Addis_መረጃ

  • Home
  • Addis_መረጃ

Addis_መረጃ ቀዳሚ የመረጃ ምንጭ

Congratulations
31/12/2021

Congratulations

ያናግሩን 👉 0921740274Telegram 👇
15/08/2021

ያናግሩን 👉 0921740274

Telegram 👇

ዜና እረፍት‼️ክብርት ዶ/ር አበበች ጎበና (እዳዬ) ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ፡፡አፍሪካዊቷ ማዘር ቴሬዛ በመባል የሚታወቁት ዶ/ር አበበች ጎበና ከአገር ባለውለታነት አልፈው ለሰው ልጆች ትልቅ ...
04/07/2021

ዜና እረፍት‼️

ክብርት ዶ/ር አበበች ጎበና (እዳዬ) ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ፡፡

አፍሪካዊቷ ማዘር ቴሬዛ በመባል የሚታወቁት ዶ/ር አበበች ጎበና ከአገር ባለውለታነት አልፈው ለሰው ልጆች ትልቅ ክብርን በመስጠት ወላጅ ለሌላቸው እናትም አባትም ሆነው ሰው ከወደቀበት ቀና እንዲል አድርገዋል።

ክቡር የሆነውን የሰውን ልጅ ከጎዳና እያነሱ አጥበው፣ አብልተው፣ አስተምረው በርካታ ልጆችን ለቁም ነገር ማብቃት የቻሉ ጀግና ሴት እንደነበሩ በርካቶች መስክረውላቸዋል።

ክብርት ዶ/ር አበበች ጎበና (እዳዬ) በጳውሎስ ሆስፒታል በጽኑ ሕሙማን ክፍል ሕክምና ሲደረግላቸው ቆይቶ ዛሬ ጠዋት ላይ ህይወታቸው አልፏል፡፡

____
Jᴏɪɴ ᴏᴜʀ ᴛᴇʟᴇɢʀᴀᴍ ᴄʜᴀɴɴᴇʟ:👇
ቴሌግራም: 👉 https://t.me/ADDIS_MEREJA

በአማራ ክልል የተፈፀመውን ጥቃት ለማስቆም ተጨማሪ የጸጥታ ኃይል መግባቱን የክልሉ መንግሥት አስታወቀ።ትናንትና ከፍተኛ ጉዳት የደረሰባትን አጣዬ ከተማን የጸጥታ ኃይሉ መቆጣጠሩንም የአማራ ክል...
18/04/2021

በአማራ ክልል የተፈፀመውን ጥቃት ለማስቆም ተጨማሪ የጸጥታ ኃይል መግባቱን የክልሉ መንግሥት አስታወቀ።ትናንትና ከፍተኛ ጉዳት የደረሰባትን አጣዬ ከተማን የጸጥታ ኃይሉ መቆጣጠሩንም የአማራ ክልል የሰላምና የሕዝብ ደኀንነት ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ ሲሳይ ዳምጤ አስታውቀዋል።

በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን በደረሰ ጥቃት ንጹሐን ተገድለዋል፣ አካል ጎድሏል፣ ሀብትና ንብረት ወድሟል።ዜጎች ቀያቸውን ለቀው ራሳቸውን ለማዳን ሸሽተዋል። አካባቢው ከአሁን በፊት የተከሰተው ችግር በመረጋጋት ላይ ባለበት ወቅት ነው ችግሩ በድጋሜ ነው የተነሳው።በአማራ ክልል ስለተፈጠረው የጸጥታ ችግር የክልሉ የሰላምና ሕዝብ ደኀንነት ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ ሲሳይ ዳምጤ ለአሚኮ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

በማብራሪያቸውም በሰሜን ሸዋ ዞንና በኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር አዋሳኝ አካባቢ መጠነ ሰፊ የሆነ ችግር ተፈጥሯል ብለዋል።በአካባቢው ከአሁን በፊት ሲከሰቱ የነበሩ ችግሮችን ከሕዝብ ጋር በመሆን ሲፈቱ እንደቆዬ ያመላከቱት ኃላፊው ችግሩ በድጋሜ ማገርሸቱን ነው የተናገሩት።

ትናንት በአጣዬና በአካባቢው የኦነግ ሸኔ ጽንፈኛ ቡድን ከፍተኛ ጉዳት ማድረሱንም አመላክተዋል። በደረሰው ጉዳትም ንጹሐን ሞተዋል፣ አካል ጎድሏል፣ የመንግሥትና የሕዝብ ሀብትና ንብረትም ወድሟል ነው ያሉት።በአጣዬ በማረሚያ ቤት የነበሩ ታራሚዎች ከእስር እንዲወጡ ተደርጓል።ከአጣዬ ባለፈ በካራቆሬ፣ በማጀቴ፣ በአንፆኪያ፣ በመኮይና በሸዋሮቢት ሕዝቡ በውጥረት ውስጥ ነው ያለው ብለዋል።

በሰሜን ሸዋ ዞን ያለው ችግር እየከፋ የመጣና ሕፃናት፣ እናቶችና አዛውንቶች ጭምር በግፍ የተገደሉበት መሆኑንም ተናግረዋል።የኦነግ ሸኔ ቡድን በሸዋሮቢት የሚገኙ ታራሚዎችን ለማስለቀቅ እንቅስቃሴ እያደረገ መሆኑን ያመላከቱት ኃላፊው በአካባቢው አሁንም የተኩስ ልውውጥ መኖሩን ነው የተናገሩት።የአማራ ልዩ ኃይል፣ የአካባቢው የጸጥታ መዋቅርና የፌዴራል የጸጥታ መዋቅር ችግሩን ለመፍታት ጥረት እያደረገ መሆኑንም አመላክተዋል።የአማራ ክልል የጸጥታ መዋቅር ከፌዴራል የጸጥታ መዋቅር ጋር በቅንጅት እየሠራ ሆኑንም ተናግረዋል። አካባቢውን ለማረጋጋት እና አጥፊውን ቡድን ለሕግ ለማቅረብ ተጨማሪ የጸጥታ ኃይል ወደ ስፍራው መግባቱንም ተናግረዋል።

የአካባቢውን ሚሊሻ በማደራጀት ከሌላው የጸጥታ ኃይል ጋር እንዲገባ እያደርግን ነውም ብለዋል። ከፍተኛ ጉዳት የደረሰባትን አጣዬ ከተማን የጸጥታ ኃይሉ መቆጣጠሩን አስታውቀዋል።በሸዋሮቢት ያለውን ችግር ለመቅረፍ የመከላከያ ሠራዊት ጥረት እያደረገ ነው ብለዋል።የኦነግ ሸኔ ጽንፈኛ ቡድን የአማራን ሕዝብና መንግሥት ወደ አልተፈለገ አቅጣጫ ለመውሰድ እየሠራ መሆኑንም አመላክተዋል።ችግሩን የፈጠሩ፣ ያደራጁና የመሩ ለሕግ መቅረብ አለባቸው፤ ጽንፈኛውን ቡድን ከሕዝብ እየነጠሉ ለሕግ ማቅረብ ይገባልም ብለዋል።

በሌላ በኩል በጭልጋ አካባቢም የታጠቁ ኃይሎች በመከላከያ ሠራዊትና በአማራ ልዩ ኃይል ላይ ጥቃት በመፈፀም ችግር መፍጠራቸውን የተናገሩት ኃላፊው የክልሉና የፌዴራል የፀጥታ መዋቅር ሰላምን ለማረጋገጥ እየሠራ መሆኑን አስታውቀዋል።የአማራ ክልል ሕዝብ የሚሰጡትን አጀንዳዎች በሰከነ መንገድ በማዬት ከመንግሥት ጎን በመቆም ችግሮችን በጋራ እንዲፈታም
ጥሪ አቅርበዋል።

____
Jᴏɪɴ ᴏᴜʀ ᴛᴇʟᴇɢʀᴀᴍ ᴄʜᴀɴɴᴇʟ:👇
ቴሌግራም: 👉 https://t.me/ADDIS_MEREJA

ቀዳሚ የመረጃ ምንጭ 🇪🇹 🇪🇹 . ⏬ምርት እና አገልግሎቶን ለማስተዋወቅ ከፈለጉ⏬ ⏬ ꜰᴏʀ ᴘᴀɪᴅ ᴘʀᴏᴍᴏᴛɪᴏɴ ⏬ ይጠቀሙ መረጃዎችን ለመላክ

🍁🍁🍁🍁🍁🍁🍁🍁🍁🍁🍁🍁Congratulations to Ami and Tsion For Canadian Student Visa Approval by Paradise  Consultancy.🍁🍁🍁🍁🍁🍁🍁🍁🍁🍁🍁🍁አሚ ...
26/02/2021

🍁🍁🍁🍁🍁🍁🍁🍁🍁🍁🍁🍁
Congratulations to Ami and Tsion For Canadian Student Visa Approval by Paradise Consultancy.
🍁🍁🍁🍁🍁🍁🍁🍁🍁🍁🍁🍁

