Gonder TIMES

Gonder TIMES Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Gonder TIMES, Media/News Company, .

 #ሰበር ዜናበፌደራል መንግሥት እና በህወሓት መካከል ዳግም ግጭት ተቀሰቀሰ። # # # # # # # # # #ከፌደራል መንግሥት የተገኘ መረጃ እንደሚጠቁመው የጦርነት ጉሰማውን የጀመረው ህወሓት...
24/08/2022

#ሰበር ዜና
በፌደራል መንግሥት እና በህወሓት መካከል ዳግም ግጭት ተቀሰቀሰ።
# # # # # # # # # #
ከፌደራል መንግሥት የተገኘ መረጃ እንደሚጠቁመው የጦርነት ጉሰማውን የጀመረው ህወሓት ነው ። በተደጋጋሚ የሚያደርጋቸው ትንኮሳዎች ውጤት ስላላመጡለት ጦርነቱን ፈልጎታል። እንደ
ጅራፍ ራሱ ገርፎ ራሱ ለመጮህ እየሞከረ ነው ብሏል።

ኢትዮጵያ ለሰላም ሁሉንም አድርጋለች። ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ለመደራደር መንግሥት ወስኖ ተግባራዊ እንቅስቃሴ አድርጓል።
ሕወሓት ከጦርነት እንጂ ከሰላም ስለማያተርፍ የአፍሪካ ኅብረትን
አልተቀበለም፣ ተደራዳሪዎቹን አላሳወቀም፣ ቅድመ ሁኔታ ይደረድራል። (መጀመሪያ 11 ቀጥሎ 5 ቀጥሎ 3)፣ ተኩስ አቁም ፈርሷል ብሎ አውጇል፣ ተደጋጋሚ ትንኮሳ በምዕራብና ደቡብ ግንባር ፈጽሟል ሲል ከሷል።
ኢትዮጵያ ለሰላማዊ መፍትሔ አሁንም ቁርጠኛ ናት። ከተጠቃች ግን ሁሉንም ዐቅም ትጠቀማለች ሲል ለጉዳዩ ቀርበት ያላቸው ምንጮቻችን አረጋግጠዋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ የትግራይ ሰራዊት ወታደራዊ ኮማንድ በሰጠው መግለጫ በፌደራል መንግስት ጦር ተወርሬአለሁ ብሏል።
በደቡባዊ ግምባር በዛ ግምባር ከቆዩትና ከሌሎች አከባቢዎች ያሰባሰባቸው የአማራ ልዩ ሀይል ክፍለጦሮች፤የወሎ ፋኖ እና ሚሊሻዎችን ባለፉት አምስት ቀናት እያዘጋጀ ከቆዬ በኋላ የፌደራል መከላከያ ሀይል አካላት የሆኑት 6ተኛ እና 8ተኛ እግረኛ እዞችና የ2ተኛ 6ተኛ እና 8ተኛ ሜካናይዝድ ክፍለጦሮችን ጨምሮ ዛሬ ነሓሴ 18 ቀን 2014 ዓ/ም ከማለዳው 11 ሰዓት ጀምሮ በጩቤበር፤ ጃኖራ፤ ጉባጋላ እና ያሎው አቅጣጫዎች ወደ አላማጣ ባላና ብሶበር ሰፊ የማጥቃት ዘመቻ ጀምረ

 #ሰበር መረጃ@ዛሬ ንጋት ላይ በሰሜን ምስራቅ ኢትዮ-ኤርትራ ድንበር ፆረና ግንባር በርካታ ቁጥር ያለው የህወሓት ሀይል ለወረራ በዝግጅት ላይ እንዳለ በኤርትራ ሰራዊት በተወሰደበት ድንገተኛ ...
23/08/2022

#ሰበር መረጃ
@ዛሬ ንጋት ላይ በሰሜን ምስራቅ ኢትዮ-ኤርትራ ድንበር ፆረና ግንባር በርካታ ቁጥር ያለው የህወሓት ሀይል ለወረራ በዝግጅት ላይ እንዳለ በኤርትራ ሰራዊት በተወሰደበት ድንገተኛ የከበባ እርምጃ በርካታ ቁጥር ያለው ታጣቂ መደምሰሱ ታውቋል።

