የስልጤ ኤፍ ኤም 92.6//Siltie FM 92.6

  • Home
  • የስልጤ ኤፍ ኤም 92.6//Siltie FM 92.6

የስልጤ ኤፍ ኤም 92.6//Siltie FM 92.6 Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from የስልጤ ኤፍ ኤም 92.6//Siltie FM 92.6, Radio Station, .
(2)

የስልጤ ዞን ፍትህ መምሪያ ሠራተኞች በምስራቅ ስልጢ ወረዳ የሚገኘውንና በዞኑ ከሚገኙ ድንቅ የቱሪስት መስህቦች መካከል አንዱ የሆነውን የአበያ/ጡፋ ሀይቅ ጎብኝተዋል።  ህዳር 06/2016 የስ...
16/11/2023

የስልጤ ዞን ፍትህ መምሪያ ሠራተኞች በምስራቅ ስልጢ ወረዳ የሚገኘውንና በዞኑ ከሚገኙ ድንቅ የቱሪስት መስህቦች መካከል አንዱ የሆነውን የአበያ/ጡፋ ሀይቅ ጎብኝተዋል።

ህዳር 06/2016

የስልጤ ዞን ፍትህ መምሪያ ሠራተኞች ከ2016 ዓ.ም የመጀመሪያ ሩብ አመት የዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ በኃላ በዞኑ ምስራቅ ስልጢ ወረዳ የሚገኘውንና በዞኑ ከሚገኙ ድንቅ የቱሪስት መስህቦች መካከል አንዱ የሆነውን የአበያ/ጡፋ ሀይቅ ጎብኝተዋል።

የተቋሙ ሠራተኞች በ2015 ዓ.ም የዕቅድ አፈፃፀም ምዘና በፐብሊክ ሰርቪስ እና በዞኑ ምክር ቤት የተሰጠው ሽልማት የተቋሙ ሁሉም ሠራተኞች የጥረት ውጤት በመሆኑ ተቋሙ የተሰጠውን እውቅናና ማትጊያ ምክንያት በማድረግ ለሁሉም የተቋሙ ሠራተኞች ምስጋና ያቀረቡት የዞኑ ፍትህ መምሪያ ኃላፊ ይህ ጉብኝት የዚህ እውቅናና ምስጋና መርሃ ግብር አካል እንደሆነ አንስተዋል። መረጃው የስልጤ ዞን ፍትህ መምሪያ ነው።

ለበለጠ መረጃ ከስር ባሉ የሚዲያ አማራጮች ቤተሰብ ይሁኑ።
👉 ፌስቡክ:-https://www.facebook.com/profile.php?id=100082825107454&mibextid=ZbWKwL

👉 Online:- https://zeno.fm/radio/silte-fm-92-6-radio/

👉 ቴሌግራም ቻናል:- https://t.me/siltieFM

👉 ዩቲዩብ:-https://youtube.com/.6?si=hRXBMraXGNfs-r15

👉 ቲክቶክ:-https://www.tiktok.com/.fm.92.6?_t=8grgs10DJyv&_r=1

የቴክኒክና ሙያ ስልጠና መግቢያ ነጥብ ይፋ ሆነ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር በ2016 ዓ.ም የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ተቋማት ገብተው በተለያዩ የሙያ መስኮች ስልጠና የሚወስዱ ተማሪዎች የመግቢያ ነ...
16/11/2023

የቴክኒክና ሙያ ስልጠና መግቢያ ነጥብ ይፋ ሆነ

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር በ2016 ዓ.ም የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ተቋማት ገብተው በተለያዩ የሙያ መስኮች ስልጠና የሚወስዱ ተማሪዎች የመግቢያ ነጥብ ይፋ አድርጓል፡፡

የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል÷ ዜጎች ወደ ቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ተቋማት የሚመጡት መሄጃ ስላጡ ሳይሆን ያላቸውን እምቅ አቅም አውጥተው መጠቀም እንዲችሉ ነው ብለዋል፡፡

ይህም የቴክኒክና ሙያ ተቋማት ለዜጎች ዕድል ፈጣሪ አቅሞች እና ተጨማሪ አማራጭ የሚሰጡ ተቋማት ያደርጋቸዋል ነው ያሉት፡፡

ከባለፈው ዓመት ጀምሮ ተግባራዊ እየተደረገ ባለው አዲሱ የትምህርትና ሥልጠና ፖሊሲ መሰረት ከዚህ ቀደም እስከ ደረጃ 5 ብቻ ተገድቦ የነበረው የቴክኒክና ሙያ ስልጠና የእድገት መሰላል እስከ ደረጃ 8 ድረስ እዲሆን መደረጉ ጠቁመዋል፡፡

ይህም ፖሊሲው ደረጃ ስድስትን ከመጀመሪያ ዲግሪ፣ ደረጃ ሰባትን ከማስተርስ እንዲሁም ደረጃ ስምንትን ከዶክትሬት ዲግሪ ትይዩ እንዲሆን አድርጓል ሲሉ ገልጸዋል፡፡

ስለሆነም በዚህ ዓመት የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ነጥብ ያመጡ ተማሪዎች ወደ ቴክኒክና ሙያ መግባት ቢፈልጉ በደረጃ 6 ገብተው መሰልጠን እንደሚያስችላቸው አመላክተዋል፡፡

ዘንድሮ ለመጀመሪያ ጊዜ በደረጃ 6 የቴክኒክና ሙያ ሰልጣኞች እንደሚስተናገዱ ጠቁመው÷ በዚህ ዓመት በተቀመጠው መስፈርት መሰረት በክልሎች አማካኝነት የሰልጣኞች ምደባ ይካሄዳል ብለዋል፡፡

በዚህም በተያዘው የሥልጠና ዘመን 632 ሺህ በላይ ተማሪዎች የሥራ ገበያውን የሰው ሃይል ፍላጎት መሠረት ባደረገ መልኩ ከደረጃ 1 እስከ ደረጃ 5 እንደ ውጤታቸው ተመድበው እንደሚሰለጥኑም ጠቅሰዋል፡፡

በወጣው መቁረጫ ነጥብ መሰረት ደረጃ አንድ እና ሁለት 110 ሺህ 15 ፣ በደረጃ ሦሰት እና አራት 412 ሺህ 557 እንዲሁም በደረጃ አምስት 110 ሺህ 15 ሰልጣኞች እንደሚሳተፉ አንስተዋል፡፡

በደረጃ ስድስት ደግሞ 2 ሺህ የሚሆኑ ሰልጣኞችን ለቀመበል ዝግጅት እንደተደረገ መናገራቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡

የ2016 የስልጠና ዘመን የተዘጋጀው መቁረጫ ነጥብ የ2015 ትምህርት እና የ2014 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ ፈተና የወሰዱ ተማሪዎች ላይ ተግባራዊ ይሆናልም ብለዋል፡፡

ከ2014 ዓ.ም በፊት ለነበሩ የ12ኛ ክፍል ተፈታኞች ደግሞ በስልጠና ዘመኑ በነበረው መቁረጫ ነጥብ መሰረት እንደሚስተናገዱ ተጠቁሟል፡፡

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር በ2016 ዓ.ም ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ተቋማት ያዘጋጀው የመግቢያ ነጥብ ከዚህ በታች ባለው ሰንጠረዥ ቀርቧል፡-

ኤፍ ቢ ሲ

በሀገር ውስጥ ከሚገኙ የኢትዮጵያ ዲያስፖራ አባላት ጋር የሚካሄድ የውይይት መድረክን በተመለከተ የተሰጠ መግለጫ።የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በሀገር ወስጥ ከሚገኙ የዲያስፖራ ማህበረሰብ ...
16/11/2023

በሀገር ውስጥ ከሚገኙ የኢትዮጵያ ዲያስፖራ አባላት ጋር የሚካሄድ የውይይት መድረክን በተመለከተ የተሰጠ መግለጫ።

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በሀገር ወስጥ ከሚገኙ የዲያስፖራ ማህበረሰብ አባላት ጋር ውይይት ሊያደርግ ነው፡፡

ለምክክሩ ሂደት ስኬታማነትና ለምክረ ሀሳቦች ተግባራዊነት ቁልፍ ከሆኑ ጉዳዮች መካከል አንዱ የሂደቱ አካታችነትና አሳታፊነት ነው፡፡ ይህንንም ለማረጋገጥ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ነባራዊ ሁኔታዎችን ከግምት በማስገባት ሂደቱን አካታችና አሳታፊ ለማድረግ ሥራዎችን እየሰራ ነው፡፡ ከነዚህም መካከል የዲያስፖራው ማኅበረሰብ ይገኝበታል፡፡

የዲያስፖራው ማህበረሰብ በምክክር ሂደቱና ኮሚሽኑ በሚያከናውናቸው ተግባራት ላይ በቂ ግንዛቤ ኖሮት በሂደቱ ንቁ ተሳታፊ እንዲሆንና እንደ አንድ ባለድርሻ አካል ተገቢውን በጎ አስተዋጽኦ ለማበርከት እንዲችል ምቹ ሁኔታን ለመፍጠር የመድረኩ መዘጋጀት አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል፡፡

የዲያስፖራ ማህበረሰቡ በሀገር ግንባታ ሂደት ውስጥ በማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ጉዳዮች ላይ የራሱን አስተዋጽኦ ሲያበረክት መቆየቱና አሁንም በተለያየ አግባብ ሚናውን እየተወጣ እንደሆነ ይታወቃል፡፡ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ሰፊ ቁጥር ያለውና በተለያዩ አገራት የሚኖረው የዲያስፖራው ማህበረሰብ ይህንኑ ሚናውን ግምት ውስጥ በማስገባት በሀገራዊ ምክክሩ ላይ እንዲካተትና እንዲሳተፍ ለማድረግ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ይገኛል፡፡

በዚሁ መሠረት የዲስፖራው ማህበረሰብ በሂደቱ ንቁ ተሳትፎ እንዲያደርግና ለገራዊ ምክክሩ የበኩሉን ገንቢ ሚና እንዲጫወት ምቹ ሁኔታን ለመፍጠር ከኢትዮጵያ ዲያስፖራ ማህበራት ህብረት ጋር በመተባባር የውይይት መድረኩን አዘጋጅቷል።

ቅዳሜ ህዳር 8 2016 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡30 ጀምሮ ለግማሽ ቀን በአዲስ ፓርክ/ ሚሊኒየም አዳራሽ/ በሚካሄደው በዚሁ የውይይት መድረክ ቁጥራቸው ከ 700 የማያንስ በሀገር ውስጥ የሚገኙ የዲያስፖራ ማህበረሰብ አባላት ይሳተፋሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

በመድረኩ ስለ ሀገራዊ ምክክር 5 ምንነት፣ በኢትዮጵያ በሂደት ላይ ያለው ሀገራዊ ምክክር አላማዎች፣ እንዲሁም የምክክሩን ሂደት የሚመራው የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን እስካሁን ያከናወናቸው ዋና ዋና ተግባራትና ቀጣይ ዕቅዶቹ ላይ ግንዛቤ በመፍጠር ለሂደቱ መሳካት በዲያስፖራው ማህበረሰብ ተሳትፎና ሚና ዙሪያ ሰፊ ውይይት በማድረግ መግባባት ላይ ይደረሳል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

መድረኩ ኮሚሽኑ ከተለያዩ ባለድርሻ ካላት ጋር የሚያካሂዳቸው የቅድመ ምክክር መድረክ አካል ሲሆን በቀጣይም ይህን መሰል መድረክ ተጠናክሮ ይቀጥላል፡፡

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን!!

