችን ውጤትና ስነምግባር ለማሻሻል በየደረጃው በርካታ ተግባራት ሲከናወኑ መቆየታቸውን የገለጸው መምሪያው ።

የተማሪዎችን ውጤትና ስነምግባር ለማሻሻል ሲደረግ የነበረው አጠቃላይ እንቅስቃሴ በእጅጉ አበረታች እንደነበር ጠቅሶ ፣ በተለይም መምህራንና የትምህርት አመራሩ የተማሪዎችን ውጤት ለማሻሻል የነበራቸው ብርቱ ጥረት በእጅጉ የሚመሰገን ነበር ብሏል ።

የዚህ ዓመት የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ሃገር-ዓቀፍ ፈተና እንደባለፈው ዓመት በዩንቨርስቲዎች የሚሰጥ ሲሆን ፣ በዞኑ ውስጥ የሚገኙ ተማሪዎችም በ3 ዩንቨርስቲዎች እና በ4 የፈተና ጣቢያዎች ፈተናውን የሚወስዱ መሆኑን ገልጿል ።

በመጀመሪያው ዙር የፈተና ፕሮግራም 14,371 የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ከሀምሌ 19-21/2015 ዓ.ም ፈተናቸውን እንደሚወስዱና ፣ በተመሳሳይ ከሀምሌ 25-28/2015 ዓ.ም በሁለተኛው ዙር በሚሰጠው የተፈጥሮ ሳይንስ ፈተና 10,104 ተማሪዎች የሚፈተኑ ይሆናል ብሏል ።
በአጠቃላይ በሁለቱም ዙር በመደበኛና በግል 24,458 ተማሪዎች እንደሚፈተኑ ገልጿል።

በአጠቃላይ የፈተና ሂደቱ በሰላማዊ መንገድ እንዲጠናቀቅ በየደረጃው የሚገኘው የፈተና አስተዳደር ግብረሃይል በበቂ ሁኔታ የቅድመ-ዝግጅት ስራዎችን ማጠናቀቁንና። በዚህም የመጀመሪያ ዙር የማህበራዊ ሳይንስ ተፈታኞች ከሀምሌ 16-17/2015 ዓ.ም ወደሚፈተኑበት ዩንቨርስቲ የሚጓጓዙ ይሆናልም ተብሏል።

ተማሪዎችን በማጓጓዝ ሂደት የአሽከርካሪ ባለቤቶች፤ አሽከርካሪዎች ፤ የትምህርት አመራሮች፤የጸጥታ አመራሩና አባላት እንዲሁም በየደረጃው ያለው አመራር በቅንጅት በመስራት የፈተና ሂደቱ ሰላማዊ በሆነ መንገድ እንዲጠናቀቅ የበኩላችሁን ድርሻና የዜግነት ግዴታ እንድትወጡ አደራ እያልኩ ለተፈታኝ ተማሪዎቻችን መልካም የፈተና ጊዜ እንዲሆንላቸውና የተሻለ ውጤት እንዲያስመዘግቡ ከልብ እመኛለሁ ሲሉ የምስራቅ ጎጃም ዞን ትምህርት መምሪያ ሀላፊ አቶ ጌታሁን ፈንቴ ገልጸዋል ።

 #የሟቾችን  #ነፍስ  #ይማር  """""""""""""""""""""""""""""""በደብረማርቆስከተማ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ5 ሰዎች ህይወት አለፈ፡፡በደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር  በተ...
23/07/2023

#የሟቾችን #ነፍስ #ይማር
"""""""""""""""""""""""""""""""
በደብረማርቆስከተማ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ5 ሰዎች ህይወት አለፈ፡፡

በደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር በተድላ ጓሉ ክፍለከተማ ቀበሌ 18 ልዩ ቦታው እነችፎ ቡልቸድ ተብሎ ከሚጠራው ቦታ ላይ ሐምሌ 15/2015 ከምሽቱ 12፡00 ሰዓት ከደብረ ማርቆስ ወደ መካልያ ሲሄድ የነበረ ኮድ (3)05722 አማ የህዝብ ማመላለሻ አይሱዙ የፌደራል ፖሊስ አሳፍሮ ከአዲስ አበባ ወደ ባህርዳር ይጓዝ ከነበረ አውቶብስ ጋር በመጋጨቱ ወድያውኑ ከአይሱዙው 3 ሰው ከአውቶብሱ 2 ሰው በድምሩ የ5 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ ቁጥራቸው በውል ያልታወቁ ሰዎች ከባድ እና ቀላል ጉዳት ደርሶባቸዋል።

ተጎጅዎቹ በደብረ ማርቆስ ሪፈራል ሆስፒታል ገብተው ህክምና እየተደረገላቸው መሆኑን የደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ የመንገድ ትራፊክ ደህንነት ማረጋገጫ ዋና ክፍል ሀላፊ ኮማንደር ቢምረው አሰፋ ገልጸዋል ሲል የደብረ ማርቆስ ፖሊስ መምሪያ ገልጿል ፡

የአደጋውን መንስኤና አጠቃላይ መረጃ አጣርቶ እንደሚያደርስ ፖሊስ አስታውቋል።

የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከሐምሌ 19 ጀምሮ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ይሰጣል።---------------------------------የተፈታኝ ተማሪዎች መብቶች፦ ➭ ከፈተና ጥያቄ ውጪ ማንኛ...
20/07/2023

የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከሐምሌ 19 ጀምሮ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ይሰጣል።
---------------------------------
የተፈታኝ ተማሪዎች መብቶች፦

➭ ከፈተና ጥያቄ ውጪ ማንኛውንም ያልተረዳውን ነገር ጠይቆ የመረዳት መብት አላቸው።

➭ በዩኒቨርሲቲ ግቢ ውስጥ የምግብ፣ የህክምና አገልግሎት፣ የማደሪያ ክፍል፣ ፍራሽ እና ትራስ የማግኘት መብት አላቸው።

➭ ማንኛውም ተፈታኝ በዩኒቨርሲቲ ግቢ ውስጥ ያለውን የቤተ መፅሐፍት፣ የመጸዳጃ ቤቶች፣ የሻወር፣ የካፍቴሪያዎች፣ የሚኒ ሱፐር ማርኬቶች፣ የተለያዩ ሱቆች እንዲሁም የመናፈሻና መዝናኛ አገልግሎቶችን የመጠቀም መብት አላቸው።

