ኢትዮጵያዊነቴ ኩራቴ

  • Home
  • ኢትዮጵያዊነቴ ኩራቴ

ኢትዮጵያዊነቴ ኩራቴ DON'T LET SOMEONE TO LEAD YOU ON HIS OWN WAY RATHER BE ASSERTIVE PERSON!

04/02/2022

ምክር ቤቱ የአገራዊ ምክክር ኮሚሽን የዕጩ ኮሚሽነሮች ላይ ህብረተሰቡ አስተያየት እንዲሰጥባቸው ዝርዝራቸውን ይፋ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ጥር 27፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የኢትዮጵያ አገራዊ ምክክር ኮሚሽን የዕጩ ኮሚሽነሮች ላይ ህብረተሰቡ አስተያየት እንዲሰጥባቸው ዝርዝራቸውን ይፋ አድርጓል፡፡

የዕጩ ኮሚሽነሮች የትምህርት ደረጃ እና የስራ ልምድ ዝርዝር እንደሚከተለው ቀርቧል፡-

1. ሎሬት ፕሮፌሰር ጥሩሰው ተሰማ

Education Level: PHD

Experience

በርካታ የጥናትና ምርምር ውጤት ያላቸው፤ በሀገራችን በትምህርት ዘርፍ የመጀመሪያው ባለሙሉ ፕሮፌሰር፤ከተባበሩት መንግስታትና ሌሎች ተቋማት ዕውቅና ያገኙ

2. ዶክተር በድሉ ዋቅጅራ

Education Level: PHD

Experience

በሰሯቸው ጥናታዊ ስራዎች፣ ድርሰቶችና ማህበረ-ፖለቲካዊ ሂሶች የሀገራችንን ችግር ነቅሰው በማውጣት የመፍትሄ ሀሳቦችን ከመጠቆም ባለፈ ያለምንም ፍርሃት ላመኑብት እውነት የቆሙ

3. Prof Afework Bekele Simegn - ፕ/ር አፈወርቅ በቀለ ስመኝ

Education Level: ፒኤችዲ

Experience

ከፍተኛ ተመራማሪ፤ ከ335 በላይ የምርምር ወረቀቶችን ያሳተሙ፤ የሳይንስ ፋክሊቲ ዲን የነበሩ፤ የተለያየ የሙያ ማህበራት ጋር በመሳተፍ አስተዋፅኦ ያበረከቱ

4. Ato Zegeye Asfaw Abdi - አቶ ዘገዬ አስፋው አብዲ

Education Level: በህግ የማስተርስ ድግሪ
Experience:

ላለፉት 40 አመታት ለሀገራቸውና ለህዝባቸው የሚችሉትን ሁሉ አገልግሎት የሰጡ

5. Ambassador Tadelech H/Mikael - አምባሳደር ታደለች ኃ/ሚካኤል

Education Level: ማስተርስ ዲግሪ

Experience:

የመጀመርያ የሴቶች ሚንሰትር በኮትዲቯር እና ፈረንሳይ አምባሳደር፣አፍሪካ ህብረት በተለያዩ ሀገራት ምርጫ ታዛቢነት፣

6. Prof Tilahun Teshome - ፕ/ር ጥላሁን ተሾመ

Education Level: የህግ ፕሮፌሰር

Experience

የረዥም ጊዜ የፍርድ ቤትና የማስተማር ልምድ ያላቸው፣ በአአዩ መምህርና ተመራማሪ፣ የ2013 በማህበራዊ ዘርፍ የበጎ ሰው ተሸላሚ

7. Ato Haile Gebre Suse - አቶ ኃይሌ ገብሬ ሱሌ

Education Level: ማስተርስ ዲግሪ

Experience

ዘመናዊ የህብረት ስራ ማህበር እንዲቋቋም ብርቱ ጥረት ያደረጉ፤በፌዴራልና በኦሮሚያ ህብረት ስራ ኤጄንሲ በርካታ ኃላፊነቶችን በብቃት የተወጡ፤ በኦሮሚያ ተከስቶ ለነበረው የጸጥታ ችግር መፍትሄ በማፈላለግ ግንባር ቀደም የነበሩ እና ከፍተኛ ህዝባዊ ተቀባይነት ያላቸው

