Kilbatti Rasuk Gaaroyse Miracsenta /የኪልባቲ ረሱ ዐቃቤ-ህግ መምሪያ

  • Home
  • Kilbatti Rasuk Gaaroyse Miracsenta /የኪልባቲ ረሱ ዐቃቤ-ህግ መምሪያ

Kilbatti Rasuk Gaaroyse Miracsenta /የኪልባቲ ረሱ ዐቃቤ-ህግ መምሪያ Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Kilbatti Rasuk Gaaroyse Miracsenta /የኪልባቲ ረሱ ዐቃቤ-ህግ መምሪያ, Media, .
(1)

Kilbatti rasuk afxeera daqaarak gaaroyse ku/buxah saqalah yan gifta qali idriis cammadu away baaxo caddol yanih yan aniy...
07/01/2022

Kilbatti rasuk afxeera daqaarak gaaroyse ku/buxah saqalah yan gifta qali idriis cammadu away baaxo caddol yanih yan aniyyi gaadut afxeera daqaarih cule kala miraacisak burkaay,darsagita kee sifra miraacisak sugem kee away kaaduk kilbatti rasuk inaytah tan abqaala magaalal yekke wararat kaaduk afxeera cule kala miraacisak isi doorik awquk geytima lunaaka ani hay ni qaliyow

Qafar ag/ra/doolatak daga raaqa gaaroyseh maktab kilbatti rasuk affara daqaara axcihiy xalooluy,konnabay,magaale kee ere...
08/02/2021

Qafar ag/ra/doolatak daga raaqa gaaroyseh maktab kilbatti rasuk affara daqaara axcihiy xalooluy,konnabay,magaale kee erebti daqooritik temeeteh tan gaaroysay,poolis kee rasi kasleh sayyo kee alaaqat takke ganaysaqo wagittaamal abqaala magaala madqa tu-cubbus aydakaakan 2 ayroh yaceen

