17/11/2023
በብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚደንት አቶ አደም ፋራህ የተመራ ልዑክ በሻንጋይ የተለያዩ ተቋማትን ጎበኘ
**************
በብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚደንት አደም ፋራህ የተመራ ከፍተኛ ልዑክ በቻይና ሻንጋይ ከተማ የተለያዩ ፕሮጀክቶችን እና ተቋማትን ጎብኝቷል፡፡
የልዑካን ቡድኑ አባላት የሁዋዌ ቴክኖሎጂ ማዕከልን፣ የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩትን፣ የሻንጋይ ከተማን እቅድና ዲዛይን እንዲሁም ደረቅ ቆሻሻን እንደገና ጥቅም ላይ የሚያውል ፕሮጀክትን መጎብኘቱ ተገልጿል፡፡
የጉብኝት መርሐ ግብሩ በሻንጋይ ከተማ ከሚከናወኑ ፕሮጀክቶች እቅድ፣ ትግበራ እና አፈጻጸም ልምድ ለመቅሰም ያለመ ሲሆን፤ ጉብኝት ካደረጉባቸው ተቋማት አመራሮች ጋርም የልምድ ልውውጥ ውይይት ማካሄዳቸው ተጠቁሟል፡፡
የጉብኝቱ ተሳታፊዎች በሻንጋይ ከተማ የተመለከቷቸውን ፕሮጀክቶች በኢትዮጵያ መተግበር የሚያስችል ተሞክሮ ማግኘታቸውን በቻይና የኢትዮጵያ ኤምባሲ መረጃ ያመላክታል፡፡