በውቄ ስታይል! 😠😠😠እቴ ልስጥሽ ፥ ለሚ ኩራን ከላዬ ገፍፌልዩ ዞንሽ ይስፋ ፥ እኔ ተሞጭልፌውሰጅ ቦሌን ሲያሻሽ ፥ ልደታንም ብትይእኔ ተጣብቤ ፥ ያንቺ ሰፍቶ ይታይየካንም ከፈለግሽ ፥ ካንቺ ...
17/08/2022

በውቄ ስታይል! 😠😠😠
እቴ ልስጥሽ ፥ ለሚ ኩራን ከላዬ ገፍፌ
ልዩ ዞንሽ ይስፋ ፥ እኔ ተሞጭልፌ
ውሰጅ ቦሌን ሲያሻሽ ፥ ልደታንም ብትይ
እኔ ተጣብቤ ፥ ያንቺ ሰፍቶ ይታይ
የካንም ከፈለግሽ ፥ ካንቺ አይበልጥም ወሰጅ
ዋኚባት ምድሪቷን ፥ ኬኛ ነው እያልሽ አርጅ
እንዳንባሻ ቆርሰሽ ፥ ከኮልፌ ካጠርሽው
ቀሪውንም ውሰጅ ፥ ሰልቅጠሽ ጨርሽው
ቂርቆስንም ብትይ ፥ አቃቂን ጨምረሽ
ከንፋስ ስልክ ላይ ፥ ጉለሌን ደምረሽ
አጥር እጠሪና ፥ ከልለሽ ከልለሽ
አራዳን ግን ተይው ፥ አትንኪ ትንፋሼን
እምዬን ማየት ነው ፥ የሚያኖረኝ እኔን!

ልዩ መረጃ‼️የሱማሌ ክልል ፕሬዘዳንት አቶ ሙስጠፋ ኡመር (ፍስጠፌ) ላይ ዛሬ ዲኬ በተባለው አካባቢ የግድያ ሙከራ ቢደረግባቸውም ሙስጠፌ በጀግናው የሱማሌ ክልል ልዩ ሃልና በአጃቢዎቻቸው ጥረት...
17/08/2022

ልዩ መረጃ‼️

የሱማሌ ክልል ፕሬዘዳንት አቶ ሙስጠፋ ኡመር (ፍስጠፌ) ላይ ዛሬ ዲኬ በተባለው አካባቢ የግድያ ሙከራ ቢደረግባቸውም ሙስጠፌ በጀግናው የሱማሌ ክልል ልዩ ሃልና በአጃቢዎቻቸው ጥረት የግድያ ሙከራው ሙሉ በሙሉ ከሽፏል:: ማምሻውን ከክልሉ ባለስልጣን ባገኘውት መረጃ መሰረት ሙስጠፌ ምንም እንዳልሆኑና ከበባውን የሱማሌ ክልል ልዩ ሃይል እና የሙስጠፌ አጃቢዎች በተቀናጀ መልኩ ከበባውን ሰብረው ወተዋል በማለት መረጃውን አድርሰውኛል::

 #ሰበር ዜናአቶ ደጀኔ ልመንህ የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ሁነው ተሾሙ~~~~~~የምዕራብ ጎጃም ዞን ብልጽግና ጽ/ቤት ኃላፊ የነበሩት አቶ ደጀኔ ልመንህ የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን...
15/08/2022