27/10/2020

በገንዘብ ኖቶች ላይ የሚፈፀሙ ህገወጥ ድርጊቶች እና የሚያስከትሉት የወንጀል
ተጠያቂነት!
----------------------------
ሰላም የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ የማህበራዊ ሚዲያ ተከታታዮቻችን
የህብረተሰቡን ንቃተ ህግ ማዳበር ያስችል ዘንድ በየሳምንቱ የተለያዩ ርእሰ
ጉዳዮችን በማንሳት ህግ ነክ ማብራሪያዎችን ወደናንተ እያደረስን እንገኛለን
በዚህ ሳምንትም "በገንዘብ ኖቶች ላይ የሚፈፀሙ ህገወጥ ድርጊቶች እና
የሚያስከትሉት የወንጀል ተጠያቂነት" በሚል ርእስ ያዘጋጀነዉን ፅሁፍ
እንድታነቡትና ራሳችሁን ከመሰል ህገወጥ ድርጊቶች እንድትጠብቁ ጋብዘናል!
መልካም ንባብ!
የገንዘብ ኖቶችን ገንዘብ ያሰኛቸዉ ወይም ትልቅ ዋጋ ያሰጣቸዉ የተሰሩበት
ወረቀት ዋጋ ዉድነት አልያም እላያቸዉ ላይ የሰፈሩት ምልከቶች ሳይሆኑ
በማህበረሰቡ ያላቸዉ ቅቡልነት በመሆኑ የገንዘብ ኖቶች እንደ መገበያያ
(Medium of exchange) ሆነዉ በማገልገል ተገቢዉን ሚና እንዲጫወቱና
በአንድ ሀገር የኢኮኖሚ እድገት ላይ አወንታዊ ሚና አንዲኖራቸዉ ከገንዘብ ኖቶች
ጋር በተያያዘ የሚፈፀሙ የወንጀል ድርጊቶችን በመከላከል የህጋዊ ገንዘቦችን
ጤናማ ዝዉዉር ማረጋገጥ እጅግ በጣም አስፈላጊና ለነገ የማይባል ተግባር
ነዉ፡፡
ህጋዊ ከሆኑ የገንዘብ ኖቶች ጋር ተመሳስለዉ የሚሰሩ የሀሰት ኖቶች የኑሮ
ዉድነትን(Inflation)፣ ማህበረሰቡ በመገበያያ ገንዘብ ላይ ያለዉን ዕምነትና
ጤናማ የሆነ የገበያ ስርአት ላይ ጉዳት የሚያደርስ፣ ህገ-ወጥ የሀብት ክምችት
እንዲኖር ምቹ ሁኔታን የሚፈጥርና ችግሩ እየተባባሰ ሲመጣም የኢኮኖሚ
ዉድቀትን (Economic depression) የሚያስከትል በመሆኑ ተመሳስለዉ
የሚሰሩ የገንዘብ ኖቶችን ለመከላከል ዉስብስብ የሆኑ የሚስጥር ኮዶችንና
ሌሎች ስልቶችን ከመጠቀም ባሻገር በድርጊቱ ተካፋይ የሆኑ ግለሰቦችን
በመለየት በወንጀል ተጠያቂ ማድረግ በሁሉም የአለማችን ሀገራት የተለመደ
ተግባር ነዉ፡፡
በሀገራችን ኢትዮጵያም በተመሳሳይ መልኩ ሀሰተኛ ገንዘቦችን የመስራትና
የማዘዋወር ድርጊት በ1997ዓ/ም በወጣዉ የኢ.ፌ.ድ.ሪ የወንጀል ህግ ከአንቀፅ
356 እስከ አንቀፅ 362 ባሉት ድንጋጌዎች መሰረት የወንጀል ተጠያቂነትን
የሚያስከትል ድርጊት ነዉ፡፡
ህገ-ወጥ ገንዘብ ማለት ምን ማለት እንደሆነ በወንጀል ህጋችን ላይ ትርጉም
ያልተሰጠዉ ቢሆንም ህገ-ወጥ ገንዘብን አስመልክቶ ከተደነገጉት የወንጀል
ድንጋጌዎች ይዘት በመነሳት ህገ-ወጥ ገንዘብ ማለት ህጋዊ የመገበያያ ገንዘብ
ሆነዉ እንዲያገለግሉ በህግ የመገበያያ ገንዘቦችን የመስራት ወይም የማሰራት
ስልጣን ባለዉ አካል አማካኝነት ወይም ፍቃድ ሰጪነት ከተሰሩት የመገበያያ
ገንዘቦች ጋር ተመሳስለዉ የተሰሩ ወይም ፍቃድ በሌለዉ አካል መሉ ለሙሉ
ህጋዊ የመገበያያ ገንዘቦችን ሆነዉ የተሰሩ የብር ኖቶች መሆናቸዉ ለመረዳት
ይቻላል፡፡
በሀገራችን በኢትዮጵያ ህጋዊ ገንዘብን የመቅረፅ፣ የማሳተም ወይም የማስቀረፅ፣
የማሳተምና የማሰራጨት ስልጣን በብሔራዊ ባንክ ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር
591/2000 አንቀፅ 5 ንዑስ አንቀፅ 1 መሰረት ለኢትዮጲያ ብሔራዊ ባንክ ብቻ
የተሰጠ ስልጣን በመሆኑ ማንም ሰዉ በኢትዮጲያ ዉስጥ ወይም ከኢትዮጲያ
ዉጪ ለማዘዋወር በማሰብ ህጋዊ ፈቃድ ሳይኖረዉ ህገ-ወጥ ገንዘቦችን የሰራ
እንደሆነ ከአምስት አመት በማያንስ ፅኑ እስራት እንደሚቀጣ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ
የወንጀል ህግ አንቀፅ 356 ላይ ሰፍሮ ይገኛል፡፡
ተመሳስለዉ ወይም ያለ ህጋዊ ፈቃድ ሆነዉ የሚሰሩ ገንዘቦችን ዝዉዉር
ለመከላከል ህገ-ወጥ ገንዘቦችን የመስራትን ተግባር የወንጀል ህግን
በመጠቀም ክልከላ ማድረግና(criminalizing approach) ተፈፅመዉ
ሲገኙም በዚህ ተግባር ላይ የተሰማሩትን ግለሰቦችን በወንጀል ተጠያቂ ማድረግ
እጅግ በጣም አስፈላጊና የተለመደ ተግባር ቢሆንም ምንጫቸዉ ያልታወቀ
ተመሳስለዉ የተሰሩ ገንዘቦች በገበያ ላይ በመበራከታቸዉ ምከንያት ድርጊቱን
ለመከላከል ህገ-ወጥ የብር ኖቶች የመስራትን ተግባርን ብቻ በህግ ተጠያቂ
ማድረግ በቂ አይደለም፡፡
በመሆኑም ህጋዊ ያሆኑ የመገበያያ ገንዘቦችን በመስራት ላይ የተሰማሩ
ግለሰቦችን በወንጀል ተጠያቂ ከማድረግ ጐን ለጐን በማዘዋወር ተግባር ላይ
የተሰማሩትን ግለሰቦች ተጠያቂ ማድረግም አስፈላጊ ነዉ፡፡
ህገወጥ የመገበያያ ገንዘብን በማዘዋወር ተግባር ላይ የተሰማሩ ግለሰቦች
የወንጀል ተጠያቂነት በሚመለከት በኢ.ፌ.ዴ.ሪ የወንጀል ህግ አንቀፅ 359 ላይ
ሰፍሮ የሚገኝ ሲሆን በዚህ የወንጀል ህግ ድንጋጌ መሰረት ማንም ሰዉ ሀሰተኛ
የሆኑ ወይም ተመሳስለዉ የተሰሩ የመገበያያ ገንዘቦችን እራሱ እንዲገለገልባቸዉ
ወይም እንዲዘዋወሩ በማሰብ ወደ ሀገር ዉስጥ ያስገባ፣ ከሐገር ያስወጣ ፣
የያዘ፣ ያስቀመጠ ወይም ያቀረበ እንደሆነ እስከ አስራ አምስት አመት በሚደርስ
ፅኑ እስራት ይቀጣል፡፡
ሁልጊዜ በሚባል መልኩ ተፈፀመ በተባለዉ የወንጀል ድርጊት ላይ የሀሳብ ከፍል
ስለመኖሩ ማለትም ተከሳሹ የወንጀል ድርጊቱን በወንጀል ህግ ቁጥር 58
መሰረት ሆንብሎ ወይም በቸልተኝነት የሚያስቀጡ የወንጀል ተግባራትን
በሚመለከት በአንቀፅ 59 መሰረት በቸልተኝነት የፈፀመ ስለመሆኑ የማስረዳት
ሸክም(burden of proof) የአቃቤ ህግ ቢሆንም ሀሰተኛ ገንዘብ ኖቶችን
የመስራት ወይም የማዘዋወር ወንጀልን በሚመለከት ሁል ጊዜ የሀሳብ ክፍል
(moral element ) አለ ተብሎ እንደሚገመት የወንጀል ህግ አንቀፅ 360 ላይ
ተደንግጎ ይገኛል፡፡
በመሆኑም ህገ-ወጥ ገንዘብ መስራት ወይም ማዘዋወር ወንጀል ፈፅሟል የሚል
ክስ የቀረበበትን ተከሳሽ ለማስቀጣት ተከሳሹ ግዙፋዊ ፍሬ ነገሩን ስመፈፀሙ
ማረጋገጥ ብቻ በቂ ነዉ፡፡
ስለሆነም ማንኛዉም አካል የገንዘብ ኖቶችን አስመልክቶ ከሚፈፀም ህገ ወጥ
ወንጀል ሊቆጠብ ይገባል መልእክታችን ነዉ፤ይህ ሳይሆን ቀርቶ ግን ወንጀሉን
ፈፅሞ ቢገኝ የወንጀል ተጠያቂነቱ ከላይ በተቀመጠዉ መሰረት የሚፈፀም
ይሆናል!

