MaYzek MiHzek-EHIO

  • Home
  • MaYzek MiHzek-EHIO

MaYzek MiHzek-EHIO ይህ MaYzek MiHzek-EHIO (ምያዚከ ምህዚከ-ኢትዮ) ፔጅ ከተለያዩ ከመረጃ ምንጮች copy paste እያረረ ወደ እናነተ ያደርሳል። የዚህ ፔጅ አላማ ...

27/10/2019
ቅዱስ ሲኖዶሱ ከከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ጋር ውይይት አደረገ!የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ከከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ጋር ውይይት አደረገ። በ...
26/10/2019

ቅዱስ ሲኖዶሱ ከከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ጋር ውይይት አደረገ!

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ከከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ጋር ውይይት አደረገ። በውይይቱ ላይ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት፣ የኢፌዴሪ ም/ጠቅላይ ሚንስተር አቶ ደመቀ መኮንን፣ የመከላከያ ሚንስትር አቶ ለማ መገርሣ፣ የሰላም ሚኒስትር ወይዘሮ ሙፈሪያት ካሚል እና በፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን የወንጀል መከላከል ዘርፍ ሃላፊ ምክትል ኮሚሽነር ጀነራል መላኩ ፈንታ በተገኙበት በዝግ ተደርጓል። በውይይቱ በወቅታዊ የቤተ ክርስቲያኒቱ እና ሀገራዊ ጉዳዮች ምክክር መደረጉን ከኢትዮጵያ ኮርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን መገናኛ ብዙኃን አገልግሎት የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

copyPast {EBC}

26/10/2019

በሀገር አቀፍ የደም ልገሳ መርሃ ግብር በአንድ ጀምበር ከ11 ሺህ ዩኒት በላይ
ደም ተሰበሰበ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 15፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በሀገር አቀፍ ደረጃ በዛሬው
እለት በተካሄደው የደም ልገሳ መርሃ ግብር ዘመቻ በአንድ ጀምበር ከ11 ሺህ
ዩኒት በላይ ደም መሰብሰብ መቻሉ ተገለፀ።
“ህይወት ለህይወት ፥ ደም ለግሰን ሕይወት እናድን” በሚል መሪ በመላ ሃገሪቱ
የደም ልገሳ መርሃ ግብሩ በዛሬው እለት ተካሂዷል።
ይህ ዘገባ እሰከተጠናከረበት ድረስም በዛሬው እለት ብቻ 11 ሺህ 376 ዩኒት
ደም በሀገር አቀፍ የደም ልገሳ መርሀ ግብር ላይ መሰብሰቡን የጤና ሚኒስትሩ
ዶክተር አሚር አማን አስታውቀዋል።
በደም ልገሳ መርሀ ግብሩ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናትን ጨምሮ ታዋቂ
ሰዎች፣ የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች፣ ተማሪዎች፣ የመንግሥት ሠራተኞች፣
ነጋዴዎችና ሌሎች የህብረተሰብ ክፍሎች ተሳትፈዋል።
በብሔራዊ ደረጃ የተካሄደው የደም ልገሳ ቀን የደም ማስተላለፍ ህክምና
በኢትዮጵያ የተጀመረበትን 50ኛ ዓመት በማስመልከት የተዘጋጀ ነው።
በዛሬው እለት በሀገር አቀፍ ደረጃ በተካሄደው የደም ልገሳ ዘመቻው 10 ሺህ
ዩኒት ደም ለመሰብሰብ ታቅዶ የነበረ ሲሆንም፥ እስካሁን ባለው መረጃ ከእቅዱ
በላይ 11 ሺህ 376 ዩኒት ደም መሰብሰብ ተችሏል።
የጤና ሚኒስትሩ ዶክተር አሚር አማን፥ በሀገሪቱ በሙሉ በደም ባንክ
ቅርንጫፎች በመገኘትና በትዕግስት በመጠበቅ ደም ለለገሱ በጎ ፈቃደኞች፣
የብሄራዊ ደም ባንክ አመራሮችና ሰራተኞች ፣ በጎ ፈቃደኛ አስተባባሪዎች በሙሉ
በጤና ሚኒስቴር እና በራሳቸው ስም አምስግነዋል።
“ይህ ክቡር የሆነውን የሰው ልጅ ህይወት የሚያተርፍ በጎ ተግባር ነውና በእጅጉ
ልትኮሩ ይገባል” ሲሉም መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።
በሚቀጥለው አንድ ወር 300 ሺህ ቋሚ ደም ለጋሾች ለመመዝገብ የተያዘውን
እቅድ እቅድ ለማሳካት bloodbank.moh.gov.et ላይ በጎ ፍቃደኛ ደም
ለጋሾች እንዲመዘገቡም ጥሪ አቅርበዋል።

ምንጭ {FBC}

የሕግ የበላይነትን ለማረጋገጥና አጥፊዎች በሕግ ፊት ቀርበው ተገቢው ሁሉእንዲያገኙ ያለማወላወል እንሠራለን:- ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ****************ጠቅላይ ሚንስትር ዶ...
26/10/2019