ህዝብ ለሚየነሳቸው ጥያቄዎች አድምጦ ምላሽ መስጠት ከጠንካራ መሪ የሚጠበቅ የሁልጊዜ ተግባር ሊሆን እንደሚገባ  የስልጤ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ገለፀ። ህዳር 6/2016 ሃሳቡ የተገለጸው የፓርቲው...
16/11/2023

ህዝብ ለሚየነሳቸው ጥያቄዎች አድምጦ ምላሽ መስጠት ከጠንካራ መሪ የሚጠበቅ የሁልጊዜ ተግባር ሊሆን እንደሚገባ የስልጤ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ገለፀ።

ህዳር 6/2016

ሃሳቡ የተገለጸው የፓርቲው ሃላፊ አቶ ቀድሩ አብደላ በዳሎቻ ከተማ አስተዳደር እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ተግባራትን በጎበኙበት ወቅት ነው።

ከጉብኝቱ በኋላ ከዞኑ የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጋር ቆይታ ያደረጉት የፓርቲው ሐላፊ በቅርቡ በከተማ አስተዳደሩ የተለያዩ ማህበራዊ መሰረት ካላቻው ነዋሪዎች ጋር ውይይት አድርገው እንደነበርና በምክክሩ ከህዝቡ የተነሱ ሃሳቦች በአጭር፣ በረዥምና መካከለኛ ጊዜ ለመፍታት ቃል ገብተን የነበረ በመሆኑ ሂደቱን ለመመልከት እዚህ ተገኝተናል ብለዋል።

የጠንካራ መሪ መገለጫው ሕዝብ አድምጦ ምላሽ መስጠት መቻሉ መሆኑን ያነሱት አቶ ቀድሩ አብደላ የብልፅግና ፓርቲ አንዱ ልዩነት የህዝብ ጥያቄን በተገቢው መንገድ አድምጦ መፍታት የፓርቲው ዋነኛ የትኩረት ነጥብ ነጥብ መሆኑን ገልጸዋል።

ከጉብኝቱ መልስ ሃሳባቸውን በስፋት የገለፁት አት ቀድሩ አብደላ በተጨማሪም የፓርቲው ማዕከሉ፣ አልፋውና ኦሜጋው ሰው መሆኑ ብቻ ሳይሆን የሰው ልጅ የብቸኝነት ጉድለት ያለበት በመሆኑ ይህን ጉድለቱን ለመሙላት መደመር ያስፈልጋል በሚል የፓርቲው እሳቤ ጠንካራ ስራዎችን እየሰራን እንገኛለን ብለዋል።

በከተማ አስተዳደሩ ሁላችንም ለከተማችን በሚል ከተደረገው ውይይት በኋላ እየተደረጉ የሚገኙ እንቅስቃሴዎችን በመመልከት ለአመራሩ ጠንካራ ግብረ-መልስ እንደተሰጠና በየደረጃው የሚገኙ ባለድርሻ አካላትም የሚያደርጉት ርብርብ አበረታች መሆኑን ተናግረዋል።

በቀጣይም በአጭር በረዥምና መካከለኛ ጊዜ የታቀዱ ተግባራት ውጤትና ሂደት ተግባቦት እየተፈጠረባቸው መሄዳቸውን እንደሚቀጥሉ አስረድተዋል።

የዳሎቻ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ሀቢብ ከድር ከሕዝባዊ ውይይቱ በኋላ ተጨባጭ ለውጦች እየመጡ ስለመሆኑ ህዝቡ እራሱ ምስክርነት እየሰጠን ይገኛል ብለዋል።

ህዝቡ ከውይይቱ በኋላ ተባባሪ መሆን መቻሉ ለመጣው ውጤት የበኩሉን አስተዋጽኦ ያበረከተ ስለመሆኑ ተናግሯል።

በተለይም ህዝቡ እንደ ችግር ባነሳቸው መንገዶችን መክፈት፣ የከተማውን ፕላን ማውረድ፣ የኢንቨስትመንት ቦታዎችን ማዘጋጀትና ሌሎችም ህዝባዊ ድጋፎች በጥቂቱም ቢሆን ለመጡት ለውጦች የራሳቸው እርሾዎች ነበሩ ብለዋል።

በቀጣይም ይህ ድጋፍ ተጠናክሮ እንዲቀጥልና ከተማዋን ለነዋሪዎቿ ምቹ ፣ ውብ ፅዱና አረንጓዴ ማድረግ ብቻ ሳይሆን ለነዋሪዎቿ በቂ የስራ እድል የሚፈጠርበት የብፅልግና ከተማ እንድትሆን የከተማ አስተዳደሩ ጥረቱን አጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።

በተጨማሪም በህዝባዊ ውይይቱ ከጤና ጣቢያ አገልግሎት አሰጣጥ፣ ከመድሓኒት አቅርቦትና ከባለሙያዎች ጋር የተያያዙ ችግሮችን ከመፍታት በሻገር የጤና ጣቢያው የቀዶ ጥገና አገልግሎት መጀመር በሚችልባቸው አስፈላጊ ጉዳዮች ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የዳሎቻ ከተማ አስተዳደር ጤና ጣቢያ ሐላፊ አቶ አብዲ ጀማል በጉብኝቱ ወቅት ገልፀዋል።

በከተማ አስተዳደሩ ከ58 ሄ/ር በላይ መሬት ለኢንቨስትመንት የተዘጋጀ መሆኑንና ከ14 በላይ ባለሀብቶች የቦታ ርክክብ አድርገው ወደ ተግባር መግባታቸውን የገለፁት ደግሞ የዳሎቻ ከተማ አስተዳደር ማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት ሐላፊ አቶ ጀማል አህመድ ናቸው።

በጉብኝቱ የስልጤ ዞን የስራ እድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዝ መምሪያ ሐላፍ አቶ አብዱራህማን ወርቅቾ፣ የዳሎቻ ከተማ አስተዳደር ስራ-አስፈፃሚ አመራሮችና የተቋማት ሐላፊዎች በጋራ ተገኝተዋል።

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ተቋማት የመግቢያ ነጥብን ይፋ አደረገወራቤ-ህዳር 6/2016 (ስልጤ ኤፍ ኤም)የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር በ2016 ዓ.ም የቴክኒክና ሙያ ስልጠና...
16/11/2023

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ተቋማት የመግቢያ ነጥብን ይፋ አደረገ

ወራቤ-ህዳር 6/2016 (ስልጤ ኤፍ ኤም)

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር በ2016 ዓ.ም የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ተቋማት ገብተው በተለያዩ የሙያ መስኮች ስልጠና የሚወስዱ ተማሪዎች የመግቢያ ነጥብ ይፋ አድርጓል፡፡

የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል የመቁረጫ ነጥቡን አስመልክቶ እንደተናገሩት ዜጎች ወደ ቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ተቋማት የሚመጡት መሄጃ ስላጡ ሳይሆን ያላቸውን አቅም አውጥተው መጠቀም እንዲችሉ ነው፡፡

ይህም የቴክኒክና ሙያ ተቋማት ለዜጎች የስራ ዕድል ፈጣሪ አቅሞች እና ተጨማሪ አማራጭ የሚሰጡ ተቋማት ያደርጋቸዋል ብለዋል፡፡

ከባለፈው ዓመት ጀምሮ ተግባራዊ እየተደረገ ባለው አዲሱ የትምህርትና ሥልጠና ፖሊሲ መሰረት ከዚህ ቀደም እስከ ደረጃ 5 ብቻ ተገድቦ የነበረው የቴክኒክና ሙያ ስልጠና የእድገት መሰላል እስከ ደረጃ 8 ድረስ እንዲሆን ተደርጓል ብለዋል፡፡

ይህም ፖሊሲው ደረጃ ስድስትን ከመጀመሪያ ድግሪ፣ ደረጃ ሰባትን ከማስተርስ እንዲሁም ደረጃ ስምንትን ከዶክትሬት ዲግሪ ትይዩ እንዲሆን አድርጓል፡፡

ስለሆነም በዚህ ዓመት የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ነጥብ ያመጡ ተማሪዎች ወደ ቴክኒክና ሙያ መግባት ቢፈልጉ በደረጃ 6 ገብተው መሰልጠን እንደሚያስችላቸው አመላክተዋል፡፡

ዘንድሮ ለመጀመሪያ ጊዜ በደረጃ 6 የቴክኒክና ሙያ ሰልጣኞች እንደሚስተናገዱ የጠቆሙት ሚኒስትሯ በዚህ ዓመት በተቀመጠው መስፈርት መሰረት በክልሎች አማካኝነት የሰልጣኞች ምደባ ይካሄዳል ብለዋል፡፡

በዚህም በተያዘው የሥልጠና ዘመን 632 ሺህ በላይ ተማሪዎች የሥራ ገበያውን የሰው ሀይል ፍላጎት መሠረት ባደረገ መልኩ ከደረጃ 1-ደረጃ 5 እንደ ውጤታቸው ተመድበው እንደሚሰለጥኑም ነው የገለጹት፡፡

በወጣው መቁረጫ ነጥብ መሰረት ደረጃ አንድ እና ሁለት 110 ሺህ 15 ፤ በደረጃ ሦሰት እና አራት 412ሺህ 557 እንዲሁም በደረጃ አምስት 110ሺህ 15 እንደሚሳተፉ የጠቆሙት ሚኒስትሯ በደረጃ ስድስት ደግሞ 2ሺህ የሚሆኑ ሰልጣኞችን ለመቀበል ዝግጅት መደረጉን አመላክተዋል፡፡

የ2016 የስልጠና ዘመን የተዘጋጀው መቁረጫ ነጥብ የ2015 ትምህርት እና የ2014 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ ፈተና የወሰዱ ተማሪዎች ላይ ተግባራዊ ይሆናል፡፡

ከ2014 ዓ.ም በፊት ለነበሩ የ12ኛ ክፍል ተፈታኞች ደግሞ በስልጠና ዘመኑ በነበረው መቁረጫ ነጥብ መሰረት እንደሚስተናገዱ ከስራና ክህሎት ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡(ኢዜአ)

ኢትዮጵያ እና ሴራሊዮን በአቻ ውጤት ተለያዩ በዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታ ኢትዮጵያ እና ሴራሊዮን 0 ለ 0 በሆነ አቻ  ውጤት ተለያዩ፡፡የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ የምድብ ...
15/11/2023

ኢትዮጵያ እና ሴራሊዮን በአቻ ውጤት ተለያዩ

በዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታ ኢትዮጵያ እና ሴራሊዮን 0 ለ 0 በሆነ አቻ ውጤት ተለያዩ፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ የምድብ የመጀመሪያ ጨዋታውን ዛሬ ከሴራሊዮን አቻው ጋር አከናውኗል፡፡

የሁለቱ ሀገራት ጨዋታ በሞሮኮ ኤል አብዲ ስታዲየም ምሽት 4 ሰዓት ላይ ተካሒዷል፡፡

ጨዋታው ከሁለተኛው አጋማሽ በኋላ በጭጋጋማ አየር መከሰት ምክንያት ለተወሰነ ደቂቃ ተራዝሞ ነው የተጀመረው።

በተካሄደው የማጣሪያ ጨዋታም ኢትዮጵያ እና ሴራሊዮን 0 ለ 0 በሆነ አቻ ውጤት ተለያይተዋል።

ለበለጠ መረጃ ከስር ባሉ የሚዲያ አማራጮች ቤተሰብ ይሁኑ።
👉 ፌስቡክ:-https://www.facebook.com/profile.php?id=100082825107454&mibextid=ZbWKwL

