Al Alam Amharic/አል አለም አማርኛ

  • Home
  • Al Alam Amharic/አል አለም አማርኛ

Al Alam Amharic/አል አለም አማርኛ Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Al Alam Amharic/አል አለም አማርኛ, News & Media Website, .

11/08/2024

Dorgommichi Baayy'ee Ulfaataa Ta'uus Biyya Koof Meedaliyaa Meetii Fiduu Kootitti Baayy'ee Gammadaadha. Ummanni Biyya Koo Hundi Yaadaa fi Deeggarsa Keessaniin Nu Faana Turuu Keessaniif Galatoomaa 🙏🙏.. O
Olympuc 2024

የኤርትራ ፕሬዝደንት ከሱዳን ሉዓላዊ ምክርቤት አመራሮች ጋር ተወያዩ!!የሱዳን የሉዓላዊ ምክር ቤት ምክትል ኃላፊ ማሊክ አጋር ከኤርትራ ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ጋር በሱዳን እየተካሄደ ያለ...
20/01/2024

የኤርትራ ፕሬዝደንት ከሱዳን ሉዓላዊ ምክርቤት አመራሮች ጋር ተወያዩ!!

የሱዳን የሉዓላዊ ምክር ቤት ምክትል ኃላፊ ማሊክ አጋር ከኤርትራ ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ጋር በሱዳን እየተካሄደ ያለው ግጭት ወደ አጎራባች ምስራቃዊ ግዛቶች እንዳይሸጋገር በሚቻልበት ስልቶች ላይ መክረዋል። የፈጣን የድጋፍ ሃይል ( # አርኤስኤፍ ) መከላከያ ቡድን በማዕከላዊ ሱዳን አል-ጃዚራህ ግዛት መገኘቱ ከኤርትራ ጋር በሚያዋስኑት የጋዳሬፍ እና ካሳላ አዋሳኝ ክልሎች ሊፈፀሙ እንደሚችሉ ስጋት ፈጥሯል።

l
18/01/2024

l

በሶማሌላንድ እና በኢትዮጵያ መካከል የተደረሰው የመግባቢያ ስምምነት ለሁለቱም ሀገራት እና ለአፍሪካ በአጠቃላይ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ጠቀሜታ ያለው ነው።

Republic Of Somaliland
Telefishanka Qaranka Somaliland

ሰበር!! ኢትዮጵያ የወደብ ባለቤት ሆነችኢትዮጵያ የቀይ ባሕር በር ለማግኘት እና ለማልማት የሚያስችላትን ስምምነት ከሶማሊ ላንድ ጋር ፈፅማለች። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና ...
01/01/2024

ሰበር!!

ኢትዮጵያ የወደብ ባለቤት ሆነች

ኢትዮጵያ የቀይ ባሕር በር ለማግኘት እና ለማልማት የሚያስችላትን ስምምነት ከሶማሊ ላንድ ጋር ፈፅማለች።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና የሶማሊ ላንድ ፕሬዚዳንት ሙሴ ባሂ ሁሉን አካታች የሆነውን የጋራ መግባቢያ ሰነድ ተፈራርመዋል።

በዚሁ መሠረት ለብዙ ዘመናት ወደብ አልባ ሆና የቆየችው ሀገራችን ከሶማሊ ላንድ ጋር ባደረገችው ስምምነት በሊዝ የወደብ ባለቤት መሆን ችላለች።

ኡጋንዳዊው አትሌት ቤንጃሚን ኪፕላጋት ኬንያ ሞቶ ተገኘ!!የ34 አመቱ ኡጋንዳ አትሌት ቤንጃሚን ኪፕላጋት ኬኒያ መኪና ውስጥ አንገቱ እና ደረቱ ላይ በስለት ተወግቶ ሞቶ መገኘቱንም የኬንያ ፖሊ...
31/12/2023

ኡጋንዳዊው አትሌት ቤንጃሚን ኪፕላጋት ኬንያ ሞቶ ተገኘ!!

የ34 አመቱ ኡጋንዳ አትሌት ቤንጃሚን ኪፕላጋት ኬኒያ መኪና ውስጥ አንገቱ እና ደረቱ ላይ በስለት ተወግቶ ሞቶ መገኘቱንም የኬንያ ፖሊስ አስታውቋል።

የአለማችን ታዋቂ አትሌቶች ልምምድ በሚያደርጉባት የኬንያዋ ኤልዶሬት ከተማ መኪና ውስጥ ሞቶ የተገኘውን ኡጋንዳዊ አትሌት ግድያ እያጣራሁ ነው ብሏል የኬንያ ፖሊስ።

ትውልደ ኬንያዊው ኪፕላጋት ኡጋንዳን ወክሎ በሶስት ኦሎምፒኮች የተወዳደረ ሲሆን፥ በለንደን ኦሎምፒክ በ3 ሺህ ሜትር መሰናክል ለግማሽ ፍጻሜ መድረሱንም የወርልድ አትሌቲክስ መረጃ ያሳያል።

(ጋዜጠኛ አርአያ ተ/ማርያም በቴሌግራም ቻናላቸው የለጠፉት መልዕክት አዘል መረጃ)ከናቅናት ቀጣይ የኢትዮጵያ ፈተና ትሆን ይሆናል!!ይሄ ትርክት በዚህ ከቀጠለ በኢትዮጵያ ውስጥ ከተከሰቱ ችግሮች...
31/12/2023

(ጋዜጠኛ አርአያ ተ/ማርያም በቴሌግራም ቻናላቸው የለጠፉት መልዕክት አዘል መረጃ)

ከናቅናት ቀጣይ የኢትዮጵያ ፈተና ትሆን ይሆናል!!

