Hiku Hikma

Hiku Hikma Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Hiku Hikma, Digital creator, .

13/06/2024

የሀረር ኢኮ ፓርክ ግንባታ ስራ 92 በመቶ ተጠናቋል- አቶ ተወለዳ አብዶሽ

በሀረር ከተማ እየተገነባ የሚገኝው የሀረር ኢኮ ፓርክ ግንባታ 92 በመቶ መጠናቀቁን የሀረሪ ክልል ባህል ፣ቅርስና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ አቶ ተወለዳ አብዶሽ ገለፁ፡፡

ከኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ የመደመር ትውልድ መፅሃፍ ሽያጭ በተገኘ ገቢ እየተገነባ የሚገኘው የሀረር ኢኮ ፓርክ ግንባታ አሁን ላይ 92 በመቶ ተጠናቋል።

ፕሮጀክቱ በአጭር ግዜ ውስጥ ለማጠናቀቅ በርብርብ እየተሰራ መሆኑን አብራርተዋል።

ፓርኩ በውስጡ ሀረር የምትታወቅበትን የጅብ ትርኢት ማሳያ አንፊ ቲያትር ጨምሮ የተለያዩ ባህላዊ የእደ ጥበብ ውጤቶች ለቱሪስቶች የሚሸጡበት ማእከላት እና የመዝናኛ ስፍራዎችን በውስጡ የያዘ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

ከዚህም በተጨማሪ ፓርኩ ሀረር እራሱን የቻለ የጅብ ትርኢት የቱሪዝም መዳረሻ እንዲኖራት የሚያስችል መሆኑን ገልፀዋል፡፡

ፓርኩ እየተገነባበት የሚገኘው ስፍራ ሀረር የምትታወቅባቸው የተለያዩ እፅዋት የነበሩበት ስፍራ መሆኑን አስታውሰው ቀደም ሲል በስፍራው ይገኙ የነበሩ አትክልት እና ቡናን ጨምሮ የተለያዩ መድሃኒትነት ያላቸው እፅዋቶችን በስፍራው መልሶ በማልማት ተጨማሪ የቱሪዝም መዳረሻ ለመፍጠር እየተሰራ እንደሚገኝም ገልፀዋል፡፡

ፕሮጀክቱ በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ከተፃፈው የመደመር ትውልድ መፅሃፍ ሽያጭ በተገኘ ከ70 ሚሊየን ብር በላይ ገቢ በክልሉ የሚገኙ ባለሃብቶች የንግዱ ማህበረሰብ የመንግስት ሰራተኞች እና የተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች ተሳትፎ እየተገነባ እንደሚገኝም ገልፀዋል፡፡

ፓርኩን ለመገንባት ከሚያስፈልገው 162 ሚሊየን ብር ከ50 በመቶ በላይ የሚሆነው የተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች የተሸፈነ መሆኑ ፕሮጀክቱን በክልሉ በመንግስት እየተገነቡ ከሚገኙ ሌሎች ፕሮጀክቶች የተለየ ያደርገዋል ነው ያሉት፡፡

የፓርኩ ግንባታ ሲጠናቀቅም ለአካባቢው ማህበረሰብ የስራ እድል ከመፍጠር ባሻገር ለክልሉ የቱሪዝም እድገት ትልቅ አስተዋጽኦ የሚያበረክት መሆኑንም አቶ ተወለዳ ገልፀዋል፡፡

13/06/2024
11/06/2024
11/06/2024
31/05/2024
29/05/2024

የሀረር ከተማን ፅዱ፣ ሳቢ እና ተመራጭ የቱሪዝም መዳረሻ ከተማ ለማድረግ እየተሠራ መሆኑ ተገለፀ

ግንቦት 21/2016 (አዲስ ዋልታ) የሀረር ከተማን ፅዱ፣ሳቢ እና ተመራጭ የቱሪዝም መዳረሻ ከተማ ለማድረግ የሚያስችሉ ሥራዎች እየተከናወኑ መሆኑን የከተማው ማዘጋጃ ቤት ገለፀ።

የሀረር ከተማ ማዘጋጃ ቤት ስራ አስኪያጅ ኢሊያስ ዩኒስ ሀረርን ፅዱ፣ ውብ እና ሳቢ ከተማ ለማድረግ ማዘጋጃ ቤቱ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ከተማዋን ለነዋሪውና ለጎብኚው ምቹ ለማድረግ በሚሠራው ሥራ ህብረተሰቡ የራሱን አስተዋጽኦ እንዲያደርግም ጥሪ ሥራ አስኪያጁ አቅርበዋል።

የዘንድሮውን አለም አቀፍ የሀረር ቀንን በፀዳች ከተማ ባሸበረቀ እና ባማረ ሁኔታ ለማክበር ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ ነው ብለዋል።

ደረቅ ቆሻሻን መሰብሰብ፣ መለየትና ጥቅም ላይ እንዲውል የማድረጉ ስራም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ጠቅሰው ውብና ፅዱ ሀረርን ለመፍጠር የፅዱና አረንጓዴ ልማት ስራዎችን በውጤታማነት መፈፀም እንደሚገባ መናገራቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመለክታል፡፡

29/05/2024

Hojiiwwan Magaalaa Harar qulqulluu, hawwattuu fi magaalaa turizimii filatamaa taasisuuf dandeessisan hojjetamaa kan jiru ta'uu manni qopheessaa magaalaa Harar ibse.

