Ethiopian prosperity

  • Home
  • Ethiopian prosperity

Ethiopian prosperity Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Ethiopian prosperity, .

22/08/2024
ሆሳዕና፤መጋቢት፣4/2016ዓ.ምየማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መስተዳድር ምክር ቤት በአጀንዳነት የመከረባቸውን ጉዳዮች በመመርመር ውሳኔ አስተላለፈ፤መስተዳድር ምክር ቤቱ ለሁለት ቀናት ሲያካሔድ የ...
13/03/2024

ሆሳዕና፤መጋቢት፣4/2016ዓ.ም
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መስተዳድር ምክር ቤት በአጀንዳነት የመከረባቸውን ጉዳዮች በመመርመር ውሳኔ አስተላለፈ፤

መስተዳድር ምክር ቤቱ ለሁለት ቀናት ሲያካሔድ የነበረው መደበኛ ስብሰባ ተጠናቋል

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ አምሪያ ስራጅ የመስተዳድር ምክር ቤቱ ያካሔደው 8ኛ መደበኛ ስብሰባ መጠናቀቁን በማስመልከት በሰጡት ማብራሪያ እንደገለጹት ምክር ቤቱ በልዩ ልዩ አጀንዳዎች ላይ በመምከር ውሳኔ አስተላልፏል።

እንደ ኃላፊዋ ገለጻ መስተዳድር ምክርቤቱ በአጀንዳነት ከቀረቡለት ጉዳዮች ውስጥ የ77 የኢንቬስትመንት ጥያቄዎችን መርምሮ ውሳኔ ማስተላለፉን አብራርተዋል።

እንደ ወ/ሮ አምሪያ ገለጻ 35 ፕሮጀክቶች ማሟላት የሚገባቸውን መስፈርት ሲያሟሉ ወደ ፊት አስፈላጊውን የማጣራት ስራ በማከናወን የሚወሰን መሆኑን አብራርተዋል። 29 ፕሮጀክቶች ደግሞ ተገቢውን ህጋዊ መስፈርት ባለማሟላታቸው ዉድቅ ስለመደረጋቸው ተናግረዋል።

በክልሉ በሰባት ዓመታት ስትራቴጂክ ዕቅድ፣ የሰው ኃይል የመዋቅር ጥናት ልዩ ልዩ አዋጆች እና ደንቦች ላይ ውይይት በማድረግ ውሳኔ መተላለፉን ኃላፊዋ በማብራሪያቸው ጠቁመዋል።

በዚህም መሰረት 10 የተለያዩ አዋጆችና 10 ደንቦችን በመመርመር አዋጆቹን ለተጨማሪ እይታ ለክልሉ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲቀርብ መስተዳድር ምክር ቤቱ የወሰነ ሲሆን ደንቦቹ የቀጣይ የስራ መመሪያ እንዲሆን ውሳኔ አስተላልፏል።

እንደ ወ/ሮ አምሪያ ገለጻ መስተዳድር ምክር ቤቱ ከተመለከታቸው ጉዳዮች ውስጥ የመንግስት ሰራተኞች የስራ ስምሪት እና የአመራር ስምሪት የጥናት ሰነድ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል።

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በሰቆጣ ቃልኪዳን ትግበራ ላይ ያተኮረ ውይይት እየተካሄደ ነውሆሳዕና:መጋቢት 2/2016(ኢዜአ)፦ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የምግብና ስርዓተ ምግብ ስትራቴጂ እና ለ...
11/03/2024

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በሰቆጣ ቃልኪዳን ትግበራ ላይ ያተኮረ ውይይት እየተካሄደ ነው

ሆሳዕና:መጋቢት 2/2016(ኢዜአ)፦ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የምግብና ስርዓተ ምግብ ስትራቴጂ እና ለሰቆጣ ቃልኪዳን ትግበራ በየደረጃው ምክር ቤት ስለማቋቋም ግንዛቤ ማስጨበጫ የምክክር መድረክ በሆሳዕና ከተማ እየተካሔደ ይገኛል።

መድረኩ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ እንዳሻው ጣሰው፣ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አንተነህ ፍቃዱ፣ የክልሉ የብሔረሰቦች ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ አቶ አቡቶ አኒቶ፣ የክልሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት አቶ ኤርሲኖ አቡሬ እንዲሁም ሌሎች የዞንና የልዩ ወረዳ ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል።

በውይይቱ ከሥርዓተ ምግብ ጋር በተያያዘ በገጠር እንዲሁም በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ በሚኖሩ የሕብረተሰብ ክፍሎችና ቤተሰቦች ዘንድ የመቀንጨር ችግር በከፋ ሁኔታ እንደሚስተዋል መጠቀሱን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያሳያል፡፡

ኢትዮጵያ ከአፍሪካ ልማት ባንክ ጋር ያላት አጋርነት ውጤታማ ሆኖ ቀጥሏል። ዛሬ ማለዳ ባንኩ በኢትዮጵያ በሚያካሂዳቸው ፕሮጀክቶች ላይ ከዶክተር አብዱል ካማራ ጋር ተወያይተናል። በተጨማሪም ወን...
08/03/2024

ኢትዮጵያ ከአፍሪካ ልማት ባንክ ጋር ያላት አጋርነት ውጤታማ ሆኖ ቀጥሏል። ዛሬ ማለዳ ባንኩ በኢትዮጵያ በሚያካሂዳቸው ፕሮጀክቶች ላይ ከዶክተር አብዱል ካማራ ጋር ተወያይተናል። በተጨማሪም ወንድሜ ዶ/ር አኪንዉሚ አዴሲና የኦባፌሚ አዎሎው የአመራር ሽልማትን በማግኘቱ ይህን ዕድል ተጠቅሜ እንኳን ደስ ያለህ ለማለት እወዳለሁ።

Ethiopia's partnership with the African Development Bank continued to be productive. This morning, I received and held discussions on AFDB's projects in Ethiopia with Dr. Abdul Kamara. Additionally, I seize this opportunity to congratulate my brother, Dr. Akinwumi Adesina, on receiving the Obafemi Awolowo Prize for Leadership.

