Ethio Addis Mereja

  • Home
  • Ethio Addis Mereja

Ethio Addis Mereja Ethio Addis Mereja brings New Information and delivers unseen, unheard and untouched issues to the public by visiting different sections of the community! If

If you are new to our channel, subscribe now and become a family! If you like our work, like it!

08/05/2024

Shout out to my newest followers! Excited to have you onboard! Tsa Econm, Yidnekachew Lemma, Kafale Waktole, Zergaw Masresha, ከመከም ውሎ የው, YA YA, Tarekegn Gebre, Tofik Hassen, Haile Yemariam Lij, Solomon Kata Gita, Mam Makaye, Habtamu Kanmi, Mehabub Bargicho, Dagne Girma, Fuad Bahamud, Nuredin Oumer Birllea, Bedlu Haylu, Hk Hassen

ሴት መስሎ ከፖሊስ ለማምለጥ የሞከረው ተጠርጣሪ    | ጀልባ በመስረቅ የተጠረጠረው የ33 ዓመቱ የፍሎሪዳ ወጣት ዊግ፣ ቀሚስ እና ትልቅ የፀሐይ መነፅር በመጠቀም ሴት መስሎ ከፖሊስ ለማምለጥ ...
07/05/2024

ሴት መስሎ ከፖሊስ ለማምለጥ የሞከረው ተጠርጣሪ

| ጀልባ በመስረቅ የተጠረጠረው የ33 ዓመቱ የፍሎሪዳ ወጣት ዊግ፣ ቀሚስ እና ትልቅ የፀሐይ መነፅር በመጠቀም ሴት መስሎ ከፖሊስ ለማምለጥ ቢሞክርም ሳይሳካለት ቀርቷል።

አሜሪካዊው ጆሹዋ ኮሎትካ በጀልባ ስርቆት መጠርጠሩን ተከትሎ ከፖሊስ ለማምለጥ አለኝ የሚለውን መላ ቢዘይድም ሳይሳካለት በቁጥጥር ስር ውሏል።

ለስርቆቱ ተጠርጣሪ ነው ተብሎ በተገለጸው ግለሰብ ቤት አካባቢ መርማሪ ፖሊሶች በመቃኘት ላይ እያሉ ሰማያዊ ቀሚስ የለበሰች፣ ነጭ ጋውን የደረበች እና ትልቅ መነጽር ያደረገች አንዲት ሴት ከቤት ስትወጣ ያስተውላሉ።

ግራ የተጋቡት መርማሪዎቹ ሴትዮዋን አስቁመው ፈተሿት። ተፈታሹ የሴት ልብስ የለበሰ ወንድ ለዚያውም ጀልባ በመስረቅ የተጠረጠረው ጆሹዋ ኮሎትካ ሆኖ ተገኘ። ወዲያውኑ በቁጥጥር ስር ዋለ።

የግለሰቡ እንደ ሴት የለበሰበት ፎቶ እና ትክክለኛ የቀድሞ ፎቶው በማኅበራዊ ሚዲያ እየተዘዋወረ መነጋገሪያም ሆኗል።

...........እንዴት ነው ነገሩ?........የዚህ ፅሁፍ ሀሳብ ወዲህ የእኛን ቤት ለመደገፍ ወዲያ ያለውን የወዳጆቼን ቤት ለመንቀፍ ዓላማ ያደረገ አይደለም!! /ግለሰቦችን ከተቋማት ጋር ...
02/05/2024

...........እንዴት ነው ነገሩ?........
የዚህ ፅሁፍ ሀሳብ
ወዲህ የእኛን ቤት ለመደገፍ ወዲያ ያለውን የወዳጆቼን ቤት ለመንቀፍ ዓላማ ያደረገ አይደለም!!
/ግለሰቦችን ከተቋማት ጋር እየለየን ከነቀፍን ተቋማቱ አጥራቸው ሳይነቀነቅ…ደጃቸው ሳይደፈር …ስማቸው ሳይጎድፍ ይዘልቃሉ!!!/
ሁሉም ቤት እሳት አለ!! ይህን ከግምት ማስገባት ተገቢ ነው!!
በእነዚህ እና ጥቂት እነዚህ በመሳሰሉ ሰዎች ጉዳይ ላይ ከእምነቱ ተከታዮች ጋር በብዙ መልኩ አውርቼ አውቃለሁ! የሚደንቀው ነገ ጉዳዩን የተነጋገርኳቸው ግለሰቦች ሁሉ ሀሳቤን ይጋራሉ! እነዚህ አጥር አሰባሪ ቤት አሰዳቢዎች ናቸው …!
ይህን ጉዳይ ሌላ ጊዜ ልመለስበት እና ይህ ፎቶ የሚናገረው ነገር ላይ ብቻ ላትኩር!
አንድ ነብይ እንዴት አድርጎ ነው ክርስቶስን ያህል ጌታ …ዋናው ዓለት! እንዲያ በትህትና ወርዶ የሐዋሪያቱን እግር እንዳጠበ አረስቶ ዛሬ እርሱ ምዕመኖቹን እንዲያጥቡት የሚያደርገው?........

24/04/2024

በኢትዮጵያ የኪነ ጥበብ ኢንዱስትሪ ውስጥ ስማቸውን በደማቁ ቀለም እያሰመሩ የሄዱ ብዙ አንጋፋ እና ወጣት ከያነያን አሉን፡፡አሁን አሁን እጅግ እየበዙ ከመጡ ብዙ የድራማ እና የፊልም ተዋ...

https://youtu.be/AJ3X8_qYK80?si=obLXyznfHqg_D94V
24/04/2024

https://youtu.be/AJ3X8_qYK80?si=obLXyznfHqg_D94V

በኢትዮጵያ የኪነ ጥበብ ኢንዱስትሪ ውስጥ ስማቸውን በደማቁ ቀለም እያሰመሩ የሄዱ ብዙ አንጋፋ እና ወጣት ከያነያን አሉን፡፡አሁን አሁን እጅግ እየበዙ ከመጡ ብዙ የድራማ እና የፊልም ተዋ...

አርቲስት አማኑኤል ሐብታሙ ለምን ታሰረ?ወደ አመሻሽ ላይ በስራ ጥድፊያ መሐል ሳለሁ ደወለልኝ።"... አስቸኳይ ነው። ለምን እንደሆነ እንጃ እቃዎቼን መልሰዋቸዋል። እኔንም እንፈልግሀለን ብለው...
23/04/2024

አርቲስት አማኑኤል ሐብታሙ ለምን ታሰረ?
ወደ አመሻሽ ላይ በስራ ጥድፊያ መሐል ሳለሁ ደወለልኝ።
"... አስቸኳይ ነው። ለምን እንደሆነ እንጃ እቃዎቼን መልሰዋቸዋል። እኔንም እንፈልግሀለን ብለው እስከ አሁን ይዘውኛል። የአውሮፕላን መነሻ ሰዓቱም ሊያልፍብኝ ነው"
- እንዴ!.. ለምን?
"እኔ እንጃ ኤርፖርት ውስጥ ነው እስከ አሁን ያለሁት። ጉዞዬ ከደቂቃዎች በኋላ ነው። ግን እስከ አሁን ጠብቅ! ብለው ይዘው እንዳቆዩኝ ነው"
ከአማኑኤል ሐብታሙ ጋር መጠነኛ መረጃዎች ከተቀያየርን በኋላ አንድ አንድ ነገሮችን አጣርቼ በቶሎ መልሼ እንደምደውልለት ከነገርኩት በኋላ ስልኩ ተቋረጠ።
ከደቂቃዎች በኋላ መልሼ ስደውል ስልኩ ተዘግቷል። በተደጋጋሚ ብሞክርም ያው ነው።
ከቤተሰቦቹ ባገኘሁት መረጃ መሰረት ይህንን ማስታወሻ እስካሰፈርኩበት ሰዓት ድረስ አማኑኤል ፖሊሶች ወደ አዲስ አበባ ፖሊስ መምሪያ ወስደውት በእስር ላይ ይገኛል።
ቤተሰቦቹ ራት እንዳደረሱለት እና በፖሊስ ስለተያዘበት ጉዳይ እርሱም ይሁን በሕግ ስር የዋሉት ፖሊሶች ምንም አይነት መረጃ እንዳልሰጧቸው አረጋግጫለሁ።
አማኑኤል ሐብታሙ "እብደት በሕብረት" የተሰኘውን ተወዳጅ አዲስ ባለ አንድ ሰው የሙሉ ሰዓት ቴአትሩን እስራኤል አገር ለሚገኙ ተመልካቾች ለማሳየት በጉዞ ላይ ሳለ ዛሬ ሚያዝያ 15 ቀን 2016 ዓ/ም አመሻሽ ላይ በኢትዮጵያ አየር መንገድ ውስጥ በፖሊስ ተይዞ ወደ እስር ቤት ተወስዷል።
ለእስር ያበቃው ጉዳይ ምን እንደሆነ የተገለጸ ነገር ባይኖርም፤ እስራኤል ውስጥ ነስ ጽዮና በተባለ ከተማ ትልቅ ቴአትር ቤት የፊታችን ሐሙስ ትርዒቱን ለማቅረብ ዝግጅቱን አጠናቆ አውሮፕላን ለመሳፈር አየር ማረፊያ ደርሶ ነበር።
ከ400 በላይ ተመልካቾች ትኬቱን በቅድሚያ ቆርጠው፣ በጠቅላላው ከ750 በላይ ተመልካቾች የሚታደሙበትን ዝግጅት ለማቅረብ በጉጉት እየተጠበቀ በድንገት ምክንያቱ ባልተገለጸ ሰበብ ለእስር መዳረጉን ለመረዳት ችያለሁ።
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ "እያዩ ፈንገስ ቁጥር 2"ን ጨምሮ የተለያዩ የኪነጥብ ዝግጅቶች ከመድረክ እንዲወርዱ እና ዕይታቸው እንዲስተጓጎል የተደረገበት አታካች አካሄድ በአዲሱ "እብደት በሕብረት" ተውኔት ላይ ተደርጎ ይሁን አይሁን ለጊዜው የታወቀ ነገር ባይኖርም፤ ተቋማዊ ድጋፍ ሳይደረግለት በግል ጥረት ዘውትር በታላቅ ትግል የሚከወነው የኢትዮጵያ ኪነጥበብ ትልቅ ጋሬጣ የሚፈጥሩ ተደጋጋሚ ሳንካዎች መከሰታቸው ለጥበብ ሙያተኞች አንገት የሚያስደፋ ሆኗል።
ብዙ ውጪ ወጥቶበት ለዕይታ ለመቅረብ ጫፍ ላይ የደረሰው ይህ ተውኔት በተወዳጁ ተዋናይ ላይ ከደረሰበት ድንገተኛ እስር ባሻገር ተዋናዪን እና አዘጋጆቹን ለኪሳራ የሚዳርግ አጋጣሚ በመፈጠሩ በእጅጉ የሚያሳዝን ሆኗል።
አማንን በቅርብ የሚያውቁ ሁሉ በስነ ምግባር የታነጸ፣ ሙያውን እለት ከዕለት በማሳደግ ምስጉን የኾነ ተዋናይ መኾኑን ይመሰክሩለታል።
በፍጥነት ከእስር ተለቆ ጉዞውን በማካሄድ አክበረውት በጉጉት ከሚጠባበቁት ተመልካቾች ጋር እንደሚገናኝ ተስፋ በማድረግ ባለበት ፈጣሪ እንዲጠብቀው እመኛለሁ።
ግን ለምን?

