Wolaita Sodo Times

  • Home
  • Wolaita Sodo Times

Wolaita Sodo Times Wolaita S**o Times brings you hot and breaking news from the globe.

ብሊንከን በመጪው ሳምንት ኬንያን ጨምሮ በ3 የአፍሪካ ሃገራት ጉብኝት ሊያደርጉ ነውብሊንከን ከኬንያ በተጨማሪ ናይጄሪያ እና ሴኔጋልን ነው የሚጎበኙት፡፡ቀጣይዋን የአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበር ሴ...
12/11/2021

ብሊንከን በመጪው ሳምንት ኬንያን ጨምሮ በ3 የአፍሪካ ሃገራት ጉብኝት ሊያደርጉ ነው

ብሊንከን ከኬንያ በተጨማሪ ናይጄሪያ እና ሴኔጋልን ነው የሚጎበኙት፡፡
ቀጣይዋን የአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበር ሴኔጋልን ጨምሮ ብሊንከን የሚጎበኟቸው ሃገራት መሪዎች በጠ/ሚ ዐቢይ በዓለ ሲመት መገኘታቸው የሚታወስ ነው።

ጉብኝቱ በመጪው ሳምንት ሰኞ የሚጀምር ሲሆን ለ6 ቀናት ማለትም እ.ኤ.አ ከህዳር 15 እስከ 20 ይዘልቃል ነው ከመስሪያ ቤታቸው ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት የተገኘው መረጃ የሚለው፡፡

ጄፍሪ ፌልትማንን የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ አድርጋ የሾመችው አሜሪካ አንድ ዓመትን ያስቆጠረው ግጭት እንዲቆምና ወደ ስምምነት እንዲመጣ ግፊት እያደረገች መሆኑ ይታወቃል፡፡

በጠ/ሚ ዐቢይ የሚመራው መንግስት ግጭቱን ለማቆም አልፈቀደም በሚል ምክንያት ኢትዮጵያን ራሷ ካመቻቸችው የንግድ ችሮታ (አጎዋ) ማስወጣቷ ይታወሳል፡፡

ሆኖም ግፊቱ ሚዛናዊ አይደለም ወገንተኝነትም ይታይበታል በሚል መንግስት የዋሽንግተንን እርምጃ መኮነኑ የሚታወስ ነው፡፡

ፕሬዝዳንት ማኪ ሳል ቀጣዩ የአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበር ናቸው፡፡ በመሆኑም አሜሪካ ተቀራርባ መስራት ትፈልጋለች፡፡

ብሊንከን በስልጣን ዘመናቸው የመጀመሪያውን ጉብኝት ነው በአፍሪካ የሚያደርጉት፡፡
በናይሮቢ ከፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ እና ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትሯ ራሽል ኦማሞ ጋር ተገናኝተው በኢትዮጵያና በሌሎችም ቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ እንደሚመክሩ ይጠበቃል፡፡

የሶማሊያ እና የሱዳን እንዲሁም ወቅታዊ የአፍሪካ ቀንድ ሁኔታ የምክክሩ መቃኛ እንደሚሆንም ይገመታል፡፡

ብሊንከን እና ኬንያታ ከአሁን ቀደምም የበይነ መረብ ውይይት አድርገው ነበረ፡፡

በቅርቡ ወደ አሜሪካ ተጉዘው የነበሩት ኬንያታ ግጭቱን ለማስቆም ኢትዮጵያውያን ይወያዩ ሲሉ ከሰሞኑ ማሳሰባቸው የሚታወስ ነው፡፡

የናይጄሪያ እና የሴኔጋል መሪዎችን አግኝተው በጸጥታና ደህንነት እንዲሁም በሌሎች የትብብር ጉዳዮች ላይ እንደሚመክሩም ነው የተነገረው፡፡

የኬንያ፣ የናይጄሪያ እና የሴኔጋል መሪዎች ባሳለፍነው ወርሃ መስከረም መገባደጃ ላይ ተካሂዶ በነበረው የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በዓለ ሲመት ላይ ተገኝተው እንደነበር ይታወሳል፡፡

የቦይንግ ኩባንያ  በኢትዮጵያ ለተከሰከሰው 737 ማክስ ጄት አውሮኘላን አደጋ ኃላፊነቱን ለመቀበል ተስማማ።ቦይንግ እ.ኤ.አ. በ 2019 በኢትዮጵያ ለደረሰው 737 ማክስ አውሮፕላን አደጋ ኃላ...
12/11/2021

የቦይንግ ኩባንያ በኢትዮጵያ ለተከሰከሰው 737 ማክስ ጄት አውሮኘላን አደጋ ኃላፊነቱን ለመቀበል ተስማማ።

ቦይንግ እ.ኤ.አ. በ 2019 በኢትዮጵያ ለደረሰው 737 ማክስ አውሮፕላን አደጋ ኃላፊነቱን ለመቀበል እና በአደጋው ከሞቱት 157 ሰዎች መካከል አብዛኞቹ ቤተሰቦች ለተሳካላቸው የካሳ ጥያቄ ሀላፊነቱን ለመውሰድ ተስማምተዋል።

በፌዴራል ፍርድ ቤት በትላንትናው እለት በቀረበው ውል መሰረት ቦይንግ በአውሮፕላኑ ላይ እስካለፈው አመት ድረስ በአለም አቀፍ ደረጃ እንዲታገድ ባደረገው አደጋ ተጠያቂነቱን ይቀበላል እና ለወደፊቱ ለተጎጂ ቤተሰቦች ለሚደርሰው የካሳ ክፍያ ብቸኛ ሀላፊነቱን ይወስዳል። የጉዳት ሰለባ ቤተሰቦች ከቦይንግ የቅጣት ካሳ ላለመጠየቅ ተስማምተዋል ተብሏል።

ቦይንግ ዋና መሥሪያ ቤቱ ባለበት ኢሊኖይ ውስጥ ለደረሰው ጉዳት ለማካካሻ ጉዳት ቤተሰቦች ክስ ካቀረቡ ጉዳዮቹን ወደ ሌላ ቦታ ለመውሰድ እንዳይሞክር ተስማምቷል ፣ ይህም በግዛቱ ውስጥ ላሉት ቤተሰቦች ድል ነው ሲል ኒዮርክ ታይምስ ዘግቧል።

“ኮ/ል መንግስቱ ከሀገር የወጡበት ጉዳይ ቢጠና የማጭበርበር ውጤት አካል እንደሚሆን ጥርጣሬ የለኝም”- ጠ/ሚ ዐቢይበ1983 ዓ.ም ከአዲስ አበባ 100፣ 150፣ 200 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ው...
12/11/2021

“ኮ/ል መንግስቱ ከሀገር የወጡበት ጉዳይ ቢጠና የማጭበርበር ውጤት አካል እንደሚሆን ጥርጣሬ የለኝም”- ጠ/ሚ ዐቢይ

በ1983 ዓ.ም ከአዲስ አበባ 100፣ 150፣ 200 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ውጊያ ሳይደረግ የመንግስት ለውጥ መደረጉንም ጠ/ሚ ዐቢይ ገልጸዋል፡፡ጠ/ሚ/ር ዐብይ አሁን እየተካሄደ ያለው ነገር በ1983 ዓ.ም ከተካሄደው ጋር ተመሳሳይ ነው ብለዋል፡፡

የዎላይታ ሕዝብ ዲሞክራሲያዊ ግንባር  በኢትዮጵያ ወቅታዊ ጉዳይ ላይ  ያወጣው አቋም መግላጫ!የኢትዮጵያ ሕዝብ  የረጅም ጊዜ ፍላጎት ፡- የፓለቲካና የሰብአዊ መብት ነጻነት፤ ዲሞክራሲያዊ አስተ...
11/11/2021

የዎላይታ ሕዝብ ዲሞክራሲያዊ ግንባር በኢትዮጵያ ወቅታዊ ጉዳይ ላይ ያወጣው አቋም መግላጫ!

የኢትዮጵያ ሕዝብ የረጅም ጊዜ ፍላጎት ፡- የፓለቲካና የሰብአዊ መብት ነጻነት፤ ዲሞክራሲያዊ አስተዳደርና እኩልነት እንዲሁም ሰላም እና ዕድገት እንደሆኑ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ይስማማበታል፡፡ ይህም የኢትዮጵያ ሕዝብ ስጠብቅ የነበረው በአጼዎች ዘመን የነበረው ፊውዳሊዝም በወታደራዊ መንግሰት እንደተገረሰሰ እንዲሁም ኢትዮጵያ ከተፈጠረችበት ጊዜ አንሰቶ እስከ ወታደራዊ መንግሰት አገዛዝ የዘለቀው የብሔረሰቦች እኩልነት ጥያቄ ምላሽ በባለፈው ኢሕዴግ ሥርዓት ማግኘት እንደተቻለ (አንጻራዊ በበሆንም)፤ በ2009/10 ዓ.ም ጀምሮ በተፈጠረው ሕዝባዊ ንቅናቄ የመንግስት ሥልጣን የተቆጣጠረው ኢሕደግ ቁጥር 02 ወይም ብልጽግና ከቀደሙት በተሸለ ቀሪ የኢትዮጵያ ሕዝብ ጥያቄዎችን ከሁሉም ባለድርሻ አካላት ጋር ሆነው ለመመለስ ከመምከር ይልቅ ከአጼዎች አገዛዝ ጊዜ አንስቶ እስከ ወታደራዊ አገዛዝ ድረስ የነበረውን የአገዛዝ ሥርዓት ለማምጣት በመታተሩ መላውን የኢትዮጵያ ሕዝብ ዋጋ እያስከፈለ ይገኛል፡፡

ከዚህም የተነሳ የሰፊው የኢትዮጵያ ሕዝብ ፍላጎት መነሻ (Public movement) እንደ ጥሩ አጋጣም በመጠቀም ድብቅ ፍላጎቱን ለማሳካት ያለመው የብልጽግና መንግሰት በባለፈው ሥርዓት የተበለሻሹ ጉዳዮችን ነክሶ በማውጣት ሁሉም ባለድርሻ አካላት የተሰማሙበትንናተራማጅ ልሆኑ የምችሉ፤ ያለንበትን ክ/ዘመን (21ኛውን) የምመጥኑ መፍትሄዎች ላይ ከማተኮር ይልቅ የአጼዎች ክ/ዘመን መፍትሄዎችን በመከተል ኢትዮጵያን ወደ ቁልቁል እየሸኛት ይገኛል፡፡