Abiy Ahmed Ali

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የፌዴራል ፓርላማ እና የክልል  ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤቶች አባላት ከወከሏቸው ህዝቦች ጋር ያደረጉትን ውይይት  አስመልክቶ በሆሳዕና ከተማ ግብረመልስ ማቅረቢያ መድ...
08/03/2024

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የፌዴራል ፓርላማ እና የክልል ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤቶች አባላት ከወከሏቸው ህዝቦች ጋር ያደረጉትን ውይይት አስመልክቶ በሆሳዕና ከተማ ግብረመልስ ማቅረቢያ መድረክ እየተካሄደ ይገኛል።

የክልሉ የፌዴራል ፓርላማ እና የክልል ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤቶች አባላት ከወከሏቸው ህዝቦች ጋር ውይይት ሲያደርጉ መቆየታቸው ይታወሳል።

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ እንዳሻው ጣሰው ፣ የክልሉ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ፋጤ ሴርሞሎ ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ፣ የፌዴራል ፓርላማ እና የክልል ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤቶች ተወካዮች በውይይቱ ተገኝተዋል ።ሲል የዘገባው(ሀድያ ቴሌቪዥን)

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በምክር ቤቱ ማብራሪያቸው ካነሷቸው ዋና ዋና ነጥቦች መካከል፡-ሰላምን በተመለከተ ፦👉ሰላም ለምናስበው ልማት፣ ብልጽግናና አብሮነት እጅግ ወሳኝ ነገር ነ...
06/02/2024

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በምክር ቤቱ ማብራሪያቸው ካነሷቸው ዋና ዋና ነጥቦች መካከል፡-

ሰላምን በተመለከተ ፦

👉ሰላም ለምናስበው ልማት፣ ብልጽግናና አብሮነት እጅግ ወሳኝ ነገር ነው፤

👉ሰላም በሌለበት ሁኔታ ትልልቅ ነገር ማለም ማቀድ ያስቸግራል፤

👉ኢትዮጵያ ውስጥ በሰላም፣ በዴሞክራሲና በምርጫ ካልሆነ ጠመንጃ ይዞ ወደ ስልጣን መምጣት ፈጽሞ አይቻልም፤

👉ሰላም ሁሌም በውድ ዋጋ የሚገኝ ነው፤

👉ችግሮች የሚፈቱት በውይይት ብቻ ነው፤

👉ጠመንጃ ታጥቆ የራስን ህዝብ እያሰቃዩ እታገልልሃለሁ ማለት ትርጉም የሌለው አካሄድ ነው፤

👉ኢትዮጵያ ውስጥ በሰላም፣ በዴሞክራሲና በምርጫ ካልሆነ ጠመንጃ ይዞ ወደ ስልጣን መምጣት ፈጽሞ አይቻልም፤

👉በኢትዮጵያ ውስጥ ባለፉት 50 ዓመታት ሃሳብን አደራጅቶ የፖለቲካ ፍላጎትን ከማሳካት ይልቅ ጠመንጃን አማራጭ የማድረጉ ልምምድ ለሰላም እንቅፋት ፈጥሯል፤ ወንድም ወንድሙን ገድሎ ምን አሳካ ብለን ብንጠይቅ መልሱ ምንም የሚለው ይሆናል፤

የአማራ ክልልን በተመለከተ ፦

👉በአማራ ክልል ሁሉም ዞኖች ባደረግነው ውይይት ከህዝቡ ሶስት ዋና ጥያቄዎች ተነስተውልናል፤ እነርሱም የልማት፣ የህገ መንግስት ማሻሻልና የወሰን ጥያቄዎች ናቸው፤

👉መንግስት በአማራ ክልል የሚነሱ የልማት ጥያቄዎች ለመመለስ ብዙ ርቀት ሄዷል፤

👉ለአብነትም 2 ነጥብ 4 ቢሊዮን ብር ወጪ በማድረግ በአባይ ወንዝ ላይ በአይነቱ ልዩ የሆነ ድልድይ ገንብተናል፤

👉በጎርጎራ ፕሮጀክት አማካኝነትም የክልሉን ቱሪዝም የሚያነቃቃ ስራ ተከናውኗል፤

👉መንግስት ከአስተዳደር ወሰን ጋር የሚነሱ ጥያቄዎች በውይይትና ዘላቂ ሰላም በሚያመጣ አግባብ እንዲፈታ በጽኑ ይፈልጋል፤

👉ከግጭት የምናተርፈው አንዳች ነገር የለም፤ ይልቁንም ያለንን እናጎድላለን፡፡ በመሆኑም ሰላማዊ ንግግርና ውይይትን በማስቀደም የትኛውንም ጥያቄ መፍታት እንችላለን

በፕሪቶሪያው ስምምነት ዙሪያ ፦

👉ከስምምነቱ በኋላ የፌደራል መንግስትና የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር በትብብር በርካታ ድሎችን አስመዝግበዋል፤

👉አውሮፕላን ማሪፊያዎችን በመጠገን የአየር ትራንስፖርት ማስጀመር ተችሏል፣ በ100 ሚሊዮኖች የሚቆጠር ብር በማውጣት የቴሌኮም አገልግሎት እንዲጀመር ተደርጓል፤