#ሰበር ዜና

አቶ ደጀኔ ልመንህ የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ሁነው ተሾሙ
~~~~~~
የምዕራብ ጎጃም ዞን ብልጽግና ጽ/ቤት ኃላፊ የነበሩት አቶ ደጀኔ ልመንህ የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ሁነው
ተሹመዋል።
አቶ ደጀኔ ልመንህ በተለያዩ የመንግሥት ኃላፊነት ቦታዎች ወረዳና ዞን አመራር ሆነው አገልግለዋል።
በተጨማሪም ከሀገር መከላከያ ሰራዊት አባልነት ጀመሮ የተለያዩ ኃላፊነቶችን በመያዝ ያገለገሉ ሲሆን ከወራሪው ውያኔ ጋር በነበረው የህልውና ዘመቻ ወቅት ግንባር አቅንተው ከጠላት ጋር
ተፋልመዋል።
ለአቶ ደጀኔ ልመንህ መልካም የስራ ዘመን እንዲሆንላቸው እንመኛለን።

13/08/2022

የምስራች ...... !!!
እስካሁን በትግራይ ወራሪ ቡድን ተይዞ የነበረውን የራያ ቆቦ ማህጎ (033) ቀበሌ ጀግናው የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊታችን ተቆጣጥሮታል !!! ላልሰሙ እንዲሰሙ ሼር አድርጉላቸው !!!
የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊትና ፋኖ ወደእኛ እየመጡ ሲያልፉ ካያችሁ አደራ ንገሩን እንሸሻለን (የጁንታው ቡድን
አባላት ማህጎ ሳይለቁ ከተናገሩት የተነገረን) ራያ አላማጣም ቀላል ይሆናል እያለ ይቀጥላል ....!!!
ድል ለኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት እና ኢትዮጵያውያን !!!
ዘላለማዊ ክብር ለኢትዮጵያ !!!

በሁለተኛው የዓለም ጦርነት በወንዝ ውስጥ ሰምጦ የነበረ ቦንብሳይፈነዳ ተገኘ።ጣሊያን ውስጥ በሁለተኛው የዓለም ጦርነት በወንዝ ውስጥ ሰምጦ እስከዛሬሳይፈነዳ የቆየ ግዙፍ ቦንብ በድርቅ ምክንያት...
08/08/2022

በሁለተኛው የዓለም ጦርነት በወንዝ ውስጥ ሰምጦ የነበረ ቦንብ
ሳይፈነዳ ተገኘ።
ጣሊያን ውስጥ በሁለተኛው የዓለም ጦርነት በወንዝ ውስጥ ሰምጦ እስከዛሬ
ሳይፈነዳ የቆየ ግዙፍ ቦንብ በድርቅ ምክንያት መገኘቱ ተዘገበ።
450 ኪሎ ግራም ወይም 1ሺ ፓውንድ የሚመዝነው ይህ ቦምብ
በድርቅ ምክንያት በተመናመነው ወንዝ ዳርቻ ላይ በአሳ
አጥማጆች እንደተገኘ ነው የተገለፀው።
የአገሪቱ ወታደራዊ ባልሥልጣናት በሰጡት ማብራሪያ ፥
ያለፈነዳው ይህ ቦንብ 240 ኪሎ ግራም የሚመዝን ፈንጂ መያዙን
ተናግረዋል።
ቦንቡ በጥንቃቄ እንዲፈነዳና እንዲበተን ለማድረግ ሲባልም ወደ
3 ሺ የሚጠጉ ነዋሪዎች ከአካባቢው እንዲነሱ መደረጉም
ተገልጿል።
በጣሊያን ከ70 ዓመታት በኋላ በተከሰተው አስከፊ ድርቅ
ያልተለመደ ሞቃታማ የአየር ሁኔታ እና ዝቅተኛ የዝናብ መጠን
በመፈጠሩ በሰሜናዊ ጣሊያን ያለውን የውሃ እጥረት እና የአየር
ንብረት ለውጥ ከፍ ያደረገው ሲሆን፥ የጣሊያኑ ትልቁ እና 650
ኪሎ ሜትር ይጓዝ የነበረው ፖ ወንዝ እየደረቀ መምጣቱም
ተጠቁሟል።
የሀገሪቱ ወታደራዊ ባለስልጣን ኮሎኔል ማርኮ ናሲ ለሮይተርስ
የዜና ወኪል እንደተናገሩት፥ በከፍተኛ ድርቅ ምክንያት በሁለተኛው
የዓለም ጦርነት በጣሊያን ፖ ወንዝ ውስጥ ሰምጦ የቆየውና
