24/01/2021
ለሀብሩ ወረዳ አርሶ አደሮች
የባህርዛፍ ተክል እና መዘዙ
የባህር ዛፍ ተክል ለም መሬት ላይ የሚያደርሰው ጉዳት
በአካባቢ ላይ ተፅዕኖ ማሳደሩ ተገለፀ፡፡
አንድ ማሣ በአመቱ እየፈራረቁ ለማምረት የሚሠራው አንድ
ማሣ በባህርዛፍ ተክል ካልተሸፈነ ብቻ ነው:: ታዲያ አርሶ
አደሮች መሬታችን በአጎራባች መሬት በተተከለ ባህርዛፍ
መድረቁ ካልቀረ ተጠግተን የዘራነው ሠብልም ካለማ
በሚል ተፅዕኖ መሬታቸውን ባህርዛፍ ለመትከለ ይገደዳሉ::
በተለይ እርሻ ማረስ የተሣናቸው አርሶ አደሮች መሬታቸውን
ተክለው ይጠቀማሉ፡፡ ወጣቱም ይሄን ተከትሎ ተክሎ ወደ
ከተማ ገብተው ሌላ ስራ እንደሚሠሩ ነው አርሶ አደሮች
የገለፁት:: የባህር ዛፍ ተክል ለም መሬት ላይ በመተከሉ
ምክንያት የምርት መቀነስ ከማስከተሉም ባሻገር በአጎራባች
ሠብሎች ላይ የሚያደርሰው ተፅዕኖ ከፍተኛ ነው:: ለአ/
አደሮች ከኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚታነት አዋጭ የሚባልለት
ባህር ዛፍ አሁን አሁን መሬት አልባ አርሶ አደሮች
እንዲፈጠሩ እያደረገ ይገኛል፡፡
የአማራ ክልል የገጠር መሬት አጠቃቀም በደንብ ቁጥር
159/2010ዓ.ም የመሬት አጠቃቀም አስተግባሪ ግብረ
ሃይል አለ፡፡ ይሄ ግብረ ሀይል አንድ መሬት በጥናት
የሚሠራው ከተለየት በኋላ የፈለጉትን ተክለው ዘርተው
በአካባቢ ላይ ተፅዕኖ እንዳይሳድሩ የሚከለክል እና
አስተዳደራዊ እርምጃ የሚወስድ ሃይል ነው፡፡
የገጠር መሬት አስተዳደርናና አጠቃቀም ዳይሬክተር አቶ
ታምራት ደምሴ እንደገለፁት አንድ መሬት ሠብል የሚዘራው
ወይም ተክል የሚተከለው የመሬት አጠቃቀም ጥናት
የግጦሽ መሬት፣የደን መሬት፣ አመታዊ ሠብልና ለጥብቅ
ስራ የምንከልለው ቦታዎች አሉ፡፡ እነዚህ የራሳቸው የሆነ
የመሬት መገምገሚያ ስልት አላቸው፡፡ የመሬት አጠቃቀም
ባለሙያ በነዚህ መመዘኛ ነጥቦች ተመዝኖ ያለቀለት መሬት
ከሆነ መትከል አይችልም ምክንያቱም መጀመሪያውኑ
ለመሬቱ የተስማማው ለአመታዊ ሠብል ከሆነ ለዚሁ
ለአመታዊ ሠብል መጠቀም አለባቸው፡፡ አንድ አካባቢ ያሉ
ቀጠናዎች ላይ መሬቶች አንድ አይነት የመሬት አጠቃቀም
ይኖራቸዋል ተብሎ ስለሚታሠብ ሊቀይር አይችልም፡፡
በጉልበት የሚተከል ወይም የሚቀይር ካለ የወረዳ የመሬት
አስተዳርና አጠቃቀም በተስማሚ ደረጃው መስራት
አለመስራቱን ይከታተላል ይቆጣጠራል አስተዳደራዊ
እርምጃ ይወስዳል፡፡
አርሶ አደር የሚተክለው ወይም የሚሠራው በጥናት
ከተረጋገጠለት ተክል ወይም ሠብል ውጭ ማሣውን በሌላ
ሸፍኖ ቢገኝ እና የመሬት አጠቃቀም አቅድ ተዘጋጂቶ ርክክብ
የተደረገ ከሆነ የቀበሌው የመሬት አጠቃቀም አስተግባሪ
ግብር ሃይል በመመሪያ ቁጥር 2/2010ዓ.ም የመሬት
አጠቃቀም እቅዱን ያላግባብ በመቀየር ሲጠቀም የተገኘ
ማንኛዉም የመሬት ባለይዞታ ወይም ተጠቃሚ
በሚመለከተዉ አካል ተዘጋጂቶ በተሰጠዉ የአጠቃቀም
እቅድ መሰረት ቀይሮ እንዲጠቀም የመጀመሪያ የፁሁፍ
ማስጠንቀቂያ በቀበሌዉ መሬት አስተዳዳር እና አጠቃቀም
ግብረ ሀይል ይሰጠዋል፡፡ በዚህ ማስጠንቀቂያ የማይማለስ
ከሆነ በቀበሌዉ የመሬት አስተዳዳር እና አጠቃቀም ግብረ
ሀይል አማካኝነት በህግ አግባብ ታቅዶ ወደነበረዉ የመሬት
አጠቃቀም አይነት እንዲመለስ ወይም እንዲስተካከል
ያደርጋል፡፡
አርሶ አደሩ በዚህ ልክ የማይማርና የማያሻሻል ከሆነ
አዋጃችን እና ደንባችን እስከ መጨረሻው መሬትን
እስከመነጠቅ የሚያደርስ ስለሆነ መረጃውን አደራጅቶ
ለፍትህ በመስጠት ክስ እንዲመሠረት እና ወደ ፍትሃዊ
እርምጃ እንዲወሰድ ይደረጋል፡፡
መረጃው የተወሰደው ከአብክመ ገጠር መሬት አጠቃቀም
ዳይሬክቶሬት ነው