👉ብሄራዊ ባንክ 10 ቢሊዮን ጥሬ ብር በመስጠት በክልሉ የባንክ አገልግሎት አስጀምሯል፤ 217 ፋብሪካዎችም ስራ ጀምረዋል፤

👉የጤና ተቋማትም አገልግሎት እየሰጡ ነው፤

👉ይሄ ትልቅ እምርታ ነው፤ ነገር ግን በቀጣይም ቀሪ ስራዎች አሉ እነርሱን በትብብርና በውይይት መስራት ይገባል፤

ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አተገባበርን በተመለከተ ፦

👉በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ በቁጥጥር ስር ከዋሉ ተጠርጣሪዎች መካከል አብዛኛዎቹ ተምረው ሰልጥነው ተለቀዋል፤

👉በሂደቱ የሚፈጠሩ ስህተቶች እንዳይኖሩ የአዋጁ መርማሪ ቦርድ እየሰራ ነው፤

👉ይህን አልፎ የሚከሰት ስህተት ካለም የማስተካከል ስራ የሚከናወን ይሆናል፤

👉የአዋጁ ዋነኛ ዓላማም የአገር ሰላምና ህልውናን መጠበቅ ነው፤

ብሔራዊ ትርክትን በተመለከተ ፦

👉በትናንት ስንባላ ነገን እንዳናፈርስ መጠንቀቅ አለብን፡፡ ነገን ለመዋጀት ትናንትን በእውቀት ማለፍ አለብን፤

👉ሁላችንም ለተፈጠሩ ችግሮች እውቅና ሰጥተን ለመፍትሄው በጋራ ለመስራት መዘጋጀት ይጠበቅብናል፤

👉ትናንት የተፈጸሙ በደሎችን በይቅርታ ማለፍ አለብን፤ ይህም በጋራ ጠንካራ አገር ለመመስረት መሰረት ይሚጥል ነው፤

ድርቅን በተመለከተ፦

👉ድርቅ በተለያዩ አካባቢዎች ተከስቷል፡፡ ድርቁ የሰው ህይወት እንዳይቀጥፍ ተባብረን መስራት አለብን፤ ነገር ግን ድርቁን ለፖለቲካ ፍጆታ ለማዋል የሚደረገው ጥረት ተገቢነት የለውም፤

👉ድርቁን ለመከላከል በሚደረገው ስራ ውስጥ ትልቁን ድርሻ የሚይዘው መንግስት ነው፤

👉መንግስት ድርቁን ለመከላከል ከ14 ቢሊዮን ብር በላይ በማውጣት ሰብዓዊ ድጋፍ ተደራሽ እንዲሆን አድርጓል፤

👉በቀጣይም ፕሮጀክቶችን በማጠፍም ጭምር ድርቁ በዜጎች ህይወት ላይ ጉዳት እንዳያደርስ የሚሰራ ይሆናል፡፡

ለማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሀብት ማሰባሰቢያ መድረክ እየተካሄደ ነው"በአዲስ ምዕራፍ፣አዲስ ተስፋ ፣ ለአዲስ ክልል" በሚል መሪ ቃል ለማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሀብት ማሰባሰቢያ እና የክልሉን ...
26/11/2023

ለማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሀብት ማሰባሰቢያ መድረክ እየተካሄደ ነው

"በአዲስ ምዕራፍ፣አዲስ ተስፋ ፣ ለአዲስ ክልል" በሚል መሪ ቃል ለማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሀብት ማሰባሰቢያ እና የክልሉን ፀጋዎች ማስተዋወቂያ መድረክ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው።

በመድረኩ የፌዴራል መንግስት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች፣ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች፣ የክልሉ ተወላጆች እና የልማት አጋሮች ተገኝተዋል።

መድረኩ የባለሀብቱን፣ የአጠቃላይ ሕዝቡን እና የልማት አጋሮችን አቅም በማቀናጀት የክልሉን ሕዝብ አጠቃላይ የልማት ፍላጎት ለማሟላት የሚያስችል አቅም ለመፍጠር ታስቦ የተዘጋጀ ነው።

በመርሃ ግብሩ ላይ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ እንደሻው ጣሰው፤ የህዝቡን ሰላም በመጠበቅና ሌሎች ዘርፎችንም በመደገፍ ወደ ስራ ገብተናል ብለዋል።

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ለኢንቨስትመንት ምቹ እና ለኢትዮጵያ ከተሞች እድገት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያለው በመሆኑ፤ ለሃገረ መንግስት ግንባታ የጀርባ አጥንት ሆኖ የቆየ ወደፊትም ሆኖ የሚሰራ ክልል ነው ብለዋል።

አክለውም፤ ከአዲስ አበባ ከተማ በቅርብ ርቀት የሚገኝ በመሆኑ ምርቶችን በፍጥነት መረከብ ለሚፈልጉ ባልሃብቶች በሮች ክፍት መሆናቸውን ገልጸዋል።

ክልሉ ሲቋቋም ድጋፍ ላደረጉ አካላት በሙሉ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

በሜሮን ምትኩ

የኢትዮጵያ የከፍታ ልኬታ እያንዳንዳችን ለአገራችን በምናደርገው አስተዋፅኦ ይወሰናል!የለውጡ መንግስት ኢትዮጵያ ከጎረቤት አገራት ጋር የሚኖራት ግንኙነት ዘላቂ እና የጋራ ተጠቃሚነትን መሰረት ...
25/11/2023

የኢትዮጵያ የከፍታ ልኬታ እያንዳንዳችን ለአገራችን በምናደርገው አስተዋፅኦ ይወሰናል!