27/10/2020
26/10/2020

አመክሮ_ምንድን_ነዉ
አመክሮ የምንለው አንድ የሕግ እስረኛ የእስራት ቅጣት ተወስኖበት ከእስራት
ዘመኑ ሁለት ሦስተኛውን እንደፈጸመ የጠባዩ መሻሻል በበቂ ሁኔታ ሲመሰከር
ከእስር ቤት እንዲፈታ የሚፈቀድበት ሁኔታ ነው፡፡ ይህም ሲባል በሕጉ የተወሰነው
የአፈጻጸም ጊዜ ሲደርስና ጠቅላላው ሁኔታ ተሟልቶ ሲገኝ ጥፋተኛውን በአመክሮ
አስቀድሞ መልቀቅ የሚቻል መሆኑን ያመለክታል፡፡
አመክሮ ጠባይ ማሻሻያና ወደ ማህበራዊ ኑሮ መመለሻ መሳሪያ ነው፡፡ከዚህ
አኳያ አመክሮ የሚፈቀደው እስረኛው በጠባዩ ሆነ በጠቅላላ ሁኔታው የሚሻል
መሆኑ ሲታመንና ይህም ውጤት የሚያስገኝ መሆኑ ሲታመን ነው፡፡በአመክሮ
መፈታት መብት ሳይሆን በተጨባጭ ሊታይ ከሚችል የጠባይ መሻሻል የተነሳ
የሚፈቀድ ጉዳይ በመሆኑ ፍርድ ቤቱ እስረኛውን በአመክሮ ሊያስፈቱ የሚችሉ
ምክንያቶች መኖራቸውን ሲያረጋግጥና ይህም በማረሚያ ቤቱ ኃላፊ ሲደገፍ ብቻ
እስረኛው በአመክሮ እንዲፈታ ሊወሰን ይችላል፡፡
በእስራት እንዲቀጡ የተፈረደባቸው ታራሚዎች የተፈረደባቸው የእስራት ጊዜ
ከመፈፀሙ በፊት በሕግ በተወሰኑ ሁኔታዎች መሰረት በአመክሮ እንዲፈቱ
በኢትዮጵያ የወንጀል ሕግ አንቀጽ 113 ተደንግጓል፡፡ እንዲሁም በወንጀል ሕግ
አንቀጽ አንቀጽ 202 መሰረት ለአመክሮ የመፍታት ትዕዛዝ የሚሰጠው በፍርድ
ቤቶች ነው፡፡
ጥፋተኛዉ በሚፈረድበት ጊዜና ወደሚላክበት ተቋም በሚገባበት ጊዜ
የተወሰነበት ቅጣት ከመፈጸሙ በፊት ቀደም ብሎ በአመክሮ ሊለቀቅ የሚችል
መሆኑን : ይህንንም እድል ለማግኘት ምን ዓይነት ግዴታ መፈጸም
እንደሚገባዉ /እንዲያዉቀዉ/ ይገለጽለታል ::
# ለመልቀቅ_የሚያበቁ_ሁኔታዎች
በአመክሮ ለመልቀቅ ሕጋዊ ሁኔታዎች ተሟልተው ካልተገኙ በአመክሮ የመፍታት
ትዕዛዝ አይሰጥም፡፡ እነዚህ ሁኔታዎች በወንጀል ሕግ አንቀጽ 202 ተዘርዝረዋል
፡-
1) ከሁሉ በፊት ተቀጪው ከተወሰነበት የእስራት ጊዜ ውስጥ ከሦስት እጅ
ሁለቱን እጅ እንዲፈፅም ግድ ይላል ፣
2) ቅጣቱ የእድሜ ልክ እስራት በሆነ ጊዜ ተቀጪው ቢያንስ ሀያ ዓመት በእስር
ሊቆይ ይገባል : ቀጥሎ ፍርድ ቤቱ ጥፋተኛዉን በአመክሮ እንዲፈታ ትእዛዝ
የሚሰጠዉ :-
# ሀ ) አስፈላጊ የሆነውን ነፃነት የሚያሳጣ ቅጣት ወይም የጥንቃቄ እርምጃ
በመፈፀም ላይ ሳለ በስራውና በጠባዩ የተረጋገጠ መሻሻል ማሳየት ይኖርበታል፣
(የወንጀል ሕግ 202/1/ሀ/)
# ለ ) በተጨማሪም ጉዳዩም የሚመለከተው ተቀጪ በሰራው ወንጀል ምክንያት
ለደረሰው ጉድለት መጠገኛ ይሆን ዘንድ በፍርድ የተወሰነበት ወይም ከተበዳዩ
ጋር የተስማማበት ካሳ ያለ እንደ ሆነ አቅሙ እስከፈቀደ ድረስ እንዲከፈል ያሻል፣
(የወንጀል ሕግ አንቀጽ 202/1/ለ/)
# ሐ ) አመሉና ጠባዩ በመልካም አኗኗር ለመኖር የሚያስችለው እና በአመክሮ
መፈታቱ መልካም ውጤት ሊያስገኝ ይችላል ተብሎ የታመነ እንደሆነ፣(የወንጀል
ሕግ አንቀጽ 202/1/ሐ/) የሚሉት ናቸው፡፡