Magaalaa Harar qulqulluu, hawwataa fi jiraattotaa fi daawwattootaaf mijataa taasisuuf hojiin hojjetamaa jiraachuu Hoji gaggeessaa olaanaa mana qopheessaa magaalaa Harar Obbo Iliyaas Yoonis ibsaniiru.

Magaalattii qulqulluu, bareedduu fi hawwataa taasisuuf hojjechaa kan jiru ta'uu ibsuun hawaasni hojii kanaaf gahee isaa akka bahu waamicha dhiyeessaniiru.

Guyyaa idiladdunyaa Harar kan bara kanaa magaalattii qulqulluu fi iftuu taasisuun bifa miidhagaa ta'een kabajuuf xiyyeeffannoon itti kennamee hojjatamaa jiraachuu hoji adeemsisaan kun itti dabaluun ibsaniiru.

Hojiin balfa goggogaa sassaabuu, addaan baasuu fi deebisanii hojiirra oolchuu cimee kan itti fufu ta'uu ibsaniiru.

Harar bareedduu fi qulqulluu uumuuf hojiiwwan misoomaa qulqullinaa fi magariisaa bu’a qabeessa ta’een hojjetamuu akka qabu hubachiisaniiru.

Jiraattonni magaalichaa qulqullina mooraa fi naannoo isaatiif xiyyeeffannaa kennuun kunuunsuu akka qabu ibsaniiru.

Magaalattii qulqulluu fi bareedduu gochuuf hojiin eegalame galma akka gahuuf miseensonni hooggansaa fi jiraattonni magaalichaa ga’ee isaanii akka ba’anis waamicha dhiyeessaniiru.

29/05/2024

ብልፅግና ፓርቲ ምቹ ፣ ንፁህ እና ተስማሚ አከባቢን በመፍጠር የበለፀገች ሀገር ለመገንባት የሚያደርገው ጥረት አጠናክሮ ይቀጥላል።

የብልፅግና ፓርቲ የትኩረት መስኮች ውስጥ አንዱ የምቹና ፅዱ አከባቢን በመፍጠር ለናዋሪዎቿ ተስማሚና የበለፀገች ከተማን መገንባት ነው

በዚህም ሀረር ከተማን ፅዱ ፣ሳቢ እና የቱሪዝም ተመራጭ ከተማ ለማድረግ የሚያስችሉ ተግባራት በመከናወን ላይ ይገኛለ።

ሀረር ከተማን ፅዱ፣ ማራኪ እና ለነዋሪውና ለጎብኚው ምቹ ከተማ ለማድረግ የሚያስችሉ ተግባራት በመከናወን ላይ እንደሚገኙ የከተማው ማዘጋጃ ቤት ስራ አስኪያጅ አቶ ኢሊያስ ዩኒስ ገለጹ።

ከተማውን ፅዱ፣ ውብ፣ ሳቢና የበለፀገች ለማድረግ ማዘጋጃ ቤቱ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑንና ለዚህም ስራ ህብረተሰቡ የራሱን አስተዋጽኦ እንዲያደርግ ጥሪ አድርገዋል።

የዘንድሮውን አለም አቀፍ የሀረር ቀንን ከተማዋን የፀዳች፣ ያሸበረቀ እና ባማረ ሁኔታ ለማክበር ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑንም ስራ አስኪያጅ አክለው ገልፀዋል።

ደረቅ ቆሻሻን መሰብሰብ፣ መለየትና ጥቅም ላይ እንዲውል እየተከናወነ ያለውን ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል።

ውብና ፅዱ ሀረርን ለመፍጠር የፅዱና አረንጓዴ ልማት ስራዎችን በውጤታማነት መፈፀም እንደሚገባ አመልክተዋል።

የከተማው ነዋሪም ለግቢውና ለአካባቢ ፅዳት ትኩረት ሰጥቶ ሊንከባከብ ይገባል ብለዋል።

በየደረጃው የሚገኙ የአመራር አባላትና የከተማዋ ነዋሪዎችም ከተማዋን ፅዱና ውብ ለማድረግ የተጀመረው ስራ ግቡን እንዲመታ የድርሻቸውን እንዲወጡም ጥሪ አስተላልፈዋል።

23/05/2024
16/05/2024
10/05/2024

Address


Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Hiku Hikma posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

  • Address
  • Alerts
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share