Gazetegaw Media

  • Home
  • Gazetegaw Media

Gazetegaw Media Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Gazetegaw Media, Media/News Company, .

30/12/2022

አንድ ያልገባን ነገር በሌላው ላይ ሸፍጥ እየያዙ ፍቅር ፍቅር መጫዎት ለማንም እንደማይጠቅም ነው።የአንደኛው ህመም ሌላኛውን ማቁሰሉ አይቀርም።የጊዜ ጉዳይ ብቻ ነው።ኦሮማራ የሚባል ፌዘኛ ጥምረት ለምን አፈር በላ? የሆነን አካል በመጥላት ላይ የተመሠረተ ስለነበር።በኢሳያስና በዶር በአብይ መካከል የነበረው ያ ሁሉ ፍቅር ለምን ደበዘዘ? ህወሃትን በመጥላት እንጂ ለዘላቂ ሰላም በመርህ ላይ የተመሠረተ ግንኙነት ስላልነበረ።አሁንም በህወሓትና በብልፅግና መካከል ያለው ሸፍጠኛና የተሽፈነፈነ አካሄድና ፍቅር የትም የማያደርስ የኢትዮጵያን ህዝብ ደጋግሞ የማጃጃል ድራማ እንዳይሆን መጠንቀቅ ያሻል።የሰሞኑ የአማራ ሸኔ ፅንፈኛው ፋኖ የሚሉ ትርክምርኪ ፍረጃዎች ይህን የሆነ ጠላት ፈጥሮ የመፋቀር አጉል ልማድ ማሳያ ከመሆን ያለፈ ትርጉም የለውም።ህወሃት ከኦነግ ሸኔ ጋር አብሮ ሲሰራ ነበር።ህወሃት ጋር ፍቅር በፍቅር እየሆነ ከኦነግ ጋር አልታረቅም የሚል ግብዝነት አይገባኝም።ጭራሽ ሌላ የትርምስ አጀንዳ አማራ ሸኔ እያሉ መፍጠር ምንድን ነው? በየተራ አታስጨፍጭፉን በየተራ አትግዴሉን።አሁን ሀቀኛና ሁሉንም ያካተተ ድርድር ነው የሚያስፈልገን።ድራማ ሰለቸን እኮ? ከህወሓት ጋር ተደራደሩ ስንል ጁንታ እያላችሁ ስትሰድቡን ነበር።አሁን ደግሞ ተገልብጣችሁ በፍቅራችን ጣልቃ አትግቡ እኛ ተዋደን ስንደንስ ለምንረግጠው ሰው ድምፅ ከሆናችሁ ወይ አማራ ሸኔ አሊያም ኦነግ ሸኔ ብለን እናሸማቅቃለን እያላችሁ ነው።እደግመዋለሁ የኢትዮጵያ ችግር በጦርነትና በሸፍጥ መቼም አይፈታም።አሁን ከአማራና ከኦሮሞ ሀይሎች ጋር ያለውን ችግር በድርድር መፍታት ካልተቻለ ከብዙ እልቂት በኋላ ከእነዚህም ጋር ድርድር መደረጉ አይቀርም።ከዚያ ደግሞ ሁለተኛው ዙር የትግራይ ጦርነት ይቀጥላል።ከኤርትራ ጋርም ጦርነት መኖሩ አይቀርም።የሚሻለው በታማኝነት ሁሉንም ያካተተ ድርድር ብቻ ነው።

23/07/2022

Address


Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Gazetegaw Media posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

  • Address
  • Alerts
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share