መረጃ ኮሮና - Info Covid 19 Updates

  • Home
  • መረጃ ኮሮና - Info Covid 19 Updates

መረጃ ኮሮና - Info Covid 19 Updates Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from መረጃ ኮሮና - Info Covid 19 Updates, Media/News Company, .

11/12/2021
"አብዛኞቹ ጁንታዎች እጃቸውን ሰጥተዋል"  *ትግላችን በየገጠሩና በጫካው የተወሸጉ ለቅመን ወደ ህግ ማቅረብ ነው * ዳዊት ከበደ በህግ ይጠየቅልን * ጀነራል አበባው ታደሰ በትግራይ TV * የ...
29/11/2020

"አብዛኞቹ ጁንታዎች እጃቸውን ሰጥተዋል"
*ትግላችን በየገጠሩና በጫካው የተወሸጉ ለቅመን ወደ ህግ ማቅረብ ነው
* ዳዊት ከበደ በህግ ይጠየቅልን
* ጀነራል አበባው ታደሰ በትግራይ TV
* የማረኩት ማረካቸው!
* ሬድዮ በትግርኛ

ኢትዮጵያዊነት ከዘር በላይ ነው!!!

የትግራይ ልጅ የሆነው አክቲቪስት መለስ ብስራት

https://youtu.be/IxoWMlEQPOU

ሰበር መረጃ "አብዛኞቹ ጁንታዎች እጃቸውን ሰጥተዋል" የትግራይ ልጅ የሆነው አክቲቪስት መለስ ብስራት

16/08/2020
  CORONAVIRUS PANDEMICLast updated: Today April 22, 2020, 21:24 GMTCoronavirus Cases:    2,629,378Deaths:               ...
22/04/2020

CORONAVIRUS PANDEMIC
Last updated: Today April 22, 2020, 21:24 GMT

Coronavirus Cases: 2,629,378
Deaths: 183,520
Recovered: 716,580

በዓለም በኮሮና ወረርሽኝ ሕይወታቸውን ያጡ ሰዎች ቁጥር ከ101 ሺህ በላይ ሆነ---በዓለም ላይ በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ እስካሁን ሕይወታቸውን ያጡ ሰዎች ቁጥር ከ101 ሺህ 474 በላይ ሆኗል...
10/04/2020

በዓለም በኮሮና ወረርሽኝ ሕይወታቸውን ያጡ ሰዎች ቁጥር ከ101 ሺህ በላይ ሆነ
---
በዓለም ላይ በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ እስካሁን ሕይወታቸውን ያጡ ሰዎች ቁጥር ከ101 ሺህ 474 በላይ ሆኗል።

ቫይረሱ በ210 ሀገራት፣ ግዛቶችና ሁለት ዓለም አቀፍ መርከቦች ላይ ተከስቶ ከ1.6 ሚሊዮን በላይ ሰዎች ላይ ተዛምቷል።

እስካሁን ባለው መረጃም ወደ 372 ሺህ ገደማ የሚሆኑ የዓለማችን ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል።

ዛሬ ብቻ ዜናው እስከተጠናቀረበት ሰአት ድረስ በወረርሽኙ 4 ሺህ 758 በላይ ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል።

በአሁኑ ሰዓት ከዓለም በርካታ በወረርሽኙ የተያዙ ሰዎች የሚገኙት በአሜሪካ ሲሆን በሀገሪቱ እስካሁን ከ488 ሺህ 755 በላይ ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል፤ ከ18 ሺህ በላይ ሰዎችም ሕይወታቸውን አጥተዋል።

በስፔን በኮሮና ቫይረውስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከ157 ሺህ በላይ ደርሷል፤ እስካሁንም 16 ሺህ የሚሆኑ ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል።

በጣልያን እስካሁን በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከ147 ሺህ በላይ ደርሷል። ከእነዚህ ውስጥ 18 ሺህ 849 ሰዎች ሕይወት አልፏል። ይህም ጣሊያንን ከዓለም በርካታ ሰዎች በቫይረሱ የሞቱባት ሀገር አድርጓታል።

በጀርመን ከ119 ሺህ በላይ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ሲገኙ ከ2 ሺህ 600 በላይ ሰዎችም ለኅልፈት ተዳርገዋል።

ፈረንሳይም ከ124 ሺህ በላይ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ያሏት ሲሆን 4 ሺህ 32 ሰዎች ደግሞ ህይወታቸውን አጥተዋል።