👉 Online:- https://zeno.fm/radio/silte-fm-92-6-radio/

👉 ቴሌግራም ቻናል:- https://t.me/siltieFM

👉 ዩቲዩብ:-https://youtube.com/.6?si=hRXBMraXGNfs-r15

👉 ቲክቶክ:-https://www.tiktok.com/.fm.92.6?_t=8grgs10DJyv&_r=

የብልፅግና ፖርቲ የጠንካራ ሃሳቦችና አደረጃጀቶች ውጤት መሆኑን የስልጤ ዞን ብልፅግና ፖርቲ ገለፃ። ህዳር፣ 5/2016 ፖርቲው ይህን የገለፀው በዞኑ በምዕራብ አዘርነት በርበሬ ወረዳ ለድርጅቱ...
15/11/2023

የብልፅግና ፖርቲ የጠንካራ ሃሳቦችና አደረጃጀቶች ውጤት መሆኑን የስልጤ ዞን ብልፅግና ፖርቲ ገለፃ።

ህዳር፣ 5/2016

ፖርቲው ይህን የገለፀው በዞኑ በምዕራብ አዘርነት በርበሬ ወረዳ ለድርጅቱ አባላት በተዘጋጀ የስልጠና መድረክ ላይ ነው።

የምዕራብ አዘርነት በርበሬ ወረዳ የብልፅግና ፖርቲ ለአባላቱ ያዘጋጀውን የ1ኛ ሩብ ዓመት የአፈፃፀም ግምገማና የባለድርሻ አካላት የስልጠና መድረክ የፖርቲው ጽ/ቤት ሐላፊ አቶ አብደላ ዴተሞ እንኳን ደህና መጣችሁ በማለት አስጀምረውታል።

የምዕራብ አዘርነት በርበሬ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሹክረቶ አባቢያም ተገኝተው የብልፅግና ፖርቲ መነሻውም መድረሻውም ሰው ተኮር በመሆኑ የሰዎችን ስጋዊ፣ ቁሳዊና የዲሞክራሲያዊ ነፃነትን ደምሮ ለሰው ልጆች ሁለንተናዊ ብልፅግና የሚሰራ ፖርቲ ነው ብለዋል።

አስተዳዳሪው አክለውም የትናንት ወረቶችን ጨምሮ ህፀፆች በማስወገድ ለተሻለ ስኬት በትጋት ላይ የሚገኝ ፖርቲ መሆኑን ገልፀዋል።

በስልጠና መድረኩ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት የስልጤ ዞን ብልፅግና ፖርቲ ሐላፊ አቶ ቀድሩ አብደላ በበኩላቸው ወረዳው እንዲህ አይነት የስልጠና መድረክ በማዘጋጀቱ አመስግነው ጀምረዋል።

ፖርቲ የሚገነባው በሶስት መሰረታዊ ሃሳቦች መሆኑንም አፅንኦት ሰጥተው ገልፀዋል።

አንደኛ በጠንካራ ሃሳቦች መሆኑን በማንሳት በተለይም ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይን ህዝቡ በጋራ ድጋፍ የሰጣቸው ሰላም፣ ፍቅር ይቅርታ የሚሉ ጥልቅ ሃሳቦችን ማስተጋባት ብቻ ሳይሆን የምንገደደልበትን ሰይፍ አስቀምጠን ከሰው ልጆች ጉድለት ከስብራት እንጀምር እንምከር ማለታቸውን በማስታወስ የፖርቲውን የጠንካራ ሃሳብ ጅማሮ ሃሳቦች አንስተዋል።

መልዕክታቸውን የቀጠሉት አቶ ቀድሩ አብደላ
ፖርቲው ከሪዮተዓለም ንትርክ ነፃ ፖርቲ መሆኑን በመግለፅ ሶሻሊዝም፣ ኮሚዩኒዝም ወይም ሊብራሊዝም ከሚሉ የፖለቲካ ፍልስፍና ሃሳቦች ወጣ ብሎ መደመር የሚል ሃገር በቀል የሆነ በነገሮች የማይቸከል(pragmatist) የሆነ ፖርቲ መሆኑን በመግለፅ ጥልቅ ማብራሪያዎችን ሰጥተዋል።

በመልዕክታቸው በሁለተኛ ደረጃ አያይዘው የነሱት ፖርቲው ጠንካራ የአሰራርና አደረጃጀት መመሪያዎች ያሉት መሆኑን በመግለፅ እነዚህን የፖርቲ አሰራሮች በአስፈላጊ ደረጃ ለአባለቱ ግልፅ ከማድረግ አንፃር ብዙ ይጠበቅብናል ብለዋል።

ሀላፊው አክለውም በሶስተኛ ደረጃ የፖርቲ ልኬቱ አባሉና አመራሩ መሆኑን ገልፀዋል።

የብልፅግና ፖርቲ አባላት ቁጥርም ከአንዳንድ የአፍሪካ ሃገራት ጥቅል የህዝብ ቁጥር የሚልቅ እንደሆነ በመግለፅ ከ13.5 ሚሊየን በላይ አባለትና እስከ 65 ሺ የሚደርሱ አመራሮች እንደሃገር ያሉት እንደሆነ በመግለፅ በስልጤ ዞን ደግሞ ከ8 መቶ በላይ አመራሮችና ከ135 ሺ በላይ አባላት ያሉት ትልቅ ፖርቲ ነው ብለዋል።

በመድረኩ የስልጤ ዞን ብልፅግና ፖርቲ ምክትል ሐላፊ አቶ ሸረፋ ሌገሶ፣ የወረዳ አመራሮች፣ በየደረጃው የሚገኙ የህዋስና መሰረታዊ ድርጅት አመራሮችና ሌሎችም ባለድርሻ አካላት ተሳትፈውበታል።

ከመድረኩ በኋላም የዞኑ አመራሮች ከወረዳው አስተዳዳሪ ጋር በመሆን በሌራ ከተማ በአንድ ባለሀብት እየተገነባ የሚገኘውን የነዳጅ ማደያ፣ በዶሮና ንብ እርባታ ውጤታማ የሆኑ አርሶአደሮች እንቅስቃሴና የሌራ ጤና ጣቢያ በቅርቡ ሊጀምር ላሰበው የቀዶ ጥገና ህክምና እያደረጋቸው የሚገኙ ዝግጅቶች ተጎብኝቷል ሲል የዘገበው የዞኑ መንግስት ኮሚኒኬሽን ነዉ።

ለበለጠ መረጃ ከስር ባሉ የሚዲያ አማራጮች ቤተሰብ ይሁኑ።
👉 ፌስቡክ:-https://www.facebook.com/profile.php?id=100082825107454&mibextid=Zb

የቻይና የንግድ ሥራ በአፍሪካ ለማህበራዊ ኃላፊነቶች ጥምረት ከሚገነባቸው መንደሮች ትልቁን ድርሻ ለኢትዮጵያ እንደሚሰጥ ገለጸወራቤ-ህዳር 5/2016(ስልጤ ኤፍ ኤም)የቻይና የንግድ ሥራ በአፍሪ...
15/11/2023

የቻይና የንግድ ሥራ በአፍሪካ ለማህበራዊ ኃላፊነቶች ጥምረት ከሚገነባቸው መንደሮች ትልቁን ድርሻ ለኢትዮጵያ እንደሚሰጥ ገለጸ

ወራቤ-ህዳር 5/2016(ስልጤ ኤፍ ኤም)

የቻይና የንግድ ሥራ በአፍሪካ ለማህበራዊ ኃላፊነቶች ጥምረት በአፍሪካ ሊያስገነባቸው ካቀዳቸው 1ሺ መንደሮች ውስጥ ትልቁን ድርሻ ለኢትዮጵያ እንደሚሰጥ የጥምረቱ ሥራ አስፈፃሚ ዲያዮ ቹንሄ ተናገሩ።

በሥራ አስፈፃሚው ዲያዮ ቹንሄ የተመራ የልዑካን ቡድን ከሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራሮች ጋር መክሯል።

ጥምረቱ በአፍሪካ ውስጥ በኢንቨስትመንት እንዲሁም በኢኮኖሚ እና ንግድ ትብብር ላይ በተሰማሩ የቻይና ኢንተርፕራይዞች በፈቃደኝነት የተቋቋመ ሲሆን በአፍሪካ የተለያዩ የማህበራዊና ኢኮኖሚ ድጋፎችንም የሚያደርግ ነው።

የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ሁሪያ አሊ ጥምረቱ ሊገነባ ካቀዳቸው መንደሮች ውስጥ ትልቁን ድርሻ ለኢትዮጵያ እንዲሰጥ ጠይቀዋል።

የቻይናና የኢትዮጵያን የጠበቀ ግንኙነት ያነሱት ሚኒስትር ዴኤታዋ ኢትዮጵያ የሴቶችናና ህፃናትን እንዲሁም የአጠቃላይ ማህበረሰቡን ህይወት ለማሻሻል የምታደርገውን ጥረት በመደገፍ የቻይና መንግስት እና ኢንተርፕራይዞች እያበረከቱት ላለው አስተዋጽኦም አመስግነዋል።

የቻይና የንግድ ሥራ በአፍሪካ ለማህበራዊ ኃላፊነቶች ጥምረት ሥራ አስፈፃሚ ዲያዮ ቹንሄ ጥምረቱ ሊገነባ ካቀዳቸው 1ሺ መንደሮች ውስጥ ትልቁን ድርሻ ለኢትዮጵያ እንደሚሰጡ ቃል ገብተዋል።

የሴቶችና ህፃናት የማህበራዊ ህይወት መሻሻል ላይ ጥምረቱ ይሰራል ያሉት ስራ አስፈፃሚው ለፕሮጀክቱ መሳካት የኢትዮጵያ መንግስት አስፈላጊውን ድጋፍ እንዲያደርግ ጠይቀዋል።

የቻይና የንግድ ሥራ በአፍሪካ ለማህበራዊ ኃላፊነቶች ጥምረት በአፍሪካ ውስጥ ለማህበራዊ ህይወት መሻሻል ያግዛሉ ያላቸውን 1ሺ መንደሮችን ለመገንባት እየሰራ መሆኑን ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴርን የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡(ኢዜአ)

የስልጤ ዞን ምክትል አስተዳዳሪና ግብርና መምሪያ ዋና ሀላፊ አቶ ሙርሰል አማን ከስልጢ ወረዳ ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች ጋር በመሆን በወረዳው በመስኖና በአረንጓዴው አሻራ የተከናወኑ የልማት ስራ...
15/11/2023

የስልጤ ዞን ምክትል አስተዳዳሪና ግብርና መምሪያ ዋና ሀላፊ አቶ ሙርሰል አማን ከስልጢ ወረዳ ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች ጋር በመሆን በወረዳው በመስኖና በአረንጓዴው አሻራ የተከናወኑ የልማት ስራዎችንና የቀጣይ የዝግጅት እንቅስቃሴዎች በማስመልከት የመስክ ምልከታ አካሄዱ።

ሕዳር 5/2016/

በመስክ ምልከታው በወረዳው በክረምት ወራት በአረንጓዴ አሻራ የለማ የሙዝ ተክል፣ የቀጣይ አረንጓዴ አሻራ የችግኝ ዝግጅትና ለ2016 መደበኛ መስኖ እየተደረጉ ያሉ የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን ጎብኝተዋል።