Via ያሬድ ሹመቴ

በወላይታ ዞን ክብር ለፖሊሶቻችን 👏👏👏ንስሮቹ የዳሞት ሶሬ ወረዳ ፖሊስ አባላት በጉሩሞ ላዲሳ 01 ቀበሌ አንድት ወጣት ከቤተሰቦቿ ጋር ባለመግባባት በተፈጠረው ጭቅጭቅእራሷን ለማጥፋት አቮካዶ ...
23/04/2024

በወላይታ ዞን

ክብር ለፖሊሶቻችን 👏👏👏

ንስሮቹ የዳሞት ሶሬ ወረዳ ፖሊስ አባላት በጉሩሞ ላዲሳ 01 ቀበሌ አንድት ወጣት ከቤተሰቦቿ ጋር ባለመግባባት በተፈጠረው ጭቅጭቅ

እራሷን ለማጥፋት አቮካዶ እንጨት ላይ ብትወጣም ፖሊሶች ግን ጥበብን ተጠቅመው ልጅቷን ከወጣችበት በሰላም አወርደዋታል

ፖሊሶች ላደረጉት የነፍስ ማዳን ሥራ👏👏👏

አገልጋይነት በተግባር👏👏👏


Via Muluken Zakarias ከስፍራው

ምክን ትውልድ!!ክሽፈት!!!ሀገር የነገ ተስፋዋን አዲሱ ትውልዷ ላይ መጣል ካልቻለች ብላሽ ነች! ይህ የማይክዱት ሀቅ ነው! በየትኛውም ዓለም ላይ ለሚኖሩ ሀገራት የነገ ተስፋቸው አዲሱ ትውልድ...
19/04/2024

ምክን ትውልድ!!
ክሽፈት!!!
ሀገር የነገ ተስፋዋን አዲሱ ትውልዷ ላይ መጣል ካልቻለች ብላሽ ነች! ይህ የማይክዱት ሀቅ ነው! በየትኛውም ዓለም ላይ ለሚኖሩ ሀገራት የነገ ተስፋቸው አዲሱ ትውልድ ነው፡፡ አንድ ትውልድ በአጋጣሚ ቢያልቅ ሀገር አትቀጥልም፡፡ትውልድ በብዙ መልኩ ይጠፋል! በስነ ምግባር የጠፋ ትውልድ ደግሞ የሀገርን ውድቀት ቁልቁል ወርውሮ ያጣድፈዋል!!
ሀገር እያደር ክምር ቁልል ድንጋይ ብታሳምር …ሳር ቅጠሉን ብታለመልም …መንገድ ብታሰፋ …ከተማ ብታስውብ …ትውልዱ ላይ ግና አንዳችም ነገር ካልሰራች ከአናቷ እንጂ አምራ ደምቃ የምትታይ ከመሰረቷ ባዶ መሆኗ እሙን ነው፡፡
ትላንት ከትላንት ወዲያ በዚህ መከረኛ ፌስ ቡክ ላይ ተለጥፎ ሲመላለስ ያየሁት አንድ ቪዲዮ መንፈሴን ቢሰብረው ነው ይህን ማለቴ ፡፡ እኚህ ምስሉ ላይ የምትመለከቷቸውን ሰው እንዲህ እንደ ማርያም ጠላት ከቦ በሽመልም በጥፊም አያሉ ማዋከብ ምን ይሉት ጭካኔ ነው፡፡
አሁን የእውነት ማን ይሙት አንድን ሰው ሊያውም የራስን ወገን…የራስን ወንድም …እንዲህ ባይተዋር አድርጎ መግረፍ ምን ይሉት ነገር ነው…. ይህ ነው እንደ ሕዝብ ….እንደ ሀገር የሚያኗኑረው …እንዲህ ያለውን ወጣት ማሳደግ ነው ሀገርን የሚያከርማት ….ጎበዝ እየከሸፈን ነው፡፡
እርግጥ ነው ይህን ቪዲዮ ስላየነው እንጂ ልባችን የተሰበረ …ሳናያቸው …የገደሉ፣የፈለጡ፣የቆረጡ ብዙ ናቸው፡፡ እኔ ኢትዮጵያዊ መሆኔ ላይ እፍረት ተሰምቶኝ አያውቅም!! የመጣሁበትን ቤተሰብ እና ማህበረሰብ ስናፍቀው የምኖር ሰው ነኝ፡፡ ያም ሆኖ ግን ሀገሬ ላይ ሰው ተዘቅዝቆ ሲገደል፣ከነ ሕይወቱ ሲቃጠል፣ፈቅዶ ወዶ ባላመጣው ማንነቱ ሲሳደድ ካየሁ በኃላ ግን ሀገሬ ተረት እየሆነችብኝ ነው፡፡
አለ አይደል አንዲት ኢትዮጵያ የምትባል እንግዳ ተቀባይ …ሀገር ነበረች …ተብሎ ተረት እንደሚነገር ሁሉ …የተረት ሀገር ሰዎች ሆነን ቀርተናል፡፡
እኛን አባት ሆናችሁ አስቡት ሀገሬ ነው ብለው …አቃፊም ደጋፊም ነው ከሚባለው ማህበረሰብ መንደር ሊሰሩ አልያ እግር ጥሏቸው ሄዱ እናም የሆነውን አየነው! እኚህ አባት ምናልባት ደብዳቢዎቹን የሚያካክሉ ወጠምሾች ያደረሱ …አልያ ደግሞ አባባ ወተት ይዞ ይመጣል ብለው ደጅ ደጅ የሚያዩ ህፃናትም ይኖራቸው ይሆናል፡፡
ከክስተቱ ማዶ አሻግሮ የሚያየውስ ሕፃን ሲያድግ ምን ይዞ ነው?…….
እሺ ግድ የለም ሰርቀውም ሊሆን ይችላል እንበል ወይ ደግሞ ያልተገባቸውን ነገር አድርገው …እንዲያም ቢሆን ወደ ፖሊስ ጣቢያ ወስዶ ለሕግ መስጠት የአባት ነው፡፡
ይህ በዘር የተዘራ የዘር ፖለቲካ ከፍሬው ልቆ አረሙ ቀድሞ እየጎመራ ነው!! ጎበዝ ስው መሆን ይቀድማል!!
የሰማነው እውነት ከሆነ ይህን ያደረጉ ግለሰቦች ተይዘዋል ! መያዛቸው ሸጋ ነገር ሆኖ ሳለ! ትውልዱን ግን እንዲህ አግድም አደግ ሆኖ እንዳያድግ በዓለሙም ሆነ በሃይማኖታዊው ውስጥ ስለ ግብረ ገብነት ማስተማሩ ነው ሀገርን የሚያከርማት!!

...............................ልሸቀትም ….ውርደትም ነው!!..................ይገርማል በጣም!!እኔ እምለው  ለምንድ ነው አንዳንድ ሰዎች መንቀፍን እና ማቅለልን ...
14/04/2024

