AA Ethio Press

  • Home
  • AA Ethio Press

AA Ethio Press About our country peace!!

ሰበር Loading ...በአዲስ አበባ የኬብል ካር ቴክኖሎጂ ተግባራዊ ሊደረግ መሆኑ ተገለጸኦቪድ ግሩፕ የትራንስፖርት ችግርን መፍታት የሚያስችል የኬብል ካር (በገመድ ላይ ተንጠልጣይ የህዝብ ...
07/03/2024

ሰበር Loading ...
በአዲስ አበባ የኬብል ካር ቴክኖሎጂ ተግባራዊ ሊደረግ መሆኑ ተገለጸ

ኦቪድ ግሩፕ የትራንስፖርት ችግርን መፍታት የሚያስችል የኬብል ካር (በገመድ ላይ ተንጠልጣይ የህዝብ ትራንስፖርት) ቴክኖሎጂ ተግባራዊ ሊያደርግ መሆኑን የድርጅቱ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ዮናስ ታደሰ ገልጸዋል።

ኦቪድ ግሩፕ በቴክኖሎጂ የታገዙ ዘመናዊ ቤቶችን ከመገንባት ባሻገር የትራንስፖርት ችግርን ለመፍታት በአዲስ አበባ የኬብል ካር ቴክኖሎጂ ተግባራዊ ለማድረግ የፕሮጀክት ጥናት ማጠናቀቁን ዋና ሥራ አስፈፃሚው አስታውቀዋል።

የባቡር እና የመኪና መሰረተ ልማቶችን ማፍረስ ሳያስፈልግ በገመድ ላይ ተንጠልጣይ የህዝብ ትራንስፖርት ወይም ኬብል ካር ቴክኖሎጂን በአዲስ አበባ ተግባራዊ ለማድረግ ያስችላል ብለዋል።

በገበታ ለሸገር፣ ገበታ ለሀገር እና ገበታ ለትውልድ የኢትዮጵያን ገጽታ የሚያጎሉ የተለያዩ ፕሮጀክቶች እየተከናወኑ መሆኑን ገልጸው፤ ኦቪድ ግሩፕም በግንባታው ዘርፍ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም ዘመናዊ ከተማ ለመገንባት በመንግስት የሚደረገውን ጥረት የበለጠ የሚደግፍ መሆኑን አረጋግጠዋል።

ኦቪድ ሀገራዊ ልማትን ከማገዝ ባለፈ በግንባታው ዘርፍ ዘመናዊ ቴክኖሎጂን በመጠቀም እና በአጭር ጊዜ የማጠናቀቅ ስራውን እንደሚቀጥል መግለጻቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

ቀን 8/3/2016 ዓ.ምዜና ቦሌ ወረዳ 11~~~~~~~~~~በካቢኔ  የግንኙነት  መድርክ ከአገልግሎት አሰጣጥና ከመልካም አስተዳደር ጋር ተያይዞ መደበኛ የመንግስት ተግባራት ያሉበት ደረጃ ተገ...
18/11/2023