የለውጡ መንግስት ኢትዮጵያ ከጎረቤት አገራት ጋር የሚኖራት ግንኙነት ዘላቂ እና የጋራ ተጠቃሚነትን መሰረት ያደረገ እንዲሆን ግልፅ አቅጣጫ አስቀምጦ ወደ ተግባር መግባቱ ይታወሳል።

የህዝብ ለህዝብ ግንኙነትን በማጠናከር፣ የሚያስተሳስሩ መሰረተ ልማቶችን በመዘርጋት፣ የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር ተሞክሮን በማጋራት፣ የቀጠናውን የመበልፀግ ፀጋ እውን ለማድረግ እና አስተማማኝ ሰላምን ለማረጋገጥ በርካታ ጥረቶች ተደርገዋል፤ በቀጣይም ተጠናክረው ይቀጥላሉ።

ኢትዮጵያ ከሌሎች አገራት ጋር ያላትን ግንኙነት ለማሳደግ ከምታከናውነው የመሰረተ ልማት ዝርጋታ በተጨማሪም ተፈጥሮም አስተሳስሯታል። ለአብነትም የዓለማችን ትልቁ ወንዝ ዓባይ 85 በመቶ አካባቢ ምንጩ ኢትዮጵያ ስትሆን የላይኛው እና የታችኛው የዓባይ ተፋሰስ አገራት በሚል 11 አገራትን አስተሳስሯል።

የተፋሰሱ አገራት በተለይም የታችኞቹ ለዓባይ ውሀ የሚያበረክቱት አንዳች አስተዋፅኦ ባይኖርም ኢትዮጵያ ብቻዬን ልጠቀም ብላ አታውቅም ወደ ፊትም አትልም። ከተፈጥሮአዊ እውነታውና ዓለም አቀፍ ህጎችን በሚፃረር መልኩ እራሳቸውን የወንዙ ዋነኛ ባለቤት አድርገው የሚቆጥሩ አንዳንድ የታችኞቹ ተፋሰስ አገራት በ21ኛው ክ/ዘመን ጭምር መኖራቸው ግን አግራሞትን ይጭራል።

ዓባይ የኢትዮጵያን እና የኢትዮጵያውያንን የውሀ ጥም አርክቶ አይደለም የሚፈሰው። በድቅድቅ ጨለማ የሚገኙ ሚሊዮኖችም ብርሀንን ይናፍቃሉ።

የዓባይ ወንዝ ጉዞ ተፈጥሯዊም ጭምር ስለሆነ ወደ ፊትም ይፈሳል። መገራቱ ደግሞ ጥቅሙ በጎርፍ ለሚጥለቀለቁ የታችኞቹ አገራት ጭምር ነው።

ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ በዓባይ ወንዝ ላይ በኢትዮጵያውያን ሙሉ አቅም እየተገነባ ያለ የዚህ ትውልድ ሀብት የቀጣዩ ትውልድ ደግሞ ቅርስም ጭምር ነው።

ግድቡም ውሀውም የኢትዮጵያ ቢሆንም ሌሎችን በማይጎዳ መልኩ ብሔራዊ ጥቅምን እና የዛሬውንም የነገውንም ትውልድ የመልማት መብት በሚያከብር መልኩ ስምምነት ላይ ለመድረስ ከታችኛው ተፋሰስ አገራት ጋር የሚደረገው ውይይት ቀጥሏል፤ አፍሪካውያን ወገኖቻችንን በማይጎዳ መልኩ የሚፈሰውን እንቁ ሀብታችንን ወደ ልማት የመቀየሩ ተግባር ከግድቡ መጠናቀቅ በኋላም ስለሚቀጥል ውይይቱም እንደሚቀጥል ይጠበቃል።

እንደ ዓባይ ወንዝ ሁሉ ቀይ ባህርም ኢትዮጵያን ጨምሮ ሌሎች የቀጠናውን አገራት በኢኮኖሚ አስተሳስሮ መቆየቱ በታሪክ ድርሳናት መጠቀሱ ብቻ ሳይሆኑ የቅርብ ጊዜ ትውስታ ነው። ቀይ ባህርን ሉዓላዊነትን ባከበረ መልኩ በሰጥቶ መቀበል መርህ በትብብር መጠቀም የሚጎዳው አገር አይኖርም።

በፍጥነት እያደገ የሚገኘውን ኢኮኖሚያችን ከማስተናገድ፣ ከሰላምና ደህንነት እንዲሁም እያደገ ካለው ከፍተኛ የህዝብ ቁጥር አንፃር የባህር በር ማግኘት ወሳኝ በመሆኑ ፍፁም ሰላማዊ እና ዓለም አቀፍ ህጎችም በሚያበረታቱት በጋራ የመልማት ትብብር ተጠቃሚ ለመሆን የሚደረጉ ዲፕሎማሲያዊ ጥረቶች ተጠናክረው ይቀጥላል።

ለኢትዮጵያ ከፍታ ከጎረቤት አገሮቻችን ጋር ለጋራ ተጠቃሚነት በትብብር መስራት ወሳኝ ቢሆንም በዋነኛነት እያንዳንዳችን ለአገራችን በምናደርገው አስተዋፅኦ ስለሚወሰን በማዕበል መነዳትን በማስወገድ ብዝሀነታችንን ይዘን አንድነታችንን ማጠናከር ከሁላችንም ይጠበቃል።

ሀዲያ ነፈራ ደምቋል።አዲስ አበባ: ጥቅምት 16/2016 ዓ.ም  የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት ምስረታ በነገው ዕለት በይፋ ይካሄዳል። የሀድያ ማኅበረሰብ ልዩ ልዩ በዓላት  ማክበሪያ የኾ...
27/10/2023

ሀዲያ ነፈራ ደምቋል።

አዲስ አበባ: ጥቅምት 16/2016 ዓ.ም የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት ምስረታ በነገው ዕለት በይፋ ይካሄዳል። የሀድያ ማኅበረሰብ ልዩ ልዩ በዓላት ማክበሪያ የኾነው ቦታ "ሀዲያ ነፈራ" ለነገው የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ምስረታ መርሀ ግብር ደምቆ ተውቧል።

ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የምክር ቤቱን ውሳኔ ካገኘ በኋላ አቶ እንደሻው ጣሰውን የክልሉ ርዕሰ መሥተዳድር አድርጎ መሾሙ የሚታወስ ነው። በነገው ዕለትም ይፋዊ የመንግስት ምስረታ ሥነ ሥርዓቱ በይፋ ይከበራል።