ይሄ ትርክት በዚህ ከቀጠለ በኢትዮጵያ ውስጥ ከተከሰቱ ችግሮችና አሁንም እየተከሰተ ካለው ችግር ሊብስ ይችላል በብልፅግና ዘመን ነገሮች ሲጀምሩ ይናቃሉ (under mine) ይደረጋሉ ያቺ የመናቅ አባዜን ስለማቃት ነው ዛሬ ለመፃፍ የተገደድኩት,ይቺ ሀገር ጫና በዝቶባታል ብየ ነው በዛሬው ዕለት ታላቅ የኢሳ ህዝብ እንመሰርታለን ሲባል ማንን ለመግጠም እንደሆነ ለማውቅ አይቸግርም ለማንኛውም በሽንሌ ዞን የጀቡቲ እናና የኢትዮጵያ ኢሳ ጎሳ የጀቡቲ ገንዘብ ሚ/ር እና የሶማሌ ክልል ም/ፕሬዚዳንት አቶ እብራሂም ኡስማን ትልቅ ህዝባዊ ስብሰባ እያካሄዱ ነው።በዚህ ስብሰባ ከተሳተፉት መሃከል አቶ አልያስ ደዋሌ ይገኙበታል፥ አቶ ኤልያስ ደዋሌ ማለት ደግሞ የጀቡቲ ገንዘብ ሚ/ር የዛሬ ሁለት አመት አዋሽ ውንዝ የጀቡቲ ነው ብሎ ትዊተር ገፅ የለጠፈ ደፋር ሰው ናቸው። ስለዚህ ይቺ መሰባሰብ ለበኋላ እንዳንነታርክባትና ወደ ማያበራ ችግር እንዳትወስደን በአግባቡ እንያት ግድ የለም ለማለት ነው።

https://t.me/ArayaNews/44?single

ቀይ-ባህር የስጋት ቀጠና!!!በቀይ ባህር በንግድ መርከቦች ላይ የሚደርሰው ጥቃት የነዳጅ እና ሌሎች ሸቀጦች ላይ ዋጋ መጨመር ሊያስከትል ይችላል ሲሉ ባለሙያዎች አስጠነቀቁ፡፡ አሁን ላይ የሃው...
19/12/2023

ቀይ-ባህር የስጋት ቀጠና!!!

በቀይ ባህር በንግድ መርከቦች ላይ የሚደርሰው ጥቃት የነዳጅ እና ሌሎች ሸቀጦች ላይ ዋጋ መጨመር ሊያስከትል ይችላል ሲሉ ባለሙያዎች አስጠነቀቁ፡፡

አሁን ላይ የሃውቲ አማፂያን በቀይ ባህር በሚቀዝፉ የንግድ መርከቦች ላይ ጥቃት መፈጸማቸውን ተከትሎ፥ በርካታ መርከቦች መስመሩን መጠቀም ማቆማቸው ነው የሚነገረው፡፡

በሶማሊ ክልል ጅግጅጋን ጨምሮ በተለያዩ አካባቢዎች የሽብር ጥቃት ለመፈጸም ሲንቀሳቀሱ የነበሩ 14 የአልሸባብ የሽብር ቡድን አባላት በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን የጸጥታና ደኅንነት የጋራ ግብረ- ...
19/12/2023

በሶማሊ ክልል ጅግጅጋን ጨምሮ በተለያዩ አካባቢዎች የሽብር ጥቃት ለመፈጸም ሲንቀሳቀሱ የነበሩ 14 የአልሸባብ የሽብር ቡድን አባላት በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን የጸጥታና ደኅንነት የጋራ ግብረ- ኃይል አስታወቀ

በሶማሊያ የሰላም ማስከበር ተልዕኮውን በብቃት በመወጣት ላይ በሚገኘው ጀግናው የሀገር መከላከያ ሠራዊት ተደጋጋሚ ሽንፈትና ኪሳራ የደረሰበት የአልሸባብ የሽብር ቡድን አባላትን በህቡእ በመመልመልና በማደራጀት በሶማሌ ክልል በጅግጅጋ ከተማ እና በተለያዩ የክልሉ አካባቢዎች የሽብር ጥቃት በመፈፀም ከፍተኛ ሰብአዊና ቁሳዊ ጉዳቶችን ለማድረስ ዕቅድ አውጥቶ ለመንቀሳቀስ ቢሞክርም ሴራው ሙሉ በሙሉ መክሸፉን የጸጥታና ደኅንነት የጋራ ግብረ- ኃይል ለመገናኛ ብዙሃን በላከው መግለጫ አስታውቋል።

አልሸባብ በህቡዕ አደራጅቶና ተልዕኮ ሰጥቶ የላካቸው 14 የቡድኑ አባላት ሊጠቀሙባቸው ካዘጋጇቸው ተቀጣጣይ ቁሶችና የተለያዩ ሰነዶች ጋር በቁጥጥር ስር የዋሉት በኢትዮጵያና በሶማሊያ ድንበር ሾልከው ወደ ሶማሌ ክልል ዘልቀው በመግባት በጅግጅጋና በሌሎችም የክልሉ ከተሞችና አካባቢዎች ኢላማዎችን በመለየት የሽብር ጥቃት ለመፈፀም ዕቅድ አውጥተው ሲንቀሳቀሱ መሆኑን መግለጫው ጠቁሟል።

በህግ ቁጥጥር ሥር እንዲውሉ ከተደረጉት ከእነዚህ ተጠርጣሪዎች መካከል አሊ አብዲ በቅፅል ስሙ መዓሊን አሊ በመባል የሚታወቀው የሽብር ቡድኑ መሪና አስተባባሪ መቀመጫውን ሶማሊያ ካደረገው የአልሸባብ ክንፍ ጋር ግንኙነት በመፍጠር በሶማሌ ክልል ውስጥ ሆኖ የሽብር ቡድን አባላትን በማደራጀት፣ በመገናኛት፣ በመመልመል፣ የሽብር እቅድ በማውጣትና ኢላማዎችን በመለየት ጥቃቶች እንዲፈፅሙ የሥልጠናና የሎጀስቲክስ ድጋፎችን ሲያደርግ ከሌሎች 13 ግብረአበሮቹ ጋር በተካሄደው የተቀናጀ ክትትል በሞያሌ ከተማ የመግቢያ ኬላ በኩል ሾልኮ ለመውጣት ሲሞክር በቁጥጥር ሥር መዋሉን የጋራ ግብረ- ኃይሉ መግለጫ አመልክቷል፡፡