ቀን 8/3/2016 ዓ.ም
ዜና ቦሌ ወረዳ 11
~~~~~~~~~~
በካቢኔ የግንኙነት መድርክ ከአገልግሎት አሰጣጥና ከመልካም አስተዳደር ጋር ተያይዞ መደበኛ የመንግስት ተግባራት ያሉበት ደረጃ ተገመገመ።
በቦሌ ክፍለ ከተማ የወረዳ 11 አስተዳደር ከአገልግሎት አሰጣጥናከመልካም አስተዳደር ጋር ተያይዞ መደበኛ የመንግስት ተግባራት ያሉበት ደረጃ በተመለከተ ከሴከተር ጽ/ቤቶች ከተዉጣጡ ኃላፊዎች ጋር በግንኙነት መድርክ ገመገመ።
መድረኩን የመሩት የወረዳዉ ዋና_ስራ አስፈፃሚ ፅ/ቤት ኋላፊ አቶ ይማም ሀሰን ሲሆኑ በመድረኩ ላይ በ2016 በጀት ዓመት የታቀዱ ዓብይ ተግባራት በታቀደላቸው ልክ ስለመፈጸማቸዉ የሚያሳዩ የተለያዩ ሪፖርቶችን በአግባቡ ሰለመደራጀቱ፡ ዉጤትን መሰረት በማድረግ ፈጻሚንና ቡድን መሪን አዘጋጅቶ ወደ ተግባር ከመግባትና ከዝግጅት ምዕራፍ ተግባራት ጋር በተያያዘ እየተከናወኑ ያሉ ተግባራት ያለቡት ደረጃ እንዲሁም ምቹ የስራ አከባቢን ለተገልጋያ ለመፍጠርና ቀልጣፍ አገልግሎት ለመስጠት የተደረጉ ጥረቶችን ምን ደረጃ ላይ እንዳሉ ተገምገሟል።
============================
በመጨረሻም በወረዳዉ አስተዳደሩ በ2016 በጀት አመት አጋማሽ የተሰሩ ስራዎችን አፈፃፀም ለመገምገም ለሚያካሂዱት የስራ ዉጤታማነት የቡድን መሪዎች እና ኃላፊዎች በ60 እና 90 ቀናት ተከፋፍሎ ስራወች መከናወን እንዳለባቸዉ እንዲሁም መደበኛ ተግባራትን በአግባቡ በማደራጀት ወረዳዉን ገጽታ በሚገነባ መልኩ ማስረዳት እንደሚጠበቅባቸዉ የትኩረት አቅጣጫወች ላይ አትኩሮ መሰራት እንዳለበት ከመድረኩ መልዕክት ተላልፏል፡፡

"ሰው ተኮር ተግባሮቻችንን ለሕዝብ በገባነው ቃል-መሠረት አጠናክረን እንቀጥላለን"🙏🙏🙏🙏🙏🙏የቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 11 አስተዳደር በወረዳዉ በሚገኙ ቀጠናወች የተገነቡና የታደሱ 17 የአቅመ ...
27/09/2023

"ሰው ተኮር ተግባሮቻችንን ለሕዝብ በገባነው ቃል-መሠረት አጠናክረን እንቀጥላለን"🙏🙏🙏🙏🙏🙏

የቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 11 አስተዳደር በወረዳዉ በሚገኙ ቀጠናወች የተገነቡና የታደሱ 17 የአቅመ ደካማ ወገኖች የመኖሪያ ቤቶች ለተጠቃሚዎች እያስረከቡ ይገኛሉ።
~~~~~~~~~~~~~~~~~~
አስተዳደሩ ሙሉ በሙሉና በከፊል ከታደሱ ቤቶች ዛሬ መስከረም 16/2016 ዓ.ም የተላለፈዉ በአጭር ጊዜ ተጀምሮ የተጠናቀቀዉን ሲሆን አሁንም የወረዳ አስተዳደሩ በጀመረው ልክ ጨርሶ እያስመረቀ ነው።
በምርቃቱ እለቱ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፀረ- ሙስና ምክትል ኮሚሽን ኮሚሺነር አቶ ፈቱ ሰማን ፣የክ/ከተማው ዋና ስራ አስፈጻሚ ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ታደሰ በሬሶና የቦሌ ክ/ከተማ የህብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፍቃድ ማስተባበሪያ ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ጌታቸው ካሳዬ ጨምሮ ሌሎች የክ/ከተማና የወረዳ ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተው ፕሮግራሙን አስጀምረዋል፡፡
==የወረዳው ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ አማን ሀምዳ ሀገር የምትገነባው እንደዚህ አይነት ቀና ልቦና ባላቸው ሰዎች ነው፡፡በዓለም ላይ ያሉ ትልልቅ ድርጅቶች የተገነቡት በበጎ ፈቃደኛ ግለሰቦችና የህዝቦች ትብብርና ተነሳሽነት እንደሆነ ታሪክ ያስረዳል፡፡በኛም ሀገር ያሉ በጎ ፈቃደኞች የማይመቹ ነገሮች ሲኖሩ ከመጠየቅና ከመጠበቅ ይልቅ በበጎ ፈቃደኝነትና በተነሳሽነት በርካታ ነገሮች እየተሰሩ ነው፡፡ይህ ተግባራችን ተጠናክሮ ይቀጥላል፡፡ይህን ለሚያደርጉ በጎ ፈቃደኞችም ክብር እንሰጣለን ብለዋል፡፡
==በተጨማሪም የእኛን ወረዳ ለየት የሚያደርገው በዘንድሮው አመት ቤት የሚታደስላቸው ወገኖቻችን በሙሉ ከአሁን በፊት ማንም ያላያቸው ለረጂም አመታት ፀሀይና ብርድ ሲፈራረቅባቸው የነበሩ አካል ጉዳተኛ እና አቅመ ደካሞች በመሆናቸው ሰው ተኮር መሆኑን ይበልጥ የሚያስመስክር ነው።
==በምርቃት መርሐ ግብሩ የቤት እድሳት ከተደረገላቸው አባት አንዱ የሆኑት አቶ ዘውዱ ገ/ስላሴ ናቸዉ።

የብልፅግና ፓርቲ ጥቅል ዓላማ -የበለፀገች ኢትዮጵያን እውን ማድረግ!የፓርቲያችን ጥቅል ዓላማ የበለፀገች ኢትዮጵያን እውን ማድረግ ነው። ብልፅግና ስንል ፈርጀ ብዙ ትርጓሜን አዝሎ የኢኮኖሚ፣ ...
15/09/2023

የብልፅግና ፓርቲ ጥቅል ዓላማ -የበለፀገች ኢትዮጵያን እውን ማድረግ!

