ቆንጆ page

  • Home
  • ቆንጆ page

ቆንጆ page Love for once country is part of faith!!

✍️መከላከያ ሰራዊት በወሰደው እርምጃ አዳምሴ የተባለ የሸኔ የሻለቃ አመራር ተገደለ!የሃገር መካከያ ሰራዊት በአሸባሪው ሸኔ ላይ የሚወስደዉን እርምጃ አጠናክሮ የቀጠለ ሲሆን ሰሞኑን በተከታታይ...
29/12/2023

✍️መከላከያ ሰራዊት በወሰደው እርምጃ አዳምሴ የተባለ የሸኔ የሻለቃ አመራር ተገደለ!

የሃገር መካከያ ሰራዊት በአሸባሪው ሸኔ ላይ የሚወስደዉን እርምጃ አጠናክሮ የቀጠለ ሲሆን ሰሞኑን በተከታታይ በተደረገ ኦፕሬሽን ከፍተኛ ቡድኑ አመራሮችን ጨምሮ በርካታ የቡድኑ አባላት መደምሰሳቸው ታውቋል፡፡
በዚህም ሶንሳ ብርጌድ በሚል የሚንቀሳቀሰውን አደረጃጃት የሚመራው አዳምሴ የተባለ ታጣቂ ከመከላከያ ሰራዊቱ በተወሰደ እርምጃ የተገደለ ሲሆን ቡድኑ ሞቱን ይፋ ከማድረግ መቆጠቡን መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ ከዚህም ውጭ ካያ፣ ሽሩቤ፣ ቃንቃ እና ወረቅሳ በመባል የሚታወቁት የቡድኑ መሪዎች የመከላከያ ሰራዊቱን ክንድ መቋቋም አቅቷቸው ከሞት የተረፉትን ውስን ታጣቂዎች በመያዝ እግሬ አውጪኝ ብለው በመፈርጠጥ ላይ እንደሚገኙም ከስፍራው የተገኘ ታማኝ መረጃ አመላክቷል፡፡

✍️በምሬ የሚመራው ታጣቂ በኮሎኔል ፈንታሁን ሙሃቤ ላይ ግድያ ለመፈፀም እየተንቀሳቀሰ መሆኑ ታውቋል!በምሬ ወዳጆ እና በኮሎኔል ፈንታሁን ሙሃቤ መካከል የተፈጠረው አለመግባባት ከቁጥጥር ውጭ እ...
29/12/2023

✍️በምሬ የሚመራው ታጣቂ በኮሎኔል ፈንታሁን ሙሃቤ ላይ ግድያ ለመፈፀም እየተንቀሳቀሰ መሆኑ ታውቋል!

በምሬ ወዳጆ እና በኮሎኔል ፈንታሁን ሙሃቤ መካከል የተፈጠረው አለመግባባት ከቁጥጥር ውጭ እየሆነ የመጣ ሲሆን ሰሞኑንም በሰሜን እና ደቡብ ወሎ አከባቢ የሚንቀሳቀሰውን ታጣቂ ሃይል ወደ አንድ ለማምጣት በሚል በተደረገ ውይይት ሁለቱም እንደተለመደው በልዩነት መለያየታቸዉን የተገኙ ታማኝ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡

በዚህም ታጣቂውን ሃይል ቤተ-አማራ ፋኖ የወሎ ዕዝ በሚል ለማዋቀር በተደረገው ውይይት ዕዙን ኮሎኔል ፈንታሁን ሙሃቤ እንዲመራው የተወሰነ ሲሆን ምሬ ምክትሉ ሆኖ እንዲቀጥል ዉሳኔ ተላልፏል፡፡
ሆኖም ከሰሜን ወሎ አከባቢ የመጡ ታጣቂዎች ቤተ-አማራ ፋኖ የወሎ ዕዝ በሚል ስያሜ የተዋቀረውን ዕዝ እና የምሬን ምክትልነት ባለመቀበላቸው በሁለቱ የታጣቂ ሃይሉ መሪዎች መካከል የተፈጠረው አለመግባባት ተፋፍሞ እንዲቀጥል ምክንያት ሆኗል፡፡
በሰሜን ወሎ አከባቢ የሚንቀሳቀሱት እና በምሬ ወዳጆ የሚመሩት የታጣቂ ሃይል አባላት በኮሎኔል ፈንታሁን መሃቤ ላይ የሃይል እርምጃ ለመውሰድ ውስጥ ለውስጥ መንቀሳቀስ መጀመራቸዉ የታወቀ ሲሆን በዚህም የምሬ ሃይል ከሰሜን ወሎ ራያ ቆቦ ወደ ደቡብ ወሎ አምባሰል ጉዞ መጀመራቸውን ከታማኝ ምንጮች የተገኘ መረጃ አመላክቷል፡፡

በአምባሰል አከባቢ የሚንቀሳቀሰዉን ታጣቂ ሃይል የሚመራው እና የኮሎኔል ፈንታሁን ሙሃቤ ወዳጅ የሆነው ድርሳን ብርሃነ እኔ እያለው የምሬ ሃይል ወደ ደቡብ ወሎ ዘልቆ አይገባም በማለት ለኮሎኔል ፈንታውን እርግጠኛ ሆኖ እየተናገረ እንደሚገኝ በመረጃው ተጠቁሟል፡፡

የጃውሳው ስርዓተ-ቀብር እየተከናወነ ነው!✍️የህዝብን ሰላም እያወኩ ነጻ አውጪ ነኝ ማለት በራሱ ከህዝብ ልብ ያወጣል፡፡የጃውሳው ስብስብ ከመከላከያ ሰራዊት የሚሰነዘርበትን ጥቃት መቋቋም ተስኖ...
29/12/2023

የጃውሳው ስርዓተ-ቀብር እየተከናወነ ነው!

✍️የህዝብን ሰላም እያወኩ ነጻ አውጪ ነኝ ማለት በራሱ ከህዝብ ልብ ያወጣል፡፡

የጃውሳው ስብስብ ከመከላከያ ሰራዊት የሚሰነዘርበትን ጥቃት መቋቋም ተስኖት ጣር ላይ ሲሆን ሰሞኑን በደቡብ ጎንደር ሀሙሲት ዓርብ ገብያ ዙሪያ መከላከያ ባደረገው ኦፕሬሽን በርካታ የቡድኑ ታጣቂዎች እርምጃ ተወስዶባቸዋል። ለዚህም የተሳካ ኦፕሬሽን የአካባቢው ህብረተሰብ ከመከላከያ ሰራዊት ጎን በመሆን ከፍተኛ ሚና የተጫወተ ሲሆን ይህም የህዝቡን ሰላም ወዳድነት እና እንደሁልጊዜውም ከመከላከያ ሰራዊቱ ጎን እንደሚቆም በግልጽ የሚያሳይ ተግባር ነው።

👉በአማራ ክልል በማዕከላዊ ጎንደር ዞን የመንግስትን የሠላም ጥሪ የተቀበሉ በርከት ያሉ ታጣቂዎች ወደ ሰላማዊ ህይወት ተመልሰዋል። መንግስት ያቀረበውን የሰላም ጥሪ ተከትሎ የሃገር ሽማግሌዎች፣...
29/12/2023

👉በአማራ ክልል በማዕከላዊ ጎንደር ዞን የመንግስትን የሠላም ጥሪ የተቀበሉ በርከት ያሉ ታጣቂዎች ወደ ሰላማዊ ህይወት ተመልሰዋል።
መንግስት ያቀረበውን የሰላም ጥሪ ተከትሎ የሃገር ሽማግሌዎች፣የሃይማኖት አባቶች፣ከወረዳ እና ቀበሌ አስተዳደሮች እና ከፀጥታ አካላት ጋር በጥምረት በመሆን በምዕራብ በለሳ ወረዳ ፣በማክሰኝት ወረዳ እንዲሁም በጎንደር ዙሪያ ወረዳ ቁጥራቸው ከ177 በላይ የሚሆኑ ታጣቂዎች ወደ ሰላማዊ ህይወት መመለሳቸውን የክፍለጦሩ አዛዥ ተናግረዋል።
አዛዡ ኮሎኔል አብርሀም በንቲ ምንግዜም ከጦርነት ባሻገር በውይይት በዲፕሎማሲያዊ መንገድ ችግሮችን የመፍታት ሂደት ከሁሉም በላይ ሊቀድም እንደሚገባ ገልፀው ይህንኑ ሂደት የተመለከቱ ሌሎች በየጫካው የታጠቁ ቡድኖች ወደ ሠላማዊ ህይወት ሊመለሱ እንደሚገባቸውም ጠቁመዋል።
ወደ ሰላማዊ ህይወት ከተመለሱት መካከል አንዳንዶች የነበርንበት የጥፋት መንገድ ማህበረሰባችንን በይበልጥ የሚጎዳ ሰላማችንን የሚያደፈርስ በመሆኑ የሠላም ጥሪውን ተቀብለን ወደ ህዝባችን ተቀላቅለናል ብለዋል።
ሰላም ወዳዶቹ በመንግስታችን እና በሠራዊታችን ጥረት ከነበርንበት የጥፋት መንገድ መመለስ ችለናል የታጠቀው ቡድን አባላትም ከእኛ መማር አለባቸው ሲሉ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።