ቻይና የኮሮና ቫይረስ መጀመሪያ የተከሰተባት ሀገር ብትሆንም ሥርጭቱን ለመቆጣጠር በወሰደችው እርምጃ ሥርጭቱ እንዳይስፋፋ በማድረግ በተነጻጻሪነት ስኬታማ ሆናለች።

በሀገሪቱ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከ81 ሺህ 900 በላይ ሲሆን ከእነዚህ ውስጥ ከ77 ሺህ በላይ ሰዎች ማገገም ችለዋል። ቻይና ውስጥ እስካሁን በቫይረሱ ምክንያት ሕይወታቸውን ያጡ ሰዎች ቁጥር 3 ሺህ 336 ነው።

10/04/2020

Report #28 🖤
በኮሮና ቫይረስ በሽታ ምክንያት በሀገራችን በዛሬው እለት ሦስተኛው ሰው ህይወት ማለፉን ስገልጽ በከፍተኛ ሀዘን ነው። ታማሚዋ በለይቶ ማቆያ ከመጋቢት 28 ጀምሮ ህክምና ሲደረግላቸው የነበርና ከገቡበት ቀን ጀምሮ በጽኑ ህሙማን ክፍል ክትትል ላይ የነበሩ ናቸው። በዚህም የተሰማኝን ጥልቅ ሀዘን በእራሴና በጤና ሚንስቴር ስም እየገለጽኩ ለቤተሰቦቻቸው እና ለወዳጅዘመዶቻቸው ልባዊ መጽናናትን እመኛለሁ።

It is with great sadness that I announce that we have lost a third patient from in Ethiopia. The patient was under strict medical follow up in the Intensive Care Unit. My sincere condolences to the family & loved ones

05/04/2020

የመጀመሪያው ሞት ተመዘገበ

በኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት የመጀመሪያው ሞት መመዝገቡን ኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አስታወቀ፡፡

በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 43 ደርሷል📌

ኢንስቲትዩቱ እንዳስታወቀው የኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) ህይወታቸውን ያጡት አንዲት የ60 ዓመት ታማሚ ናቸው፡፡

ታማሚዋ መጋቢት 19 ፣2012 ዓ.ም በኮሮና ቫይረስ በሽታ ምልክት ታይቶባቸው በለይቶ ማከሚያ ገብተው የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው የነበረ ሲሆን በመጋቢት 22፣2012 ዓ.ም የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው መረጋገጡን ኢንስቲትዩቱ ገልጿል፡፡

ይሁን እንጂ ታማሚዋ ከመጋቢት 22 አንስቶ ላለፉት ስድስት ቀናት በፅኑ ህክምና ላይ የነበሩ ሲሆን በዛሬው እለት ህይወታቸው ማለፉ ነው የተነገረው፡፡

ህብረተሰቡ በዚህ ሳይደናገጥ ለተለያዩ ጉዳዮች በአንድ ቦታ መሰባሰብን በማስወገድ፣ እጅን አዘውትሮ በመታጠብ፣ በአካል ንክኪ የሚደረግ ሰላምታን በመተውና አካላዊ መራራቅን (ቢያነስ አንድ ሜትር) ተግባራዊ በማድረግ የበሽታውን ስርጭት እንዲከላከልም የጤና ሚኒስቴርና የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አሳስበዋል፡፡

የጤና ሚኒስቴርና የኢትዮጵያ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት
በህልፈተ ህይወታቸው የተሰማቸውን ሀዘን እየገለጹ ለቤተሰቦቻቸውም መፅናናትን ተመኝተዋል፡፡

🛑 It is my deepest regret to announce the first death of a patient from in Ethiopia. The patient who was in critical condition after being admitted to Eka Kotebe hospital was in ICU care and strict medical follow up. My sincere condolences to the family and loved ones.
Via : Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)

05/04/2020

በኮቪድ19 ሕይወቷ ላለፈው ኢትዮጵያዊት ቤተሰብ እና ወዳጆች ከልቤ መጽናናትን እመኛለሁ።
ኢንጅነር ታከለ ኡማ

03/04/2020

የአርቲስት ሀናን ታሪክ መልእክት
JE 123 Studio

  : በሀገረ ፈረንሳይ በ24 ሰዐት ሪፖርቷ 1,120 ሞት ሪፖርት ያደረገች ሲሆን ከነዚህ መካከል 532 የሚሆኑት በ(Nursing Home) የነበሩ ፣ ከዚህ በፊት ያልተቆጠሩትን ይጨምራል። እ...
03/04/2020

