VoE News - አማሪኛ

  • Home
  • VoE News - አማሪኛ

VoE News - አማሪኛ የVoE News - አማሪኛ (የትዮጵያ ድምፅ አማርኛ ) "ለኢትዮጵያ ፤ ለኢ?

በሁሉም መስክ የተግባር ሰዉ በመሆን፣ በጀግንነት በመቆምና መስዋዕትነት በመክፈል  ዉዷ ሀገራችን ኢትዮጵያን እናጸናለን! የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ፕረዝዳንት ክቡር አቶ ሽመልስ አብዲ...
23/11/2021

በሁሉም መስክ የተግባር ሰዉ በመሆን፣ በጀግንነት በመቆምና መስዋዕትነት በመክፈል ዉዷ ሀገራችን ኢትዮጵያን እናጸናለን!

የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ፕረዝዳንት ክቡር አቶ ሽመልስ አብዲሳ

የኦሮሞ ህዝብ ትላንት እንደ ህዝብ የተወጋውን ውግ፣ የወጋውን ጠላትም ሆነ የተወጋበትን ጦር ይረሳ ዘንድ በፍጹም አይችልም፡፡ የተፈጸመብንን ግፍ፣ የተጎነጨነውን መራራ የመከራ ጽዋ፣ ተጭነው የገፉንን የግፍ እጆች፣ አንገታችንን ቆልምመው በሀፍረት ያስጎነበሱንን የወራሪዉ እና የአሸባሪዉን ትህነግ የባርነት መዳፎች፣ ከሰውነት ተርታ አውርደው ትቢያ ላይ የረገጡንን ጨካኝ እግሮቹን መቼም አንረሳቸውም፡፡

ገዳዮቻችን መግደላቸውን ቢዘነጉ ወይም ቢያዘናጉ እንኳ እኛ ግን ሞት እና አንባው- ዋይታው - ሰቀቀን እና እሪታው- ሀዘን እና መጎሳቆሉ መናቅ እና መበደሉ ከልባችን አለና አንዘነጋውም፡፡ ረስተን ሳይሆን ትተን፣ ለበቀል ሳይሆን ለይቅርታ ጀግነን ህዝብ እና ሀገርን ብለን የተውነው ጠላታችን ለሌላ ሞት፣ ለሌላ እንግልት፣ ለሌላ ስደት፣ ለሌላ ባርነት ሊያጨን ደም እና እውነት አላስቀምጥ ብለውት ከህጻን እስከ ሽማግሌ በማዝመት ለሁለተኛ ዙር ባርነት ቀንበር ሊጭንብን መደንፋት ከጀመረ ውሎ አድሯል፡፡

በመሆኑም ውጭ ካሉ ጌቶቹ እና እኛው ውስጥ ከተሰገሰጉ አሽከሮቹ ጋር ሀገር የማፍረስ ሰፊ ሴራ አሲረው በሰው ልጆች - ያውም በገዛ ወገን ላይ ይፈጸማል ተብሎ የማይታሰብ ዘግናኝ ጭፍጨፋ እና እልቂት በንጹሀን ላይ እያደረሱ ለዳግም መከራ ሊያጩን መፍጨርጨራቸዉን ቀጥለዋል፡፡

ይህንኑ አደገኛ አካሄዳቸውን ተከትሎም ሰው በላውን ጁንታም ሆነ አሽከሩ ሸኔን አይቀጡ ቅጣት ለመቅጣት እና ከኢትዮጵያ ህዝብ ትከሻ ላይ ለአንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ ነቅሎ ግብአተ መሬቱን ለማጠናቀቅ ክቡር ጠቅላይ ሚንስትራችን ራሳቸው ግንባር በመዝመት ጦሩን ለመምራት እና በአጭር ጊዜ ውስጥ የታላቋን ኢትዮጵያ ታላቅ ድል ለመላ ኢትዮጵያውያን ለማብሰር የወሰኑትን ቆራጥ ውሳኔ እና ያስተላለፉትን ታሪካዊ ሀገራዊ ጥሪ የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት እና መላው የኦሮሞ ህዝብ በፍጹም አድናቆት፣ ፍቅር፣ ክብር እና ተነሳሽነት ተቀብለውታል፡፡