➭ ዩኒቨርሲቲ ግቢ ውስጥ የጋራ የደህንነት ጥበቃ የማግኘት መብት አላቸው።

➭ በፈተና ሰዓት መፈተኛ ክፍል ገብቶ ብርሃናማ የመፈተኛ ቦታ፣ ወንበርና መፃፊያ ጠረጴዛ የማግኘት መብት አላቸው።

➭ ፈተና ከመጀመሩ አንድ ቀን ቀድሞ ስለፈተናው ገለጻ (ኦሬንቴሽን) የማግኘት መብት አላቸው።

የተፈታኝ ተማሪዎች ግዴታዎች፡-

➤ ማንኛውም ተፈታኝ በፈተና ማዕከልና መፈተኛ ክፍል አድሚሽን ካርድ ይዞ የመገኘት ግዴታ አለበት።

➤ ማንኛውም ተፈታኝ ወደ ዩኒቨርሲቲ ሲመጣ የትምህርት ቤት ወይም የነዋሪነት መታወቂያ ይዞ መገኘት አለበት።

➤ ማንኛውም ተፈታኝ ወደ ግቢ ከመግባቱ በፊትና ወደ መፈተኛ ክፍል ከመግባቱ በፊት ሙሉ አካላዊ ፍተሻ የመፈተሽ ግዴታ አለበት።

➤ ማንኛውም ተፈታኝ በዩኒቨርሲቲ ግቢና በመፈተኛ ክፍል የተከለከሉ ዕቃዎችን መያዝ የለበትም።

➤ ማንኛውም ተፈታኝ እርሳስ፣ ላጲስና የእርሳስ መቅረጫ ይዞ መገኘት አለበት።

➤ ማንኛውም ተፈታኝ የፈተና ደንብን የማክበር ግዴታ አለበት።

➤ ማንኛውም ተፈታኝ በፈተና ማዕከል/በመፈተኛ ክፍል ውስጥ የፈተና አስፈጻሚዎች የፈተና አስተዳደር ሥራን ውጤታማ ለማድረግና ሁኔታዎችን ለማመቻቸት የሚያደርጉትን ጥረት የመተባበር ግዴታ አለበት።

➤ ማንኛውም ተፈታኝ ፈተና ከመጀመሩ በፊት መፈተኛ ክፍል የመገኘት ግዴታ አለበት።

➤ ተፈታኙ ፈተናው ሳይጠናቀቅ ከፈተና ክፍል የሚወጣ ከሆነ የፈተና ጥያቄ የያዘውን ቡኩሌት ለፈታኙ የማሰረከብ ግዴታ አለበት።

➤ ማንኛውም ተፈታኝ ወደተመደበበት ዩኒቨርሲቲ ሲመጣ አንሶላ፣ ብርድ ልብስ እና የትራስ ጨርቅ ይዞ የመምጣት ግዴታ አለበት።

ለተፈታኝ ተማሪዎች የተፈቀዱ ነገሮች፦

➣ አዲስ ወይም ቀድሞ ለመማር እና ለማጥናት ሲጠቀሙበት የነበሩ ማስተወሻ ደብተር፣ የትምህርት መፅሐፍ፣ መንፈሳዊ/ኃይማኖታዊ መፅሐፍት፣ ባዶ ወረቀት

➣ ደረቅ ምግቦች (ጩኮ፣ በሶ፣ ዳቦ ቆሎ፣ ቆሎ….)

➣ ገንዘብ (ብር)

➣ የልብስ ወይም የእጅ ቦርሳ፣ የግል ልብስ፣ ጫማ

➣ የግል ንጽህና መጠበቂያዎች (ሳሙና፣ ሞዴስ፣ የጥርስ ብሩሽ፣ የጥርስ ሳሙና፣ ፎጣ፣ ሶፍት፣ ሻምፖ፣ ኮንዲሽነር፣ ሎሽን፣ ቻፕስቲክ፣ የጸጉር ቅባት፣ የፊት ቅባት)

ለተፈታኝ ተማሪዎች የተከለከሉ ነገሮች፦

➣ ማንኛውንም ዓይነት የጦር መሣሪያ ይዞ መገኘት የተከለከለ ነው፡፡

➣ ማንኛውንም ዓይነት ስለት እና ሹልነት ያላቸውን ብረታ ብረቶችና ጠንካራ ፕላስትኮች ይዞ መገኘት የተከለከለ ነው።

➣ ማንኛውም ድምጽ የሚቀዳ፣ ፎቶ የሚያነሳ፣ ቪዲዮ የሚቀርጽ፣ ከቴሌ መስመርም ሆነ ከቴሌ መስመር ውጭ መልዕክት በዲጂታል መንገድ የሚሰጥ ወይም የሚቀበል የግል ዕቃ/መሳሪያ/የቴክኖሎጂ ውጤት፣ ስልክ፣ አይ-ፓድ፣ ታብሌት፣ ኮምፕዩተር፣ ላፕቶፕ፣ ስማርት ሰዓት፣ ማጂክ ብዕር/እስክሪብቶ፣ ማጂክ ኮት/ጃኬት እና ሌሎች ማንኛቸውም ፎቶ፣ ምስል እና ድምጽ የሚቀርጹ የኤሌክትሮኖክስ መሣሪያዎችን በዩኒቨርሲቲው ግቢ ውስጥም ሆነ ግቢ ዙሪያ ይዞ መገኘት ወይም መጠቀም የተከለከለ ነው፡፡
----------------------------------
አቶ ጌታሁን ፈንቴ የምስራቅ ጎጃም ዞን ትምህርት መምሪያ ሀላፊ ።

ገዳማውያኑ ወደ በዓታቸው እየተመለሱ ነው++++++++++++++++በምሥራቅ ጎጃም ሀገረ ስብከት በደብረ ኤልያስ ወረዳ የሚገኘው የብሔረ ብጹዓን አፄ መልክዓ ሥላሴ ገዳም መነኮሳት ወደ ገዳማቸው...
19/07/2023

ገዳማውያኑ ወደ በዓታቸው እየተመለሱ ነው
++++++++++++++++
በምሥራቅ ጎጃም ሀገረ ስብከት በደብረ ኤልያስ ወረዳ የሚገኘው የብሔረ ብጹዓን አፄ መልክዓ ሥላሴ ገዳም መነኮሳት ወደ ገዳማቸው እየተመለሱ መሆናቸው ተገለጠ።

ባለፈው ጊዜ በገዳሙ በተከሰተው ከፍተኛ ችግር ምክንያት ከበዓታቸው ወጥተው የነበሩ አባቶችንና እናቶችን ወደ ቀደመ ቦታቸው እንዲመለሱና ገዳማዊ ህይወታቸውን እንዲቀጥሉ የማድረግ ሥራ በሀገረ ስብከቱና በሌሎችም አካላት ትብብር እየተሠራ መሆኑን ከሀገረ ስብከቱ ጽ/ቤት የተገኘው መረጃ አብራርተል።

