ወሎ ሱና ቲዩብ

  • Home
  • ወሎ ሱና ቲዩብ

ወሎ ሱና ቲዩብ #ደዓዋ እና

✔️  በሰፈሩት ቁና… …!!!!!الجزاء من جنس العمل!!!!!!!➡️ የዛሬዋ በሩሲያ  ምሳኤሎች እንዳልነበረ እየሆነች  ያለችው ዩክሬን አሜሪካ እና ምዕራባውያን በጥምረት ኢራቅን ሲደ...
26/02/2022

✔️ በሰፈሩት ቁና… …!!!!!
الجزاء من جنس العمل!!!!!!!
➡️ የዛሬዋ በሩሲያ ምሳኤሎች እንዳልነበረ እየሆነች ያለችው ዩክሬን አሜሪካ እና ምዕራባውያን በጥምረት ኢራቅን ሲደበድቡ ከአሜሪካ ጋር አብረው ኢራቅን ከደበደቡ ግፈኛ ሀገራት መካከል አንዷ ነበረች ዛሬ ግን ያኔ ዩክሬን ኢራቅን ለማፍረስ አብራቸው የዘመተችላቸው እነ አሜሪካና የምዕራቡ ሀገራት ዩክሬን በሩሲያ ሚሳኤሎች ስትማገድ ዳር ቆመው እንደ ፊልሙ እያዩ ይገኛሉ !!!!!!!!!!!።
እጇ በንፁሐን ፍልስጤማውያን ደም የተጨማለቀው ወራሪዋ እስራኢል የእጇን የምታገኘው ሩቅ አይሆንም!!!!!!!!
👌ወገን ንቃ!!!!!!!
የካቲት 19/06/2014 ዓ ል
✍ ካቲብ
abu hisham

ሞሮኮ ውስጥ ጥልቅ ጉድጓድ ውስጥ የገባውን ህፃን ራያንን ለማዳን የሚደረገውን ርብርብ ዓለም በቀጥታ እየተከታተለው ይገኛል።የሰው ልጅ ህይዎት ከዚህም በላይ ከፍተኛ ክብር ይገባዋል። ዓለማችን ...
05/02/2022

ሞሮኮ ውስጥ ጥልቅ ጉድጓድ ውስጥ የገባውን ህፃን ራያንን ለማዳን የሚደረገውን ርብርብ ዓለም በቀጥታ እየተከታተለው ይገኛል።
የሰው ልጅ ህይዎት ከዚህም በላይ ከፍተኛ ክብር ይገባዋል። ዓለማችን ላይ የሰው ልጅ ህይዎት በረከሰበት ዘመን ለሰው ልጅ ህይዎት ክብር የሚሰጥ ክስተትን መመልከት ተስፋ ያጭራል።
አላህ(ሱ.ወ.) ህፃን ረያንን ለእናቱ እቅፍ ያበቃው ዘንድ እንለምነዋለን።

ይህ ምስል በሶሪያ መጠለያ ካንፕ ውስጥ ነውየዚህ ቤተሰብ አባላት በሙሉ ማለትም አባት :ትናንሽ ልጆቹ በብርድ ምክንያት በዱካኑ ውስጥ ሙተው ተገኙ .... ይህ ክስተት ልብ ይሰብራል......💔...
25/01/2022

ይህ ምስል በሶሪያ መጠለያ ካንፕ ውስጥ ነው
የዚህ ቤተሰብ አባላት በሙሉ ማለትም አባት :ትናንሽ ልጆቹ በብርድ ምክንያት በዱካኑ ውስጥ ሙተው ተገኙ ....
ይህ ክስተት ልብ ይሰብራል......💔
አላህ ይማራቸው ያረብ
ﺣﺴﺒﻨﺎ ﺍﻟﻠﻪ ﻭﻧﻌﻢ ﺍﻟﻮﻛﻴﻞ
ﻭﻻ ﺣﻮﻝ ﻭﻻ ﻗﻮﺓ ﺇﻻ ﺑﺎﻟﻠﻪ