አሁን ያለንበት ዝቅታ እንደምመጣ በመገንዘብ በኢትዮጵያ ውስጥ የምገኙ ፓለቲካ ፓርቲዎች ዎሕዴግን ጨምሮ በተለያዩ ጊዜያት አማራጭ የውሳኔ ሃሳቦቹን ቢያቀርቡም ብልጽግና የእኔ ውሳኔ ሃሳብ ከሰማይ የመጣ ነው በማለት ለሌሎች ቦታ ባለመስጠት ኢትዮጵያ አሁን ያለችበት ቅርቃር ውስጥ እንዲትደርስ አድርጓታል፡፡ በዚህ ቅርቃር ውስጥም ሆኖ ሁሉንም ያሳተፈ የፓለቲካ አማራጮችን ከመፈለግ ይልቅ የፓለቲካ አማራጮችን ልያቀርቡ የምችሉ ፖለቲካኞችንና የሕዝብ አንቂዎችን በሁሉም አገራችን ክፍል በተላይም በኦሮሚያ፤ በዎላይታ እንዲሁም በአማራ ክልል የምገኙትንና በተጨማሪ በመላው ኢትዮጵያ ውስጥ የምገኙ ተጋሩዎችን በገፍ እያሰረ ይገኛል፡፡

ለማሳያ ያህል አሁን ባለንበት ሁኔታ በዎላይታ ውስጥ የምንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲ (ዎሕዴግናዎብን) አመራሮችና አባላት እንዲሁም የሕዝብ አንቂዎች እነዚህም 1) ዶ/ር ብስራት ኤልያስ፤ 2) ረ/ፕሮፌ አሰፋ ወዳጆ፤ 3) ዶ/ር ቸርነት ዎራና፤ 4) ጠበቃ አቶ አሰፋ አየሌ፤ 5) ጠበቃ አቶ አምሳሉ መሰነ፤6) አቶ ሚልክያስ ሣንጣ፤ 7) አቶ ጎበዜ አበራ፤ 8) ወ/ሪት ቆንጅት ጌታቸው፤ 9) አቶ ተሰማ ታደሴ፤ 10) አቶ አብነት ኤልያስ እና 11) አቶ ስጦታው መስፍን በብልጽግና አገዛዝ ታስሮ ይገኛሉ፡፡ በተጨማሪ ሌሎችም እየተፈለጉና እየታደኑ ይገኛሉ፡፡

ስለሆነም ዎህዴግ በወቅታዊ አገራዊ እና ክልላዊ ጉዳዮችን በተመለከተ የሚከተሉትን አቋም መግለጫ አዉጥቷል፡፡
1. መንግሰት ኢትዮጵያን እታደጋታለሁ ብሎ የሚያስብ ከሆነ ያለምንም ቅደመ-ሁኔታ ከሚመለከተው ሁሉ ባለድርሻ አካላት ጋር ለድርድር እንዲቀመጥ፤ በአስቸኳይ ጦርነትን ያቁም፤
2. ድርድሩም ዉጤታማና ተራማጅ እንዲሁም የውጭ ሃይሎችን እከይ ዓለማ ልያከሽፍ የምችል ይሆን ዘንድ ሁሉም የፓለቲካ እስረኞች እንዲፈቱና እንዲሳተፉ፤
3. በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ጥላ ሥር ሆነው የብልጽግና መንግሰት የሚያደርገውን አፈና እስራት በአስቸኳይ እንዲቆም፤
4. ሁሉም የኢትዮጵያ ሕዝብ ዝምታን እንዲሰብርናየብልጽግና መንግስትን የተሳሳተ ዓላማ በመተው ለሕዝብ ዓላማ መስዋዕትነትን ለመክፈል እንዲዘጋጅ፤
5. የዎላይታ ሕዝብ ሆይ ከዚህ ቀደም የሕዝብን ዓላማ ለማሳካት(ዎጋጎዳን ለማክሸፍ) አኩሪ ታርክ ፈጽመሃልና አሁንም ከአብራክህ የተገኙ የሕዝብ ጥያቄ አራማጆችን ማፈንና ማሰር የብልጽግና መንግስት ዓላማው የዎላይታ ሕዝብ ጥያቄ ምላሽ የምያገኘው በብልጽግና መቃብር ላይ ነው ማለት ነውና የምትታወቅበትንና ዘመን ተሻጋሪውን ሰለማዊ ትግል ለመቀላቀል ተዘጋጅ፤

ሁለም ሕዝብ ያሸንፋል፤ፈጣሪም ከጎናቸው ይሆናል፡፡
የዎላይታ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ግንባር
ጥቅምት ፣ 2014 ዓ.ም
ዎላይታ ሶዶ

የሰሜኑን ጦርነት በሰላም ለመፍታት ከተፈለገ፤ የህወሓት ኃይሎች ሶስት ቅድመ ሁኔታዎችን ሊያሟሉ ይገባል- ዲና ሙፍቲአንድ ዓመት ያስቆጠረውን የሰሜን ኢትዮጵያን ጦርነት በሰላም ለመፍታት ከተፈለ...
11/11/2021

የሰሜኑን ጦርነት በሰላም ለመፍታት ከተፈለገ፤ የህወሓት ኃይሎች ሶስት ቅድመ ሁኔታዎችን ሊያሟሉ ይገባል- ዲና ሙፍቲ

አንድ ዓመት ያስቆጠረውን የሰሜን ኢትዮጵያን ጦርነት በሰላም ለመፍታት ከተፈለገ፤ የህወሓት ኃይሎች ሶስት ቅድመ ሁኔታዎችን ሊያሟሉ እንደሚገባ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ዲና ሙፍቲ አስታወቁ። ቅድመ ሁኔታዎቹ፤ የህወሓት ኃይሎች ጥቃት እንዲያቆሙ፣ ከአማራ እና አፋር ክልሎች እንዲወጡ እና የፌደራል መንግስቱን ህጋዊነት እንዲቀበል የሚጠይቁ ናቸው።

ቅድመ ሁኔታዎቹን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዲኤታ አቶ ሬድዋን ሁሴን እና የፍትህ ሚኒስትሩ ዶ/ር ጌዲዮን ጢሞቲዮስ፤ ለውጭ ሀገር ዲፕሎማቶች ባለፈው ሳምንት ማሳወቃቸውን አቶ ዲና ተናግረዋል። ሁለቱ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት ስለ ቅደመ ሁኔታዎቹ የተናገሩት፤ ተቀማጭነታቸውን አዲስ አበባ ላደረጉ ዲፕሎማቶች በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ዙሪያ ማብራራያ በሰጡበት ወቅት ነው።

ባለስልጣናቱ “በጁንታው የተፈጠሩ የሰላም እንቅፋቶች በሙሉ መነሳት እንዳለባቸው፤ ይሄ እስከሆነ ድረስ በኢትዮጵያ መንግስት በኩል ለሰላም ምንጊዜም ዝግጁነቱ እንዳለ” ለዲፕሎማቶቹ እንዳብራሩ አቶ ዲና ገልጸዋል። በኢትዮጵያ መንግስት በኩል ያለው የሰላም ዝግጁነት “ከአንዴም ሁለቴ በግልጽ ታይቷል” ያሉት ቃል አቃባዩ፤ ለዚህም የፌደራል መንግስት የተናጥል ተኩስ አድርጎ ከትግራይ የወጣበትን ሁነት ለማሳያነት ጠቅሰዋል።

ሙሉ ዘገባውን ለማንበብ ይህን ሊንክ ይጫኑ:- https://ethiopiainsider.com/2021/4959/

የኢፌዴሪ መከላከያ የአርማ ለውጥ አደረገየኢፌዴሪ መከላከያ ሚኒስቴር ከዚህ በፊት ሲጠቀምበት የነበረውን ተቋማዊ አርማ መቀየሩን የመከላከያ ኢንዶክትሪኔሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ተወካይ ብ/ጄ...
11/11/2021

የኢፌዴሪ መከላከያ የአርማ ለውጥ አደረገ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሚኒስቴር ከዚህ በፊት ሲጠቀምበት የነበረውን ተቋማዊ አርማ መቀየሩን የመከላከያ ኢንዶክትሪኔሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ተወካይ ብ/ጄ አስፋው ማመጫ አስተወቁ።

ጄነራል መኮንኑ ፣ ተቋሙ ከዚህ በፊት ሲጠቀምበት የነበረውን አርማ የቀየረው አዲስ ከፈጠረው አደረጃጀትና እየተገበረ ካለው ሪፎርም አኳያ ገላጭ ባለመሆኑ መሆኑን አብራርተዋል ፡፡

እንደ ብ/ጄ አስፋው ማመጫ ገለፃ ፣ ተቋሙ አዲስ ይፋ ያደረገው አርማ ከተቋሙ ተልዕኮና ባህርይ አንፃር ልዩ ልዩ ትርጓሜዎችን የያዘ ነው።(መከላከያ ሰራዊት)

ሱዳን፤ አስገዳጅ ሁኔታ እስካልገጠማቸው ድረስ ዜጎቿ ኢትዮጵያን ለቆ ለመውጣት እንዲዘጋጁ አሳሰበችወቅታዊ የኢትዮጵያ ሁኔታዎችን በተመለከተ መግለጫ ያወጣው በኢትዮጵያ የሱዳን ኤምባሲ አዲስ አበ...
10/11/2021

ሱዳን፤ አስገዳጅ ሁኔታ እስካልገጠማቸው ድረስ ዜጎቿ ኢትዮጵያን ለቆ ለመውጣት እንዲዘጋጁ አሳሰበች

ወቅታዊ የኢትዮጵያ ሁኔታዎችን በተመለከተ መግለጫ ያወጣው በኢትዮጵያ የሱዳን ኤምባሲ አዲስ አበባን ጨምሮ በተለያዩ የኢትዮጵያ ከተሞች የሚገኙ ሱዳናውያን እንዲጠነቀቁ አሳስቧል፡፡

በምትንቀሳቀሱበትም ሆነ በየትኛውም አጋጣሚ ማንነታችሁን የሚገልጽ መታወቂያ መያዛችሁን እንዳትረሱ ሲል ዜጎቹን ያሳሰበው ኤምባሲው ከመሰባሰቦች እንዲርቁ እና ከአዲስ አበባ ውጪ እንዳይጓዙ አስጠንቅቋል።

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መታወጁን በማስታወስም አስገዳጅ ሁኔታዎች ካልገጠሟቸው በስተቀር ሱዳናውያኑ ኢትዮጵያን ለቆ ለመውጣት የሚያስችላቸውን አስፈላጊውን የበረራ ዝግጅት በፈቃደኝነት እንዲያደርጉም አስጠንቅቋል ኤምባሲው፡፡

ኤምባሲው በማሳሰቢያው ላይ ለውጦችን ሊያደርግ እንደሚችል እና በኢትዮጵያ የሱዳን ዜጎችን ደህንነትና ደህንነት ለማረጋገጥ እንደሚሰራ አስታውቋል።

ሰበርየቀድሞዋ የሴቶች ሕፃናትና ወጣቶች ሚኒስትሯ ፊልሰን አብዱላሒ ቤተሰቦቿ በሶማሌ ክልል ጅግጅጋ ከተማ ላይ በፀጥታ ሀይሎች መታሰራቸውን በትዊተር ገፃቸው አስታወቁ።©ኢኽላስ
10/11/2021

ሰበር
የቀድሞዋ የሴቶች ሕፃናትና ወጣቶች ሚኒስትሯ ፊልሰን አብዱላሒ ቤተሰቦቿ በሶማሌ ክልል ጅግጅጋ ከተማ ላይ በፀጥታ ሀይሎች መታሰራቸውን በትዊተር ገፃቸው አስታወቁ።
©ኢኽላስ

''የህወሓት ቡድን በነፋስ መውጫ በ16 ሴቶች ላይ የአስገድዶ መድፈር ጥቃቶችን ፈፅሟል'' ሲል አምነስቲ አስታወቀ!ከ16ቱ ሴቶች መካከል 14ቱ በቡድን መደፈራቸውንም ገልጿል======= #===...
10/11/2021

''የህወሓት ቡድን በነፋስ መውጫ በ16 ሴቶች ላይ የአስገድዶ መድፈር ጥቃቶችን ፈፅሟል'' ሲል አምነስቲ አስታወቀ!