ይህ የተገለጠው ዛሬ ሐምሌ ፲፪ ቀን ፳፻፲፭ ዓ. ም ለመመለስ ፈቃደኛ ለሆኑ እናቶችና አባቶች በሀገረ ስብከቱ ግቢ ውስጥ በብፁዕ አቡነ ዲዮናስዮስ የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ጸሎትና ቡራኬ ሽኝት በተደረገበት ወቅት ነው።

ገዳማውያኑ በሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ጸሎትና ቡራኬ ከተቀበሉ በኋላ በሀገረ ስብከቱ ዋና ጸሐፊና በሀገረ ስብከቱ የገዳማት ክፍል ኀላፊ መሪነት ወደ ገዳማቸው እንዲጓዙ ተደርጓል።

ሌሎችንም አባቶችና እናቶች ወደ ገዳሙ የመመለስ ሥራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የገለጠው ሀገረ ስብከቱ በችግሩ ምክንያት ከገዳማቸው ተፈናቅለው በተለያዩ አካባቢዎች ያሉ አባቶችና እናቶች እንደ ዛሬዎቹ ሁሉ ወደ ገዳማቸው እንዲመለሱ ጥሪ አቅርቧል።
+++++++++++++++
ሐምሌ12/2015 ዓ.ም
የምስራቅ ጎጃም ሀገረ ስብከት የህዝብ ግንኙነት ክፍል ።
ደ/ማርቆስ

እራሱን ያገተው አጋች»»»»»»»»»»»»»»»»»»በውሸት ታግቻለሁ በማለት ቤተሰቦቹን  500 መቶ ሽ ብር  የጠየቀው ግለሰብ ከወንጀል ተባባሪዎቹ ጋር በፖሊሰ  ቁጥጥር ስር ዋለ።ሀምሌ 10/2...
18/07/2023

እራሱን ያገተው አጋች
»»»»»»»»»»»»»»»»»»
በውሸት ታግቻለሁ በማለት ቤተሰቦቹን 500 መቶ ሽ ብር የጠየቀው ግለሰብ ከወንጀል ተባባሪዎቹ ጋር በፖሊሰ ቁጥጥር ስር ዋለ።

ሀምሌ 10/2015 ዓ/ም ሳይታገት ታግቻለሁ በማለት ቤተሰቦቹን 500 መቶ ሽ ብር የጠየቀው ተጠርጣሪ ግለሰብ ከደቡብ ወሎ ዞን መካነ ሰላም ወረዳ ወደ ደሴ በመምጣት ደሴ ከተማ ቧንቧ ውሀ ክፍለ ከተማ በካራ ጉቱ ከሚባለው አካባቢ ጫካ ውስጥ በመግባት ከጓደኛው ጋር በመመካከር ጓደኛው የታገተ በማስመሰል እራሱን በገመድ ዛፍ ጋር በማሰር ፎቶውን ለቤተሰቦቹ በመላክና በስልክ 500 መቶ ሽ ብር ላኩልኝ በማለት ይነግራቸዋል ቤተሰቦቹም ጉዳዩን ለፓሊስ ያመለክታሉ ።

ፓሊስም የደረሰውን ጥቆማ ልዩ ትኩርት በመስጠት ልዩ የመረጃ መረቡን በመዘርጋት ባደረገው ከፍተኛ ክትትል ታግቻለሁ እያለ ቤተሰቦቹን እና የአካባቢውን ሰው ያስጨነቀው ተጠርጣሪ ከሌሊቱ 07:00 ስዓት በህብረተሰቡ ጥቆማ መነሀሪያ አካባቢ አልጋ ቤት ውስጥ ከወንጀል ተባባሪዎቹ ጋር በቁጥጥር ስር ማዋሉን የደሴ ከተማ አሰተዳደር ፖሊሰ መምሪያ ሚዲያና ኮሚኒኬሽን ዋና ክፍል ገልጿል ።
amara police commission

13 ሰዎች በትራፊክ አደጋ ሞቱ„„„„„„„„„„„„„„„„„„„„„„„„„ ከአዲስ አበባ በስተሰሜን በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ውስጥ በደረሰ የትራፊክ አደጋ አንዲት እና አራት ልጆቿን ጨምሮ 13...
17/07/2023

13 ሰዎች በትራፊክ አደጋ ሞቱ
„„„„„„„„„„„„„„„„„„„„„„„„„

ከአዲስ አበባ በስተሰሜን በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ውስጥ በደረሰ የትራፊክ አደጋ አንዲት እና አራት ልጆቿን ጨምሮ 13 ሰዎች ሞቱ።

እሁድ ሐምሌ 9/2015 ዓ.ም. ንጋት ላይ በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ደገም ወረዳ ወረቢ ተብሎ በሚጠራው ስፍራ በደረሰ አሰቃቂ የትራፊክ አደጋ አንዲት እናትና አራት ልጆቿን ጨምሮ የ 13 ሰወች ሂወት አልፏል ።

ለዚህ የትራፊክ አደጋ መከሰት ምክንያት የሆነው ቁልቁለት ቦታ ላይ ከባድ የጭነት መኪና በሕዝብ ማመላለሽ ሚኒባስ ላይ ስለወጣበት መሆኑን በደገም ወረዳ ፖሊስ ጽሕፈት ቤት ባልደረባ የሆኑት ኢንስፔክተር ሽመልስ ቦሬሳ ለቢቢሲ ተናግረዋል።

ኢንስፔክተሩ እንዳሉት አደጋውን ያደረሰው የጭነት ተሽከርካሪ ከአዲስ አበባ ወደ ባሕር ዳር 500 ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ ጭኖ ሲጓዝ የነበረ ተሳቢ መኪና ሲሆን፣ “ቁልቁለት ላይ ጥንቃቄ በጎደለው ሁኔታ ሲጓዝ ነበር” ብለዋል።

ከባድ ተሸከርካሪው ቁልቁለት መንገድ ላይ ከቁጥጥር ውጭ ከሆነ በኋላ፣ ሁለት መኪኖችን ገጭቶ በመጨረሻ የሕዝብ ማመላለሻ ሚኒባስ መኪና ላይ ሙሉ በሙሉ ስለወጣበት በውጡ የነበሩ ሰዎችን ለሞት ዳርጓል።

በአደጋው ሕይወታቸውን ካጡት 13ቱ ሰዎች መካከል መምህርት አስመሬ ጎሶማ እና አራት ልጆቿ ይገኙበታል።

መምህርቷ የ18፣ 15፣ 8 እና የ1 ዓመት ልጆቻቸውን ይዘው ከአዲስ አበባ ወደ ጎሃ ጽዮን ቤተሰብ ጥየቃ እየጓዙ የነበረ ሲሆን፣ በአደጋው የእናት እና የሁሉም ልጆቻቸው ሕይወት አልፏል።

