FENTA AREAL TUBE

  • Home
  • FENTA AREAL TUBE

FENTA AREAL TUBE Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from FENTA AREAL TUBE, News & Media Website, .

የአውሮጳ ሕብረት አዲስ አበባ ከሚገኙ ልዑካኑ ብዙም የማያስፈልጉ ያላቸው ሠራተኞቹ እንዲወጡ ትዕዛዝ አስተላለፈ። የሕብረቱ ቃል አቀባይ ናቢላ ማስራሊ ዛሬ ከብራስልስ ባስተላለፉት መልእክት ከአ...
02/12/2021

የአውሮጳ ሕብረት አዲስ አበባ ከሚገኙ ልዑካኑ ብዙም የማያስፈልጉ ያላቸው ሠራተኞቹ እንዲወጡ ትዕዛዝ አስተላለፈ። የሕብረቱ ቃል አቀባይ ናቢላ ማስራሊ ዛሬ ከብራስልስ ባስተላለፉት መልእክት ከአባል ሃገራት በተሰጠው መመሪያ መሠረት እና ከዚህም ጋር በመተባበር ብዙም የማያስፈልጉ ያሏቸው ባልደረቦች እና ከእነሱ ጋር የሚኖሩ ሀገሪቱን ለቀቅቀው እንዲወጡ እንጠይቃለን ማለታቸውን አዣንስ ፍራንስ ፕረስ ዘግቧል። አክለውም ቃል አቀባይዋ ለአውሮጳ ሕብረት እና የሀገሪቱ ዜጎች ለሆኑ ሠራተኞች ደግሞ የጸጥታ ርምጃዎችን አጠናክረናል ማለታቸውም ተጠቅሷል። በርካታ የአውሮጳ ሃገራት ዜጎቻቸው ከኢትዮጵያ እንዲወጡ የጠየቁ ሲሆን የሕብረቱ ቃል አቀባይ ዜጎቹ የየመንግሥታቸውን ምክር እንዲያስተውሉም አሳስበዋል። በአንጻሩ የኢትዮጵያ መንግሥት የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዛሬ በሰጠው መግለጫ በሀገሪቱ የጸጥታ ጉዳይ ስጋት አለመሆኑን አመልክቷል። የጸጥታውን አስተማማኝነት ለማረጋገጥም በመጪው የገና በዓል 1 ሚሊየን በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያ እንዲሁም የኢትዮጵያ ወዳጆች ወደ ሀገር ቤት እንዲገቡ ጥሪ ቀርቧል።

Address


Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when FENTA AREAL TUBE posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

  • Address
  • Alerts
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share