አልሸባብ የሽብር ጥቃቶችን እንዲፈጽሙ ስምሪት የሰጠው በሶማሌ ክልል ጅግጅጋ፣ ፊቅ፣ ዋርዴር እና ቢኬ አካባቢዎች እንደነበር ያመለከተው መግለጫው ፤ የህቡዕ አደረጃጀት በመፍጠር የሽብር ተልዕኮ ለመፈጸም የተንቀሳቀሱት ተጠርጣሪዎች ለሽብር ጥቃቶች ሊጠቀሙባቸው ካዘጋጇቸው በርካታ ክላሽንኮቭ መሳሪያዎች፣ ጥይቶች ፣ሽጉጦች፣ ቦንቦች፣ ተቀጣጣይ ቁሶችና የተለያዩ ሰነዶች ጋር መያዛቸውን አስታውቋል፡፡

በተጨማሪም የጸጥታና ደኅንነት የጋራ ግብረ- ኃይሉ በሶማሌ ክልል በሲቲ ዞን ምኤሶ ወረዳ ፣ ፋፋን ዞን ጅግጅጋ ከተማና ዙሪያው ፣ ዶሎ ዞን ዋርደር ከተማና ዙሪያው ፣ ቆራሄ ዞን ህግሎሌ ወረዳ እና ኤረር ዞን ፊቅ ከተማ ባካሄደው ተከታታይ ኦፕሬሽኖችና የአሰሳ ሥራዎች የሽብር ቡድኑ ለጥቃት ሊያውሏቸው የነበሩ 84 ክላሽንኮቭ መሣሪያዎች፣ 10 የቡድን መሣሪያዎችና 12 ሽጉጦች በቁጥጥር ሥር እንዲውሉ መደረጉን መግለጫው አክሎ ገልጿል።

በተለይም አልሸባብ በኢትዮጵያ ላይ ዒላማ ያደረገውን የሽብር እኩይ ሴራና ጥቃት ለማሳካት የፈንጅ መቀመሚያ ንጥረ ነገሮች በህቡዕ ባደራጃቸው ህዋሶች አማካኝነት በህገ ወጥ መንገድ በኢትዮጵያ ድንበር ወደ ደቡብ ሶማሊያ በሟጓጓዝ ላይ እያለ በኤረር ዞን ጋሻሞ ወረዳ በቁጥጥር ሥር እንዲውል መደረጉን የጸጥታና ደኅንነት የጋራ ግብረ- ኃይል ባወጣው መግለጫ አያይዞ ጠቁሟል።

የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ከሶማሊያና ሌሎች አጎራባች ክልሎች ጋር ሰፊ ድንበር የሚጋራ በመሆኑ የአልሻባብ የሽብር ቡድን ሃሰተኛ መታወቂያዎችና ፓስፖርቶችን እንዲሁም ሌሎች ሰነዶችን በመጠቀም አባላቶቹን ወደ ኢትዮጵያ አስርጎ በመስገባት በመሠረተ ልማቶችና የነዳጅ ማጠራቀሚያዎች ላይ የሽብር ጥቃቶችን ለመፈጸም ተደጋጋሚ ጥረቶችን ሲያደረግ ቆይቷል ያለው መግለጫው ፤ ከውጭ አቻ የመረጃ ተቋማት ጋር በሚደረግ የመረጃ ልውውጥ እንዲሁም እየተካሄዱ ባሉ ጥብቅ ክትትሎችና ኦፕሬሽኖች አማካኝነት የሽብር ሴራዎችንና ተልዕኮዎችን ማክሸፍ መቻሉን የጋራ ግብረ- ኃይሉ ጠቁሟል።

በዚህ አጋጣሚ የሽብር ቡድኑ ሴራዎች እንዲከሽፉ፤ የሶማሌ ክልል መንግስት የፀጥታ መዋቅር እና የክልሉ ህዝብ ላደረገው ከፍተኛ አስተዋፅኦ የጋራ ግብረ- ኃይሉ ምስጋናውን አቅርቧል፡፡

በመጨረሻም በመላ ሀገሪቱ የፀጥታና ደኅንነት ስጋቶችን በማስወገድና በሽብር ቡድኖች እንዲሁም በፀረ-ሰላም ሀይሎች የሚታቀዱ የጥፋት ሴራዎችን በማክሸፍ እና በቁጥጥር ስር እንዲውሉ በማድረግ በኩል የብሄራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት፣ የሀገር መከላከያ ሠራዊት፣የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ እና የኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት አስተዳደር ከመላው የኢትዮጵያ ህዝብ ጋር በመቀናጀት እየወሰዱት ያለው እርምጃ ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን የጸጥታና ደኅንነት የጋራ ግብረ- ኃይል ለመገናኛ ብዙሃን በላከው መግለጫ አረጋግጧል፡፡
የጸጥታና ደኅንነት የጋራ ግብረ- ኃይል

ታህሳስ 9/2016 ዓ.ም

እንኳን ደስ አለን....🇪🇹🇪🇹👌አትሌት ለተሰንበት ግደይ የዓለም አቀፍ የአትሌቲክስ የስፖርታዊ ጨዋነት ሽልማት አሸናፊ ሆነች!ትውልደ ኢትዮጵያዊት የሆነችው እና በአሁኑ ጊዜ ለሆላንድ የምትሮጠ...
09/12/2023

እንኳን ደስ አለን....🇪🇹🇪🇹👌

አትሌት ለተሰንበት ግደይ የዓለም አቀፍ የአትሌቲክስ የስፖርታዊ ጨዋነት ሽልማት አሸናፊ ሆነች!