25/10/2020
18/09/2020

ከ1 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር በታች የሆነን ገንዘብ በህገ-ወጥነት መያዝ
እንደማይቻል ተገለጸ፡፡
*****************************************
የፀጥታ ኃይሎች ከ1 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር በታች የሆነን ገንዘብ በህገ ወጥነት
መያዝ እንደሌለባቸው ተገለፀ።
የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሽዴ እና የብሄራዊ ባንክ ገዢ ዶክተር ይናገር
ደሴ በዛሬው እለት አዲሱን የብር ኖት ለውጥ ተከትሎ መግለጫ ሰጥተዋል።
በመግለጫው ላይም የብሔራዊ ባንክ ገዢ ዶክተር ይናገር ደሴ ከብር ኖት
ለውጡ ጋር በተያያዘ የተወሰነ ውዥንብር መፈጠሩን ገልጸዋል።
በዚህም የፀጥታ ሀይሎች በመቶ ሺዎች ይዘው የሚንቀሳቀሱ ሰዎችን እየያዙ
መሆኑን እና ይህም ተገቢ አለመሆኑን ጠቅሰው እስከ 1 ነጥብ 5 ሚልየን ብር
ያላቸው ሰዎች ያለመሳቀቅ መንቀሳቀስ እንደሚችሉ ገልጸዋል።
ከ1 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር በላይ መያዝን የሚከለክለው መመሪያ እንደ ነዳጅ
ማደያ እና ሌሎች ከፍተኛ ሽያጭ የሚያከናውኑ ተቋማትን እንደማይመለከትም
ተጠቅሷል።
ነገር ግን ባለሀብቶች በእነዚህ ተቋማት በኩል ገንዘባቸውን በዚህ መንገድ
እናስገባለን ብለው ከሞከሩ የንግድ ተቋማቱ የሽያጭ ታሪካቸው ክትትል
ስለሚደረግበት እንዳይሞክሩትም አሳስበዋል።
አንዳንድ ግለሰቦች መመሪያው ባንክ ብቻን የሚመለከት ነው በሚል በርከት ያለ
ገንዘብ በማይክሮ ፋይናንስ ተቋማት በኩል ለማስገባት ሙከራ እያደረጉ መሆኑ
የተገለፀ ሲሆን መመሪያው ለባንኮችም ለማይክሮ ፋይናስ ተቋማትም እኩል
የሚያገለግል ነው ተብሏል፡፡
በተለያዩ በባንኮች ሂሳብ በመክፈት ገንዘብ በትኖ ለማስቀመጥ የሚሞክሩ
ካሉም ይህንን የሚቆጣጠር ግብረ ሀይል በመቋቋሙ ይህንን ተግባር ፈጽሞ
በተገኙት ላይ ብራቸውን እስከ መውረስ የሚደርስ ህጋዊ እርምጃ እንደሚወሰድ
አስገንዝበዋል።
እንዲሁም በተለያዩ ሰዎች አማካኝነት ገንዘብ ማስቀመጥ እንዲሁም በሌላ ሰው
ስም ገንዘብ ማስገባት እንደማይቻልም ተጠቅሷል።
ከአሽከርካሪዎች ጋር በተያያዘም ከጎረቤት ሀገራት በተለይ የጅቡቲ
አሽከርካሪዎች ገንዘብ ይዘው ስለሚንቀሳቀሱ፤ ሁሉም ገንዘብ ህገ-ወጥ ነው
ተብሎ መያዝ እንደሌለበት በመግለጫው ተጠቅሷል።
አሽከርካሪዎች ከሀገር ሲወጡ እስከ 30 ሺህ ብር ይዘው መውጣት እንደሚችሉ፤
ሲገቡ ደግሞ እስከ 10 ሺህ ብር መያዝ የሚችሉ መሆኑም ታውቋል።
ሆኖም ግን በህገ-ወጥ መንገድ ብር በተሽከርካሪያቸው ውስጥ ደብቀው
ለማስገባት የሚመክሩ ካሉ እንደሚወረስባቸው ተጠቅሷል።
46 mins · Public

Kilbatti rasuk gaaroyse miracsenta kee giitisso buxa sittalih cattiimak qusbih xissiimak geytima giitisso buxah gasol co...
10/08/2020

Kilbatti rasuk gaaroyse miracsenta kee giitisso buxa sittalih cattiimak qusbih xissiimak geytima giitisso buxah gasol coox xaabisaanamih taama asaaku abak maacisen

Erebti daqaarak gaaroyse Ku/buxa  rasuk gaaroyse miracsenta luk cattiimak kovid 19 wagsiisak baaxo caddol yewqeh yan sis...
25/06/2020

Erebti daqaarak gaaroyse Ku/buxa rasuk gaaroyse miracsenta luk cattiimak kovid 19 wagsiisak baaxo caddol yewqeh yan sissik kukta kee kukti abnissoh yewqeh yan Eddie xinta kee 4 takke miracsenta wagittamal daqaarak miraacinuy, poolise, baxsale cayla kee miqem abitto qinxaaneytah asaakih ayro axcihiy 18/10/2012 I.l.l aynabaabad baritto yacen

Kilbatti rasuk Afxeera daqaarak gaaroyse Ku/buxa kovid 19 wagsiisak baaxo caddol yewqeh yan sissik kukta kee kukti abnis...
23/06/2020

Kilbatti rasuk Afxeera daqaarak gaaroyse Ku/buxa kovid 19 wagsiisak baaxo caddol yewqeh yan sissik kukta kee kukti abnissoh yewqeh yan edde xinta kee 4 takke miracsenta wagittaamal ayrok 15/10/2012 I.l.l daqaar poolisih yacen aydakaakana

Kilbatti rasih xintok xalol daqaarak gaaroyse Ku/buxa kovid 19 wagsiisak baaxo caddol yewqeh yan sissik kukta kee kukti ...
23/06/2020

Kilbatti rasih xintok xalol daqaarak gaaroyse Ku/buxa kovid 19 wagsiisak baaxo caddol yewqeh yan sissik kukta kee kukti abnissoh yewqeh yan edde xinta kee 4 take miracsentitte wagittaamal daqaar poolisih aydakaakan yacen

19/06/2020

ቀን 12/10/2012 ዓ/ም
የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ጥሰው የተገኙ አምስት (5) ግለሰቦች በገንዘብ ተቀጡ
በክልባት ራሱ በራህሌ ወረዳ በሀገራችን በኮሮና ወረርሽን ምክንያት የታወጀውን አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ቁጥር 3 / 2012 እና አዋጁን ለማስፈፅም የወጣውን ደንብ ቁጥር 466/2012 ቁጥር 3 በተራ ቁጥር 5 እና 21 ተላልፈው የተገኙ አምስት (5) ግለሰቦች በአቃቢ ህግ ክስ ተመስርቶባቸው በፍርድ ቤት በገንዘብ መቀጮ ተቀጡ፡፡
በአጠቃላይ ዘጠኝ ሽ (9000) ብር
ተቀጥተዋል፡፡
ስለሆነም ሁሉም የወረዳው ህዝብ እራሱንና ቤተሰቡን እንዲሁም ወገኑን ከወረርሽኝ ለመጠበቅ አስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ማክበርና ማስከበር ይጠበቅበታል እርምጃዎችንም አተናቅረን ስለምንቀጥ ሁሉም ህብረተሰብ የተከለከሉ ተግባራትን ሲፈፅም ወይም ሲያስፈፅም ያየ ሰው ጥቆማ እንዲሰጥ እንጠይቃለን ብለዋል፡፡
መረጃውን የበራህሌ ወረዳ አቃቢ ህግ ፅ/ቤት

Waysuk 08/ 2012I.L.LBaracle daqaarak garoose kutbeh buxa kee polis kutbeh buxaittalih gacak koronah kalali taama diggowt...
15/06/2020

Waysuk 08/ 2012I.L.L
Baracle daqaarak garoose kutbeh buxa kee polis kutbeh buxa
ittalih gacak koronah kalali taama diggowtoh baxaabaxsale
tamooma abak geytiman.
Tohuuk ugutak baxabaxasake madaaqa edde qeerisan
uwwaytiy uqrah edde antifiquk sugeeni gaabossa heenih
kimaalih ayro cararisen.
Madaaqa hirgaanam /xugaanam korinah dalka baxcisaamak
qimbot tan taamaay siltam faxxinta kinnuk woh dubuh hinnay
koronah dalka qawwadu akak tayyaaqe marak qimbo sabab
takkem tet kunnuk soolisnam faxxinta.
BISO MAXCO DAABIMTUH QAAFIYAT NINNIK

