Ewnet Check

Ewnet Check Ewnet Check is a project to combat misinformation, hate speech and fraud in Ethiopia'a internet landscape and beyond.

በኢትዮጵያ ጥቁር ገበያ የዶላር ምንዛሪ ባለፉት አመታት ከብሄራዊ ባንክ ተመን ጋር ሲነጻጸር ምን ይመስል ነበር? ኢኮኖሚያዊ ተጽዕኖውስ? ሙሉ ትንተናው ይመልከቱ።https://www.ewnetch...
07/01/2022

በኢትዮጵያ ጥቁር ገበያ የዶላር ምንዛሪ ባለፉት አመታት ከብሄራዊ ባንክ ተመን ጋር ሲነጻጸር ምን ይመስል ነበር? ኢኮኖሚያዊ ተጽዕኖውስ? ሙሉ ትንተናው ይመልከቱ።
https://www.ewnetcheck.org/data-report/ethiopia-birr-dollar-exchange-rate-dossier/

በኢትዮጵያ ጥቁር ገበያ የዶላር ምንዛሪ በዚህ አመት ምን ይመስል ነበር? ኢኮኖሚያዊ ተጽዕኖውስ ትንተናው ይመልከቱ..Continue readingዳታ ሪፖርት : በኢትዮጵያ ጥቁር ገበያ የዶላር ምንዛሪ ኢኮኖ....

Wanna know what Ethiopians are interested in and are searching on Google & Youtube. Check out our Twitter Bot twitter.co...
21/12/2021

Wanna know what Ethiopians are interested in and are searching on Google & Youtube. Check out our Twitter Bot
twitter.com/EthGoogling
that tweets daily what's trending in 🇪🇹

Check your business names for hateful or unwanted meanings in multiple Ethiopian languages with our tool here.https://ew...
30/11/2021

Check your business names for hateful or unwanted meanings in multiple Ethiopian languages with our tool here.
https://ewnetcheck.org/hate-check

Trying to decide a name for your business or child? have you considered what your potential name might mean in another language? What if it's something hateful? checks your word against swear words and unwanted associations in 9 Ethiopian languages/dialects. Including Amharic, Afaan Oromo, Af Somali...

Telegram, the social messaging app, was widely used as a fraud tool in Ethiopia’s national exams, our investigation reve...
14/11/2021

Telegram, the social messaging app, was widely used as a fraud tool in Ethiopia’s national exams, our investigation revealed.
The government blocked the app last time nationwide exams took place in March and also now in November.
https://t.co/79wboepSp9?amp=1

Telegram widely used as a fraud tool in Ethiopia’s national examination Posted on November 10, 2021November 12, 2021 The national examination for Grade 12 students, also known as Ethiopian University Entrance Exam(EUEE), conducted earlier in march and ended on March 11, 2021. It was marred with co...

https://youtu.be/H-Wjp7CM5jg
14/11/2021

https://youtu.be/H-Wjp7CM5jg

Volume . Addis Habtamu on her work at Wolaita S**o University COVID19 treatment center.Dr. Addis is MD graduate from Hawassa Universit...

      Top Performing posts on Social Media Election Day.1. EBC: ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በበሻሻ ድምፅ መስጫ ጣቢያ ተገኝተው ድምፃቸውን ሰጥተዋል ...
21/06/2021



Top Performing posts on Social Media Election Day.

1. EBC: ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በበሻሻ ድምፅ መስጫ ጣቢያ ተገኝተው ድምፃቸውን ሰጥተዋል (2.5M likes,207.3ሺ views in 4 hours)
2. EBC: ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ 6ኛው አገራዊ ምርጫን አስመልክተው ለኢቲቪ የሰጡት አስተያየት (2.5M likes,59.2ሺ views in 1 hour)
3. Fana: ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ በበሻሻ ድምጽ ሰጥተዋል (2.5M likes,108.2ሺ views in 4 hours)

using CrowdTangle

   ኢንጅነር የታከለ ኡማ በቁጥጥር ስር ዉለዋል ተብሎ የሚናፈሰዉ መረጃ የሀሰት ነዉ ተባለ። አሁን ላይ የቴክኖሎጂ አብዮት መምጣቱ ተከትሎ በርካታ የሀሰተኛ መረጃዎች በተለያዩ የሚዲያ አማራጮ...
21/06/2021