አሚ እና ጺዮን ለካናዳ የተማሪ ቪዛ ይሁንታ በፔራዳይዝ ስም እንኳን ደስ አላችሁ ።

Telegram 👇
https://t.me/joinchat/RKTVopXWtp62vNiu

Paradise Travel Agency
Contact 👉 0921740274

🇨🇦🇨🇦🇨🇦🇨🇦 ይህን ያውቁ ኖሯል? 🇨🇦🇨🇦🇨🇦🇨🇦የካናዳ መንግስት በቀጣዮቹ ሶስት አመታት ለ አንድ ሚሊዮን ሰዎች መኖሪያ ፍቃድን ጨምሮ🇨🇦    በስራ🇨🇦    በትምህርት🇨🇦    በጉብኝትለመቀበ...
26/02/2021

🇨🇦🇨🇦🇨🇦🇨🇦 ይህን ያውቁ ኖሯል? 🇨🇦🇨🇦🇨🇦🇨🇦

የካናዳ መንግስት በቀጣዮቹ ሶስት አመታት ለ አንድ ሚሊዮን ሰዎች መኖሪያ ፍቃድን ጨምሮ

🇨🇦 በስራ

🇨🇦 በትምህርት

🇨🇦 በጉብኝት

ለመቀበል ኘሮግራም ተከፍቷል። በመሆኑም ይህን አገልግሎት መጠቀም የምትፈልጉ አመልካቾች ከዛሬ ጀምሮ ምዝገባ የጀመርን መሆኑን እየገለፅን ለመመዝገብ የሚያስፈልገውን ዝርዝር ከዚህ በታች ባለው ቻናል ያገኙታል።

ያናግሩን 👉
0921740274

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በመቀሌ ከከፍተኛ የጦር መኮንኖች ጋር ተወያዩ።ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ የሕግ ማስከበር ሂደቱን ከመሩ ከፍተኛ የጦር መኮንኖች ጋር መቀሌ ላይ ተወያይተዋል...
13/12/2020

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በመቀሌ ከከፍተኛ የጦር መኮንኖች ጋር ተወያዩ።

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ የሕግ ማስከበር ሂደቱን ከመሩ ከፍተኛ የጦር መኮንኖች ጋር መቀሌ ላይ ተወያይተዋል።ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ በአካባቢው ለሕዝቡ እየተደረገ ያለው ሠብዓዊ ድጋፍ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል።መቀሌ ላይ በተካሄደው ውይይት ጄኔራል አበባው ታደሰና ሌተናል ጄኔራል ባጫ ደበሌን ጨምሮ በርካታ ከፍተኛ የጦር መኮንኖች ተሳትፈዋል።ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ድሉ የመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ መሆኑን በውይይቱ ላይ ተናግረዋል።

በጁንታው ላይ የተገኘው ድል የሚያኩራራ ሳይሆን 'የምንማርበትና የኢትዮጵያን ቀጣይነት የምናረጋግጥበት ነው' ማለታቸውን ኢዜአ ከስፍራው ዘግቧል።ጠቅላይ ሚኒስትሩ የትግራይን ክልል መልሶ ለማቋቋም መንግስት በሙሉ ትኩረት ይሰራል ብለዋል።በአካባቢው ለሕዝቡ የተጀመረው ሠብዓዊ ድጋፍ እንደሚቀጥልና መንግስት በሕግ ማስከበሩ ወቅት ጉዳት የደረሰባቸውን እንደሚደግፍ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ተናግረዋል።ጠቅላይ ሚኒስትሩ በተጨማሪም ከትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር አመራር አባላት ጋር በወቅታዊ የክልሉ ሁኔታ ላይ ተወያይተዋል።በተለይም ክልሉን መልሶ ለማቋቋም በሚሰሩ ስራዎች ላይ መክረዋል።
____
Jᴏɪɴ ᴏᴜʀ ᴛᴇʟᴇɢʀᴀᴍ ᴄʜᴀɴɴᴇʟ:👇
ቴሌግራም: 👉 https://t.me/ADDIS_MEREJAS

ጠቅላይ ሚኒስትሩ መቀሌ ናቸው!ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ዛሬ ወደ መቀሌ አቅንተው ህግ በማስከበር ዘመቻ ላይ ከሚገኙ የጦር አመራሮች ጋር መወያየታቸውን ኦቢኤን በቀጥታ ስርጭቱ ዘግቧል፡፡...
13/12/2020

ጠቅላይ ሚኒስትሩ መቀሌ ናቸው!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ዛሬ ወደ መቀሌ አቅንተው ህግ በማስከበር ዘመቻ ላይ ከሚገኙ የጦር አመራሮች ጋር መወያየታቸውን ኦቢኤን በቀጥታ ስርጭቱ ዘግቧል፡፡
____
Jᴏɪɴ ᴏᴜʀ ᴛᴇʟᴇɢʀᴀᴍ ᴄʜᴀɴɴᴇʟ:👇
ቴሌግራም: 👉 https://t.me/ADDIS_MEREJAS

በአሁን ሰዓት በራያ ቆቦ ወረዳ ህዝባዊ ሰልፍ እየተካሄደ ነው !መንግሥት እየወሰደ ያለውን ሕግ የማስከበር እርምጃ በመደገፍ እና የህወሕርት የግፍ አገዛዝ የሚያወግዝ ህዝባዊ ሰልፍ አሁን በራያ...
06/12/2020

በአሁን ሰዓት በራያ ቆቦ ወረዳ ህዝባዊ ሰልፍ እየተካሄደ ነው !

መንግሥት እየወሰደ ያለውን ሕግ የማስከበር እርምጃ በመደገፍ እና የህወሕርት የግፍ አገዛዝ የሚያወግዝ ህዝባዊ ሰልፍ አሁን በራያ ቆቦ ወረዳ እየተካሄደ ነው፡፡

በርካታ ቁጥር ያለው ህዝብ በሰልፉ ተገኝቶ መንግሥት እየወሰደ የሚገኘውን ሕግ የማስከበር ርምጃ እንደሚደግፍ በመግለጽ ርምጃውን አጠናክሮ እንዲቀጥል እየጠየቀ ነው፡፡
____
Jᴏɪɴ ᴏᴜʀ ᴛᴇʟᴇɢʀᴀᴍ ᴄʜᴀɴɴᴇʟ:👇
ቴሌግራም: 👉 https://t.me/ADDIS_MEREJAS

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በሆስፒታል የሚገኙ የመከላከያ አባላትን ጎበኙ!ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ዛሬ ጠዋት በሆስፒታል በህክምና ላይ የሚገኙ የመከላከያ ሠራዊት አባላትን መጎብኘታ...
06/12/2020

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በሆስፒታል የሚገኙ የመከላከያ አባላትን ጎበኙ!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ዛሬ ጠዋት በሆስፒታል በህክምና ላይ የሚገኙ የመከላከያ ሠራዊት አባላትን መጎብኘታቸውን በትዊተር ገጻቸው ገልጸዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ “ዛሬ ጠዋት #ኢትዮጵያን ከራስ በላይ ያስቀመጡ በሆስፒታል የሚገኙ ሴት እና ወንድ የሀገር መከላከያ ሰራዊት ጀግኖቻችንን ጎብኝቻለሁ! አገልግሎታችሁን እናከብራለን” ብለዋል፡፡ ይሁንና ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጉብኝት ስላደረጉበት ሆስፒታል የገለጹት ነገር የለም፡፡
____
Jᴏɪɴ ᴏᴜʀ ᴛᴇʟᴇɢʀᴀᴍ ᴄʜᴀɴɴᴇʟ:👇
ቴሌግራም: 👉 https://t.me/ADDIS_MEREJAS

 :-  ከሀገረ-ሰላምጠ/ሚኒስተሩ የጁንታውን እንቅስቃሴ በቀጥታ ስርጭት ሲከታተሉ!____Jᴏɪɴ ᴏᴜʀ ᴛᴇʟᴇɢʀᴀᴍ ᴄʜᴀɴɴᴇʟ:👇ቴሌግራም: 👉 https://t.me/ADDIS_MEREJAS
02/12/2020

:- ከሀገረ-ሰላም

ጠ/ሚኒስተሩ የጁንታውን እንቅስቃሴ በቀጥታ ስርጭት ሲከታተሉ!
____
Jᴏɪɴ ᴏᴜʀ ᴛᴇʟᴇɢʀᴀᴍ ᴄʜᴀɴɴᴇʟ:👇
ቴሌግራም: 👉 https://t.me/ADDIS_MEREJAS

ሰበር ዜና ❗️Breaking የኤርትራ ዋና ከተማ  አስመራ ምሽቱን በበርካታ ሮኬት ተመታለች❗️ዛሬ ማምሻውን ከትግራይ የተወነጨፉ በርከት ያሉ ሮኬቶች አስመራን እንደመቱ ኤርትሪያን ፕሬስ በፌስ...
28/11/2020

ሰበር ዜና ❗️
Breaking

የኤርትራ ዋና ከተማ አስመራ ምሽቱን በበርካታ ሮኬት ተመታለች❗️

ዛሬ ማምሻውን ከትግራይ የተወነጨፉ በርከት ያሉ ሮኬቶች አስመራን እንደመቱ ኤርትሪያን ፕሬስ በፌስቡክ ገፁ ፅፏል ።

ሮኬቶቹ ብዙ ነዋሪዎች በሚኖሩበት አከባቢ እንደተመቱ የገለፅ ሲሆን ነገር ግን የተጎዳ ሰው አለመኖሩን ጨምሮ ገልጷል።
____
Jᴏɪɴ ᴏᴜʀ ᴛᴇʟᴇɢʀᴀᴍ ᴄʜᴀɴɴᴇʟ:👇
ቴሌግራም: 👉 https://t.me/ADDIS_MEREJAS

ሰበርዜና!የሀገር መከላከያ ሰራዊት ውቅሮን፣ ሀውዜን፣ አልነጃሺ፣ አዲቀየህ እና ማይመሳኖን ሙሉ በሙሉ መቆጣጠሩን አሳውቋል።በመቀሌ ያለውን የወንጀለኛ ቡድን የመቆጣጠር ተግባር በማጠቃላይ ምዕራ...
28/11/2020

ሰበርዜና!