ሱብሀነክ ያረብ እንድህም ወጥቶ መቅረት አለ  የኔስ መጨረሻ እንደት ይሆን ይሆን?  ዛሬ እንሙት ነገ ለማናቀው የአዱኒያ ህይወት ብዙ እናስባለን ብዙ እንጨነቃለን  ውለን እንገባለን ብለው ያሰ...
24/01/2022

ሱብሀነክ ያረብ
እንድህም ወጥቶ መቅረት አለ የኔስ መጨረሻ እንደት ይሆን ይሆን? ዛሬ እንሙት ነገ ለማናቀው የአዱኒያ ህይወት ብዙ እናስባለን ብዙ እንጨነቃለን ውለን እንገባለን ብለው ያሰቡት ደግሞ ባንድቀን ከ50 ሰው 47 ሰው ህይወቱን አጥቶ እያየን ነው ።መቸ ይሆን እርስበርስ ተዋደን ይቅር ተባብለን ከወንጀላችን ተመልሰን ከአላህ ጋር የምንገናኘው?
እጅግ አሰዛኝ አደጋ፦
በመኪና አደጋ 47 ሰዎች ይወታቸው አለፉ።
ትላንት ጥር 15/2014 ከባህር ዳር እና እብናት ከ50 ሠዉ በላይ አሣፍሮ ወደ ሠቆጣ ይጓዝ የነበረ የህዝብ ማመላሻ ምሽት ላይ 150 ሜትር በላይ ገደል በመግባቱ ከ50 ሰዎች ውስጥ 47ቱ ህይወታቸው አልፏል።
አንዲት ተሣፋሪ ወደ ሠቆጣ ለመሄድ ሂሣብ ከፍላ እቃዋን ጭና ፤ ጥሏት ሥለሄደ ህይወቷ ሲተርፍ ፥ሌላኛዉ ለትራንስፖርቱ 50ብር ጎድሎት ወርዶ በመቅረቱ ህይወቱን ሊተርፍ ችሏል።

የሙስሊም ወጣቶች ድምፅ በደሴ

አልሀምዱሊላህ♥ ሸይኽ አብዱልለጢፍ ተፈተዋል‼
24/01/2022

አልሀምዱሊላህ♥ ሸይኽ አብዱልለጢፍ ተፈተዋል‼

ይህ በምስሉ ላይ ፊቱ በጥቁር የተሸፈነው የታሊባን የአገር ውስጥ ሚኒስቴር ሲሆን ሲራጁዲን ሐቀኒ ይባላል። ሚዲያ ላይ ሲቀርብ ፊቱ እንዲታይ አይፈቅድም። አሜሪካ እሱን ለገደለ 5ሚሊዮን በጅታ ...
24/01/2022

ይህ በምስሉ ላይ ፊቱ በጥቁር የተሸፈነው የታሊባን የአገር ውስጥ ሚኒስቴር ሲሆን ሲራጁዲን ሐቀኒ ይባላል። ሚዲያ ላይ ሲቀርብ ፊቱ እንዲታይ አይፈቅድም። አሜሪካ እሱን ለገደለ 5ሚሊዮን በጅታ ነበረ። እንዲሁ ሌሎች የታሊባን ሚኒስትሮችም ፊታቸውን ማሳየት አይፈቅዱም።
እውቅና ሳይፈልጉ ከሰው ደበቅ ብሎ መስራት የተረሳ ሱንና ሲሆን ምናልባት እነዚህ ሰዎች እንደገና ያንሰራሩት ይሆናል። ቢኢዝኒላህ።

ዓለም አቀፍ የድጋፋ ጥሪ ከሃሩን ሚዲያ ድጋፍ አስተባባሪ."ሃሩን ሚድያ የሁላችንም ድምፅ" በሚል መሪ ቃል ዛሬ ቅዳሜ ጥር 14 በኢትዮጵያ ሰአት አቆጣጠር ከምሽቱ 2 ሰአት ጀምሮ በሃሩን ሚድያ...
23/01/2022