8. Prof Baye Yimam - ፕ/ር ባዬ ይማም

Education Level: ፒኤችዲ በማህበረሰብ ቋንቋ ጥናት

Experience

በአአዩ መምህርና ተመራማሪ፣ ከ30 በላይ ጥናቶችን ያሳተሙ ፤ በቋንቋ ፖሊሲ ዝግጅት ወቅት ከፍተኛ ሚና የተጫወቱ

9. Dr Semir Yesuf - ዶ/ር ሰሚር የሱፍ

Education Level: በፖለቲካ ሳይንስ 3ኛ ዲግሪ

Experience

በምክክር ስራዎች ዙሪያ አለምአቀፍ ተሞክሮዎችን ጨምሮ ጥናት ያደረጉ፤ በሰላምና ጸጥታ በግጭት አፈታትና ሀገረ መንግስት ግንባታ ላይ ጥናቶችን ያቀረቡ

10. Dr Abdisa Zeray Bemano - ዶ/ር አብዲሳ ዘርዓይ በማኖ

Education Level: ሁለት ማስተርስ ዲግሪ

Experience

በጆርናሊዝም እና ኮሙኒኬሽን ት/ት ክፍል ሀላፊ በመሆን አገልግለዋል:: በኢትዮጵያ ብሮድካስት ኮርፖሬሽን ባለስልጣን ቦርድ አባል የነበሩ፤ በመንግስት እና ተቃዋሚ ፓርቲዎች መካከል ተከታታይ የዉይይት ባህል እንዲዳብር የሰሩ፤ በመካከለኛው አፍሪካ ሀገራት እና በኢትዮጵያ የፖለቲካ ኢኮኖሚ እና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ምርምር ያካሄዱ

11. Prof Habtamu Wondimu - ፕ/ር ሀብታሙ ወንድሙ

Education Level: ፒኤችዲ

Experience

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከ 40 ዓመታት በላይ ያገለገሉ፤ በትምህርት ክፍል ሃላፊነት፣ በትምህርትና ባህርይ ጥናት ኮሌጅ ዲንነት፣ በመምሪያ አስተባባሪነት፣ በሙያ ማህበራት መሪነት፣ ኮንፈረንሶችን በማዘጋጀትና በመምራት ወዘተ በብቃት አገልግለዋል፡፡ ያደረጓቸው ከ100 በላይ የምርምር ሥራዎቻቸው በአገር ጉዳዮች በተለይም በትምህርት፣ በብዝሃነት፣ በሰላምና ግጭት ጉዳዮች እና ማህበራዊ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ፤ በርካታ ሽልማቶችንና ዕውቅናዎችን ከአገርና ከአገር ውጭ ያገኙ፤

12. Ato Gemechu Dubiso Gudina - አቶ ገመቹ ዱቢሶ ጉደና

Education Level: ማስተርስ ዲግሪ

Experience

ዋና ኦዲተር ሆነው ሀገራቸውን ለረዥም ጊዜ ሀላፊነታቸውን በታማኝነት የተወጡና ያገለገሉ

13. Ato Samuel Tasew Tefera - አቶ ሣሙኤል ጣሰው ተፈራ

Education Level: በህግ የመጀመሪያ ዲግሪ

Experience

በ 34 የመንግስት፤ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች በአማካሪነት ያገለገሉ፤ በተለያዩ ሀገራት በህግ ዙሪያ ስልጠና የሰጡ፤

14. Ambassador Muez G/hiwot W/silassei - አምባሳደር ሙዕዝ ገ/ህይወት ወ/ስላሴ

Education Level: ዲግሪ/በማኔጅመንት

Experience

በሰብአዊ ጉዳይ ስራዎች፣ በበጎ ፍቃድ አገልግሎቶች፣ አለመግባባቶች ሲፈጠሩ በመቻቻል፣ በመከባበርና በመደማመጥ ላይ የተመሰረተ የእርቅና የሽምግልና ተግባራት በመከወንና፤ ነፃ የሕብረተሰብ አገልጋሎት በመስጠትና፤ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች፣ የመልካም አስተዳደር ችግሮችና የፍትህ ጥያቄዎች በማጋለጥ ይታወቃሉ

