Alemu belayneh

  • Home
  • Alemu belayneh

Alemu belayneh Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Alemu belayneh, Digital creator, .

08/12/2022

በእዉነተኛ ታሪክ ላይ የተመሰረተ

" ኪ ያ ዬ "

ክፍል 3

በበዓል ሙዚቃዎች ድምቀት ሽብርቅ ብሎ በቀረበ የቡና አፈላል ስነስርአትና በእጣን ጢስ የታጀበ ግሩም ቁርሰ ነበር

" ቢኒያም ባልወልደዉም የልጄ ምትክ ልጄ ነዉ አንቺን የመሰለች ቆንጆ አማች ስላመጣልኝ ደስተኛ ነኝ " አሉና ኪያዬ ሰረቅ አድርገዉ ተመለከቷት በሀፍረት ማቀርቀሯን ካስተዋሉ በሗላ " ደሞ የምን መፍዘዝ ነዉ ልጅ በልጅነት ነዉ ቶሎ ተጋብታችሁ ዉለዱና እኔንም ወጣት አያት አድርጉኝ " ብለዉ ሀፍረቷን ወደ ሳቅ ለወጡት " ስማኝ ቢኒያም ፍቅር ትዕግስትን ይፈልጋል! በጥላቻ ዓመት የሚፈጀዉ በፍቅር በአንድ ቀን ይከናወናል ግን ትዕግስትን ይሻል ፍቅር ደግሞ ከመቀበል ይልቅ ወደ መስጠቱ ያመዝናልና

ለዚህች ቆንጆ ልጅ ፍቅር ለመስጠት እንዳትሰንፍ " ብለዉ መርቀዉ ሸኙን ኪያዬ ከታላቅ እህቷ ከትዕግስት ጋር ልታስተዋዉቀኝ ቀጠሮ ስለነበራት ልብሴን በፍጥነት ቀይሬ መኪናዉን አስነስቼ ወደ እህቷ ቤት አመራን

ትዕግስት የ 7 ወር ነፍሰጡር ስትሆን ባለቤቷ በስራ ምክንያት በሀገር ዉስጥ አይኖርም ጥሩ መስተንግዶ ተደረገልኝ " ወጣት ስለሆኑክ በግልፅ ንግግርና በንፁህ ፍቅር አምናለሁ እናትም አባትም ሆኜ ያሳደኳት እኔ ነኝ

የቤተሰብ አደራ አለብን አኛ ጋር ትደግ ብለዉ ከዘመዶቻችን ጋር እስከመጣላት ደርሼ ነበር ኪያዬ ብቸኛ የእናትና የአባት ዉርሴ ናትና አደራ " አለችኝ አደራዋን ተቀብዬ ለመሄድ ተነሳሁ ጨለምለም ብሎ ነበር ሔርሜላ እኔን እስከ በር ለመሸኘት ተከተለችኝ

የመስከረም የመጀመሪያዉ ምሽት እንደ ማለዳዉ ብሩህ ሳይሆን በተቃራኒዉ ያኮረፈና ደመናን ያዘለ ነበር ለ3 ቀን በስራ ጉዳይ ወደ ክፍለ ሀገረ ነገ ጠዋት ስለምሄድ ኪያዬ ክፍት ብሏት ነበር ወደ ደረቴ ጠጋ አድርጌ አቀፍኳት አቀረቀረች! ከአገጯ ቀና አድርጌ አይኖቿን ተመለከትኩ እንባ አቅረዋል " እራስህን ጠብቅ ሁሌም አፈቅርሃለሁ "

አለችኝ ከንፈሯን ስሜ ወደ መኪናዉ ገባዉ የ 3ቀን ናፍቆቴን ለመቻል እየታገልኩ መኪናዉን ወደ ፊት አንቀሳቀስኩ

የሁለት ቀናት የክፍለ ሀገር ስራዬን በጥሩ ሁኔታ አጠናቅቄ በሶስተኛዉ ቀን ጠዋት ላይ ኪያዬ ደወለች እንዴት አደርክ ? ድምጿ እንደ ሌላዉ ቀን በህይወት መኖርን የሚያስመኝ መሆኑ ቀርቶ በሀዘን የተዋጠ ነበር " እንዴት አደርሽ የእኔ ቆንጆ የተፈጠረ ነገር አለ ድምፅሽ ጥሩ አይደለም ? አልኳት " ወ/ሮ ሙሉ በጣም ታመዋል

እሳቸዉ ጋር ነኝ ዛሬ መድረስ አለመድረስህን ላረጋግጥ ብዬ ነዉ " አለችኝ በድንጋጤ ክዉ ብዬ ቀረሁ " ሄሎ የት ሄድክ ?" " አለሁ የእኔ ቆንጆ በጣም ታ.መ.ዋ.ል? ተንተባተብኩኝ! በሰላም የተሰናበትኳቸዉ ሰዉ በ 2ቀናት ዉስጥ ምን አገኛቸዉ ? ብዬ ክፉኛ ደነገጥኩ " ዛሬ ማታ 12:30 አከባቢ እደርሳለሁ ስልኩን ስጫቸዉና ላናግራቸዉ " አልኳት ማንንም ማናገር እንደማይፈልጉ ገልፃልኝ በቅጡ እንኳን ቻዎ ሳትለኝ ስልኩን ዘጋችዉ

ህመማቸዉ የከፋ ደረጃ ላይ ቢደርስ እንጂ ኪያዬ እንዲህ አይነቱን ከባድ ዜና ይቅርና ቀላል የሚባሉትን እንኳ ስራ ላይ ሆኜ እንዳይደነግጥ ብላ በማሰብ እንደማትነግረኝ አዉቃለሁ በቀጥታ አቶ እንዳለ ጋር ደወልኩና አስፈላጊዉን ስራ መጨረሴንና የደንበኞች ፊርማ ያረፈበት ሰነድም በእጄ እንደሚገኝና መነሳት ከነበረብኝ ሰዓት ቀደም ብዬ ወደ አዲስ አበባ ጉዞ እንደምጀምር የተፈጠረዉን ነገር ገልጬ አስረዳሗቸዉ አልተቃወሙኝም አመስግኜ ስልኩን ዘጋሁትና በቀጥታ ጉዞዬን ጀመርኩ..

ይቀጥላል follow.like.shere ማረጋቹህን አትርሱ

Address


Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Alemu belayneh posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

  • Address
  • Alerts
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share