ያልፈነዳው ቦምብ በወንዙ ዳርቻ ላይ በዓሳ አጥማጆች
አማካይነዝት የተገኘ መሆኑን ቢቢሲ ዘግቧል።
ቦምቡ በትናንትናው እለት በባለሙያዎች አማካይነት ጥንቃቄ
በተሞላበት መንገድ እንዲፈነዳና እንዲበተን ለማድረግ ተችሏል።

በትግራይ የባንክ አገልግሎት ጀመረየመጀመሪያው የባንክ አገልግሎት በትግራይ ዳግምጀምሯል። ሌሎችም እንዲሁ ወደ አገልግሎት እንደሚገቡይገመታል። የባንክ፣ የቴሌና ማብራት አገልግሎት ህወሓትለድርድ...
08/08/2022

በትግራይ የባንክ አገልግሎት ጀመረ
የመጀመሪያው የባንክ አገልግሎት በትግራይ ዳግም
ጀምሯል። ሌሎችም እንዲሁ ወደ አገልግሎት እንደሚገቡ
ይገመታል። የባንክ፣ የቴሌና ማብራት አገልግሎት ህወሓት
ለድርድር ቅድመ ሁኔታ ማቅረቡ ይታወሳል። በዚህም
መሰረት DW tv እንደዘገበው ዛሬ የባንክ አገልግሎት
ዳግም ጅማሮ በስኬት ተጠናቋል ብሏል።

ከባልደራስ ፓርቲ በወቅታዊ ጉዳይ ዙሪያ የተሰጠ መግለጫጉዳዩየአማራ ተወላጆች ወደ አዲስ አበባ እንዳይገቡ ስለመከልከላቸው***ከዚህ ቀደም በቄሮነት የተደራጁ ወጣቶች በኦሮሚያ የፀጥታኃይሎች በመ...
08/08/2022

ከባልደራስ ፓርቲ በወቅታዊ ጉዳይ ዙሪያ የተሰጠ መግለጫ
ጉዳዩ
የአማራ ተወላጆች ወደ አዲስ አበባ እንዳይገቡ ስለመከልከላቸው
***
ከዚህ ቀደም በቄሮነት የተደራጁ ወጣቶች በኦሮሚያ የፀጥታ
ኃይሎች በመታገዝ ከአማራ ክልል ወደ አዲስ አበባ የሚጓጓዙትን
ተሳፋሪዎችን በየቦታው እያስቆሙ ሲያጉላሉ እንደነበር ይታወሳል።
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ቋሚ ፀረ-
አማራ ፖሊሲ በሚመስል መልኩ ከአማራ ክልል ወደ አዲስ አበባ
የሚጓጓዙ ተሳፋሪዎችን በተለይ ደብረ ብርሃንን ካለፉ በኃላ
በኦሮሚያ ልዩ ኃይል አውቶቡሶች እንዲቆሙ እየተደረገ የአማራ
ክልል መታወቂያ ያላቸው እንዲወርዱና እንዲመለሱ እየተገደዱ
ነው።
ሁሉም የሀገራችን ዜጎች በሁሉም የሀገሪቱ ግዛቶች ያለምንም
ቅድመ ሁኔታ የመንቀሳቀስ እና ሃብት የማፍራት የመማርና
የመኖር ተፈጥሯዊም ሆነ ህገ- መንግስታዊ መብት አላቸው።
ነገር ግን ይህ ሆኖ ሳለ በቅርቡ ከአማራ ክልል ወደ አዲስ አበባ
የሚመጡ አማራዎች ምንም ወንጀል ሳይፈፅሙ አማራ ስለሆኑ
ብቻ በተረኛው የኦህዴድ መራሹ ብልፅግና ስርዓት አስፈፃሚዎች
ወደ አዲስ አበባ አትገቡም ተብለው ከፍተኛ የሆነ መጉላላትና
እንግልት እንዲሁም በደል እየደረሰባቸው ይገኛል።
በመሆኑም ገዥው መንግስት ይህን የአፓርታይድ ድርጊቱን
እንዲያቆም ዜጎች ሰብአዊ መብታቸው ተከብሮ ከቦታ ቦታ
ተንቀሳቅሶ የመኖር መብታቸውን እንዲያስከብር እናሳስባለን።
እንዲሁም መላው የሀገራችን ህዝብ ይህን ድርጊት በፅኑ
እንዲያወግዝ እየጠየቅን ፓርቲያችንም ጉዳዩን እየተከታተለ
የሚያሳውቅ መሆኑን በዚሁ አጋጣሚ እንገልፃለን።

 # እውነተኛ__ታሪክ /የደግነት ጫፍ/ሁለት ሰዎች በአንድ ሆስፒታል ክፍል ውስጥ አልጋ ይዘውተኝተዋል! ... ሁለቱም በጠና ታመው በአምላክ እጅ ተይዘዋል።አንደኛው ሳንባው የቋጠረውን ውሀ ለማ...
08/08/2022

# እውነተኛ__ታሪክ /የደግነት ጫፍ/
ሁለት ሰዎች በአንድ ሆስፒታል ክፍል ውስጥ አልጋ ይዘው