የሀገር መከላከያ ሰራዊት ውቅሮን፣ ሀውዜን፣ አልነጃሺ፣ አዲቀየህ እና ማይመሳኖን ሙሉ በሙሉ መቆጣጠሩን አሳውቋል።

በመቀሌ ያለውን የወንጀለኛ ቡድን የመቆጣጠር ተግባር በማጠቃላይ ምዕራፍነት የተያዘ ሲሆን ሰራዊቱ ግዳጁን በምን አኳኋን መፈጸም እንዳለበት በቂ ዝግጅት አድርጎ የወንጀለኛውን ቡድን በቁጥጥር ስር ለማዋል መዘጋጀቱን ተገልጿል።

የጁንታው ቡድንም በፕሮፓጋንዳ ጭምር እያፈገፈገ መሄዱ ሽንፈቱን እያረጋገጠ መሆኑን አመልክተዋል። በማጠቃለያው ምዕራፍ መቀሌን ለመቆጣጠር የሚያስሉ ስትራቴጂክ ቦታዎች መያዙን አስታወቀ። በራያ በኩልም አድቀይህ ፣ አዲመሳኖን እና ሂዋናን ከታጣቂ ሃይሉ ነፃ ማድረጉን ገልጸዋል። በጉላን በኩል መንገድ ለመዝጋት ቢሞክርም እንዳልተሳካለትና ወደ ኋላ ማፈግፈጉን ተናግረዋል።

አሁን ላይ መቀሌ ብቻ መቅረቱን የገለጹት ሌተናል ጀነራል ሀሰን በጥቂት ቀናት ወስጥ ተጠናቆ ጁንታው ለሀግ እነደሚቀርብ አረጋግጠዋል። የጁንታው ሃይል በራያ በኩል ያለ የሌለ ሃይሉን በመጠቀም የሰራዊቱን ጥቃት ለመቋቋም ቢሞክርም በመመታቱ ለመልቀቅ ተገዷል ነው ያሉት። የህወሃት ጁንታ ሽንፈቱን እያረጋገጠ በመምጣቱ በሀሰት ወሬ ላይ ተጠምዶ ህዝብን በማደናገር ላይ ነው ብለዋል። ዘገባው የኢዜአ ነው፡፡
____
Jᴏɪɴ ᴏᴜʀ ᴛᴇʟᴇɢʀᴀᴍ ᴄʜᴀɴɴᴇʟ:👇
ቴሌግራም: 👉 https://t.me/ADDIS_MEREJAS

  !ጠዋት  #በባህርዳር ለደረሰው የሚሳኤል ጥቃት የትግራይ ክልል ሀላፊነቱን ወሰደ !🔰ዛሬ ጥዋት በባህርዳር አየር ማረፍያ  ውጤታማ  የሮኬት ድብደባ  አካሂደናል ሲል ትግራይ ቴሌቨዥን ዘግቦ...
23/11/2020

!

ጠዋት #በባህርዳር ለደረሰው የሚሳኤል ጥቃት የትግራይ ክልል ሀላፊነቱን ወሰደ !

🔰ዛሬ ጥዋት በባህርዳር አየር ማረፍያ ውጤታማ የሮኬት ድብደባ አካሂደናል ሲል ትግራይ ቴሌቨዥን ዘግቦል።
____
Jᴏɪɴ ᴏᴜʀ ᴛᴇʟᴇɢʀᴀᴍ ᴄʜᴀɴɴᴇʟ:👇
ቴሌግራም: 👉 https://t.me/ADDIS_MEREJAS

22/11/2020

የመከላከያ ሰራዊት ትህነግ የያዛቸውን ቁልፍ እስቸጋሪ ቦታዎች በታላቅ ድል እያስለቀቀ #ከመቀሌ በቅርብ ርቀት ላይ ደርሷል ❗️

🎬 የምስል ዘገባ 🎬

💰 ፓኬጅ ከገዙ 2.03 ብር 💰
____
Jᴏɪɴ ᴏᴜʀ ᴛᴇʟᴇɢʀᴀᴍ ᴄʜᴀɴɴᴇʟ:👇
ቴሌግራም: 👉 https://t.me/ADDIS_MEREJAS

"ጁንታው ከአሁን በኋላ ያለው ብቸኛው አማራጭ ተዋግቶ መሞት አሊያም እጅ መስጠት ብቻ ነው"ብ/ጄ/ል ተስፋዬ አያሌውየመከላከያ ህብረት ዘመቻ ዋና መምሪያ ኃላፊ ብ/ጄኔራል ተስፋዬ አያሌው ፣ ጁ...
22/11/2020

"ጁንታው ከአሁን በኋላ ያለው ብቸኛው አማራጭ ተዋግቶ መሞት አሊያም እጅ መስጠት ብቻ ነው"
ብ/ጄ/ል ተስፋዬ አያሌው

የመከላከያ ህብረት ዘመቻ ዋና መምሪያ ኃላፊ ብ/ጄኔራል ተስፋዬ አያሌው ፣ ጁንታው የህወሐት ቡድን የሰራዊታችንን ሕግ የማስከበር እርምጃ መቋቋም እንደተሳነው ተናገሩ።

ጄኔራል መኮንኑ የሠራዊታችንን ፈጣን የማጥቃት እንቅሰቃሴን አስመልክተው በካርታ የደገፈ ገለፃ አድርገዋል።

ፅንፈኛው የህወሃት ቡድን የሠራዊታችንን ወቅታዊ አቋም በተሳሳተ መንገድ ገምግሞ በድሮ የጫካ ስሌት ወደ ውጊያ በመግባቱ ለውርደት ተዳርጓል ብለዋል።

ብ/ጄ ተስፋዬ አክለውም ፅንፈኛው ቡድን ልዩ ኃይል ብሎ የሚጠራውን ታጣቂና ሚሊሻውን ከፊት አሰልፎ ፣ ከሰራዊቱ በተለያየ ምክንያት የወጡ ከሃዲያንን ከኋላ በማሰለፍ በግዴታ እንዲዋጉ እያደረገ ነው ብለዋል።

ፅንፈኛው የህወሃት ጁንታ ህዝቡን ከመናቁ የነተነሳ ፣ የልማት አውታሮችን እያወደመ እንደሚገኝ ተናግረው ፣ ይህም የሽንፈቱ ማሳያ ነው ሲሉ ገልፀዋል ።

ጁንታው ከአሁን በኋላ ያለው ብቸኛው አማራጭ ተዋግቶ መሞት አሊያም እጅ መስጠት ብቻ ነው ብለዋል።
___
Jᴏɪɴ ᴏᴜʀ ᴛᴇʟᴇɢʀᴀᴍ ᴄʜᴀɴɴᴇʟ:👇
ቴሌግራም: 👉 https://t.me/ADDIS_MEREJAS

ሰበርዜና! #መቀሌየኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ወደ ትግራይ መዲና መቀሌ እየደረሰ መሆኑን የኢትዮጵያ መንግሥትን ጠቅሶ ሮይተርስ ዘገበ። በትግራይ የሕወሓትን ቡድን ወደ ሕግ  ለማቅረብ በሚል የ...
19/11/2020

ሰበርዜና!