...............................ልሸቀትም ….ውርደትም ነው!!..................
ይገርማል በጣም!!
እኔ እምለው ለምንድ ነው አንዳንድ ሰዎች መንቀፍን እና ማቅለልን ለዕውቀታቸው መለኪያ መሳሪያ አድርገው የሚያስቡት?.......
ዌል ....በቅን ሀሳብ እና በተነጠረ ዕውቀት ይህ ልክ አይደለም …እንዲህ ያለው ነገር ላይ ይህ ግብዓት ቢጨመር እንዲያ ያለ ውጥዓት/output/ ሊያመጣ ይችላል የሚል ቀና እና ገንቢ ሀሳብ መስጠት የአባት ነው፡፡ ከዛ በመለስ ግን አውቃለሁም …አለሁም ለማለት የማያስቅፈውን በመንቀፍ እና በማጥላላት የተጠመዱ ሰዎችን ሳይ ግን ግርምምም ይለኛል!!!
አሁን እንደው ማን ይሙት የበዛ ወርቅ እንዲህ ያለ ልብ ስብር የሚያደርግ መዝሙር ማውጣት ያስነቅፋል?….. አጃኢብ እኮ ባካችሁ!!!
ትላንት ዘፈነች …እኛም …በትዝታዎቿም ተክዘን …በአዝናኙም ስራዋ ተዝናንተን ነበር፡፡ዛሬ ደግሞ መጨረሻዬ አሳሰበኝ …ዓለም በቃችኝ …ብላ አምላኳን ደጅ ጠናች….ጠናችናም ….የልቧን ውስጥ ስጋት …ፍርሃቷን ….እኔ ያንተ ባሪያ ባከበርከኝ ልክ …ሳልከብር …የትም ሜዳ ስዋልል …ስዋትት… ከርሜ …ሲመሽብኝ ….በዓለም ድካም ጉልቤቴ ሲዝል …ከእቅታዬ በፊት ለይቅርታ ደጅህ መጣሁ …እናም ይቅር በለኝ ብሎ ማለት …..ምኑ ነው የሚያስኮንነው?…
አንዱ እኮ ነው ከዚሁ መንደር /ብዙ አውቃለሁ፣አነባለሁ/የሚል ሰው ነው ደግሞ ፡፡
የትም ጨፍራ ሲበቃት …ዘፈኑ ሲያልቅባት …በመዝሙር ልትሸቅል መጣች የሚል የልጅም የጅልም ሀሳብ ብጤ ጫጭሮ …መመለሷን ሊመፃደቅበት ሲሞክር አይቼ በግኜ ነው ይህን መፃፌ ፡፡
እውነት ለማውራት በዛር ወርቅ መዝሙሯን የሰራቸው ለራሷም ብቻ አይመስለኝም፡፡ እንደ እኔ ላለን በዓለም ክፋት በብዙ ለምንመላለስ ሰዎች ነው፡፡ መዝሙሯን ሰምቶ የራሱ ሁኔታ የማያሳስበው አማኝ ቢኖር ይህ የተመፃደቀባት ሰው ብቻ ይመስለኛል፡፡ ሰው እንዴት በራሱ ዕውቀት ይመፃደቃል?….እንደምን የመጀመሪያውን ጠጠር አንስቶ ሊወረውር ተጣደፈሳ?
ወዳጄ ሀጥያታችን እንደጠጉራችን እየበቀለብን የሚታይ ቢሆን ኑሮ ከቤትም አትወጣም ነበር፡፡ ይቅር ይበልህ!!!
እንደ ጴጥሮስ ፀፀት እንደ ማርያም መቅደላዊት ያለ የመማር ፍላጎት /ይቅር የመባል/ ሲኖርህ ሸጋ ነው…ያንተ ዕውቀት …የዚህ ዓለም ንባብ እንዲህ ያለውን የልብ መሰበር እንድትረዳ ካላደረገህ ከፎረሽክ ሰንብተሃል ማለት ነው!!! ወርደኃል ወዳጄ …
ይህ ልሸቀትም ውርደትም ነው….ከንቱ ዕውቀት!!!!

........ልጆችን በልጅነት ጥብቆ .....ይህች ልጅ ዛሬ በየ ማህበራዊው ሚዲያ እየተመላለሰች ያለ አቅሟ ስትብጠለጠል አየሁና ምን አድርጋ ይሆን ብዬ የቀረበችበትን መሰናዶ አየሁት፡፡ እናም...
08/04/2024

........ልጆችን በልጅነት ጥብቆ .....
ይህች ልጅ ዛሬ በየ ማህበራዊው ሚዲያ እየተመላለሰች ያለ አቅሟ ስትብጠለጠል አየሁና ምን አድርጋ ይሆን ብዬ የቀረበችበትን መሰናዶ አየሁት፡፡ እናም ለካ ሕዝቤ እንዲህ ከፍ ዝቅ እያደረገ የወቀሳት ለዚህ ነው ብዬ አልኩና እኔም የእውነት የተሳመኝን ነገር ለማለት ሲዳዳኝ ከኔ በፊት በሷ ጉዳይ ብዙ ያሉ ሰዎች አሉ እና የእኔን ሀሳብ ለራሴው ፍጆታ አውዬው አለፍኩ፡፡ ቆይቼ አሁንም ፋታ ሳገኝ ወደዚያው መንደር ስመለስ …አንድ ሰው አብዛኞቹን በልጀቱ እና በቤተሰቦቿ ላይ እንዲሁም በቴሌቪዥኝ ጣቢያው ላይ ትችት ያቀረቡትን ሰዎች ሲነቅፍ አነበብኩ፡፡ እናም ሰውዬው ምን እያለ ነው ስል እራሴን ጠይቄ…እኔም ከጹሑፉ ስር የራሴን ሀሳብ አሰፈርኩለት፡፡ ደግሞ ማምሻዬንም ወደ ጎራው መለስ ስል አሁንም ይህ ሰው ሌላ ሀሳብ አስፍሮ አነበብኩ፡፡ ልጅቱንም ቤተሰቦቿንም ደግሞ ልክ ናቸው …መብቷ ነው …ምናምን የሚሉ ሀሳቦችን ማለቴ ነው፡፡
እርግጥ ነው በመብት ደረጃ የመሰለውንም ያመነበትንም ነገር መፃፍ ይቻላል!! መፃፍ ከመቻል ወዲህም ወዲያም ግን ጥርት ንጥር ያለ አመክንዮ ቢቀድም ሸጋ ነበር፡፡
እውነት ለማውራት በዚች ልጅ ውስጥ ያየሁት አስተዳደጓ ነው፡፡ እንዲህ ያለውን የልጅ ባህሪ ከመዘመን፣ከመሰልጠን፣ከመንቃት እና ከመብቃት ጋር ማያያዙ ተገቢ ነው ብዬ አላስብም፡፡ ልጅነት የራሱ የሆኑ ጥብቆዎች አሉት…ተፈጥሮ፣ባህል፣ሐይማኖት የሚባሉ ነገሮች ተገምደው የሚሰፉት ግብረ ገብነት አለው፡፡
እርግጥ ነው ተፈጥሮ በልዩ ሁኔታ ብቁም ንቁም አድርጋ የምትፈጥራቸው ለዕውቀት የተሰጡም በክሎት የተካኑም /gifted and talented/ የሆኑ ልጆ አሉ፡፡ ይህ መሰጠታቸው እንዳለ ሆኖ ከሰው ጋር አግባብቶ የሚያኖራቸውን ማህበረሰባዊ ፋይዳው ወሳኝ የሆነው ግብረ ገብነታቸው ላይ ካልተሰራ ግን ሁሉ ነገር ኪሳራ ነው፡፡
ልጅ በዕድሜው…. ነገሮችን በመረዳት መጠኑም ልክ እያወቀ ማደግ አለበት ባይ ነኝ፡፡ ከዕድሜው እና ከመረዳት መጠኑ በላይ ነገሮችን ቀድሞ አውቆ ቀድሞ መሞከር ልክ ማሳው ላይ ከተዘሩት እና ወቅታቸውን ጠብቀው በልክ ካደጉት ሁሉ ቀድሞ በወውጣት አንገቱን አሰግጎ አደግኩ አደኩ እንዳለው እና ቀድሞ እንደተበጠሰው የእህል ዘር አይነት መሆን ነው፡፡ ከልክ በታች ሆኖ መዘግየትም አረም ነው ተብሎ እንደሚያስነቅል ሁሉ የልጆች ዕድገት በዕድገት ስርዓታቸው ልክ መሆን አለበት፡፡
ልጅ ሲያጠፋም ሆነ ያልተገባ ባህሪ ሲያሳይ በልምጩም በቁንጥጫው፣ መግራት አይገድላቸውም፡፡ እናን እንዳልገደለን ሁሉ ማለቴ ነው፡፡
ወደ ልጅቱ ስመለስ ቤተሰቦቿ ጋር አንድ ዘመናዊነት ባያሌው ያጠቃው ክፍተት ይታየኛል … ..አለ አይደል የሆነ ማቀማጠል አይሉት ማጨማለቅ …ብቻ ልጅቱ በተፈጥሮ በተሰጣት ፈጣንነት ልክ ረገብ …ረጋ የሚያደርጋት ምክር እና ተግሳፅ …ያስፈልጋታል ባይ ነኝ፡፡
ስቼም ከሆነ እታረማለሁ !!

የኩላሊት ታማሚ በማስመሰል ጓደኛቸውን መኪና ውስጥ አስተኝተው ገንዘብ ሲሰበስቡ የተገኙ 10 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ። ***ምንም አይነት የጤና ችግር የሌለበት ጓደኛቸውን ሁለቱም ኩላሊቶቹ...
04/04/2024

የኩላሊት ታማሚ በማስመሰል ጓደኛቸውን መኪና ውስጥ አስተኝተው ገንዘብ ሲሰበስቡ የተገኙ 10 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ።
***
ምንም አይነት የጤና ችግር የሌለበት ጓደኛቸውን ሁለቱም ኩላሊቶቹ ከጥቅም ውጪ የሆኑ በማስመሰል በህክምና ሰበብ ገንዘብ ሲያሰባስቡ የነበሩት 10 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር የዋሉት በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 14 ልዩ ቦታው አዲስ ሰፈር እየተባለ በሚጠራው አካባቢ ነው ።

ግለሰቦቹ የሰሌዳ ቁጥር ኮድ 3- B21705 አ.አ የሆነ ሚኒባስ ተሽከርካሪን በመጠቀም ገንዘቡን ሲሰበስቡ የቆዩት የኩላሊት ታማሚ ነው ያሉትን ጓደኛቸውን መኪና ውስጥ በማስተኛት ሲሆን በተያዙበት ወቅት ከአምስት ሺህ ብር በላይ ገንዘብ እጃቸው ላይ ተገኝቷል፡፡

በመዲናችን አዲስ አበባ በተለያዩ አካባቢዎች ተመሳሳይ የድጋፍ ጥያቄዎች ሲቀርቡ የሚስተዋል መሆኑን የጠቀሰው ፖሊስ፤ ነገር ግን ህብረተሰቡ እንዲህ አይነት የማታለል ተግባር የሚፈፅሙ ሰዎች መኖራቸውን ተገንዝቦ ድጋፍ በሚያደርግበት ወቅት ከህክምናው ጋር የተያያዙ አግባብነት ያላቸውን ሰነዶች በማየትና ትክክለኛነቱን በማረጋገጥ ሊሆን እንደሚገባ አሳስቧል፡፡

ዘገባ፡- ሳጅን ጤናው ፈጠነ

የኩላሊት ታማሚ በማስመሰል ጓደኛቸውን መኪና ውስጥ አስተኝተው ገንዘብ ሲሰበስቡ የተገኙ 10 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ። ***ምንም አይነት የጤና ችግር የሌለበት ጓደኛቸውን ሁለቱም ኩላሊቶቹ...
04/04/2024