15. Ato Ahmed Husen Mohamed - አቶ አህመድ ሁሴን መሀመድ

Education Level: በህግ የመጀመሪያና ሁለተኛ ዲግሪ

Experience

የኢትዮጵያ ሲቪል ማህበራት ድርጅቶችን ም/ቤት ም/ፕሬዘዳንት፤ በሰብሳቢ ዳኝነት፤ የሲቪል ማህበራት ድርጅቶች ባለስልጣን የቦርድ አባል

16. Prof Mesfin Araya - ፕ/ር መስፍን አርአያ

Education Level: ፒኤችዲ በአእምሮ ህክምና

Experience

በአእምሮ ህክምና ዘርፍ ከ30 አመታት በላይ ያገለገሉ፣ ከ30 በላይ ጥናታዊ ጽሁፎችን ያሳተሙ፣ ብሄራዊ ኤችአይቪ ስክሬታሪያት እንዲቋቋም ከፍተኛ ጥረት አድርገዋል፣ በተለያዩ የሀገራችን ከፍሎች በመዘዋወር ሆስፒታሎችን መርተዋል፡፡ በአአዩ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ እና በአማኑኤል ሆስፒታሎች በኃላፊነት ያገለገሉ፤ በተለያዩ ሀገራዊ የሰላም መድረኮች በሚያቀርቧቸው አስተማሪና መካሪ ሀሳቦች በመነሳት ለሀገራዊ መግባባት እየሰሩ ያሉ

17. Dr Abera Deresa - ዶ/ር አበራ ዴሬሳ

Education Level: PHD

Experience

በርካታ የምርምር ስራዎችን ሰርተዋል፤ የተለያዩ አለም አቀፍ ተሞክሮዎችን በመጎብኘት ለሀገረችን የሚመጥን ልምድ እንዲቀመር አድርገዋል። በሰላም፤ በልማትና በማህበራዊ አገልግሎት ከፍተኛ ድጋፍ ያበረከቱ

18. Wro Hirut G/Silassei Oda - ሂሩት ገ/ስላሴ ኦዳ

Education Level: ህግ ማስተርስ

Experience

የተመድ ልዩ መልእክተኛ ሆነው ያገለገሉ፤ የተለያዩ መንግስታዊ ያልሆኑ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ውስጥ የሰሩ

19. Ambassador Mohamed Dirir - አምባሳደር ሙሐመድ ድሪር

Education Level: በህግ የማስተርስ ድግሪ

Experience

በምክር ቤት አባልነት፤ በአምባሳደርነት፤ በሚንስቴርነት፤ በከፍተኛ አማካሪነት፤ በኢጋድ አስተባባሪነት፤ በሱዳን ልዩ መልእክተኝነትና በአፍሪካ ቀንድ ሰፊ ልምድና እውቀት ያላቸው።

20. Ato Nigusu Aklilu - አቶ ንጉሱ አክሊሉ

Education Level: ማስተርስ ዲግሪ

Experience

ፎረም ፎር ኢንቫይሮንመንት የሚባል ሀገር በቀል ተቋም ያቋቋሙና ዘላቂ ልማት ለሀገራችን ሰላም፣ እድገት ያለውን ፋይዳ ያሳወቁ፣ የማወያት አቅም ያጎለበቱ፣ ዴስቲኒ ኢትዮጵያን ያቋቋሙ፣

21. Prof Yaekob Arsano - ፕሮፌሰር ያዕቆብ አርሳኖ

Education Level:

ፒኤች ዲ በፖለቲካል ሳይንስ፣ ማስተርስ አፍሪካን ስተዲስ ኤንድ ኮምፓራቲቭ ፖሊቲክስ፣ቢኤ ፖሊቲካል ሳይንስ ኤንድ ኢንተርናሽናል ሪሌሽንስ

Experience:

በደቡብ አፍሪካ የኦኤዩ የምርጫ ታዛቢ(1994 እ.ኤ.አ)፣Chairman advisory council for north – south research for sustainable mitigation of development and conflict problems in the horn of Africa(2006 – 2016), national leader for water and society project in Northeastern Africa( 2014 – 2019), National leader for water essence Africa project(on going: 2021 – 2026), ድንበር ዘለል ውሃዎች ድርድር የውሃ፣መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አማካሪ፣ የታላቂ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ National Panel of Experts (NPoE) ምክትል ሰብሳቢ፣ የታላቂ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ የህዝብ ተሳትፎ ብሄራዊ ምር ቤት አባል፣የታላቂ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ላይ የ international Panel of Experts (IPoE) አማካሪ፣የወሰንና የማንነት ጉዳዮች ኮሚሽን አባል፣