#መቀሌ

የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ወደ ትግራይ መዲና መቀሌ እየደረሰ መሆኑን የኢትዮጵያ መንግሥትን ጠቅሶ ሮይተርስ ዘገበ።

በትግራይ የሕወሓትን ቡድን ወደ ሕግ ለማቅረብ በሚል የጀመረዉ ጦርነት ሁለት ሳምንት እንደሞላዉ የዜና ወኪል ሮይተርስ ጨምሮ ዘግቦአል። በጠቅላይ ሚኒስትር የተቋቋመዉ የትግራይ ግጭትን የሚከታተለዉ ግብረ ኃይል የትግራዩን ጦርነት ሸሽተዉ ወደ ወደ ሱዳን የሸሹ ዜጎችን ለመመለስ እቅድ መያዙንም ሮይተርስ ዘግቦአል። ከዚህ በተጨማሪ በትግራይ የሰብዓዊ ቀዉስ መርጃ የሚሆን ቁሳቁሶችን ለመላክ የልዑካን ቡድን ወደ ስፍራዉ ማቅናቱ ተመልክቶአል።

በተጨማሪ ትግራይ መከላከያ ሀይል ወታደራዊ ቃል አቀባይ ለመጀመርያ ግዜ መግለጫ ሰጥተዋል ተብሎአል። መከላከያ ሀይሉ እየተካሄደ ባለው ጦርነት ከኢትዮጵያ ውጭ የሆኑ አፍሪካዊና ሌሎች ሀይሎች እየተሳተፉ ናቸዉ ሲል በመግለጫዉ ገልፆአል። በተጨማሪ ዛሬ ሃሙስም እንዲሁ በመቀሌ የጦር አውሮፕላን ሲያንዣብብ እና የየተኩስ ድምጽ ሲሰማ ዉሎአል።
____
Jᴏɪɴ ᴏᴜʀ ᴛᴇʟᴇɢʀᴀᴍ ᴄʜᴀɴɴᴇʟ:👇
ቴሌግራም: 👉 https://t.me/ADDIS_MEREJAS

ለመከላከያ ሠራዊታችን  ክብር እቆማለሁ !ዛሬ ዕለት ማክሰኞ ኅዳር 8 ቀን 2013 ዓ.ም "ለሀገር መከላከያ ክብር እቆማለሁ" በሚል ርእስ ለመከላከያ ሰራዊታችን አብሮነት ይገለፃል ። ከጠዋቱ ...
17/11/2020

ለመከላከያ ሠራዊታችን ክብር እቆማለሁ !

ዛሬ ዕለት ማክሰኞ ኅዳር 8 ቀን 2013 ዓ.ም "ለሀገር መከላከያ ክብር እቆማለሁ" በሚል ርእስ ለመከላከያ ሰራዊታችን አብሮነት ይገለፃል ።

ከጠዋቱ 5:30 ላይ ሁሉም ነዋሪ ለአንድ ደቂቃ ቀኝ እጃቸውን በግራ ደረታቸው ላይ አድርገው በመቆም ለመከላከያ ሠራዊታችን ያላቸውን ክብር ይገልጣሉ።

ለአንድ ደቂቃ የመቆም ሥርዓቱ ሲጠናቀቅ በቀጣዩ አንድ ደቂቃ ባሉበት ሆነው ባለማቋረጥ ያጨበጭባሉ።
____
Jᴏɪɴ ᴏᴜʀ ᴛᴇʟᴇɢʀᴀᴍ ᴄʜᴀɴɴᴇʟ:👇
ቴሌግራም: 👉 https://t.me/ADDIS_MEREJAS

      !አሜሪካ ለኢትዮጵያ አየር ሀይል ሄርኩለስ (Hercules) C-130E የተባለውን እጅግ ዘመናዊውንና ግዙፍ የጦር አውሮፕላን ተሰጠ የተባለው የ #ሀሰት ዜና ነው ።ይሄ ፎቶ የተነሳው...
16/11/2020

!

አሜሪካ ለኢትዮጵያ አየር ሀይል ሄርኩለስ (Hercules) C-130E የተባለውን እጅግ ዘመናዊውንና ግዙፍ የጦር አውሮፕላን ተሰጠ የተባለው የ #ሀሰት ዜና ነው ።

ይሄ ፎቶ የተነሳው ባለፈው አመት የካቲት ላይ ነው።
____
Jᴏɪɴ ᴏᴜʀ ᴛᴇʟᴇɢʀᴀᴍ ᴄʜᴀɴɴᴇʟ:👇
ቴሌግራም: 👉 https://t.me/ADDIS_MEREJAS

 አስመራ ላይ ለተፈፀመው የሮኬት ጥቃት ህወሀት ሀላፊነቱን ወሰደ!!የትግራይ ክልል ፕሬዚዳንት ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል አስመራ ላይ የሮኬት ጥቃት መፈፀማቸውን ለሮይተርስ የተናገሩ ሲሆን ም...
15/11/2020



አስመራ ላይ ለተፈፀመው የሮኬት ጥቃት ህወሀት ሀላፊነቱን ወሰደ!!

የትግራይ ክልል ፕሬዚዳንት ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል አስመራ ላይ የሮኬት ጥቃት መፈፀማቸውን ለሮይተርስ የተናገሩ ሲሆን ምፅዋ ላይ ግን ምንም ጥቃት አልፈፀምንም ብለዋል።
____
Jᴏɪɴ ᴏᴜʀ ᴛᴇʟᴇɢʀᴀᴍ ᴄʜᴀɴɴᴇʟ:👇
ቴሌግራም: 👉 https://t.me/ADDIS_MEREJAS

በኤርትራ አስመራ ከተማ ላይ ከፍተኛ ፍንዳታ ተሰምቷል !ህወሐት ሶስት ሚሳኤል አስወንጭፎ አስመራ ላይ ጥቃት አድርሷል። ህወሐት የኤርትራን አየር መንገድንና የኢንፎርሜሽን ሚኒስቴርን በጥቃቱ እ...
14/11/2020

በኤርትራ አስመራ ከተማ ላይ ከፍተኛ ፍንዳታ ተሰምቷል !

ህወሐት ሶስት ሚሳኤል አስወንጭፎ አስመራ ላይ ጥቃት አድርሷል። ህወሐት የኤርትራን አየር መንገድንና የኢንፎርሜሽን ሚኒስቴርን በጥቃቱ እንደመታ ኤርትራ ሪፖርት እንዳደረገች ማርቲን ፕላዉት በትዊተር ገፁ ጽፏል።
____
Jᴏɪɴ ᴏᴜʀ ᴛᴇʟᴇɢʀᴀᴍ ᴄʜᴀɴɴᴇʟ:👇
ቴሌግራም: 👉 https://t.me/ADDIS_MEREJAS

  !ለሚሳኤል ጥቃቱ ህወሀት ሀላፊነቱን ወሰደ!!" ኣብይ ኣህመድ በተለያዩ የትግራይ ኣከባቢዎች ለካሄደው የኣየር ድብደባ ጀግናው የትግራይ መከላከያ ሰራዊት በወሰደው ኣፀፋዊ ምላሽ በባህርዳር ...
14/11/2020

!

ለሚሳኤል ጥቃቱ ህወሀት ሀላፊነቱን ወሰደ!!

" ኣብይ ኣህመድ በተለያዩ የትግራይ ኣከባቢዎች ለካሄደው የኣየር ድብደባ ጀግናው የትግራይ መከላከያ ሰራዊት በወሰደው ኣፀፋዊ ምላሽ በባህርዳር እና ጎንደር በወታደራዊ ካምፕ የሚሳኤል ጥቃት ኣካሂዷል፡፡"

©ኣቶ ጌታቸው ረዳ
____
Jᴏɪɴ ᴏᴜʀ ᴛᴇʟᴇɢʀᴀᴍ ᴄʜᴀɴɴᴇʟ:👇
ቴሌግራም: 👉 https://t.me/ADDIS_MEREJAS

ትናንት ምሽት ወደ ባሕርዳር እና ጎንደር  #ሮኬት ተተኩሷል !ስግብግቡ የሕወሓት ጁንታ ትናንት ምሽት ወደ ባሕርዳር እና ጎንደር ሮኬት መተኮሱን ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መረጃ ማጣሪያ ያገኘነው ...
14/11/2020

ትናንት ምሽት ወደ ባሕርዳር እና ጎንደር #ሮኬት ተተኩሷል !

ስግብግቡ የሕወሓት ጁንታ ትናንት ምሽት ወደ ባሕርዳር እና ጎንደር ሮኬት መተኮሱን ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መረጃ ማጣሪያ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። በዚህም በአውሮፕላን ማረፊያ አካባቢ መጠነኛ ጉዳት መድረሱ ተመልክቷል።

ስግብግቡ ጁንታ በእጁ ያሉትን የመጨረሻዎቹን መሣሪያዎች ጠጋግኖ ለጥፋት ተልዕኮ ለማዋል መሞከሩን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መረጃ ማጣሪያ አስታውቋል። ይህም ከመሞቱ በፊት የመጨረሻውን ዐቅሙን እየሞከረ መሆኑን ያመለክታል ነው ያለው መረጃው። ዝርዝሩን መርማሪ ቡድን ተመድቦ እያጣራው እንደሆነ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መረጃ ማጣሪያ አሳውቋል፡፡
____
Jᴏɪɴ ᴏᴜʀ ᴛᴇʟᴇɢʀᴀᴍ ᴄʜᴀɴɴᴇʟ:👇
ቴሌግራም: 👉 https://t.me/ADDIS_MEREJAS

ጎንደር እና ባህርዳር!!ምሽት ላይ በባህር ዳር  ከተማ  በተለምዶ መኮድ በሚባለው አካባቢ የቦምብ ፍንዳታ ተከሰተ!በአማራ ክልል ባህር ዳር ከተማ ዛሬ ምሽት ላይ የቦምብ ፍንዳታ የተከሰተ ሲሆ...
14/11/2020

ጎንደር እና ባህርዳር!!

