Lafto Woreda 15 Communication.

  • Home
  • Lafto Woreda 15 Communication.

Lafto Woreda 15 Communication. Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Lafto Woreda 15 Communication., Media, .

ኢትዮጵያ በአፍሪካ ሰላምን በማረጋገጥ ረገድ የመሪነት ሚናዋን መወጣት እንደምትቀጥል ሙሉ እምነት አለኝ - የደቡብ ሱዳን መከላከያ ሚኒስትር************************** ኢትዮጵያ ...
10/01/2022

ኢትዮጵያ በአፍሪካ ሰላምን በማረጋገጥ ረገድ የመሪነት ሚናዋን መወጣት እንደምትቀጥል ሙሉ እምነት አለኝ - የደቡብ ሱዳን መከላከያ ሚኒስትር
**************************

ኢትዮጵያ በቀጣናው ብሎም በአፍሪካ ሠላምን በማረጋገጥ ረገድ የመሪነት ሚናዋን መወጣት እንደምትቀጥል ሙሉ እምነት አለኝ አሉ የደቡብ ሱዳን መከላከያ ሚኒስትር አንጀሊና ቴኒ።

በደቡብ ሱዳን የኢትዮጵያ አምባሳደር ነቢል ማህዲ ከደቡብ ሱዳን መከላከያ ሚኒስትር አንጀሊና ቴኒ ጋር በወቅታዊ የኢትዮጵያ ጉዳዮች እና ቀጣናዊ ሁኔታዎች ላይ ውይይት አካሂደዋል።

አምባሳደር ነቢል ÷ አሸባሪው የህወሓት ቡድን በአማራ እና በአፋር ክልሎች የፈጸመውን ወረራ እና ግፍ አስመልክቶ ለደቡብ ሱዳን መከላከያ ሚኒስትሯ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

ኢትዮጵያውያን እና የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት በጥምረት በመቆም የሽብር ቡድኑን ወረራ እና የሽብር ተግባር ቀልብሰዋል ብለዋል አምባሳደሩ በውይይታቸው።

አሸባሪ ቡድኑ ያደረሰውን ጥፋት እና የንብረት ውድመትም በተቻለ መጠን ለመመለስ በተደረገው ጥረት በሀገር ውስጥ እና በውጪ ያሉ ኢትዮጵያውያን ትብብር ከፍተኛ እንደነበርም አንስተዋል።

የሱዳን መከላከያ ሚኒስትር አንጀሊና ቴኒ በበኩላቸው የኢትጵያ መንግስት የውስጥ ጉዳዮቹን በራሱ የመፍታት ሙሉ አቅም እንዳለው አሳይቷል ብለዋል።

አንጀሊና ቴኒ አያይዘውም፥ ኢትዮጵያ ሠላም መሆን ለቀጣናው ብሎም ለአፍሪካ ሠላም መሆን ዓይነተኛ ሚና እንዳለው አውስተው የምሥራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት( ኢጋድ ) ሚናም ለቀጣናው ሰላም ዋስትና መስጠት እንደሆነ አስረድተዋል።

አንጀሊና ቴኒ ኢትዮጵያ በቀጣናው ብሎም በአፍሪካ ሠላምን በማረጋገጥ ረገድ ያላትን የመሪነት ሚና መወጣቷን እንደምትቀጥል ሙሉ እምነት እንዳላቸውም ነው የገለጹት።

በደቡብ ሱዳን የኢትዮጵያ አምባሳደር ነቢል ማህዲ እና የደቡብ ሱዳን መከላከያ ሚኒስትር አንጀሊና ቴኒ ሁለቱን ሀገራት በሚመለከቱ ሌሎች ጉዳዮች ላይ መምከራቸውንም የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል።

በን/ስ/ላ/ክ/ከተማ የወረዳ 15 አስተዳደር ጠቅላላ አመራር የመጀመሪያዉን ዉይይት ዛሬ አድርጓል።የወረዳዉ የፓርቲ ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ጋሻዉ መብሬ ለአመራሩ የቀጣይ ስራዎችን ስምሪት ሰጥተዋል።...
05/01/2022

በን/ስ/ላ/ክ/ከተማ የወረዳ 15 አስተዳደር ጠቅላላ አመራር የመጀመሪያዉን ዉይይት ዛሬ አድርጓል።የወረዳዉ የፓርቲ ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ጋሻዉ መብሬ ለአመራሩ የቀጣይ ስራዎችን ስምሪት ሰጥተዋል።
ላፍቶ ወረዳ 15 ኮሙኒኬሽን
27/04/2014 ዓ.ም

Address


Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Lafto Woreda 15 Communication. posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

  • Address
  • Alerts
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share