✍️አንድ አማራ በሚል በሚንቀሳቀስ እና በመከታው ማሞ በሚመራው ታጣቂ ሃይል መካከል በተፈጠረ ግጭት መገዳደል ተከስቷል!በሰሜን ሸዋ ዞን ሚዳ ወረሞ ወረዳ በሚንቀሳቀሱት የአንድ አማራ ታጣቂ እ...
29/12/2023

✍️አንድ አማራ በሚል በሚንቀሳቀስ እና በመከታው ማሞ በሚመራው ታጣቂ ሃይል መካከል በተፈጠረ ግጭት መገዳደል ተከስቷል!

በሰሜን ሸዋ ዞን ሚዳ ወረሞ ወረዳ በሚንቀሳቀሱት የአንድ አማራ ታጣቂ እና በመከታው ማሞ በሚመሩት ታጣቂዎች መካከል ጥቅምን መሰረተ ያደረገ ግጭት ተፈጥሮ የቆየ ሲሆን ሰሞኑንም በተከሰተው ግጭት አለመግባባት አንድ አማራ በሚል የሚንቀሳቀሰው ታጣቂ በመከታው ሞሞ በሚመራው ታጣቂ ላይ ጠንከር ያለ ጥቃት መፈፀሙን ከታማኝ ምንጮች የተገኙ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡

ጥቃቱን ተከትሎ በርካታ የመከታው ሞሞ ታጣቂዎች በአንድ አማራ ታጣቂ ሃይል መታገታቸው የታወቀ ሲሆን እገታውን ለመፈፀም በተደረገ ፍልሚያ በሁለቱም በኩል ቀላል የማይባል ታጣቂ መሞቱ ታውቋል፡፡ ከሞት ተርፈው የታገቱ ታጣቂዎቹን ለማስለቀቅም በመከታው ማሞ የሚመራው ታጣቂ ተጨማሪ የሃይል እርምጃ በአንድ አማራ ታጣቂ ላይ ለመፈፀም ዝግጅት እያደረገ እንደሚገኝ የተገኙ መረጃዎች ጠቁመዋል፡፡

ትውልደ ኢትዮጵያዊው ሄማን በቀለ የ2023 የአሜሪካ ቁጥር አንድ ታዳጊ ሳይንቲስት ውድድር አሸናፊ ሆነ ✍️ ለቆዳ ካንሰር ሕክምና የሚሆን ሳሙና የሠራው ትውልደ ኢትዮጵያዊው ታዳጊ ሄማን በቀለ...
29/12/2023

ትውልደ ኢትዮጵያዊው ሄማን በቀለ የ2023 የአሜሪካ ቁጥር አንድ ታዳጊ ሳይንቲስት ውድድር አሸናፊ ሆነ

✍️ ለቆዳ ካንሰር ሕክምና የሚሆን ሳሙና የሠራው ትውልደ ኢትዮጵያዊው ታዳጊ ሄማን በቀለ የዘንድሮው 2023 የአሜሪካ ቁጥር አንድ ታዳጊ ሳይንቲስት ውድድር አሸናፊ መሆኑ ተገለጸ፡፡
ላለፉት አራት ወራት የአሜሪካ ቁጥር አንድ ታዳጊ ሳይንቲስት ለመሆን ከሌሎች እኩዮቹ ጋር ሲፎካከር የነበረው ሄማን ለቆዳ ሕክምና የሚሆን ሳሙና በመፍጠር ከሌሎች ልቆ መገኘቱ ተጠቁሟል፡፡
ውድድሩ ተማሪዎች ለውጥ ማምጣት የሚችል ፈጠራ እንዲሠሩ የሚያበረታታ ሲሆን የዚህ ውድድር አሸናፊ የሆኑ ታዳጊዎች የ25 ሺሕ ዶላር ሽልማትና ከፍተኛ እውቅና ያገኛሉ ተብሏል።
ግኝቱን እንዴት እንዳመጣ የተጠየቀው ታዳጊው ሄማን “እኔ የፈጠርኩት ለቆዳ ሕክምና የሚሆን ሳሙና ነው፤ ይህም የተለያዩ የቆዳ ካንሰሮችን ማከም የሚችል ነው” ሲል ለቢቢሲ ተናግሯል።
እንደ ሄማን ገለፃ ሳሙናው ለማከም የሚሆኑ የተለያዩ ንጥረ ነገሮችን የያዘ ሲሆን አልፎም ቆዳችን ውስጥ ያሉ ካንሰርን መከላከል የሚችሉ ህዋሶችን (ሴሎችን) ያነቃቃል።
ሳሙናው ከሌሎች የቆዳ ካንሰርን ከሚያክሙ ምርቶች ጋር ሲነፃፀር ዋጋው እጅግ ዝቅ ያለና 8 ዶላር ከ50 ሳንቲም መሆኑን የጠቀሰው ታዳጊ የሌሎች የቆዳ ካንሰርን የሚያክሙ መድኃኒቶች ዋጋ በአማካይ 40 ዶላር ነው ብሏል።
በሽታን ለመከላከል የሚመረቱ መድኃኒቶች ውጤታማነታቸው ብቻ ሳይሆን ለሁሉም ተደራሽ መሆን እንዳለባቸው የጠቆመው ታዳጊ ሄማን ሳሙናው ከውጤታነቱ በሻገር ዋጋው ተመጣጣኝ እንዲሆን ፈልጎ መሥራቱንም ተናግሯል። ሳይንስ ለሰው ልጆች እኩል ጥቅም ላይ መዋል አለበት ሲልም ገልጿል።
በኢትዮጵያ የተወለደው ሄማን ሃገር ቤት የተመለከታቸው ነገሮች በሳይንስ ዘርፍ አንድ ለውጥ የሚያመጣ ምርት ለመሥራት እንዳነሳሱትም ተናግሯል።
ኢትዮጵያ እያለሁ ሰዎች ፀሐይ እየመታቸው ለረዥም ሰዓታት ሲሰሩ አያለሁ፤ በድኅነት ምክንያት ሰዎች የጤና አገልግሎት በቀላሉ ማግኘት እንደማይችሉ ተመልክቻለሁ፣ ይህም የበርካታ የዓለማችን ሃገራት እውነታ ነው ብሏል።
ልጅ ሳለሁ ያልተረዳኋቸው አሁን እየገቡኝ የመጡ እውነታዎች አሉ የሚለው ታዳጊ ሄማን መድኃኒቶች ለሁሉም ተደራሽ መሆን አለባቸው ሲልም ይከራከራል።
ወደፊት ሊያሳካቸው የሚልፈጋቸው በርካታ ሐሳቦች እንዳለውና ለጊዜው ቅድሚያ መስጠት የሚፈልገው ግኝቱን ማሳደግ ነው ብሏል።
ሥራው ለዚህ ሽልማት ፕሮጀክት ጥቅም ብቻ እንዲውል ሳይሆን ለመላው ዓለም እንዲሰራጭ እንደሚፈልግ ጠቅሶ ሽልማት እና እውቅና ካስገኘለት የምርምር ውጤት ባለፈ በሌሎች የሳይንስ መስኮች የራሱን አሻራ ማሳረፍ እንደሚፈልግም ተናግሯል።
በቨርጂኒያ ግዛት የሚገኘው የውድሰን ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የ9ኛ ክፍል ተማሪው ሄማን 3ኤም እና ዲስከቨሪ ኤዱኬሽን የተሰኙት ተቋማት የሚያዘጋጁትን ሀገር አቀፍ ሽልማት አግኝቷል።
በአሜሪካ ውስጥ የቆዳ ካንሰር ከሁሉም የካንሰር ዓይነቶች በላይ የተስፋፋ መሆኑና አገሪቱ በየዓመቱ ለቆዳ ካንሰር ሕክምና 8.1 ቢሊዮን ዶላር ወጭ እንደምታደርግም መረጃው አመላክቷል።