የፓርቲያችን ጥቅል ዓላማ የበለፀገች ኢትዮጵያን እውን ማድረግ ነው። ብልፅግና ስንል ፈርጀ ብዙ ትርጓሜን አዝሎ የኢኮኖሚ፣ ፖለቲካ እና ማህበራዊ ገጽታ ያለው ነው።

የኢኮኖሚ ብልፅግና፣ የህዝቦች መሰረታዊ ፍላጎቶች በተገቢና በዘላቂነት ለማሟላት ፈጣን እና ሁለንተናዊ ዕድገትን በማስመዝገብና ዓለም-አቀፋዊ ተወዳዳሪነት ያለው ኢኮኖሚ በመገንባት ፍትሃዊ ተጠቃሚነትን ማረጋገጥና የህዝቦችን ድህነትና ኋላ-ቀርነትን ለመቅረፍ መቻልን ያካተተ ነው።

የፖለቲካ ብልፅግና ስንል ለዴሞክራሲ ባህል ማበብ አስፈላጊ የሆኑ ተቋማትን በመገንባት፣ የህዝቦች ነፃነትና እኩልነት ተረጋግጦ፣ ሁሉም ኢትዮጵያውያን ሰብአዊ እና ዴሞክራሲያዊ መብቶቻቸው ተከብረውላቸው የሚኖሩባት፣ ህብረ-ብሔራዊ አንድነቷ የተረጋገጠ፣ ፌዴራላዊት ዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያን በጽኑ መሰረት ላይ ማቆም ማለታችን ነው።

ማህበራዊ ብልፅግና መልካም ሀገራዊ ወጎችን፣ ዕሴቶችን እና ባህሎችን በማዳበር በስነ-ምግባር የታነፀ ትውልድ ማፍራት፣ በአካልና በአእምሮው የዳበረ ጤናማ ዜጋ መፍጠር፣ ከአስከፊ ማህበራዊ ችግር የተጠበቀ ህብረተሰብ መገንባት እና በህዝቦች መካከል አዎንታዊ ሰላም በመፍጠር ሁለንተናዊ ብልፅግናን ማረጋገጥ ማለት ነው።

የብልፅግና ፓርቲ ፕሮግራም (2014) ገፅ 9

የአገልጋይነት ቀንን ምክንያት በማድረግ ውይይት ተካሂያደ። የቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 11 ፐብሊክ ሰርቪስ ፅ/ቤት ጳግሜ 1 የአገልጋይነት ቀንን ምክንያት በማድረግ ከአጠቃላይ ሰራተኞች ጋር ውይይት...
05/09/2023

የአገልጋይነት ቀንን ምክንያት በማድረግ ውይይት ተካሂያደ።

የቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 11 ፐብሊክ ሰርቪስ ፅ/ቤት ጳግሜ 1 የአገልጋይነት ቀንን ምክንያት በማድረግ ከአጠቃላይ ሰራተኞች ጋር ውይይት አካሂዷል።

በውይይት መድረኩን የመሩት የወረዳው የዲሞክራሲ ስርአት ግንባታ ማስተባበሪያ ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ አዲሱ ደበላና ፐብሊክ ሰርቪስ ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ታደሰ በለጠ ለውይይት የተዘጋጀውን ሰነድ በማንበብ አስጀምረውታል ።

በ2014 ጳግሜ ወር በ2015 በጀት አመት የተሻለ ስራ ለመስራት ቃል በመግባት ጀምረን ነበር የገባነውን ቃል በመጠበቅ በርካታ ስራ ሰርተናል የተሻለ አፈፃፀምም ማስመዝገብ ችለናል። ዛሬም ለ2016 አዲስ አመት ድክመቶቻችንን አርመን ጠንካራ ጎናችንን በማስቀጠል የተሻለ ቅንነት የተሞላበት አገልግሎት ለመስጠት ቃል የምንገባበት ነው ብለዋል።