ምሽት ላይ በባህር ዳር ከተማ በተለምዶ መኮድ በሚባለው አካባቢ የቦምብ ፍንዳታ ተከሰተ!

በአማራ ክልል ባህር ዳር ከተማ ዛሬ ምሽት ላይ የቦምብ ፍንዳታ የተከሰተ ሲሆን ፍንዳታው በጸጥታ ኃይሉ በትንሽ ደቂቃዎች ውስጥ በቁጥጥር ስር ውሏል ተብሏል፡፡ ከዚህ ጋር ተያይዞ በከተማዋ የተለየ የመብራት መቆራረጥ አልተፈጠረም ያለው የክልሉ ኮሙኒኬሽን ከተማዋ በሰላማዊ ሁኔታ ውስጥ ትገኛለች ሲልም በፌስቡክ ገጹ አስታውቋል፡፡ የተፈጠረው ፍንዳታ "ከጁንታው ቡድን" የአጥፍቶ ጠፊነት የሽብር ተግባር ጋር ስለመገናኘት አለመገናኘቱ ለመለየት መረጃዎቹ በሚመለከተው አካል በመጣራት ላይ እንዳሉም ገልጿል።

ጎንደር ፦

የአማራ ክልል መንግስት በጎንደር አዘዞ አካባቢ ከ5:00 በኃላ ልክ የባህር ዳሩን አይነት ፍንዳታ መፈፀሙን አሳውቋል። በአሁን ሰዓት ሁሉም ነገር ሰላም እንደሆነ ገልጿል። የክልሉ መንግስት ሁሉም ህብረተሰብ ተረጋግቶ አካባቢውን እና እራሱን እንዲጠብቅ በጥብቅ አሳስቧል።
____
Jᴏɪɴ ᴏᴜʀ ᴛᴇʟᴇɢʀᴀᴍ ᴄʜᴀɴɴᴇʟ:👇
ቴሌግራም: 👉 https://t.me/ADDIS_MEREJAS

ቀዳሚ የመረጃ ምንጭ 🇪🇹 🇪🇹 . ⏬ምርት እና አገልግሎቶን ለማስተዋወቅ ከፈለጉ⏬ ⏬ ꜰᴏʀ ᴘᴀɪᴅ ᴘʀᴏᴍᴏᴛɪᴏɴ ⏬ ይጠቀሙ መረጃዎችን ለመላክ

የጠቅላይ ሚኒስትሩ የትግርኛ መልዕክት ፦ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አህመድ፥ የትግራይ ክልል ልዩ ሃይል እና የፀጥታ አካላት ከቀናት ያልበለጠ ዕድሜ ለሌለው ቡድን ሲሉ ህይወታቸው እንዳያጡ ጥሪ አቀረቡ...
13/11/2020

የጠቅላይ ሚኒስትሩ የትግርኛ መልዕክት ፦

ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አህመድ፥ የትግራይ ክልል ልዩ ሃይል እና የፀጥታ አካላት ከቀናት ያልበለጠ ዕድሜ ለሌለው ቡድን ሲሉ ህይወታቸው እንዳያጡ ጥሪ አቀረቡ።

የሕወሓት አመራር የተሰለፈው ሰራዊት በቀጣይ 3 ቀናት ውስጥ ለመከላከያ ሰራዊት በሰላም እጁን እንዲሰጥ ጠ/ሚ አብይ አሳሰቡ።
____
Jᴏɪɴ ᴏᴜʀ ᴛᴇʟᴇɢʀᴀᴍ ᴄʜᴀɴɴᴇʟ:👇
ቴሌግራም: 👉 https://t.me/ADDIS_MEREJAS

የተከዜ የኤሌክትሪክ ሃይል ማመንጫ ግድብ በፌዴራል መንግሥት ተደብድቧል የሚለውን የህወሓት ውንጀላ ሀሰት ነው ሲል የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ፋክት ቼክ አስታወቀ። በውሃ የተሞላ ትልቅ ግድብ ላይ ...
13/11/2020

የተከዜ የኤሌክትሪክ ሃይል ማመንጫ ግድብ በፌዴራል መንግሥት ተደብድቧል የሚለውን የህወሓት ውንጀላ ሀሰት ነው ሲል የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ፋክት ቼክ አስታወቀ። በውሃ የተሞላ ትልቅ ግድብ ላይ የተባለው ጥቃት ደርሶበት ቢሆን ዜና ብቻ ሚሆን ሳይሆን ከባድ አደጋን ያስከትል እንደነበር በወጣው መግለጫ ተጠቅሷል።
____
Jᴏɪɴ ᴏᴜʀ ᴛᴇʟᴇɢʀᴀᴍ ᴄʜᴀɴɴᴇʟ:👇
ቴሌግራም: 👉 https://t.me/ADDIS_MEREJAS

በወጋገን ባንክ ዋናው መስሪያ ቤት ከሚያስፈልገው በላይ የጦር መሳሪያ መገኘቱ ተሰማ!የፋይናንስ አገልግሎት ሰጭ በሆነው ወጋገን ባንክ ዋና መሥሪያ ቤት፣ ለጥበቃ አገልግሎት ከሚያስፈልገው ውጭ ...
13/11/2020

በወጋገን ባንክ ዋናው መስሪያ ቤት ከሚያስፈልገው በላይ የጦር መሳሪያ መገኘቱ ተሰማ!

የፋይናንስ አገልግሎት ሰጭ በሆነው ወጋገን ባንክ ዋና መሥሪያ ቤት፣ ለጥበቃ አገልግሎት ከሚያስፈልገው ውጭ በዛ ያለ የጦር መሣሪያ ተከማችቶ መገኘቱ ተሰማ።በአዲስ አበባ በርካታ የጦር መሳሪያ የተገኘባቸው ሌሎች ድርጅቶችም አሉ ተብሏል።በወጋገን ባንክ ዋና መሥሪያ ቤት የተገኙት የጦር መሣሪያዎች ለሌላ ዓላማ ሊውሉ የሚችሉ መሆናቸውን ኮሚሽነሩ ለሸገር ነግረዋል።

በወጋገን ባንክ ዋና መሥሪያ ቤት ለጥበቃ አገልግሎት ከሚያስፈልገው ውጭ የጦር መሠሪያ ተከማችቶ መገኘቱን የተናገሩት የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጌቱ አርጋው፣ ከተገኙት መሣሪያዎች አንዳንዱ በፀጥታ ኃይሉ እጅ የሌሉ ጭምር ናቸው ብለዋል፡፡ሱር ኮንስትራክሽንም የተለያየ ተልዕኮ ወስዶ ሲንቀሳቀስ የነበረ ሌላው የሕወሓት አካል ነው ተብሏል።በእነዚህ መሥሪያ ቤቶች በሕዝብ ጥቆማ እና ኮሚሽኑ ካለው መረጃ በመነሳት ብርበራ እና ፍተሻ መደረጉን ሸገር ሰምቻለው ብሏል።

የጦር መሣርያ እና ሌሎች ቁሳቁሶችን መከላከያ በራሱ ካምፕ ነው የሚያስቀምጠው ያሉት ኮሚሽነር ጌቱ በእነዚህ ተቋማት በብርበራ የተገኙትም ከፍተኛ የጦር መሣርያዎች ናቸው ብለዋል።በከተማው ውስጥ ካሉ ባለሀብቶች መካከል ለሕወሓት ድጋፍ የሚያደርጉ እንደነበሩም ኮሚሽነሩ ለሸገር ነግረዋል፡፡ ባለሀብቶች በተለያየ መንገድ ንብረት ሊያፈሩ ይችላሉ ያሉት ኮሚሽነር ጌቱ፣ የፖሊስ ኮሚሽኑ ከወንጀል ጋር የተያያዘ ተጨባጭ መረጃ እና ሕገ መንግሥታዊ ስርአቱን አደጋ ላይ የሚጥል ጥፋት በመፈፀም ተቀናጅተው የሚሠሩ አካላት ላይ ያተኮረ ሥራ ነው የሚያከናውነው ብለዋል፡፡

Via Sheger FM
____
Jᴏɪɴ ᴏᴜʀ ᴛᴇʟᴇɢʀᴀᴍ ᴄʜᴀɴɴᴇʟ:👇
ቴሌግራም: 👉 https://t.me/ADDIS_MEREJAS

አምነስቲ ኢንተርናሽናል ዛሬ ባወጣው ሪፖርት በማይካድራ በመቶ የሚቆጠሩ ሰዎች ከሶስት ቀን በፊት በጅምላ መገደላቸውን ገልፇል። ግድያውንም የፈፀሙትን አካሎች መንግስት ለህግ እንዲያቀርብ ጠይቋ...
13/11/2020