29/12/2023
✍️ሰውዬው ዘመኑን የቀደመ ፖለቲከኛ እና የዲፕሎማሲ ሰው ነው❗️አይገርምም ከኛው መሪ ውጪ፡ ይህንን የማድረግ አቅም ያለውን አንድም መሪ ልትጠራልኝ አትችልም። አለም እሱ ያመጣውን ሰላም ተረባ...
28/12/2023

✍️ሰውዬው ዘመኑን የቀደመ ፖለቲከኛ እና የዲፕሎማሲ ሰው ነው❗️
አይገርምም ከኛው መሪ ውጪ፡ ይህንን የማድረግ አቅም ያለውን አንድም መሪ ልትጠራልኝ አትችልም። አለም እሱ ያመጣውን ሰላም ተረባርቦ አደፈረሰ። ቆስቁሶ ቆስቁሶ ጦር ከተማዘዙ በሁላ እንዳላየ ዝም አለ። እሱ ግን በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ሁለቱንም ተፋላሚዎች ከማናገር አልፎ፡ በአዲስ አበባ ላይ ቀን ከሌት ለሰላማቸው የሚሰራ ሀይል አለ።
በዚህና በርካታ መሰል ማሳያ ነው በኩራት The smartest man in the universe የሚለው መጠሪያ የሚመጥነው። 💪🏾🙏
ሰላም ለሀገራችን፡ ሰላም ለአፍሪካ🙏🙏

ኢትዮጵያ የእኛም የእናንተም ናት መጥተው ይጎብኟት! ✍️ለሁለተኛ ትውልድ ዳያስፖራ ኢትዮጵያዊያን ሀገራቸውን እንዲጎበኙ ትልቅ እድል ተመቻችቷል! በውጭ ሀገር የተወለዱ ኢትዮጵያዊያን ወይም የሁ...
28/12/2023

ኢትዮጵያ የእኛም የእናንተም ናት መጥተው ይጎብኟት!

✍️ለሁለተኛ ትውልድ ዳያስፖራ ኢትዮጵያዊያን ሀገራቸውን እንዲጎበኙ ትልቅ እድል ተመቻችቷል!
በውጭ ሀገር የተወለዱ ኢትዮጵያዊያን ወይም የሁለተኛ ትውልድ ዳያስፖራ ኢትዮጵያዊያን ሀገራቸውን እንዲያውቁ ጥሪ ቀርቦላቸዋል። ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ትኬት ሰርቪስ ጀምሮ የሆቴል ማረፊያዎች እና የተለያዩ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ሁለተኛ ትውልድ ዜጎቻችን ኢትዮጵያን እንዲጎበኙና እንዲያውቁ ለማበረታታት ታላቅ ቅናሽ ማድረጋቸውም ታውቋል፡፡

በኢትዮጵያ የተለያዩ አከባቢዎች የሚገኙ ታሪካዊ ስፍራዎችን እየጎበኙ የባህል፣ የቋንቋ፣ የሀይማኖት ታሪካቸውን እንዲያስታውሱ ጥሪ የቀረበላቸው ሲሆን ከወግ፣ ባህል፣ ታሪካቸው ጋር በደንብ ከተቆራኙ በኋላ የተቸገሩ ወንድም እህቶቻቸውን በመርዳት እና በሀገራቸው ችግኝ በመትከል ለትውልድ የሚሻገር አሻራቸውን እንዲያሳርፉም ገብዣ ተደርጎላቸዋል።

መረጃ✍️የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ሃሙስ ታህሳስ 18 ቀን 2016 ዓ.ም ክፍለጦሩ ከሰሞኑ ባደረገው ዘመቻ የፅንፈኛው ቡድን መገልገያዎች በቁጥጥር ስር ሲውሉ በርካታ የቡድኑ አባላት ከጥቅም ው...
28/12/2023

መረጃ

✍️የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ሃሙስ ታህሳስ 18 ቀን 2016 ዓ.ም
ክፍለጦሩ ከሰሞኑ ባደረገው ዘመቻ የፅንፈኛው ቡድን መገልገያዎች በቁጥጥር ስር ሲውሉ በርካታ የቡድኑ አባላት ከጥቅም ውጪ ሆነዋል።
የተሠጠውን የሠላም አማራጭ ወደጎን በመተው የሠላምና የልማት ፀር ሆነው በዝርፊያ የግል ጥቅሙን ማስከበር እና በጠመንጃ መንግስት መሆንን በመረጠው ሀይል ላይ በተደረገው ዘመቻ ጥቂት የማይባሉ የቡድኑ አባላት ከጥቅም ውጪ ሲሆኑ ሲጠቀምባቸው የነበሩ የጦር መሳሪያዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የክፍለ ጦሩ ምክትል አዛዥ ለኦፕሬሽናል ሌተናል ኮሎኔል ሸለመው ሙለታ ገልፀዋል።
ቡድኑ በማዕከላዊ ጎንደር ዞን በምስራቅ በለሳ ወረዳ ረዘም ላለ ጊዜ በዘረፋ ላይ ተሠማርቶ የተለያዩ የመንግስት ንብረቶችን ሲዘርፍ ሲያቃጥል ሲያወድም የነበረ መሆኑን ጠቅሰው በተደረገው ዘመቻ ከጥቅም ውጪ በማድረግ አከባቢውን ከስጋት ነፃ ማድረግ ተችሏል ብለዋል።
በዘመቻው ቡድኑ ላይ ከደረሰው ሰብአዊና ቁሳዊ ኪሳራ ባሻገር በዝርፊያ ሲጠቀምበት የነበረውን ባለቤትነቱ የመንግስት የሆነ ተሽከርካሪ በቁጥጥር ስር መዋሉንም የሬጅመንት አዛዥ ሻለቃ ጌታ በላይ ገልፀዋል።

የድሬዳዋ ከንቲባ ከዲር ጁሃር የቁልቢ ገብርኤል መንገደኞችን እየተቀበለ ነው❤ይህ ሰው ይለያልእንዲህ ያሉ አመራሮችን ያብዛልን!🙏
28/12/2023

የድሬዳዋ ከንቲባ ከዲር ጁሃር የቁልቢ ገብርኤል መንገደኞችን እየተቀበለ ነው❤
ይህ ሰው ይለያል
እንዲህ ያሉ አመራሮችን ያብዛልን!🙏

✍️ወጣቱ ጀግናዉን የሃገር የመከላከያ ሰራዊት በገፍ እየተቀላቀለ ነው!ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት በአለም አቀፍ ደረጃ ጠንካራ ሰራዊት ካላቸው ሀገራት አንዷ መሆን ችላለች። ስለዚህ አሁን የሰላም ...
28/12/2023

✍️ወጣቱ ጀግናዉን የሃገር የመከላከያ ሰራዊት በገፍ እየተቀላቀለ ነው!
ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት በአለም አቀፍ ደረጃ ጠንካራ ሰራዊት ካላቸው ሀገራት አንዷ መሆን ችላለች። ስለዚህ አሁን የሰላም ችግር ሆኖ ኢትዮጵያን የሚያስጨንቃት አካል የለም። ኢትዮጵያ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የተደገፈ ጠንካራ ሰራዊት እንደገነባችና ማንም ተነስቶ ኢትዮጵያን መድፈር እንደማይችል የውስጥ እና የውጭ ጠላቶቻችን ያውቃሉ። ሀገራችን ኢትዮጵያ እጅግ ዘመናዊ እና ፍጹም ህዝባዊ የሆነ የሀገር መከላከያ ሰራዊት መገንባት ችላለች።ሀገራችን ኢትዮጵያ በአለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ የሆነ የአየር ሃይል፣ የባህር ሃይል እና የምድር ሃይል በመገንባት ላይ ትገኛለች። በተጨማሪም ኢትዮጵያ በብሔራዊ ደህንነት ከራሷ አልፋ ለአፍሪካ ትልቅ ተስፋ ሆናለች።ጽንፈኞችና ሀገር ጠል የሆኑ ቡድኖች ሁሌ ፕሮፓጋንዳ መንዛት እንጂ የሀገር መከላከያ ሰራዊትን ማሸነፍ አይችሉም። ስለዚህ ኢትዮጵያ ጠንካራ እረኛ ስላላት በወንበዴዎች ፕሮፓጋንዳ አትናወጥም አትፈራቸውም። ይህንም አላማ ለማሳካት በርካታ ወጣቶች ይህን ታላቅ ተቋም ለመቀላቀል ወስነዋል።

✍️መከላከያ ሰራዊታችን በሚያደርገው ጠንካራ ኦፕሬሽን  ጃውሳ ክፉኛ መጎዳቱ ታውቋል!መከላከያ ሰራዊታችን በአማራ ስም  በሚነግደው ጃውሳ ላይ የማያዳግም እርምጃ እየወሰደ ይገኛል። የአማራ ህዝ...
28/12/2023

✍️መከላከያ ሰራዊታችን በሚያደርገው ጠንካራ ኦፕሬሽን ጃውሳ ክፉኛ መጎዳቱ ታውቋል!