Qafar A/R/Doolatak Daga Raaqa Gaaroyseh maktaba Qusbih Bicisen Loogol Mabla Ucuya
14/06/2020

Qafar A/R/Doolatak Daga Raaqa Gaaroyseh maktaba Qusbih Bicisen Loogol Mabla Ucuya

Rakaakayak naharsi saqal massakaxxale cajji Awwal Qarba anxarin raatih caagid wagsiisak tatruse farmo
05/06/2020

Rakaakayak naharsi saqal massakaxxale cajji Awwal Qarba anxarin raatih caagid wagsiisak tatruse farmo

Beerak xabbahanam kulli num isil tan dirkik yawqem nek faxximta
04/06/2020

Beerak xabbahanam kulli num isil tan dirkik yawqem nek faxximta

Kulli num gaanun daga raaqiyyah rammitam dirkih kaal tan
30/05/2020

Kulli num gaanun daga raaqiyyah rammitam dirkih kaal tan

29/05/2020

ጠ/ሚ ዐቢይ በመጠንቀቅና ባለመዘናጋት ኮሮናን ማሸነፍ እንደሚገባ አስታወቁ
አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 21 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ
አሕመድ በመጠንቀቅና ባለመዘናጋት የኮሮናቫይረን ማሸነፍ እንደሚገባ
አስታወቁ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በፌስ ቡክ ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት ቫይረሱን ይበልጥ
በመጠንቀቅ እንዲሁም ባለመዘናጋት ማሸነፍና ማጥፋት እንደሚቻል
አስታውቀዋል።
በመልዕክታቸውም “ኮሮና ከሚያሸንፈን እናሸንፈው፤ ከሚዘምትብን
እንዝመትበት፤ ከሚያጠፋን እናጥፋው፤” ብለዋል።
መዘናጋት የኮሮናቫይረስ ወዳጅ መሆኑን ያነሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፥ “ኮሮና
ከመዘናጋት ጋር ከተባበረ አንችለውም፤ ሁለቱን መነጣጠል አለብንም” ነው
ያሉት።
መዘናጋት በመፈጠሩ ሳቢያም ሰሞኑን በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር
እየጨመረ ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ፥ ጥንቃቄ ለኮሮናቫይረስ
እንደማይመችም ጠቅሰዋል።
ቫይረሱ “ጥንቃቄ ባለበት ወይ አይደርስም፤ ወይ የከፋ ጉዳት አያደርስምም” ነው
ያሉት በመልዕክታቸው።
አሁን ላይ በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር ከእኛ መዘናጋት ጋር በተያያዘ
እየጨመረ መሆኑን አንስተው፥ ተባብሮ መነሳት እንደሚገባ ጠቁመዋል።
“ሁኔታው ሳይመርብን፣ እኛ እናምርበት። ኮሮና ሳያሸንፈን እናሸንፈው። ኮሮናን
የማሸነፊያ ቀን ዛሬ፣ የማሸነፊያ ሰዓት አሁን፣ የሚያሸንፈውም ሰው እርስዎ ነዎት”
ብለዋል።
ትናንት የኢፌዴሪ የጤና ሚኒስቴር ባወጣው እለታዊ ሪፖርቱ በአንድ ቀን ብቻ
100 ሰዎች በሀገሪቱ የኮሮናቫይረስ ተገኝቶባቸዋል።
ይህንንም ተከትሎ በሀገረቱ ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 831 ደርሷል።
# FBC
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር
ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ
እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።
2 hrs · Public

28/05/2020

በቀን 20/9/2012 ዓ.ም
የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ጥሰው የተገኙ ግለሰቦች በገንዘብ ተቀጡ
በኪልባቲ ረሱ አፍዴራ ወረዳ በሀገራችን በኮሮና ወረርሽን ምክንያት የታወጀውን
አስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ለማስፈፀም የወጣውን ደንብ ቁጥር 466/2012
ተላልፈው የተገኙ 15 ገለሰቦች ላይ በአቃቢ ህግ ክስ ተመስርቶባቸው በፍርድ
ቤት በገንዘብ ተቀጡ፡፡
የተቀጡትም ግለሰቦችም
3 ጫት ቤቶች ለያንዳንዳቸው 1000 ብር እና 1 ምግብ ቤት ባለቤት ደም 1000
ብር 5 ገለሰቦች ተሰባስበው ምጥጥ ሲጥጡ የነበሩ ለያንዳንዳቸው 2500 ብር
እና የመጥጥ ቤቱ ባለቤት 2 ግለሰቦች ለያንዳንዳቸው 1500 ብር እንደሁም
ተርፍ ሰው ጭነው የነበሩ 3 ባጃጆች ደግሞ ለያንዳንዳቸው 1000 ብር ፍ/ቤቱ
በመቅጣት በድምሩ 22500 ብር ከመቀጮ ገቢ መሆኑን የአፋዴራ ወርዳ ዐ/ህግ ጽ/ቤት አስታውቋል