ኢንስፔክተር ሽመልስ ቦሬሳ እንዳሉት የትራፊክ አደጋው እንደደረሰ 13ቱ ሰዎች ወዲያውኑ ሕይወታቸው ማለፉን ገልጸው፣ ሌሎች ሦስት ሰዎች ከባድ የአካል ጉዳት ደርሶባቸው በኩዩ ሆስፒታል ሕክምና እየተደረገላቸው መሆኑን ጨምረው ተናግረዋል።

አደጋው የደረሰባቸው ሰዎች ሲጓዙበት የነበረው ሚኒባስ ሙሉ በሙሉ መውደሙን እና ሌሎች ሦስት ተሸከርካሪዎች ላይም ከባድ ጉዳት ማጋጠሙን ኢስፔክተር ሽመልስ ተናግረዋል።

“20 ዓመት ፖሊስ ሆኜ ሰርቻለሁ። እስካሁን በሕይወቴ እንዲህ አይነት አሰቃቂ አደጋ አይቼ አላውቅም። የሰዎችን አስክሬን ማውጣት በራሱ እጅግ ሰቅጣጭ ነበር” ብለዋል ኢንስፔክተር ሽመልስ።

በዚህም ምክንያት በሕዝብ ማመላለሻ ሚኒባሱ ውስጥ ከነበሩት መካከል በሕይወት የወጡት ሁለት ብቻ መሆናቸውን ተናግረው እነርሱም ከባድ የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል ብለዋል።

ኢንስፔክተሩ የአካባቢው መንገድ ጠመዝማዛማ እና ቁልቁለታማ ከመሆኑም በላይ ወቅቱ የዝናብ በመሆኑ አሸከርካሪዎች በከፍተኛ ጥንቃቄ ማሽከርከር እንዳለባቸው መክረዋል።

በኢትዮጵያ የተሸከርካሪዎች ቁጥር ከሌሎች አገራት ጋር ሲነጻጸር አነስተኛ ቢሆንም በአገሪቱ በሚደርሱ የትራፊክ አደጋ ሕይወታቸውን የሚያጡ ሰዎች ቁጥር ግን እጅግ ከፍተኛ ነው።
via~getu

 #ዜናሹመት»»»»»»»»»»»»»»»»»»»»ኮማንደር ልንገረው በዛ የደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር የሠላም እና ጸጥታ መምሪያ ምክትል ሀላፊ ሆነው ተሾሙ ፡፡በደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር ...
17/07/2023

#ዜናሹመት
»»»»»»»»»»»»»»»»»»»»
ኮማንደር ልንገረው በዛ የደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር የሠላም እና ጸጥታ መምሪያ ምክትል ሀላፊ ሆነው ተሾሙ ፡፡

በደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ በሰው ሀይል ልማት አስተዳደር በዋና ክፍል ሀላፊነት ሲያገለግሉ የነበሩ እና ከዚህ በፊትም በምስራቅ ጎጃም ዞን ፖሊስ መምሪያ በዋና ክፍል እና በተለያዩ የሀላፊነት ቦታዎች ለበርካታ አመታት መንግስት እና ህዝብ የጣለባቸውን ሀላፊነት በቅንነት እና በታማኝነት ሲያገለግሉ የቆዩት ፣ እጅግ ትሁት በሆነ ስነ ምግባራቸውና በቅን አገልጋይነታቸው እንዲሁም በስራ ወዳድነታቸው የሚታወቁት ኮማንደር ልንገረው በዛ ፣
ከሃምሌ 7 ቀን 2015 ዓ/ም ጀምሮ የደብረ ማርቆስ ከተማ አስዳደር ሰላምና ፀጥታ መምሪያ ምክትል ሀላፊ ሆነው ተሹመዋል ።
»»»»»»»»»»»»»»»»»»»»»»
መልካም የስራ ጊዜ እንዲሆንላቸው እንመኛለን !!
------------------------------------
መረጃው የደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ ነው !!

"የመሪነት ሚናችን ከፍታ ላይ እንዲገኝ ከተፈለገ ከሠላም ወዳዱና ከልማት አርበኛው ህዝባችን ጋር በጋራ ሆነን ሁሉን አቀፍ ተግባር ልንሰራ ይገባል" !  የምስራቅ ጎጃም ዞን ዋና አስተዳዳሪና ...
12/07/2023

"የመሪነት ሚናችን ከፍታ ላይ እንዲገኝ ከተፈለገ ከሠላም ወዳዱና ከልማት አርበኛው ህዝባችን ጋር በጋራ ሆነን ሁሉን አቀፍ ተግባር ልንሰራ ይገባል" !

የምስራቅ ጎጃም ዞን ዋና አስተዳዳሪና የብልፅግና ፓርቲ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል

የምስራቅ ጎጃም ዞን አስተዳድር የፀጥታ ምክር ቤት የ2015 ዓ.ም የተግባራት አፈፃፅም ግምገማና ወቅታዊ የፀጥታ ስራዎች ውይይት እንዲሁም የቀጣይ ተልዕኮዎችን አፈፃጻም አቅጣጫ ለማስቀመጥ የሚመክር መድረክ በደ/ማርቆስ ከተማ አካሄደ።

በግምገማዉና የምክክር መድረኩ ላይ የምስራቅ ጎጃም ዞን ዋና አስተዳዳሪና የብልፅግና ፓርቲ የማዕከላዊ ኮሚቴ አባል ክቡር አቶ አብርሃም አያሌው፣ የምስ/ጎጃም ዞን የብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ዋለ አባተ፣ የዞን ጠቅላላ አመራር፣ የወረዳና ከተማ አስተባባሪ አመራሮች እንዲሁም የፀጥታ ሚኒ ካቢኔ አባላትና የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላትም በመድረኩ ውይይት ተሳትፈውበታል።

በአፈፃጸም ግምገማ መድረኩ ላይ የተገኙት የምስራቅ ጎጃም ዞን ፖሊስ መምሪያ ኃላፊ ኮማንደር አያልነህ ተስፋዬ እደገለጹት ሠላም የጋራ የመሻትና የመስራት ውጤት እንጅ የነጠላ ግለሰብ ወይም ተቋም ብቻ ተግባር ስላልሆነ ሁሉም የድርሻውን ሰለሠላም መስፈን ሊተባበር ይገባል ብለዋል።