ትውልደ ኢትዮጵያዊት የሆነችው እና በአሁኑ ጊዜ ለሆላንድ የምትሮጠው ሲፋን ሐሰን በሩጫ ወቅት መውደቋ ይታወሳል፡፡

ይህን ተከትሎም አትሌት ለተሰንበት ግደይ ባደረገችው መልካም ተግባር የዓለም አትሌቲክስ የስፖርታዊ ጨዋነት አሸናፊ እንደሆነች ተሰምቷል፡፡

ሰበር ዜና...🇪🇷በኤርትራ በደቡባዊ ዳንካሊያ የሚኖሩ አፋሮች በኤርትራ መንግስት ትዕዛዝ እስርና እንግልት እየደረሰባቸው ነው ተባለ። ከቀናት በፊት በፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፍወርቅ የሚመራ የሀገ...
28/11/2023

ሰበር ዜና...🇪🇷

በኤርትራ በደቡባዊ ዳንካሊያ የሚኖሩ አፋሮች በኤርትራ መንግስት ትዕዛዝ እስርና እንግልት እየደረሰባቸው ነው ተባለ።

ከቀናት በፊት በፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፍወርቅ የሚመራ የሀገሪቱ ከፍተኛ ባለስልጣናት በደቡባዊ ዳንካሊያ በመገኘት ህዝቡን በማነጋገር ትምህርትቤቶች የጤና የውሃ ተቋማት በመገንባት አስፈላጊውን ሁሉ እናደርጋለን ማለታቸው ይታወቃል። ባለፉት 20 ቀናት ጀምሮ እናንተ ከሃዲ ናችሁ ፕሬዝደንቱ ያደረገው ሚስጥራዊ ጉብኝትና የተለያዩ የደንካሊያ መረጃዎችን አሳልፋችሁ ለኢትዮጵያ ሰጥታችኋል የእርዳታ እህልም ከኢትዮጵያ እንደሚመጣላችሁና ኤርትራ የማታውቅ ድብቅ ግንኙነት ከኢትዮጵያ እንዳላችሁ ደርሰንበታል በማለት እስካሁን ከ70 በላይ ወጣቶች አፍነው ወደ አስመራ ተወስደዋል። ወጣቶቹን አትወስዱም ያሉትን የሀገር ሽማግሌዎች ላይ ድብደባ ፈፅመዋል። ከዚህ ወር ጀምሮ ምንም አይነት እርዳታ አይቀርብላችሁም ብለዋል።ወጣቶችን አፍነው ከወሰዱ በኋላ ህዝቡን ለማረጋጋት ህዝባዊ ውይይት መድረክ ቢያዘጋጁም ህዝቡ ፍቃደኛ መሆን አልቻለም። በዚህ የተደናገጠው የደቡባዊ ደንካሊያ የመንግስት ተወካዮች ከፍተኛ ድንጋጤ ውስጥ ገብተው የሀገር ሽማግሌዎች የጎሳ መሪዎችን ለመግባባት ያደረጉት ሙከራዎች እንዳልተሰካላቸው የመረጃ ምንጬ አሳውቆኛል። ከልማቱ ውጭ የሆነን ህዝብ መልሶ ማንገላታት በጣም ከባድ ነው።
Ahmed Habib Alzarkawi

አላህ ለደቡባዊ ደንካሊያ ህዝብ ፅናት ይስጣቸው እንላለን

የኢትዮጵያ አየርመንገድ 11 ኤርባስ አውሮፕላኖችን ለመግዛት የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረመ 🇪🇹ስምምነቱ ከ2023ቱ የዱባይ አየር ትርኢት ጎን ለጎን ተፈርሟል።የኢትዮጵያ አየርመንገድ 20 ኤ350-...
15/11/2023

የኢትዮጵያ አየርመንገድ 11 ኤርባስ አውሮፕላኖችን ለመግዛት የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረመ 🇪🇹

ስምምነቱ ከ2023ቱ የዱባይ አየር ትርኢት ጎን ለጎን ተፈርሟል።

የኢትዮጵያ አየርመንገድ 20 ኤ350-900 ኤርባስ አውሮፕላኖችን በመጠቀም ከአፍሪካ ቀዳሚው ነው ተብሏል።

የዛሬው ስምምነትም አየርመንገዱ ከኤርባስ ለመግዛት ያዘዛቸውን አውሮፕላኖች ቁጥር 33 ያደርሰዋል ነው ያለው የኤርባስ ኩባንያ በድረገጹ።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በትናንትናው እለትም ከቦይንግ ጋር 67 (የ36ቱ በሂደት የሚፈጸም) አውሮፕላኖችን ለመግዛት መስማማቱ ይታወሳል።

Update!ፅዮናዊቷ እስራኤል ከባድ ኪሳራን እያስተናገደች ትገኛለች ህንፃዎች በሮኬት እየተመቱ ዶግ አመድ እየሆኑ ነው ጀናዛቸው እዚህም እዚያም ይወድቁ ይዘዋል። ሊቆጣጠሩት ፍፁም ያልቻሉትን ...
08/10/2023

Update!