ኢንጅነር የታከለ ኡማ በቁጥጥር ስር ዉለዋል ተብሎ የሚናፈሰዉ መረጃ የሀሰት ነዉ ተባለ።

አሁን ላይ የቴክኖሎጂ አብዮት መምጣቱ ተከትሎ በርካታ የሀሰተኛ መረጃዎች በተለያዩ የሚዲያ አማራጮች ሲሰራጩ ይስተዋላል።

ከቀናት በፊት በይትዮብ ቻናሎች በአዲስ አበባ ቦምብ እንዲፈነዳ እና ይህንም እንዲሆን ያደረገዉ ኢንጅነር ታከለ ኡማ ነዉ በማለት ከአንድ ቪዲዮ ላይ የሚናገር ግለሰብን በመጥቀስ ያሰራጩት መረጃ የሀሰት እንደሆነ እዉነት ቼክ ባደረገዉ ማጣራት አረጋግጧል።

የቀድሞ የአዲስ አበባ ከንቲባ የአሁኑ ደግሞ የማዕድን እና ነዳጅ ሚኒስተር የሆኑት ታከለ የኡማ ለእስር እንደተዳረጉ ተደርጎ የተናፈሰዉ የፈጣራ መረጃ እንደሆነ እና ከአራት ቀናት ማለትም ሰኔ 10/2013 ዓ.ም ላይ ደግሞ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ከአቶ አሻድሊ ሀሰን ጋር በመሆን በአሶሳ ከተማ ሁለተኛውን የከሰል ድንጋይ ማምረቻ ፋብሪካ ግንባታ ማስጀመራቸዉን የሀገር ዉስጥ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል

እንዲሁም ዛሬ ሰኔ 14/2013 ዓ.ም ደግሞ የሀገር አቀፍ ምርጫዉን ተከትሎ
ድምፅ መስጠታቸዉን በራሳቸዉ ማህበራዊ ድረገፅ ላይ አስፍረዋል።

ከዚህ በተጨማሪም እዉነት ቼክ ያደረገዉ ማጣራት በአዲስ አበባ ዉስጥ ኢንጅነሩ ታስረዋል ተብሎ በይትዮብ የተናፈሰዉ ወሬ የሀሰት እንደሆነ ለማወቅ ችለናል።

https://www.ewnetcheck.org/minister-takele-uma-not-arrested/
ምንጭ :

 ምርጫዉን በማስመልከት ዛሬ ሁሉም የሀገር ውስጥ በረራዎች ተሰርዘዋል ስለተባለዉ መረጃ እዉነታዉ ምንድነዉ...? ዛሬ ሰኔ 14/2013 ዓ.ም ምርጫዉን በማስታከክ  የሀገር ውስጥ በረራዎች እን...
21/06/2021


ምርጫዉን በማስመልከት ዛሬ ሁሉም የሀገር ውስጥ በረራዎች ተሰርዘዋል ስለተባለዉ መረጃ እዉነታዉ ምንድነዉ...?