የኩላሊት ታማሚ በማስመሰል ጓደኛቸውን መኪና ውስጥ አስተኝተው ገንዘብ ሲሰበስቡ የተገኙ 10 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ።
***
ምንም አይነት የጤና ችግር የሌለበት ጓደኛቸውን ሁለቱም ኩላሊቶቹ ከጥቅም ውጪ የሆኑ በማስመሰል በህክምና ሰበብ ገንዘብ ሲያሰባስቡ የነበሩት 10 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር የዋሉት በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 14 ልዩ ቦታው አዲስ ሰፈር እየተባለ በሚጠራው አካባቢ ነው ።

ግለሰቦቹ የሰሌዳ ቁጥር ኮድ 3- B21705 አ.አ የሆነ ሚኒባስ ተሽከርካሪን በመጠቀም ገንዘቡን ሲሰበስቡ የቆዩት የኩላሊት ታማሚ ነው ያሉትን ጓደኛቸውን መኪና ውስጥ በማስተኛት ሲሆን በተያዙበት ወቅት ከአምስት ሺህ ብር በላይ ገንዘብ እጃቸው ላይ ተገኝቷል፡፡

በመዲናችን አዲስ አበባ በተለያዩ አካባቢዎች ተመሳሳይ የድጋፍ ጥያቄዎች ሲቀርቡ የሚስተዋል መሆኑን የጠቀሰው ፖሊስ፤ ነገር ግን ህብረተሰቡ እንዲህ አይነት የማታለል ተግባር የሚፈፅሙ ሰዎች መኖራቸውን ተገንዝቦ ድጋፍ በሚያደርግበት ወቅት ከህክምናው ጋር የተያያዙ አግባብነት ያላቸውን ሰነዶች በማየትና ትክክለኛነቱን በማረጋገጥ ሊሆን እንደሚገባ አሳስቧል፡፡

ዘገባ፡- ሳጅን ጤናው ፈጠነ

አኮቴትኢቢኤስ እና ድንቅ ተግባሩ  በዓለማችን ካለው ሕዝብ ውስት እጅግ በጣም ጥቂቶቹ ካልሆኑ በስተቀር አብላጫውን እጅ የሚይዘው ሰው ሕይወቱን ፈቅ የሚያደርገው ተቀጥሮ በመስራት ነው፡፡ አንድ...
17/01/2024

አኮቴት
ኢቢኤስ እና ድንቅ ተግባሩ

በዓለማችን ካለው ሕዝብ ውስት እጅግ በጣም ጥቂቶቹ ካልሆኑ በስተቀር አብላጫውን እጅ የሚይዘው ሰው ሕይወቱን ፈቅ የሚያደርገው ተቀጥሮ በመስራት ነው፡፡ አንድም ቀን …ተቆጥሮ በወር በሚከፈል ቋሚ ደሞዝ… አልያም በስራ ልኬት ተቀጣሪ ባመረተው ልክ የሚከፈል፡፡ ይህ የአብዛኞቹ ቀጣሪ መስሪያ ቤቶች የአከፋፈል ስርዓት ነው፡፡ ከዛ በመለስ ሰራተኛውን ለማትጋት እና ለመቅጣት በሰራተኞቹ የሕብረት ስምምነት መሰረት ቅጣት ወይንም ዓመት እየቆጠሩ የደሞዝ ጭማሪ ከማድርግ ውጪ ለሰራተኞቻቸው ብዙ ርቆት ሄደው ለክፉ ቀን የሚሆኑ ቀጣሪዎች ማየት ብዙ አልተለመደም፡፡
መግቢያዬ ላይ እንደገለፅኩት መንግስታዊም ይሁኑ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ሰራተኞቻውን ለማበረታታት አንዳንድ ወጪያቸውን ሲሸፍኑ ይስተዋላል፡፡ ገሚሶቹ ደግሞ እንዲህ ካለው ሰራተኛን ከማትጋት ሀሳብ በብዙ መልኩ ነፃ ናቸው፡፡ በጣም ጥቂቶቹ ደግሞ ዛሬ ልናወራለት እንደፈለግነው የቴሌቪዥን ጣቢያ በልዩነት ወጥተው ያልተለመደ እና ይበል የሚያሰኝ ድጋፍ ሲያደርጉ ይስተዋላሉ ….
ከዚህ ቀደም በታሪካችን የምናውቀው መኖሩንም …መስራቱንም የማናውቀው የአንድ የሚዲያ ተቋም ጋዜጠኛ ወይንም የሆነ ክፍል ሰራተኛ የነበረ ሰው ስም ተጠርቶ እዛ ተቋም ውስጥ ይሰራ እንደነበር ተጠቅሶ ማለፉ/መሞቱ/ ይነገራል፡፡እርግጥ ነው በሟች ዘመን የነበሩ ሰዎች ግለሰቡን ቢያውቁትም ቅሉ …ሰራተኛው በጡረታ ይሁን ወይ በሌላ ጉዳይ ከተገለለ በኃላ ማንም ሰው መኖሩን ሳያውቅ አልያ ዘንግቶት በሞቱ ምክንያት ብቻ ስሙ ይጠራል፡፡ ከዛም የቀብር ስነ ስርዓቱ በስንት ሰዓት እንደሚፈፀም ተጠቅሶ ይታለፍና ማምሻውን ደግሞ ‹‹በድርጅታችን ውስጥ ይህን ለሚያክል ጊዜ ሲሰሩ የነበሩ የአቶ እከሌ እከሌ የቀብር ስነ ስርዓት ወዳጅ ዘመዶቻቸው በተገኙበት እንዲህ ባለ ቦታ ተፈፀመ..›› ተብሎ ከፍየል ጭራ ያነሰች ዜና ብጤ ይሰራላቸዋል፡፡ አንዳንዶቹ እድለኞች እና በወቅቱ በድርጅቱ ውስጥ አለቃ ብጤ ሆነው የሰሩ ከነበሩ …ትንሸ ከዚች ዘለግ ያለች መሰናዶ ብጤ ይሰራላቸዋል፡፡ በቃ አበቃ…. ስንት ዓመት ሙሉ በዕውቀትም በጉልበትም ሰርተው ዛሬ ባደረሱት ተቋም ውለታቸው ከዚህ ዘሎ አያውቅም፡፡
ለዛሬው ጉዳዬ መነሻ የሆነኝ ኢቢየስ ግን እንዲህ ካለው ወቃሳ ከሚድንበት ማማ ላይ ተቀምጦ ታይቷል፡፡ኢቢየስ በሚዲያው መስክ በልዩነት የራሱን ቀለም እና አዳዲስ መሰናዶዎችን ይዞ የመጣ የሚዲያ ተቋም ነው፡፡
ዕጣ ፈንታው ሆኖ ነው መሰል …መወደድን እንደ ሸማ ለብሶ የሰነበተው የአስፋው መሸሻ ሕመም ከተሰማ በኃላ …ድርጅቱ/ ኢቢኤስ/ ያደረገው ነገር እጅግ እጅግ የሚያስመሰግነው ነገር ነው፡፡
አስፋው መሻሻ በጠና ታሟል እና ከፍተኛ ሕክምና እና ክትትል ያሻዋል ከተባለበት ጥቅምት ወር ጀምሮ ሙሉ ወጪውን በመሸፈን ወደ አሜሪካን ሀገር ወስዶ በማሳከም ከፍተኛውን ድርሻ አበርክቷል፡፡ እንዲህ ያለው ነገር መንግስታዊም ሆኑ መንግስታዊ ላልሆኑ ድርጅቶች ቢጋባባቸው እና እንደ ልምድ ቢወስዱት እንላለሁ፡፡
ኢቢኤስ በዚህም ብቻ አላበቃም …አስፋው መሸሻ የሄደበት ሀገር ሁሉ ሰው በሕይወት ውጥረት መካከል የሚዳክርበት ሜዳ በመሆኑ ልክ እንደ ሀገር ቤት ሌት ተቀን እየተፈራረቁ የሚያድሩለት አስታማሚዎች የማይገኙበት በመሆኑ የተነሳ አንድያ ልጁን ሙሉ ወጪውን ከፍሎ …ሲሰራ የሚያገኘውን ደመወዝ ሳይቀር ከፍሎ የአስፋው መሸሻን ሕይወት ለመታደግ ያደረገው ጥረት እንዲህ ነው ተብሎ የሚጠቀስ አይደለም፡፡ አስፋው መሸሻ የልጄን የጃፒን ነገር አደራ እንዳለ ኢቢየስ አደራውን መቀበል የጀመረው አስፋው ገና በሕይወት ሳለ ጀምሮ ነበር፡፡ ልጁ ጃፒም ቢሆን ይህንን ጉዳይ በግሉ ማህበራዊ ሚዲያው ላይ ገልፆታል፡፡
መቼም ሁሉ ሰው እንኳ ዛሬን ቆሞ በዓለም ሲመላለስ ቢታይም ሞት ይሉትን ነገር ተቀሸክሞ ነውና የሚኖረው …አስፋው መሻሻ ከዛሬ ነገ ሀገሬ ገብቼ እንዲህ ከፍ ዝግ ብሎ በፀሎት በምልጃ ያልተለየኝን ሕዝብ ለማመስገን ያብቃኝ እያለ ሞት ቀደመው፡፡ የአስፋውን ሞት ተከትሎም እናት ድርጅቱ ዘወትሮአዊው የዕለተ እሁድ መሰናዶዎች በሙሉ አቁሞ በሀዘን መግለጫ እንዲያልፍ አድርጓል፡፡ የስራ ባልደረቦቹም በሙሉ ማቅ ለብስው፣ሀዘን ተኮራምተው፣በእንባ ጎርፍ ተሞልተው የወዳጃቸውን ገሚሶቹ እንደሚሉት ደግሞ የአባታቸውን የአስፋው መሸሻን ሀዘን በቀጥታ ስርጭት አሳይተውናል፡፡ ኢቢኤስ ለአንድ ሰራተኛው በዚህ መጠን ተጨንቆ ስንት እና ስንት ሺ ብሮችን ከስሮ እንዲህ ማድረጉ እጅጉን የሚያስመሰግነው ጉዳይ ነው፡፡ ሁሉ ሰው እንደሚያውቀው የትኞቹም የቴሌቪዥን ጣቢያዎች ከአዘቦት ቀናት ይልቅ በሰንበት ቀናት በተለይ ዕሁድ ዕሁድ ከማስታወቂያ የሚያገኙት ገቢ የት ድረስ እንደሆነ ማሰብ ብዙ አይከብድም ፡፡ታድያ እነዚህ ሁሉ ፕሮግራሞች እና ማስታወቂዎችን ወደ ጎን ተወት አድርጎ እንደ ቤተሰብ ሀዘን መቀመጡም አስደንቆኛል እና ይበል እሰየው ብያለሁ!!!
ሰው መቼም ካልሄደ ውለታውም ጥቅሙም አይታወቅም እና አስፋው መሸሻ ሕልፈት እውነት እስካይመስላቸው ድረስ ባልደረቦቹ ሲንገበገቡ ማየት በድርጅታቸው ውስጥ እንዴት ያለ የስራ ፍቅር እና ስምምነት ቢኖር ነው እንዲህ ሁሉ ነገራቸው ሁሉ ቤተሰባዊ የሆነው የሚል ጥያቄን ያጭራል፡፡ ይህ የሆነው ድርጅቱ ሰላማዊ በመሆኑ ምክንያት እንደሆነ ማወቅ ቀላል ነው፡፡