ከ16ቱ ሴቶች መካከል 14ቱ በቡድን መደፈራቸውንም ገልጿል
======= #========

ባለፈው ዓመት ነሐሴ ወር የህወሓት ኃይሎች በአማራ ክልል ደቡብ ጎንደር ነፋስ መውጫ ከተማ ላይ ጥቃት ባደረሱበት ወቅት የአስገድዶ መድፈር፣ የዘረፋ፣ የአካላዊና የቃላት ጥቃቶችን በነዋሪዎች ላይ መፈጸማቸውን አምነስቲ ኢንተርናሽናል ገለጸ።

አምነስቲ ኢንተርናሽናል ባወጣው ሪፖርት እንዳመለከተው በከተማዋ ነዋሪ የሆኑና ያናገራቸው 16 ሴቶች በህወሓት ቡድን የአስገድዶ መደፈር ጥቃት ተፈጽሞባቸዋል።

ሴቶቹ እንዳሉት በህወሓት ኃይሎች መሳሪያ ተደቅኖባቸው እንደተደፈሩ፣ ዝርፊያ እንደተፈጸመባቸው እንዲሁም አካላዊና የአፀያፊ ቃላት ጥቃቶች እንደደረሰባቸው አመልክተዋል።

አምነስቲ ኢንተርናሽ ጨምሮ ካነገራቸው አስገድዶ የመድፈር ጥቃት ከተፈጸመባቸው 16 ሴቶች መካከል 14ቱ ጥቃቱ በቡድን እንደተፈጸመባቸው ገልጸዋል። ቡድኑ በከተማ ባሉ የህክምና ተቋማት ላይ ዝርፊያና ውድመትን አድርሰዋል ብሏል።

ትግራይ ውስጥ ሲካሄድ የነበረው ጦርነት ወደ አማራ ክልል ከተስፋፋ በኋላ የህወሓት ቡድን ወደተለያዩ የክልሉ አካባቢዎች በመግባት ጥቃት በፈጸሙበት ጊዜ ነበር ወደ ንፋስ መውጫ ከተማ የገቡት።

በአማራ ክልል በደቡብ ጎንደር ዞን ውስጥ የምትገኘውን የነፋስ መውጫ ከተማን የህወሓት ኃይሎች ተቆጣጥረው የቆዩት ከነሐሴ 06 እስከ 15/2013 ድረስ ለዘጠኝ ቀናት ነበር።

አንድ የክልሉ አስተዳደር ባለሥልጣን ለአምነስቲ እንደገለጹት አማጺያኑ በንፋስ መውጫ ከተማ በቆዩባቸው ቀናት ውስጥ ከ70 በላይ ሴቶች የአስገድዶ መድፈር ጥቃት እንደተፈጸመባቸው ሪፖርት አድርገዋል።

"የአስገድዶ መድፈር ጥቃቱ ከደረሰባቸው የሰማናቸው ምስክርነቶች የህወሓት ተዋጊዎችን አጸያፊ ተግባራት፤ ከጦር ወንጀሎች እና በሰብአዓዊነት ላይ ከተፈጸሙ ወንጀሎች ጋር የሚስተካከሉ ናቸው። ድርጊቶቹ ከሞራል ወይም ከሰብዓዊነት ያፈነገጡ ናቸው" ሲሉ የአምነስቲ ኢንትርናሽናል ዋና ፀሐፊ አግነስ ካላማርድ ተናግረዋል።

ጨምረውም የህወሓት ተዋጊዎች ወሲባዊ እና ፆታዊ ጥቃቶችን ጨምሮ የሰብዓዊ መብቶችን እና የዓለም አቀፍ ሕጎች ጥሰቶችን በሙሉ በማቆም በፈጻሚዎቹ ላይ እርምጃ እንዲወሰድ ጠይቀዋል።

አንድ የአካባቢው የሴቶች፣ ህጻናትና ወጣቶች ጉዳይ ሃላፊ ለአምነስቲ እንደገለጹት ቡድኑ በንፋስ መውጫ ከተማ ባደረሰው ጥቃት በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ 71 ሴቶች በህወሓት ታጣቂዎች መደፈራቸውን ገልፀዋል። የፌደራል ፍትህ ሚኒስቴር በበኩሉ ቁጥሩን 73 አድርሶታል።

የአስገድዶ መድፈር ጥቃት ከደረሰባቸው 16ቱ ሴቶች ውስጥ 15ቱ በጥቃቱ ምክንያት የአካልና የአይምሮ ጤና ችግሮች እንደደረሰባቸውም ሪፖርቱ አመላክቷል።

የጀርባ ህመም፣ የደም መፍሰስ፣ የሽንት መቆጣጠር ችግር፣ የመራመድ ችግር፣ ጭንቀትና ድብርት ጨምሮ የተለያዩ ምልክቶችን እያሳዩ መሆኑን አምነስቲ ኢንተርናሽናል ቃለ መጠይቅ ባደረገላቸው ጊዜ መናገራቸውንም ገልጿል።

የአማራ ክልል መንግስት ባለስልጣናት ለአምነስቲ ኢንተርናሽናል እንደተናገሩት ከጥቃቱ በኋላ በንፋስ መውጫ ከአስገድዶ መድፈር የተረፉ 54 ሰዎችን ጨምሮ የመተዳደሪያ ድጋፍ ማድረጉን አስታውቀዋል።

በክልሉ በተዘረፉ ሆስፒታሎችና ተቋማት ላይ የህክምና ቁሳቁሶችንና ሌሎች አቅርቦቶችን መልሶ ለማቋቋም፣ የተረፉ ሰዎችን የምክርና የስነ ልቦና አገልግሎት ለመስጠት በዝግጅት ላይ መሆናቸውንም ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ መንግስት አቋም እየተለሳለሰ መምጣቱ እየተነገረ ይገኛል። ***********ከተባበሩት መንግስታት እስከ አፍሪካ ህብረት፤ ከልዕለ ሃያላን አገራት እስከ ደሃ ጎረቤት አገራት፣ ከሙሳ ...
08/11/2021

የኢትዮጵያ መንግስት አቋም እየተለሳለሰ መምጣቱ እየተነገረ ይገኛል።
***********
ከተባበሩት መንግስታት እስከ አፍሪካ ህብረት፤ ከልዕለ ሃያላን አገራት እስከ ደሃ ጎረቤት አገራት፣ ከሙሳ ፋቂ እስከ ሲይሪሊ ራሞፎሳ ለኢትዮጵያ መንግስት የተደራደሩ ጥሪ ያላቀረበ የለም ማለት ይቻላል።

ይሁን እንጂ 'ከአሸባሪ' ጋር ማንኛውንም አይነት ድርድር አላካሂድም' ከማለት አልፎ ባላንጣዎቹን በአሸባሪነት በመፈረጅ የሠላም አማራጮችን ሁሉ ዝግ በማድረግ በጦርነት የተጀመረን በጦርነት ለመቋጨት በማሰብ ለቁጥር የሚታክት ኪሳራ እንዲደርስ ሆኗል።

አሁን አሁን የሃይል ሚዛኑ ወደ ተቀናቃኞች ማጋደል ሲጀምር እና የውጪ ግፊት ሲበዛበት አብይ አህመድ በሩን ለውይይት ክፍት ማድረጉን እየገለፀ ይገኛል።

ዛሬ በብሔራዊ ቴሌቪዥን ቀርበው ሃሳባቸውን የሰጡት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ድኤታ እና የመንግስት ኮሙኒኬሽን ኃላፊ በኦባሳንጆ የተጀመረውን የሽምግልና ሀሳብ እንደሚደግፉ ሁኔታዎችንም እንደሚያመቻቹላው እንዲሁም ለአፍሪካዊ ችግር አፍሪካዊ መፍትሔ ለሚለው መርህም እንደሚገዙ በይፊ ተናግረዋል።

ኦባሳንጆ በበኩላቸው የፌደራሉ መንግስት ወደ ትግራይ ተጉዘው ከህወሓት ሀይሎች ጋር እንዲወያይ ይሁንታ እንደሰጣቸው እና ችግሩ ፖለቲካዊ ስለሆነ ፖለቲካዊ መፍትሄ እንጂ ጦርነት አማራጭ አለመሆኑን እንደተስማሙ ዛሬ በነበረው የአፍሪካ ህብረት ጸጥታው ምክር ቤት በነበረው ስብሰባ ተናግረዋል።

የተባበሩት መንግስታት ጸጥታው ምክር ቤት ባለፈው ሳምንተ ባደረገው ስብሰባ ሁሉም ተዋጊ ሀይሎች በአስቸኳይ ተኩስ እንዲያቆሙ በአንድ ድምጽ መወሰኑም ይታወሳል።

የክፍት ሥራ ማስታወቂያ ለጤና ባለሙያዎች በሙሉ _______________________________________በዎላይታ ሶዶ ከተማ በቅርቡ አገልግሎት መስጠት የሚጀምረው እንያት ሆስፒታል ጤና ...
08/11/2021

የክፍት ሥራ ማስታወቂያ ለጤና ባለሙያዎች በሙሉ
_______________________________________

በዎላይታ ሶዶ ከተማ በቅርቡ አገልግሎት መስጠት የሚጀምረው
እንያት ሆስፒታል ጤና ባለሙያዎችን አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል ።

ዝርዝሩን እዚህ 👇 ይመልከቱ

በዎላይታ ሶዶ ከተማ የጫኚና አዉራጅ ዋጋ ተመን ወጣ
08/11/2021

በዎላይታ ሶዶ ከተማ የጫኚና አዉራጅ ዋጋ ተመን ወጣ

በኢትዮጵያ ፌስቡክና ቴሌግራምን ጨምሮ የማኅበራዊ ሚዲያዎች አገልግሎት ተቋረጠየብሔራዊ ፈተና ጥያቄዎች በማኅበራዊ መገናኛ መድረኮች ላይ ሲዘዋወሩ ነበር ተብሎ ከተነገረ በኋላ በኢትዮጵያ ፌስቡክ...
08/11/2021