አምነስቲ ኢንተርናሽናል ዛሬ ባወጣው ሪፖርት በማይካድራ በመቶ የሚቆጠሩ ሰዎች ከሶስት ቀን በፊት በጅምላ መገደላቸውን ገልፇል።

ግድያውንም የፈፀሙትን አካሎች መንግስት ለህግ እንዲያቀርብ ጠይቋል።ግድያው ወደ ሁመራ መውጫ ባለ ስፍራ በሚገኘው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አካባቢ በሚገኝ ስፍራ መፈፀሙን በፎቶና ከአይን እማኞች አረጋግጫለው ሲል ሪፖርቱ ፅፏል።ግድያው ምንም ፖለቲካዊ ቁርኝት በሌላቸው በቀን ሰራተኞች ላይ የተፈፀመ ሲሆን የግድያው እውነተኛ አጀንዳ ጊዜ ያወጣዋል ያለ ሲሆን መንግስት እያደረገ ላለው የሚሊታሪ ኦፕሬሽን ግልፀኝነት ሲባልና የሰብአዊ እርዳታ ስራዎች በቀላሉ ለመስራት እንዲያግዝ በትግራይ የተቋረጠው የስልክና የኢንተርኔት ግንኙነት አንዲመለስ አምነስቲ የጠየቀ ሲሆን አምነስቲ በስፍራው የሚደርሰውን ማንኛውንም ኢ ሰብአዊ የመብት ጥሰትና ወንጀል እየመዘገብኩ ለአለም ህዝብ አጋልጣለው ብሏል።

Via FidelPost
____
Jᴏɪɴ ᴏᴜʀ ᴛᴇʟᴇɢʀᴀᴍ ᴄʜᴀɴɴᴇʟ:👇
ቴሌግራም: 👉 https://t.me/ADDIS_MEREJAS

ቀዳሚ የመረጃ ምንጭ 🇪🇹 🇪🇹 . ⏬ምርት እና አገልግሎቶን ለማስተዋወቅ ከፈለጉ⏬ ⏬ ꜰᴏʀ ᴘᴀɪᴅ ᴘʀᴏᴍᴏᴛɪᴏɴ ⏬ ይጠቀሙ መረጃዎችን ለመላክ

ዶክተር ሙሉ ነጋ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ ዋና ስራ አስፈጻሚ ሆነው ተሾሙ።በፌደሬሽን ምክር ቤት ውሳኔ መሠረት በትግራይ ብሔራዊ ክልል የሚቋቋመውን ጊዜያዊ አስተዳደር አስመልክቶ የሚኒስትሮች ም...
13/11/2020

ዶክተር ሙሉ ነጋ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ ዋና ስራ አስፈጻሚ ሆነው ተሾሙ።

በፌደሬሽን ምክር ቤት ውሳኔ መሠረት በትግራይ ብሔራዊ ክልል የሚቋቋመውን ጊዜያዊ አስተዳደር አስመልክቶ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ማጽደቁ ይታወቃል።

በጸደቀው ደንብ መሠረት ዶ/ር ሙሉ ነጋ በክልሉ የተቋቋመው ጊዜያዊ አስተዳደር ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሆነው ተሰይመዋል።

ዋና ሥራ አስፈጻሚው የጊዜያዊ አስተዳደሩ አካል ሆነው፣ የክልሉን የመንግሥት አስፈጻሚ አካላትን የሚመሩ ኃላፊዎችን ፣ በክልሉ ከሚንቀሳቀሱ የተለያዩ ሕጋዊ የፖለቲካ ፓርቲዎች በመመልመል እንደሚሾሙ ጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር አብይ አህመድ በፌስቡክ ገጻቸው አስፍረዋል።
____
Jᴏɪɴ ᴏᴜʀ ᴛᴇʟᴇɢʀᴀᴍ ᴄʜᴀɴɴᴇʟ:👇
ቴሌግራም: 👉 https://t.me/ADDIS_MEREJAS

  !የአገር ክህደት ወንጀል በፈፀሙ የጁንታው ሕወሓት ቡድን ላይ የፍርድ ቤት የመያዣ ትዕዛዝ እንደወጣባቸው የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ ❗️የጥፋት ቡድኑ አባላት ከኦነግ ሸኔ እና ከሌሎች...
12/11/2020

!

የአገር ክህደት ወንጀል በፈፀሙ የጁንታው ሕወሓት ቡድን ላይ የፍርድ ቤት የመያዣ ትዕዛዝ እንደወጣባቸው የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ ❗️

የጥፋት ቡድኑ አባላት ከኦነግ ሸኔ እና ከሌሎች ፀረ-ሰላም ሃይሎች ጋር በመቀናጀትም ከተለያዩ ክልሎች አገርን የማፍረስ ተልዕኮ ያለቸውን ኃይሎች በመመልመል ትግራይ ክልል ድረስ በመውሰድ ለእኩይ ተልዕኮቸው ስኬት የተለያዩ ስልጠናዎችን በመስጠት እንዲሁም የገንዘብና የቁሳቁስ ድጋፎችን በማድረግ በተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች ብሄርን ከብሄር በማጋጨት እና በሃይማኖት ሽፋን ሁከትና ብጥብጥ እንዲፈጠር በማድረግ በርካታ ንፅሁን ዜጎች እንዲገደሉ፣ በአካልና በንብረት ላይም ከባድ ጉዳት እንዲደርስ ማድረጋቸውን የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን በላከው መግለጫ አመልክቷል፡፡

▪️እነዚህ የሀገር ህልውናን አደጋ ላይ በመጣል እንዲሁም ህገ-መንግስቱንና ህገ-መንግስታዊ ስርዓቱን በሀይል በመናድ ወንጀል የሚፈለጉትና የፍርድ ቤት የመያዣ ትዕዛዝ የወጣባቸው፡-

1.ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል
2.ጌታቸው ረዳ
3. ፈትለወርቅ ገ/እግዝያብሄር
4. አስመላሽ ወ/ስላሴ
5.ዶ/ር አብርሃም ተከስተ
6.ኪሪያ ኢብራሂም
7.ረዳይ አለፎም
8.አማኑኤል አሰፋ
9.ዶ/ር አትንኩት መዝገቡ
10.ኪሮስ ሀጎስ
11.ያለም ፀጋ
12.ሰብለ ካህሳያ
13.ጌታቸው አሰፋ
14.ዳንኤል አሰፋ
15.ኢሳያስ ታደሰ
16.ዶ/ር አክሊሉ ሀ/ሚካኤል
17.አለም ገ/ዋህድ
18.ተክላይ ገ/መድህን
19.ዶ/ር እያሱ በርሄ
20.ዶ/ር ረዳይ በርሄ
21.ዶ/ር ኪዳን ማርያም በርሄ
22.ነጋ አሰፋ
23.ሺሻይ መረሳ
24. ዶ/ር ገ/ህይወት ገ/እግዝያብሄር
25. አፅብሃ አረጋዊ
26.ዶ/ር ኢ/ር ሰለሞን ኪዳኔ
27.ሀዱሽ ዘነበ
28.በርሄ ገ/እየሱስ
29.ይትባረክ አምሃ
30.ዶ/ር ገ/መስቀል ካህሳይ
31.ዶ/ር ፍስሃ ሀ/ፂዮን
32.ርስቀ አለማየው
33.ዶ/ር አዲስ አለም ቤሌማ
34.ዘነበች ፍስሃ
35.ፍሬወይኒ ገ/እግዝያብሄር
36.አቶ ስዩም መስፍን
37.አቶ አባይ ፀሐዬ
38.እያሱ ተስፋይ
39.ለምለም ሀድጎ
40.ፕሮፌሰር ክንድያ ገ/ህይወት
41.ሀብቱ ኪሮስ
42.በየነ ምክሩ
43.ካሳዬ ገ/ህይወት
44.ሩፈኤል ሽፈራ
45.ሊያ ካሳ
46.ተወለደ ገ/ፃዲቅ
47.ሙሉ ገ/እግዝያብሄር
48.ኪሮ ስጉዑሽ
49.ዶ/ር አማኑኤል ሀይሌ
50.ደሳለኝ ተፈራ
51.ኢንጅነር አርአያ ብርሀኔ
52.አልማዝ ገ/ፃድቅ
53.ሰለሞን መአሾ
54.ተኪኡ ማዕሾ
55.ገነት አረፈ
56.ብርክቲ ገ/መድህን
57.ዶ/ር ሀጎስ ገዳፋይ
58.ዘራይ አስጎዶም
59.አሰፋ በላይ
60.አቶ ሸዋንግዘው ገዛኸኝ
61.አፅብሃ ግደይ
62.አቶ ስብሀት ነጋ
63.አቶ ሴኮትሬ ጌታቸው
64.በሪሁን ተ/ብርሃን የፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ዳኛ የነበረ ናቸው፡፡