የወረዳው ፐብሊክ ሰርቪስ ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ታደሰ በለጠ በበኩላቸው ጳግሜን ለኢትዮጵያ በሚል መሪ ሀሳብ የጳግሜን ቀናት በተለያየ ስያሜ ለማክበር ተዘጋጅተናል ያሉ ሲሆን ጳግሜ 1የአገልጋይነት ቀንን ሀገሬን መቼም፣የትም፣በምንም ሀኔታ አገለግላለሁ በሚል መሪ ሀሳብ እናከብራለን ብለዋል።

በተጨማሪም ወረዳ አስተዳደሩን በተለያየ ተቋም ውስጥ በባለሙያነት ተመድበው ሲያገለግሉ የነበሩ በጡረታ እንዲወጡ የሽኚት ፕሮግራምና በበጀት አመቱ አፈፃፀማቸው የተሻሉ ኦፊሰሮችን የእውቅናና ሽልማት ተካሂዷል።

በውይይት መድረኩ የመልካም አገልግሎት አሰጣጥ ችግሮችና መፍተሄው ላይ ሰፊ ውይይት ተካሂዷል።
ቦሌ ወረዳ 11 ኮምኒኬሽን ጽ/ቤት /bole wereda 11 communication

Congratulations to Ethiopian Airlines which last week celebrated the 10th year anniversary of the commencement of its fl...
20/07/2023

Congratulations to Ethiopian Airlines which last week celebrated the 10th year anniversary of the commencement of its flight to Seoul, South Korea 🇰🇷

In the picture, the brand ambassador CC posing at the event.

Share your best contents for a chance to be featured on the page.

17/07/2023
ሰኔ 29/10/2015 ዓም  =====በቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 11 ፐብሊክ ሰርቪስ የሰው ሀብት ልማት ጽ/ቤት ከወረዳው አመራሮች፣ ቡድን መሪዎች እና ሰራተኞች ጋር ለ3 ተከታታይ ቀን  ሲሰጥ የነ...
06/07/2023

ሰኔ 29/10/2015 ዓም
=====በቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 11 ፐብሊክ ሰርቪስ የሰው ሀብት ልማት ጽ/ቤት ከወረዳው አመራሮች፣ ቡድን መሪዎች እና ሰራተኞች ጋር ለ3 ተከታታይ ቀን ሲሰጥ የነበረዉ ስልጠና ተጠናቀቀ ።
===========በቦሌክ/ከተማ ወረዳ 11 ፐብሊክ ሰርቪስ የሰው ሀብት ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ ስልጠናዉ በአገልግሎት አሰጣጥ ማኑዋል፣በስታንዳርድ አፈፃፀም እና በሰራተኞች ድስፒሊን ዙሪያ የሚሰጠዉ ስልጠና ለሁሉም አካላትመነሳሳትን ይበልጥ የሚፈጥር መሆኑን አስታዉሰዉ ከአመራሩ እስከ ሰራተኛው ድረስ መደበኛ ስራዎቻቸውና አገልግሎት አስጣጣቸውን ለማሻሻል የሚያስችል አደረጃጀት ለሀገር ሁ ለንተናዊ ለውጥ አስፈላጊ ስለሆነ የአቻ ሰራተኞች ፎረም የአፈጻጸም ደረጃ ለመለየት ከማስቻሉም በላይ ትልቅ የሆነ ጠቀሜታው የእርስበእርስ መገነባባትና በክህሎት ፣በአስተሳስብ፣ በስነምግባር ፣በአፈጻጸም የተቀራረበ አቅም መገንባቱን ለመለካት በሚያስችል መልኩ የተዘጋጀ ስልጠና ነው በማለት ለወረዳው ቡድን መሪዎች ተናግረዋል፡፡
የጽ/ቤቱ ሀላፊ የሆኑት አቶ ይማም ሀሰን እዳሉት መፈጸምና የማስፈጸም ብቃትናውጤታማነት ወደላቀ ደረጃ ለማድረስ የለተለያዩ ሪፎርምና የአገልግሎት አስጣጥ ስራዎች በማንኛውም መመዘኛ ሳይንሳዊና አለማቀፋዊ ደረጃቸውን የጠበቁ ተግባራዊ ሆነው ተጨባጭ ውጤት ያመጡ በመሆኑ መልካሙን ውጤት መነሻ በማድረግ በቅልጥፍናና በውጤታማነት ለመፈጽም የሚያስችል አቻ ሰራተኛ ፎርም መገንባቱ ቀልጣፋና ከዘመኑን ጋር አብሮ የሚንቀሳቀስ ሰራተኛ ለማፍራት ያስችላል ብለዋል።