በዞናችን ያለውን አንፃራዊ ሠላም ወደ ሙሉ ሠላም ለማስገባት የፀጥታ አካላት፣ የሃይማኖት ተቋማትና መላው ህዝባችን የበኩሉን አስተዋፆኦ ሊያበርክት ይገባል ሲሉ ኮማንደር አያልነህ አሳስበዋል።

በግምገማና በውይይት መድረኩ ላይ የተገኙት የምስ/ጎጃም ዞን ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ዋለ አባተ የልማትም ይሁን የመልካም አስተዳድር ጥያቄዎቻችንን በአግባቡ ተደማምጠን ለመፍታት ሠላም የመጀመሪያው አስፈላጊ እሴታችን ስለሆነ የቅድሚያ ቅድሚያ ሠጠን ስለሠላም ልንሰራ ይገባል በማለት በመልዕክታቸው ገልፀዋል።

አቶ ዋለ አያይዘዉም ህብረተሰባችን የዕለት ከዕለት ተግባሩን ተረጋግቶ በየአካባቢው እንዲያከናውን የፀጥታ አመራሩ ከተከበረው ህዝባችን ጋር ሆኖ የህግ የበላይነትን በውል ሊያረጋግጥለት እንደሚገባ በውይይት ማጠቃለያው ላይ አሳስበዋል።

በውይይቱና በግምገማ መድረኩ የመሩትና የማጠቃለያ መልዕክት ያስተላለፉት የምስራቅ ጎጃም ዞን ዋና አስተዳዳሪ ክቡር አቶ አብርሃም አያሌው እንደገለፁት የመሪነት ሚናችን ከፍታ ላይ እንዲገኝ ከተፈለገ ከሠላም ወዳዱና ከልማት አርበኛው ህዝባችን ጋር በጋራ ሆነን ሁሉን አቀፍ ተግባር ለህዝባችን ልንሰራ ይገባል በማለት ገልፀዋል ።

ዋና አስተዳዳሪው አያይዘዉም ዛሬ ላይ የዞናችን ህዝብ በአፅንኦት የቅድሚያ ቅድሚያ የሚፈልገው ዘላቂነት ያለው ሠላም፣ የተረጋጋ የገበያ ስርዓትና የተረጋጋ የፖለቲካ አካባቢ በመሆኑ አመራሩ በህዝብ የተጣለበትን ኃላፊነት በሀቅና በእውነት ላይ ቆሞ ሊታገልና ሊያታግል ይገባል ሲሉ አሳስበዋል ።

በመጨረሻም ክቡር አቶ አብርሃም አመራራችን ፍጥነትንና ፈጠራን በማዋሃድ የመንግሰትን ፖለቲካዊ አቅጣጫዎች በመረዳትና በመተግበር የህብረተሰባችንን ሁለንተናዊ የሠላም ፣የልማትና የመልካም አስተዳድር ፍላጎቱን እንዲያከናውን በሙሉ አቅሙ ሊያገልግል ይገባል ብለዋል።

መረጃዉ የምስራቅ ጎጃም የመንግስት ኮሙኒኬሽን ነዉ

የጊዜ ጉዳይ ካልሆነ በስተቀር ወንጀል ፈፅሞ ማምለጥ አይቻልም !!"""""""""""""""""""""""""""""""ሹፌርና እረዳቱን በመግደል 100 ኩንታል ሰሊጥ የጫነን FSR መኪና ይዘው የ...
06/07/2023

የጊዜ ጉዳይ ካልሆነ በስተቀር ወንጀል ፈፅሞ ማምለጥ አይቻልም !!
"""""""""""""""""""""""""""""""
ሹፌርና እረዳቱን በመግደል 100 ኩንታል ሰሊጥ የጫነን FSR መኪና ይዘው የተሰወሩ ወንጀለኞችን 48 ሰዓት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ በቁጥጥር ስር ማዋሉን የደብረወርቅ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ አስታወቀ፡፡
""""""""""""""""""""""""""""
በምስራቅ ጎጃም ዞን ደብረወርቅ ከተማ አስተዳደር አባጀምበር ቀበሌ የጨረቃን ጎጥ ከተባለው ቦታ ፣ ሰኔ 28 ቀን 2015 ዓ/ም ፣ ከምዕራብ ጎንደር ዞን ገንዳ ውሃ ከተማ መቶ ኩንታል ሰሊጥ ጭኖ ወደ አዲስ አበባ በመጓዝ ላይ የነበረን FSR መኪና ፣ ሌሊት ባልታወቀ ሰዓት ማንነታቸው ያልታወቁ ሰወች መኪናውን አስቁመው ሾፌርና እረዳቱን በመግደል መኪናውን ይዘው ይሰወራሉ ፣

የደብረወርቅ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ከአካባቢው ነዋሪዎች የደረሰውን መረጃ መሰረት በማድረግ በሰራው እጅግ ፈጣንና ጥብቅ የሆነ ክትትል ፣ ወንጀለኞቹ መኪናውን ወደኋላ በመመለስ በእነብሴ ሳር ምድር ወረዳ ዲቦ ከተማ ወስደው ማሳደራቸውን መረጃ ይደርሰዋል፡፡

ፖሊስ የወንጀለኞችን ዱካ ይዞ ጠንካራ ክትትል በማድረግና እግር በእግር በመከታተል ላይ እያለ ፣ ወንጀለኞቹ ሰኔ 29/2015 ዓም መኪናውን ይዘው ወደ ግንደወይን ከተማ በመመለስ ላይ ሳሉ ፣ ግንደወይን ከተማ አካባቢ ሲደርሱ በጎንቻ ሲሶ እነሴና በግንደወይን ከተማ ህዝብና የጸጥታ አካላት ብርቱ ጥረት አንዱ ወንጀለኛ ከመኪናው ጋር በቁጥጥር ስር ሲውል ፣ ሌሎች ወንጀለኞችን ለመያዝ ርብርብ እየተደረገ መሆኑን የደብረወርቅ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ አስታወቋል፡፡

ወንጀለኛን የተጸየፈ ማህበረሰብ ባለበት ወንጀለኞች ወንጀል ፈጽመው እንደማይሰወሩ የጎንቻ ሲሶ እነሴና ግንደወይን ከተማ ነዋሪዎች፣ የጸጥታ አካላት ርብርብ ጥሩ ማሳያ ነው፡፡

ወንጀለኞችን ለመያዝ በተደረገው ጥረትም የጎንቻ ሲሶ እነሴና ።፣ የግንዶይን ከተማ አስተዳደር ህዝብና የፀጥታ አካላትን ፣ እንዲሁም መረጃ በመስጠት ለተባበሩት ሁሉ የደብረወርቅ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ጽ/ቤት ከፍተኛ ምስጋና አቅርቧል ።