ዓለም አቀፍ የድጋፋ ጥሪ ከሃሩን ሚዲያ ድጋፍ አስተባባሪ.
"ሃሩን ሚድያ የሁላችንም ድምፅ" በሚል መሪ ቃል ዛሬ ቅዳሜ ጥር 14 በኢትዮጵያ ሰአት አቆጣጠር ከምሽቱ 2 ሰአት ጀምሮ በሃሩን ሚድያ እና ሌሎችም አጋር ሚድያዎች፤ የፌስ ቡክ እና You Tube ቻናሎች የቀጥታ ስርጭት አለም አቀፍ የድጋፍ ፕሮግራም ይካሄዳል::..
በመሆኑም ሃሩን ሚድያን በመደገፍ እና በማሳደግ ግልጋሎቱን ለማጠናከር የጠየቃችሁን በመላው አለም የምትገኙ ሁሉ ዛሬ ምሽት በኢትዮጵያ ሰአት አቆጣጠር ምሽት 2 ጀምሮ በአሏህ ﷻ ፍቃድ ይጠብቁን!.
ሃሩንን ሚዲያን በማጠናከር ወርሃዊ አባል በመሆን ከጎኑ እንቁም
© የድጋፋ አስተባባሪ ኮሚቴው.
በቀጥታ በባንክ ድጋፍ ለማድረግ፦
1000353425173 - ንግድ ባንክ
የአካውንቱ ስም ፦
Harun multimedia production..
ይህ የሀሩን ሚዲያ ዌብሳይት ሲሆን በዚህ ገብታችሁ ወርሃዊ membership ሁኑ ! በአንድ ጊዜ ከምትረዱት ባሻገር በየወሩ ሜንበርሺፕ ሁኑ https://www.harunmedia.org/.
ኒያችሁን ለማስቀመጥ ከስር ያለውን ፎርም መሙላት ትችላላችሁ
https://docs.google.com/.../1FAIpQLSc5J9p.../viewform....
የሀሩን ሚዲያ ቁጥር +1 (202) 931-8685.
የነገው ዝግጅት የዙም ሊንክ .
Meeting ID: 613 669 3090
Passcode: 9999
Find your local number: https://us02web.zoom.us/u/kVvC0x31t

23/01/2022

#ወሎ በጀግንነት እንጂ በክህደት፣በባንዳነት የሚታወቅ ማህበረሰብ አይደለም!!"♥🙏
(ኡስታዝ አቡበክር አህመድ)

የከሚሴው ሸይህ አብዱለጢፍ ጉዳይ*************************************ሸሆቻችን መንታሎች ናቸው..ለአላህ ብለው ይባክናሉ..በዚህም ሁኔታ ሰው ናቸውና  ደግም ክፉም ያገኛቸ...
23/01/2022

የከሚሴው ሸይህ አብዱለጢፍ ጉዳይ
*************************************
ሸሆቻችን መንታሎች ናቸው..ለአላህ ብለው ይባክናሉ..በዚህም ሁኔታ ሰው ናቸውና ደግም ክፉም ያገኛቸዋል ። ዋናው ምክንያት ደሞ የኛው የተከታዩ ውስብስብነት, የምንሰጣቸው ግራ የሚያጋቡ መረጃዎች እና የነገሮች ፍጥነት እና ጉራማይሌነት ብቻ ናቸው። በዚህ ሁኔታ ላይ እያሉ ታዲያ ጉዳት ይቀንሳል ብለው ባያምኑበትም ለማባባል ፈተናንም ለማቅለል የመሀልም ይሁን የዳር የመሰለን ሀሳብን በማቅረብ ለማስታረቅ ሲጥሩ ይታያሉ። አላማቸው ለኡማው ኸይር በመሻት እንጅ በዙልም በፍጹም አይጠረጠሩም። ችግሩ አንዱ ወገን ሲያሸንፍ የሌላው ደጋፊ አድርጎ በመሳል ኡለማዎችን ሲያሰቃያቸው ይታያል። ነገሩን ላስተዋለ ግን ስብሀት ነጋ ቤቱ ቁጭ ብሎ ሰላጣ እየበላ ሸይህ አብዱለጢፍ በእስር የሚማቅቁበት ምንም አመክንዩ የለም። እናም ሸይኹን ፍቷቸው። ያሳለፉት ውጣውረድና ልምድ ለኖሩለት ህዝብ ግንባታ ወሳኝ እሴት ነውና!!!
KH abate