በኢትዮጵያ ፌስቡክና ቴሌግራምን ጨምሮ የማኅበራዊ ሚዲያዎች አገልግሎት ተቋረጠ

የብሔራዊ ፈተና ጥያቄዎች በማኅበራዊ መገናኛ መድረኮች ላይ ሲዘዋወሩ ነበር ተብሎ ከተነገረ በኋላ በኢትዮጵያ ፌስቡክ፣ ቴሌግራም፣ ዋትስአፕ እና ኢንስታግራም አገልግሎታቸው ተቋረጠ።

የኢንተርኔት ዕቀባዎችን የሚከታተለው ኔትብሎክስ ባወጣው መረጃ ከሰኞ ጥቅምት 29/2014 ዓ.ም ከሰዓት በኋላ አንስቶ በኢትዮጵያ የፌስቡክ እና የፌስቡክ ሜሴንጀር አገልግሎቶች መቋረጥ እንደገጠማቸው ማረጋገጡን ገልጿል።

ጨምሮም መረጃዎች እንዳመለከቱት፤ ከሁለቱ የማኅበራዊ ሚዲያ መገልገያዎች በተጨማሪ በአገሪቱ የኢንተርኔት አገልግሎት ሰጪው ኢትዮቴሌኮም ሰርቨር ላይ የዋትስአፕ እና የቴሌግራም የመልዕክት መለዋወጫ መድረኮች ተቋርጠዋል ብሏል።

ቢቢሲ በአዲስ አበባ ካሉ የማኅበራዊ መገናኛ መድረክ ተጠቃሚዎች ለማጣራት እንደሞከረው የተጠቀሱትን የማኅበራዊ መገናኛ መድረኮችን በቀጥታ መጠቀም እንደማይቻልና ቪፒኤን የተባለውን መንገድ እየተከተሉ መሆናቸውን ገልጸዋል።

ከዚህ በፊት የሁለተኛ ደረጃ አገር አቀፍ ፈተናዎች በሚሰጡበት ጊዜ ኩረጃንና ሐሰተኛ የመልስ ልውውጥን ለመከላከል በሚል የማኅበራዊ ሚዲያ አገልግሎቶች ተዘግተው የነበሩባቸው አጋጣሚዎች አሉ።

ሰኞ ዕለት የአገር አቀፍ ብሔራዊ ፈተና መጀመርን ተከትሎ አንዳንድ የመንግሥት ተቃዋሚዎች የፈተናው የጥያቄ ወረቀት ቅጂዎች ናቸው ያሏቸውን ፎቶዎች እንዲሁም የመልስ ዝርዝሮችን በማኅበራዊ ሚዲያዎች ላይ ሲያሰራጩ ነበር።

ነገር ግን የአገሪቱ የትምህርት ሚኒስቴር እየተሰጠ ካለው ፈተና ላይ ምንም አይነት ጥያቄም ሆነ መልስ እንዳልወጣና በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ እየተሰራጩ ያሉት ሐሰተኛ መሆናቸውን ገልጿል።

ቢቢሲ

የሸካ ዞን መቀመጫ ቴፒ እንዲሆን ተወሰነ።የሸካ ዞን ም/ቤት ባካሄደው አስቸኳይ ጉባኤ የዞኑ ዋና መቀመጫ   እንዲሆን በሙሉ ድምፅ ወሰኔ አሳልፏል።ምክር ቤቱ ቅዳሜ ባካሄደው 9ኛ የሥራ ዘመን ...
08/11/2021

የሸካ ዞን መቀመጫ ቴፒ እንዲሆን ተወሰነ።

የሸካ ዞን ም/ቤት ባካሄደው አስቸኳይ ጉባኤ የዞኑ ዋና መቀመጫ እንዲሆን በሙሉ ድምፅ ወሰኔ አሳልፏል።

ምክር ቤቱ ቅዳሜ ባካሄደው 9ኛ የሥራ ዘመን 4ኛ ዙር 1ኛ አስቸኳይ ጉባኤ የአሠራር ቅልጥፍናና የአገልግሎት አሰጣጥን ለማሻሻል የዞኑን ዋና ከተማ ከነበረበት ማሻ ከተማ ወደ ቴፒ ከተማ ለማዛወር የቀረበውን የውሣኔ አጀንዳ በመወያየት የዞኑ ዋና ከተማ ቴፒ እንዲሆን በሙሉ ድምፅ ወስኗል።

ውሳኔው በተሻሻለው የደ/ብ/ብ/ህ/ክልል መንግስት ህገ መንግስት አንቀፅ 81 ንኡስ አንቀፅ 2 ላይ የዞን ምክር ቤቶች በዞኑ ውስጥ የበላይ የፖለቲካ ስልጣን ባለቤቶች ናቸው ተብሎ በተገለፀው መሠረት በጉዳዩ ላይ በመወያየት ካለው ህዝባዊ ጠቀሜታ እና ፋይዳ አንጻር የዞኑ ማዕከል አሁን ካለበት ማሻ ከተማ ወደ ቴፒ ከተማ እንዲዛወር በሙሉ ድምፅ ውሳኔ መተላለፉ ተገልጿል።

መረጃው የደረሰን ከሸካ ዞን ኮሚኒኬሽን ነው።

ዛሬ ሁለት የህወሓት ኢላማዎች በአየር ሃይል ተደብድበዋል*****************      በዛሬው እለት በራያ አካባቢ አረዳ ባታ የሚገኘው የህወሓት ሠራዊት ማሠልጠኛ  የሆነው ቦታ በኢፌዲሪ...
08/11/2021

ዛሬ ሁለት የህወሓት ኢላማዎች በአየር ሃይል ተደብድበዋል
*****************

በዛሬው እለት በራያ አካባቢ አረዳ ባታ የሚገኘው የህወሓት ሠራዊት ማሠልጠኛ የሆነው ቦታ በኢፌዲሪ አየር ሃይል ተደብድቧል።

ከመንግስት ኮምንኬሽን አገልግሎት በወጣው መረጃ መሰረት በአሁኑ ወቅት የህወሓት በርካታ ታጣቂዎች በዚህ ቦታ እየሰለጠኑበት የሚገኝ ነው።

በተመሳሳይ በሠሜን ወሎና አፋር አዋሳኝ ኪሊዋ ወይም ሃጂሜዳ የሚገኝ የስልጠና እና የሎጅስቲክስ ማከማቻ እንዲሁም የተጠባባቂ ሃይል በአየር መደንደቡን መንግስት ኮምንኬሽን አገልግሎት አስታውቋል ።

የአፍሪካ ህብረት የምስራቅ አፍሪካ ልዩ መልዕክተኛ የሆኑት የቀድሞ የናይጀሪያው ፕሬዚዳንት ኦሊሰንጎ ኦባሳንጆ ከዶ/ር ደብረጽዮን ገ/ሚካኤል ጋር መቀሌ ውስጥ ተገናኝተው ተወያዩ
07/11/2021

የአፍሪካ ህብረት የምስራቅ አፍሪካ ልዩ መልዕክተኛ የሆኑት የቀድሞ የናይጀሪያው ፕሬዚዳንት ኦሊሰንጎ ኦባሳንጆ ከዶ/ር ደብረጽዮን ገ/ሚካኤል ጋር መቀሌ ውስጥ ተገናኝተው ተወያዩ

07/11/2021

የታሪኩ ጋንኪሲ /ዲሽታ ጊና/ ሙሉ ንግግር

ኢትዮጲያዊያን እንዴት ናቹ
እኔ አልዘፍንም ልዘፍን አይደለም የመጣሁት
በደስታውም በሀዘኑም መዝፈን ብቻ ነው እንዴ
የሚዘፈን እና የማይዘፈንበትን ቀን ልወቃ እኔ እራሴ
የቱጋ ቆሜ ልዝፈን የቱጋ ቆሜ ልዘምር የቱ ጋር ቆሜ ልናገር
እንደዚህ ተጣቧል ሰፈሩ እኔ የምዘፍነውም የለም የምናገረውም የለም
በዘፈኑም ካልተማርን በመዝሙሩም ካልተማርን
የሚዘፈን ነገር የለም አሁን የሚዘመርም ነገር የለም አሁን

በቤተክርስቲያን በል በቄሶች በፕሮተስታንት ፓስተሮች በሀይማኖት አባቶች ካልተማርን
በሙስሊሞች በሼዎች በሚያስተምሩን ካልተማር
ዘፈኑም አያስተምረንም

ምን አለ ብዬ ነው የምዘምረው
ሁሌ ጥቁር መልበስ አያምርብንም
ሁሌ ጥቁር መልበስ አያምርብንም ይበቃል ጥቁር መልበስ
ይበቃል ጆሯችን ደማ
ይበቃል

ማን መጥቶ ነው የሚናገረን
ማነው እየሄደ እየሞተ ያለው
ለምንድን ነው ለመሞት ብቻ ሲሆን ወደ ፊት የምንለው

አሁን ወጣቶች ይቁሙ አይሂዱ ሽማግሌዎች ይሂዱ
ድንጋይ ያንሱ እና ሳር ይበጥሱ አናታቸው ላይ ይዘው በሽምግልና ይሻላል
አፈ ሙዙ ይበቃል መፍትሄ የለውም

ምነው እኔም ተዋግቻለው ከወንድሜ ጋር ነው ሲባል ጎንበስ ብዬ ብቻዬን ሄድኩ ተውኩኝ
ደም አላስተማረንም ጉልበት አላስተማረንም
የኢትዮጲያ ከዳር እስከ ዳር የሁሉም ደሙ ትኩስ ነው

ቱርክ በኢትዮጵያ ጦርነት ተፋላሚ አካላት መካከል አስቸኳይ የተኩስ አቁም እንዲደረግ ጠየቀች ረጀብ ጠይብ ኤርዶጋን የሚመሯት ቱርክ፣ በኢትዮጵያ ጦርነት ተፋላሚ አካላት በአስቸኳይ የተኩስ አቁም...
06/11/2021

ቱርክ በኢትዮጵያ ጦርነት ተፋላሚ አካላት መካከል አስቸኳይ የተኩስ አቁም እንዲደረግ ጠየቀች

ረጀብ ጠይብ ኤርዶጋን የሚመሯት ቱርክ፣ በኢትዮጵያ ጦርነት ተፋላሚ አካላት በአስቸኳይ የተኩስ አቁም እንዲደረግ ጠይቃለች፡፡

አገሪቱ ተባብሶ የቀጠለውን ውጊያ እየተከታተለች መሆኑን ያመለከተው የአገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ በኢትዮጵያ ሰላም እንዲሰፍን እና ተፋላሚ አካላት ለንግግር እንዲቀመጡ ሁሉንም ድጋፍ ለማድረግ ቱርክ ዝግጁነት እንዳላት አሳውቋል፡፡

የአገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአገራት ታሪካዊ እና ባሕላዊ ትስስር ተጠብቆ መሄድ የሁልጊዜም የቱርክ መሻት መሆኑን የገለጸ ሲሆን፣ አገሪቱ በኢትዮጵያ ውጊያው ከጀመረ አንስቶ የምታደርገውን ድጋፍ መቀጠሏንም አስታውሷል፡፡