: በሀገረ ፈረንሳይ በ24 ሰዐት ሪፖርቷ 1,120 ሞት ሪፖርት ያደረገች ሲሆን ከነዚህ መካከል 532 የሚሆኑት በ(Nursing Home) የነበሩ ፣ ከዚህ በፊት ያልተቆጠሩትን ይጨምራል። እንዲሁም 5,233 ሰዎች በዛሬው ዕለት ብቻ በቫይረሱ ተይዘዋል።

03/04/2020
03/04/2020

ድምፃዊ እሱባለው ይታየው

02/04/2020
‪የኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ ሁኔታ መግለጫ‬‪Status update on   ‬
02/04/2020

‪የኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ ሁኔታ መግለጫ‬

‪Status update on ‬

ዛሬ በአሜሪካን በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ የሞቱት ሰዎች ቁጥር 1,049 ገብቷል ከነዚህ ውስጥ ትልቁን የሟቾች ቁጥር የያዘው ከተማ ኒዮርክ ሲሆን እስካሁን የ 505 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ሞተዋ...
02/04/2020

ዛሬ በአሜሪካን በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ የሞቱት ሰዎች ቁጥር 1,049 ገብቷል ከነዚህ ውስጥ ትልቁን የሟቾች ቁጥር የያዘው ከተማ ኒዮርክ ሲሆን እስካሁን የ 505 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ሞተዋል::

01/04/2020

በሳምባ ኢንፌክሽን ዛሬ ማለዳ ህይወታቸው ያለፈው የ68 ዓመት ኢትዮጵያዊ የኮሮናቫይረስ እንዳልነበረባቸው በላብራቶሪ ምርመራ መረጋገጡ የጤና ሚኒስቴር ገለጸ።
Via : Natnael Mekonnen

Koronaa Ittisuuf/ኮሮናን ለመከላከልHerrega armaan gadiitiin waan dandeenye haa gumaannu!ከዝህ በታች ባሉት የህሳብ ቁጥሮች የአቅማችንን እንተባበር!
01/04/2020

Koronaa Ittisuuf/ኮሮናን ለመከላከል
Herrega armaan gadiitiin waan dandeenye haa gumaannu!
ከዝህ በታች ባሉት የህሳብ ቁጥሮች የአቅማችንን እንተባበር!

📌ሃያ ስድስት (26) ደርሷል 📌የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዛሬ ባካሄደው ተጨማሪ የላብራቶሪ ምርመራ አንድ (1) በኮሮና ቫይረስ የተያዘ ሰው በማረጋገጡ በአጠቃላይ በሀገራችን በ...
31/03/2020

📌ሃያ ስድስት (26) ደርሷል 📌
የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዛሬ ባካሄደው ተጨማሪ የላብራቶሪ ምርመራ አንድ (1) በኮሮና ቫይረስ የተያዘ ሰው በማረጋገጡ በአጠቃላይ በሀገራችን በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ሃያ ስድስት (26) ደርሷል፡፡

በቫይረሱ መያዙ የተረጋገጠው ግለሰብ የ42 ዓመት የድሬዳዋ ከተማ ነዋሪ የሆነ ኢትዮጵያዊ ሲሆን የአስገዳጅ ለይቶ ማቆያ ከመጀመሩ አስቀድሞ መጋቢት 9/2012 ከአውስትራሊያ አዲስ አበባ እንዲሁም መጋቢት 10/2012 ከአዲስ አበባ ወደ ድሬዳዋ ተጉዟል፡፡ ግለሰቡ የበሽታው ምልክት በማሳየቱ በላብራቶሪ ምርመራ በቫይረሱ መያዙ ተረጋግጧል፡፡ በአሁን ሰዓት ግለሰቡ በድሬዳዋ የለይቶ ህክምና መስጫ ማዕከል የህክምና እርዳታ እየተደረገለት ይገኛል፡፡

በአሁኑ ሰዓት በሀገራችን በለይቶ ህክምና መስጫ ማዕከል የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው ያሉ ሃያ ሁለት (22) ታማሚዎች ሲኖሩ ሁለት ታማሚዎች በጽኑ ህሙማን ህክምና ክፍል ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛል፡፡