ፅዮናዊቷ እስራኤል ከባድ ኪሳራን እያስተናገደች ትገኛለች ህንፃዎች በሮኬት እየተመቱ ዶግ አመድ እየሆኑ ነው ጀናዛቸው እዚህም እዚያም ይወድቁ ይዘዋል። ሊቆጣጠሩት ፍፁም ያልቻሉትን ጥቃት እያስተናገዱ ይገኛል።

ፅዮናዊቷ ሀገር በአየር ሃይል በባህር ሃይል በምድር ሃይል ጋዛ ላይ የአፀፋ ምላሽ የቦምብና የሮኬት እያዘነበች ትገኛለች። ጠ/ሚ ቤኒያሚን ጋዛን ወደ ፍርሽራሽነት እቀይራታለሁ ህዝቡ ጋዛን ለቆ እንዲወጣ መልዕክት አስተላልፈዋል።

የሞሳድ ሳይበርን አልፎ በየብስ በባህርና በአየር የገባው የ"አልቀሳም ሳይበር" ቡድን ለረጂም ግዜ ድምፁን አጥፍቶ የዘረጋው የቴክኖሎጂ መስመር ፅዮናዊቷ ኢስራኤልን እያንኮታኮተ ይገኛል። የሞሳ...
08/10/2023

የሞሳድ ሳይበርን አልፎ በየብስ በባህርና በአየር የገባው የ"አልቀሳም ሳይበር" ቡድን ለረጂም ግዜ ድምፁን አጥፍቶ የዘረጋው የቴክኖሎጂ መስመር ፅዮናዊቷ ኢስራኤልን እያንኮታኮተ ይገኛል። የሞሳድን ቴክኖሎጂ ያለምንም ገደብ "Bypass" ማድረግ እንደቻለ የአለም ሚዲያዎች እየዘገቡ ይገኛል።

የአፋር ህዝብ ራሱን በራሱ እንዲያስተዳድር ትልቅ ዋጋ የከፈሉት መሪ፡- ሱልጣን አሕመድ አሊሚራህ*******************በአፋር ሱልጣኔት ታሪክ ከታላቁ መሪ ከሱልጣን አሊሚራህ አብራክ ከ...
14/09/2023

የአፋር ህዝብ ራሱን በራሱ እንዲያስተዳድር ትልቅ ዋጋ የከፈሉት መሪ፡- ሱልጣን አሕመድ አሊሚራህ
*******************
በአፋር ሱልጣኔት ታሪክ ከታላቁ መሪ ከሱልጣን አሊሚራህ አብራክ ከተገኙ ልጆች መካከል ስድስተኛው ልጅ ሱልጣን አሕመድ አሊሚራህ ናቸው፡፡ የቀድሞ የአፋር ሱልጣኔት መሪ ሱልጣን ሃንፍሬ አሊሚራህ ከዓመታት በፊት ሕይወታቸው ማለፉን ተከትሎ ወንድማቸው ሱልጣን አህመድ አሊሚራህ የሱልጣንነት ሹመታቸውን መጋቢት 4 ቀን 2015 ዓ.ም ተቀብለዋል።

ሱልጣን አሕመድ አሊሚራህ በ1944 ዓ.ም በሱልጣኔቶች መናገሻ በአሳይታ ወረዳ ልዩ ስሙ ሂናሌ በተባለ ቀበሌ ነበር የተወለዱት። እድሜያቸው ለቁርዓን ሲደርስ ሱልጣን አሊሚራህ ወዳስገነቧቸው መድረሳ ገቡ። ከመድረሳው ከ1ኛ እሰከ 4ኛ ክፍል የቀለም ትምህርት ቀስመዋል። ከአምስተኛ ክፍል እስከ ስምንተኛ ክፍል በአስመራ ከተማ ተከታተሉ፤ ቀሪውን ትምህርታቸውን በአዲስ አበባ እና በግብፅ "ኢስማኤል ቃቢሲያ" በተባለ ትምህርት ቤት አጠናቀቁ።

በ1962 ዓ.ም ወደእንግሊዝ በማምራት ለአንድ ዓመት ተኩል የቋንቋ ትምህርት የተማሩት ሱልጣን አህመድ፤ ለከፍተኛ ትምህርት ወደ አሜሪካ በመጓዝ ከ1963 እስከ 1967 ዓ.ም ከፍተኛ ትምህታቸውን ተከታትለዋል።

ሱልጣን አሕመድ አሊሚራህ የደርግ መንግሥት በአፋር በገባበት ወቅት እና አባታቸው ሱልጣን አሊሚራህ በስደት ወደሳዑዲ አረቢያ ሲያቀኑ ከወንድማቸው ከሱልጣን ሐንፋሬ ጋር በመሆን ደርግን በመዋጋት ለ17 አመታት ህይወታቸውን ለአፋር ህዝብ ነፃነት ሲታገሉ ኖረዋል።

በተለይም ከ1967 እስከ 1973 ድረስ የአፋር ነፃ አውጪ ፓርቲን በማቋቋም በዞን አንድ፣ በዞን ሶስት፣ በዞን አራት በመንቀሳቀስ ከአፋምቦ ወረዳ ኦጋግና_ዓዳይቶ ላይ በትግል ምሽግ ውስጥ ለአምስት አመታት የፓርቲው የጦር ግንባር ዋና መሪ በመሆን ከደርግ ጋር እልህ አስጨራሽ ጦርነት አድርገዋል።

ሱልጣን አሕመድ አሊሚራህ በርካታ የጦርነት ውሎዎችን ያካሄዱ ሲሆን አዳይቱ፣ ኡሙሌይታ፣ ኦጋግ፣ ኢድግሎ፣ ሃሪሳ፣ አሳይታ፣ አልገና፣ አፋምቦ፣ ዳትባህሪ፣ ክፊሉ፣ ጉርጉራ፣ ዓስማራ፣ ዳሊይ፣ ሃዶላ እና የመሳሰሉት ደርግን ላይ ድል በማድረግ በፓርቲው ቁጥጥር ሥር ለማድረግ የቻሉባቸው አካባቢዎች ነበሩ።

ሱልጣኑ የደርግ ሥርዓትን ለመገርሰስ እስከተቻለበት ድረስ በሳዑዲ የአፋር ነፃ አውጭ የውጭ ግኑኝነት አመራር በመሆን ለትግሉ ድጋፍ ከተለያዩ ሀገራት ጋር በመገናኘት ስኬታማ የወዳጅነት ድጋፍ የሚገኝበትን ሁኔታ ለማመቻቸት ሰርተዋል።