  ከታች የፋኖን ልብስ ለብሶ የተቀመጠው ወጣት በትናትናው እለት የአረብ ገንዳን መስጅድን በጥይት የደበደበው ግለሰብ ነው።ስሙ አቡሽ ሲሆን አብዝሀኛው የደሴ ከተማ ህዝብ የሚያውቀው ደሴ ፒያሳ...
20/01/2022


ከታች የፋኖን ልብስ ለብሶ የተቀመጠው ወጣት በትናትናው እለት የአረብ ገንዳን መስጅድን በጥይት የደበደበው ግለሰብ ነው።
ስሙ አቡሽ ሲሆን አብዝሀኛው የደሴ ከተማ ህዝብ የሚያውቀው ደሴ ፒያሳ አካባቢ ኪያ ተብሎ በሚጠራው ካፌ ውስጥ ሲሰራ ነው።
ግለሰቡ ርካሽ ተግባር በመፈፀም የሀይማኖት ግጭትን ለማነሳሳት ያደረገው ጥረት ከሽፏል።
ከትናት ማታ ጀምሮ ዛሬም ጭምር ከክርስትና የእምነት ተቋማት ከከተማ አስተዳደሩና ከሚመለከተው የፀጥታ ሀይል ጋር ውይይት እየተደረገ ነው።
የክርስትና እምነት የሀይማኖት አባቶችም በዛሬው እለት አረብ ገንዳ መስጅድ ድረስ መተው የደረሰውን ጉዳት አይተዋል።
©ሙስተፋ አብደላህ

20/01/2022

#እስልምና ላይ የሚደርሰውን ግፍ እና ትንኮሳ ለማዉገዝ እና ለመከላከል ክልል አያግደኝም ፣ሀገር አያግደኝም ፣አህጉር አያግደኝም ምክንያቱም ነዉና»

20/01/2022
ይድረስ ለሚመለከተው ሁሉ============✍ ''ወሎና አፋር መስጂድ ሲቃጠል ዝም ብላችሁ እኛ ስናቃጥል ነወይ የምትጮሁት? ወሎና አፋር ሙስሊም ሲገደል ዝም ብላችሁ እኛ ስንገድል ነወይ የምት...
20/01/2022