ምንጭ ፦ ወረዳ 11 ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት
ሰኔ29/10/2015

ሰኔ 26/10/2015 ዓም  =====በቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 11 ፐብሊክ ሰርቪስ የሰው ሀብት ልማት ጽ/ቤት ከወረዳው አመራሮች፣ ቡድን መሪዎች እና ሰራተኞች ጋር ለ3 ተከታታይ ቀን የሚቆይ ስል...
03/07/2023

ሰኔ 26/10/2015 ዓም
=====በቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 11 ፐብሊክ ሰርቪስ የሰው ሀብት ልማት ጽ/ቤት ከወረዳው አመራሮች፣ ቡድን መሪዎች እና ሰራተኞች ጋር ለ3 ተከታታይ ቀን የሚቆይ ስልጠና መጀመሩ ተገለፀ ።
===========በቦሌክ/ከተማ ወረዳ 11 ፐብሊክ ሰርቪስ የሰው ሀብት ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ የሆኑት አቶ ይማም ሀሰን እንዳሉት ስልጠናዉ በአገልግሎት አሰጣጥ ማኑዋል፣በስታንዳርድ አፈፃፀም እና በሰራተኞች ድስፒሊን ዙሪያ የሚሰጠዉ ስልጠና ለሁሉም አካላትመነሳሳትን ይበልጥ የሚፈጥር መሆኑን አስታዉሰዉ ከአመራሩ እስከ ሰራተኛው ድረስ መደበኛ ስራዎቻቸውና አገልግሎት አስጣጣቸውን ለማሻሻል የሚያስችል አደረጃጀት ለሀገር ሁ ለንተናዊ ለውጥ አስፈላጊ ስለሆነ የአቻ ሰራተኞች ፎረም የአፈጻጸም ደረጃ ለመለየት ከማስቻሉም በላይ ትልቅ የሆነ ጠቀሜታው የእርስበእርስ መገነባባትና በክህሎት ፣በአስተሳስብ፣ በስነምግባር ፣በአፈጻጸም የተቀራረበ አቅም መገንባቱን ለመለካት በሚያስችል መልኩ የተዘጋጀ ስልጠና ነው በማለት ለወረዳው ቡድን መሪዎች ተናግረዋል፡፡
የጽ/ቤቱ ሀላፊ የሆኑት አቶ ይማም ሀሰን እዳሉት መፈጸምና የማስፈጸም ብቃትናውጤታማነት ወደላቀ ደረጃ ለማድረስ የለተለያዩ ሪፎርምና የአገልግሎት አስጣጥ ስራዎች በማንኛውም መመዘኛ ሳይንሳዊና አለማቀፋዊ ደረጃቸውን የጠበቁ ተግባራዊ ሆነው ተጨባጭ ውጤት ያመጡ በመሆኑ መልካሙን ውጤት መነሻ በማድረግ በቅልጥፍናና በውጤታማነት ለመፈጽም የሚያስችል አቻ ሰራተኛ ፎርም መገንባቱ ቀልጣፋና ከዘመኑን ጋር አብሮ የሚንቀሳቀስ ሰራተኛ ለማፍራት ያስችላል ብለዋል።

ምንጭ ፦ ወረዳ 11 ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት
ሰኔ26/10/2015

👉 መደመር አዲስ የፖለቲካ paradigm ነው፡፡👉 ብልፅግና ያን paradigm ተሸክሞ የሚያስፈፅም ስብስብ ነው፡፡ ሃይል ነው ፓርቲ ነው፡፡👉 መደመር ማእቀፍ ነው፡፡ ብልፅግና ይዘት ነው፡፡👉...
21/06/2023

👉 መደመር አዲስ የፖለቲካ paradigm ነው፡፡

👉 ብልፅግና ያን paradigm ተሸክሞ የሚያስፈፅም ስብስብ ነው፡፡ ሃይል ነው ፓርቲ ነው፡፡

👉 መደመር ማእቀፍ ነው፡፡ ብልፅግና ይዘት ነው፡፡

👉 መደመር container ነው፡፡ ብልፅግና content ነው፡፡

👉 ኮንቴይነር ከኮንቴንቱ ወይም እኩል ወይም የላቀ መሆን አለበት፡፡

👉 መደመር አቅጣጫን ይወስናል፡፡ ብልፅግና ግን መዳረሻን ይወስናል፡፡

👉 መደመር direction ብልፅግና destination ይወስናል፡፡

👉 ለዚህ ነው መደመር መንገዳችን ብልፅግና መዳረሻችን የምንለው፡፡

👉 መደመር ፍልስፍና ነው፡፡ ፓርቲ ግን ክዋኔ ነው፡፡

👉 ይሄኛው theory ይህኛው practice ነው፡፡

👉 መደመር ቴዎሪውን ያወራዋል፡፡ ብልፅግና ይኖረዋል ይሰራዋል፡፡

አቡበከር ናስር ከጉዳት በተመለሰበት ጨዋታ ጎል አስቆጥሯል   | ከሁለት ወራት በላይ በጉዳት ከሜዳ ርቆ የነበረው ኢትዮጵያዊው የማሜሎዲ ሰንዳውንስ አጥቂ አቡበከር ናስር ቡድኑ በካፍ ቻምፒየን...
01/04/2023