በሥነ ሥርዓቱም ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኀላፊዎችና ተጋባዥ እንግዶች ይታደማሉ ተብሎ ይጠበቃል ሲል የዘገበው (አሚኮ)

09/10/2023
የ12ኛ ክፍል ተፈታኞች ውጤታቸውን ነገ ከጠዋቱ 12 ሰዓት ጀምሮ በሚከተሉት አማራጮች ማየት ይችላሉ******************   የ2015 ዓም የ12ኛ ክፍል ተፈታኞች ውጤታቸውን መስከረም ...
09/10/2023

የ12ኛ ክፍል ተፈታኞች ውጤታቸውን ነገ ከጠዋቱ 12 ሰዓት ጀምሮ በሚከተሉት አማራጮች ማየት ይችላሉ
******************

የ2015 ዓም የ12ኛ ክፍል ተፈታኞች ውጤታቸውን መስከረም 29 ቀን 2016 ዓ.ም ከጠዋቱ 12 ሰዓት ጀምሮ በሚከተሉት አማራጮች ማየት እንደሚችሉ የትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል፦

በዌብሳይት - https://eaes.edu.et/
በአጭር መልዕክት - 6284
በቴሌግራም - https://t.me/eaesbot

ለሠላምና ንግግር የሚረፍድ ጊዜ የለም - ፕሬዚዳንት ሣኅለወርቅምን ጊዜም ቢሆን ለሠላምና ለንግግር የሚረፍድ ጊዜ የለም ሲሉ ፕሬዚዳንት ሣኅለወርቅ ዘውዴ ገለጹ፡፡6ኛው የሕዝብ ተወካዮች እና የ...
09/10/2023

ለሠላምና ንግግር የሚረፍድ ጊዜ የለም - ፕሬዚዳንት ሣኅለወርቅ

ምን ጊዜም ቢሆን ለሠላምና ለንግግር የሚረፍድ ጊዜ የለም ሲሉ ፕሬዚዳንት ሣኅለወርቅ ዘውዴ ገለጹ፡፡6ኛው የሕዝብ ተወካዮች እና የፌደሬሽን ምክር ቤቶች 3ኛ ዓመት የሥራ ዘመን የጋራ መክፈቻ ሥነ-ሥርዓት እየተካሄደ ነው፡፡

በሥነ- ሥርዓቱ ላይ ፕሬዚዳንት ሣኅለወርቅ ዘውዴ ባደረጉት ንግግር÷ በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል ሲካሄድ የነበረውን ደም አፋሳሽ ጦርነት በሠላም ስምምነት እንዲቋጭ መደረጉን አስታውሰዋል፡፡

በዚህም ለአፍሪካዊ ችግሮች አፍሪካዊ መፍትሔ የሚለው የአኅጉራችን መርኅ በተግባር ተፈትሾ ውጤታማ እንደሆነ አሳይተናል ነው ያሉት፡፡አሁን ላይ ስምምነቶቹ ወደ ተግባር ተቀይረው የመልሶ ግንባታ ምዕራፍ ላይ እንገኛለን ብለዋል በንግግራቸው፡፡

በሰሜኑ ሀገራችን ክፍል የነበረው ሁኔታ ለሀገራችን ትልቅ ትምህርት የሚወሰድበት ሆኖ አልፏል ሲሉ በአጽንኦት ገልጸዋል፡፡የሰሜኑን ጦርነት በንግግር መፍታት መቻሉ ብዙ ዜጎችን ከዕልቂትና ሰቆቃ የገላገለና እፎይታን የፈጠረ መሆኑንም ነው ያስገነዘቡት፡፡

ከዚህ በኋላ በሀገራችን በጠመንጃ እና ኃይል ልዩነቶችን የመፍታት አማራጭ ማክተም እንደሚኖርበትና እንደሚችልም በተግባር ያሳየ ነው ሲሉ ገልጸዋል፡፡

መንግሥት ከማንኛውም ኃይል ጋር ችግሮችን በመወያየትና በንግግር የመፍታት ቁርጠኝነት እንዳለው በተግባር ያስመሰከረበት ስለመሆኑም ነው የተናገሩት፡፡

ምን ጊዜም ቢሆን ለሠላምና ለንግግር የሚረፍድ ጊዜ የለም ብለዋል ፕሬዚዳንት ሣኅለወርቅ በንግግራቸው፡፡

በ100 ቀናት እቅድ አፈጻጸም ሂደቱ የተገኙ ውጤቶችን ማጠናከርና ማስፋፋት ይጠበቃል፡- ርእሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው      ሆሳዕና፣ መስከረም 23 ፣2016 ፡- የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክል...
04/10/2023

በ100 ቀናት እቅድ አፈጻጸም ሂደቱ የተገኙ ውጤቶችን ማጠናከርና ማስፋፋት ይጠበቃል፡- ርእሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው

ሆሳዕና፣ መስከረም 23 ፣2016 ፡- የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት መስተዳድር ምክር ቤት በሆሳዕና ከተማ ዛሬ ባካሄደው 2ኛ መደበኛ ስብሰባው በ100 ቀናት እቅድ አፈጻጸም ላይ እና በሌሎችም ጉዳዮች ተወያይቶ ውሳኔዎችን አሳልፏል፡፡

መስተዳድር ምክር ቤቱ በ100 ቀናት እቅድ አተገባበሩ ላይ በዝርዘር በመወያያት ጥንካሬዎችንና ጉድለቶችን ለይቷል፡፡

በመድረኩ በተለይም በጸጥታና በሰላም ጉዳዮች ፣ በግብርናና ገጠር ልማት፣ በትምህርት እና በጤና ዘርፎች አንዲሁም በገቢ አሰባሰብ ላይ ያተኮሩ ሪፖርቶች ቀርበው በዝርዝር ተገምግመዋል፤ አቅጣጫዎችም ተቀምጠዋል፡፡