ይድረስ ለሚመለከተው ሁሉ
============
✍ ''ወሎና አፋር መስጂድ ሲቃጠል ዝም ብላችሁ እኛ ስናቃጥል ነወይ የምትጮሁት? ወሎና አፋር ሙስሊም ሲገደል ዝም ብላችሁ እኛ ስንገድል ነወይ የምትጮሁት?" የሚሉ ማፈሪያዎችን እያየን ነው። እየውልህ አብጤ! ስለተወለድኩበት፣ ስለወጣሁበት ወሎ ቀርቶ ስለ ጎጃምና ጎንደር ሙስሊም ለመፃፍ ያንተ ፈቃድ አያስፈልገኝም። ምን መፃፍ እንዳለብኝና መቼ መፃፍ እንዳለብኝ ያንተን ትእዛዝ የምጠብቅ ሞኝ አይደለሁም። ኦሮሚያ ውስጥ በፅንፈኛ ቁማርተኞች ሙስሊሞች ላይ ጥቃት ሲደርስ ዝም ከተባለ እኛም ዘንድ ሲደርስ ምንም ሊባል አይገባም የሚለው ብሸቅ ሎጂክህ ምን ያክል በአስተሳሰብ መቀንጨር የተጠቃህ እንደሆንክ የሚያሳይ ነው። አማራ ክልል ውስጥ የሚገኙ ሙስሊሞች ላይ የሚደርሰውን የሚያወግዙ ሁሉ ኦሮሚያ ውስጥ ሙስሊሞች ላይ የሚደርሰውን ዝም ያሉት ናቸው ማለትህ የድንቁርናህ መጀመሪያ ነው። አንተ የምታወቀው ጅምላ ፍረጃ ነው። ሁሉ እንዳንተ በዘር የሚያስብ ይመስልሃል። ለኔ ያንተ አማራነት ከኦሮሞነትም ይሁን ከሌላው ብሄር ስሙኒ ታክል ክፍም ዝቅም ያለ ዋጋ የለውም፡፡ ይሄ በዘር የተለወሰ you too fallacyህን ቀቅለህ ብላው። ቢገባህ ለአማራ ሙስሊም ጠብ የሚያደርገው ነገር የለም። የእውነት ለሙስሊም የምትቆርቆር ከሆንክ የወለጋውንም የወሎውንም፣ የኦሮሞውንም የአማራውንም አውግዝ። ያለበለዚያ አንተ እንደምታደርገው ሌላውም ይሞግትሃልኮ። ያንተን ያክል ማሰብ የሚያቅተን ይመስልሃል? "አማራ ውስጥ ያለውን አንተ ነጥለህ እየሸፈንክ፤ ወለጋ ስላለው ምን የምታወራበት ሞራል አለህ?" ማለት የሚሳነን ይመስልሃል? ግና ያንተን ሰንካላ ሂሳብ አንጠቀምም። ያኔ አውግዘሃል አላወገዝክም? የሚል የጅል ሂሳብ አንሰራም። አማራ ውስጥ የሚደርሰውን ያወገዘም ያላወገዘም የወለጋውን ማወገዝ ይችላል። ወለጋ የሚደርሰውን ያወገዘም ያላወገዘም የአማራውን ማወገዝ ይችላል። ቆሜ ሂሳብ እሰራለሁ የሚል አካል በሞኝነቱ የሚኮፈስ ህሊና ቢስ ፍጡር ነው።
በተረፈ የዘርህ ጉዳይ ይህን ያክል ከእምነትህ በላይ የሚያሳስብህ ከሆነ አጀንዳው እንዲነሳ ሰበብ እየሆኑ ያሉ ዋልጌዎችን እጃቸውን እንዲሰበስቡ ጣር። ከዚያ ውጭ ደሴ ሆኖ ስለ መስቀል አደባባይ የሚጮህ አካል ጋምቤላ ሆኜ ስለ ወሎ እንዳልጮህ ሊያግደኝ ቢጋጋጥ "ሞኝህን ፈልግ" ነው የምለው። ለጥቂት በዘር ብቅል ለሰከሩ አሽቃባጮች ብለን ተቋሞቻችን ላይ፣ ሰፊው ሙስሊም ላይ የሚደርሰውን እያየን ዝም አንልም። በጥቂት የዞረባቸው ወላዋዮች ሰበብም በድፍን ህዝብ ላይ የምንፈርድና የምንፈርጅ አይደለንም።
©: ኢብኑ ሙነወር

"ሰበር ዜና!!! ተክቢር!!!"🌹🥀🌹🌷🥀🌷🌼🌹🌸🌺🌾💐🌷🌹🥀🌾 የጀግናው ኡስታዛችንና የታሪክ ምሁራችን የአህመዲን ጀበል የታሪክ መፅሐፍ በአረብኛ ቋንቋ ተተርጉሞ በቀጠር ኳታር በታላቅ ስነስርአት ተ...
20/01/2022