መከላከያ ሰራዊታችን በአማራ ስም በሚነግደው ጃውሳ ላይ የማያዳግም እርምጃ እየወሰደ ይገኛል። የአማራ ህዝብም ኦፕሬሽኑን በመደገፍ የጃውሳውን ፍጻሜ እያፋጠነ ይገኛል። በዚህም የተነሳ ቡድኑ በአሁኑ ሰዓት መውጫ መግቢያ አጥቶ በሄደበት ሁሉ እንደ አበደ ውሻ ያገኛውን ይናከሳል።

ሰሞኑን በተረገው ኦፕሬሽን በምስራቁ የጃውሳ ክንፍ ላይ ከፍተኛ ክሳራ መድረሱ የውስጥ መረጃዎች ያመላክታሉ። መከላከያ ሰራዊቱ በወሰደው እርምጃ በርካታ የቡድኑ አባላት ስደመሰሱ የተቀሩት ቁስለኛ ሆነዋል። ከሁሉ በላይ ቡድኑን ያስደነገጠው ራሱን የምስራቅ ፋኖ ክንፍ መሪ ነኝ የሚለው ምሬ ወዳጆ ተመቶ ክፉኛ መጎዳቱ መታወቁ ነው። ይህንን ተከትሎ ቡድኑን ለመምራት በሚደረገው ሂደት ውስጥ የስልጣን ሽኩቻ መባባሱም እየወጡ ያሉ መረጃዎች ያስረዳሉ። እነ ዘመነ ካሴም የራቸውን ሰው ለማስቀመጥ እንቅስቃሴ ላይ መሆናቸው የታወቀ ሲሆን በቡድኑ ውስጥ በአከባቢ እና በሃይማኖት መከፋፋል ጎራ ተፈጥሯል።
የጃውሳ ፍጻሜ ተቃርቧል!

✅ኮይሻ፣ ወንጪ እና ሌሎች ፕሮጀክቶችን የምናደንቀው ዶ/ር ዓቢይ የሃሳቡ ባለቤት ስለሆኑ እንዳይመስላችሁ።✅በቱሪዝም ዘርፍ ሀገራችን እየደረሰችበት የምትገኘውን ከፍታ ማሳያ ውብ ፕሮጀክት ስለሆ...
27/12/2023

✅ኮይሻ፣ ወንጪ እና ሌሎች ፕሮጀክቶችን የምናደንቀው ዶ/ር ዓቢይ የሃሳቡ ባለቤት ስለሆኑ እንዳይመስላችሁ።
✅በቱሪዝም ዘርፍ ሀገራችን እየደረሰችበት የምትገኘውን ከፍታ ማሳያ ውብ ፕሮጀክት ስለሆኑ ብቻ ነው
✅በጫካ ታጥሮ የተቀመጠና የተረሳን በተፈጥሮ የታደልን ውብ ቦታን አሳምሮ የገቢ ምንጭ እንዲሆን ማድረግ በራሱ ትልቅ ነገር ነው። ሊያውም የዶላር ገቢ የሚገኝበት። ውበቱ እና የጥራት ደረጃው ደግሞ በማንም የሰው ልጅ የሚወደድ ነው።

መከላከያ ሰራዊታችን በአሸባሪው ሸኔ ላይ የሚያደርገውን ኦፕሬሽን አጠናክሮ ቀጥሏል! ✍️ሀገርን ለማፈራረስ ቆርጦ የተነሳው አሸባሪ ቡድን ሸኔ በመከላከያ ሰራዊታችን ብርቱ ተጋድሎ እየተደመሰሰ ...
27/12/2023

መከላከያ ሰራዊታችን በአሸባሪው ሸኔ ላይ የሚያደርገውን ኦፕሬሽን አጠናክሮ ቀጥሏል!

✍️ሀገርን ለማፈራረስ ቆርጦ የተነሳው አሸባሪ ቡድን ሸኔ በመከላከያ ሰራዊታችን ብርቱ ተጋድሎ እየተደመሰሰ ይገኛል። የጥፋት ቡድኑ በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ የጮማን ጉዱሩ ወረዳ አካባቢ ሰላም በማወክ ህዝቡ ላይ ዝርፊያ እና ሌሎች ዘግናኝ ጥቃቶችን ለፈፀም እየተንቀሳቀሰ እያለ በጀግናው የመከላከያ ሰራዊታችን በተወሰደበት ርምጃ ክፉኝ ተመትቷል። አይቀጡ ቅጣት እየተቀጣ ያለው ይህ አሸባሪ ቡድን በጮማን ጉዱሩ በመከላከያ ሰራዊታችን በተደረገ ኦፕሬሽን 10 የሚሆኑ ታጣቂዎችን በሞት ሲያጣ 6 የሚሆኑት ከታጠቁት ኋላ ቀር መሳሪያ ጋር በመከላከያ ሰራዊቱ ተማርከዋል

የሰላም ዘብ የሀገር መከላከያ ሰራዊት!✍️ኢትዮጵያን በዘመናት መቀያየርና በመንግስታት መለዋወጥ ምክንያት ያልተቀየረ ! ስለ ሀገር ሲል ለሰላም ዘብ ለመሆን ለሀገር ሉአላዊነት መጠበቅ ጭምር እ...
27/12/2023

የሰላም ዘብ የሀገር መከላከያ ሰራዊት!

✍️ኢትዮጵያን በዘመናት መቀያየርና በመንግስታት መለዋወጥ ምክንያት ያልተቀየረ ! ስለ ሀገር ሲል ለሰላም ዘብ ለመሆን ለሀገር ሉአላዊነት መጠበቅ ጭምር እራሱን አሳልፎ በመስጠት ፀንቶ የቆመ! የሀገር መከላከያ ሰራዊት ኢትዮጵያ አላት! ይህንን ፅናት በተግባር ዛሬም ያለ ምንም መንገጫገጭ እንዳስቀጠለ ይገኛል! ምክንያቱም የኢትዮጵያ የሀገር መከላከያ ሰራዊት ስለ ኢትዮጵያችን የነበረ እንዲሁም የሚኖር ።ዛሬን ብቻ ሳይሆን ነገንም አሻግሮ እየተመለከተ በፅናት ሀገርን ጠብቆ ለመጪው ትውልድ ለማስረከብ ሀገርን የመጠበቁን ሀላፊነት እየተወጣ ዛሬም በፅናቶ ቆሞ ይገኛል!!

ወ ን ጪ ኦ ሮ ሚ ያ🌈
27/12/2023

ወ ን ጪ ኦ ሮ ሚ ያ🌈

✍️የባህር በር አጀንዳ የሕዝቦች በጋራ የመልማት ጥያቄ ነው! የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ በፍጥነት እያደገ ከመሆኑ እና የህዝብ ቁጥርም በፊት ከነበረው እጅግ ከፍ እያለ በመምጣቱ የባህር በር ማግኘት ...
27/12/2023

✍️የባህር በር አጀንዳ የሕዝቦች በጋራ የመልማት ጥያቄ ነው!

የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ በፍጥነት እያደገ ከመሆኑ እና የህዝብ ቁጥርም በፊት ከነበረው እጅግ ከፍ እያለ በመምጣቱ የባህር በር ማግኘት ለሃገሪቱ ግድ እየሆነ መጥቷል። በዚህም ምክንያት በቅርቡ የአለም አቀፍ ህጎችን በመከተል እና መሰረት በማድረግ የባህር በር ጥያቄን በማንሳት ለመነጋገር ዝግጁ እንደሆነ የኢዮጵያ መንግስት አሳውቋል። ይህም ደግሞ የሰጥቶ መቀበልን እና የጋር ተጠቃሚነትን መሰረት ማድረጉ በሚገባ ተጠቅሷል።

የኢትዮጵያ የበህር በር ጥያቄ እየቀረበ ያለው የጎረቤት ሃገራት አብሮ የማደግ መርህን በጠበቀ እና ፍትሃዊ በሆነ መልኩ ሲሆን በዚህም የኢትዮጵያ መንግስትም ጥያቄው በሰላም እንዲሄድ የሚያደርገው እንቅስቃሴ ዓለምን እያስደመመው ነው ብንል ማጋነን አይሆንም። ስለዚህ መላው የኢትዮጵያ ህዝብም የውሸት ፕሮፖጋንዳ በማሰራጨት ለግል ጥቅማቸው ሲሉ ጠብን ለሚጭሩ ፖለቲከኞች ጆሮ ባለመስጠት ከመንግስት ጎን በመሆን በአንድልብ ለአንድ አላማ መቆም ይገባል።

የኢትዮጵያ የባህር በር ባለቤትነት ጉዳይ ያለቀለት ጉዳይ አይደለም ተስፋ ያለው እና በመንግስት ዘንድም አመኔታን ያገኘ ነው።የቀይ ባሕር ቀጣናን ከፉክክር ይልቅ የትብብርና የጋራ ተጠቃሚነት አካባቢ ለማድረግ ያሉ ዕድሎች ሰፊ በመሆናቸው የኤርትራ እህትና ወንድሞቻችን ከኢትዮጵያ ህዝብ ጎን በመቆም አለኝታነታቸውን ሊገልጹልን ይገባል። የባህር በር አጀንዳ የሕዝቦች በዘላቂነት የመልማት ጥያቄ ነው።

✍️የኢትዮጵያን የባህር በር የማግኘት ፍላጎት እዉን እንዲሆን በጋራ እንትጋ! ከአፍሪካ ሀገራት ፈጣን የኢኮኖሚ እድገት በማስመዝገብ ላይ የምትገኘው ሀገራችን ኢትዮጵያ በፍጥነት እያደገ ያለውን...
26/12/2023

✍️የኢትዮጵያን የባህር በር የማግኘት ፍላጎት እዉን እንዲሆን በጋራ እንትጋ!

ከአፍሪካ ሀገራት ፈጣን የኢኮኖሚ እድገት በማስመዝገብ ላይ የምትገኘው ሀገራችን ኢትዮጵያ በፍጥነት እያደገ ያለውን ኢኮኖሚዋን የሚሸከም የወደብ አማራጭ ለማግኘት የምታደርገውን ጥረት መላው የዓለም ህዝብ ሊደግፈው ይገባል!

የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ በፍጥነት እያደገ በመሆኑና የህዝብ ቁጥሯም ከዛሬ 30 ዓመት በፊት ከነበረው እጅግ ከፍ እያለ በመምጥቱ የባህር በር የማግኘቷ ጉዳይ የህልውና ጉዳይ ሆኗል።

አፍራካዊያን ጎረቤቶቻችን እና ኤርትራዊያን ወንድሞቻችንም ፀብ አጫሪ ጠላቶች ለሚያራግቡት ፕሮፓጋንዳ ጆሮ ባለመስጠት የኛ የኢትዮጵያዊያን የባህር በር ፍላጎት ለጋራ ተጠቃሚነት የሚበጅ መሆኑን ተረድተው ከጎናችን ሊቆሙ ይገባል።

ሁሉም ዜጋ ኢትዮጵያ በሰጥቶ መቀበል መርህ ወደብ ለማግኘት የምታደርገውን ጥረት ከመደገፍ ባሻገር ከኤርትራዊያን ወንድሞቻችን ጋር ዳግም መቃቃር ውስጥ ሊያስገቡን የሚችሉ አፍራሽ እንቅስቃሴዎችን በመዋጋት ሃገራዊ ግዴታችንን እንወጣ!

የኢትዮጵያ ወደብ የማግኘት ጥያቄ ለቀጠናው ነውጥ ወይስ ለውጥ?  ✍️ሀገራችን ከ30 ዓመት በፊት ከአንድም ሁለት ወደቦች ያሏት ሀገር ነበረች ሆኖም ግን በወቅቱ ኢኮኖሚያችን እንብዛም ያላደገ ...
26/12/2023

የኢትዮጵያ ወደብ የማግኘት ጥያቄ ለቀጠናው ነውጥ ወይስ ለውጥ?

✍️ሀገራችን ከ30 ዓመት በፊት ከአንድም ሁለት ወደቦች ያሏት ሀገር ነበረች ሆኖም ግን በወቅቱ ኢኮኖሚያችን እንብዛም ያላደገ በመሆኑ እንዲሁም የህዝብ ቁጥራችን ከአሁኑ አንፃር በጣም አነስተኛ ስለነበር የወደብን ጥቅምና አስፈላጊነት እንዲህ እንዳሁኑ ለመረዳት አዳጋች ነበር። ሆኖም ግን አሁን ኢትዮጵያ ካላት የህዝብ ቁጥር አንፃር እንዲሁም እያስመዘገበች ባለችው ፈጣን ኢኮኖሚ ምክንያት የባህር ወደብ ማግኘት ለነገ የሚባል ቅንጦት አይደለም ። ኢትዮጵያ ብቻዋን የመበልፀግ አላማ ስለሌላት ወደብ የማግኘቷ ጥቅም ለቀጠናውም ጭምር ነው። ስለዚህም አፍሪካዊያን እንዲሁም ኤርትራዊያን ወንድሞቻችን ያለንን በጋራ የመልማትና የማደግ ፍላጎት ተረድተው ከጎናችን መቆም አለባቸው። ከዚህ ውጭ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ቅንጣት ታክል የሀገር ፍቅር ስሜት የሌላቸው እና ለሆዳቸው ያደሩ ፀብ አጫሪዎችን ባለመስማት ኢትዮጵያ ለራሷ እና ለቀጠናው ልማት ወደብ ለማግኘት የምታደረገውን ጥረት በሙሉ ልብ መደገፍ አለበት።

✍️ኢትዮጵያን የባህር በር ለማግኘት የምታራምደውን እዉነተኛ ፍላጎት መላው የዓለም ህዝብ ሊደግፈው ይገባል!   ኢትዮጵያ ሃገራችን ከ30 ዓመታት በፊት የሁለት ወደብ ባለቤት የነበረች ሲሆን በ...
26/12/2023

✍️ኢትዮጵያን የባህር በር ለማግኘት የምታራምደውን እዉነተኛ ፍላጎት መላው የዓለም ህዝብ ሊደግፈው ይገባል!

ኢትዮጵያ ሃገራችን ከ30 ዓመታት በፊት የሁለት ወደብ ባለቤት የነበረች ሲሆን በወቅቱ ኢኮሚያዋ ያላደገ እና የህዝብ ቁጥርም እንዲሁ ብዙ ያልነበረ በመሆኑ የወደብ ጉዳይ በወቅቱ ብዙም ትኩረት ያገኘ አልነበረም።

ሆኖም አሁን አሁን የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ በፍጥነት እያደገ ከመሆኑ እና የህዝብ ቁጥርም ከዛሬ 30 ዓመት በፊት ከነበረው እጅግ ከፍ ያለ መሆኑ የባህር በር ማግኘት ለሃገሪቱ ግድ እየሆነ መጥቷል።
ከዚህም አልፎ የኢትዮጵያ ወደብ ማግኘት ከራሷ ጥቅም አልፎ ለቀጠናው ጭምር ጠቀሜታው የጎላ በመሆኑ ጎረቤት ሃገራት ጭምር አጀንዳዉን እንደራሳቸው አጀንዳ ወደፊት ገፍቶ መውሰድ እንደሚገባቸው ይሰማኛል።