ዛሬ ሰኔ 14/2013 ዓ.ም ምርጫዉን በማስታከክ የሀገር ውስጥ በረራዎች እንደተሰረዙ የሚገልፁ ፅሁፎች በማህበራዊ ሚድያ ላይ፣ ሲሰራጩ ነበር።

ይህን ተመልክቶ እዉነት ቼክ ባደረገዉ ማጣራት በዛሬዉ ዕለት ምንም አይነት በረራ እንዳልተቋረጠ ተመልክቷል። ፍላይት ራደር (FlightRadar24) ን በመጠቀም ዳሰሳ ያደረገዉ በሀሰተኛ መረጃ ላይ የሚሰራ ተቋሙ በዛሬዉ ዕለት ሀዋሳን ጨምሮ ወደ ሦስት ቦታዎች በረራ እንዳለ ተመልክቷል።

ከዚሁ ጋር በተለያያ የኢትዮጵያ አየር መንገድ እንዳስታወቀዉ የሰዓት መሸዋወዳ ካልሆነ በስተቀር ሁሉም የሀገር ዉስጥ በረራዎች እንዳልተቋረጡ ተናግረዋል።

"በረራዎች እንደበፊቱ እንደቀጠሉ ናቸው። ከሌላው ቀን ምንም የተለየ ነገር የለም" በማለት ደግሞ ምላሽን የሰጡት የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን ዳይሬክተር ጀነራል ኮ/ል ወሰንየለህ ሁነኛው ናቸዉ ሲል Ethiopia Check በድረገፁ አስነብቧል።

በአጠቃላይ ወደ ባህርዳር፣ ደሴ እና ሌሎች ከተሞች በረራዎች እንዳሉ ባደረግነዉ ማጣራት አረጋግጠናል።

"በኢትዮጵያ የሚገኙ ከ 100 በላይ የሀሰተኛ ገፆችን እና አካዉንቶችን መዝጋት ችያለሁ" ሲል ፌስቡክ አስታዉቋልከኢትዮጵያ የመረጃ መረብ ደህነት ኤጀንሲ (ኢንሳ) ጋር ግንኙነት አላቸዉ ያላቸዉ...
17/06/2021

"በኢትዮጵያ የሚገኙ ከ 100 በላይ የሀሰተኛ ገፆችን እና አካዉንቶችን መዝጋት ችያለሁ" ሲል ፌስቡክ አስታዉቋል

ከኢትዮጵያ የመረጃ መረብ ደህነት ኤጀንሲ (ኢንሳ) ጋር ግንኙነት አላቸዉ ያላቸዉን እና የሃሰተኛ እና አሳሳች ይዘቶችን የሚያወጡ በርካታ አካዉንቶችን ማገዱን አስታዉቋል።

ምርጫ ሊካሄድ ቀናት ሲቀረዉ ትላንት ፌስብክ ባወጣዉ ወራዊ በሪፖርቱ ላይ መቀመጫቸዉን በሀገር ዉስጥ እና በባህር ማዶ በማድረግ እንዲሁም ብዙ ተከታዮችን በማፍራት ያልሆነ/ያልተፈጠረ ክስተቶችን በመዘገብ እና ማህበረሰቡን ለማሳሳት ትኩረት አድርገዉ ይሰራሉ ያላቸዉን 176 የፌስቡክ እና የኢንስታግራም አካዉንቶችን ማገዱን አስታዉቋል።

ፌስብክ ባወጣው ሪፖርት ላይ የሰኔን ወርን ጨምሮ ያለፈዉን ማለትም የግንቦትን ወር ላይ የተከሰቱ ክዋኔዎች ዳሰሳ አድርጓል።

ላለፉት አራት ዓመታት በዚህ ስራዉ ላይ ትኩረት አድርጎ የሚሰራዉ ተቋሙ በዚህ ወር ደግሞ ትክክለኛ እና የተቀናጀ ያልሆነ ባህሪን እንዲሁም ግንኙነቶችን በማሻከር ያልተገባ ስም በመስጠት እና በማሳሳት ዉዥንብርን የፈጠሩ ገፆችን ነዉ አግጃለሁ ያለዉ።

እነዚህም 65 የፌስቡክ አካዉንቶች ፣ 52 የፌስቡክ ገፆች ፣ 27 ግሩፖች ፣ እንዲሁም 32 መለያዎችን ከኢንስታግራም በአጠቃላይ 176 የማህበራዊ ትስስር ገፆችን እና አካዉንቶችን አስወግጃለሁ ብሏል ፌስብክ ባወጣዉ ሪፖርት።

https://www.ewnetcheck.org/fb-removes-coordinated-inauthentic-behavior-from-ethiopia/

“በኢትዮጵያ የሚገኙ ከ 100 በላይ የሀሰተኛ ገፆችን እና አካዉንቶችን መዝጋት ችያለሁ” ሲል ፌስቡክ አስታዉቋል Posted on June 17, 2021June 17, 2021 “በኢትዮጵያ የሚገኙ ከ 100 በላይ የሀሰተኛ ገፆችን .....