ሱልጣን አሕመድ ከተለያዩ ሀገራት ጋር መልካም ግንኙት እንዲፈጠር የሰሩ ሲሆን፤ ከእነዚህም መካከል ሶሪያ፣ ሶማሊያ፣ ጂቡቲ፣ ፈረንሣይ፣ ጣለያን፣ ባህሬን፣ ኢራቅ፣ አሜሪካ፣ ቤልጅየም፣ ሆላንድ፣ ሊቢያ፣ ኬኒያ፣ ኢንግሊዝ፣ ሞሮኮ፣ ታንዛኒያ እና ኩዌት ተጠቃሽ ሀገራት መሆናቸውን በ2008 ዓ.ም ለ"አፋር ህዝብ ትግል" መፅሐፍ ደራሲ በሰጡት ሃሳብ ተናግረዋል።

ሱልጣን አህመድ አሁን ያለው የፌዴራሊዝም ሥርዓት እንዲመጣና የአፋር ህዝብ ራስን በራስ የማስተዳደር ጥያቄ እንዲመለስለት ዱር ቤቴ ብለው የወጡት ገና በ23 ዓመታቸው ሲሆን፣ ጦር መርተው የትግሉን ፍሬ ለማየት ከቻሉ መሪዎች መካከል አንዱ ናቸው።

በ1983 በኢትዮጵያ የሽግግር መንግሥት ሲቋቋም የአፋር ነፃ አውጪን በመወከል የምክር ቤቱ ተሳታፊ የነበሩት ሱልጣን አህመድ፤ ድሉ ከተገኘ በኋላ ፊታቸው ወደግል ሥራ በማዞር በንባብና ጥናት ላይ አተኩረዋል። ሱልጣን አሕመድ አሊሚራህ በሃይማኖትም በሳይንሱም ትልቅ ዕውቀት አሏቸው ከሚባሉ የአፋር ምሁራን መካከል አንዱ ናቸው።

ሱልጣን አህመድ አሊሚራህ ከአርባ ዓመት በላይ የትዳር አጋራቸው ከሆኑት አሜሪካዊት እንስት 9 ልጆችን ያፈሩ ሲሆን፤ በአውሳ ሱልጣኔቶች ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ከውጭ ዜጋ ጋር ትዳር የመሰረቱም ብቸኛው መሪ ናቸው፡፡

Ebc

የኢትዮጵያ ብሄሮችና ክልሎች  #ውበት  #ባህል  #የጥበብ ደረጃዎችን ለማወቅ ፔጁን ተቀላቀሉ
17/10/2022

የኢትዮጵያ ብሄሮችና ክልሎች
#ውበት #ባህል #የጥበብ ደረጃዎችን ለማወቅ ፔጁን ተቀላቀሉ

Ethiopia 🇪🇹

Latest 2022 Ranking of Regional with the most Beautiful Women in Ethiopia 🌍💚

1. Adisababa
2. Amhara
3. Oromia
4. Tigrai
5. Afar
6. Harar
7. Somali
8. Diredawa
9.Benishangul
10. Sidama

20/09/2022
የሕወሓት ቃል አቀባዩ የኤርትራ ጦር በሙሉ ኃይሉ ጥቃት ሰንዝሮብናል አሉአምባ ዲጂታል፤ ማክሰኞ መስከረም 10፣ 2015 ― የሕወሓት ቃል አቀባዩ አቶ ጌታቸው ረዳ በጎረቤት ኤርትራ ጦር ጥቃት ...
20/09/2022

የሕወሓት ቃል አቀባዩ የኤርትራ ጦር በሙሉ ኃይሉ ጥቃት ሰንዝሮብናል አሉ

አምባ ዲጂታል፤ ማክሰኞ መስከረም 10፣ 2015 ― የሕወሓት ቃል አቀባዩ አቶ ጌታቸው ረዳ በጎረቤት ኤርትራ ጦር ጥቃት ተሰንዝሮብናል ያሉት ዛሬ ማክሰኞ መስከረም 10፣ 2015 ነው፡፡

አቶ ጌታቸው በትዊተር ባሰፈሩት ጽሑፍ የኤርትራ ጦር ከተከዜ እስከ ኢሮብ ባሉት በሁሉም ግንባሮች በሙሉ ኃይል ጥቃት ተሰንዝሮብናል ብለዋል፡፡ ቃል አቀባዩ ከባድ ውጊያ አለባቸው በማለትም የተለያዩ ቦታዎችን ዘርዝረዋል፡፡ እነዚህም ማይ ኩህሊ፣ ዝባን ገደና፣ አዲ አዋላ፣ ራማ፣ ፀሮና እና ዛላንበሳ ናቸው፡፡

እግረ መንገድ፡ በምሥራቅ አፍሪካዊቷ አገር ኡጋንዳ የኢቦላ ቫይረስ መመዝገቡ ተነግሯል፡፡ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት በቫይረሱ የተያዘ የ24 ዓመት ሰው ዛሬ ማለዳ ሕይወቱ አልፏል፡፡ አገሪቱ በ...
20/09/2022

እግረ መንገድ፡ በምሥራቅ አፍሪካዊቷ አገር ኡጋንዳ የኢቦላ ቫይረስ መመዝገቡ ተነግሯል፡፡ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት በቫይረሱ የተያዘ የ24 ዓመት ሰው ዛሬ ማለዳ ሕይወቱ አልፏል፡፡ አገሪቱ በሌሎች የ6 ሰዎች ሞት ላይ ምርመራ እያካሄደች ነው ተብሏል፡፡

ከአካል በሚወጣ ፈሳሽና በመነካካት የሚተላለፈው ገዳዩ የኢቦላ ቫይረስ፤ ኃይለኛ ትኩሳት፤ ራስ ምታትና የጡንቻ ህመም ያስከትላል፡፡