የኦሮሚያ ክልል አመራሮችም የመሪያችንን ወቅታዊ እና ሀገራዊ ጥሪ በፍጹም ልበ ሙሉነት ተቀብለን፤ እኛም እንደ አባቶቻችን ሁሉ በክብር በደም እና በአጥንታችን መስዋዕትነት ከፍለን የተከበረች ሀገር ለልጆቻችን ለማቆየት እንዲሁም በልማት እና በአስተዳደር ስራ መስክም የላቀ ዉጤት በማስመዝገብ ሀገራችንን ከተጋረጠባት ፈተና ለመታደግ ዝግጁ መሆናችንን በቆራጥነት እናረጋግጣለን፡፡

የክልላችን ህዝብም የልጁን- የመሪውን እና ሀገር እና ህዝቡን ለመታደግ ጦር ሜዳ የወረደውን የዶክተር አቢይ አህመድ አሊን ጥሪ ተቀብሎ ሁሉም ከያለበት ነቅሎ በመውጣት የጠላቶቻችንን፤ የሸኔን እና የአሸባሪዉ የትህነግን ቀብር በመፈጸም ሀገራዊ ነቀርሳነታቸዉ ለአንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ እንዲያከትም እንዲያደርግ ጥሪዬን በአክብሮት አስተላልፋለሁ፡፡
ትላንት ባዶ እጃቸውን ታንክ፣ መድፍ እና መትረየስ ፊት ቆመው ወያኔን ወደወጣበት ዋሻ የመለሱት ቄሮ እና ቀሬዎቻችን ዛሬም እንደገና ላስገብራቹ- እንደገና ልግዛቹ- እንደገና ልዝረፋቹ ብሎ የመጣውን ይህንን እብሪተኛ ሀይል ከምድረ ገጽ ለማጥፋት የጠቅላይ ሚንስትራችንን ጥሪ ተቀብለው ነቅለዉ በመዉጣት ጀግናዉ የመከላከያ ሰራዊታችንን በመቀላቀል እና በጦር ሜዳ ጀብዱ የነ አብዲሳ አጋ፣ ባልቻ ሰፎ፣ ገረሱ ዱኪ፣ የጃጋማ ኬሎ ልጆች እንደሆኑ ዳግም እንዲያስመሰክሩ ታሪካዊ ጥሪዬን አቀርባለሁ፡፡

የተጋረጠብንን የህልውና አደጋ የመመከቱ ታሪካዊ ሀላፊነት እንዳለ ሆኖ በገባንበት ጦርነት ሳቢያ ሀገራችን ወደማንቆጣጠረው የከፋ የኢኮኖሚ ችግር እንዳትገባ ደጀን ህዝባችን ከሌላዉ ጊዜ በተለየ መልኩ በልማት ስራና በየተሰማራበት መስክ ሁሉ ውጤታማ ስራዎችን በመስራት፣ የአከባቢዉን ሰላምና ደህንነት በማረጋገጥ የዚህ ታሪካዊ ምእራፍ አሻራ ባለቤት እንዲሆን አደራ እላለሁ፡፡

በመጨረሻም ሁሉም ህዝብ በየእምነቱ እና አምልኮቱ ጥላ ስር ሆኖ በዱኣ እና በጸሎት ሀገሩን እንዲያግዝ ጥሪዬን አቀርባለሁ!

ምንም ጥርጥር የለውም እግዚአብሄር ይረዳናል፡፡ ኢትዮጵያ እንደለመደችው በአጭር ጊዜ አሸንፋ በጠላቶቿ መቃብር ላይ ክቡር ሰንደቋን ትሰቅላለች፡፡

"ቀላል ይሆናል" ቴዲ አፍሮ ዳገቱ ላይ አትዛል ጉልበቴ የተራራው ጫፍ ፍቅር ናት ርስቴቀላል ይሆናል ቀና አርገኝ ፅናቴደመና ሲያይ መስሎት የጨለመአለ ቂል ሰው ሁሉም አከተመደቂቅ ተስፋን ካየና...
10/11/2021

"ቀላል ይሆናል" ቴዲ አፍሮ

ዳገቱ ላይ አትዛል ጉልበቴ
የተራራው ጫፍ ፍቅር ናት ርስቴ
ቀላል ይሆናል ቀና አርገኝ ፅናቴ
ደመና ሲያይ መስሎት የጨለመ
አለ ቂል ሰው ሁሉም አከተመ
ደቂቅ ተስፋን ካየናት አርቀን
ነገ ሌላ ይሆናል ጡሩ ቀን....

ኢትዮጵያ ታሸንፋለች!
Ethiopia Prevails!

Address


Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when VoE News - አማሪኛ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

  • Address
  • Alerts
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share