መላው ዓለምም ከጊዜ ወደጊዜ እየያደገ የመጣውን የኢትዮጵያን የህዝብ ቁጥር እና የኢኮኖሚ መመንደግን ከግንዛቤ ውስጥ በማስገባት ሃገራችንን ወደብ የማግኘት ፍላጎት እዉን እንዲሆን መስራት አለባቸው። ከዚህም ውጭ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ዜጋ ኢትዮጵያ በሰጥቶ መቀበል መርህ ወደብ ለማግኘት የምታደርገውን ጥረት ከመደገፍ ባሻገር ከ ዕርትራ ጋር ዳግም መቃቃር ውስጥ ሊያስገቡን የሚችሉ አፍራሽ እንቅስቃሴዎችን በመዋጋት ሃገራዊ ግዴታዉን መወጣት አለበት።

ኤርትራዊያን ወንድሞቻችንም ይሄን እዉነታ ተረድተው ፀብ አጫሪዎች ለሚያራግቡት ፕሮፓጋንዳ ጆሮ ባለመስጠት በሁለቱ ሃገራት መካከል የተፈጠረው መልካም የሚባል ግንኙነት እንዳይሻክር ነገሮችን በጥንቃቄ መመልከት አለባቸው።

በሸኔ አባላት ላይ እርምጃ ተወሰደባቸውየኢፌዴሪ መላከያ ሠራዊት ማክሰኞ ታህሳስ 16 ቀን 2016 ዓ.ም ✍️በቀጠናው የሚገኘው ሠራዊት በአሽባሪው ሸኔ ላይ በወሰደው እርምጃ የቡድኑ አባላት ተማ...
26/12/2023

በሸኔ አባላት ላይ እርምጃ ተወሰደባቸው

የኢፌዴሪ መላከያ ሠራዊት ማክሰኞ ታህሳስ 16 ቀን 2016 ዓ.ም

✍️በቀጠናው የሚገኘው ሠራዊት በአሽባሪው ሸኔ ላይ በወሰደው እርምጃ የቡድኑ አባላት ተማርከዋል።
ክፍለጦሩ በተቀናጀና በተናበበ መልኩ ባደረገው ውጤታማ ስምሪት የንፁሃንን ህይወት ለመቅጠፍና የአካባቢውን ሰላም ለማደፍረስ ሲንቀሳቀስ በነበረው አሸባሪው ሸኔ ቡድን ላይ ጠንካራ እርምጃ በመውሰዱ ጥቂት የማይባል የቡድኑ አባላት ሲመታ ቀሪው መማረኩን በምዕራብ ዕዝ የአንድ ክፍለጦር አዛዥ ተናግረዋል።
የክፍለጦሩ አዛዥ ኮሎኔል መሀመድ ሙሳ በምስራቅ ወለጋ ዞን በጊዳ አያና ወረዳና በኢቨንቱ ሀሮ ሊሙ አካባቢ በመንቀሳቀስ ዘረፋዎችንና ግድያዎችን ሲፈፅም የነበረው የአሸባሪው ሸኔ ቡድን የለመደውን ዘረፋ ለማድረግ እየተንቀሳቀሰ ባለበት ወቅት የክፍለጦሩ ሰራዊቱ ከአካባቢው ህብረተሰብ በደረሰው ጥቆማ መሰረት ተከታትሎ እርምጃ መውሰዱንና ጥቂት የማይባሉ መመታታቸውን እና መማረካቸውን ገልፀዋል።
ቀጣይም የህዝብን ሰላም በመንሳት በንፁሃን ዜጎች ላይ ግፍና ስቃይ እያደረሰ የሚገኝ ማንኛውም በቀጠናው የሚገኝ ፀረ-ሰላም ሀይል ላይ ርምጃው ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን የክፍለጦሩ አዛዥ ተናግረዋል

🌈ሙሉ ጄኔራል አበባው ታደሰ! የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጇ! እሳት ነው ፣ አበባም ነው! ምርጥ ወቶአደር፣ ሀገሩን ከራሱ በላይ ያፈቅራል ፣ ደፋር ነው ፣ ለወታደራዊ ሳይንስ አእምሮውንም አካሉ...
26/12/2023

🌈ሙሉ ጄኔራል አበባው ታደሰ!
የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጇ!
እሳት ነው ፣ አበባም ነው!
ምርጥ ወቶአደር፣ ሀገሩን ከራሱ በላይ ያፈቅራል ፣ ደፋር ነው ፣ ለወታደራዊ ሳይንስ አእምሮውንም አካሉንም ያስገዛል፣ ሂዎቱን ለሞት አሲዞ ከሞት ጋር በየቀኑ ግብ ግብ ይገጥማል ፣ሰርክ '' ሀገሬ እኔ ከአንቺ በፊት '' ይላል ፣ ስለሃገሩ በልበሙሉነት ይወጋል ፣ ያዋጋል!
ጄኔራል አበባው ታደሰ እንዲህ አይነት ምርጥ ወቶአደር ነው ። በጎጥ ጉያ ገብቶ ሲደናበር አታዩትም ። የእሱ ጎጥ አንዷ ሀገሩ ፣ አንዷ እናቱ ፣ አንዷ ምድሩ ፣ አንዷ ኢትዮጵያ ብቻ ነች ። ስለ ኢትዮጵያ አንገትህን ስጥ በሉት ፣ ለሰከንድ ሳያስብ አንገቱን እየሳቀ ይሰጥላታል ።
ከወሎ ላስታ፣ ከእነ ቅዱስ ላሊበላ ምድር ፣ ከጀግኖቹ ከዋግሹሞቹ ሀገር ፣ ከአገዎቹ ፣ ከአማሮቹ ሰማይ ስር፣ እትብቱን ቀብሮ አንደ ደቦል አንበሳ እየተንጎራደደ ወቶአደርነትን የተቀላቀለው ገና በ14 አመቱ ነበር በ1988 ዓም የብርጋዴር ጄኔራልነት መዓረግ ሲሰጠው ገና የ29 አመት ለግላጋ ወጣት ነበር። በወቅቱ የአፍሪካ ወጣቱ ብርጋዴር ጄኔራል ተብሎ በአፍሪካ ወታደራዊ የታሪክ መዝገብ ላይ ሰፍሯል። ከወቶአደርነት ውጭ ሌላ ሂዎት የለውም። የጎጥ ፖለቲካ አያስደነግጠው ፣ ሀብት አያስጎመጀው፣ ዝና ሚዛኑን አያስተው ፣የእሱ ሂዎቱ ሀገሩ ፣ ሀብቱ አይቶ የማይጠግባቸው ወቶአደሮቹ ብቻ ናቸው ። ታታሪው የጦር ገበሬ ፣ የእሳቱ ጉማጅ ፣የጋሽ ታደሰ ልጅ ፣ ወሎየው ፣ ኢትዮጵያዊው አፍሪካዊው ጄኔራል አበባው ታደሰ!!
ባድሜ ትናገር! ጀግንነቱን ትመስክር! ሰሜን ዕዝ ይናገር ፣ የተንጎራደደበት ፣እየዘለለ የጣላቱን አንገት የቀላበት፣ ድንቅ የጦር መሪነቱን ያሳየበት የጦር አውድማ ሁሉ ይጠየቅ!! ከሁሉም ከሁሉም ገና ሲያዩት ከፍቅራቸው የተነሳ በሲቃ የሚዋጡት ፣ ከጀግንነቱ የተነሳ ልባቸው የሚያብጠው ፣ ሳተና ወቶአደሮቹ ስለ ጄኔራል አበባው ይመስክሩ! ኮታቸውን እየቀደዱ ልባቸውን ሊያሳዩት እንዴት እንደሞከሩ እነሱው ጀግኖቹ ይመስክሩ!
የኢትዮጵያ ወቶአደሮች ከራሱ በላይ እንደሚሳሳላቸው ያወቃሉና እነሱም ከራሳቸው በላይ ይሳሱለታል ፣ደጋግመውም በተግባር አሳይተውታል ።
ጄኔራሉ የጀግኖች ቁና መስፈሪያ ፣ ትንታግ፣ ምራቁን የዋጠ፣ ሀሞተ ኮስታራ ፣ ጠላቶቹን በክንዱ የሚያደቅ ፣ አባ ደፋር ድንቅ ፣ ወቶአደር ነው። ለጣሉቱም ለወዳጁም መድሃኒት ነው። ጠግቦ ሀገር ላፍረስ ላለ ጥይት ፣ ለተራበው ወገኑ ደግሞ እንጀራ እና ሰላም መስጠትን ያውቅበታል። በማህበራዊ ሂዎቱ ሳቅ ጨዋታ አብዝቶ የሚወድ ፣ፎልፏላ፣ ሩህሩህ እና ፍፁም ትሁት ፣ ቅንና ደግ ሰው ነው።
ሀገርክን እናፍርስ ያላችሁት ቀን ግን እኔ እናንተን አያድርገኝ! ወቶአደሮቹ ሁሉ አልቀው እሱ ብቻ እንኳ ቢቀር ሳይሸበር ሳይናወጥ ብቻውን ይገጥማችኋል! በሃገሩ ለመጣ ርህራሄ የለሽ ፍፁም አረመኔ ነው። በአንድያ ሀገሩ ቀልድ አያውቅም ፣ ሀገሩን አሲዞ ቁማር አይጫወትም ። የሀገሩን አንድነት ለመጠበቅ ንግግር ሳያበዛ… በቃ! ቃታውን ይሰባል ፣ መድፉን ያስጓራል ፣ ሚሳኤሉን ያስወነጭፋል ፣ ጀቶቹን ያሰነሳል፣ ጠላቶቹን ያበራያል ፣ያለ ስስት ኢትዮጵያዊ ደሙን ለኢትዮጵያ ደስስ እያለው ያፈሳል ። ሃይማኖቱም፣ ዘሩም፣ ፖለቲካውም ኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያ ብቻ ናቸው!
የፈለገችሁትን ያህል ብትጎትቱት ፣ ብትዘልፉት ፣ ብታንቋሹት… ጄኔራል አበባው አይሰማም ፣ የእናንተን የዘር ፖለቲካ ከነብሱ ይጠየፋል!! ጄኔራልነቱ ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ እንጂ ለእናንተ ጎጥ እንዳልሆነ ጠንቅቆ ያውቃል ። ከኢትዮጵያ አልፎ አፍሪካ ካፈራቻቸው ምርጥ ሙሉ ጄኔራሎቿ ውስጥ አንዱ ጄኔራል አበባ ታደሰ ነው!! የእናንተ ቁፅል ሃሳብ በጣም ትጠበዋለች ። ክንዱ እሳት ነው ይፋጃል ፣ አበባም ነው፣ ፍቅርን ሰላምን እና አንድነትን አጥብቆ ይወዳል ።
ከአንድም ሁለት፣ ሶስት ፣አራት ፣ አምስት ጊዜ ሀገሩ ልትፈርስ ምጥ ላይ በወደቀችበት ጊዜ ፈጥኖ እየደረሰ ከጓዶቹ ጋር ሆኖ የታደጋት ፣ ዛሬም እየታደጋት ያለችው ኢትዮጵያ ሀገሩ ምስክሩ ናት ። ከምትወዳቸው ልጇቿ ውስጥ አንዱ እሱ ነው! ኢትዮጵያ ውለታውን ሁሌም እንዳሰበች ፣ ሁሌም እንዳከበረችው ሁሌም ትኖራለች! ከ14 ዓመቱ ጀምራ በጀግንነት ኮትኩታ ያሳደገችው እሷው ናትና በደንብ አድርጋ ለሷ ያለውን ፍቅር ታውቀዋለች!
የቁርጥ ቀን ጄኔራላችን! አበባችን ፣ እሳታችን እንወድሃለን! እናከብርሃለን! ሰራዊትህ ዛሬም ከአንተ አመራር ጋር ሆኖ በየጋራው በየሸንተረሩ ስለምትሳሳላት ኢትዮጵያ ከወንበዴ ጋር እየተናነቀልህ ነው። ጦርህ ይወድሃል ፣ ያከብርሃል! ኢትዮጵያ ትወድሃለች! ታከብርሃለች! ታመሰግንሃለች!
Salute!!