ሞት የማይቀር የተፈጥሮ ህግ ነዉ፣ ለእዉነት እና ለህዝብ ፣ ለሙያ ግዴታ መሞት ደግሞ ክብር ነዉ።"""""""""""""""""""""""""""""""እነዚህ ጀግና የፖሊስ መኮንኖች  የሰማዩ ጌታ...
05/07/2023

ሞት የማይቀር የተፈጥሮ ህግ ነዉ፣ ለእዉነት እና ለህዝብ ፣ ለሙያ ግዴታ መሞት ደግሞ ክብር ነዉ።
"""""""""""""""""""""""""""""""
እነዚህ ጀግና የፖሊስ መኮንኖች የሰማዩ ጌታም በፈሪሃ እግዚአብሔር ጥላ ስር የወደቀ እዉነተኛ ህዝብም ስራቸዉን ያቁታል ።
ወረዳው ጠላት በአይነቁራኛ የሚከታተለዉ ወረዳ በመሆኑ ከጦርነት ጊዜ ጀምሮ እስካሁን እስከ ህልፈታቸው ድረስ ከዓባይ በርሃ እግራቸውንና ዓይናቸውን ሳይነቅሉ ሰርተዋል ።
ህዝብንና የፀጥታ መዋቅራቸውን ከሌሎች አካባቢ የሚጨመረዉንም አስተባብረው ሌትና ቀን ተብከንክነዉ ሰርተዉ አልፈዋል ዉለታቸዉ ብዙ ነዉ።
በተለይ ኢንስፔክተር ወርቁ ሽመልስ ለበርካታ ዓመታት የደጀንን ህዝብና መንግስትን ያየዉን ስህተት ሳይሰስት ትንሽና ትልቅ ሳይል በመታገል በቀተቆርቋሪነት አገልግሏል።
ዛሬ በተለያየ መልክ ስራቸዉ ባይጎላ እርግጠኛ ነኝ አይደለም እዉነተኛዉ ህዝብ የዓባይ ጅረት ሞገዶች ስለ ጓዶቻቸው ድምፅ አዉጥተዉ ይናገራሉ ።
"""""""""""""""""""""""""""""""
ነብሳችሁ በሰላም ትረፍ !!
-----------------------------
ኮማንደር አያልነህ ተስፋየ የምስራቅ ጎጃም ዞን ፖሊስ መምሪያ ሀላፊ ።

🍂🔥🍂  #ነፍሳቸውን  #ይማር🍂🔥🍂             =============የደጀን ወረዳ ፖሊስ ጽ/ቤት ሀላፊ እና የማህበረሰብ አቀፍ ፖሊስ አገልግሎት ክፍል ሀላፊ በስራ ላይ እያሉ በደረሰባቸ...
04/07/2023

🍂🔥🍂 #ነፍሳቸውን #ይማር🍂🔥🍂
=============
የደጀን ወረዳ ፖሊስ ጽ/ቤት ሀላፊ እና የማህበረሰብ አቀፍ ፖሊስ አገልግሎት ክፍል ሀላፊ በስራ ላይ እያሉ በደረሰባቸው ድንገተኛ ጥቃት ሂወታቸው አልፏል ።
~~~~~~~~~~~~~~
ሰኔ 27 ቀን 2015 ዓ/ም
በምስራቅ ጎጃም ዞን የደጀን ወረዳ ፖሊስ ጽ/ቤት ሀላፊ የነበሩት ዋ/ኢ ዘውዱ ታደለ እና የወረዳው ፖሊስ የማህበረሰብ አቀፍ ፖሊስ አገልግሎት ክፍል ሀላፊ የነበሩት ም/ኢ ወርቁ ሽመልስ ፣ ሰኔ 26 ቀን 2015 ዓ/ም ለስራ በመንቀሳቀስ ላይ እያሉ ፣ ለጊዜው ማንነቱ ባልታወቀ ግለሰብ በደረሰባቸው ድንገተኛ ጥቃት ሂወታቸው ያለፈ ሲሆን ፣ ሾፌራቸው ቆስሎ በደጀን የመጀመሪያ ደረጃ በሆስፒታል የህክምና እርዳታ እየተደረገለት ይገኛል ፣ የሟቾች የቀብር ስነስርዓት ሰኔ 27ቀን 2015ዓ/ም በትውልድ ቀያቸው ተፈጽሟል ።

ሟች የፖሊስ መኮንኖች በአባይ ማዶ ከመሸገው ኦነግ ሸኔ ጋር 24 ሰዓት ተፋጠው አካባቢያቸውን ላለማስደፈር ፣ ካለምንም እረፍት በአባይ ጎርጅ በርሀ ውሎ አዳራቸውን አድርገው ሌት ከቀን በመስራት ላይ የነበሩ የህዝብ ልጆች ነበሩ ።

የምስራቅ ጎጃም ዞን ፖሊስ መምሪያ የአካባቢያቸውን ሰላም ለማስከበር ሌት ከቀን ሲደክሙ ፣ ገና በለጋ እድሜአቸው ክቡር መስዋትነት በከፈሉ ጀግኖች ድንገተኛ ህልፈተ ሂወት የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን እየገለፀ ፣

የፖሊስ መኮንኖች የህዝባቸውን ሰላምና ደህንነት ለማረጋገጥ ደፋ ቀና ሲሉ የተሰውለትን አላማ ከግቡ ለማድረስ በቁርጠኝነት የሚሰራ መሆኑን በማረጋገጥ ።
ለሟች ቤተሰቦች ፣ ለወዳጅ ዘመዶቻቸውና ፣ ለመላው የዞናችን ፖሊስ አባላት መጽናናትን ይመኛል ።
~~~~~~~~~~~~~~
ነፍሳቸውን በአፀደ ገነት ያሳርፍልን !!
የምስራቅ ጎጃም ዞን ፖሊስ መምሪያ ።

የስምንተኛ ክፍል ፈተና በሁሉም የፈተና ጣቢያወች ላይ በሰላም ተጀምሯል ።»»»»»»»»»»»»»»»»በምስራቅ ጎጃም ዞን ትምህርት መምሪያ ስር በሚገኙ 584 የ8ኛ ክፍል አስፈታኝ ት/ቤቶች የጧ...
03/07/2023

የስምንተኛ ክፍል ፈተና በሁሉም የፈተና ጣቢያወች ላይ በሰላም ተጀምሯል ።
»»»»»»»»»»»»»»»»
በምስራቅ ጎጃም ዞን ትምህርት መምሪያ ስር በሚገኙ 584 የ8ኛ ክፍል አስፈታኝ ት/ቤቶች የጧቱ ፈተና በሰላም መጀመሩን የምስራቅ ጎጃም ዞን ትምህርት መምሪያ ሀላፊ አቶ ጌታሁን ፈንቴ ገልፀዋል።

መምሪያ ሀላፊው ለተፈታኝ ተማሪዎችም መልካም ፈተና እንዲሆንላቸው ተመኝተዋል !!

በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው ከደብረማርቆስ_ረቡዕገበያ ድጎጺዮን_ሞጣ የሚሰራዉ አስፋልት መንገድ አሸናፊዉ ተለይቶ እነሆ ሎት አንድ የካምፕ ርክክብ በዛሬዉ እለት ተደረጓል።  -------------...
30/06/2023

በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው ከደብረማርቆስ_ረቡዕገበያ ድጎጺዮን_ሞጣ የሚሰራዉ አስፋልት መንገድ አሸናፊዉ ተለይቶ እነሆ ሎት አንድ የካምፕ ርክክብ በዛሬዉ እለት ተደረጓል።
-----------------------------------
እንኳን ደስ አለን እንኳን ደስ አላችሁ!
-----------------------------------

የምስራቅ ጎጃም ዞን ዋና አስተዳዳሪ
----------------------------------
የምስራቅ ጎጃም የቱሪዝም ማእከል የምስራቅ አፍሪካ የዉሃ ማማ የሆነዉንና የዞናችንን ዋና ከተማ የሆነችዉን ደብረማርቆስ ከክልላችን ዋና ከተማና ከዞናችን ሁለተኛዋ ዉብ ከተማ ሞጣ ጋር በማገናኘት ከዞናችን አልፎ የክልሉን ገቢ በማሳደግ የማይተካ ሚና የሚኖረው አስፋልት መንገድ ግንባታ የካምፕ ርክክብ በዛሬዉ እለት በስናን ወረዳ ተካሂዷል።

ይህ ስራ የመንግስት ጅምር ስራ ቢመስልም የብዙ ጥረት ዉጤቱ ላይጨርስ ቃል እንደማይገባ ማሳያ ነዉ።

በድጋሜ የምስራቅ ጎጃም ህዝብ እንኳን ደስ አላችሁ እንኳን ደስ አለን!

በምስራቅ ጎጃም ዞን ሰናን አስተዳዳሪ አቶ ስሜነህ አዝመራዉ ከደብረማርቆስ ከተማ የምስራቅ አፍሪካ የዉሃ ማማ በሆነችዉ ስናን_ ዲጎ ፂዎን የአስፓልት መንገድ ሎት አንድ ፕሮጀክት የካፕ የቦታ ልየታ በመደረጉ እንኳን ደስያላችሁ መልእክት አስተላልፈዋል።

በቦታ ልየታው ላይ የፕሮጀክቱ ምክትል ዳይሬክተር ሚስተር ሪኪ እና የሰው ሀይል አስተዳደር ወ/ሪት ሀና ክፍሌ እንዲሁም የስናን ወረዳ ኮር አመራሮች በተገኙበት የቦታ ልዬታ እርክክብ እንደተደረገም አቶ ስሜነህ ተናግረዋል ሲል East Gojjam Communication ዘግቧል ።

በድንገተኛ የትራፊክ አደጋ  #የ7  #ሰወች  ሂወት አለፈ ።˝˝˝˝˝˝˝˝˝˝˝˝˝˝˝˝˝˝˝˝˝˝˝ሰኔ ቀን10 2015ዓ /ም ፤በደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር አብማ ክፍለ ከተማ ቀበሌ 20  ...
17/06/2023

በድንገተኛ የትራፊክ አደጋ #የ7 #ሰወች ሂወት አለፈ ።
˝˝˝˝˝˝˝˝˝˝˝˝˝˝˝˝˝˝˝˝˝˝˝
ሰኔ ቀን10 2015ዓ /ም ፤
በደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር አብማ ክፍለ ከተማ ቀበሌ 20 ወይም እነራታ ልዩ ቦታው መሊት ተብሎ ከሚጠራው ስፍራ ፣ ሰኔ 10 ቀን 2015 ዓ/ም ከቀኑ 5 ሰዓት በሚሆንበት ጊዜ ፣
ከረቡዕ ገበያ ወደ ደብረ ማርቆስ በመጓዝ ላይ የነበረ ፣የሰሌዳ ቁጥሩ ኮድ3 /25769 አማ የሆነ የህዝብ ማመላለሻ ኤፍ ኤስ አር መኪና ፤ ህዝብ ጭኖ ቁልቁለት በመውረድ ላይ እንዳለ በአጋጠመው አደጋ መንገድ ስቶ በመውጣቱ እና በመገልበጡ በደረሰው አደጋ ፤ ለጊዜው ሹፌሩን ጨምሮ የ7 ሰው ህይወት ማለፉን እና በ22 ሰው ላይ ከባድ እና ቀላል አደጋ ደርሶባቸው በደብረ ማርቆስ ሪፈራል ሆስፒታል ህክምና እየተደረገላቸው መሆኑን የ1ኛ ፖሊስ ጣቢያ የታክቲክ ወንጀል ምርመራ ንዑስ ክፍል ሀላፊ ዋና ሳጅን ግዜአለው ምንዋግ ገልጸዋል፡፡

ዋናሳጅን ግዜአለው እንደገለጹት የአደጋው መንስኤ እየተጣራ መሆኑን ጠቅሰው ፣ አሽከርካሪዎች የክረምት ወቅቱን መሠረት አድርገው እና የመንገዱን አስቸጋሪነት ተረድተው ተገቢውን ጥንቃቄ በማድረግ እንዲያሽከረክሩ አሳስበዋል ፣ ሲል የዘገበው የደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ ህዝብ ግንኙነት ነው፡፡
˝˝˝˝˝˝˝˝˝˝˝˝˝˝˝˝˝˝˝˝˝˝˝˝˝˝˝
የሟቾችን ነፍስ ይማር ፤
ለቤተሰቦቻቸው ፅናቱን ይስጥልን።
˝˝˝˝˝˝˝˝˝˝˝˝˝˝˝˝˝˝˝˝˝˝˝˝˝˝˝“

ሞዴል ፈተና !!======================= በምስራቅ ጎጃም ዞን ትምህርት መምሪያ የ8ኛ ክፍል  ዞናዊ ሞዴል ፈተና በ584 ት/ቤቶች እየተሰጠ ይገኛል። በዞኑ  ከ35,000 በላይ የ...
15/06/2023