ተቀብለናል!!!አጠፉም አላጠፉም ይቅርታ መጠይቅ ትልቅነት ነው !!የሰው ልጅ ሀሳብ ብዙ ነው፡፡ ሁሉ ሰው ሀሳቡን ይመቸኛል …እንዲህ አድርጌ ብገልፀው ይሻለኛል ብሎ ባለበት መንገድ ሀሳቡን ይገ...
12/01/2024

ተቀብለናል!!!
አጠፉም አላጠፉም ይቅርታ መጠይቅ ትልቅነት ነው !!

የሰው ልጅ ሀሳብ ብዙ ነው፡፡ ሁሉ ሰው ሀሳቡን ይመቸኛል …እንዲህ አድርጌ ብገልፀው ይሻለኛል ብሎ ባለበት መንገድ ሀሳቡን ይገልጣል፡፡ ጥሩ በመናገር እና ቃላትን አዋቅሮ ንግግርን አሳምሮ በቻለው መጠን የልቡን ሀሳብ ያወጣል፡፡ ሀሳቡን መሸጥ በቻለበት መጠን ይሸጣል፡፡ በሌላኛው ወገን ደግሞ አንዲህ ያለውን ሀሳብ ወዶት የተረዳው ደስ ብሎት ይገዛዋል፡፡ አልያም ይህ ሀሳብ እንዲህ ባለ መልኩ ባይገለጥ ጥሩ ነበር ብሎ …ማስተካካየ የሚሰጥም አድማጭ ተመልካች ብዙ ነው፡፡
ከሰው ልጆች ባህሪያት ውስጥ አንዱ ስህተት ነው፡፡ ሁሉ ሰው ሰህተት ይሰራል፡፡ ማንም ሰው እንደ ክርስቶስ ፈፁም ነኝ ካላለ በስተቀር ከስህተት ሊነፃ አይችልም፡፡ፍፅምና በሰው ልጆች ዘንድ ከቶ የለም፡፡ በኃይማኖት በቁ ነቁ የምንላቸው አባቶች ሳይቀሩ ከስህተት የነጡ አይደሉም፡፡ በዓለም እንዳለን ሰዎች ደጋግመው ደጋግመው በጥፋት መስመር ላይ አይገኙ ይሆን መሳሳታቸው የማይቀር እውነት ነው፡፡
ወዲህ ደግሞ ስራ ልስራ ብሎ ሕይትን ፈቅ ለማድረግ በብዙ መልኩ ጎንበስ ቀና የሚል…ስራ የሚሰራ ሰው ሁሉ …ስህተት ሊሰራ ግድ ነው፡፡ እጅ እግሩን አጣጥፎ ምንም ሳይሰራ በቤተሰብ ወይ በሌላ አካል እየተደገፈ የሚኖር ሰው ከሚሰራው ሰው ጋር ሲነፃፀር የሚሰራው ስህትት እምብዛምነ ነው፡፡ ይህ ማለት ባለመስራት ስህተት የማይሰራው ሰው ይሻላል ማለቴም አይደለም፡፡ሰርቶ መሳሳት የአባት ነው፡፡ በመስራት እና በመንቀሳቀስ ውስጥ የሚፈጠሩ ሰህተቶች በሙሉ ስህተቱ በተፈጠረበት ሰዓት የሚያስከትሉት ተግዳሮቶች ቢኖሩም ሲያልፉ ግን መማሪያ እና ማስተማሪያነታቸው ይበልጣል፡፡
ሌላው አንዳንድ ስህተቶች ስህተት ናቸው ተብለው የሚፈረጁት በሶስተኛ ወገን ሲተያዩ ይሆናል …ሰህተት ሰራ የተባለው ሰው የሰራሁት ስህተት አይደለም ….ስህተቱ የተረዳችሁበት መንገድ ነው….እኔ ይህን ያደረኩት እንደዚህ ያለ ሸጋ ውጥኣት ወይንም መልካም ውጤት እና መረዳት ያመጣል ብዬ ነው ሲል ይሰማል፡፡አሁን እዚህ ጋር ያለው ቁም ነገር በአንድ ስው ንግግር እና ስራው ውስጥ የተፈጠረው ነገር ስህተት ነው የሚል ሌላ ሰው ከተነሳ እና ክህተቱን በአመክንዩ ማስረዳት ተችሎ መግባባት ላይ ካልተደረሰ …ያ ሰው እንዳይከፋ እና ወዳጅነት እንዳይሻክር ጉዳዩ ላይ ይቀርታ መጠየቅ እና ሀሳቡ ላይ በለመስማማት መስማማት ብልህነትም ተገቢም ነው፡፡
ለዛሬው ጉዳዬ መነሻ የሆነኝ የዝነኞቹ ኮሜዲያን የይቅርታ መልዕክት ነው፡፡በዓባይ ቲቪ እየተዘጋጀ በሚቀርበው የዋሸው እንዴ መሰናዶ ላይ ከሴት ልጅ ጥቃት ጋር ተያይዞ አንድ ርዕሰ ጉዳይ ተነስቶ ነበር፡፡በዚህ ርዕሰ ጉዳይ ላይ ታድያ የዓባይ ቲቪ ተመልካቾችም ሆኑ የኮሚዲያኑ አድናቂዎች ቅር የተሰኙበተን ጉዳይ አንስተው ቅሬታቸውን ሲገልፁላቸው ነበር፡፡ወዲህ ደግሞ ገሚሶቹ ኮሜዲያኑ ሊያስተላልፉ የፈለጉትን ነገር ተረድተው ችግሩ ያለው አድማጭ ተመልካች ጋር ነው እንጂ እነርሱ ምንም አላጠፉም ያሏቸውም ነበሩ፡፡
በመግቢያዬ ላይ እንደጠቀስኩት ኮሜዲያኑ ይህንን ነገር የገለፁት ሰው በተረዳው መልኩ መግለፅ ተፈልጎ ሳይሆን የሴትን ልጅ ጥቃት አስመልክቶ ከተለመደው ገለፃ በተለየ መልኩ በቀልድ አዋዝቶ ሁነኛ መልዕክት ለማስተላለፍ እንደነበረ ገልፀዋል፡፡ እርግጥ ነው እነርሱ እንዳሉት በዚህ ርዕሰ ጉዳይ ላይ እንዲህ ባለ መልኩ የሚቀልድ ሰብዕና አላቸው ብለን አናስም፡፡…..በመስኩ ያካበቱት የሰው ፍቅር እና መውደድ ላይም የሚቀልድ ስነ ምግባርም የላቸውም፡፡ ሁሉም ኮሜዲያን በየ ግላቸው የየራሳቸው ክብር እና አክባሪም አላቸው እና፡፡
ወደ ዋነና ነገረ ጉዳዬ ስመለስ እኛ ‹ልንገልፅ የፈለግነው ነገር እንዲህ የሚልን ሀሳብ ነበር ሰው የተረዳው በሌላ ነው ስለዚህ ምንም ዓይንት ስህተት አልሰራንም› ብለው ሳይሉ እርግጥ ነው የተከሰተው ነገር በሰዎች የመረዳት መጠን እና ነገርን ከአንድ አቅጣጫ ብቻ ከመመልት የተፈጠረ የሀሳብ አለመረዳት ቢሆንም …ለተከተሰተው ነገር ግን ይቅርታ እንጠይቃለን ብለው ማለታቸው ትልቅነታቸውን እና ለአድናቂዎቻቸው ያላቸውን ክብር እና ፍቅር የሚያሳይ በመሆኑ ልናከብራቸው እና ልናደንቃቸው ይገባል፡፡
እንዲህ ያለው ሰህተት ይሁን በሀሳብ አልተግብቶም የተከሰተው ስለሰራችሁ ስለሆነ ችግሩ የሚጠበቅ ነው፡፡ ባትሰሩ ባትንቀሳቀሱ መች ስህተቱ ይሰራ ነበር፡፡ ዋናው እንዲህ ባለው አጋጣሚ ወደፊት የትኛው ርዕሰ ጉዳይ እንዴት መነሳት እንዳለበት …እንዲሁም የትኛው ርዕሰ ጉዳይ ደግሞ ቢነሳ ብዥታ ይፈጥርና እንደ አሁኑ ያለ ችግር ይፈጥራል የሚሉ ርዕሰ ጉዳዮችን እንዳስተማራችሁ አድርጎ ማለፉ ነው፡
ተቀብለናል!!!

......................ተቀብለናል!!!............................አጠፉም አላጠፉም ይቅርታ መጠይቅ ትልቅነት ነው !!የሰው ልጅ ሀሳብ ብዙ ነው፡፡ ሁሉ ሰው ሀሳቡን...
12/01/2024

......................ተቀብለናል!!!............................
አጠፉም አላጠፉም ይቅርታ መጠይቅ ትልቅነት ነው !!