በጉብኝቱ የተገኙት የስልጤ ዞን ምክትል አስተዳዳሪና ግብርና መምሪያ ዋና ሀላፊ አቶ ሙርሰል አማን አርሶ ኣደሩ ፈጥኖ ምርቱን በመሰብሰብ ወደ መደበኛ መስኖ ልማት እንዲገባ የተጀመሩ ስራዎችን አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባ ተናግረዋል።

ወረዳው ለመስኖ ልማት እምቅ አቅም ያለው እንደሆነ የገለጹት አቶ ሙርሰል አርሶ ኣደሮች ይህን መልካም እድል ተጠቅመው ምርትና ምርታማነታቸውን ማሳደግ እንዳለባቸውም ምክረ ሀሳብ ለግሰዋል።
አመራሩ ተግባሩን የእቅዱ አካል በማድረግ የቅርብ ድጋፍና ክትትል ማድረግ ይጠበቅበታል ተብሏል።

የስልጢ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ከድር ደድገባ በበኩላቸው ባደረጉት ንግግር በወረዳው በርካታ አርሶ ኣደሮች በመስኖ በመሰማራት ራሳቸውንና ቤተሰባቸውን መለወጥ ችለዋል ብለዋል።
የወረዳው አርሶ ኣደር በማሳ ላይ ያሉ ሰብሎችን ፈጥኖ በመሰብሰብ ወደ መስኖ ልማት መሰማራት እንዳለበት ተናግረዋል።
በክረምት በአረንጓዴ አሻራ የለሙ የጓሮ አትክልቶችና ፍራፍሬዎች ተገቢውን እንክብካቤ በማድረግ ለቀጣይ የአረንጓዴ ልማት ስራ መዘጋጀት ይገባል ሲሉም ዋና አስተዳዳሪው አሳስበዋል ሲል የዘገበው የስልጤ ዞን መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ነው።

ለበለጠ መረጃ ከስር ባሉ የሚዲያ አማራጮች ቤተሰብ ይሁኑ።
👉 ፌስቡክ:-https://www.facebook.com/profile.php?id=100082825107454&mibextid=ZbWKwL

👉 Online:- https://zeno.fm/radio/silte-fm-92-6-radio/

👉 ቴሌግራም ቻናል:- https://t.me/siltieFM

👉 ዩቲዩብ:-https://youtube.com/.6?si=hRXBMraXGNfs-r15

👉 ቲክቶክ:-https://www.tiktok.com/.fm.92.6?_t=8grgs10DJyv&_r=1

የዓለም ህዝብ ቁጥር በአንድ ዓመት ውስጥ ብቻ ከ72 ሚሊዮን በላይ መጨመሩ ተገለፀበፈረንጆቹ 2022 የዓለም የሕዝብ ቁጥር 8 ቢሊዮን መድረሱን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ህዳር ላይ ባወጣው...
15/11/2023

የዓለም ህዝብ ቁጥር በአንድ ዓመት ውስጥ ብቻ ከ72 ሚሊዮን በላይ መጨመሩ ተገለፀ

በፈረንጆቹ 2022 የዓለም የሕዝብ ቁጥር 8 ቢሊዮን መድረሱን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ህዳር ላይ ባወጣው ሪፖርት አስታውቆ የነበረ ሲሆን፤ ይህ ቁጥር በአንድ ዓመት ብቻ ከ72 ሚሊዮን በላይ መጨመሩ ተገልጿል፡፡

ሊጠናቀቅ የወራት እድሜ በቀሩት የፈረንጆቹ 2023 አመት የዓለም የሕዝብ ብዛት ይጨምራል ተብሎ የተተነበየው 70 ሚሊዮን ነበር፡፡

በትንበያው መሰረት የዓለም ህዝብ ብዛት በ 0.88 በመቶ የእድገት ምጣኔ 8,072,971,485 (8 ቢሊዮን 72 ሚሊዮን 971 ሺህ 485) መድረንሱም ነው የወልዶ ሜትር መረጃ የሚያሳው፡፡

በህዝብ ብዛት አንደኛ ተብላ ለዘመናት የቆየችው ቻይና በ2023 ለመጀመሪያ ግዜ በህንድ ብልጫ ተወስዶባታል፡፡

በቅርብ ጊዜ በወጡ ሪፖርቶች መሰረት ህንድ በ 1.428 ቢሊዮን የህዝብ ቁጥር በዓለማችን ከፍተኛ የህዝብ ብዛት ያላት ሀገር ሆናለች፡፡

በ2023 ግማሽ ዓመት ላይ በ 2.9 ሚሊዮን የህዝብ ብዛት ብልጫ የተወሰደባት ቻይና በ1.425 ቢሊዮን የህዝብ ቁጥር ሁለተኛ ደረጃን ይዛለች፡፡

በ2023 ከፍተኛ የህዝብ ቁጥር በማስመዝገብ አሜሪካ፣ ኢንዶኔዥያ፣ ፓኪስታን፣ ብራዚል፣ ባንግላዲሽ፣ ሩሲያ እና ሜክሲኮ ከቀዳሚዎቹ 10 ሀገራት መካከል የሚገኙ ሲሆን፤ ከአፍሪካ በህዝብ ብዛት ቀዳሚ የሆነችው ናይጄሪያም በ225 ሚሊዮን ህዝብ ብዛት 6ኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች፡፡

ከ 15 ዓመት በፊት በህዝብ ብዛት ከዓለም 22ኛ ደረጃ ላይ የነበረችው ኢትዮጵያ አሁን 11ኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠች ሲሆን፤ በቀጣዮቹ አመታትም በህዝብ ብዛቷ ከመጀመሪያዎቹ 10 ሀገራት መካከል አንዷ ትሆናለች ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ከ 100 ዓመታት በፊት የዓለማችንን 30 በመቶ ህዝብ ይዛ የነበረችው አውሮፓ በአፍሪካ እና እስያ የህዝብ ቁጥር ጭማሪ ምክንያት አሁን ላይ ድርሻዋ ከ10 በመቶ በታች ወርዷል፡፡

እ.አ.አ በ1974 የዓለማችን ህዝብ 4 ቢሊዮን የነበረ ሲሆን፤ ይህ ቁጥር እጥፍ ሆኖ 8 ቢሊዮን ለመድረስ 48 ዓመት ፈጅቶበታል፡፡(etv)

የኢትዮጵያ ብሔራዊ  ቡድን ዛሬ በዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ከሴራሊዮን ጋር ይጫዎታሉየኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በዓለም ዋንጫ ማጣርያ ከሴራሊዮን ጋር የሚያደርገው የመጀመርያ ጨዋታ ዛሬ በሞሮኮዋ ኤል-...
15/11/2023

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ዛሬ በዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ከሴራሊዮን ጋር ይጫዎታሉ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በዓለም ዋንጫ ማጣርያ ከሴራሊዮን ጋር የሚያደርገው የመጀመርያ ጨዋታ ዛሬ በሞሮኮዋ ኤል-ጀዲዳ ከተማ በሚገኘው ኤል-አብዲ ስታዲየም ከምሽቱ 4፡00 ሰዓት ላይ ይከናወናል።

በዛሬው ጨዋታ ላይ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አረንጓዴ ማልያ፣ ቢጫ ቁምጣ እና ቀይ ካሶተኒ ለብሶ ወደ ሜዳ ሲገባ ሴራሊዮን ሙሉ ነጭ መለያን ትጠቀማለች።

ጨዋታውን ሞዛምቢካዊው አልቫሲዮ ሴልሶ ከአንጎላዊያን ረዳት ዳኞች ጄርሰን ኤሚሊያኖ እና ኢቫኒልዶ ኦ ሳንቾ እንዲሁም ሞዛምቢካዊው አራተኛ ዳኛ ጉዋምቤ በርናርዶ ጋር ይመራዋል።

ደቡብ ሱዳናዊው ራሳስ ሊብራቶ ደግሞ በኮሚሽነርነት መመደባቸውን ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።(ebc)

የድህረ ምረቃ ተማሪዎች መግቢያ ፈተና በሀገር አቀፍ ደረጃ ከነገ ጀምሮ ይሰጣልየድህረ ምረቃ ተማሪዎች መግቢያ ፈተና በሀገር አቀፍ ደረጃ ለ2ኛ ጊዜ ነገ እና ከነገ በስቲያ እንደሚሰጥ የትምህር...
14/11/2023

የድህረ ምረቃ ተማሪዎች መግቢያ ፈተና በሀገር አቀፍ ደረጃ ከነገ ጀምሮ ይሰጣል

የድህረ ምረቃ ተማሪዎች መግቢያ ፈተና በሀገር አቀፍ ደረጃ ለ2ኛ ጊዜ ነገ እና ከነገ በስቲያ እንደሚሰጥ የትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

ፈተናው በ46 የፈተና ማዕከላት የሚሰጥ ሲሆን ÷ 90 ሺህ 70 ተማሪዎች ለመፈተን መመዝገባቸው ተመላክቷል፡፡

በዚህም ፈተናው ሕዳር 5 እና 6 2016 ዓ.ም እንደሚሰጥ ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል ሲል FBC በፌስቡክ ገጹ አስነብቧል።

ለበለጠ መረጃ ከስር ባሉ የሚዲያ አማራጮች ቤተሰብ ይሁኑ።
👉 ፌስቡክ:-https://www.facebook.com/profile.php?id=100082825107454&mibextid=ZbWKwL

👉 Online:- https://zeno.fm/radio/silte-fm-92-6-radio/

👉 ቴሌግራም ቻናል:- https://t.me/siltieFM

👉 ዩቲዩብ:-https://youtube.com/.6?si=hRXBMraXGNfs-r15

👉 ቲክቶክ:-https://www.tiktok.com/.fm.92.6?_t=8grgs10DJyv&_r=1

በተቀናጀ ግብርና ውጤታማ የሆኑ አርሶ ኣደሮችን ተሞክሮ ወደሁሉም አርሶ ኣደሮች ለማስፋፋት ትኩረት ተሰጥቶ ሊሰራ ይገባል ኣሉ -የስልጤ ዞን ምክትል አስተዳዳሪና ግብርና መምሪያ ዋና ሀላፊ አቶ...
14/11/2023

በተቀናጀ ግብርና ውጤታማ የሆኑ አርሶ ኣደሮችን ተሞክሮ ወደሁሉም አርሶ ኣደሮች ለማስፋፋት ትኩረት ተሰጥቶ ሊሰራ ይገባል ኣሉ -የስልጤ ዞን ምክትል አስተዳዳሪና ግብርና መምሪያ ዋና ሀላፊ አቶ ሙርሰል አማን!