22. Ato Tesfaye Habiso - አቶ ተስፋዬ ሃቢሶ

Education Level: ማስተርስ ዲግሪ

Experience

በተለያዩ መንግስታዊ ተቋማት በከፍተኛ ስራ ሃላፊነት፣ በደቡብ አፍሪካ እና በኡጋንዳ የኢትዮጵያ አምባሳደር፣ የሽግግር መንግስት ዋና ጸሀፊ፣

23. Dr Ayiforit M/Diyasin - ዶ/ር አይሮሪት መ/ድያሲን

Education Level: ፒኤች ዲ በህግ

Experience

አምባሳደር ሆነው ያገለገሉ፤ በተለያየ የሀላፊነት ቦታ የሰሩ

24. Prof Kifle W/Mikael Hajeto - ክፍሌ ወ/ሚካኤል ሐጀቶ

Education Level: ፕሮፌሰር

Experience

በተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች በቦርድ አባልነት ያገለገሉ፤ ብዙ የምርምር ጥናቶች ያቀረቡ፤ በተለያየ የምርምር ተቐማትና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ያገለገሉ፤

25. Dr Tegegnework Gete Mengesha - ዶ/ር ተገኘወርቅ ጌጡ መንገሻ

Education Level: ፒኤችዲ እና ሁለት ማስተርስ በኢኮኖሚክስና ፖለቲካ

Experience

በተመድ ልማት ድርጅት የአፍሪካ ዳይሬክተር ሆነው ያገለገሉ፤በ ሀገራት የልማት ፕሮግራሞች የመሩ፤ በርካታ ፅሁፎችን ያበረከቱ፤ በተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች ያስተማሩ፤ የልማት ባንክ የቦርድ ሰብሳቢ ሆነው ያገለገሉ፤ ግጭቶችን ለመፍታት አለም አቀፍ ተሞክሮ ያላቸው፤የተመሰከረ የአመራርና የአስተዳደር ክህሎት ያላቸው

26. Prof Kasahun Birhanu Alemu - ፕ/ር ካሣሁን ብርሃኑ አለሙ

Education Level: ፒኤችዲ

Experience

በተለያዩ ሀገር አቀፍና ዓለም አቀፍ ምክክሮች በአባልነትና በአመራርነት የሰሩ፤ ትውልድን ከመቅረፅ አንፃር በዙ ጥናቶችንና ምክረ ሀሳቦችን ያበረከቱ

27. Ato Abate Kisho Hora - አባተ ኪሾ ሆራ

Education Level: ማስተርስ ዲግሪ

Experience

ለ10 አመታት ደቡብ ኢትዮጵያን በርእሰ መሰተዳደርነት የመሩ፣

28. Dr Dawit Yohanes - ዶ/ር ዳዊት ዮሐንስ

Education Level: ፒኤችዲ

Experience

በአፍሪካ ቀንድ ያሉ የምክክር ኮሚሽን ልምዶችን የቀመረና የፖሊሲ ምክረ ሀሳብ ያቀረበ፤ በሰላምና ደህነት ተቐም በርካታ የምርምር ጥናቶችን ያከናወነ

29. Prof Hizkias Asefa - ፕ/ር ህዝቅያስ አሰፋ

Education Level: ፒኤችዲ

Experience

በሰላምና እርቅ ዙርያ ከ50 በላይ አገራት በመዘዋወር ሰርተዋል፡፡ ለተ/መ/ድ፣ የአውሮፓ ህብረት እና ለተለያዩ አለምአቀፍና አገር በቀል መ/ያ/ዶች በአማካሪነት አገልግለዋል፡፡ እንዲሁም በግጭት አፈታት፣ በሰላምና እርቅ ዙርያ በርካታ ሴሚናሮችና አውደ-ጥናቶች ከማካሄዳቸውም በላይ ብዙ መጽሐፍትንና መጣጥፎች አበርክተዋል። ሩዋንዳ፣ ኬንያ፣ ጋና፣ ናይጄሪያ፣ ሴራሊዮን፣ ላይቤሪያ፣ ደቡብ አፍሪካ፣ ሲሪላንካ፣ አፍጋኒስታን፣ ኮሎምቢያ፣ ጓቲማላ ወዘተ የሰላምና እርቅ ውይይቶችን በመምራት የተሳካ ስራ ሰርተዋል::