ፕሬዝዳንቱ ኤርዶጋን ባለፈው ዓመት ነሐሴ ወር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ወደ ቱርክ ጉብኝት ባደረጉበት ወቅት ኢትዮጵያ እያለፈችበት ያለውን ሒደት ‹‹ስሱ›› መሆኑን እንዲሁም ስትራቴጂካዊ አቀማመጥ እና ጠቀሜታ ጠቅሰው፣ ለአገሪቱ ሰላም፣ ጸጥታ እና አንድነት ትኩረት እንደሚሰጡ አመልክተው ነበር፡፡

በሌላ በኩል ቱርክ በቅርቡ ሰው አልባ አውሮፕላኖች ወይም ድሮኖችን ለኢትዮጵያ ሳትሸጥ እንዳልቀረች ሲነገርባት ነበር፡፡

የፀጥታው ምክር ቤት በሰሜን ኢትዮጵያ የሚካሄደው ጦርነት እንዲቆም ጥሪ አቀረበአርብ ምሽት ከተካሄደው የምክር ቤቱ ስብሰባ በኋላ በአስራ አምስቱም አባላቱ ተቀባይነት አግኝቶ በወጣው መግለጫ ላ...
06/11/2021

የፀጥታው ምክር ቤት በሰሜን ኢትዮጵያ የሚካሄደው ጦርነት እንዲቆም ጥሪ አቀረበ

አርብ ምሽት ከተካሄደው የምክር ቤቱ ስብሰባ በኋላ በአስራ አምስቱም አባላቱ ተቀባይነት አግኝቶ በወጣው መግለጫ ላይ ሁሉም በግጭቱ ተሳታፊ የሆኑ ወገኖች ጦርነቱን በማቆም "ዘላቂ ሰላም የሚያመጣ የተኩስ አቁም ለማድረግ" ውይይት እንዲጀምሩ ጥሪ አቀርቧል።

መግለጫው አክሎም ለተፈጠረው ቀውስ መፍትሔ ለማግኘት እንዲቻል እና ሰላምና መረጋጋት ለማስፈን ሁሉን አቀፍ ብሔራዊ ውይይት ለማካሄድ አመቺ ሁኔታ እንዲፈጠር ጠይቋል።

የምክር ቤቱ አባላት ችግሩን ለመፍታት የአፍሪካ ሕብረትን በመሰሉ አካባቢያዊ ድርጅቶች በኩል የሚደረገውን ጥረት እንደሚደግፉና የሕብረቱ ልዩ መልዕክተኛ ኦሉሴጉን ኦባሳንጆ ተኩስ እንዲቆምና ጦርነቱ ሰለማዊ መቋጫ እንዲያገኝ የሚያደርጉትን ጥረት እንደሚደግፍ ገልጿል።

ጨምሮም ሁሉም ወገኖች "ከአደገኛ ጥላቻ ከሚያስፋፉ፣ ግጭትንና መከፋፈልን ከሚያነሳሱ ንግግሮች" እንዲቆጠቡ አሳስቧል።

በሆሳዕና ከተማ አካል ጉዳተኛ መስለው ህብረተሰቡን ሲያጭበረበሩ የነበሩ 2 ግለሰቦች በቁጥጥር ሥር ዋሉ ======== #==========በትላንትናው ዕለት ማለትም ጥቅምት 24/2014 በሀዲያ ...
05/11/2021

በሆሳዕና ከተማ አካል ጉዳተኛ መስለው ህብረተሰቡን ሲያጭበረበሩ የነበሩ 2 ግለሰቦች በቁጥጥር ሥር ዋሉ
======== #==========

በትላንትናው ዕለት ማለትም ጥቅምት 24/2014 በሀዲያ ዞን ሆሳዕና ከተማ አካል ጉዳተኛ መስለው ህብረተሰቡን ሲያጭበረበሩ የነበሩ 2 ግለሰቦችን በቁጥጥር ሥር ማዋሉን የዞኑ ፖሊስ መምሪያ አስታውቋል።

በቁጥጥር ሥር እንደዋሉ የተነገረው 2 ግለሰቦች ፍጹም ጤነኛ ሆነው ሳሉ አካላቸው ላይ ጉዳት እንደደረሰባቸውና ተንቀሳቅሰው መስራት እንደማይችሉ በማስመሰል ህብረተሰቡን የማጭበርበር ወንጀል ሲፈጽሙ እንደተገኙ ነው ፖሊስ የገለፀው።

ግለሰቦቹ ይህን ተግባር ለመፈጸም ጎማ ከጀርባው እስከ እግር ታፋቸው በማሰር ሲንቀሳቀሱ እንደነበርና ህብረተሰቡ ለፖሊስ በሰጠው ጥቆማና ፖሊስ ባካሄደው ክትትል መሰረት በቁጥጥር ሥር መዋላቸው ተገልጿል።

ፖሊስ ግለሰቦቹን በቁጥጥር ሥር ካዋለ በኋላ በጤንነታቸው ላይ ባካሄደው ምርመራ መንቀሳቀስ እንደሚችሉ ማረጋገጡን የሀዲያ ዞን ፖሊስ ማህበረሰብ ወንጀል መከላከል ዲቪዥን ኃላፊ ኮማንደር ሳህሉ ኃይሌ ተናግረዋል።

በመቀጠልም ፖሊስ የግለሰቦቹን ማንነት እንዲሁም ፍላጎታቸው የገንዘብ መሆኑን አልያም ደግሞ ከጥፋት ሃይሎች ጋር ቁርኝት ያላቸው መሆኑን ለማጣራት ምርመራ እያደረገ እንደሚገኝ ኮማንደሩ ጠቁመዋል።

እንደ ኮማንደር ሳህሉ ገለጻ ፖሊስ ይህን ፍንጭ በመጠቀም በዞኑ የተለያዩ አካባቢዎች በአካል ጉዳተኝነትና በሌላም ሽፋን የሚንቀሳቀሱ ግለሰቦችን በቁጥጥር ሥር ለማዋል ልየታ እያደረገ ነው።

ህብረተሰቡ በሚያደርጋቸው ማንኛውም እንቅስቃሴ በአካል ጉዳተኝነት እና በሌላም ሽፋን ወንጀል የሚፈጽም አካላት በመኖራቸው ተገቢውን ጥንቃቄ እንዲያደርጉ አሳስበዋል።

የ12ኛ ክፍል አጠቃላይ የትምህርት ማጠናቀቂያ ፈተና ከሰኞ ጥቅምት 29፣ 2014 ጀምሮ እንደሚሰጥ የሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ አስታወቀ፡፡የ2013 የ12ኛ ክፍል ማጠናቀ...
05/11/2021

የ12ኛ ክፍል አጠቃላይ የትምህርት ማጠናቀቂያ ፈተና ከሰኞ ጥቅምት 29፣ 2014 ጀምሮ እንደሚሰጥ የሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ አስታወቀ፡፡

የ2013 የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና ከጥቅምት 29 እስከ ህዳር 2/2014 ባሉት አራት ተከታታይ ቀናት ይሰጣል ብሏል፡፡
ተፈታኞች ፈተናው ቀደም ብሎ በተቀመጠለት የጊዜ ገደብ የሚሰራ መሆኑን አውቀው በተረጋጋ ሥነ-ልቦና ቅድመ ዝግጅት እንዲያደርጉ ኤጀንሲው አሳስቧል፡፡

የሱዳኑ ወታደራዊ መሪ አብዱልፈታህ አል ቡርሃን የጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሐምዶክን ካቢኔ ወደ ኃላፊነቱ ለመመለስ መስማማታቸው ተሰማ፡፡አልቡርሃን ሲቪሉን አስተዳደር ወደ ስፍራው ለመመለስ የተ...
05/11/2021

የሱዳኑ ወታደራዊ መሪ አብዱልፈታህ አል ቡርሃን የጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሐምዶክን ካቢኔ ወደ ኃላፊነቱ ለመመለስ መስማማታቸው ተሰማ፡፡

አልቡርሃን ሲቪሉን አስተዳደር ወደ ስፍራው ለመመለስ የተስማሙት ከአሜሪካው የሱዳን ልዩ ልዑክ ቮልከር ፔርትዝ ጋር ከተነጋገሩ በኋላ እንደሆነ ቢቢሲ ፅፏል፡፡

የተባበሩት መንግሥታት ተወካይም በንግግሩ ተካፋይ ነበሩ ተብሏል፡፡

የሱዳን የጦር አለቆች ከወር በፊት የጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሐምዶክን ካቢኔ ከሀላፊነት ማስወገዳቸው ይታወቃል፡፡

አገሪቱን ወደ ሲቪል አስተዳደር የመመለሱን ተግባር ሲያቀላጥፍ የነበረው ሉዓላዊ የሽግግር ምክር ቤትም በትነውታል፡፡

ምክር ቤቱ የተሰየመው ከጦር አለቆች እና ሲቪል ሹሞች ተውጣጥቶ ነበር፡፡

ሐምዶክ ወደ ኃላፊነታቸው ይመለሳሉ ቢባልም አሁንም በቁም እስር ላይ ናቸው ተብሏል፡፡

አራት ሚኒስትሮቻቸው ግን ከእስር ተፈተዋል ተብሏል፡፡

 #ማስታወቂያ!! የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ከዚህ በታች በተመለከቱ ክፍት የስራ መደብ አመልካች መምህራንን አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል። የቅጥር ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ረዕቡ ጥቅምት ...
05/11/2021

#ማስታወቂያ!!

የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ከዚህ በታች በተመለከቱ ክፍት የስራ መደብ አመልካች መምህራንን አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል።

የቅጥር ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ረዕቡ ጥቅምት 24/2014 ዓ.ም በወጣው ዕትም የታወጀ ሲሆን፤ ከታች አያይዘነዋል👇

#ማሳሰቢያ፦ የምዝገባ ጊዜ ከጥቅምት 29/2014 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት እንደሚሆን የዩኒቨርሲቲው ሰው ሀብት አስተዳደር አሳውቋል።

በደቡብ ክልል መሳሪያ የታጠቀ ግለሰብ በአምስት ቀናት ውስጥ እንዲያስመዘግብ ጥሪ ቀረበየደቡብ ክልል የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ መግለጫ ሰጥቷል። የደቡብ ...
05/11/2021

በደቡብ ክልል መሳሪያ የታጠቀ ግለሰብ በአምስት ቀናት ውስጥ እንዲያስመዘግብ ጥሪ ቀረበ

የደቡብ ክልል የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ መግለጫ ሰጥቷል።

የደቡብ ክልል የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ሃላፊ ወይዘሮ ሰናይት ሰለሞን ፥ በወቅታዊ ጉዳይ ላይ የክልሉ ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች ትናንት ያካሔዱትን ውይይት መድረክ በማስመልከት ለመገናኛ ብዙሃን በሰጡት መግለጫ በሀገራችን የተቃጣውን ወረራ ለመመከት የክልሉ መንግስት ዘርፈ ብዙ ተግባራት ሲያከናውን መቆየቱን ተናግረዋል።

አሸባሪው ቡድን እያደረሰ ያለውን ጉዳት በመደበኛው ህግ ማስከበር ባለመቻሉ በመላው ሀገሪቱ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ታውጆ ወደ ተግባር መገባቱን የገለጹት ሃላፊዋ፥ በክልሉ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን አተገባበር ውጤታማ ለማድረግ በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ የአመራሩ ሚና ምን መሆን እንዳለበት በስፋት መወያየት መቻሉን ጠቁመዋል።

አመራሩ እራሱን የህልውና ዘመቻው አካል በማድረግ መላውን ህዝብ በማስተባበር የተቃጣብንን ወረራ መመከት እንደሚገባም ከስምምነት ላይ መደረሱን ወይዘሮ ሰናይት በመግለጫቸው አስረድተዋል።

ህዝባዊ ማዕበል በመፍጠር ህብረተሰቡ የመከላከያው እና የልዩ ሀይሉ ደጀን እንዲሆን መስራት እንደሚገባም ጠቁመዋል።

የህልውና ዘመቻውን አመራሩ በብቃት መምራት እንዲችል ዝርዝር ውይይት የተካሔደ ሲሆን ፥ ህብረተሰቡ አካባቢውን በንቃት መጠበቅ፣ የሰርጎ ገቦችን እንቅስቃሴ መከታተል እንዲችል ማደራጀት እና መምራት ይገባልም ሲሉ በመግለጫቸው አብራርተዋል።

እንደ ሀላፊዋ ገለጻ አመራሩ በትኩረት ከተወያየባቸው ነጥቦች ውስጥ የክልሉን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አፈጻጸም አተገባበር በብቃት መምራት ሲሆን ለዚህም የክልሉ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እዝ በስፋት የተወያየ ሲሆን ልዩ ልዩ ውሳኔዎችን አስተላልፏል።

በዚህም መሰረት ማንኛውም የጦር መሳሪያ የታጠቀ አካል ከዛሬ ከጥቅምት 26 ቀን ጀምሮ እስከ ጥቅምት 30 ቀን 2014 ዓ.ም ባሉት ተከታታይ ቀናት በአካባቢው በሚገኙ የፖሊስ ጣቢያዎች ቀርቦ ማስመዝገብ ይኖርበታል ብለዋል።

እንዲሁም ማንኛውም መታወቂያ የሚሰጥ አካል አዲስ መታወቂያ መስጠት አልያም የመታወቂያ እድሳት ማካሔድ ክልክል መሆኑን ጠቁመዋል።

አስቸጋሪ ሁኔታ ቢፈጠር እና መታወቂያ ማግኘት ግዴታ ሆኖ ከተገኘ ግን የክልሉ የአስቸኳይ ጊዜ መምሪያ እዝ አውቆት ውሳኔ ሊሰጥበት እንደሚችልም አብራርተዋል።

ወይዘሮ ሰናይት አክለውም በሀገራችን የተቃጣውን ወረራ እጅ ለእጅ ተያይዘን መመከት ጊዜ የሚሰጠው ተግባር አለመሆኑን አስረድተዋል።

ጄፍሪ ፌልትማን ከሶስት ከፍተኛ የኢትዮጵያ መንግስት ባለስልጣናት ጋር ተወያዩየአሜሪካ ፕሬዝዳንት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ጄፍሪ ፌልትማን በትላንትናው ዕለት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደ...
05/11/2021

ጄፍሪ ፌልትማን ከሶስት ከፍተኛ የኢትዮጵያ መንግስት ባለስልጣናት ጋር ተወያዩ

የአሜሪካ ፕሬዝዳንት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ጄፍሪ ፌልትማን በትላንትናው ዕለት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንንን ጨምሮ ከሶስት ከፍተኛ የኢትዮጵያ መንግስት ባለስልጣናት ጋር መወያየታቸውን የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ቃል አቃባይ ገለጹ። ልዩ መልዕክተኛው በዛሬው ዕለትም ከሌሎች የኢትዮጵያ ባለስልጣናትን አግኝተው እንደሚነጋገሩ ገልጸዋል።

ከአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ልዩ መልዕከተኛ ጋር ትላንት ተገናኝተው ከተወያዩ የኢትዮጵያ ባለስልጣናት መካከል፤ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ደመቀ መኮንን አንዱ እንደሆኑ ኔድ ፕራይስ ተናግረዋል። ፌልትማን ባለፈው ነሐሴ ወር ወደ አዲስ አበባ በመጡበት ወቅት ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ጋር ተገናኝተው መነጋገራቸው ይታወሳል።

አሜሪካዊው ዲፕሎማት፤ ከአቶ ደመቀ በተጨማሪ ከመከላከያ ሚኒስትሩ ዶ/ር አብርሃም በላይ እና ከገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሺዴ ጋር ተገናኝተው መወያየታቸውን የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ቃል አቃባይ ለጋዜጠኞች ገልጸዋል።

ተጨማሪ ለማንበብ ይህን ሊንክ ይጫኑ፦ https://ethiopiainsider.com/2021/4823/

የዩናይትድ ስቴትስና የኢትዮጵያ ግንኙነት መስቀለኛ መንገድ ላይ ነው - የአሜሪካ ልዩ ልዑክ ፌልትማንበሰሜን ኢትዮጵያ እየተካሄደ ባለው ጦርነት ምክንያት ለረጅም ግዜ የኖረው የኢትዮጵያ እና የ...
05/11/2021

የዩናይትድ ስቴትስና የኢትዮጵያ ግንኙነት መስቀለኛ መንገድ ላይ ነው - የአሜሪካ ልዩ ልዑክ ፌልትማን

በሰሜን ኢትዮጵያ እየተካሄደ ባለው ጦርነት ምክንያት ለረጅም ግዜ የኖረው የኢትዮጵያ እና የዩናይትድ ስቴትስ ግንኙነት መስቀለኛ መንገድ ላይ መድረሱን የዩናይትድ ስቴትስ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ጄፈሪ ፌልትማን አስታውቀዋል። ፌልትማን ይህን ያሉት ዛሬ በዩናይትድ ስቴትስ የሰላም ተቋም ተገኝተው በኢትዮጵያ ወቅታዊ ጉዳይ ላይ ንግግር ባደረጉበት ወቅት ሲሆን ጦርነት በሀገሪቱ እየተስፋፋ ባለበት ወቅቱ የሁለቱ ሀገራት ግኙነት ፀንቶ ሊቆይ እንደማይችል ተናግረዋል።

ፌልትማን ከአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር ጋር ተወያዩየአሜሪካ መንግሥት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ አምባሳደር ጄፈሪ ፌልትማን ከአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ ጋር ተወ...
04/11/2021

ፌልትማን ከአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር ጋር ተወያዩ

የአሜሪካ መንግሥት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ አምባሳደር ጄፈሪ ፌልትማን ከአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ ጋር ተወያዩ።

ሙሳ ፋኪ ከአምባሳደሩ ጋር በወቅታዊ የኢትዮጵያ እና ሱዳን ጉዳዮች ላይ መወያየታቸውን በትዊተር ገጻቸው ላይ አስታውቀዋል።

ኮሚሽነሩ ከጄፈሪ ፌልትማን ጋር ከብሔራዊ እና አህጉራዊ አካላታት ጋር በመሆን ውይይት እና ፖለቲካዊ መፍትሔ ለማምጣት ልናደርግ የምንችለውን ጥረት በተመለከተ ተነጋግረናል ብለዋል።

ዛሬ እኩለ ቀን አዲስ አበባ የገቡት ፌልትማን ወደ ኢትዮጵያ የመጡት እየተባባሰ ለመጣው ጦርነት መላ ለመሻት እንደሆነ በስፋት ተዘግቧል።

የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት እንዳለው የጦርነቱ መጠነ ሰፊነት አሁን አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል፡፡

ደሴና ኮምቦልቻን መቆጣጠራቸው የተነገረላቸው የትግራይ ኃይሎች ትናንት ከሚሴ ከተማን መቆጣጠራቸውን ይፋ አድርገዋል።

መንግሥት በዚህ ረገድ ያለው ነገር የለም። ከሚሴ ከዋና ከተማዋ አዲስ አበባ በሰሜን አቅጣጫ 330 ኪሎ ሜትር ላይ የምትገኝ ናት።

የአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ ተጨማሪ አዳዲስ የደንብ ልብሶችን ስራ ላይ ማዋሉን ዛሬ አሳውቋል። ነባሩን የደንብ ልብስ መጠቀም ማቆሙን ተቋሙ ገልጿል፡፡የአዲስ አበባ ፖሊስ  አሮጌውን የደንብ ልብ...
04/11/2021

የአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ ተጨማሪ አዳዲስ የደንብ ልብሶችን ስራ ላይ ማዋሉን ዛሬ አሳውቋል። ነባሩን የደንብ ልብስ መጠቀም ማቆሙን ተቋሙ ገልጿል፡፡

የአዲስ አበባ ፖሊስ አሮጌውን የደንብ ልብስ ለብሶ የተገኘ አመራር እና አባል ላይ ጠንከር ያለ የዲስፕሊን እርምጃ ይወሰድበታል ተብሏል።

ህብረተሰቡ እና ባለድርሻ አካላት አሮጌው የደንብ ልብስ ሙሉ በሙሉ በአዳዲሶቹ መቀየሩን ተገንዝበው አሮጌውን የደንብ ልብስ የለበሰ የፖሊስ አባል ሲያጋጥማቸው መረጃ በመስጠት እንዲተባበሩ ጥሪ ቀርቧል።

በተጨማሪም የአዲስ አበባ ፖሊስ ስራ ላይ ካዋላቸው አዳዲስ የደንብ አልባሳት ጋር ወይም ከሌሎች የፀጥታ አካላት የደንብ ልብስ ጋር ተመሳሳይ ወይም ተቀራራቢ ዩኒፎርም መጠቀም ክልክል መሆኑ በህግ የተደገገ ስለሆነ ከአ/አ ፖሊስ የደንብ ልብስ ጋር ተመሳሳይ ዩኒፎርም የሚጠቀሙ አካላት ማስተካከያ እንዲያደርጉ ተቋሙ መልዕክቱን አስተላልፏል።

ወርቅነህ ገበየሁ፤ ጦርነቱ እንዲቆምና በአስቸኳይ ተኩስ አቁም እንዲደረግ ጥሪ አቀረቡየኢጋድ ዋና ፀሃፊው መካረሩ ረግቦ ልዩነቶች ለሃገሪቱ ብሎም ለቀጠናው በሚበጅ መልኩ በውይይት እንዲፈቱ ጥሪ...
04/11/2021