ህዳር 4/2016/

አቶ ሙርሰል ይህን ያሉት በሳንኩራ ወረዳ የ2016 በጀት አመት የሲንክሮናይዜሽን ማስጀመሪያ እና የሌማት ቱርፋት ንቅናቄ መድረክ በተካሄደበት ወቅት ነው።

በወረዳው በተለያዩ ቀበሌያት የተሻሻሉ ዝርያ ያላቸው ከብቶችን በማርባት፣ንብ በማነብ፣ በዶሮ እርባታ፣ በጓሮ አትክልትና ፍራፍሬ ፕሮግራም ተደራጅተው ውጤታማ የሆኑ አርሶ ኣደሮችን ተሞክሮ ወደሌሎች ለማስፋት ያለመ ጉብኝትም ተካሄዷል።

በመርሃ-ግብሩ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የስልጤ ዞን ምክትል አስተዳዳሪና ግብርና መምሪያ ዋና ሀላፊ አቶ ሙርሰል አማን የምግብ ዋስትናን ማረጋገጥ የሚቻለው የእንስሳትና የሰብል ልማትን አቀናጅቶና አዘምኖ መስራት ሲቻል ነው ብለዋል።

በዚህ ዘርፍ ውጤታማ የሆኑ አርሶ ኣደሮችን ተሞክሮ ወደሁሉም አርሶ ኣደሮች ለማስፋፋት ትኩረት ተሰጥቶ ሊሰራ ይገባልም ብለዋል።

ሳንኩራ ወረዳ ለሌማት ቱርፋት ማለትም ለንብ ማነብ ፣ የተሻሻሉ ዝርያ ያላቸው እንስሳትንና ሰብሎችን ለማልማት የሚያስችሉ አቅሞች መኖራቸውን ገልጸው ካለው እምቅ አቅም አንጻር አሁን ከተሰራው በላይ መስራት እንደሚቻልም ጠቁመዋል።

የሳንኩራ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ በድሩ ሰንገሮ
በመድረኩ ባደረጉት የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር በወረዳው በምግብ ሰብል ራስን ለመቻል በሌማት ቱርፋት ፕሮግራም የተጀመሩ ስራዎችን በማጠናከርና በማስፋት በዘርፉ የሚገኘውን ጠቀሜታ ይበልጥ ማጠናከር መስራት እንደሚገባ ተናግረዋል።

በወረዳው በተለያዩ ቀበሌያት በዘርፉ ተሰማርተው ውጤት እያስመዘገቡ ያሉትን አርሶ ኣደሮች ተሞክሮ ወደ ሌሎች የማስፋት ስራ እንደሚሰራ ገልጸዋል።

የሳንኩራ ወረዳ ምክትል አስተዳዳሪና ግብርና ጽህፈት ቤት ሀላፊ የሆኑት አቶ ረሻድ ሀሰን በበኩላቸው በወረዳው በሌማት ቱሩፋት እቅድ ታቅዶ ወደ ተግባር
በተገባባቸው ቀበሌያት ተጨባጭ ውጤት ማምጣት ተችሏል ብለዋል።

ባለፉት አራት አመታት በሌማት ቱርፋት መርሃ ግብር ላይ በተሰራው የንቅናቄ ስራ በርካታ የወትት፣የእንቁላልና የዶሮ መንደሮችን በመመስረት ማህበረሰቡ በአቅራቢያው የተመጣጠነ ምግብ ማግኘት እንዲችል ተደርጓል ብለዋል።

ምንጭ የስልጤ ዞን መንግስት ኮምኒኬሽን

በስልጤ ዞን ስልጢና ምስራቅ ስልጢ ወረዳዎች የኮሌራ ክትባት ዘመቻ ተጀመረ!ህዳር 4/2016፣ ወራቤ፣  በስልጤ ዞን ለኮሌራ ተጋላጭ በሆኑት ስልጢና ምስራቅ ስልጢ ወረዳዎች የተለያዩ ቀበሌያት ...
14/11/2023

በስልጤ ዞን ስልጢና ምስራቅ ስልጢ ወረዳዎች የኮሌራ ክትባት ዘመቻ ተጀመረ!

ህዳር 4/2016፣ ወራቤ፣

በስልጤ ዞን ለኮሌራ ተጋላጭ በሆኑት ስልጢና ምስራቅ ስልጢ ወረዳዎች የተለያዩ ቀበሌያት የኮሌራ መከላከያ ክትባት ዘመቻ ተጀምሯል፡፡

በስልጢ ወረዳ ደረጃ የክትባት ዘመቻው ከዚህ በፊት የኮሌራ ወረርሺኝ በተከሰተበት ጎፍለላ ቀበሌ የተለያዩ የወረዳ፣ የዞንና የክልል ባለድርሻ አካላት በተገኙበት በይፋ የተጀመረ ሲሆን በሌሎች የስልጢና የምስራቅ ስልጢ ወረዳዎች ቀበሌያትም ትምህርት ቤቶችን ጨምሮ በቀበሌ ማዕከላትና ለክትባቱ በተመረጡ ማዕከላት መጀመሩ ተጠቁሟል፡፡

የክትባት መርሃ ግብሩ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ከአለም ጤና ድርጅት ጋር በመተባበር የተዘጋጀ ሲሆን ይኸውም ዛሬ ማክሰኞ ህዳር 4/2016 ተጀምሮ እስከ ቀጣዩ ቅዳሜ ህዳር 18/2016 ለተከታታይ አምስት ቀናት የሚቀጥልና በዚህም ዕድሜያቸው ከ 1 ዓመት በላይ የሆኑ ሁሉም የህብረተሰብ ክፍሎች ክትባቱን የሚወስዱ መሆኑ ተመላክቷል፡፡

በጎፍለላ ቀበሌ ተገኝተው በወረዳ ደረጃ የክትባት ዘመቻውን ያስጀመሩት የስልጤ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ከድር ደድገበ የኮሌራ በሽታ በስልጢ ወረዳ ጎፍለላ ቀበሌ ከፍ ያለ ጉዳት ማድረሱን አስታውሰው በሽታውን ለመከላከል ባለድርሻ አካላት የተቀናጁበት ዘርፈ ብዙ ጥረት መደረጉን ተናግረዋል፡፡

ለክትባት መርሃ ግብሩ ስኬታማነት የአለም ጤና ድርጅትን ጨምሮ ሌሎች ባለድርሻ አካላት አስተዋጽኦ ማድረጋቸውን የተናገሩት አቶ ከድር እድሜያቸው ከ 1 ዓመት በላይ የሆኑ የማህበረሰብ ክፍሎች ሁሉ በተቀመጠው የጊዜ ሰሌዳ ክትባቱን እንዲወስዱ አሳስበዋል፡፡

በፕሮግራሙ ላይ የተገኙት የአለም ጤና ድርጅት ተወካይ አቶ ጀማል ሀሰን በበኩላቸው የዓለም ጤና ድርጅት ወረርሺኙን ለመከላከል ከፍተኛ ወጪ የሚጠይቁ መድኃኒቶችን ድጋፍ ማድረጉን በማንሳት መድሃኒቶቹ በተገቢው ጥቅም ላይ መዋል እንዳለባቸው ገልጸዋል፡፡

የስልጤ ዞን ጤና መምሪያ ኃላፊው አቶ ሸምሱ ሀይረዲን ባስተላለፉት መልዕክት የኮሌራ ወረርሺኝ በዞን ደረጃ በተከሰተበት ወቅት አስቸጋሪ ሁኔታዎች ገጥመው እንደነበር አንስተው ባለድርሻ አካላትን በማስተባበር በተሰራው ጠንካራ ስራ ወረርሺኙን መቆጣጠር መቻሉን አንስተዋል፡፡

የንጽህና ጉድለትና የመጸዳጃ ቤት አጠቃቀም ችግሮች ለወረርሺኙ አጋላጭ ሁኔታዎች መሆናቸውን ያነሱት አቶ ሸምሱ የግልና የአከባቢን ንጽህና በሚገባ መጠበቅ እንዲሁም መጸዳጃ ቤቶችን በተገቢው መጠቀም ላይ ባለድርሻ አካላት በትኩረት እንዲሰሩ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል፡፡

በክትባት መርሃ ግብሩ ላይ በስልጢ ወረዳ ከ155 ሺህ በላይ የማህበረሰብ ክፍሎች ክትባቱ ይሰጣቸዋል ተብሎ እንደሚጠበቅ ከስልጢ ወረዳ ጤና ጽ/ቤት የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

መረጃው የዞኑ መንግስት ኮምኒኬሽን ነው።

በስልጤ ዞን የዳሎቻ ከተማ አስተዳደር የፖሊስ አባላት፣የሰላምና ፀጥታ ክላስተር ባለሙያዎችና የብሄራዊ በጎ ፍቃድ አገልጋይ ወጣቶች በገቴ ኩትዮ ቀበሌ ለዘማች ቤተሰብ የበቆሎ ሰብል ምርት አሰባ...
14/11/2023

በስልጤ ዞን የዳሎቻ ከተማ አስተዳደር የፖሊስ አባላት፣የሰላምና ፀጥታ ክላስተር ባለሙያዎችና የብሄራዊ በጎ ፍቃድ አገልጋይ ወጣቶች በገቴ ኩትዮ ቀበሌ ለዘማች ቤተሰብ የበቆሎ ሰብል ምርት አሰባሰብ ድጋፍ አድርገዋል።

የዳሎቻ ከተማ አስተዳደር ሰላምና ፀጥታ ክላስተር አስተባባሪ አቶ ሙዲን ያሲን በመርሃ- ግብሩ ላይ የተገኙ ሲሆን ዘማቾች ለራሳቸው እና ለቤተሰቦቻቸው ሳይሳሱ ስለ ሀገር ክብር እና ሉዓላዊነት መዝመታቸውን አንስተው ሁሉም የከተማዋ ነዋሪ ለዘማች ቤተሰብ የደረሱ ሰብሎችን በመሰብሰብ እና ድጋፍ በማድረግ ደጀን መሆኑን በተግባር ማሳየት አለበት ብለዋል።

የፀጥታው መዋቅር አባላት በተሰጣቸው ህዝባዊ እና ሀገራዊ ተልዕኮ ወንጀልን ከመከላከል ጎን ለጎን የልማት ስራዎችን እና የበጎ ፍቃድ አገልግሎቶችን በተጠናከረ ሁኔታ እያከናወኑ ሲሆን የዘማቾች ቤተሰብን እና አቅመ ደካማ ወገኖችን የማገዙ ተግባር የሚቀጥል መሆኑንም ገልፀዋል።

የህግ ማስከበር ግዳጆችንና የሀገር ዳር ድንበርን በብቃትና በቁርጠኝነት ከማስከበር አልፎ አሁን በሱዳን ሀገር በሰላም ማስከበር ግዳጅ ተልዕኮ ላይ ላለው ለሀምሳ አለቃ ፈታዲን ሸህ ሀሰን ቤተሰብ እና ለሌሎችም ዘማች ቤተሰብ የበቆሎ ሰብል ምርት አሰባሰብ ድጋፍ የተደረገ ሲሆን በዛሬው ድጋፍ ከ1.5 ሄክታር በላይ ሰብል ምርት መሰብሰብ ተችሏል ሲል የወረዳው መንግስት ኮምኒኬሽን ዘግቧል።

ከአለምገና - ቡታጅራ - ሆሳዕና ያለው መንገድ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ካለው የግብርና፣ ማዕድንና ቱሪዝም ጸጋ አንጻር ልዩ ትኩረት እንደሚሻ ተገለፀ።ህዳር 4/2016 የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ...
14/11/2023

ከአለምገና - ቡታጅራ - ሆሳዕና ያለው መንገድ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ካለው የግብርና፣ ማዕድንና ቱሪዝም ጸጋ አንጻር ልዩ ትኩረት እንደሚሻ ተገለፀ።

ህዳር 4/2016

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ እንዳሻው ጣሰው ከኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የስራ ኃላፊዎች ጋር በጽህፈት ቤታቸው መክረዋል።