27/05/2020

ከኢፌዲሪ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ
የተሰጠ ፕሬስ መግለጫ
*********************************************
በአገራችን የኮሮና ቫይረስ ከተከሰተበት እለት ጀምሮ በመንግስትና በባለድርሻ
አካላት በርካታ ተግባራት እየተከናወኑ ሲሆን ትዕዛዞች፣ ክልከላዎችና
መልዕክቶች እየተላለፉ ነዉ፡፡ እነዚህን መልእክቶችና ትእዛዞች ሰምቶ ለራስ
በመፈጸምና ሌሎችን እንዲፈፅሙት በማድረግ በኩል በአንዳንድ የህብረተሰብ
ክፍሎች የተሻሉ ሁኔታዎች ቢኖሩም ነገር ግን በርካታ በሚባለዉ ህብረተሰቡ
ዘንድ የመዘናጋት፣ የቸልተኝነትና በሽታዉን አስመልክቶ የሚሰጡ ትእዛዛቶች ወደ
ጎን በመተዉ የሚሰጡ መግለጫዎችን የመላመድና ትኩረት ያለመስጠት
ሁኔታዎች እየተስተዋለ ይገኛል፡፡
በቅርቡ በመንግስት ተቋማት፣ በልማት ድርጅቶችና በግል ተቋማት ወሰጥ
ያደረግነዉ ምልከታ ከቅደመ ጥንቃቄ ጋር በተያያዘ የመዘናጋት፣ ትኩረት
ያለመሰጠት ሁኔታ አሳሳቢ እንደሆነ ለማረጋገጥ ችለናል፡፡ ማህበረሰባችን
በተለያዩ ቦታዎች ላይ በተለይም በግብዒት ቦታዎችና በትራንስፖርት አገልግሎት
መሰጫ አካባቢ እያሳየ ያለዉ መዘናጋትና ህጎቹን ያለማክበር ጉዳይ አሳሳቢ
ነዉ፡፡
ይህ የኮሮና ቫይረስ በአገራችን በተገኘበት እና የአሰቸኳይ ጊዜ አዋጅ በታወጀበት
ሰሞን የነበሩ ጥንቃቄዎች ጋር ሰነጻጸር እየቀነሰ መዘናጋት እየጨመረ ሲሆን
በተቃራኒዉ አሁንም በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ
መምጣቱ እጅጉን አሳሳቢና ዋጋ የሚያስከፍል ጉዳይ እየሆነ ይገኛል፡፡
መንግስት በሽታዉን ለመከላከልና ስርጭቱን ለመቀነስ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ
አዉጆ ደንብና መመሪያዎችን በማዉጣት ተግባራዊ እያደረገ መሆኑ ይታወቃል፡፡
ከዚሁ ጋር በተያያዘ የሚኒስትሮች ኮሚቴ ከዚህ ቀደም የወጡ መመሪያ ቁጥር
1/2012 እና መመሪያ ቁጥር 2/2012 ማሻሻያዎችን የያዘ መመሪያ ቁጥር
4/2012ን አፅድቆ ስራ ላይ እንዲዉል አቅጣጫ ሰጥቷል፡፡
በዚሁ መሰረትም በመመሪያ ቁጥር 4 በኮድ 2 የቤት ተሸከርካሪዎች ተጥሎ
የነበረዉ ከፊል የእንቅስቃሴ ክልከላ ፣የማሰክ አጠቃቀም ፣ በአገር አቋራጭ
የህዝብ ተሸከርካሪዎች ላይ እንዲሆም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር
የመንግስት ሰራተኞች መግቢያና መዉጫ ስአት ላይ ማሻሻያ አድርጓል፡፡
የኮድ ሁለት የቤት ተሸከርካሪዎች ላይ መጣል ሚገባው የትራንስፖርት
ሚኒስቴር በኩል የተደረገውን ጥናት መነሻ በማድረግ በከፊል በመገደብ
ግለሰቦች ቤታቸዉ እንዲዉሉ በማድረግ የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመከላከልና
ለመቆጣጠር ታሳቢ ተድርጎ በሙሉና በጎዶሎ መለያ ቁጥር ከፊል እገዳ ተጥሎ
መቆየቱ የሚታወስ ሲሆን ሆኖም የኮድ 2 ተሸከርካሪ ባለቤቶች በታሰበዉ መልኩ
ቤታቸዉ ከመዋል ይልቅ የህዝብ ትራንስፖርት በመጠቀም እና ታርጋዎችን
እየቀያየሩ የመጠቀም ሁኔታ መታየቱ እንዲሁም ተራቸዉ ባልሆነ ቀን ቤታቸዉ
ከመዋል ይልቅ በሰፊዉ የመንቀሳቀስ ሁኔታ የተስተዋለ መሆኑ ክልከላዉን መልክ
መቀየር አሰፈላጊ ሆኗል፡፡
በመሆኑም በአጠቃላይ በኮድ ሁለት የቤት ተሸከርካሪዎች ተጥሎ የነበረዉ
ክልከላ ተነሰቶ አጠቃላይ የትራንስፖርት እንቅስቃሴውን ለመገደብ የሚያስችል
አማራጭ ክልከላ እንድተገበር የሚኒስትሮች ኮሚቴ ወስኗል፡፡
የእንቅስቃሴ ገደብ መቀነሻ አሰራሮች አንዱ የሆነዉ በሀገር አቋራጭ
ተሸከሪካሪዎች የሚንቀሳቀሱ ሰዎችን ቁጥር መቀነስ ነው፡፡
የዋጋ ጭማሪ ማድረግ ሰዎች ከቦታ ቦታ እንዳይንቀሳቀሱ ለመገደብ አሰተዋጽኦ
እንደሚያደረግ በትራንስፖርት ሚኒስቴር የተደረገው ጥናት ያመላክታል፡፡
በዚሁ መሰረት አገር አቋራጭ የህዝብ ማመላለሻ ተሸከርካሪዎች መደበኛ
የወንበር አቅማቸዉ ከ45(አርባ አምስት) ሰዉ በላይ የሆነ ተሸከርካሪዎች
የሚያስከፍሉት የታሪፍ ጭማሪ ከመደበኛ ዋጋዉ 75% እንዲሆን የተወሰነ ሲሆን
መደበኛ የወንበር ቁጥራቸዉ እስከ (45) አርባ አምስት ሰዉ የሆኑ የህዝብ
ማመላለሻ ተሸከርካሪዎች የሚያስከፍሉት የታሪፍ ጭማሪ ደግሞ 100% መሆኑ
ተወሰኗል፡፡
በተያያዘ የሚኒስትሮች ኮሚቴ በተሻሻለዉ መመሪያ መሰረት የማስክ
አጠቃቀምን አስመልክቶ ከቤት ዉጭ በማንኛዉም ቦታ የአፍና አፈንጫ መሸፈኛ
ማስክ ማድረግን ግዴታ እንዲሆን ወስኗል፡፡ የአፍና አፈንጫ መሸፈኛ ማሰክ
በፋብሪካዎች የተሰራ ወይም ባህላዊ ጨርቅ ሊሆን ይችላል፡፡ ይህን ግዴታ
በማሰፈጸም ረገድ የጸጥታ መዋቅሩ ኃላፊነት እንዳለበት ተወሰኗል፡፡
በሌላ በኩል የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ሰራተኞች የስራ
መግቢያ ስአት 1፡30 እንዲሆን የተቀመጠ ሲሆን መዉጫ ስአቱም 9፡30
እንዲሆን ተደርጎ ተሸጋሽጓል፡፡ ይህም የትራንስፖርት መጨናነቅ ለመቀነስ ነው፡፡
በአጠቃላይ የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የሁሉም
ህብረተሰብ ኃላፊነትና ግዴታ ያለበት በመሆኑ የሚታዩ መዘናጋቶችን እና ችላ
ባይነትን በመቅረፍ ሁላችንም ህግና ሥርዓቱን ማክበር ግዴታ እንደሆነ
በመገንዘብ መላዉ የሀገራችን ህዝብ እራሱ፣ቤተሰቡንና ሀገሩን የኮሮና ቫይረስ
ከሚያስከትለው ጉዳት ለአፍታም ሳይዘናጋ ለመጠበቅ ርብርብ እንዲያደረግ
ጥሪያችንን እናቀረባለን፡፡
የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ
ቀን፡- ግንቦት 19 ቀን 2012 ዓ.ም
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ
ለተጨማሪ መረጃ ስልክ፡- 0111-5-51-50-99