ኢቦላ ቫይረስ ለመጀመሪያ ጊዜ የተከሰተው በሱዳን ናዛር እና በዴሞክራቲክ ሪፑብሊክ ኮንጎ ያምቡኩ በፈረንጆቹ 1976 ነበር፡፡

ዴይሊ ሜል የተባለው በእንግሊዝ ትልቅ ተነባቢነት ያለው  ሚዲያ ፡ ከደቂቃዎች በፊት  በንግስት ኤልሳቤጥ አስከሬንን በያዘው ሳጥን ላይ የፀሃይ ጨረር ታየ ፡ የመንግስተ ሰማያት በሮችም ፡ ለግ...
13/09/2022

ዴይሊ ሜል የተባለው በእንግሊዝ ትልቅ ተነባቢነት ያለው ሚዲያ ፡ ከደቂቃዎች በፊት በንግስት ኤልሳቤጥ አስከሬንን በያዘው ሳጥን ላይ የፀሃይ ጨረር ታየ ፡ የመንግስተ ሰማያት በሮችም ፡ ለግርማዊት ንግስት ወለል ብለው ተከፈቱ በማለት ፃፈኮ ።.......
ጋዜጣው ስለጉዳዩ ሲያብራራም ፡ ንግስት ኤልሳቤጥ በሞቱ ቀን ሰማይ በቀስተ ደመና ተውቦ ነበር ፡ ዛሬ ደግሞ ረዥምና አንፀባራቂ የፀሃይ ጨረር በንግስቲቱ አስከሬን ላይ አርፎ ፡ በሰላም ገነት መግባታቸውን አብስሮናል ሲል ፡ የምሩን ፅፏል ። ይህን ዘገባም ሚረር እና ሌሎች ጋዜጦች በሰፊው እያራገቡት ይገኛሉ ።

08/09/2022

ስለ ንግሥት ኤልሳቤት II ምን ያህል ያውቃሉ?

የእንግሊዝ ንግስት "Queen Elizabeth II" ከእንግሊዝ ውጪ የ 15 ሃገራት ንግስት ናት! ስምንቱ ጥቃቅን የካረቢያን ሃገራት ሲሆኑ ሌሎቹ ደግሞ እንደ ካናዳ፣ አውስትራሊያ እና ኒውዚላንድን የመሳሰሉ ሃገራት ናቸው!

እንግሊዝ አሁንም ድረስ "Constitutional Monarchy (ህገ መንግስታዊ የዘውድ አገዛዝን)" ትከተላለች! ንግስቲቷ በእንግሊዝ አያሌ መብቶች አሏት !

ንግስቲቷ የእንግሊዝ ቤተ ክርስቲያን (Church of England) አለቃ ናት። እሱ ብቻ አይደለም የሃገሪቷ ጦር አዛዥም ጭምር ናት! በፈለገችሁ ሰዓት የትኛውንም ሃገር ጦርነት የመግጠም መብት አላት! የትኛውም የእንግሊዝ ሃገር ወታደር ወደ ውትድርና ከመግባቱ በፊት ቃለ መሃላ የሚፈፅመው በንግስቲቱ ስም ነው።
የንግስቲቷ አጠቃላይ ዓመታዊ ወጪ እስከ 68 ሚልዮን ፓውንድ ይደርሳል! ይህ እንግዲህ ከታክስ ከፋዩ ህዝብ የሚሰበሰብ ገንዘብ ነው!
የእንግሊዝ ፓርላማ ስለ ንጉሳዊ ቤተሰቡ ምንም አይነት ጥያቄዎችን መጠየቅም ሆነ የወደፊት እጣ ፈንታቸው ላይ መወያየት አይችልም! ፓርላማው የሚያወጣቸው ህጎች የሚፀድቁት በንግስቲቷ ብቻ ነው።

ጌታዬ! ዓለም ላይ የፈለገችው ቦታ ለመሄድ "passport" የማያስፈልጋት ሴት የእንግሊዟ ንግስት ብቻ ናት!
ንግስቲቷ የሃገሪቷ "Head of State" ናት። በሃገረ እንግሊዝ መኪና ካለ መንጃ ፍቃድ ማሽከርከር የምትችለው ንግስቲቷ ብቻ ናት። እሱ ብቻ ሳይሆን ካለ ፍጥነት ገደብ መንዳት የሚፈቀደው ለሷ ብቻ ነው። በ 150 ብትነዳ እንኳን የእንግሊዝ ትራፊክ የማስቆም መብት የለውም! ካለ ታርጋ ቁጥር መኪና የማሽከርከር መብትም ጭምር ያላት እሷ ብቻ ናት።

ታክስ(ግብር) ለመንግስት ያለመክፈል መብት ያላት ንግሥቲቷ ብቻ ናት።

ሌላ የሚደንቀው ህግ ንግስቲቷ በፍፁም ልትከሰስ አትችልም! ምንም አይነት ወንጀል እንኳን ብትሰራ መቶ በመቶ ያለመከሰስ መብት አላት።

እንግሊዝ ውስጥ ያሉ ሁሉም አሳ ነባሪዎች እና ዶልፊኖች የግል ሃብቶቿ ናቸው።

የንግስቲቷ የግል ሃብት ብቻ ወደ 550 ሚልዮን ዶላር ይገመታል። በአጠቃላይ የንጉሳዊያኑ ቤተሰብ ሃብት እስከ 30 ቢልዮን ዶላር ድረስ ይደርሳል!

ንግስቲቷ በእጇ የምትይዛት የዘነጠች ቦርሳ ትልቅ መሳርያዋ ናት። እንግዶችን ተቀብላ እያወራችው ከደበራት፣ ከደከማት አልያም ደህንነቷ ካሳሰባት ለሰራተኞቿ እና ለጥበቃዎቿ መልዕክቶችን የምታስተላልፈው በዚህች ሁሌ በማትለያት ቦርሳዋ እንቅስቃሴ ነው።

የምትኖርበት "Buckingham palace" ውስጥ ለሷ ብቻ የተቀመጠላት "ATM" ማሽን ያላት፣ አለፍ ሲልም የፃፈችው ደብዳቤ ጨረቃ ላይ የተቀመጠላት ሴት ነች!