የሰው ልጅ ሀሳብ ብዙ ነው፡፡ ሁሉ ሰው ሀሳቡን ይመቸኛል …እንዲህ አድርጌ ብገልፀው ይሻለኛል ብሎ ባለበት መንገድ ሀሳቡን ይገልጣል፡፡ ጥሩ በመናገር እና ቃላትን አዋቅሮ ንግግርን አሳምሮ በቻለው መጠን የልቡን ሀሳብ ያወጣል፡፡ ሀሳቡን መሸጥ በቻለበት መጠን ይሸጣል፡፡ በሌላኛው ወገን ደግሞ አንዲህ ያለውን ሀሳብ ወዶት የተረዳው ደስ ብሎት ይገዛዋል፡፡ አልያም ይህ ሀሳብ እንዲህ ባለ መልኩ ባይገለጥ ጥሩ ነበር ብሎ …ማስተካካየ የሚሰጥም አድማጭ ተመልካች ብዙ ነው፡፡
ከሰው ልጆች ባህሪያት ውስጥ አንዱ ስህተት ነው፡፡ ሁሉ ሰው ሰህተት ይሰራል፡፡ ማንም ሰው እንደ ክርስቶስ ፈፁም ነኝ ካላለ በስተቀር ከስህተት ሊነፃ አይችልም፡፡ፍፅምና በሰው ልጆች ዘንድ ከቶ የለም፡፡ በኃይማኖት በቁ ነቁ የምንላቸው አባቶች ሳይቀሩ ከስህተት የነጡ አይደሉም፡፡ በዓለም እንዳለን ሰዎች ደጋግመው ደጋግመው በጥፋት መስመር ላይ አይገኙ ይሆን መሳሳታቸው የማይቀር እውነት ነው፡፡
ወዲህ ደግሞ ስራ ልስራ ብሎ ሕይትን ፈቅ ለማድረግ በብዙ መልኩ ጎንበስ ቀና የሚል…ስራ የሚሰራ ሰው ሁሉ …ስህተት ሊሰራ ግድ ነው፡፡ እጅ እግሩን አጣጥፎ ምንም ሳይሰራ በቤተሰብ ወይ በሌላ አካል እየተደገፈ የሚኖር ሰው ከሚሰራው ሰው ጋር ሲነፃፀር የሚሰራው ስህትት እምብዛምነ ነው፡፡ ይህ ማለት ባለመስራት ስህተት የማይሰራው ሰው ይሻላል ማለቴም አይደለም፡፡ሰርቶ መሳሳት የአባት ነው፡፡ በመስራት እና በመንቀሳቀስ ውስጥ የሚፈጠሩ ሰህተቶች በሙሉ ስህተቱ በተፈጠረበት ሰዓት የሚያስከትሉት ተግዳሮቶች ቢኖሩም ሲያልፉ ግን መማሪያ እና ማስተማሪያነታቸው ይበልጣል፡፡
ሌላው አንዳንድ ስህተቶች ስህተት ናቸው ተብለው የሚፈረጁት በሶስተኛ ወገን ሲተያዩ ይሆናል …ሰህተት ሰራ የተባለው ሰው የሰራሁት ስህተት አይደለም ….ስህተቱ የተረዳችሁበት መንገድ ነው….እኔ ይህን ያደረኩት እንደዚህ ያለ ሸጋ ውጥኣት ወይንም መልካም ውጤት እና መረዳት ያመጣል ብዬ ነው ሲል ይሰማል፡፡አሁን እዚህ ጋር ያለው ቁም ነገር በአንድ ስው ንግግር እና ስራው ውስጥ የተፈጠረው ነገር ስህተት ነው የሚል ሌላ ሰው ከተነሳ እና ክህተቱን በአመክንዩ ማስረዳት ተችሎ መግባባት ላይ ካልተደረሰ …ያ ሰው እንዳይከፋ እና ወዳጅነት እንዳይሻክር ጉዳዩ ላይ ይቀርታ መጠየቅ እና ሀሳቡ ላይ በለመስማማት መስማማት ብልህነትም ተገቢም ነው፡፡
ለዛሬው ጉዳዬ መነሻ የሆነኝ የዝነኞቹ ኮሜዲያን የይቅርታ መልዕክት ነው፡፡በዓባይ ቲቪ እየተዘጋጀ በሚቀርበው የዋሸው እንዴ መሰናዶ ላይ ከሴት ልጅ ጥቃት ጋር ተያይዞ አንድ ርዕሰ ጉዳይ ተነስቶ ነበር፡፡በዚህ ርዕሰ ጉዳይ ላይ ታድያ የዓባይ ቲቪ ተመልካቾችም ሆኑ የኮሚዲያኑ አድናቂዎች ቅር የተሰኙበተን ጉዳይ አንስተው ቅሬታቸውን ሲገልፁላቸው ነበር፡፡ወዲህ ደግሞ ገሚሶቹ ኮሜዲያኑ ሊያስተላልፉ የፈለጉትን ነገር ተረድተው ችግሩ ያለው አድማጭ ተመልካች ጋር ነው እንጂ እነርሱ ምንም አላጠፉም ያሏቸውም ነበሩ፡፡
በመግቢያዬ ላይ እንደጠቀስኩት ኮሜዲያኑ ይህንን ነገር የገለፁት ሰው በተረዳው መልኩ መግለፅ ተፈልጎ ሳይሆን የሴትን ልጅ ጥቃት አስመልክቶ ከተለመደው ገለፃ በተለየ መልኩ በቀልድ አዋዝቶ ሁነኛ መልዕክት ለማስተላለፍ እንደነበረ ገልፀዋል፡፡ እርግጥ ነው እነርሱ እንዳሉት በዚህ ርዕሰ ጉዳይ ላይ እንዲህ ባለ መልኩ የሚቀልድ ሰብዕና አላቸው ብለን አናስም፡፡…..በመስኩ ያካበቱት የሰው ፍቅር እና መውደድ ላይም የሚቀልድ ስነ ምግባርም የላቸውም፡፡ ሁሉም ኮሜዲያን በየ ግላቸው የየራሳቸው ክብር እና አክባሪም አላቸው እና፡፡
ወደ ዋነና ነገረ ጉዳዬ ስመለስ እኛ ‹ልንገልፅ የፈለግነው ነገር እንዲህ የሚልን ሀሳብ ነበር ሰው የተረዳው በሌላ ነው ስለዚህ ምንም ዓይንት ስህተት አልሰራንም› ብለው ሳይሉ እርግጥ ነው የተከሰተው ነገር በሰዎች የመረዳት መጠን እና ነገርን ከአንድ አቅጣጫ ብቻ ከመመልት የተፈጠረ የሀሳብ አለመረዳት ቢሆንም …ለተከተሰተው ነገር ግን ይቅርታ እንጠይቃለን ብለው ማለታቸው ትልቅነታቸውን እና ለአድናቂዎቻቸው ያላቸውን ክብር እና ፍቅር የሚያሳይ በመሆኑ ልናከብራቸው እና ልናደንቃቸው ይገባል፡፡
እንዲህ ያለው ሰህተት ይሁን በሀሳብ አልተግብቶም የተከሰተው ስለሰራችሁ ስለሆነ ችግሩ የሚጠበቅ ነው፡፡ ባትሰሩ ባትንቀሳቀሱ መች ስህተቱ ይሰራ ነበር፡፡ ዋናው እንዲህ ባለው አጋጣሚ ወደፊት የትኛው ርዕሰ ጉዳይ እንዴት መነሳት እንዳለበት …እንዲሁም የትኛው ርዕሰ ጉዳይ ደግሞ ቢነሳ ብዥታ ይፈጥርና እንደ አሁኑ ያለ ችግር ይፈጥራል የሚሉ ርዕሰ ጉዳዮችን እንዳስተማራችሁ አድርጎ ማለፉ ነው፡
ተቀብለናል!!!

ክሽፈት.........................እሳት በሌለበት ጭስ አይታይም!.................................ዛሬ ደጉ መንግስታችን ያደረገውን ነገር ስስማ ምን እንደተሰማኝ...
29/12/2023

ክሽፈት.........................እሳት በሌለበት ጭስ አይታይም!.................................