አቡበከር ናስር ከጉዳት በተመለሰበት ጨዋታ ጎል አስቆጥሯል

| ከሁለት ወራት በላይ በጉዳት ከሜዳ ርቆ የነበረው ኢትዮጵያዊው የማሜሎዲ ሰንዳውንስ አጥቂ አቡበከር ናስር ቡድኑ በካፍ ቻምፒየንስ ሊግ ኮተን ስፖርትን 2ለ1 በረታበት ጨዋታ በ62ኛው ደቂቃ ተቀይሮ በመግባት በ86ኛው ደቂቃ ሁለተኛው ጎል በስሙ አስመዝግቧል።

በአዳስ ከተማ ክፍለ ከተማ  በግለሰብ መኖሪያ ግቢ ውስጥ ተከማችቶ የነበረ በርካታ ሟስልና ኮንትሮባድ ሲጋራ  በህብረተሰቡ ጥቆማ ከ1 ተጠርጣሪ ጋር በቁጥጥር ስር መዋሉን የአዲስ አበባ ፖሊስ ...
01/04/2023

በአዳስ ከተማ ክፍለ ከተማ በግለሰብ መኖሪያ ግቢ ውስጥ ተከማችቶ የነበረ በርካታ ሟስልና ኮንትሮባድ ሲጋራ በህብረተሰቡ ጥቆማ ከ1 ተጠርጣሪ ጋር በቁጥጥር ስር መዋሉን የአዲስ አበባ ፖሊስ ገለፀ።
***
ተጠርጣሪው በቁጥጥር ስር የዋለው መጋቢት 22 ቀን በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 9 ልዩ ቦታው በተለምዶው አበራ ወጌሻ ሰፈር ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ነው።
ግለሰቡ መጋዘኑን የትራስ መስሪያ ቁርጥራጭ እስፖንጅ ማስቀመጫ ነው ብሎ የቤቱን አከራዮች በማሳመን ከተከራየ በኃላ ምሽትን እንደመልካም አጋጣሚ ተጠቅሞና ከሰው እይታ ውጭ በሆነ መንገድ 498 ፓኬት ኦሪስ የሚባል በኮንትሮባንድ ወደ ሃገር ውስጥ የገባ ሲጋራ እና 121 ካርቶን ወይም 14 ሺህ 520 ፍሬ ሟስልን አከማችቶ ለገበያ ለማቅረብ በዝግጅት ላይ እያለ ፖሊስ ከህብረተሰቡ በደረሰው ጥቆማ የፍርድ ቤት መበርበሪያ ትዕዛዝ በማውጣት ወደ ማህበረሰቡ ሳይሰራጭ ከነተጠርጣሪው በቁጥጥር ስር ሊውል መቻሉን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል።

ግለሰቡ ከተያዘበት ሰዓት ጀምሮ አስፈላጊው ምርመራ እየተጣራበት የሚገኝ ሲሆን የግል ጥቅማቸውን ብቻ በማስቀደም በህገ-ወጥ ተግባራትና በተለያዩ ወንጀሎች ላይ የሚሳተፉ ግለሰቦችን ማህበረሰቡ ጥቆማ በመስጠት በህግ እንዲጠየቁ እያደረገ ያለው ተሳትፎ የሚበረታታ መሆኑን የገለፀው ፖሊስ ቤት የሚያከራዩ ግለሰቦች የሚያከራዩትን ግለሰብ ማንነት ማወቅና ለምን አላማ ቤታቸውን እንደሚከራይ መረዳት እንደሚገባቸው አስታውቋል። በቀጣይም ህዝብና ሃገርን የሚጎዱ ህገወጥ ተግባራትን በመቆጣጠር ረገድ ለሚደረገው ርብርብ ህብረተሰቡ እንደከዚህ ቀደሙ ትብብሩን አጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት የአዲስ አበባ ፖሊስ ጥሪውን አቅርቧል።