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ክቡር አቶ እንዳሻው ጣሰው በመድረኩ አንደገለጹት፣ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በሽግግር ሂደቱ ውስጥ ሆኖ የልማትና የመልካም አስተደደር ተግባራትን አጠናክሮ ማስቀጠል ያስችል ዘንድ ከነሀሴ 20 ቀን 2015 ዓመተ ምህረት ጀምሮ የሚፈጸም የ100 ቀናት እቅድ አቅዶ ወደ ስራ በመግባት ያደረገው አንቅስቃሴ አበረታች ውጤቶች የተገኙበት መሆኑን ገልጸዋል፡፡
በ100 ቀናት እቅድ አፈጻጸም ሂደቱ የተገኙ ውጤቶችን ማጠናከርና ማስፋፋት ይጠበቃል ሲሉም ርእሰ መስተዳዳር እንዳሻው ጣሰው አሳስበዋል፡፡

የሰላምና የጸጥታ ጉዳይ ህብረተሰቡን ባሳተፈ መንገድ በልዩ ትኩረት መመራት አንደሚገባው በመስተዳድር ምክር ቤቱ በአእጽኖት ውይይት የተካሄደበት መሆኑ ተገልጿል፡፡
በአንዳንድ አካባቢዎች እየታዩ ያሉትን የጸጥታ ችግሮች የየደረጃው አመራር፣ የጸጥታ ኃይሉ እንዲሁም ህብረተሰቡ ተቀናጅተው በመፍታት ህብረተሰቡ መላ ትኩረቱ በልማት ተግባር ላይ የሚያውልበት ሁኔታ አንዲፈጠር መስራት አንደሚገባ አቅጣጫ ተቀምጧል፡፡

ከግብርናና ገጠር ልማት ተግባራት አኳያም የተጀመሩ ተግባራትን ይበልጥ ማሳደግና ማስፋፋት አንዲሁም የየአካባቢውን ጸጋዎች መሰረት ያደረገ የስፔሻላይዜሽን ስራን በማጠናከር ምተርታማነትን ከፍ ለማድረግና ተጠቃሚነትን ለማሳደግ በትኩረት አንዲሰራ አቅጣጫ ተቀምጧል፡፡

መሬት፣ ውሃ፣ ጉልበትን፣ ቴክኖሎጂዎችን እንዲሁም ግብዓትን በማቀናጀት ምርትና ምርታማነትን በማሻሻል ሀብት የመፍጠርንና ድህነትን የመርታቱን ጥረት ማጠናከር አንደሚገባም ተመላክቷል፡፡

በትምህርትና በጤናው ዘርፍ ማህበረሰቡን በተደራጀ ቅኝት ያሳተፈ ንቅናቄ በማካሄድ የትምህርት ብክነትን መቀነስ ፣ የኮሌራና የወባ ወረርሽኞችን ጫናና ጉዳት ለመቀልበስ ሁሉም አካላት ጥረት አንዲያደርጉ አቅጣጫ ተቀምጧል፡፡

በክልሉ አንዳንድ አካባቢዎች እያጋጠመ ያለውን የኮሌራና የወባ ወረርሽኝ በተደራጃ መንገድ አደረጃጀቶችን በመጠቀም ለመቀልበስ ፈጣን ርብርብ አንደሚያስፈልግም ተሰምሮበታል፡፡

የትምህርት ልማቱን ዘርፍ ጥራት በማሻሻል መጠነ መድገምንና ሌሎችንም የትምህርት ጥራት ጉድለቶችን ለማሻሻል በመማር ማስተማሩ ሂደት ተዋኒያን ከሆኑት መምራን፣ የትምህርት ቤት አመራሮችና አንዲሁም ከተማሪዎች ወላጆችና ከሌሎችም የትምህርት አጋሮች ጋር መወያያት እና ተቀራራቢ አስተሳሰብና ግንዛቤ በመፍጠር በተቀናጀ መንገድ በጋራ መስራት ይገባል ተብሏል፡፡
ከገቢ አሰባሰብ አንጻርም የገቢ ምንጮችን እና እድሎችን በጥልቀት በመፈተሽና ገቢን ከፍ በማድረግ ልማቱን ለማፋጥን በተቀናጀ መንገድ መስራት አንደሚገባ አቅጣጫ ተቀምጧል፡፡
በአጠቃላይ በዛሬው ዕለት ሲካሄድ የዋለው የክልሉ መስተዳድር ምክር ቤት 2ኛ መደበኛ የካብኔ ስብስባ በ100 ቀናት እቅዱ አፈጻጸም

መስከረም 18/2016የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ ማስተካከያ ተደረገ  በነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ ማስተካከያ መደረጉን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡...
29/09/2023

መስከረም 18/2016

የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ ማስተካከያ ተደረገ

በነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ ማስተካከያ መደረጉን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

በዚህም መሠረት ከዛሬ መስከረም 18 ቀን 2016 ከሌሊቱ 6 ሰዓት ጀምሮ በአዲስ አበባ ከተማ ተግባራዊ የሚሆነው የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡
በዚሁ መሠረት
1. ቤንዚን በሊትር 77 ብር ከ65 ሳንቲም
2. ነጭ ናፍጣ በሊትር 79 ብር ከ75 ሳንቲም
3. ነጭ ጋዝ በሊትር 76 ብር ከ75 ሳንቲም
4. የአውሮፕላን ነዳጅ በሊትር 70 ብር ከ83 ሳንቲም
5. ቀላል ጥቁር ናፍጣ በሊትር 62 ብር ከ36 ሳንቲም
6. ከባድ ጥቁር ናፍጣ በሊትር 61 ብር ከ83 ሳንቲም መሆኑ ተገልጿል፡፡(ኤፍ ቢ ሲ)