ዛሬ ደጉ መንግስታችን ያደረገውን ነገር ስስማ ምን እንደተሰማኝ የምናውቅ እኔና ፈጣሪ ብቻ ነን፡፡ በተለይ እንደ ወላጅ የሆነው ሳስብ አቅሌን ስቼ የምሆነውን ነው ያጣሁት …ሀገር እንዴት እንዲህ ትዘቅጣለች ያስባለኝ ጉዳይ ነው፡፡
ነገሩ እንዲህ ነው
ሁላችሁም እንደምታውቁት የአቡነ ጎርጎሪዎስ ተማሪዎች በሙሉ ጠዋት ትምህርት ከመጀመራቸው በፊት አምላካቸውን አመስግነው ደግሞም ስለ ሀገራቸው በልጅ አንደበታቸው ፀልይው …ብሔራዊ መዝሙርን አክለው ነው ትምህርታቸውን የሚጀምሩት፡፡ በዚህ ላይ ግብረ ገብም ይማራሉ፡፡ ባለቻቸው የእረፍት ጊዜም በመዝሙር አምላካቸውን ያመሰግናሉ፡፡ይሄ ጉዳይ ይመስለኛል ለጆችን በአቡነ ጎርጎሪዎስ ለማስተማር የማይቀመስ እና በቀላሉ ቦታ ማግኘት እንዳይቻል ያደረገው፡፡ ምክንያቱም ሁሉም ወላጅ ልጆቹ ልክ ባለው ግብረ ገብ አምላካቸውን በመፍራት እንዲድጉ ስለሚፈልጉ ነው፡፡ እና ይሄንን ነው እንግዲህ ይህ ፀሐዩ መንግስታችን ከዛሬ ጀምሮ መዝሙር የለ ፀሎት የለ አቁሙ ብሎ ቀጭን ትዕዛዝ አስተላልፎ ያስቆማቸው፡፡ ኣጃኢብ ውርደት!
ነገሩ እንዲህ ያበገነኝ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታይ ስለሆንኩ አይደለም፡፡ ጉዳዩ በሌሎችም ኃይማኖታዊ አስተምሮን መሰረት ባደረገ መልኩ ዓለማዊውን ትምህርት የሚሰጡ ተቋማትም ላይ ቢፈፀም በቸልተኝነት የማልፈው ጉዳይ አይመስለኝም፡፡ ምክንያቱም የቱም ትውልድ በየትኛውም ኃይማኖታዊ ስነ ምግባር አድጎ ሀገር ከተረከበ በዳይ እና ገፊ እንደማይሆን ይገባኛል እና ነው፡፡ ሌላው ቢቀር የሚፈራው አምላክ ስላለው ፍርድ የማይጓደልበት ዜጋ ይወጣዋል ነው፡፡
አንዲት ሀገር ሀገር ሆና ለመቀጠል ሰው/ትውልድ ያስፈልጋታል! ሀገር ማለት ጋራው ሸንተረሩ፣ሜዳ ገደሉ ብቻ ነው ብዬ አላምንም፡፡ እኔ ሀገር ማለት ሰው ነው ሚሉት ጎራ የምሰለፍ ነኝ! ጋራ ሸንተረሩማ …ሜዳ ገደሉማ የትም ዓለም …የትም ሀገር አለ፡፡ ለእኔ ሀገር ማለት ሰው ነው!
ምንም እንኳ የምጣኔ ሀብት ባለሙያ/Economist/ ባልሆንም ቅሉ ባለችኝ ቅንጣት ታህል መረዳት የአንዲትን ሀገር ዕድገት የምለካው እያደር በሚከመሩ የድንጋይ ቁልል ክምሮች አይደለም፡፡ አምረው ተውበው በሚያሸበርቁ የመንገድ ዳርቻዎችም አይደለም፡፡ በእኔ በጨዋው ሰው መረዳት ሀገር አደገች የምለው የዜጎቿ መሰረታዊ ፍላጎት በአስተማማኝ ሁኔታ ሲሟላ….ሰው እንደ ሰው የመኖር፣የማሰብ፣የመናገር፣ የፈቀደውን ኃይማኖት የመከተል ፣መብቶቾ ተጠብቀው ሰላም ወጥቶ ሰላም ሲገባ እና የመሳሰሉ ዝርዝር ጉዳዮች ሲሟሉ ነው፡፡ ሌላው ብልጭልጭ ነገር ሁሉ ርካሽ ትርፍ ነው፡፡
የነገዋ ሀገር የምትገነባው የዛሬ ሕፃናትላ ላይ ነው፡፡ ዛሬ ልጆቻችንን በሃይማኖት እና በግብረ ገብ ካላሳደግን የነገዋ ሀገር ህልውና እጅግ አሳሳቢ ደረጃ ይደርሳል፡፡እልፍ ሲልም በጦርነት ከፈረሱት በባሰ ከቁጥጥር ውጭ የምትሆን ቅጥ አምባሯ የጠፋባት ሀገር ትሆናለች፡፡ ዛሬ ለወላጆች መታዘዝን፣ መስረቅ፣መግደል፣መዋሸት፣ስድብ፣ጥላቻ እና ሌሎች መሰል ነገሮች እንዲጠየፉ አድርገን ካላሰደግን የነገዋ ሀገር የከሸፈች አካሏ የተሰነከለ፣ ዓይኗ የተንሸዋረረ…ሸፋፋ …ጠማማ…ስለመሆኗ ምንም ጥርጥር የለም፡፡
መቼም የእብድ ቀን /crazy day/፣የቀለም ቀን/color day/ የምንትስ ቀን እያሉ የቀን አስረሸ ምቺው /day party/ የሚያዘጋጁ ትምህርት ቤቶችን እንዲህ ያለ ማፈንገጣችሁን አቁሙ እንደማይላቸው እርግጠኞች ነን፡፡
የእውነት ግን መንግስት ምን አስቦ ነው ህፃናትን አትፀልዩ…አታመስግኑ የሚው….፡፡ዛሬ በግብረ ገብ ተኮትኩቶ…በሃይማኖት አጥር ተጠልል ያላደገ ትውልድ እኮ ሲነጋ ለራሱም አይታዘዝለትም…የነገውን ወጣት ዛሬ እየገሩ ካላስተማሩ ..ወጥቶ ጎማ እያቃጠለ መንገድ ከመዝጋት የሚካላከው አንዳችም ኃይል የለም፡፡ የሰው ልቡ የሚገራው በአምላኩ ነው፡፡
ይህ ነገር ልቤ ውስጥ አንዳች ነገር ሰንቅሮብኛል
አንድም እንደ ቀደመ ተግባሩ ቤተ ክርስቲያኑቱን ከመሰረቷ መምታት
ሲቀጥል ደግሞ ከሰሞኑ በሌሎች የስምምነት ሰነዶች ውስጥ ተሰንቅሮ በመግባት በንዑሳን የስምምነት መስፍርቶች ውስጥ የተጠቀሰው የተመሳሳይ ፆታ ጋብቻን ጉዳይ ወደ ፊት እንዳላስፈፅም እክል ይፈጥርብኛል በሚል ስጋት የተፈፀም ለጉዳዩ መረማመጃ ምቹ መደላደል ማመቻቸትም ሆኖ ይሰማኝ ይዟል፡፡ ምክንያቱም ይህ ጭስ አንዳች የተለኮሰ እሳት እንዳለው ይነግረኛል፡፡ እሳት በሌለበት መች ጭስ ታይቶ ታወቃል፡፡

ይህ ከመንግሰት የመጣ መሆኑን መስማት የክሽፈት ምልክት ነው!!!!
ለማናቸውም ሀገርን በኣማን አሰንብቶ ያቆየን!

https://youtu.be/uEwZBb3xu1k?si=5VwCr06eR--WTil-
27/12/2023

https://youtu.be/uEwZBb3xu1k?si=5VwCr06eR--WTil-

በቅርቡ ብንሄድ ይሻለናል በሚል ራሷን ካጠፋችው ወጣት ናዝራዊት ቀጥሎ ብዙ ወጣቶች እራሳቸውን ሲያጠፉ ተስተውለዋል፡፡ የዛሬዋ የጊዜ ሚዲያ እንግዳም እንዲሁ በቅርቡ በቀጥታ የቲክቶክ .....

አንድ ለመንገድ 13    -----------ፓንታችሁን አውልቃችሁ ብሉ----------------ዕድሜ መቼም ፀጋ ነው! ኑረው ከከረሙ አይሰሙት ጉድ አያዩት መዓት የለም! ወዲህ ፖለቲካው፣ጎጠኝነ...
23/12/2023

አንድ ለመንገድ 13
-----------ፓንታችሁን አውልቃችሁ ብሉ----------------
ዕድሜ መቼም ፀጋ ነው! ኑረው ከከረሙ አይሰሙት ጉድ አያዩት መዓት የለም! ወዲህ ፖለቲካው፣ጎጠኝነቱ፣የኑሮ ልዩነቱ፣የሰውን ልጅ ጭካኔ ….የሀሳቡን ክርፋት ፣የግብሩን ክፋት ወዲያ ደግሞ በኃይማኖት ስም በየ አዳባባዩ እየወጡ የሚነቃቀፉ…በክርስቶስ ክርስቲያን መሆናቸውን ዘንግተው ጥድቅን በማይጨምሩላቸው ጉዳዮች ላይ አትኩረው …በነገር ሲጠባጠቡ …ሲጠዛጠዙ ውለው የሚያድሩትን ሐይማኖተኞችን/ሐሜተኞችን/ ማየት ያስገርማል፡፡
ከእነዚህ ሁሉ ልቆ ዘወትር የሚገርመኝ ደግሞ በየ ስብከቶቻቸው መኃል ዋናውን ዓለት/ክርስቶስን/ረስተው ስብከቶቻቸው ሁሉ በተጭበረበረ፣በተጠና ትንቢት እና በምድራዊ ድሎት ላይ ብቻ አድርገው ምዕመኖቻቸውን እንደ በግ የሚነዱ ግብራቸውም አስተምሮቶቻቸውም ሁሉ ቢዝነስ ተኮር የሆኑቱ ግለሰቦች እንደ አሸን ሲፈሉ መመልከቴ ነው፡፡ ደግሞ የመብዛታቸውን ያህል ይዘውት የሚመጡት አስገራሚ ነገርስ ብትሉ …አንዱ ላቡን የጠረገበትን ሶፍት ብሉ ሲል ሌላኛው ቅባት…ዘይት ወይ ሌላ ነገር ግዙ ሲል …ደግሞ ሌላኛው ወፈፌ እልም ባለ የቺቺኒያ ሙዚቃ ቤተ እምነት ውስጥ ደንሱ ሲል ….የአልጋ ላይ ቆይታቸውን በተመለከተ ውሳኔ ሲሰጥ …ውሳኔ ሲያሳልፍ …አጃኢብ ነው እኮ ነው፡፡
መቼም እንዲህ ያሉቱን ተኩላዎች የቀደሙ የኃይማኖት አባቶች ኑሮው አይተዋቸው ቢሆን ምን እንደሚሉ እሰቡት!
ወደ ነገረ ጉዳዬ ስመለስ ለዚህ ሁሉ ነገር መንደርደሪያ የሆነኝ ከወደ ደቡብ አፍሪካ የተሰማው ጉዳይ ነው፡፡
ነገሩ እንዲህ ነው እዚህ ምስሉ ላይ የምትመለከቱት ሰው ‹‹የፍፃሜ ቀን ደቀመዛሙርት››/End Times Disciples/ የሚል ቤተ እምነት ከፍቶ ሲንቀሳቀስ የነበረ እና እራሱን ነብይ ብሎ የሚጣራ ግለሰብ ነው፡፡
ታድያላችሁ ከቀናት በአንዱ ድንገት በአገልግሎቱ መኃየል እዛ ያሉ ምዕመናን ሁሉ ወንድ ከሴት ሳይለይ የውስጥ ሱሪያቸውን አውልቀው እንዲበሉ ያዛቸዋል፡፡ ይሄን ጊዜ ታድያ እንዲህም አድርጎ በጌታ ስም መቀለድ የለም ያሉ እና የነቁቱ ነብይ ባይ ነኝ ባዩን እንዳይሞት እንዳይድን አድርገው ይደበድቡታል፡፡ ‹‹ኣረ እርሱ ነብይ ነው እንዴት ይመታል ትዕዛዙ ይከበራል እንጂ›› ብለው ያሉቱም ከኑግ ጋር የተገኙ ሰሊጦች ሁነው እንዲህ እንደምትመለከቷቸው የኃሊት ተጠፍንገው በድብደባ ተስካራቸው ሊበላ ሲለ ፖሊሶች ደርሰው ታድገዋቸዋል፡፡
ቤተ እምነቱንም እንዲህ የሰከረ ፈረስ የገባበት በረት እስኪመስል አፈራርስ ወንበሮችንም ሰባብረው አቃጥለውታል፡፡
አሁን ይሄን ምን ይሉታል!
አጃኢብ ነው መቼም!