27/05/2020

ህዝባችንን ከኮሮና ወረርሽኝ ለመጠበቅ የህግ የበላይነትን ማረጋገጥ ለነገ
የማይባል ተግባር ነዉ!
-------------------------------------
ህዝባችንን ከኮሮና ቫይረስ ወርርሽኝ ለመጠበቅና ወረርሽኙን ለመቆጣጠር
እንዲያስችል የተቀመጡ ግዴታዎችን ህብረተሰቡ አዉቆ እንዲተገብራቸዉ
ከማድረግ በተጨማሪ ይህ ሳይሆን ቀርቶ በአንዳንድ ግዴለሽ ግለሰቦች
የህብረተሰባችን ጤናና ህይወት አደጋ ላይ እንዳይወድቅ በደንብ እና
በመመሪያዎች የተቀመጡ ክልከላዎችንና ግዴታዎችን እንዲተገብሩ በማድረግ
የህግ የበላይነት ጥያቄ ዉስጥ በማይገባበት መልኩ የህዝባችንን ሰብአዊ
መብት በመጠበቅ ህግን ለማስከበር ከመቼዉም ጊዜ በላይ መረባረብ
የሚያስፈልግበት ወቅት በመሆኑ የህግ የበላይነትን በማስከበር የህዝባችንን
ህይዎት ለመታደግ በቁርጠኝነት መስራት ያስፈልጋል ፡፡
በመሆኑም ከጤና ባለሙያዎችና ከሐይማኖት አባቶች የሚሰጡ ምክሮችን
የሚሰሙ፤ ከመንግስት የሚተላለፉ ህግ፣ ደንብና መመሪያዎችን የሚተገብሩ
የሚያከብሩ አልፎም የሚያስከብሩ በጎ ፈቃደኞችና በርካታ የህብረተሰብ ክፍሎች
እንዳሉ ሁሉ በተቃራኒዉ ደግሞ በግዴለሽነትና በመዘናጋት ምክሮችንና
ግዴታዎችን ጭምር የማይተገብሩ የህብረተሰብ ክፍሎች መኖራቸዉ የሌሎችን
በጤና የመኖር መብት አደጋ ላይ የሚጥሉና የቫይረሱን ስርጭት በከፍተኛ መልኩ
የሚጨምሩ በመሆናቸዉ የቫይረሱ ስርጭት አሁን ካለበት ፍጥነት በከፋ መልኩ
ከቁጥጥር ዉጭ ከመሆኑ በፊት እነዚህ አካላት ላይ ጠበቅ ያለና የወጡ ህጎችን
የማስከበር ስራ አስፈላጊ በመሆኑ ህብረተሰቡ ራሱን ብሎም ሌሎችን
ከመጠበቅ በዘለለ ከህግ አስከባሪዎች ጎን በመቆም ለራሱ ጤና ዘብ ሊቆም
ይገባል፡፡

Kilbatti rasuk konnabi daqaarak gaaroyse ku/buxa kovid 19 kalalu kee lowsiisih baaxo caddol yewqeh yan kukta abbinoysoon...
26/05/2020

Kilbatti rasuk konnabi daqaarak gaaroyse ku/buxa kovid 19 kalalu kee lowsiisih baaxo caddol yewqeh yan kukta abbinoysoonuh yeyyeqen tellemmo miracsenta ixximak 3/2012 wagsiisak konnabi magaala geytimta tellemmo abeenitih tu-cubbus baritto yacen

QIID MUBAARAK Inkih tan muslimiin kee Qafar ummattak Qiid nel yamqaytahallih kaaduk kovid 19 viyresik ninni kalallam kee...
23/05/2020

QIID MUBAARAK Inkih tan muslimiin kee Qafar ummattak Qiid nel yamqay
tahallih kaaduk kovid 19 viyresik ninni kalallam kee qaafiyat tu-taaxago neh tace feyu inkih abnisnam nek faxximta baxsaluk sissik kuktal waaso leh tan abtootak ninni nayxeexem nek faxximta

23/05/2020

የኢድ‒አልፈጥር በአልን እና የኮሮና ቫይረስን አስመልክቶ ለ41 የህግ
ታራሚዎች ይቅርታ ማድረጉን የአፋር ከልል የጠቅላይ አቃቢ ህግ መስሪያቤት
አስታወቀ ፡፡
ይቅርታ የተደረገላቸው ታራሚዎች በ5ት ዞን ከሚገኙ ማረሚያ ቤቶች ውስጥ 32
የክልል ታራሚዎች እና ከፌዴራል በተሰጠ ውክልና መሰረት ደግሞ በክልሉ
በሁለት ዞኖች ከሚገኙ የፌዴራል ታራሚዎች ውስጥ 9 ታራሚዎች በአጠቃላይ
41 የህግ ታራሚዎችን ይቅርታ ማድረጉን የከልል የጠቅላይ አቃቢ ህግ መስሪያ
ቤት ገልጾል ፡፡
የአፋር ከልል የጠቅላይ አቃቢ ህግ መስሪያቤት ወኪል ጠቅላይ አቃቢ ህግ
የሆኑት አቶ መሀመድ አብዱ እንደገለጹት ይቅርታ የተደረገላቸው ታራሚዎች
ታሳቢ የተደረገው መስፈርት አነስተኛ ወንጀል የሰሩና ጥፋታቸው እስከ3አመት
ሊያስፈርድባቸው የሚችሉ ታራሚዎችን መሆኑን በመግለጽ በዚህም የፌዴራል
እና የክልል ታራሚ የሆኑ 41 ታራሚዎች በይቅርታ የተፈቱ መሆኑን ተናግረዋል ፡፡
ከዚህ በፊትም የኮሮና ቫይረስን አስመልክቶ በመጀመሪያ ዙር በክልሉ ከሚገኙ
ከ5ቱም ማረሚያ ቤቶች 155 ታራሚዎችን በይቅርታ የለቀቀ መሆኑን አቶ
መሀመድ አብዱ አስታውሰዋል ፡፡
በሊላ በኩል ወኪል ጠቅላይ አቃቢ ህግ የሆኑት አቶ መሀመድ አብዱ በሀገራችን
የተከሰተውን የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ለመከላከል አስመልክቶ የወጣውን
የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ተግባራዊ እንዲሆን በመስራት ላይ የሚገኙ መሆኑን እና
አዋጁን በሚተላለፉም ላይ እርምጃ እየውስድን ነው ብለዋል