✍️በጭፍን ፖለቲካ እየተመሩ ዘመነ ካሴን አውርደው እስክንድርን ቢሾሙትም ያው ሌባ ሌባ ነው መስረቁን አያቆምም! እስክንድር ነጋ ካልመራን የሚሉት እነ ሃብታሙ በሻ እርስ በእርሳቸው በጎጥ እየ...
26/12/2023

✍️በጭፍን ፖለቲካ እየተመሩ ዘመነ ካሴን አውርደው እስክንድርን ቢሾሙትም ያው ሌባ ሌባ ነው መስረቁን አያቆምም!

እስክንድር ነጋ ካልመራን የሚሉት እነ ሃብታሙ በሻ እርስ በእርሳቸው በጎጥ እየተከፋፈሉ ይገኛሉ። በዚህ ምክንያት የጎጃም ወጠጤ የሚል ስም ለዘመነ ካሴ የሰጡ ሲሆን እርስ በእርሳቸው እየተባሉ ለአማራ ህዝብ ቆምን ሲሉ አለማፈራቸው የሌባ አይነ ደረቅ መልሶ ልብ አድርቅ መሆናቸውን በግልፅ ያሳያል። ለዘመነ ካሴ ሲያሸረግዱ ከርመው አሁን ደግሞ አይኔን ለአፈር ብለዋል። የሚገርመው ዘመነ ካሴ እስክንድር ነጋ ከኋላ መጥቶ የመሪነቱን ዙፋን ሊቀራመተው መሆኑን ሲመለከት እጁን አጣጥፎ ይቀመጣል ማለት ዘበት ነው። እስከዛው ግን እስኬው ያጣፍጥልሽ።

መከላከያ የሁሉም ብሔር ብሄረሰብ ስብስብ ነው ✍️እውነተኛ ኢትዮጵያን የሚያውቋትም  እነሱ ናቸው። ለአላማ የቆሙ፣ በዲሲፕሊን የሚኖሩ፣ ስለሀገር የሚሞቱ ናቸው።  የሃገሪቷ መከላከያ ሰራዊት የ...
26/12/2023

መከላከያ የሁሉም ብሔር ብሄረሰብ ስብስብ ነው

✍️እውነተኛ ኢትዮጵያን የሚያውቋትም እነሱ ናቸው። ለአላማ የቆሙ፣ በዲሲፕሊን የሚኖሩ፣ ስለሀገር የሚሞቱ ናቸው። የሃገሪቷ መከላከያ ሰራዊት የብሔር የሚመስላቸው እራሳቸው ፅንፈኛ ስለሆኑ በሚያዉቁት ልክ ስለሚለኩ ነው። ጆሮአችን እስኪሰለቸን ይቀደዳሉ እንጂ መከላከያ ሰራዊታችን ከኢትዮጵያዊነት ደረጃ አይነቃነቅም።

✍️የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ሰኞ ታህሳስ 15 ቀን 2016 ዓ.ም የክፍለጦሩ አባላት የፅንፈኛውን ቡድን ዕኩይ ሴራ በማክሸፍ የማያዳግም ርምጃ ወስደዋል፡፡ በምስራቅ ጎጃም ዞን በደጀን ወረዳ ...
25/12/2023

✍️የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ሰኞ ታህሳስ 15 ቀን 2016 ዓ.ም
የክፍለጦሩ አባላት የፅንፈኛውን ቡድን ዕኩይ ሴራ በማክሸፍ የማያዳግም ርምጃ ወስደዋል፡፡
በምስራቅ ጎጃም ዞን በደጀን ወረዳ ግዳጅ ለመወጣት በተሰማራ አሃድ ላይ የማጥቃት ሙከራ በማድረግ የለመደውን የህዝብና የመንግስት ንብረት የመዝረፍ አባዜ የተጠናወተው የፅንፈኛውን ቡድን ዕኩይ ሴራ ማክሸፍ መቻሉን የክፍለጦሩ አዛዥ ኮሎኔል አይቼው ግለጠው ገለፁ፡፡
ሰሞኑን በደጀን ወረዳ ጉቢያ በተባለ ቦታ ሰላምንና ፀጥታን በማስፈን ግዳጅ ላይ በተሰማራው ሠራዊት ላይ በተሳሳተ ስሌት የማጥቃት ሙከራ ያደረገው አጥፊው ቡድን ክፋኛ መመታቱንና ከስልሳ በላይ የቡድኑ ታጣቂ ከጥቅም ውጪ መደረጉን የተናገሩት አዛዡ ፅንፈኛው ሃይል ቁስለኛውን እያንጠባጠበ እግሬን-አውጪኝ ብሎ መፈርጠጡን ገልፀዋል፡፡
መቶ አለቃ ይማም በዛን በበኩላቸው ከላይኛው አመራር እስከ ታችኛው አባላት በመግባባትና በመቀናጀት የፅንፈኛውን ቡድን ፍላጎት ማምከን እንደተቻለ ገልፀው ታጥቆት የነበረ በርካታ መሳሪያና ተተኳሽ በቁጥጥር ስር መዋሉንም ተናግረዋል፡፡
via FDRE