በጣም ልብ ይሰብራል!አሳዛኝ ክስተት!
11/12/2023

በጣም ልብ ይሰብራል!
አሳዛኝ ክስተት!

.......................የሚሄድ ነገር ያጓጓል .............ኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ነፍሱን የነጠቀው ብላቴና .ሁሉ ስራ በፍቅር በፍላጎት እና በኃላፊነት ሲሰራ ግብኣቱ ...
09/12/2023

.......................የሚሄድ ነገር ያጓጓል .............
ኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ነፍሱን የነጠቀው ብላቴና .

ሁሉ ስራ በፍቅር በፍላጎት እና በኃላፊነት ሲሰራ ግብኣቱ ከውጥኣቱ ጋር በልክ ይገጥምና ትክክለኛውን የስራ ትርጉም ይወስዳል፡፡ ከዛ በመለስ ግን ወር ቆጥሮ ደሞዝ ለመውሰድ እና ሰሩ ለመባል ብቻ የሚሰሩ ስራዎች የኃላ የኃላ በሕዝብ እና በሀገር ላይ የሚያስከትሉት ኪሳራ እንዲህ ነው ተብሎ የሚጠቀስ አይደለም …የትየለሌ ነው፡፡
‹‹ኣረ መላ በለኝ ልጄን፣የወንድሜን ልጅ፣ እከሌን …ዘመዴን …አዝማዴን አንድ ቦታ ወሽቅልኝ ››
ተብለው በአምቻና በጋብቻ ስለተዛመዱ ብቻ የስራ ቦታው የሚጠይቀውን በቂ የትምህርት ዝግጅት እና ልምድ ሳይዙ እንዲያው በዘ ፈቀደ በሲሾም ያልበላ…ያላስበላ በሲሻር ይቆጨዋል ስሜት በየ ድርጅቱ እንዲሰገሰጉ የተደረጉ ሰዎች ተገልጋዩን ሲያማርሩት እና በሚሰሩት ሰራ ሳቢያ ሀገር ከማትወጣው ኪሳራ ውስጥ ስትገባ በብዙ አስተውለናል፡፡
ለተመደቡበት ቦታ የሚሆን የትምህርት ዝግጅት ያላቸው ሰዎችም ቢሆን በሚፈጥሩት ቸልተኝነት ተነሳ የብዙ ድርጅቶች እና ግለሰቦች ሕይወት አደጋ ላይ ወድቋል፡፡
ዓመታዊ የተሽከርካሪ ምርመራን አልፎ ሕዝብ ሊያመላልስ ቀርቶ ቆሞ ቦታ ሊይዝ የማይገባውን ተሸከርካሪ በአሁኑ ዋጋው አንድ ኪሎ ሸንኩርት መግዛት በማይችል መደለያ አሳልፈው እና ወደ ስራ አሰማርተውት ከነ ጫናቸው ተሳፋሪዎች አደጋ ያደረሰ መኪና ቢቆጠር ብዛቱ ቀላል አይደለም፡፡
እንዲህ ያለው ስህተት እንደየ ሴክተር መስሪያ ቤቱ እና እንደሚሰጡት አገልግሎት ይለያያል፡፡
ለዛሬ ጽሑፌ መነሻ ሀሳብ የሆነኝ ጉዳይ የተከሰተው አንድ ዳተኛ እና ቸልተኛ የኢትዮጵያ ኤሌትሪክ ኃይል ሰራተኛ እጅግ ከፍተኛ ጥንቃቄ የሚፈልገውን የኤሌክትሪክ መስመር ዝርጋታ በዳተኝነት ምናልባትም በዕውቀት ማነስ ምክንያት ወደ አንድ ቤተሰብ ቤት የሚገባ የቆጣሪ መስመር ላይ በፈጠረው ስህተት እጅግ አስገራሚ እና አስደናቂ የሆነ ብሩህ አእምሮ ያለው የ12 ዓመት ታዳጊ ሕይወቱን ሊያጣ ችሏል፡፡
ይህ ሟች ቴዎድሮስ ናሆም የተባለን የ12 ዓመት ታዳጊ ከዚህ በፊት ላይ የመጨረሻው ፊደል የሚል ውድድር ላይ ከአባቱ ከአቶ ናሆም ጋር ቀርቦ ያደረገውን ጨዋታ መመልከት የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ኢትዮጵያን እንዴት ያለ ታዳጊ ልጅ እንዳሳጣት መረዳት ይቻላል፡፡
ከሟች ቴዎድሮስ አባት ጋር በጊዜ ሚዲያ የዩቱዩብ ቻናሌ ( ) ላይ በነበረኝ ቆይታ የተረዳሁት ነገር ቢኖር ቤተሰቡ እጅግ እጅግ በጣም ከባድ ሀዘን ውስጥ መሆኑን ነው፡፡ በተለይ አባትየው አቶ ናሆም ያለበት ሁኔታ እንዲህ በቀላሉ በቃል የሚገለጥ አይደለም፡፡ በጣም አሳሳቢ ደረጃ ላይ ነው የሚገኘው፡፡
‹‹የሚሄድ ነገር ያጓጓል …ሊሄድብኝ ነው ለካ ዘመኔን ሙሉ የጓጓሁለት›› ብሎ ተንሰቅስቆ አንሰቀሰቀኝ…..እህህህህ
በጣም ያብከነከነኝ ነገር ቢኖር ያ ከንቱ ሰራተኛ ዛሬም ምንም እንዳልተፈጠረ እዛው መስሪያ ቤቱ ውስጥ ስራውን ቀጥሏል፡፡ ምናልባትም ሌላ ቦታ ሌላ ተመሳሳይ ስህተት ሰርቶ ሌላ ነፍስ ነጥቋል፡፡ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይልም በድርጅቱ ሰራተኛ ምክንያት ለተፈጠረው ነገር ካሳም አልከፈለም ይቅርታም አልጠየቀም፡፡
ከቻላችሁ ከአባትየው ጋር ያደረኩትን ቆይታ ከታች ያኖርኩላችሁን ማስፈንጠሪያ ተጭናችሁ ተመልከቱት እና ልባችሁ ይፍረድ፡፡
ያቆየን
ኤልሻድ የሺ
ሕዳር 29 2016 ዓ.ም

https://youtu.be/PP3IF3nN_as?si=Eo5cvEs4vtmY5DqJ
27/11/2023

https://youtu.be/PP3IF3nN_as?si=Eo5cvEs4vtmY5DqJ

ቬሮኒካ አዳነ ከሰይፉ ጋር በነበራት ጨዋታ አንድ ቀን አምላኬን የማገለግል ዘማሪት ሆኜ እዚህ ወንበር ላይ ቁጭ ብለን እናዋራለንም ስትል ተደምጣለች፡፡እዚህ ጋር አንድ ነገር ለማንሳት ወ...

https://youtu.be/0NHABVe6Np0?si=IHvl3FmAeWR3pY4r
02/11/2023

https://youtu.be/0NHABVe6Np0?si=IHvl3FmAeWR3pY4r

አባታቸው ጥሏቸው ከሄደ እና ሌላ ሚስት ካገባ በኃላ በ14 ዓመቷ የቤተሰቡን ኃላፊነት የወሰደችው እርሷ ነች።በለምጣ ምክንያት ከፈቅ ሊወረውሯትን ነበር።አርሴማ ከትምህርት ቤት የሚሰጣት....

https://youtu.be/guCN3PK7Z5s?si=i6IcKuLNU7g21tjv
29/10/2023

https://youtu.be/guCN3PK7Z5s?si=i6IcKuLNU7g21tjv

ትላንት ወደድኩሽ አፈቀርኩሽ ብሎ ካገባት እና ለዓመታት አብረው ከኖሩ በኃላ 2ተኛ ልጃቸውን የ5 ወር ነፍሰጡር ሆና ሳለ አንድ ቀን እንደው ድንገት ከቤት ወጥቶ ይጠፋል።ከዛም ትንሽ ቆይቶ .....

10/10/2023

ጊዜ ሚዲያ በተለያዩ ስፍራዎች የሚገኙ የማህበረሰብ ክፍሎችን በመጎብኘት ያልታዩ፣ ያልተሰሙ እና ያልተዳሰሱ ጉዳዮችን ወደ ህዝብ በማምጣት ለተመልካች ያደርሳል! ለቻናላችን አዲስ ከሆኑ...

በጣም ልብ ይሰብራል!!!
10/10/2023

በጣም ልብ ይሰብራል!!!

ጊዜ ሚዲያ በተለያዩ ስፍራዎች የሚገኙ የማህበረሰብ ክፍሎችን በመጎብኘት ያልታዩ፣ ያልተሰሙ እና ያልተዳሰሱ ጉዳዮችን ወደ ህዝብ በማምጣት ለተመልካች ያደርሳል! ለቻናላችን አዲስ ከሆኑ...

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን አርቲስት ሰራዊት ፍቅሬን አመስግና በማዕረግ ሸለመችው።
06/09/2023

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን አርቲስት ሰራዊት ፍቅሬን አመስግና በማዕረግ ሸለመችው።

Address


Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethio Addis Mereja posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Ethio Addis Mereja:

Shortcuts

  • Address
  • Alerts
  • Contact The Business
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share