የድምፃዊ ማዲንጎ አፈወርቅ ሀውልት ተመረቀ*******************ልክ የዛሬ አመት በድንገት ህይወቱ ያለፈው የዝነኛው ድምፃዊ ማዲንጎ አፈወርቅ የአንደኛ አመት መታሰቢያ በተለያዩ ዝግጅቶ...
28/09/2023

የድምፃዊ ማዲንጎ አፈወርቅ ሀውልት ተመረቀ
*******************
ልክ የዛሬ አመት በድንገት ህይወቱ ያለፈው የዝነኛው ድምፃዊ ማዲንጎ አፈወርቅ የአንደኛ አመት መታሰቢያ በተለያዩ ዝግጅቶች እየታሰበ ነው::

ዛሬ ማለዳ የድምፃዊው ቤተሰቦች፣ የሙያ አጋሮች እና አድናቂዎች በተገኙበት በቅድስት ስላሴ ካቴድራል ቤተክርስቲያን የማዲንጎ ሀውልት ተመርቋል::

ከኤፍ ኤም አዲስ 97.1 ጋር ቆይታ ያደረገው የማዲንጎ የሙያ ባልደረባ አርቲስት ብርሀኑ ተዘራ በቀጣይ በድምፃዊው ተጀምረው የተጠናቀቁ የሙዚቃ ሥራዎች ለአድማጭ እንደሚቀርቡ ገልጿል::

ኤፍ ኤም አዲስ 97.1 በዛሬው እለት የድምፃዊውን ህይወት እና ሥራ የሚዳስስ "የማዲንጎ ማይክ" የተሰኝ ዘጋቢ ፕሮግራም ከቀኑ 7:00 ለአድማጭ ያቀርባል::

የወላይታ ዘመን መለወጫ በዓል - ጊፋታ  መስከረም 13/2016ዓምጊፋታ የወላይታ ብሔር የዘመን መለወጫ በዓል ነው። የወላይታ ብሔር የማንነቱ መገለጫ የሆኑ የተለያዩ የሚዳሰሱና የማይዳሰሱ ባህ...
24/09/2023

የወላይታ ዘመን መለወጫ በዓል - ጊፋታ

መስከረም 13/2016ዓም
ጊፋታ የወላይታ ብሔር የዘመን መለወጫ በዓል ነው። የወላይታ ብሔር የማንነቱ መገለጫ የሆኑ የተለያዩ የሚዳሰሱና የማይዳሰሱ ባህላዊና ታሪካዊ ቅርሶች አሉት። የአለባበስ ፣ የባህላዊ በዓላት አከባበር ፣ የለቅሶ እንዲሁም የጋብቻ ስርዓተ ክዋኔዎች እና ሌሎችም የወላይታ ብሔር በራሱ ባህላዊ ይዘት የሚከውናቸው እሴቶች ናቸው። የወላይታ ብሔር የዘመን መለወጫ የሆነው ጊፋታ በዓልም በብሔሩ ዘንድ የተለየ ቦታ የሚሰጠው በዓል ነው።

የወላይታ ብሔር የራሱ የሆነ የዘመን መቁጠሪያ ቀመር አለው። በአቆጣጠርም የዓመቱ የመጀመሪያ ወር "ጊፋታ" ይባላል ። የቃሉ ትርጓሜ ባይራ (ታላቅ)፣ የመጀመሪያ ፣ በኩር ማለት ነው። ጊፋታ በብሔሩ ዘንድ ትልቅ ቦታ የሚሰጠውና ከትውልድ ትውልድ ሲተላለፍ የመጣ የአሮጌ ዓመት ማብቂያና የአዲሱ ዓመት ማብሰሪያ ነው።

ጊፋታ ከአሮጌ ወደ አዲስ ተስፋ ፣ ከክረምት ወደ በጋ፣ ከጨለማ ወደ ብርሃን፣ ከአሮጌው ወደ አዲሱ ዓመት የሚሸጋገሩበት ነው።
በብሔሩ ዘንድ የጊፋታ በዓል የዕርቅ በዓል እንደሆነም ይታመናል። ስለሆነም የጊፋታ በዓል ሲቃረብ የተጣላ ዘመድ ፣ ጎረቤት ፣ ቤተሰብ ይሁን ጓደኛ እንዲታረቁ ይገደዳሉ።

የጊፋታን በዓል ሰው ባለዕዳ ሆኖ ማክበር አይችልም ። ስለሆነም የጊፋታ በዓል ሲደርስ ሰው ከዕዳ ነፃ መሆን ይጠበቅበታል። ይህም ይታወቃልና ማንም ባለዕዳ ሆኖ ጊፋታን አያከብርም ። ያለበትን ዕዳ ይከፍላል ።
የጊፋታ በዓል እየተቃረበ መምጣቱን የሚገልጹ የተለያዩ ክዋኔዎች አሉ፤ ከክዋኔዎቹም መካከል በወጣቶች ለጉሊያ/ደመራ/ የሚሆን እንጨት መሰብሰብና መከመር እንዲሁም በእናቶች የሚከናወን የእንሰት መፋቅ ሥነ ሥረአትም ሌላኛው የበዓሉ መዳረሻ ማብሰሪያ ነው።

ዓመት ሙሉ በየወሩ የቆጠቡትን ገንዘብ ሰብስበው ገበያ ሄደው አባቶች ሙክት ፣በሬ የሚገዙበት ሥርዓትም ለበዓሉ የራሱ የሆነ ድምቀት አለው ። የእርድ በሬ ከሶስት ወር ቀደም ተብሎ ተገዝቶ እስከ ዕርዱ ቀን በአንድ አባወራ ቤት እንዲቀለብ ይደረጋል።