▪️ከላይ ስማቸው የተዘረዘረው የወንበዴው የጁንታው ሕወሓት የጥፋት ቡድን አባላት የአገር ክህደት ወንጀል ከመፈጸማቸውም በተጨማሪ በከፍተኛ የአገር ሃብት ምዝበራና ዘረፋ እንዲሁም በሰበአዊ መብት ጥሰት ወንጀልም ጭምር የሚፈለጉ መሆናቸውን ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን በመግለጫው አሳውቋል፡፡

▪️በተመሳሳይም ከጁንታው ሕወሓት ቡድን አባላት ጋር እየተገናኙ የሀገር ክህደት ወንጀል በፈፀሙና አገር በማፍረስ ሴራ በተሳተፉ የሀገር መከላከያ ሰራዊት እና የፖሊስ አመራሮች ላይም የፍርድ ቤት የመያዣ ትዕዛዝ እንደወጣባቸው የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን በመግለጫው አስታውቋል፡፡

▪️ተጠርጣሪዎቹ መንግስት እና ሕዝብ የጣለባቸውን አገራዊ ኃላፊነትና ህገመንግስታዊ ግዴት ወደጎን በመተው መቀመጫዉን ትግራይ ክልል ካደረገዉ ከወንበዴው የህወሃት የጁንታው ቡድን አባላት ተልዕኮ በመቀበል በሰሜን ዕዝ ሰራዊት አባላት ውስጥ ሴሎችን በማደራጀት ከማዕከል የነበረው ግንኙነት እንዲቋረጥና ጥቅምት24 ቀን 2013 ዓ/ም ጥቃት እንዲፈጸም በማድረግ የሞት፣የአካል ጉዳት እና የጦር መሳሪያ ዝርፊያ እንዲፈፀም ማድረጋቸውን የኮሚሽኑ መግለጫ ያመለክታል፡፡

▪️ባለፉት 21 አመታት በምሽግ አብረው ሲኖሩ የነበሩ ጓዶቻቸውን የጁንታው ቡድን እኩይ አላማ ማስፈጸሚያ በማድረግ አገር በማፍረስ ተልዕኮው በመምራትና በመሳተፍ የሚፈለጉት ከፍተኛ ወታደራዊ መኮንኖችና የፖሊስ አባላት፡-

1.ሌ/ጀኔራል ታደሰ ወረደ ተስፋዬ (ውድወርደ)
2.ሜ/ጄኔራል ዮሐንስ ወ/ጎርጊስ ተስፋይ (መዲድ)፣
3.ሜ/ጄኔራል ብርሃነ ነጋሽ በየነ (ውድመድህን)፣
4.ብ/ጄኔራል ሀ/ስላሴ ግርማይ ገ/ሚካኤል
5.ብ/ጄኔራል ምግበ ሃይለ ወ/አረጋይ (አባበርሃ፣)
6.ሜ/ጄኔራል ኢብራሂም አብዱልጀሊል መሀመድዙን
7.ብ/ጄኔራል ገ/ኪዳን ገ/ማርያም የእብዮ
8.ሜ/ጄኔራል ገብረ ገ/አድሃና ወ/ዘጉ (ገብረዲላ)
9.ሜ/ጄኔራል ገ/መስቀል ገ/ዮሀንስ /አስቴር/
10.ብ/ጄኔራል አብርሃ ተስፋይ በርሄ /ድንኩል/
11.ብ/ጄኔራል ፍስሃ በየነ (ወርቅአይኑ)
12.ሜ/ጄኔራል ህንፃ ወ/ጎርጊስ ዮሐንስ
13.ብ/ጄኔራል አለፎም አለሙ ወ/ማርያም /ቸንቶ/
14.ብ/ጄኔራል ገ/መስቀል ገ/እግዝያብሄር (ጠቀም)
15.ብ/ጄኔራል ተ/ብርሃን ወ/አረጋዊ
16.ሜ/ጄኔራል አታክልቲ በርሄ ገ/ማርያም
17.ኮሚሽነር መኮንን ካህሳይ ገ/መስቀል (ፅንቡላ) የትግራይ ክልል ፖሊስ ኮሚሽነር
18.ም/ኮሚሽነር መንግስቴ አረጋዊ የትግራይ ክልል ፖሊስ ም/ኮሚሽነር
19.ኮ/ር ጌታቸው ኪሮስ የትግራይ ፖሊስ አመራር የነበረ
20.ም/ኮሚሽነር ግርማይ ከበደ (ማንጁስ/ የፌደራል ፖሊስ ወንጀል መከላከል ዘርፍ ሃላፊ የነበረ 21.ም/ኮሚሽነር ተክላይ ፀሃዬ የፌደራል ፖሊስ ወንጀል መከላከል ዘርፍ ም/ሃላፊ የነበረ
22.ኮ/ር ንጉስ ወ/ገብርኤል የትግራይ ልዩ ሃይል ፖሊስ ሃላፊ፣
23.ኮ/ር ገ/ስላሴ ታፈረ የፌደራል ፖሊስ ወንጀል መከላከል አመራር የነበረ
24.ኮ/ር ፍስሃ ተ/ማርያም (ወዲአርባ) የፌደራል ፖሊስ ወንጀል መከላከል አመራር የነበረ
25.ኮ/ር ተስፋዬ ገ/ኪዳን (ተስፋዬ ባንዳ) የፌደራል ፖሊስ ወንጀል መከላከል አመራር የነበረ 26.ሜ/ጀነራል ገ/መድህን ፍቃዱ ሃይሉ (ውድነጮ) በቁጥጥር ስር የዋሉ
27.ሜ/ጀነራል ይርዳው ገ/መድህን ገ/ፃድቅ(አስቴር)በቁጥጥር ስር የዋሉ
28.ብ/ጀነራል ገ/ህይወት ሲስኖስ ገብሩ በቁጥጥር ስር የዋሉ
29.ብ/ጀነራል ኢንሶ እጃጆ እራሾ በቁጥጥር ስር የዋሉ
30.ብ/ጀነራል ፍስሃ ገ/ስላሴ እንሁን በቁጥጥር ስር የዋሉ
31.ኮ/ል ደሳለኝ አበበ ተስፋዬ በቁጥጥር ስር የዋሉ
32.ኮ/ል እያሱ ነጋሽ ተሰማ በቁጥጥር ስር የዋሉ

▪️በመጨረሻም የጁንታው ሕወሓት ወንበዴ ቡድን ተፈላጊዎችን በዝርዝር እየገለፅን የምንሄድ መሆኑን በዚህ አጋጣሚ የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን እናሳውቃለን፡፡
____
Jᴏɪɴ ᴏᴜʀ ᴛᴇʟᴇɢʀᴀᴍ ᴄʜᴀɴɴᴇʟ:👇
ቴሌግራም: 👉 https://t.me/ADDIS_MEREJAS

ሰበር!!የሰሜን ዕዝን የሬዲዮ መገናኛ በመጥለፍ የተጠረጠሩ 7 የጄኔራል መኮንኖች ፍርድ ቤት ቀረቡ። የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን የመከላከያ ሠራዊት ሰሜን ዕዝን የሬዲዮ መገናኛን በመጥለፍ እና የመ...
12/11/2020

ሰበር!!

የሰሜን ዕዝን የሬዲዮ መገናኛ በመጥለፍ የተጠረጠሩ 7 የጄኔራል መኮንኖች ፍርድ ቤት ቀረቡ።

የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን የመከላከያ ሠራዊት ሰሜን ዕዝን የሬዲዮ መገናኛን በመጥለፍ እና የመገናኛ ሥርዓት እንዲቋረጥ በማድረግ፣ ዕዙ በጁንታው የሕዋሓት የጥፋት ቡድን ጥቃት እንዲፈፀምበት ሲያመቻቹ ተገኝተዋል በሚል የጠረጠራቸውን 7 የጄኔራል መኮንኖች ዛሬ ፍርድ ቤት አቅርቧል።
ጄኔራል መኮንኖቹ በሀገር ክህደት እና ሕገ-መንግሥታዊ ሥርዓቱን በመናድ ወንጀል የተጠረጠሩ መሆናቸው ተገልጿል።
____
Jᴏɪɴ ᴏᴜʀ ᴛᴇʟᴇɢʀᴀᴍ ᴄʜᴀɴɴᴇʟ:👇
ቴሌግራም: 👉 https://t.me/ADDIS_MEREJAS

በሱማሌ ክልል ጅግጅጋ በሕወሓት ላይ የሚደረገውን ሕግ የማስከበር እርምጃ የሚደግፍ ሰልፍ ተከናወነ።____Jᴏɪɴ ᴏᴜʀ ᴛᴇʟᴇɢʀᴀᴍ ᴄʜᴀɴɴᴇʟ:👇ቴሌግራም: 👉 https://t.me/ADDIS...
12/11/2020