ህብረተሰቡ የበሽታውን ስርጭት ግምት ውስጥ በማስገባት የመከላከያ መንገዶችን እና ከመንግስት የሚተላለፉ እርምጃዎችን ትኩረት በመስጠት እንዲተገበር እናሳስባለን፡፡

ለተጨማሪ መረጃ በነፃ የስልክ መስመር 8335 ወይም በ952 ወይም በመደበኛ የስልክ ቁጥር 0118276796 ወይም በኢሜል አድራሻችን [email protected] በመጠቀም ማግኘት ይቻላል፡

📌 ዶ/ር ሊያ ታደሰ
የጤና ሚኒስትር
መጋቢት 22 ፣ 2012 ዓ.ም

የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ፕሮፌሰር ሂሩት በአዲስ አበባ ጀሞ አከባቢ በመገኘት በዛሬው ዕለት ነዋሪዎችን የኮሮና ቫይረስ መከላከያ መንገዶችን በማስተማር ላይ ይገኛሉ።
31/03/2020

የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ፕሮፌሰር ሂሩት በአዲስ አበባ ጀሞ አከባቢ በመገኘት በዛሬው ዕለት ነዋሪዎችን የኮሮና ቫይረስ መከላከያ መንገዶችን በማስተማር ላይ ይገኛሉ።

ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ 66 የላብራቶሪ ምርመራ ተካሄዶ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ተጨማሪ ሶስት ሰዎች መኖራቸው ተረጋግጧል!በዚህም መሰረት በአጠቃላይ በሀገራችን በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር...
31/03/2020

ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ 66 የላብራቶሪ ምርመራ ተካሄዶ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ተጨማሪ ሶስት ሰዎች መኖራቸው ተረጋግጧል!

በዚህም መሰረት በአጠቃላይ በሀገራችን በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ሃያ አምስት ደርሷል፡፡ አንድ በበሽታው ተይዛለች ተብላ የነበረች ግለሰብ በተደረገላት ተደጋጋሚ ምርመራ ነፃ እንደሆነች ትናንት ተገልፆ ነበር።

Via Ministryof Health

30/03/2020


ኮሜድያን ደረጄ ሀይሌ

30/03/2020


ኡስታዝ አቡበከር

30/03/2020


አክቲቪስት ኦባንግ ሜቶ

30/03/2020


አርቲስት ግሩም ኤርሚያስ

30/03/2020

የአርቲስት ጥላሁን ጉግሳ መልዕክት

Good news   : የኮሮና ቫይረስ በሽታ (ኮቪድ-19)ን አስመልክቶ የጤና ሚኒስቴር አሁን ባወጣው መረጃ የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በተለያዩ ሆስፒታሎች በተኝቶ ማከሚያ ውስጥ...
30/03/2020

Good news

: የኮሮና ቫይረስ በሽታ (ኮቪድ-19)ን አስመልክቶ የጤና ሚኒስቴር አሁን ባወጣው መረጃ የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በተለያዩ ሆስፒታሎች በተኝቶ ማከሚያ ውስጥ ያሉ የከፍተኛ አጣዳፊ የመተንፈሻ አካል በሽታ ካለባቸው ሰዎች ላይ ናሙና በመውሰድ የኮሮና ቫይረስ ምርመራ እያደረገ እንደሚገኝ ተገልጽዋል፡፡

በመሆኑም፣

- ከዚሁ ጋር በተያያዘ ከቅዱስ ጴጥሮስ ሆስፒታል ከተወሰደ ናሙና ውስጥ አንዲት ታካሚ ላይ የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባት በመጀመሪያ የላብራቶሪ ምርመራ በመታወቁ ለሕብረተሰቡ መጋቢት 18፣ 2012 በተሰጠው መግለጫ ማሳወቃችን ይታወቃል ይላል መግለጫው፡፡

- ይህች 16ኛ ታማሚ የ24 ዓመት ኢትዮጵያዊት ስትሆን የውጭ ሐገር የጉዞ ታሪክ የሌላት እንዲሁም በበሽታ መያዙ ከተረጋገጠ ሰው ጋር ንክኪ ያልነበራት በመሆኑ በድጋሚ ሦስት ጊዜ በተደረገላት የላብራቶሪ ምርመራ ሦስቱም ውጤት ኔጌቲቭ በመሆኑ በቫይረሱ አለመያዟን ማረጋገጥ ተችሏል፡፡