ለበዓሉ መዳረሻ አስራ አምስት ቀን ቀደም ብሎ ሶስት ከወትሮው በተለየ ግብይት የሚከናወንባቸው ገበያዎች አሉ። እነዚህም ሀረሀይቆ፣ ቦቦደ እና ጎሻ ይባላሉ ። የሀራይቆ ገበያ ማኅበረሰቡ የጊፋታ በዓልን ታሳቢ አድርጎ ምርት በገፍ የሚቀርብበትና የጋማ ከብትም ወገባቸው እስኪጎብጥ ድረስ ስለሚሸከሙ፣ “የጋማ ከብት የሚያጎብጥ” ገበያ ተብሎ ይታወቃል።

ሌላኛው ቦቦዳ ገበያ ሲሆን ገበያው ጥሩ መዓዛ ያለው ገበያ ተብሎ ይጠራል። በዚህ ገበያ ሁሉም ሰው በአቅሙ የሚያስፈልገውን የሚገዛበት ነው። በጎሻ ገበያ ደግሞ ሁሉም ገበያተኛ ቁርስ ሳይበላ በማለዳ የሚያቀናበት ነው። ጎሻ የቃሉ ትርጉም እብደት ማለት ሲሆን ማህበረሰቡ የመጨረሻው ሣምንት ገበያ በመሆኑ ሁሉንም ነገር የሚገዙበትና በጧት ተነስተው ወደ ገበያ የሚያቀኑቡት በመሆኑ ጎሻ ተብሎ ይጠራል ።

ቁጠባ የጊፋታ አንደኛው መገለጫ ሲሆን በዓሉ በሚከበርበት ቀን ዕርድ ከተከናወነ በኋላ በእርጥብ ቆዳ ላይ ተቀማጭ ብር በማዋጣት ለመጪው ዓመት ጊፋታ ቁጠባ ይጀምራል። በቁጠባው ሴቶች በምግብ ቅቤ ቁጠባ፣ ወጣቶች በገንዘብ ቁጠባ ይሳተፉበታል ።
“ጊፋታ” ከመስከረም 8 እስከ 20 ባለው አንዱ እሁድ በጉጉት እና በከፍተኛ ዝግጅት በየዓመቱ የሚከበር የወላይታ የዘመን መለወጫ በዓል ነው። በብሔሩ ዘመን አቆጣጠር ቀመር መሠረት የዘንድሮ የጊፋታ በዓል በዛሬው ዕለት መስከረም 13 / 2016 ዓ.ም በድምቀት ይከበራል ።

24/09/2023
ያሆዴ ባህላዊና ታሪካዊ የስልጣኔ ማሳያ ነው - አቶ ቀጀላ መርዳሳመስከረም 12፣ 2016 (EP)ያሆዴ ባህላዊና ታሪካዊ የሆነ የሀዲያን ማህበረሰብ ቀደምት ስልጣኔ የሚያሳይ ነው ሲሉ የባህልና ...
23/09/2023

ያሆዴ ባህላዊና ታሪካዊ የስልጣኔ ማሳያ ነው - አቶ ቀጀላ መርዳሳ

መስከረም 12፣ 2016 (EP)ያሆዴ ባህላዊና ታሪካዊ የሆነ የሀዲያን ማህበረሰብ ቀደምት ስልጣኔ የሚያሳይ ነው ሲሉ የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ቀጀላ መርዳሳ ተናገሩ።

የሀዲያ የዘመን መለወጫ የሆነው ያሆዴ በአል የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ቀጀላ መርዳሳ፣የሀዲያ ዞን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ እቴነሽ ሙሉጌታ ፣የዞኑ አመራሮች፣የሃገር ሽማግሌዎች እና ተጋባዥ እንግዶች በተገኙበት በተለያዩ ዝግጅቶች እየተከበረ ነው።

በመርሃ ግብሩ ላይ ንግግር ያደረጉት የባህልና ስፖርት ሚኒስትሩ÷ያሆዴ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ እሴቶችን አቅፎ መያዙን ገልፀው ለበአሉ እድገት እንሰራለን ብለዋል።

ቀጣዩ ዘመንም የፍቅር ፣የደስታ፣ የሰላም፣ እና የብልፅግና እንዲሆን መልካም ምኞታቸውን አስተላልፈዋል።

የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አብርሀም መጫ÷ይህንን ኢትዮጵያዊ እሴት በዩኔስኮ ለማስመዝገብ ጥረቶች መቀጠላቸውን ተናግረው ለዚህም ሁሉም የድርሻውን እንዲወጣ ጥሪ አቅርበዋል።
EP

"ያሆዴ" የሀዲያ የዘመን መለወጫ በዓል በሀዲይ ነፈራ በድምቀት እየተከበረ ነው።ሆሳዕና፡ መስከረም 12/2016 ዓ.ም  "ያሆዴ" የሀዲያ ዘመን መለወጫ በዓል በሀዲይ ነፈራ በተለያዩ ዝግጅቶች ...
23/09/2023

"ያሆዴ" የሀዲያ የዘመን መለወጫ በዓል በሀዲይ ነፈራ በድምቀት እየተከበረ ነው።

ሆሳዕና፡ መስከረም 12/2016 ዓ.ም "ያሆዴ" የሀዲያ ዘመን መለወጫ በዓል በሀዲይ ነፈራ በተለያዩ ዝግጅቶች እየተከበረ ነው።

በአከባበር ስነስርዓቱ የኢሬድሪ ባህልና ስፖርት ሚንስትር አቶ ቀጀላ መርዳሳ የሀዲያ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አብርሃም መጫን ጨምሮ የተለያዩ ከፍተኛ የመንግሥት የስራ ኃላፊዎችን እና በርካታ የብሔሩ ተወላጆችና ወዳጆች በተገኙበት እየተከበረ ይገኛል።

Address


Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethiopian prosperity posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Videos

Shortcuts

  • Address
  • Alerts
  • Videos
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share