በሱማሌ ክልል ጅግጅጋ በሕወሓት ላይ የሚደረገውን ሕግ የማስከበር እርምጃ የሚደግፍ ሰልፍ ተከናወነ።
____
Jᴏɪɴ ᴏᴜʀ ᴛᴇʟᴇɢʀᴀᴍ ᴄʜᴀɴɴᴇʟ:👇
ቴሌግራም: 👉 https://t.me/ADDIS_MEREJAS

❤ መከላከያ በሰራዊታችን ለራሱ ሞቶ እኛን ያኖራል                                Respect 🙏____Jᴏɪɴ ᴏᴜʀ ᴛᴇʟᴇɢʀᴀᴍ ᴄʜᴀɴɴᴇʟ:👇ቴሌግራም: 👉 https://...
11/11/2020

❤ መከላከያ በሰራዊታችን ለራሱ ሞቶ እኛን ያኖራል

Respect 🙏
____
Jᴏɪɴ ᴏᴜʀ ᴛᴇʟᴇɢʀᴀᴍ ᴄʜᴀɴɴᴇʟ:👇
ቴሌግራም: 👉 https://t.me/ADDIS_MEREJAS

 መከላከያ ሰራዊት የትግራይ ልዩ ሀይል እና የትግራይ ሚሊሻ አባላት የጥፋት ቡድኑ ከለላ ከመሆን ይልቅ ለሀገር መከላከያ  እጃቸውን እንዲሰጡ አሳስቧል። እጃቸውን ለመከላከያ ሰራዊት የማይሰጡ ...
11/11/2020



መከላከያ ሰራዊት የትግራይ ልዩ ሀይል እና የትግራይ ሚሊሻ አባላት የጥፋት ቡድኑ ከለላ ከመሆን ይልቅ ለሀገር መከላከያ እጃቸውን እንዲሰጡ አሳስቧል።

እጃቸውን ለመከላከያ ሰራዊት የማይሰጡ ከሆነ መከላከያው "ያለምንም ቅድመ ሁኔታ" ለመደምሰስ እንደሚገደድ በዛሬው ዕለት በሰጠው መግለጫ አስጠንቅቋል።
____
Jᴏɪɴ ᴏᴜʀ ᴛᴇʟᴇɢʀᴀᴍ ᴄʜᴀɴɴᴇʟ:👇
ቴሌግራም: 👉 https://t.me/ADDIS_MEREJAS

የመከላከያ ኃይል በምእራብ ትግራይ ግንባር እየወሰደ ባለው ህግን የማስከበር እርምጃ እስካሁን 550 የህወሓት ታጥቂ ቡድን አባላት ተደምስሰዋል !በተጨማሪም 29 የልዩ ሃይል እና ሚኒሻ አባላት...
10/11/2020

የመከላከያ ኃይል በምእራብ ትግራይ ግንባር እየወሰደ ባለው ህግን የማስከበር እርምጃ እስካሁን 550 የህወሓት ታጥቂ ቡድን አባላት ተደምስሰዋል !

በተጨማሪም 29 የልዩ ሃይል እና ሚኒሻ አባላትም ተማርከዋል።

የፅንፋኛው ህውሓት ታጣቂ ቡድን በዚህ በግንባር ከፍተኛ ቁሳዊ ኪሳራ የደረሰበት መሆኑም ተነግሯል።

እስካሁንም 115 ክላሽንኮቭ ጠመንጃ፣ 11 መትረየስ፣ 2 ድሽቃ፣ 8 አር ፒጂ ከባድ መሳሪያ፣ 152 የእጅ ቦንብ፤ 2 ስናይፕር፣ 4 ኤም-14 ጦር መሳሪያ፣ 2 ኢንኮም ሬድዬ ተማርኳል።

በተጨማሪም 21 ሺህ 650 የክላሽ ጥይት፣ 14 ሸህ 730 የመትረየስ ጥይት፣ 1 የጦር ሜዳ መነፅር፣ 64 የጦር ሜዳ ቀበቶ፣ 6 የአር ፒ ጂ ቅንቡላ፣ 90 የክላሽ መጋዘን እና 10 የመትረየስ ዝናር ተማርኳል።

እንዲሁም ከስሜን እዝ 5ኛ ሜካናይዝድ ክፍለ ጦር ተዘርፈው የነበሩ 5 ታንኮች ሲመለሱ አንዱ ወድሞ፤ አንድ ታንክ በጠላት እጅ ይገኛል።

የስሜን እዝ ዋና አዛዥ ሜጀር ጀነራል በላይ ስዩም፥ ህግን የማስከበር ዘመቻው በስፋት እና በድል ተጠናክሮ መቀጠሉን ተናግራዋል።

የሰራዊቱ ተልእኮን የመፈፀም ብቃት ከየትኛውም ጊዜ በላይ አስተማማኝ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ የተናገሩት ዋና አዛዡ፥ ስራዊቱ ዳንሻ ትርካን ዲቪዥን ባእኸር ራውያንን እና የሁመራ ከተሞችን መቆጣጠሩንም ተናግረዋል።

©ፋና
____
Jᴏɪɴ ᴏᴜʀ ᴛᴇʟᴇɢʀᴀᴍ ᴄʜᴀɴɴᴇʟ:👇
ቴሌግራም: 👉 https://t.me/ADDIS_MEREJAS

‘የኤርትራ ወታደር ጥቃት እያደረሰብን ነው’ በሚል በደብረፂዮን ገብረሚካኤል የተሰጠው መግለጫ ፍፁም ሐሰት ነው ! "🗣ሜጀር ጄነራል መሐመድ ተሰማ “የኤርትራ ወታደር ጥቃት እያደረሰብን ነው በ...
10/11/2020

‘የኤርትራ ወታደር ጥቃት እያደረሰብን ነው’ በሚል በደብረፂዮን ገብረሚካኤል የተሰጠው መግለጫ ፍፁም ሐሰት ነው ! "

🗣ሜጀር ጄነራል መሐመድ ተሰማ

“የኤርትራ ወታደር ጥቃት እያደረሰብን ነው በሚል በደብረፂዮን ገብረሚካኤል የተሰጠው መግለጫ ፍፁም ሐሰት መሆኑን የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት ኢንዶክትሪኔሽን ዋና ዳይሬክተር ሜጀር ጄነራል መሐመድ ተሰማ ተናገሩ።

ሜጀር ጄነራል መሐመድ ለኢዜአ በሰጡት መግለጫ እንዳሉት፤ ጁንታው በተለያዩ አጋጣሚዎች ለማደናገር ጥረት እያደረገ ይገኛል።

ጁንታው ቀደም ሲል "በቂ ተዋጊ አለኝ፣ ሰሜን አዝም አብሮን ተሰልፏል፣ የመከላከያ ኃይሉን የጦር ጀቶች በሚሳኤል እንመታለን" የሚል ፉከራ ውስጥ እንደነበረ በማስታወስ፣ 'የትግራይ ምድር ለሚዋጉን ሁሉ መቀበሪያ ትሆናለች’ የሚል ዛቻም ያሰማ እንደነበር ገልጸዋል።

“አሁን ያ ሁሉ ፉከራ ነገር አልሳካ ብሎ በመከላከያ ኃይሉ አከርካሪው እየተሰበረ ሲመጣ ሌላ የማደናገሪያ ሐሳብ ይዞ ብቅ ብሏል” ሲሉ ተናግረዋል ሜጀር ጄነራል መሐመድ ተሰማ።

በመሆኑም ‘አሁን ላይ የኤርትራ ወታደር ጥቃት እያደረሰብን ነው’ በሚል በደብረፂዮን ገብረሚካኤል የተጠው መግለጫ ፍፁም ሐሰት መሆኑን ገልጸዋል።
____
Jᴏɪɴ ᴏᴜʀ ᴛᴇʟᴇɢʀᴀᴍ ᴄʜᴀɴɴᴇʟ:👇
ቴሌግራም: 👉 https://t.me/ADDIS_MEREJAS

አቶ ወርቁ አይተነው 100 ሰንጋ ለግሰዋል !አቶ ወርቁ አይተነው ለመከላከያ ሰራዊታችን፣ ለአማራ ልዩ ሀይል እና ለአማራ ፋኖ ግምታቸው 3 ሚሊየን ብር የሚያወጡ 100 ሰንጋዎችን አበርክተዋል።...
10/11/2020

አቶ ወርቁ አይተነው 100 ሰንጋ ለግሰዋል !

አቶ ወርቁ አይተነው ለመከላከያ ሰራዊታችን፣ ለአማራ ልዩ ሀይል እና ለአማራ ፋኖ ግምታቸው 3 ሚሊየን ብር የሚያወጡ 100 ሰንጋዎችን አበርክተዋል።

እንዲሁም አቶ በላይነህ ክንዴ 50 ሰንጋ ለግሰዋል

እናመሠግናለን🙏🙏
___
Jᴏɪɴ ᴏᴜʀ ᴛᴇʟᴇɢʀᴀᴍ ᴄʜᴀɴɴᴇʟ:👇
ቴሌግራም: 👉 https://t.me/ADDIS_MEREJAS

Address


Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Addis_መረጃ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

  • Address
  • Alerts
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share