Kilbatti rasih xintok xalol daqaarak gaaroyse ku/buxa daqaarak fanteenah tan qadokuwah magaalal kovid 19 kalaloonu kee l...
22/05/2020

Kilbatti rasih xintok xalol daqaarak gaaroyse ku/buxa daqaarak fanteenah tan qadokuwah magaalal kovid 19 kalaloonu kee lowsisonuh baaxo caddol yewqeh yan sissik kuktal waaso leh tan abtoota yaysexeexegenimih taama asaaki macsenta abak maacisen

21/05/2020

በቀን 13/9/2012 ዓ.ም
የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ጥሰው የተገኙ ግለሰቦች በገንዘብ ተቀጡ
በኪልባቲ ረሱ በራህሌ ወረዳ በሀገራችን በኮሮና ወረርሽን ምክንያት የታወጀውን አስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ለማስፈፀም የወጣውን ደንብ ቁጥር 466/2012 ተላልፈው የተገኙ አምስት ግለሰቦች በአቃቢ ህግ ክስ ተመስርቶባቸው በፍርድ ቤት በገንዘብ ተቀጡ፡፡
የተቀጡትም ግለሰቦችም
1ኛ. አቶ ጎሩም ፉፁም በ13-09-2012ዓ.ም በበራህሌ ወረዳ በ01ቀበሌ ባጃጅ ላይ ትርፍ አንድ ሰው በመጫኑ
2ኛ. አቶ መሀመድ ከድር በ13-09-2012 ዓ.
በበራህሌ ወረዳ በ01ቀበሌ ባጃጅ ላይ ትርፍ አራት ሰው በመጫኑ
3ኛ. አቶ ከህሳይ ገ/አናንያ እና ራዳት ያሲን ሁሴን በ11-09-2012 ዓ.ም ከዳሎል ወረዳ በዳ ቀብሌ ወደ በራህሌ ወረዳ 01 ቀበሌ ከተፈቀደው ውጭ ትርፍ በህዝብ ማመላለሻ ቅጥቅጥ አውቶብስ አምስት ሰዎችን በመጫኑ
አቶ ከህሳይ ገ/አናንያ : ራዳት ያሲን ሁሴን እና ጎሩም ፉፁም እያዳንዳቸወን በ1000ብር (አንድ ሺህ ብር ) ሲቀጡ መሀመድ ከድር በ1500 ብር (በአንድ ሺህ አምስት መቶ ብር ተቀጥተዋል፡፡
ስለሆነም ሁሉም የወረዳው ህዝብ እራሱንና ቤተሰቡን እንዲሁም ወገኑን ከወረርሽኝ ለመጠበቅ አስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ማክበርና ማስከበር ይጠበቅበታል እርምጃዎችንም አጠናክረን ስለምንቀጥል ሁሉም ህብረተሰብ የተከለከሉ ተግባራትን ሲፈፅም ወይም ሲያስፈፅም ያየ ሰው ጥቆማ እንዲሰጥ እንጠይቃለን ብለዋል፡፡
መረጃውን የበራህሌ ወረዳ አቃቢ ህግ ፅ/ቤት

Kilbatti rasih xintok konnabi daqaarak gaaroyse ku/buxa kovid 19wagsiisak kalalonu kee lowsisonuh baaxo caddol yewqeh ya...
19/05/2020

Kilbatti rasih xintok konnabi daqaarak gaaroyse ku/buxa kovid 19wagsiisak kalalonu kee lowsisonuh baaxo caddol yewqeh yan sissik kuktay,edde xinta kee miracsentitte wagittamal daqaaral geytimtah tan poolis xagorti kee miqem abitto qunxaaneytah tu-cubbus baritto yacen

Rakaakayak daga raaqa gaaroyse maktaba kilbatti rasih xintok 8daqaarak temeete qadli xagortiy rasuk xinto saqolti kee qa...
14/05/2020

Rakaakayak daga raaqa gaaroyse maktaba kilbatti rasih xintok 8daqaarak temeete qadli xagortiy rasuk xinto saqolti kee qadli xagortih kovid 19wagsiisak baaxoh caddol yewqeh yan sissik kuktay,edde xinta kee miracsenta wagittamal abqaala magaalal tu-ced barittoy yecen

Kilbatti rasuk afxeera daqaarak gaaroyse ku/buxa kovid 19 lowsiisonuh baaxo caddol yewqeh yan sissik kukta wagsiisak daq...
12/05/2020

Kilbatti rasuk afxeera daqaarak gaaroyse ku/buxa kovid 19 lowsiisonuh baaxo caddol yewqeh yan sissik kukta wagsiisak daqaaral geytimta saay xagorti luk walal gexisen

Magaale daqaarak gaaroyse ku/buxa baaxo caddol kovid 19 wagsiisak yewqeh yan sissik kukta wagittamal daqaaral geytimta s...
08/05/2020

Magaale daqaarak gaaroyse ku/buxa baaxo caddol kovid 19 wagsiisak yewqeh yan sissik kukta wagittamal daqaaral geytimta saay xagorti luk walal gexisen

Address


Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Kilbatti Rasuk Gaaroyse Miracsenta /የኪልባቲ ረሱ ዐቃቤ-ህግ መምሪያ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

  • Address
  • Alerts
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share