30. Dr Takele Seboka - ዶ/ር ታከለ ሰቦቃ

Education Level: ፒኤችዲ

Experience

ተመራማሪ፤ የፖሊሲ አማካሪ ሆነው ያገለገሉ፤ ዳኛ ሆነው ያገለገሉ፤ ብዙ ምርምር ጥናቶችን ያሳተሙ

31. Eng Getahun Husen Shikur - ኢንጂነር ጌታሁን ሁሴን ሽኩር

Education Level: ቢኤስ ሲ ኢንጂነሪንግ፣ ኤም ቢ ኤ

Experience

የ ኢትዮጵያ የሰላም፣ የልማትና የዴሞክራሲ ህዝበዊ የምክክር መድረክ የሙህራን ፎረም አቋቋመዋል፤ በ2008 እና በ2009 ተፈጥሮ የነበርውን አለመረጋጋት ተከትሎ ሀገራዊ የሙህራን መድረክ በማካሄድ 16 የመፍትሄ ሀሳቦች ለቀድሞ ጠ/ሚ/ር ኃይለማርያም ደሳለኝ አቅርበዋል፡፡ የኦሮሚያና የሶማሊ ክልሎች አዋሳኝ አካካባቢዎች ተፈጥሮ ለነበረው ፣ በኣማራና ትግራይ፣ በኢሳና አፋር ለነበሩት ግጭቶች በተቋቋመው ሀገር አቀፍ የሽማግሌዎች ህበረት አማካኝነት እንዲፈታ ጥረት አድርገዋል፤ በአፍሪካ የመገምገሚያ መድረክ ላይ በመገኘት በሰላምና መግባባት ለአፍሪካ በሚል ምክረ ሀሳብ አቅርበዋል፡፡ የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ህዝባዊ ተሳትፎ ም/ቤት አባል፣ የኢትዮጵያ ፐብሎክ ዲፕሎማሲ መስራችና አባል፣

32. Ato Bekele Gutema Jebesa - ፕሮፌሰር በቀለ ጉተማ ጀቤሳ

Education Level: ፒኤችዲ በፊሎሶፊ

Experience

ከፍተኛ የማህበረዊ ሳይንስና የፍለስፍና እውቀት ያላቸው፣ትሁትና ታታሪ

33. Prof Daniel Kitaw - ፕሮፌሰር ዳንኤል ቅጣው

Education Level: ፒኤችዲ በቴክኖሎጂ

Experience

በቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ዲን፤ የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ መስራች አባል፤ የኢትዮጵያ ስካር ኮርፖሬሽን አባል፤ የተለያዩ ተቐማት የቦርድ አባል ሆነው አገልግለዋል

34. Wro Zenebework Tadese Markos - ወይዘሮ ዘነበወርቅ ታደሰ ማርቆስ

Education Level: ማስተርስ በስነ ህዝብና በህግ

Experience

በሀገር ውስጥ፥ በብዙ የአፍሪካ ሀገራትና ዓለም አቀፍ መድረኮች ሰፊ ጥናቶች፥ፅሁፎች፥የማማከር ሥራዎችን በማህበራዊ ልማት፥ በመልካም አስተዳደር፥ በሴቶች ተሳትፎና መብት ዙሪያ እያበረከቱ ያሉ ፤ በተለያዪ የሞያ ማህበራት፥ ትምህርት ተቋማት፥ መንግስታዊ ባልሆኑ እንዲሁም በተባበሩት መንግሥታት ውስጥ በተለያዩ የአባልነት፥ሀላፊነት ቦታዎች በሀገር ውስጥና ከሀገር ውጭ የተሳተፉ