ወርቅነህ ገበየሁ፤ ጦርነቱ እንዲቆምና በአስቸኳይ ተኩስ አቁም እንዲደረግ ጥሪ አቀረቡ

የኢጋድ ዋና ፀሃፊው መካረሩ ረግቦ ልዩነቶች ለሃገሪቱ ብሎም ለቀጠናው በሚበጅ መልኩ በውይይት እንዲፈቱ ጥሪ አቅርበዋል

ሰበር ዜናኬንያ ከኢትዮጵያ ጋር የሚያዋስናትን ድንበር ላልተወሰነ ጊዜ ዘጋች።ኬንያ ከኢትዮጵያ ጋር የሚያዋስናትን ድንበር ላልተወሰነ ጊዜ የዘጋች መሆኑን የዘገበው የኬንያው JK ቴሌቪዥን ነው።
03/11/2021

ሰበር ዜና

ኬንያ ከኢትዮጵያ ጋር የሚያዋስናትን ድንበር ላልተወሰነ ጊዜ ዘጋች።

ኬንያ ከኢትዮጵያ ጋር የሚያዋስናትን ድንበር ላልተወሰነ ጊዜ የዘጋች መሆኑን የዘገበው የኬንያው JK ቴሌቪዥን ነው።

የአፍሪካ ህብረት በኢትዮጵያ ያለው ወታደራዊ ግጭት መባባስ እንዳሳሰበው ገለፀየአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር ሙሳ ፋኪ ማሃማት በኢትዮጵያ ያለው ወታደራዊ ግጭት መባባስ እንዳሳሰባቸውና በ...
03/11/2021

የአፍሪካ ህብረት በኢትዮጵያ ያለው ወታደራዊ ግጭት መባባስ እንዳሳሰበው ገለፀ

የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር ሙሳ ፋኪ ማሃማት በኢትዮጵያ ያለው ወታደራዊ ግጭት መባባስ እንዳሳሰባቸውና በቅርበትም እየተከታተሉት እንደሆነ አስታውቀዋል።

ህብረቱ በዛሬው ዕለት በድረ-ገፁ ባወጣው መግለጫ ሊቀ መንበሩ ጦርነቱ በተቀሰቀሰበት ሰሞናት ያወጡትን መግለጫም በማስታወስ የጦርነቱ ተሳታፊ ሁሉም ወገኖች የኢትዮጵያን ግዛት አንድነት፣ ብሄራዊ ሉዓላዊነት እንዲጠብቁ በድጋሚ አሳስበዋል።

በአገር ጉዳይ ላይ ሰላማዊ መፍትሄ ለመፈለግ ሁሉም ወገኖች ወደ ውይይት እንዲገቡም አሳስበዋል።

በዚህ ረገድ ሊቀመንበሩ ጦርነቱ በአስቸኳይ እንዲቆም፣ የዜጎች ህይወትና ንብረት ሙሉ በሙሉ እንዲከበር፣ እንዲሁም የመንግስት መሠረተ ልማት እንዲከበር ጥሪ አቅርበዋል።

ሊቀመንበሩ አክለውም የጦርነቱ ተሳታፊ ወገኖች ደጋፊዎቻቸው በማንኛውም ማህበረሰብ ላይ የበቀል እርምጃ እንዳይወስዱ እንዲሁም ከጥላቻ ትርክቶች፣ ክፍፍልንና ግጭቶችን ከሚያበረታቱ ሁኔታዎች እንዲቆጠቡ እንዲያደርጉም አሳስበዋል።

የጦርነቱ ተዋናዮች ዓለም አቀፍ ሰብዓዊ መብት ህግጋትን በማክበር በተለይም የሲቪሎችን ጥበቃ እና በችግር ላይ ያሉ ህዝቦች ሰብዓዊ እርዳታ እንዲደርሳቸው በማድረግ ዓለም አቀፍ ግዴታቸውን መወጣትም አለባቸው በማለት መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

የአፍሪካ ህብረት ከጦርነቱ ተሳታፊ አካላት ጋር የጋራ ስምምነትን መሰረት ያደረገ የፖለቲካ ሂደትን ለመደገፍ ቁርጠኝነት እንዳለውም የድርጅታቸውን አቋም አሳውቀዋል።

ከዚህም በተጨማሪ ከህብረቱ አፍሪካ ቀንድ ከፍተኛ ተወካይ ከቀድሞው የናይጄሪያ ፕሬዝዳንት ኦሉሴጎን ኦባሳንጆ ጋር ውይይት እንዲጀመርም ሊቀመንበሩ ጥሪ አቅርበዋል።

አስገራሚ  ዜና………………ፌስቡክ የጠ/ሚር ዶ/ር ዐብይን አንድ 'ፓስት' ማጥፋቱን ቢቢሲ ዘግቧል።ታዋቂው የማህበራዊ ሚዲያ ፌስቡክ የአብይ አህመድን ፖስት ያነሳው ግጭት ቀስቃሽና ሲቪሊያኑን ህዝ...
03/11/2021

አስገራሚ ዜና
………………
ፌስቡክ የጠ/ሚር ዶ/ር ዐብይን አንድ 'ፓስት' ማጥፋቱን ቢቢሲ ዘግቧል።

ታዋቂው የማህበራዊ ሚዲያ ፌስቡክ የአብይ አህመድን ፖስት ያነሳው ግጭት ቀስቃሽና ሲቪሊያኑን ህዝብ ለጦርነት የሚቀሰቅስ በመሆኑ ነው ተብሏል።

በአሁን ወቅት በርካቶች የአብይ ፖስት መሰረዝ ብቻ ሳይሆን የትዊተርን ጨምሮ የፌስቡክ አካውንቱ እንዲዘጋ የማህበራዊ ሚዲያ ዘመቻ መደረግ አለበት እያሉ ይገኛል።

ከዚህ ቀደም ዶናልድ ትራምፕ ግጭት ቀስቃሽ ንግግር አድርጓል በሚል አካውንቱ መዘጋቱ ይታወቃል።

የአሜሪካ ኤንባሲ አሜሪካዊያን ወደ ኢትዮጵያ እንዳይመጡ፤ የመጡትም በአስቸኳይ ሀገሪቱን ለቀው ለመውጣት እንዲዘጋጁ አሳሰበ።  *************በኢትዮጵያ የጸጥታ ሁኔታ አሽቆልቁሏል ያለው ...
02/11/2021

የአሜሪካ ኤንባሲ አሜሪካዊያን ወደ ኢትዮጵያ እንዳይመጡ፤ የመጡትም በአስቸኳይ ሀገሪቱን ለቀው ለመውጣት እንዲዘጋጁ አሳሰበ።
*************
በኢትዮጵያ የጸጥታ ሁኔታ አሽቆልቁሏል ያለው በአዲስ አበባ የሚገኘው የአሜሪካ ኤንባሲ በአማራ፣ በአፋርና ትግራይ ክልሎች ግጭት በመባባሱ አዲስ አበባን ከሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል የሚያገናኙ መንገዶች ገደብ ተጥሎባቸዋል ብሏል።

የኤንባሲው ሠራተኞች ከአዲስ አበባ ከተማ ውጪ ከመጓዝ እንደተገደቡ በማስታወስ ወደ ኢትዮጵያ ለመጓዝ ያሰቡ የአሜሪካ ዜጎች አስቀድመው በሚገባ እንዲያጤኑ በማሳሰብ ቀድመው የገቡትም አገሪቱን ለቀው ለመውጣት እንዲዘጋጁ የጥንቃቄ መልዕክት አስተላልፏል።

ከዛሬ ጀምሮ በመላ አገሪቱ በታወጀው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የተከለከሉ ተግባራትና ግዴታዎች• ሁሉም ሰው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መምሪያ ዕዝ በአዋጁ መሰረት የሚያወጣቸውን መመሪያዎችና የሚሰጣቸው...
02/11/2021

ከዛሬ ጀምሮ በመላ አገሪቱ በታወጀው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የተከለከሉ ተግባራትና ግዴታዎች

• ሁሉም ሰው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መምሪያ ዕዝ በአዋጁ መሰረት የሚያወጣቸውን መመሪያዎችና የሚሰጣቸውን ትዕዛዞች የመቀበል ግዴታ አለበት

• የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መምሪያ ዕዙን እንቅስቃሴ እና የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ዓላማ የሚቃረን፣ የሚቃወም እና ለሽብር ቡድኖች ዓላማ መሳካት አስተዋፅዖ የሚያደርግ፣ የሽብር ቡድኖችን የሚያበረታታ፣ ሰላማዊ ዜጎችን የሚያሸብር ንግግር በማንኛውም መንገድ ማድረግ ወይም ማሰራጨት የተከለከለ ነው

• በየትኛውም መንገድ፣ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ለሽብር ቡድኖች የገንዘብ፣ የመረጃ፣ የቁስም ሆነ የሞራል ድጋፍ ማድረግ የተከለከለ ነው

• የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መምሪያ ዕዙ በተዋረድ ውክልና ከሰጣቸው አካላት ፈቃድ ውጭ ማንኛውንም የአደባባይ ስብሰባ ወይም ሰላማዊ ሰልፍ ማድረግ የተከለከለ ነው

• ከመከላከያ፣ ከፌዴራል ፖሊስ ወይም ሌሎች ፈቃድ ከሚሰጣቸው የፀጥታ አካላት ወይም ከነዚህ አካላት እውቅናና ፈቃድ ውጭ ማናቸውንም የጦር መሳሪያ ይዞ መንቀሳቀስ የተከለከለ ነው

• በከተሞች አካባቢ የነዋሪ መታወቂያ፣ የመንጃ ፈቃድ፣ የሰራተኛ መታወቂያ፣ ፓስፖርት ወይም ከነዚህ ተመጣጣኝ የሆነ መታወቂያ ሳይዙ መንቀሳቀስ የተከለከለ ነው

• ማንኛውም ወሳኝ በሆነ የአገልግሎት ዘርፍም ሆነ በምርት ሂደት ላይ የስራ ማስተጓጎል ወይም የኢኮኖሚ አሻጥር መፈፀም የተከለከለ ነው

• የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን አፈፃፀም ሰበብ በማድረግ የግል ጥቅም ለማግኘት ስልጣንን አላግባብ መጠቀም፣ ምክንያታዊ የሆነ ጥርጣሬ ሳይኖር ሆን ብሎ ዜጎችን ማሰር ወይም መሰል እርምጃ መውሰድ የተከለከለ ነው

ሰበር ዜና*******የአሜሪካው ፕረዚዳንት ጆ ባይደን ኢትዮጵያ ከአፍሪካ ዕድገትና ተጠቃሚነት ድንጋጌ አባልነት እንድትሰርዝ ውሳኔ አሳልፏል። ውሳኔው ኢትዮጵያ ያለ ቀረጥ ወደ አሜሪካ ምርቶቿን...
02/11/2021

ሰበር ዜና
*******
የአሜሪካው ፕረዚዳንት ጆ ባይደን ኢትዮጵያ ከአፍሪካ ዕድገትና ተጠቃሚነት ድንጋጌ አባልነት እንድትሰርዝ ውሳኔ አሳልፏል።