“ካልሰራን ካልደከምን ሀገራችንን መቀየር አንችልም”  ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ
25/12/2023

“ካልሰራን ካልደከምን ሀገራችንን መቀየር አንችልም”
ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ

✍️ሃብታሙ አያሌው እጅ የገባ ብር ማለት እሳት ውስጥ የገባ ቅቤ ማለት ነው። ማህይሙ ሃብታሙ አያሌው ኑሮውን በምስኪኑ የአማራ ህዝብ ጀርባ ላይ በማድረግ የግፍ ስርቆቱን ቀጥሎበታል። የቀመሳት...
25/12/2023

✍️ሃብታሙ አያሌው እጅ የገባ ብር ማለት እሳት ውስጥ የገባ ቅቤ ማለት ነው።

ማህይሙ ሃብታሙ አያሌው ኑሮውን በምስኪኑ የአማራ ህዝብ ጀርባ ላይ በማድረግ የግፍ ስርቆቱን ቀጥሎበታል። የቀመሳት የዲያስፖርው ገንዘብ ጣፍጣ ለሌሎች የጃውሳ መሪዎች አላስቀምስ ብሎ ብቻውን መሰልቀጡንም የተያያዘ ሲሆን ከተማሩት ጓደኞቹ ጋር ተለጥፎ ዶላር የማለብ ስትራቴጂዎችን ነድፎ በሰው ሀገር የሚለፋውን የምስኪኑን የዲያስፖራ አንጀት እየበላ ዶላር መለመኑንም ቀጥሎበታል።

አንድ አማራ ንቅናቄ VS የአማራ ህዝባዊ ግንባር!በፅንፈኛው ካምፕ መጠዛጠዙ ቀጥሏል!✍️በግል ጥቅም እና በገንዘብ ፍቅር የተጀመረ ትግል ፍቺው የሚፈፀመው በገንዘብ ምክንያት ነው ይሉ ነበር ሀ...
25/12/2023

አንድ አማራ ንቅናቄ VS የአማራ ህዝባዊ ግንባር!
በፅንፈኛው ካምፕ መጠዛጠዙ ቀጥሏል!

✍️በግል ጥቅም እና በገንዘብ ፍቅር የተጀመረ ትግል ፍቺው የሚፈፀመው በገንዘብ ምክንያት ነው ይሉ ነበር ሀቀኞቹ ታጋዮች። ፅንፈኛው ሃይል አንዳችም የህዝብ ጥያቄን ይዞ አለመነሳቱን ይልቁንስ ገንዘብ እና የግል ጥቅም ብቻ በሚያሳድዱ እንደ እስክንድር፣ ሃብታሙ አያሌው እና ዳዊት ወልደጊዮርጊስ ባሉ የሚመራ ሃይል ነው መሆኑን ደጋግመን ተናግረናል። ይኸው በአማራ ትግል ስም የሰሰቡትን ሚሊየን ዶላር ሶስቱ ግለሰቦች ማንንም አናስቀምስም ብለው ለሶስት ተከፋፍለውታል። ይህንን ተከትሎ ሌላኛው ጽንፈኛ ሃይል አንድ አማራ ለቅሶ ተቀምጧል። እኛንም አስቀምሱን የሚል ክርክር ላይ ናቸው። ኮሌጅ እንኳን መማር ያልቻለ እና እራሱን በመደበኛ ስራ መምራት ያልቻለ ሃብታሙ አያሌው እጁ የገባውን ዶላር አሳልፎ ይሰጠኛል ብለ አትልፋ 😁😁 ባይሆን አንተም ተነስተህ "በፋኖ ስም" የተወሰነ ቀፈ ቀፈል አድርግ። ታልቦ የማሰለቸው ምስኪን ዲያስፖራ እያለልህ ሃብታሙ አያሌው እጅ የገባ ዶላር ለምን ትለምናለህ? ሃብታሙ አያሌው እጅ የገባ ብር ማለት እሳት ውስጥ የገባ ቅቤ ማለት ነው። ቀልጧል! 😁 ዝም ብለው በምስኪኑ የአማራ ህዝብ ስም በልና ዲያስፖራውን ለምነው ይሰጥሃል!

✍️ጥላቻ የትም አያደረስም!ፊልድ ማርሻል ዛሬ አይደለም ኢትዮጵያዊነታቸውን የሚያስመሰክሩት! ለዛውም ፌስቡክ ሀሜተኞችን ቦታ ሰጥተው! ደናቁርት ስለሆኑ እንጂ የሳቸውን ኢትዮጵያዊነት ከሚያጠያይ...
25/12/2023

✍️ጥላቻ የትም አያደረስም!
ፊልድ ማርሻል ዛሬ አይደለም ኢትዮጵያዊነታቸውን የሚያስመሰክሩት! ለዛውም ፌስቡክ ሀሜተኞችን ቦታ ሰጥተው! ደናቁርት ስለሆኑ እንጂ የሳቸውን ኢትዮጵያዊነት ከሚያጠያይቁ የራሳቸውን ሀገር ወዳድነት ቢፈትኑ ይበልጥ ለሀገር ይጠቅሙ ነበረ! ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ የኢትዮጵያን መከላከያ ነፍስ የዘሩበት እሳቸው ናቸው! አመራር ማለት እንደሳቸው ነው! ተቋምን ለሀገራዊ ተልዕኮ ብቁ ማድረግ! ኢትዮጵያዊ ማንነትን በመከላከያ ውስጥ ያሰረፁ ኢትዮጵያዊ ጀግንነትን የተላበሱ የክፉ ቀን ደራሽ ናቸው! በሰሩት ስራ ዉጤታማ ናቸው! ዛሬ ለአንድአንዶች ስላልጣማቸው ሰነፍ የሚሆኑበት እና በብሔራቸው የሚመዘኑበት ምክንያት አላማው ሌላ ቢሆን ነው! ደነዞች የታላቅ ሰው ዋጋ መቼ ይገባቸውና! ለማንኛውም ሁሉንም ጉዳይ በብሄር መመዘን ትክክል አይደለም ብለን አሁንም እንናገራለን! በትርፍ ሰኣታችሁ የፅንፈኞችን አጀንዳ የምትካድሙ ዱኩማኖች ከእናንተ ያነሰ ኢትዮጵያዊነት ያለው ማንም የለም!

✍️«በእመቤቴ በቅድስት ድንግል ማርያም አማካኝነት ድኜ አሁን ለምስክርነት መጥቻለሁ፣ ያለፈው የፈተና ጊዜ ከባድ ነበር፣ እመቤቴ ከአንድ ሁለት ጊዜ መጥታ አድናኛለች፣ አንድ ጊዜ ቤት መጥታ ኦ...
25/12/2023

✍️«በእመቤቴ በቅድስት ድንግል ማርያም አማካኝነት ድኜ አሁን ለምስክርነት መጥቻለሁ፣ ያለፈው የፈተና ጊዜ ከባድ ነበር፣ እመቤቴ ከአንድ ሁለት ጊዜ መጥታ አድናኛለች፣ አንድ ጊዜ ቤት መጥታ ኦፕራሲዮን አድርጋ አድናኛለች፣ ኪዳነምህርትም አብርታ ቤቴ መጥታ ዳብሳ አይዞ ልጄ አሁን ድነሃል ብላኝ ሄደች፣ አዲስ አልበም ሰርቼ ጨርሼ ነበር ከአርቱ ወጣለሁ ብዬ አስቤ አላውቅም ነበር፣ እኔ የፅድቅ ስራ አልሰራውም እግዚዓብሔር ቸር ስለሆነ በእናቱ ሊያድነኝ ስለፈለገ እሱ የፈቀደው አደረገ ከሙዚቃው ስራ ሙሉ በሙሉ ወጣው»

የቀድሞ ድምፃዊ አሌክስ ኦሎምፒያ

Address


Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ቆንጆ page posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to ቆንጆ page:

Videos

Shortcuts

  • Address
  • Alerts
  • Contact The Business
  • Videos
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share