35. Ato Ibrahim Mulushewa Ishete - አቶ ኢብራሂም ሙሉሸዋ እሸቴ

Education Level: በታሪክ የመጀመርያ ዲግሪ የማስተርስ ዲግሪ
Experience

የብሔራዊ እና ክልላዊ የውህደት ጥናት ማዕከል (CeNRIS) መስራች እና ዋና ስራ አስኪያጅ ሲሆኑ፣የጥናት ማእከሉ በኢትዮጵያና በአፍሪካ ቀንድ ህዝቦች መካከል ያለውን መግባባትና ውህደት ደረጃውን በማሳደግ ረገድ ይሰራል. አቶ ኢብራሂም በአገርአቀፍ ደረጃ በሚካሄዱ የልማት፡ የሰላም፤ የሰብአዊ እና ማህበራዊ እንቅስቃሴዎች በንቃት ይሳተፋሉ፤ ከተለያዩ መንግስታዊ እና መንግስታዊ ካልሆኑ አለም አቀፍ እና ሀገር በቀል ተቋማት ጋር ይሰራሉ፡፡

36. Prof Zekarias Kenea Tesgera - ፕ/ር ዘካሪያስ ቀነአ ተስገራ

Education Level: በህግ ሁለተኛ ድግሪ

Experience

በአአዩ የህግ መምህር እና ተመራማሪ፤ በርካታ የምርምር ስራዎችን ለህትመት ያበቁ፣ በህግ ማሻሻያ ካውንስል በጎ ፍቃድ አባል በመሆን ለህግ መሻሻያዎች ስኬት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያበረከቱ፣ ሀገር ወዳድና የሀገር ሽማግሌ

37. Ato Melaku W/Mariam - አቶ መላኩ ወ/ማሪያም

Education Level: በህግ የመጀመርያ ድግሪ

Experience

ጠበቃና የህግ አማካሪ፣ በህዝባዊ ተቋማት በርካታ ሁኔታ አገልግሎት የሰጡ; በሽግግር መንግሰት ምክር ቤት በህግ አማካሪነት፤ በመንግስት ምክር ቤት በህግ ባለሙያነት፤ በኢትዮጵያ ሠብዓዊ መብት ጉባኤ (ኢሠመጉ) ዋና ፀሀፊነት፤በልማት ማህበራት በአመራርነት፡፡

38. Dr Yonas Adaye - ዶ/ር ዮናስ አዳዬ

Education Level: ፒኤችዲ

Experience

ተመራማሪ፤ አሰልጣኝ

39. Dr Wedajo W/Giyorgis - ዶ/ር ወዳጆ ወ/ጊዮርጊስ

Education Level: ፒኤችዲ
Experience

በዩኒቨርስቲ መምህርነት ያገለገሉ

40. Ato Indargachew Asegid - አንዳርጋቸው አሰግድ

Education Level: የመጀመሪያ ዲግሪ

Experience

ፀሀፊ፤ ለህዝብ ነፃነት የታገሉ፤ ለሰላምና ለእርቅ የሰሩ፤ በተለያዩ ሰብዓዊና መንግስታዊ ባልሆኑ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ውስጥ የሰሩ፤

41. Dr Mulugeta Aregawi - ዶ/ር ሙሉጌታ አረጋዊ

Education Level: PHD

Experience

የህግ መምህር፣ የተለያዩ የምርምርና ጥናት ውጤቶችን ያሳተሙ::

42. Dr Negalign Birhanu Baye - ነጋልኝ ብርሃኑ ባዬ

Education Level:

ፒኤችዲ በአለም አቀፍ ጤና

Experience

የረዥም ጊዜ የማስተማር ልምድ ያላቸው፤ የማህበረሰብ ዓቀፍ አገልግሎት፤ በርካታ የምርምር ስራዎችና ህትመት ያላቸው፡

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

አስተያየትዎን ለመስጠት ሊንኩን ይጫኑ፡-

http://www.hopr.gov.et/am/web/guest/dialog-candidate

28/01/2022
12/08/2021

Peace!!

12/08/2021

የሚገርም ምስክርነት

12/08/2021

Peace for Ethiopia, peace for all nations!!!

20/09/2020

በኢትዮጵያ የፖለቲካ ታሪክ ሰላማዊ ትግል በማድረግ የምታወቁት ጀግናዉ ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ ከሰይፉ ፋንታሁን ጋር ያደረጉት ቃለምልልስ።

Address

43213

43081

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ኢትዮጵያዊነቴ ኩራቴ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to ኢትዮጵያዊነቴ ኩራቴ:

Videos

Shortcuts

  • Address
  • Alerts
  • Contact The Business
  • Videos
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share