በክልሉ በአስተዳደሩ ማዕቀፍ የሚገኙ መንገዶች አጠቃላይ ሁኔታም ውይይት ተካሂዷል።

በዉይይቱ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ እንዳሻው ጣሰው ክልሉ ካለው የግብርና፣ ማዕድንና ቱሪዝም ጸጋ አንጻር ከአለምገና - ቡታጅራ - ሆሳዕና ያለው መንገድ ልዩ ትኩረት እንደሚሻ ለኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የስራ ኃላፊዎች ገልጸዋል።

ርዕሰ መስተዳድሩ ክልሉ በጸጥታ፣ በግብርና፣ በትምህርት፣ በጤና ዘርፎች እንዲሁም በገቢ አሰባሰብ ላይ በትኩረት እየሰራ እንደሚገኝ በመግለጽ ለስራው ስኬት የመንገድ መሠረተ ልማት ጉልህ ሚና እንደሚያበረክት ገልጸዋል።

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የመንግስት ዋና ተጠሪ ዶክተር ዲላሞ ኦቶሬ እንዳሉት መንገዱ ለክልሉ ከሚኖረው ፋይዳ አኳያ በልዩ ትኩረት መስራት ይገባል ብለዋል።

የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር አቶ መሃመድ አብዱረህማን በበኩላቸው ከአለምገና - ቡታጅራ -ሆሳዕና ያለውን የመንገድ ችግር ተቋማቸው እንደሚገነዘበው በመግለጽ ችግሩን ለመቅረፍ ትኩረት ተሰጥቶ እንደሚሰራ ገልጸዋል።

መንገዱ በርካታ አመት ያገለገለና የአገልግሎት ዘመኑን የጨረሰ እንዲሁም ተደጋጋሚ ጥገና ሲሰራለት የቆየ መሆኑን በማስታወስ ጥገና እየደረጉ መቀጠል የማያስችልና አዋጭ ባለመሆኑ መንገዱን በአዲስ መልክ ለመስራት የሚያስችል የዲዛይን ስራ መጠናቀቁን አቶ መሃመድ ተናግረው በቀጣይ ወደስራ እንደሚገባም ገልጸዋል።

የመንገዱ ስራ ባጠረ ጊዜ የራስ አቅምን በመጠቀም እንደሚጀመር እንዲሁም የጨረታ ማውጣት ሂደት እንደሚከናወን ዋና ዳይሬክተሩ ተናግረዋል።

በውይይቱ ጉዳዩ የሚመለከታቸው የስራ ኃላፊዎች፣ የዞን አስተዳዳሪዎች እና ሌሎችም የተገኙ ሲሆን የጋራ መግባባት ላይም ተደርሷል ሲል የዘገበው የማዕከላዊ ኢትዮጵያ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ነው።

ለበለጠ መረጃ ከስር ባሉ የሚዲያ አማራጮች ቤተሰብ ይሁኑ።
👉 ፌስቡክ:-https://www.facebook.com/profile.php?id=100082825107454&mibextid=ZbWKwL

👉 Online:- https://zeno.fm/radio/silte-fm-92-6-radio/

👉 ቴሌግራም ቻናል:- https://t.me/siltieFM

👉 ዩቲዩብ:-https://youtube.com/.6?si=hRXBMraXGNfs-r15

👉 ቲክቶክ:-https://www.tiktok.com/.fm.92.6?_t=8grgs10DJyv&_r=1

የስልጤ ዞን ምክር ቤት ህዳር 29 ለሚከበረው የብሔር ብሔር ሰቦች ቀንን ምክንያት በማድረግ ለአቢይ ኮሚቴው ኦረንቴሽን ሰጠ! ወራቤ፣ህዳር  4/2016 18ኛው የኢትዮጵያ ብሄሮች፣ ብሄረሰቦችና...
14/11/2023

የስልጤ ዞን ምክር ቤት ህዳር 29 ለሚከበረው የብሔር ብሔር ሰቦች ቀንን ምክንያት በማድረግ ለአቢይ ኮሚቴው ኦረንቴሽን ሰጠ!

ወራቤ፣ህዳር 4/2016

18ኛው የኢትዮጵያ ብሄሮች፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች ቀን የማስፈፀሚያ ሰነድ ቀርቦ በአቢይ ኮሚቴው ውይይት ተደርጎበት ከመግባባት ላይ ተደርሶዋል።

18ኛው የኢትዮጵያ ብሄሮች፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች ቀን ህዳር 29 በልዩ ልዩ ዝግጅቶች እንደሚከበር ወ/ሮ አለይካ ሽኩር የስልጤ ዞን ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ ገልፀዋል፡፡

በዓሉ “ብዝኃነትና እኩልነት ለሀገራዊ አንድነት” በሚል መሪ ቃል እንደሚከበር የስልጤ ዞን ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ ወ/ሮ አለይካ ሽኩር አስታውቀዋል።

ዋና አፈ ጉባኤዋ በዓሉን አስመልክተው ለአቢይ ኮሚቴዎች ባስተላለፉት መልዕክት ወቅቱ ከመቼውም ጊዜ በላይ አንድነታችንን የምናጠናክርበትና ለሰላም ዘብ የምንቆምበት ወቅት ነውም ብለዋል።

የበዓሉ ዓለማ የኢትዮጵያ ብሄሮች፣ ብሄረሰቦች እና ህዝቦች ሰላማቸውን በማጽናት ለዴሞክራሲ መከበርና መረጋገት በጋራና በመተባበር ጠንክረው የሚሰሩበትን የጋራ አቅጣጫ እንዲይዙ ማድረግ እንደሆነም ዋና አፈ- ጉባኤዋ ተናግረዋል።

ባአሉን ስናከብር የስልጤን ባህል የሚያጎሉ የበህል አልባሰትንና መሰል ዝግጅቶችን የዞኑ የባህል ቡድን ባህላችንን ልያስተዋውቅ በሚችል መልኩ መዘጋጀት እንዳለበትም አሳስበዋል።

በአሉ በሁሉም ወረዳዎችና ከተማ አስተዳደሮች ከቀበሌ ጀምሮ እስከ ትምህርት ቤት ድረስ በተለያዩ ዝግጅቶች ህዳር 12 እና 13 በድምቀት ይከበራል ሲሉም ወ/ሮ አለይካ አስገንዝበዋል::ዘገባው የስልጤ ዞን መንግስት ኮሚኒኬሽን ነው።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ ከምክር ቤት አባላት ለቀርቡላቸው ጥያቄዎች በሰጡት ማብራሪያ. ➙ መሰረታችን ሰው መሆን ነው፤ በጋራ በመኖር በጋራ መበልጸግ እንችላላን፣ ➙  የሀሳብ ጥ...
14/11/2023

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ ከምክር ቤት አባላት ለቀርቡላቸው ጥያቄዎች በሰጡት ማብራሪያ.

➙ መሰረታችን ሰው መሆን ነው፤ በጋራ በመኖር በጋራ መበልጸግ እንችላላን፣

➙ የሀሳብ ጥራት ያስፈላጋል ሀሳብ ብቻውን ሳይሆን ከትጋት ጋር ሲሆን ውጤት ያመጣል፣

➙ አፍራሽ ትርክት ሀገር አይገነባም፤ አሰባሳቢ ትርክትን መገንባት ያስፈልጋል፣

➙ በአሉታዊ ትርክት አገር አይገነባም፤ ታላቅና ሀገርዊ ትርክት ሀገር ይገነባል፣

➙ እንደፓርቲ ሀገራዊ ዕይታ ሁሉም የሚከበርበት ሀገር ነው፤ አካታች ዲሞክራሰያዊ ስርአት መገንባት ነው፣

➙ የኢትዮጵያ መሰረት የእያንዳንዱ ዜጋ ድምር ውጤት ነው፣

➙ ኢትዮጵያ ውስጥ ችግሮች ቢኖሩም ችግር አባባሽ ደግሞ ትርክት ነው፣

➙ ሀገራዊ ታላቅ ትርክት ይሰበስበናል፣ የምንገነባው ትርክት ለሰው ልጅ ክብር ያለው ቢሆን ይሻላል፣

➙ በማላከክ መፍትሄ አይመጣም ሌት ተቀን መስራት ነው መፍትሄ ያለው በማላከክ ውጤት አይመጣም፣

➙ ህብረ ብሄራዊት ኢትዮጵያን እንነባለን፤የጋራ የሆነ ሁሉን ያቀፈ ብሄራዊነት እንገንባ፣

➙ ታሪክ ሙያዊ ዘርፍ ነው ሁሉም ሰው እኩል አይረዳውም አይናገረውም አይፅፈውም ፣

➙ ኢትዮጵያ ፖለቲካዊ ታሪክ ብቻ አይደለም ያላት ማህበራዊ ታሪክ በእምነት በባህል ሊነገር የሚገባ ታሪኮች አሉን፣

➙ ታሪክን የምናይበት መነፅር ሚዛናዊ መሆን አለበት፣

የሕዝብ ተወካዮች ምክር መደበኛ ስብሰባ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) በተገኙበት መካሄድ ጀመረ             ============6ኛው የኢፌዲሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 3...
14/11/2023

የሕዝብ ተወካዮች ምክር መደበኛ ስብሰባ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) በተገኙበት መካሄድ ጀመረ
============
6ኛው የኢፌዲሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 3ኛ ዓመት የስራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ስብሰባ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) በተገኙበት መካሄድ ጀምሯል።

የምክር ቤቱ አባላት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ማብራሪያ ሊሰጡባቸው ይገባል ያሏቸውን ጉዳዮች እና ጥያቄዎችን እያቀረቡ ይገኛሉ።

ምክር ቤቱ ጠቅላይ ሚኒስትሩን እና ሌሎች የፌዴራል መንግስት ባለስልጣናትን ለጥያቄ የመጥራትና የሕግ አስፈጻሚውን አካል አሠራር የመመርመር ሥልጣን እንዳለው በኢፌዴሪ ህገ መንግስት አንቀጽ 55 ንዑስ አንቀጽ 17 ተደንግጓል።

በዚህም መሰረት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ መስከረም 28 ቀን፣ 2016 ዓ.ም ለሕዝብ ተወካዮች እና ለፌዴሬሽን ምክር ቤቶች ያቀረቡትን የፌደራል መንግስቱን ዓመታዊ ዕቅድ የመክፈቻ ንግግር አስመልክቶ ከምክር ቤቱ አባላት ለተነሱ ጥያቄዎች ማብራሪያ እና ምላሽ ይሰጣሉ።ምክር ቤቱ የድጋፍ ሞሽኑን ያፀድቃል ተብሎ ይጠበቃል።

በምክር ቤቱ መደበኛ ስብሰባ የሐይማኖት አባቶች ተወካዮች፣ የተፎካካሪ ፓርቲ ተጠሪዎች፣ መቀመጫቸውን አዲስ አበባ ያደረጉ የተለያዩ ሃገራት ዲፕሎማቶች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

ማስታወቂያ!!!
13/11/2023

ማስታወቂያ!!!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ነገ በህዝብ ተወካች ምክር ቤት ተገኝተው ማብራሪያ ይሰጣሉ ወራቤ-ህዳር 3/2016(ስልጤ ኤፍ ኤም) የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 3ኛ ዓመት የስራ ዘመን 4ኛ መ...
13/11/2023

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ነገ በህዝብ ተወካች ምክር ቤት ተገኝተው ማብራሪያ ይሰጣሉ

ወራቤ-ህዳር 3/2016(ስልጤ ኤፍ ኤም)