"ሰበር ዜና!!! ተክቢር!!!"
🌹🥀🌹🌷🥀🌷🌼🌹🌸🌺🌾💐🌷🌹🥀🌾
የጀግናው ኡስታዛችንና የታሪክ ምሁራችን የአህመዲን ጀበል የታሪክ መፅሐፍ በአረብኛ ቋንቋ ተተርጉሞ በቀጠር ኳታር በታላቅ ስነስርአት ተመረቀ አላሁ አክበር!!!
የመጀመሪያዋ የሒጅራ ሀገር ሐበሻ ሙስሊሞች ታሪክ ዳግም ከፍ ብሎ በመላው አረብ ዓለም በሚሊዮኖች ይነበባል ማሻ ዓላህ!!!

abu wildan

20/01/2022
11 የነቢዩ (ዐሰወ) ድንቅ ባህርያት♦ ሰውን በጎሪጥ ወይም በጎን አያዩም። ማየት ከፈለጉ ሙሉበሙሉ ዞረው ያዩታል።♦ ሰዎችን በዓይን ጥቅሻ አያናግሩም። መናገር የፈለጉትን በቀጥታ ይናገራሉ።♦...
20/01/2022

11 የነቢዩ (ዐሰወ) ድንቅ ባህርያት
♦ ሰውን በጎሪጥ ወይም በጎን አያዩም። ማየት ከፈለጉ ሙሉበሙሉ ዞረው ያዩታል።
♦ ሰዎችን በዓይን ጥቅሻ አያናግሩም። መናገር የፈለጉትን በቀጥታ ይናገራሉ።
♦ ምግብ ላይ አስተያየት አይሰጡም። የቀረበላቸውን ይበላሉ ካልሆነ ትተውት ይነሳሉ።
♦ አንድን ሰው በጥፋቱ አያሳንሱትም። ሲመክሩም ለሁሉም እንዲሆን ይናገራሉ።
♦ ሰዎችን በመጥፎ አይጠረጥሩም። እገሌ እንዲህ አስቦ ነው ብለው በክፉ አያስቡም።
♦ ሰው ሲያወራቸው ወሬውን ቢያረዝም እንኳን እስኪጨርስ ይጠብቃሉ እንጅ ተነስተው አይሄዱም። በመሀል ሌላ ሰው ከመጣም ይሄኛውን እስኪሸኙ አያናግሩትም።
♦ አንድ ቃል እንደ ቀልድ ቢናገሩት እንኳን ሳይፈፅሙ አይተውትም።
♦ አንድ ጉዳይ ለአኼራ ወይም ለዱንያ የማይጠቅም ከሆነ አይናገሩም። ንግግራቸው ሁሉ ጥቅም አለው።
♦ ንግግራቸውን ሁሉ በብስራት ይጀምራሉ። አንድ ጥሩና አንድ መጥፎ ነገር ከተከሰተ ቅድሚያ ጥሩውን ይናገራሉ።
♦ ገዳማ ናቸው። አንድ ጉዳይ ሲከሰት ጥሩ ያመጣልናል ብለው ተስፋ ያደርጋሉ።
♦ ሲሄዱ ከፊት ልቀደም አይሉም። ሚስቶቻቸውን ጋር እንኳን ሲሄዱ ከጎናቸው ሆነው ነው።
👉 ሁሉም የነቢዩ (ዐሰወ) ባህርያት ድንቅ ቢሆኑም እነዚህን የጠቀስኳቸው ብዙዎቻችን የማናተኩርባቸው የምሉዕነት መገለጫወቻቸው ስለሆኑ ነው።

(በወንድም ሰል ማን)

ፔጁን ላይክ አድርጉት

Address


Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ወሎ ሱና ቲዩብ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

  • Address
  • Alerts
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share