የሕግ የበላይነትን ለማረጋገጥና አጥፊዎች በሕግ ፊት ቀርበው ተገቢው ሁሉ
እንዲያገኙ ያለማወላወል እንሠራለን:- ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ
****************
ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳይ ላይ የሰጡት
ሙሉ መግለጫ
የተከበራችሁ የሀገሬ ሕዝቦች!
ሰሞኑን በተከሠተው እጅግ አሳዛኝ ግጭት በዜጎቻችንና በንብረታቸው ላይ
በደረሰው ሁሉ ማዘኔን አስቀድሜ ለመግለጥ እወዳለሁ፡፡
ያጋጠመን ፈተና ኢትዮጵያውያን ካልተባበርንና አንድ ሆነን ካልቆምን መንገዳችን
ምን ያህል አስቸጋሪና አስፈሪ ሊሆን እንደሚችል ማሳያ ነው፡፡ ችግሩ የብሔርና
የሃይማኖት መልክ እንዲኖረው ለማድረግ ተሞክሯል፡፡ በዚህም የተነሣ
ወገኖቻችን በአሰቃቂ ሁኔታ መሥዋዕት ሆነዋል፡፡
የጸሎት ቤቶች ተቃጥለዋል፡፡ የንግድ ድርጅቶችና የመኖሪያ ቤቶች ወድመዋል፡፡
የተፈናቀሉ ወገኖች በተለያዩ ቦታዎች ተጠልለዋል፡፡ መተላለፊያ ያጡ ዜጎችም
በየከተሞቹ ከርመዋል፡፡ እንኳንስ ለማየት ለመስማት የሚዘገንን እኩይ ተግባር
በወገናችን ላይ ተፈጽሟል፡፡
በልብ ሰባሪው ክሥተት ብናዝንም ኢትዮጵያውያን ዛሬም ታላቅ ሕዝቦች፣
አስተዋዮችና አመዛዛኞች መሆናቸውንም አይተናል፡፡ ቤተ ክርስቲያን
እንዳይቃጠል የሚከላከሉ ሙስሊሞች፣ መስጊድ እንዳይቃጠል ዘብ የሚቆሙ
ክርስቲያኖች አሉን፡፡ ከእነርሱ ብሔር ውጭ ለሆነው ወገናቸው ሲሉ
መሥዋዕትነት የከፈሉ ኢትዮጵያውያን አሉን፡፡ ሰላምና ደኅንነትን ለማውረድ ሌት
ተቀን የሚደክሙ ሽማግሌዎች አሉን፡፡ ቤት ንብረታቸውን ላጡ መጠለያ የሚሆኑ፣
መንገድ ለተዘጋባቸው ማደሪያ የሚያዘጋጁ ብዙ ወገኖች አሉን፡፡ የፈተናው ዓላማ
ተስፋ እንድንቆርጥና መንገዳችንን እንድንቀይር መሆኑን ተረድተው፣ ዛሬ በሆነው
ነገር ሳይደናገጡ፣ ነገን አሻግረው የሚመለከቱ ዜጎች አሉን፡፡ ለሕግና ለኅሊና
የሚቆሙ የመከላከያና የፖሊስ አባላት አሉን፡፡
ይህ ሁሉ ለምን እንደመጣብን እናውቃለን፡፡ ከዚህ የበለጠ ፈተና ቢያጋጥመንም
እንኳን የጀመርነውን ጉዞ አናቋርጥም፡፡ አረሙን እየነቀልን፤ ስንዴውን
እየተከባከብን እንሄዳለን እንጂ ለአረሙ ስንል ስንዴውን አንተወውም፡፡
በመንገዳችን የሚያጋጥመንን ዕንቅፋት እያነሣን መንገዳችንን እንቀጥላለን እንጂ
ወደ ቀኝም ወደ ግራም ወለም ዘለም አንልም፡፡ ፈታኞቻችን ያልተገነዘቡት ነገር
ቢኖር የተከፈለውን መሥዋዕትነት ሁሉ ከፍለን የኢትዮጵያና የሕዝቦቿን ብልጽግና
የምናረጋግጥ መሆናችንን ነው፡፡
የሕግ የበላይነትን ለማረጋገጥና አጥፊዎች በሕግ ፊት ቀርበው ተገቢው ሁሉ
እንዲያገኙ ያለማወላወል እንሠራለን፡፡ በተፈጠረው አሳዛኝ ክሥተት የተጎዱት
እንዲያገግሙ፤ ከቤት ንብረታቸው የተፈናቀሉት እንዲመለሱ፣ ንብረታቸው
የጠፋባቸው እንደገና እንዲቋቋሙ ከሕዝባችን ጋር ሆነን በጽናት እንሠራለን፡፡
ይህንን ለማሳካትም የሃይማኖት ተቋማት፣ የሲቪክ ማኅበራትና መላው ሕዝብ
ከጎናችን እንዲቆም ጥሪ እናደርጋለን፡፡
እርስ በርሳችን ከተከፋፈልንና ከተጋጨን አሸናፊዎቹ ሌሎች ናቸው፡፡ ማናችንም
አናሸንፍም፡፡ ጠላቶቻችን ምን እንድንሆን እንደሚፈልጉ በጥቂቱ አይተነዋል፡፡
ከዚህ የከፋ እንዳይገጥመን መንግሥትና ሕዝብ የሚጠበቅባቸውን ማድረግ
አለባቸው፡፡ መንግሥት ከመንግሥት የሚጠበቀውን ሁሉ ያደርጋል፡፡ ሕዝቡም
ባለመለያየት፣ ለአጥፊዎች አጀንዳ ባለመመቻቸት፣ አንዱ ለሌላው ጋሻና መከታ
በመሆን፤ ወንጀለኞችን አሳልፎ ለሕግ በመስጠት፣ የተጎዱ ወገኖቹን በመርዳት
ታላቅነቱን ሊያስመሰክር ይገባል፡፡
ኢትዮጵያ በልጆቿ ጥረት ታፍራ፣ ተከብራና በልጽጋ ለዘላለም ትኑር!
ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይባርክ!

ጥቅምት 15 ቀን 2012 ዓ.ም
ምንጭ{EBC}

Address


Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when MaYzek MiHzek-EHIO posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

  • Address
  • Alerts
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share