ዘገባው፦ዋና ሳጅን ዘላለም አበበ
*
ለፈጣን መረጃዎች:
በፌስቡክ :- https://www.facebook.com/Addisababapolice
በቴሌግራም:- https://t.me/addispolice
በዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/AddisAbabaPoliceCommission
በትዊተር፦Twitter https://twitter.com/AddisPolice
ድረ ገጽ፦ web https://www.addispolice.gov.et/
**
“በጀግንነት መጠበቅ በሰብዓዊነት ማገልገል!”
**

ምቹና ማራኪ የስራ ቦታን በመፍጠር ለተገልጋይ ቀልጣፋ አገልግሎት መስጠት ቁልፍ ተግባራችን ነው!! የቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 11 አስተዳደር የ7/24 መርህን በመከተል የ90 ቀናት ዕቅዱ በስኬ...
07/03/2023

ምቹና ማራኪ የስራ ቦታን በመፍጠር ለተገልጋይ ቀልጣፋ አገልግሎት መስጠት ቁልፍ ተግባራችን ነው!!

የቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 11 አስተዳደር የ7/24 መርህን በመከተል የ90 ቀናት ዕቅዱ በስኬት እንዲጠናቀቅ በትጋት በመሥራት የሰራተኛ ካፌ፣ የዴይኬር እና የግቢ የማስዋብና የሌማት ትሩፋት ስራዎች ተሰርቷል፣ ዋናውን ህንጻ የማስዋብ ስራም በማገባደድ ላይ ይገኛል።

ጠንክሮ በመሥራት ለፍሬ ለማብቃት የመጨረሻው ምዕራፍ ላይ ተደርሷል።

የካቲት 28/2015 ዓ.ም

"የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በኦሮሚያ ክልል ቦረና ዞን ባጋጠመው ድርቅ ለተጎዱ ወገኖች ከ255 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ አደረገ"   አስተዳደሩ ከሁሉም ክፍለ ከተሞች እንዲሁም ከተቋማትና...
28/02/2023

"የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በኦሮሚያ ክልል ቦረና ዞን ባጋጠመው ድርቅ ለተጎዱ ወገኖች ከ255 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ አደረገ"

አስተዳደሩ ከሁሉም ክፍለ ከተሞች እንዲሁም ከተቋማትና ባለሀብቶች ያሰባሰበው ይህ ድጋፍ 131 ሚሊየን ብር ዋጋ ያለው የዓይነትና ከ120 ሚሊየን ብር በላይ በጥሬ ገንዘብ የተደረገ ሲሆን፣ ድጋፉን ለኦሮሚያ ብሔራዊ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አወሉ አብዲ ያስረከቡት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ የከተማ አስተዳደሩ በድርቅ ለተጎዱ ወገኖች ድጋፍ ለማድረግ ላቀረበው ጥሪ ከተለያዩ አካላት ፈጣን ምላሽ ለማግኘት መቻሉን ተናግረዋል። “በችግር ወቅት አብሮነትን ማሳየት የቆየና ያልደበዘዘ እሴታችን ነው” ያሉት ከንቲባ አዳነች፣ የቦረና ዞን ለረዥም ጊዜ በድርቅ እየተጎዳ ያለ አካባቢ ቢሆንም፣ ችግሩን ለኦሮሚያ ክልል ብቻ የሚተው ባለመሆኑ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በአጋርነት በመቆም ድጋፉን ማበርከቱን አክለው ገልጸዋል።

ከተደረገው ድጋፍ ውስጥ የቦሌ ክፍለ ከተማ ከ5.2 ሚሊየን ብር በላይ በማሰባሰብ አስተዋጽኦ አበርክቷል።

የካቲት 21/2015

Ethiopia's current leader is Abiy Ahmed, who has been in office since 2018. Ahmed has implemented  market-oriented econo...
24/02/2023

Ethiopia's current leader is Abiy Ahmed, who has been in office since 2018. Ahmed has implemented market-oriented economic policies, privatized state-owned enterprises, and attracted foreign investment.

He has made efforts to increase access to healthcare and education, and has introduced a genderbalanced cabinet. In terms of political reforms, Abiy has opened up the media landscape, released political prisoners, and invited previously banned opposition groups to return from exile. Ahmed's government has also undertaken several mega projects, including the Grand Ethiopian Renaissance Dam (GERD), the Addis Ababa–Djibouti Railway, and various industrial parks.