ተኝተዋል! ... ሁለቱም በጠና ታመው በአምላክ እጅ ተይዘዋል።
አንደኛው ሳንባው የቋጠረውን ውሀ ለማድረቅ ሲባል
ለሰአታት ያህል አልጋው ላይ ቁጭ እንዲል ይደረጋል ...
ከመስኮት አጠገብ ነው።
ሌላኛው ህመምተኛ ደግሞ በተቃራኒው ለሰአታት
በጀርባው እንዲተኛ ይደረጋል።
እነዚህ ህሙማን በቆይታቸው ብዙ ተጨዋውተዋል። ስለ
ቤተሰቦቻቸው፣ ስለ ኑሯቸው፣
በወታደር ቤት ስለሰጡት አገልግሎት፣ የእረፍት ጊዜያቸውን የት
እንደሚያሳልፉ... ወዘተ
አውርተዋል።
⚂ከመስኮት አጠገብ ያለው ህመምተኛ ቁጭ በሚልበት ሰአት
ወደ
ውጭ እየተመለከተ
ሁሉን ነገር # በጀርባ ለተኛው ሰው ይገልጽለታል።
".....በሚያማምሩ ዛፎች የተከበበ ሀይቅ ይታየኛል ... በሀይቁ
ላይ ዳኪዬዎች ይዋኛሉ...... ህጻናት ደግሞ ከወረቀት የሰሩትን
መርከቦች በሀይቁ ዳርቻ በማስቀመጥ ይጫወታሉ...
ፍቅረኛሞች በአንድ
እጆቻቸው አበባ በሌላው ደግሞ ተቃቅፈው ሀይቁን ይዞራሉ ..
ከሀይቁ ባሻገር ውብ
የሆነ ከተማ ይታየኛል .... ህፃናቶችም በደስታ ይቦርቃሉ "
በማለት ዘወትር የሚያየውን ሁሉ በሚያምር አገላለፅ
ይተርክለታል! ... በዚህ
አይነት ሁኔታ ሳምንታት አለፉ።
አንድ ማለዳ ነርስዋ ገላቸውን ልታጥብ ውሀ ይዛ መጣች።
ከመስኮት አጠገብ ያለው የተቀመጠው
በሽተኛ ግን በህይወት አልነበረም። በጣም ደነገጠች።
ጓደኛውም እንዲሁ አዘነ።
ነርስዋ አስከሬኑን በቶሎ እንዲያነሱ ሰዎች ሌሎች ነርሶችን
ጠርታ አዘዘቻቸቸው! ...
ያ ብቻውን የቀረው በጀርባው የተኛው በሽተኛ አልጋውን
ከመስኮቱ አጠገብ እንዲወስዱለት ጠየቀ።
ወሰዱለት።
ሟች የነገርውን በሙሉ በመስኮት ለማየት በጣም ቸኩሏል። ቀና
ብሎ ወደ
ውጭ ተመለከተ። ከመስኮቱ ባሻገር ያለው ጥቁር ቀለም የተቀባ
ግድግዳ ብቻ ነው። ደነገጠ!!!
"ምን ሆንክ?" አለቸው ነርሰዋ። "ሰዉዬው ብዙ አስደሳች
ነገሮችን በዚህ መስኮት
አሻግሮ ይመለከት ነበር" አላት። "ኧረ ሰዉዬው ማየት የማይችል
# አይነስውር ነበር
አለችው።"
ልብ የሚነካ ነገር.... ስቅስቅ ብሎ አለቀሰ። ለካስ እሱን
ለማስደሰትና የመኖር ተስፋ
ለመስጠት ነበር ያን ሁሉ ነገር ፈጥሮ የሚያወራው።
******
አንዱን ለማጠንከር ወይም ለማበርታት የኛ ጥንካሬና ብርታት
አስፈላጊ ነው።
ለሰወች ደግ ነገር በማድርግ
የተጨነቀ አምሮአቸውን ፈታ ዘና
እናድርግ
ስለዚህ ይሄንን ታሪክ ሼር በማድርግ
ደስታን እናስተምር፣
እንማር
አስተማሪ አዳዲስ ፓስቶች እንዲደርስወ
ፔጁን ላይክ፣ሼር ያርጉት

08/08/2022

Gonder Times share እና like ያድርጉ!!!
በጎንደር ታይምስ ወቅታዊ መረጃዎችንና መዝናኛዎችን ያገኛሉ። ስለተለያዩ ታሪካዊና መንፈሳዊ ቦታዎች መረጃዎችን ያገኙበታል።

Address


Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Gonder TIMES posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

  • Address
  • Alerts
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share