ንግስቲቷ ፊት ቱታ ወይም ቲሸርት አድርገህ መቅረብ አትችልም! "formal" ያልሆነ ልብስ ለብሶ መቅረብ ከቤቷ ያስባርርሃል! ንግስቲቷን መንካት ወይም ማቀፍ ፍፁም ክልክል ነው፣ እንደ ሃገር መሪ እንኳን እሷ መጀመሪያ ለመጨበት እጇን ካልዘረጋች አንተ ቀድመህ መዘርጋት አትችልም! ቀድማ ሳትቀመጥ መቀመጥ አትችልም! በመኖርያዋ ቤት ግብዣ ላይ ተገኝተህ እሷ ምግቧን ሳትጨርስ አንተ መብላትህን ማቆምም ሆነ ተነስተህ መሄድ አትችልም!

በአመት ሁለት ግዜ ልደቷ የሚከበርላት ብቸኛ ሴት የእንግሊዟ ንግስት ናት። ለምን? በትክክል የተወለደችበት ቀን ዝናባማ ስለሆነና ሰዎች አደባባይ ወጥተው ልደቷን ማክበር ስለማይችሉ በበጋ ወቅት ሌላ የልደት ቀን ተሰይሞላታል።

የትኛውንም ህግ የመጣስ መብት ያላት ብቸኛዋ ሴት መሆን አይደንቅም? 14 የእንግሊዝ ጠቅላይ ሚንስትሮች ስልጣን ላይ ወጥተው ሲለቁ እስካሁን በንግስትነቷ ለ 70 ዓመታት ያህል ቆይታ ዛሬ ከዚህ ዓለም በሞት የተለየቸው ንግስት ኤልሳቤት ሁለተኛ (Queen Elizabeth II) እንግሊዛውያን "What happens after the queen ?" በሚል ጥያቄ ላይ እያወጡ እያወረዱ ነው!😀
https://www.facebook.com/profile.php?id=100085420814622

የአመቱ ጀግና 🙏ስንቱ እጅ እግር እያለው የሰው ሀቅ በሚያሳድበት  ለትንሽ ብር ብሎ የሰው ንፍስ ቀሚቀጠፍበት ኢትዮጵያ ለይ እንደዚህ አይነት ጀግኖችን ስታይ ደስታ ይሰማሃል የ2014 ጀግናዬ ...
08/09/2022

የአመቱ ጀግና 🙏

ስንቱ እጅ እግር እያለው የሰው ሀቅ በሚያሳድበት ለትንሽ ብር ብሎ የሰው ንፍስ ቀሚቀጠፍበት ኢትዮጵያ ለይ እንደዚህ አይነት ጀግኖችን ስታይ ደስታ ይሰማሃል የ2014 ጀግናዬ ነው ለኔ።

ሰበር ዜና ጀግናው ጥምር ሀይላችን በአዲርቃይ ግንባር ከፍተኛ ድል እያገኘ ነውጠላት ለበርካታ ወራት በወረራ ይዟቸው የነበሩ  የአድርቃይ አካባቢዎች ነፃ እየወጡ ነው ።  የጥምር ጦር  ሀይሉን...
04/09/2022

ሰበር ዜና

ጀግናው ጥምር ሀይላችን በአዲርቃይ ግንባር ከፍተኛ ድል እያገኘ ነው

ጠላት ለበርካታ ወራት በወረራ ይዟቸው የነበሩ የአድርቃይ አካባቢዎች ነፃ እየወጡ ነው ። የጥምር ጦር ሀይሉን ብቃት እና የሰሜን ጎንደር ህዝብ ጀግንነት ከፍ ያደረገ ጠላት አማራን የማዋረድና ኢትዮጵያን የማፈራረስ ህልሙን የመከነበት ድል ነው።

ጠላት ለረጅም ጊዜ ይዟቸው የቆያቸውን ተናፋቂዎቹ የቱሪስት መዳራሻ የነበሩት የሃገራችን ምልክት የሆኑት የሃዋዛ ተራሮችንና የአዝማች ያዕቆብ እምብርቷን መኒ ወንበርጌን ሙሉ በሙሉ ጥምር ጦራችን ተቆጣጥሯል።

ጥምር ሀይሉ ጠላትን ለወራት ቀን ከሌት የሰራውን ኮንክሪት ምሽግ ደረማምሶ ነፃ አውጥቶ ወደ አዲአርቃይ አናትና ማይሊሃም አቅጣጭ እየገሰገሰ ይገኛል!!

ድሉ ይቀጥላል። ህዝባዊ ድጋፉ ይቀጥል።

ሰበር ዜና...🇪🇹👌ህወሃት ሳያስብበት በከፈተው ጦርነት በርካታ አመራሮቹን እያጣ ይገኛል። በዚህም 1:- ጀነራል አስርተ2:- ኮ/ል ጉዕፅ3:- ኮ/ል በርሀ በጊዕ እና4:- ኮ/ል ወርቂ የተባሉ...
31/08/2022

ሰበር ዜና...🇪🇹👌

ህወሃት ሳያስብበት በከፈተው ጦርነት በርካታ አመራሮቹን እያጣ ይገኛል። በዚህም

1:- ጀነራል አስርተ
2:- ኮ/ል ጉዕፅ
3:- ኮ/ል በርሀ በጊዕ እና
4:- ኮ/ል ወርቂ የተባሉት አመራሮች በመከላከያ ሰራዊት መደምሰሳቸው ታውቋል።

Address


Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Al Alam Amharic/አል አለም አማርኛ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Videos

Shortcuts

  • Address
  • Alerts
  • Videos
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share