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 3ኛ ዓመት የስራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ስብሰባውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በተገኙበት ነገ ከጠዋቱ 2፡00 ጀምሮ ያካሂዳል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የምክር ቤቱ 4ኛ መደበኛ ጉባኤ ላይ በመገኘት ፕሬዘዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ መስከረም 28 ቀን፣ 2016 ዓ/ም ለሕዝብ ተወካዮች እና ለፌዴሬሽን ምክር ቤቶች ያቀረቡትን የፌደራል መንግስት ዓመታዊ ዕቅድ የመክፈቻ ንግግር አስመልክቶ ከምክር ቤት አባላት ለሚነሱላቸው ጥያቄዎች ማብራሪያና ምላሽ ይሰጣሉ።

ምክር ቤቱ የድጋፍ ሞሽኑን ያፀድቃል ተብሎም ይጠበቃል፡፡የ(ኢትዮጵያ ሬዲዮ)

በቀጣይ ዓመታት 25 ሚሊዮን አርሶ አደሮች የይዞታ ማረጋገጫ ደብተር ያገኛሉበቀጣይ 10 ዓመት 25 ሚሊዮን አርሶ አደሮች ለማሳ ይዞታቸው ማረጋገጫ ሰርተፍኬት እንደሚያገኙ የግብርና ሚኒስቴር አ...
13/11/2023

በቀጣይ ዓመታት 25 ሚሊዮን አርሶ አደሮች የይዞታ ማረጋገጫ ደብተር ያገኛሉ

በቀጣይ 10 ዓመት 25 ሚሊዮን አርሶ አደሮች ለማሳ ይዞታቸው ማረጋገጫ ሰርተፍኬት እንደሚያገኙ የግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ።

እስካሁን 30 ሚሊዮን የእርሻ ቦታዎችን በመመዝገብ ለ25 ሚሊዮን አርሶ አደሮች የማሳ ይዞታ ማረጋገጫ ሰርተፍኬት ተሰጥቷል።

በግብርና ሚኒስቴር የገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም መሪ ሥራ አስፈጻሚ አቶ ትዕግስቱ ገብረ መስቀል ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ እንደ ሀገር በአርሶ አደሩ እጅ የሚገኙ ከ50 ሚሊዮን በላይ የተለያየ ስፋት ያላቸው ማሳዎች አሉ።

ከዚህ ውስጥ ባለፉት 10 ዓመታት የአርሶ አደሩን የባለቤትነት መብት ለማረጋገጥ 30 ሚሊዮን ማሳዎችን የመመዝገብና የማሳዎቹን ካርታ የመቀየስ ሥራ መሠራቱን ጠቁመው፤ በተጓዳኝነት ለ25 ሚሊዮን አርሶ አደሮች የማሳ ይዞታቸው ማረጋገጫ ሰርተፍኬት ተሰጥቷል ብለዋል።

ቀሪ ማሳዎችን የመመዝገብና የባለቤትነት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት የመስጠት ሂደቱን በማስቀጠል በቀጣይ አስር ዓመት ለ25 ሚሊዮን አርሶ አደሮች ውስጥ አገልግሎቱን ለማዳረስ መታቀዱን አስታውቀዋል።

ብሔራዊ የገጠር መሬት አስተዳደር የመረጃ ሥርዓት በማበልጸግ ወደ ተግባር ማስገባት መቻሉን የተናገሩት አቶ ትዕግስቱ፤ የመሬት አስተዳደርና አጠቃቀምን በማዘመን በተለያዩ ክልሎች ለሚገኙ የአርሶ አደር ማሳዎች የይዞታ ማረጋገጫ ለአርሶ አደሮች እየተሰጠ መሆኑን አስረድተዋል።

የተመዘገቡና የካርታ ሰርተፍኬት የተሰጣቸውን የአርሶ አደር ይዞታዎችን በዘመናዊ የመረጃ ሥርዓት ውስጥ ማስቀመጥ መቻሉን አስረድተዋል።

የገጠር መሬት አስተዳደር የመረጃ ሥርዓቱ ከወረዳ እስከ ፌዴራል ተቋማት ደረጃ የተዘረጋ መሆኑን ገልጸው፤ በአሁኑ ወቅት በተለያዩ ክልሎች በሚገኙ 341 ወረዳዎች ላይ አሠራሩ ተግባራዊ በመደረጉ ለአርሶ አደሮች አገልግሎት እየተሰጡ መሆኑን ተናግረዋል።

የገጠር መሬት አስተዳደር የይዞታ ማረጋገጫ ሥራው በሁሉም ክልሎች ላይ እየተሠራበት መሆኑን የጠቆሙት መሪ ሥራ አስፈጻሚው፤ በአርብቶ አደር አካባቢዎች የይዞታ ማረጋገጫ ሥራው ልዩ ጥናት የሚያስፈልገው በመሆኑ ሥራው በልዩ ሁኔታ እንደሚከናወን አስገንዝበዋል።

በተጨማሪም በሀገሪቱ ያልተመዘገቡና ያልተቀየሱትን መሬቶችን የመመዝገብ ሥራ የሚከናወን መሆኑን ገልጸው፤ ዘመናዊ የመረጃ ሥርዓቱን የማስፋትና በበርካታ ወረዳዎች ላይ አገልግሎቱን ለማዳረስ ይሠራል ብለዋል።

የገጠር መሬት አስተዳደርን ዘመናዊ መሠረት ለመጣል እንዲቻል በ1997 የወጣውን የገጠር መሬት አዋጅ ተፈጻሚ እየተደረገ መሆኑን ጠቁመው፤ የአርሶ አደሩን መሬት ይዞታ ማረጋገጫ የመስጠት ሥራው የተለያዩ ግብዓቶችን ለማቅረብም ሆነ ሌሎች ተያያዥ ሥራዎች ወሳኝነት እንዳለው ተናግረዋል።

የማሳ ይዞታ ማረጋገጫ ሰርተፊኬቱ በመሬት ጉዳይ የሚነሱ ክርክሮችን በመቀነስ አርሶ አደሩ በፍርድ ቤት ክርክር የሚያጠፋውን ገንዘብ፣ ጉልበትና ጊዜ በማስቀረት ምርቱን ማሳደግ ላይ እንዲያተኩር ያደርጋል ሲል የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት አዲስ ዘመን የኅዳር 3/2016 እትም ዋቢ በማድረግ በትስስር ገፁ አስፍሯል።

ሦስተኛዋን ሳተላይት ለማምጠቅ የቴክኒካል ጥናት መጠናቀቁን እስፔስ ሳይንስና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት ገለጸETRSS-2 የተባለችውን ሦስተኛዋን ሳተላይት ለማምጠቅ የቴክኒካልና የገንዘብ ጥናት መ...
13/11/2023

ሦስተኛዋን ሳተላይት ለማምጠቅ የቴክኒካል ጥናት መጠናቀቁን እስፔስ ሳይንስና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት ገለጸ

ETRSS-2 የተባለችውን ሦስተኛዋን ሳተላይት ለማምጠቅ የቴክኒካልና የገንዘብ ጥናት መጠናቀቁን የኢትዮጵያ እስፔስ ሳይኒስና ጂኦስፓሻል ኢኒስቲትዩት ገለጸ፡፡

የእስፔስ ሳይንስና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አቶ አብዲሳ ይልማ ለኢፕድ እንደገለጹት፣ ዓለም አቀፍ ጨረታ በማውጣት ሦስተኛዋን ሳተላይት ለማምጠቅ ዝግጀት እየተደረገ ነው፡፡ ከገንዘብ ጋር የተያዙና ቴክኒካል የሆኑ ጥናቶች ተጠናቀው በመንግስት የኤሌክትሮኒክስ ግዚ ስርዓት ውስጥ እንደተካተተ አስረድተዋል፡፡

የጨረታ ሰነድም በመዘጋጀት ላይ የሚገኝ ሲሆን በቀጣዮቹ ወራት ዓለም አቀፍ ግልጽ ጨረታ ይወጣል ብለዋል፡፡

ሦስተኛዋ ሳተላይት ባለከፍተኛ ኃይል በመሆኗ ከመጀመሪያዋ ሳተላይት ለበለጠ ጊዜ ህዋ ላይ ትቆያለች። ከአገልግሎት አንጻር እንደመጀመሪያዋ ሳተላይት የመሬት ምልከታ ሳተላይት ናት ሲሉ አብራርተዋል፡፡(ኢ ፕ ድ)

ወራቤ-ህዳር 3 ቀን 2016 ዓ.ም

አትሌት ትዕግሥት አሰፋ የመጨረሻዎቹ 5 ዕጩዎች ውስጥ ተካተተች!! በሴቶች ማራቶን የሪከርድ ባለቤት የሆነችው አትሌት ትዕግሥት አሰፋ በዓመቱ ምርጥ አትሌት ምርጫ የመጨረሻዎቹ አምስት ዕጩዎች ...
13/11/2023

አትሌት ትዕግሥት አሰፋ የመጨረሻዎቹ 5 ዕጩዎች ውስጥ ተካተተች!!

በሴቶች ማራቶን የሪከርድ ባለቤት የሆነችው አትሌት ትዕግሥት አሰፋ በዓመቱ ምርጥ አትሌት ምርጫ የመጨረሻዎቹ አምስት ዕጩዎች ውሰጥ መካተቷን የዓለም አትሌቲክስ አስታውቋል።(ኢፕድ)

የእጅ መታጠብ ቀን በስልጤ ዞን ወራቤ ከተማ አስተዳደር አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ላይ ተከበረ!ወራቤ-ህዳር 03/03/2016 (ስልጤ ኤፍ ኤም)በስልጤ ዞን ወራቤ ከተማ አስተዳደር አንደኛ ደ...
13/11/2023

የእጅ መታጠብ ቀን በስልጤ ዞን ወራቤ ከተማ አስተዳደር አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ላይ ተከበረ!

ወራቤ-ህዳር 03/03/2016 (ስልጤ ኤፍ ኤም)

በስልጤ ዞን ወራቤ ከተማ አስተዳደር አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ላይ የእጅ መታጠብ ቀን ተከበረ።

የስልጤ ዞን ጤና መምሪያ ሀላፊ አቶ ሸምሱ ሀይራዲን በፕሮግራሙ ተገኝተው ባደረጉት ንግግር ዋናው ነገር ቀኑን መከበር ብቻ ሳይሆን የእጅ መታጠብ ልምድ እንዲያዳብር ለማህበረሰቡ ግንዛቤ መፍጠርና ማስረፅ ነው ሲሉም አሳስበዋል።

አለም አቀፍ የእጅ መታጠብ ቀን ማህበረሰቡን የማንቃት እና እጅ መታጠብን ባህል አድርጎ ሁልጊዜ እና ወሳኝ በተባሉ ጊዜያት ሁሉ መታጠብን እንዲለማመዱ የሚያደርግ ዘመቻ ነው ብለዋል፡፡

ተማሪዎች እጆት ወሳን በተባሉ ጊዜያት በመታጠብ ላልተፈለገ በሽታ እንዳይዳረጉ እና በቀላሉ መዳን በሚቻልባቸው በሽታዎች በመጠቃት ከትምህርት ገበታቸው እንዳያቋርጡ ጥንቃቄ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል ብለዋል።

በአሁኑ ሰአት የኮሌራ ወረርሽኝን ለመከላከልና ለመቆጣጠር ከምንተግብራቸው መከላከያ መንገዶች አንዱ የሆነው እጅ መታጠብ ተላላፊ በሽታዎችን ለመከላከል አይነተኛ ሚና ያለው መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

የዞኑ በሽታ መከላከል ጤና ማጎልበት አስተባባሪ የሆኑት አቶ አዩብ ከድር በበኩላቸው የፕሮግራሙ ዋና አላማም የግልና የአካባቢ ንፅህና በመጠበቅ ጤናማ አምራች ዜጋ ለመፍራት ያለመ መሆኑንም አንስተዋል።

በፕሮግራሙ የእጅ መታጠብ ቀንን አስመልክት ለተማሪዎች የጥያቄና መልስ ውድድር በማዘጋጀት በአቶ አዩብ ከድር አቅራቢነት የማወዳደር ስነ- ስርአት ተካሄዷል።

በእለቱም በዞኑ ጤና መምሪያ ኃላፊ እጅ የመታጠብ እና የፕሮግራሙ ተሳታፊዎች እንዲሁም ተማሪዎችና መምህራን እጃቸውን በሳሙና መታጠብ ችለዋል።(ጤና መምሪያ)

የስልጤ ልማት ማህበር ስራ አመራር ቦርድ ስብሰባ ተካሄደ!ህዳር 1/2016፣ ወራቤ፣ በቅርቡ በአዲስ መልክ የተዋቀረው የስልጤ ልማት ማህበር ስራ አመራር ቦርድ ስብሰባውን በማካሄድ በተለያዩ ጉ...
11/11/2023

የስልጤ ልማት ማህበር ስራ አመራር ቦርድ ስብሰባ ተካሄደ!