Abiy has also launched the Green Legacy program, which aims to plant four billion trees across Ethiopia in a single year. The program was launched in 2019 and has since exceeded its target, with over five billion trees planted in 2020. The Green Legacy initiative is part of a broader effort to combat deforestation and address climate change in Ethiopi

ማን ነበር ''አርሰናሎችን ወደ ቦታቸው እንመልሳቸዋለን'' ብሎ የነበረው? እውነት ነው ወደሚገባን ቦታ መልሳችሁናል።መድፈኞቹ ❤❤❤❤❤❤💪💪💪💪💪    ars 3-2 mutd
22/01/2023

ማን ነበር ''አርሰናሎችን ወደ ቦታቸው እንመልሳቸዋለን'' ብሎ የነበረው? እውነት ነው ወደሚገባን ቦታ መልሳችሁናል።

መድፈኞቹ ❤❤❤❤❤❤💪💪💪💪💪
ars 3-2 mutd

የዓለም አትሌቲክስ ሻምፕዮና አሸናፊዎች ቤተሰቦቻቸውን ማግኘታቸው ተነገረበሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ምክኒያት ከቤተሰቦቻቸው ጋራ በአካል ሳይተያዩና በስልክ ሳይነጋገሩ ሁለት ዓመታት ያሳለፉ የትግ...
10/01/2023

የዓለም አትሌቲክስ ሻምፕዮና አሸናፊዎች ቤተሰቦቻቸውን ማግኘታቸው ተነገረ

በሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ምክኒያት ከቤተሰቦቻቸው ጋራ በአካል ሳይተያዩና በስልክ ሳይነጋገሩ ሁለት ዓመታት ያሳለፉ የትግራይ ተወላጅ አትሌቶች ዛሬ ከቤተሰቦቻቸው ጋራ ተገናኝተዋል።

በኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌደሬሽን ፕሬዚዳንት አትሌት ደራርቱ ቱሉ የሚመራው ልዑክ አትሌቶቹን ከቤተሰቦቻቸው ጋራ ለማገናኘት ዛሬ መቐለ ከተማ ገብቷል::

53 አባላትን የያዘው ይህ ቡድን ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ ዩጂን - ኦሬገን ላይ በተካሄደው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፕዮና አሸናፊዎች የነበሩት ለተሰንበት ግደይ፣ ጎተይቶም ገብረስላሴ እና ጉዳፍ ፀጋይን ያካተተ ነው።
(VOA)

የትግራይ ክልል ተወላጅ የሆኑ አትሌቶችን የያዘ የልዑካን ቡድን ነገ ወደ መቀለ ሊጓዝ ነውየኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን አመራሮች እና የትግራይ ክልል ተወላጅ የሆኑ አትሌቶችን የያዘ የልዑካን...
09/01/2023

የትግራይ ክልል ተወላጅ የሆኑ አትሌቶችን የያዘ የልዑካን ቡድን ነገ ወደ መቀለ ሊጓዝ ነው

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን አመራሮች እና የትግራይ ክልል ተወላጅ የሆኑ አትሌቶችን የያዘ የልዑካን ቡድን፤ ነገ ማክሰኞ ጥር 2፤ 2015 ወደ መቐለ ከተማ ሊጓዝ ነው። በአትሌቲክስ ፌደሬሽን ፕሬዝዳንት አትሌት ደራርቱ ቱሉ የሚመራው ልዑክ ወደ መቐለ የሚጓዘው፤ የክልሉ ተወላጅ የሆኑ አትሌቶችን ከቤተሰቦቻቸው ጋር ለማገናኘት መሆኑ ተገልጿል።

ወደ ትግራይ ክልል መዲና ነገ ረፋድ በአውሮፕላን የሚጓዘው ይህ የልዑካን ቡድን፤ በመቐለ ከተማ የሚኖረው ቆይታ የአንድ ቀን ብቻ መሆኑን በጉዞው ላይ ተሳታፊ የሆነ አንድ አትሌት ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናግሯል። ይህንኑ መረጃ በኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የኮሚዩኒኬሽን ባለሙያ የሆኑት አቶ ቴዎድሮስ ለገሰ አረጋግጠዋል።

በዚህ ጉዞ ላይ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን አመራሮች፣ የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት እና “የተለያዩ የስራ ክፍል አባላት” ተሳታፊ እንደሚሆኑ የኮሚዩኒኬሽን ባለሙያው ገልጸዋል። በነገው ጉዞ ከሚሳተፉ የትግራይ ክልል ተወላጅ ከሆኑ አትሌቶች መካከል፤ በቶኪዮ ኦሎምፒክ እና በአሜሪካው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና የወርቅ ሜዳሊያ አሸናፊዎች የነበሩት ለተሰንበት ግደይ፣ ጎተይቶም ገብረ ስላሴ እና ጉዳፍ ጸጋይ እንደሚገኙበት ተናግረዋል።

Address


Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when AA Ethio Press posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

  • Address
  • Alerts
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share