- ይሁንና ታማሚዋ የቆየ ተጓዳኝ የጤና ችግር ያለባት በመሆኑ የሕክምና ክትትል እየተደረገላት ይገኛል፡፡

- ለታማሚዋ የሕክምና ክትትል ሲያደርጉላት የነበሩ የሆስፒታሉ ሰራተኞች እና ሌሎች ከእነርሱ ጋር ግንኙነት የነበራቸው በድምሩ 24 ሰራተኞች ለጥንቃቄ ሲባል በተዘጋጀው ለይቶ ማቆያ ውስጥ ክትትል እየተደረገላቸው እንዲቆዩ የተደረገ ሲሆን በሚቀጥሉት ቀናት ወደ ሥራ ገበታቸውና ቤተቦቻቸው የሚመለሱ ይሆናል ይላል መግለጫው፡፡

CNC፣ CCTV፣ CGTN እና Xinhua የተባሉ የቻይና ሚድያ ጣብያዎችን ዛሬ ስከታተል እንዳየሁት በርካታ ቻይናውያን የጤና ባለሙያዎች ቫይረሱን ለመዋጋት በአለም ዙርያ እየተሰማሩ ነው! እነ...
30/03/2020

CNC፣ CCTV፣ CGTN እና Xinhua የተባሉ የቻይና ሚድያ ጣብያዎችን ዛሬ ስከታተል እንዳየሁት በርካታ ቻይናውያን የጤና ባለሙያዎች ቫይረሱን ለመዋጋት በአለም ዙርያ እየተሰማሩ ነው!

እነዚህ ቻይና ውስጥ በሚገርም ሁኔታ ቫይረሱን የተዋጉ ልምድ ያላቸው ባለሙያዎች ከአሜሪካ እስከ ፓኪስታን እየዘመቱ ነው። የእርዳታ ተቀባይ ሀገራት መሪዎች አየር ማረፊያ ድረስ በመሄድ ለቻይናዎቹ ባለሙያዎች ተገቢ አቀባበል እያረጉ ነው።

የቻይናን እርዳታ በዚህ ሰአት የማይፈልግ የለም።

መንግስትም እነዚህ የጤና ባለሙያዎች ወደ ሀገራችን እንዲመጡ ጥሪ ቢያቀርብ መልካም አይመስላችሁም?
Via : Elias Meseret

ወጣቶች ቤት እንሁን፤ ህይወት እናድን!አስፈላጊ ካልሆነ በቀር  'ከቤት ባለመውጣት'  የሰዎችን  ህይወት ልንታደግ ፣ ወገኖቻችን በሽታ ላይ እንዳንጥል እና የጤና ባለሞያዎቻችን ላይ የሚደርሰው...
29/03/2020

ወጣቶች ቤት እንሁን፤ ህይወት እናድን!

አስፈላጊ ካልሆነ በቀር 'ከቤት ባለመውጣት' የሰዎችን ህይወት ልንታደግ ፣ ወገኖቻችን በሽታ ላይ እንዳንጥል እና የጤና ባለሞያዎቻችን ላይ የሚደርሰውን ፈተና ልንቀንስ ይገባል። በተለይ ወጣቶች ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ወደቤታችሁ የተመለሳችሁ ይህን ፈታኝ ወቅት እስክናልፍ ድረስ ቤታችሁ ቁጭ በሉ!

[Siyumeegziabher shawl - GRAPHICS]

  : በኢትዮጵያ በኮሮናቫይረስ የሞተ አንድም ሰው እንደሌለ እና ህብርተሰቡ ራሱን ከሀሰተኛ ዜናዎች መጠበቅ እንዳለበት የኢፌዴሪ የጤና ሚኒስቴር ገለፀ።አሁን ላይ በአለማችንም ሆነ በአገራችን ...
29/03/2020

: በኢትዮጵያ በኮሮናቫይረስ የሞተ አንድም ሰው እንደሌለ እና ህብርተሰቡ ራሱን ከሀሰተኛ ዜናዎች መጠበቅ እንዳለበት የኢፌዴሪ የጤና ሚኒስቴር ገለፀ።

አሁን ላይ በአለማችንም ሆነ በአገራችን ከኮሮና ቫይረስ ስርጭት ባልተናነሰ ፍጹም ከእውነት የራቁና ምንጫቸው ያልታወቁ የሀሰት መረጃዎች በማህበራዊ የትስስር ገጾች እየተለቀቁ መሆኑን ሚኒስቴሩ ማምሻውን ባወጣው መግለጫ አስታውቋል፡፡