ህዳር 1/2016፣ ወራቤ፣
በቅርቡ በአዲስ መልክ የተዋቀረው የስልጤ ልማት ማህበር ስራ አመራር ቦርድ ስብሰባውን በማካሄድ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔዎችን አሳልፏል።

ስራ አመራር ቦርዱ ባደረገው ስብሰባ ላይ የስልጤ ልማት ማህበር የእስካሁን እንቅስቃሴዎችና አጠቃላይ ነባራዊ ሁኔታዎች እንዲሁም የቀጣይ የለውጥ አቅጣጫዎችንና ስራ አስኪያጅ መመደቢያ መስፈርቶችን የተመለከተ የውይይት ሰነድ በስልጤ ልማት ማህበር ቦርድ ሰብሳቢና በዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ አሊ ከድር ቀርቦ ምክክር ተደርጓል፡፡

ከዚህ በማስከተልም ተቋሙን በሁለንተናዊ መልኩ ሪፎርም ለማድረግ ከተያዘው አቅጣጫ መነሻ የህግ ሪፎርም አካል የሆኑ የስልጤ ልማት ማህበር የፋይናንስ አስተዳደር መመሪያ እና የተቋሙ የሰራተኞች አስተዳደር መመሪያ በስልጤ ዞን ፍትህ መምሪያ ኃላፊ አቶ በረከት ከድር ለቦርዱ አባላት በዝርዝር እንዲቀርብ ተደርጎ ውይይት በማድረግ በቦርድ አባላቱ ጸድቋል፡፡

በሌላም በኩል ስልጤ ልማት ማህበር ከ2011 እስከ 2015 ከተለያዩ ፕሮግራሞችና ተግባራት ጋር ተያይዞ የወጣ ወጪና ገቢን አስመልክቶ ሪፖርት ቀርቦ በመወያየት እንዲጸድቅ ተደርጓል፡፡

ልማት ማህበሩ የጀመረውን የለውጥ እንቅስቃሴ ወደ መሬት ማውረድ፣ ተጀምረው ያልተጠናቀቁ ፕሮጀክቶች የሚጠናቀቁበትን አማራጭ መፈለግ፣ የገቢ አማራጮችን ማስፋት፣ መደበኛና ኮርፖሬት አባላትን ቁጥር ማሳደግ፣ መላውን ህብረተሰብ በአዲስ መንፈስ ማነቃቃት፣ የተጀመረውን የልማት ማህበሩን ተቋማዊ የመዋቅር አደረጃጀት አጠናቆ ወደ ስራ ማስገባት፣ በቋንቋና ባህል ዘርፍ የተጀመሩ ስራዎችን አጠናክሮ ማስቀጠል፣ በተለያዩ የኢንቨስትመንት ስራዎች መሳተፍና የተቋሙን ገጽታ በሁለንተናዊ መልኩ መለወጥ በሚሉ ዝርዝር ጉዳዮች ላይ ስራ አመራር ቦርዱ በትኩረት በመምከርና የጋራ መግባባት በመፍጠር መድረኩን አጠናቋል ሲል የዘገበው የስልጤ ዞን መንግስት ኮሚኒኬሽን ነው።

ከ37.1 ቢልዮን ብር በላይ የሚያወጡ መድሀኒቶች ለጤና ተቋማት መሰራጨቱተገለጸወራቤ-ህዳር 1/2016 (ስልጤ ኤፍ ኤም)የኢትዮጵያ መድሃኒት አቅራቢ አገልግሎት በ2015 በጀት ዓመት ከ37.1 ...
11/11/2023

ከ37.1 ቢልዮን ብር በላይ የሚያወጡ መድሀኒቶች ለጤና ተቋማት መሰራጨቱተገለጸ

ወራቤ-ህዳር 1/2016 (ስልጤ ኤፍ ኤም)

የኢትዮጵያ መድሃኒት አቅራቢ አገልግሎት በ2015 በጀት ዓመት ከ37.1 ቢልዮን ብር በላይ የሚያወጡ መድሀኒቶችን ከ5ሺህ በላይ ለሚሆኑ ጤና ተቋማት ማሰራጨቱን የኢትዮጵያ መድሃኒት አቅራቢ አገልግሎት አስታወቀ፡፡

ተቋሙ 5ተኛውን ሀገር አቀፍ የመድሃኒት አቅርቦት ሰንሰለት ዓመታዊ ጉባኤ" ዘለቄታዊ አጋርነት ለማይበገር የጤና ግብዓት አቅርቦት ስርዓት "በሚል መሪ ሀሳብ እያከናወነ ይገኛል፡፡

የኢትዮጵያ መድሃኒት አቅራቢ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አብዱልቃድር ገልጋሎ አገልግሎቱ በሀገሪቱ ባሉት 19 ቅርንጫፎች አማካኝነት መድሃኒቶቹን ማሰራጨቱን ተናግረዋል፡፡፡

በአገልግሎቱ ባለፉት ሶስት ዓመታት አጠቃላይ የአቅርቦት ሰንሰለቱ በዓለም አቀፍም ሆነ በሀገር አቀፍ ደረጃ በእጅጉ የተፈተነ መሆኑን ዶ/ር አብዱልቃድር ገልጸዋል፡፡

ከነዚህ ችግሮች ውስጥ የተለያዩ የበሽታ ወረርሽኞች፣ የፀጥታ ችግርና በከፍተኛ ደረጃ በተለያዩ የጤና ተቋማት የመድሀኒት ፍላጓት መጨመር ትልቅ ተግዳሮት መፍጠሩን አንስተዋል፡፡

የተለያዩ ፈተናዎች አገልግሎቱን ቢገጥሙትም የቅንጅት ስራን በማጠናከር የመድሀኒት አቅርቦቱን ማሳለጥ ተችሏልም ተብሏል፡፡

በሌላ በኩል ጤና ተቋማት አገልግሎቱ ቅርንጫፎች በዱቤ መድሃኒት ገዝተዉ ክፍያ ባለመፈፀማቸው ምክንያት 91 ለሚደርሱ ጤና ተቋማት እዳቸውን እንዲከፍሉ የህግ ማስጠንቀቂያ ደርሷቸዋል ተብሏል፡፡(አዲስ ዋልታ)

የኮሌራ በሽታ መከላከያ ክትባት ለመስጠት ቅድመ-ዝግጅት እያደረገ መሆኑ የስልጤ ዞን ጤና መምሪያ ገለፀ! ====ህዳር 1 /2016 (ስልጤ ኤፍ ኤም 92.6)==== የስልጤ ዞን ጤና መምሪያ ከ...
11/11/2023

የኮሌራ በሽታ መከላከያ ክትባት ለመስጠት ቅድመ-ዝግጅት እያደረገ መሆኑ የስልጤ ዞን ጤና መምሪያ ገለፀ!

====ህዳር 1 /2016 (ስልጤ ኤፍ ኤም 92.6)====

የስልጤ ዞን ጤና መምሪያ ከ240 ሺህ በላይ ዕድሜያቸው ከአንድ ዓመት በላይ ለሆኑ ሰዎች የኮሌራ በሽታ መከላከያ ክትባት ለመስጠት ቅድመ-ዝግጅት መደረጉም ገልፆል።

በኮሌራ በሽታ መከላከያ ክትባት ዘመቻ ለሚሳተፉ ባለድርሻዎች የተዘጋጀ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና በወራቤ ከተማ ተካሂዷል።

የኮሌራ ወረርሽኝን ክትባቶችን ለመስጠት ለህብረተሰቡ የሚያስፈልጉ ዋና ዋና ነጥቦችን የሚዳስስ የስልጠና ሰነዶችን በተለያዩ የክልልና የዞን የዘርፍ ባለሙያዎች ተሰጥቷል።

የስልጤ ዞን ጤና መምሪያ ኃላፊ አቶ ሸምሱ ሀይረዲን የኮሌራ በሽታን መከላከል ሲቻል በንፁህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት ውስንነት፣ በግልና በአካባቢ ንፅህና አጠባበቅ ጉድለት በሽታው ተከስቶ በጤና እና በሀገር ኢኮኖሚ ላይ ጫና እያሳደረ ነው ብለዋል።

የመከላከያ ክትባቱ ከሚቀጥለው ሳምንት ጀምሮ በዞኑ ባሉ ሁለት ወረዳዎች ማለትም ስልጢ እና ምስራቅ ስልጢ ወረዳዎች ዕድሜያቸው ከአንድ ዓመት በላይ ለሆኑ 240 ሺህ 500ሰዎች ለተከታታይ አምስት ቀናት ይሰጣል ሲሉም አቶ ሸምሱ ጠቁመዋል።

ማህበረሰቡ የተሻሻለ መጸዳጃ ቤት ሽፋንን በማሰደግና እጆቹን በወሳኝ ጊዜያት በመታጠብ ከተለያዩ ተላላፊ በሽታዎች እራሱን መከላከል እንዳለበት ጠቁመዋል።

ከክትባት ዘመቻው ጎን ለጎን የበሽታ ቅኝት እና አሰሳ ስራዎች፣ ታማሚዎችን የመለየትና የማከም፣ በግል፣ በአካባቢና በውኃ ንፅህና አጠባበቅ ዙሪያ ማህበረሰቡን ግንዛቤ የማስጨበጥ ተግባራት እና የሕብረተሰብ ተሳትፎ ተቀናጅቶ ሊሰራ እንደሚገባ የማዕከላዊ ኢትዬጲያ ክልል የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ከፍተኛ ኤክስፐርት አቶ ዘሪሁን አሳስበዋል።

በስልጠና መድረኩ ሀሳብ አስተያታቸውን የሰጡ ሰልጣኞች ስልጠና መሰጠቱ ጥሩ እንደሆነና ሊስታወሉ የሚችሉ የግንዛቤ እጥረቶችን መቅረፍ ያስችላልም ብለዋል።

(ስልጤ ዞን ኮሙኒኬሽን)

Address


Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when የስልጤ ኤፍ ኤም 92.6//Siltie FM 92.6 posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Videos

Shortcuts

  • Address
  • Alerts
  • Videos
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share