ሞዴል ፈተና !!
=======================
በምስራቅ ጎጃም ዞን ትምህርት መምሪያ የ8ኛ ክፍል ዞናዊ ሞዴል ፈተና በ584 ት/ቤቶች እየተሰጠ ይገኛል።
በዞኑ ከ35,000 በላይ የሚሆኑ የ8ኛ ክፍል ተማሪዎች እንደሚወስዱ ይጠበቃል ።
መልካም ፈተና !!
አቶ ጌታሁን ፈንቴ የምስራቅ ጎጃም ዞን ትምህርት መምሪያ ሀላፊ።

በምስራቅ ጎጃም ዞን ከ35 ሽህ በላይ ተማሪዎች የ8ኛ ክፍልና ከ24ሽ 500 የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ክልል አቀፍ ና ሃገር አቀፍ ፈተና እንደሚወስዱ መምሪያዉ አስታወቀ።መምሪያዉ የ2015 የትም...
14/06/2023

በምስራቅ ጎጃም ዞን ከ35 ሽህ በላይ ተማሪዎች የ8ኛ ክፍልና ከ24ሽ 500 የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ክልል አቀፍ ና ሃገር አቀፍ ፈተና እንደሚወስዱ መምሪያዉ አስታወቀ።

መምሪያዉ የ2015 የትምህርት ዘመን 8ኛ ክፍልና የ12ኛ ክፍል ክልልና ሃገር አቀፍ ፈተና የቅድመ ዝግጅትና በቀጣይ ስራዎች ዙሪያ የሚመክር የውይይት መድረክ እያካሄደ ነው።

መድረኩ "ለሀገር ግንባታና ሁለንተናዊ እድገት መሰረት የሆነውን የትምህርት ዘርፍ ማነቆ በመፍታት ጠንካራ፣ በቁ፣ ተወዳዳሪና ምክንያታዊ ዜጋ የማፍራት ሁነኛ ተልዕኳችንን ከዳር ለማድረስ የዘርፉ ባለቤቶች ጠንክረን በመስራት ሙያዊና የዜግነት ድርሻችንን በአግባቡ ልንወጣ ይገባል!" በሚል መሪ ሀሳብ እየተካሄደ ሲሆን በመድረኩ የዞን፣ የወረዳና የከተማ አስተዳደር የስራ ኃላፊዎች፣ የዘርፉ ባለሙያዎች፣ አጋርና ባለድርሻ አካላት ተሳትፈውበታል።

የምስራቅ ጎጃም ዞን ትምህርት መምሪያ ኀላፊ አቶ ጌታሁን ፈንቴ እንደገለፁት በተያዘው 2015 የትምህርት ዘመን በዞኑ በግልና በመንግስት ትምህርት ቤት ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የቆዩ የ8ኛ ክፍል ወንድ 16960 ሴት 18597 በድምሩ 35557 በ584 ትምህርት ቤቶች ክልል አቀፍ እንዲሁም በ60 ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች በማህበራዊና ተፈጥሮ ሳይንስ የትምህርት ዘርፍ የ12ኛ ክፍል ወንድ 12007 ሴት 12511 በድምረ 24518 ተማሪዎች ሀገር ዓቀፍ ፈተና ይወስዳሉ ብለዋል ።

ሀገር በትውልድ ፤ትውልድ ደግሞ በትምህርት ይገነባል። ስለሆነም የሃገር ግንባታ መሰረቱ የሆነዉን የትምህርት ዘርፍ ለመቀየር መረባረብ የሁላችንም ሀላፊነት ሊሆን ይገባል ያሉት መምሪያ ኀላፊው በ2015 ዓ.ም የሚሰጠውን ክልልና ሃገር አቀፍ ፈተና ያለምንም የጸጥታና የስነ-ምግባር ችግር ለማሳካት ዓላማ ያደረገ መሆኑን አስረድተው በመድረኩ የፈተና ቅድመ-ዝግጅት ስራዎችን መገምገም፣ የቀሩ ተግባራትን ቆጥሮ መለየትና በአጭር ጊዜ ማጠናቀቅ የሚያስችል ስምሪት ይሰጣል ብለዋል።

የሚሰጠዉ የ8ኛ እና 12ኛ ክፍል ክልልና ሀገር-ዓቀፍ ፈተና በውጤታማነት መፈፀም የዞኑን ህዝብ ከፍታ የማረጋገጥ ጉዳይ በመሆኑ ለስኬታማነቱ ሁሉም በቅንጅት፣ በፍጹም የስራ ትጋትና የሀላፊነት ስሜት ሊረባረብ እንደሚገባ አሳስበዋል።

የደብረ ማርቆስ ዩንቨርስቲ የአካዳሚክ ዘርፍ ምክትል ፕሬዘዳንት ይኸይስ ሀረጉ(ዶ/ር) ብቁ ተወዳዳሪና የነገ አገር ተረካቢ ትውልድ ለማፍራት የሁሉንም ርብርብና ተሳትፎ ይጠይቃል ብለዋል።

በራሱ የሚተማመንና የሚሰጠውን ፈተና በራሱ አቅም የሚወጣ ተማሪ ለመፍጠር ከወዲሁ በትኩረት መስራት እንደሚገባ ያሳሰቡት ይኸይስ ሀረጉ (ዶ/ር) ተማሪዎች ከወዲሁ ለፈተና እራሳቸውን በተገቢው መንገድ እንዲያዘጋጁ አሳስበዋል።
via~gashaye getahun

ስልጠና ላይ ለሚገኙ የቀድሞ ልዩ ሀይል አባላት 13 የእርድ ሰንጋወች ድጋፍ ተደረገላቸው ።“““““““““““““““““““““““በደብረ ማርቆስ ከተማ አማራ ፖሊስ ኮሌጅ በአድማ ብተና ፖሊስነት...
29/05/2023

ስልጠና ላይ ለሚገኙ የቀድሞ ልዩ ሀይል አባላት 13 የእርድ ሰንጋወች ድጋፍ ተደረገላቸው ።
“““““““““““““““““““““““
በደብረ ማርቆስ ከተማ አማራ ፖሊስ ኮሌጅ በአድማ ብተና ፖሊስነት እየሰለጠኑ ለሚገኙ የቀድሞው የአማራ ልዩ ሃይል አባላት የደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር 13 የእርድ ሰንገዎችን ድጋፍ አደርጓል።

በድጋፍ በርክክብ ፕሮግራሙ ላይም የከተማ አስተዳደሩ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች፣የአማራ ፖሊስ ኮሌጅ የስራ ሃላፊዎች፣የንግዱ ማህበረሰብ ተወካዮች፣የሀገር ሽማግሌዎችና ሰልጣኞች ተገኝተዋል ሲል የዘገበው የደብረማርቆስ ከተማ አስተዳደር ኮሙኒኬሽን ነው።

Address


Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when East Gojjam Zone Police posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Videos

Shortcuts

  • Address
  • Alerts
  • Videos
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share