ውሳኔው ኢትዮጵያ ያለ ቀረጥ ወደ አሜሪካ ምርቶቿን የማስገባት መብት የሚነፍግ ሲሆን ይህም የአገሪቱን ኢንዱስትሪ በከፍተኛ ደረጃ የሚያናጋ እንደሚሆን ይጠበቃል። ለውሳኔው መነሻ ምክንያት የኢትዮጵያ መንግስት በትግራይ ክልል የፈጸመው የሰብዓዊ መብት ጥሰት መሆኑ ተነግሯል።

ማለዳ ሚዲያ

የሚኒስትሮች ምክር ቤት በመላ ሀገሪቱ  የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አወጀየመንግስት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዶክተር ለገሰ ቱሉና ፍትህ ሚኒስትሩ ዶክተር ጌዴዮን ጢሞቲዎስ በጋራ መግለጫ  እ...
02/11/2021

የሚኒስትሮች ምክር ቤት በመላ ሀገሪቱ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አወጀ

የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዶክተር ለገሰ ቱሉና ፍትህ ሚኒስትሩ ዶክተር ጌዴዮን ጢሞቲዎስ በጋራ መግለጫ እየሰጡ ነው።

የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችሎት በእነ አቶ ባሌሉበት እንዲመሰክሩ ቀጠሮ ተይዞላቸዉ የነበሩት የፌድራል አቃቤ ህግ ምስክሮች ቃል ሳይሰማ ቀረ።======================...
01/11/2021

የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችሎት በእነ አቶ
ባሌሉበት እንዲመሰክሩ ቀጠሮ ተይዞላቸዉ የነበሩት የፌድራል አቃቤ ህግ ምስክሮች ቃል ሳይሰማ ቀረ።
=======================
ጃዋር መሐመድ የክስ መዝገብ ተከሳሾች ላይ የዐቃቤ ሕግ ምስክሮችን ለመስማት የያዘው ቀጠሮ ተፈጻሚ ሳይሆን ቀርቷል።

ፍርድ ቤቱ የዐቃቤ ሕግ ምስክሮችን ሳይሰማ የቀረበው የተከሳሽ ጠበቆች ለፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት አቤቱታ ማቅረባቸውን ተከትሎ መሆኑ ነው የተነገረው።
ከተከሳሽ ጠበቆች መካከል አንዱ የሆኑት አቶ ከድር ቡሎ ነገሩኝ ብሎ ቢቢሲ እንደ ዘገበው ፣ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ጃዋር መሐመድን ጨምሮ አራት ተከሳሾች በሌሉበት የዐቃቤ ሕግ ምስክሮች ይሰሙ ሲል ያሰጠውን ውሳኔ በመቃወም ለፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት አቤቱታ አቅርበዋል።

ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ የቀረበው ይግባኝ መርምሮ ውሳኔ እስኪሰጥ ድረስ የዐቃቤ ሕግ ምስክሮች እንዳይሰሙ ማዘዙንም ጠበቃው ከድር ቡሎ ተናግረዋል።
የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤቱ በተከሳሾቹ ላይ የዐቃቤ ሕግ ምስክሮችን ከዛሬ ሰኞ ጥቅምት 22፣ 2014 ጀምሮ ለመስማት ቀጠሮ ይዞ ነበር። ጃዋር መሐመድ፣ በቀለ ገርባ፣ ሐምዛ አዳና እና ደጀኔ ጣፋ “ፍርድ ቤት የሚሰጠው ውሳኔ በአስፈጻሚው አካል እየተከበረ አይደለም። ሥራ አስፈጻሚው አካል ሕግ እስካላከበረ ድረስ ፍርድ ቤት አንገኝም” በማለታቸው አራቱ ተከሳሾች በሌሉበት ጉዳያቸው እንዲታይ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ውሳኔ አስተላልፎ እንደነበረ ይታወሳል።

የፌደራሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የተከሳሽ ጠበቆች አቤቱታን መርምሮ ውሳኔ ለመስጠት ለኅዳር 7፣ 2014 ቀጠሮ ሰጥቷል።

በዚህ የክስ መዝገብ ሥር የተካተቱት ተከሳሾች የፀረ ሸብር አዋጅ፣ የቴሌኮም አዋጅ፣ የጦር መሳሪያ አስተዳደር እና ቁጥጥር አዋጅን በመተላለፍ ክስ ተመስርቶባቸው በእስር ላይ ይገኛሉ።

KMN:-November 01/2021

ሰበር ዜና መንግሥት ከሕወሓት ጋር የንግግር ዕድል ሊኖር እንደሚችል ፍንጭ ሰጠየፌዴራል መንግስት ጦርነት ውስጥ ከሚገኘው ሕወሓት ጋር የንግግር ዕድል ሊኖር እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል።የጠቅላይ ...
01/11/2021

ሰበር ዜና

መንግሥት ከሕወሓት ጋር የንግግር ዕድል ሊኖር እንደሚችል ፍንጭ ሰጠ

የፌዴራል መንግስት ጦርነት ውስጥ ከሚገኘው ሕወሓት ጋር የንግግር ዕድል ሊኖር እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል።

የጠቅላይ ሚኒስትር ቃል አቀባይ ቢልለኔ ሥዩምን ጠቅሶ ኤንፒአር እንደዘገበው፣ መንግስት ከሕወሓት ጋር ለመነጋገር እድል ሊሰጥ ይችላል።

አንድ ዓመት ሊደፍን ሁለት ቀናት የቀሩት በፌዴራል መንግስት እና በሕወሃት ኃይሎች መካከል ያለው ጦርነት የሔወሃት ኃይሎች የአማራ ክልል ከተሞች የሆኑትን ደሴን እና ኮምቦልቻን ተቆጣጥረናል ማለታቸው መነገሩ ይታወሳል።

እነዚህ ሪፖርቶች መውጣታቸውን ተከትሎ መግለጫ የሰጡት ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድ ሕዝቡ የክት ጉዳዩን አቆይቶ ሕወሓትን ‹ለመመከት፣ ለመቀልበስና ለመቅበር ማናቸውንም መሳሪያ እና አቅም ይዞ በሕጋዊ አደረጃጀት መዝመት አለበት›› ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ‹‹የመረረውን ትግል ታግለን፣ ጣፋጩን ድል እናጣጥማለን›› ባሉበት መግለጫ፣ ‹‹ሕወሓት በአራት ግንባሮች ተኩስ ከፍቶ አገር የማፍረስ ተግባሩን ገፍቶበታል›› ያሉ ሲሆን፣ ‹‹ሰሞኑን ያለ የሌለ ኃይሉን ወደ ወሎ ግንባር አምጥቷል። አገር ለማጥፋት የመጣ መንጋ አገር ለማዳን የተነሣን ኃይል ይረብሸው ይሆናል፣ ሊያሸንፈው ግን አይችልም›› ሲሉም ገልፀው ነበር።

©amba digital - አምባ ዲጂታል

"በወሎ ግንባር በነበረው ውጊያ ኢትዮጵያውያን ያልሆኑ ኃይሎች ተሳትፈዋል"፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ  በወሎ ግንባር በነበረው ውጊያ ኢትዮጵያውያን ያልሆኑ ኃይሎች ከአሸባሪው ቡድን ጋር...
01/11/2021

"በወሎ ግንባር በነበረው ውጊያ ኢትዮጵያውያን ያልሆኑ ኃይሎች ተሳትፈዋል"፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ

በወሎ ግንባር በነበረው ውጊያ ኢትዮጵያውያን ያልሆኑ ኃይሎች ከአሸባሪው ቡድን ጋር መሳተፋቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አስታወቁ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለከፍተኛ የመንግሥት አመራሮች በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

በጦርነቱ ኢትዮጵያውያን ያልሆኑ እና የኢትዮጵያውያ ዝርያ የሌላቸው ነጮች እና ጥቁሮች ከአሸባሪው ቡድን ጋር ተሳትፈው መስዋትነት መክፈላቸውን ነው ጠቅላይ ሚኒስትሩ ያረጋገጡት።

የደሴ እና ኮምቦልቻ ተፈናቃዮች አዲስ አበባ እንዳይገቡ በመከልከላቸው ለከፍተኛ እንግልት ተዳርገዋል ተባለ ወደ አድስ አበባ እንዳይገባ ነጋደም ይሁን ተፈናቃይ ከደብረ ብርሃን ወዳ ያለ ሰው ሸ...
01/11/2021

የደሴ እና ኮምቦልቻ ተፈናቃዮች አዲስ አበባ እንዳይገቡ በመከልከላቸው ለከፍተኛ እንግልት ተዳርገዋል ተባለ

ወደ አድስ አበባ እንዳይገባ ነጋደም ይሁን ተፈናቃይ ከደብረ ብርሃን ወዳ ያለ ሰው ሸኖ ላይ ተግዷል!! የአዲስ አበባ – ደብረ ብርሃን መንገድ ከትላንት ጀምሮ ተዘግቷል፤ በአማራ ክልል የኢንተርኔት አገልግሎት ተቋርጧል፤ ደብረ ብረሀን የሚገኘው መኪና ተራ እየገቡ ያሉ ተጓዦች እንግልት እየደረሰብን ነው ሲሉ በውስጥ መስመር አሳውቀውኛል። ከደብረ ብረሀን አዲስ አበባ ለመጓዝ ደብረ ብረሀን አውቶብስ ተራ ያሉ ተጓዦች እንደነገሩኝ ከሆነ ብዙ መኪና መናህሪያ ውስጥ ቢኖርም ከመንግስት የስምሪት ትዕዛዝ እስኪደርሰን ማንም ተጓዥ መሳፈር እንደማይችል እና በጣም ብዙ ሰው እየተጉላላ እንደሆነ በምሬት በውስጥ መስመር ነግረውናል።

ከቅዳሜ ጀምሮ ሸኖ ላይ ወደ አድስ አበባ መግባት ተከልክሎ ወገኖቻችን ብዙ መከራና እንግልት እያስተናገዱ ነው።ከ1500 በላይ መኪና የአድስ አበባ ነዋሪዎች ካልሆናችሁ ወደ ከተማ አትገቡም በሚል ታግተው አድረው አሁን እየደበደቡ ወደ መጣችሁበት ተመለሱ እየተባሉ ነው!!

ያለ ምግብ እና መኝታ መንገድ ላይ ያደሩ እናቶች እና ህፃናት ላይ ይሄን አይነት ግፍ መንግስት ነኝ ከሚል ቡድን አስነዋሪ ተግባር ነው!!
እንግዲህ የወሎ ሰው በዚህ ሰዓት በህይወት ተርፈው ለተፈናቀሉት መድረስ ካልቻልክ አስቸጋሪ ነው።

መረጃ ቲቪ

Address


Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Wolaita Sodo Times posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Videos

Shortcuts

  • Address
  • Alerts
  • Videos
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share