የተሳሳተ መረጃን መልቀቅም ሆነ ተቀብሎ ማሰራጨት ከተፈጠረው ቀውሱ እኩል ስነ ልቦናዊና ማህበራዊ ችግሮችን ያስተከትላልም ነው ያለው

በመሆኑም ይህ አይነት እኩይ፣ ኢ-ሞራላዊና ህገ ወጥ ድርጊትን ሁሉም በጥብቅ ሊያወገዘውና ሊከላከለው ይገባል።

ይህን የሀሰት መረጃ በማመን ህብረተሰቡ እንዳይደናገጥና እንዳይደናገር በማሳሰብም መረጃዎችን በማዛባት የሚያሰራጩ ኃላፊነት የጎደላቸውን ግለሰቦችና ቡድኖችንም በማጋለጥና ለህገ በማቅብ በጋራ መከላከል ይገባናል ብሏል፡፡

ኮቪድ-19ን በተመለከተ መንግስት ወቅታዊና ትክክለኛ መረጃዎችን በማደራጀት በየዕለቱ የማሠራጨት ሥራን እያከናወነ መሆኑንም አስታውቋል።

ስለሆነም ማህበረሰቡ ወቅታዊ እና ትክክለኛ መረጃ በመከተል እና በመጠቀም በሽታውን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር የሚደረገውን ጥረት በተረጋጋ አካሄድ እንዲያግዝ ጥሪ አቅርቧል

Via

የኮሮና ቫይረስ ተጠቂዎች 21 ደረሱ! የታማሚዎች ሁኔታ፦ የ38 ዓመት ወንድና የ35 ዓመት ሴት የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪ ኢትዮጵያውያን ናቸው። ሁለቱም  ግለሰቦች በተለያየ ቀናት ወደ ዱባይ ...
29/03/2020

የኮሮና ቫይረስ ተጠቂዎች 21 ደረሱ! የታማሚዎች ሁኔታ፦ የ38 ዓመት ወንድና የ35 ዓመት ሴት የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪ ኢትዮጵያውያን ናቸው። ሁለቱም ግለሰቦች በተለያየ ቀናት ወደ ዱባይ የጉዞ ታሪክ የነበራቸውን ሲሆን የበሽታው [ኮቪድ-19] ምልክት በማሳየታቸው የላብላቶሪ ምርመራ በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።
Via : Natnael Mekonnen

29/03/2020

: የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል ያለው ብቸኛው አማራጭ በመንግሥት እና በጤና ሚኒስቴር እየተላለፉ ያሉትን ውሳኔዎች እና የጤና ምክሮች መተግበር ይገባል።

የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ህክምና ኮሌጅ ባለሙያዎች መልዕክት!

በሕንድ(ማላንካራ) ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን የሰሜን ምሥራቅ አሜሪካ ሊቀ ጳጳስ ብጹዕ አቡነ ዘካርያስ የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸው ወደ ለይቶ ማቆያ ተወሰዱ። ሀገረ ስብከቱ እንደገለፀው ብጹዕ...
29/03/2020

በሕንድ(ማላንካራ) ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን የሰሜን ምሥራቅ አሜሪካ ሊቀ ጳጳስ ብጹዕ አቡነ ዘካርያስ የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸው ወደ ለይቶ ማቆያ ተወሰዱ።
ሀገረ ስብከቱ እንደገለፀው ብጹዕነታቸው በደኅና ሁኔታ ውስጥ ናቸው።
(ዳንኤል ክብረት)

28/03/2020
የፊት ማስክ በሚጠቀሙበት ወቅት ልብ ሊሏቸው የሚገቡ ነጥቦች፡፡የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት☎8335 ☎952አዲስ ሚድያ ኔትወርክ (ኤ ኤም ኤን) መጋቢት 18፤2012
28/03/2020

የፊት ማስክ በሚጠቀሙበት ወቅት ልብ ሊሏቸው የሚገቡ ነጥቦች፡፡

የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት

☎8335 ☎952

አዲስ ሚድያ ኔትወርክ (ኤ ኤም ኤን) መጋቢት 18፤2012

Address


Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when መረጃ ኮሮና - Info Covid 19 Updates posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to መረጃ ኮሮና - Info Covid 19 Updates:

Videos

Shortcuts

  • Address
  • Alerts
  • Contact The Business
  • Videos
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share