Code for Africa (CFA) and DW Akademie ባዘጋጁት ከፊት ለፊታችን ያለዉን ምርጫ በተመለከተ የሀሰተኛ መረጃ ስርጭቶችን መቆጣጠር  ዙሪያ በተጨማሪም ደግሞ CIB (Coordi...
17/06/2021

Code for Africa (CFA) and DW Akademie ባዘጋጁት ከፊት ለፊታችን ያለዉን ምርጫ በተመለከተ የሀሰተኛ መረጃ ስርጭቶችን መቆጣጠር ዙሪያ በተጨማሪም ደግሞ CIB (Coordinated inauthentic behavior) በሀገራችን ምን እንደሚመስል በስፋት ስልጠና ተሰጥቶናል።

በዚህ ስልጠና ላይ EwnetCheck ተሳትፎ አድርጓል። ጥሩ ጊዜም አሳልፈናል።

አዘጋጆቹ እና ባለሞያዎች ያላቸዉን ልምድ ስላካፈሉ እናመሰግናለን።

Code for Africa (CfA) and Deutsche Welle Akademie provided us with extensive training on how to control the spread of false information during the upcoming elections, as well as how to discern CIB (Coordinated Inauthentic Behavior) online.

EwnetCheck colleagues participated in this training. We had a good time.

Thank you to the organizers and experts for sharing their knowhow.

15/06/2021

ይህን ያውቁ ኖሯል?

በመራጮች ምዝገባ ወቅት የተመዘገቡ ዜጎች በቦርዱ በተወሰነው የድምፅ መስጫ ቀን የተመዘገቡበት የምርጫ ጣቢያ በመሄድ ድምፅ ይሰጣሉ፡፡ የድምፅ አሰጣጥ ሂደቱ የሚከተለውን ይመስላል:

• የድምፅ መስጠት ሂደት በሁሉም የምርጫ ጣቢያዎች በተመሳሳይ ሰዓት ይጀመራል፡፡

• በዕለቱም መራጮች በምርጫ ጣቢያው ከጠዋቱ 12፡00 ጀምሮ እከስ ምሽት 12፡00 ሰዓት ድረስ በመገኘት ድምፃቸውን መስጠት ይችላሉ፡፡ በነዚህ ሰዓታት ከአቅም በላይ በሆነ ምክንያት ካልሆነ በስተቀር ያልተቋረጠ የድምፅ መስጠት ተግባር ይከናወናል፡፡

• ማንኛውም መራጭ ዜጋ በምርጫ ጣቢያው በአካል በመገኘት በሙሉ ነፃነት ድምፅ ይሰጣል፡፡

• ማንኛውም ዜጋ ድምፅ መስጫ ወረቀቱ ላይ ከሚመርጠው እጩ አጠገብ ባለው ቦታ ማንኛውንም (ኤክስ፣ ራይት ወይም የጣት አሻራ) ምልክት በማድረግ ድምፁን ይሰጣል፡፡

• ማንኛውም ድምፅ የሚሰጠው በሚስጥር ነው፡፡ ድምፅ ለመስጠት እገዛ የሚያስፈልጋቸው ድምፅ ሰጪ ዜጎች ድጋፍ የሚሰጣቸውን ሰው ይዘው የሚስጥር ድምፅ መስጫ ውስጥ መገኘት ይችላሉ፡፡ ድጋፍ ሰጪው መብቱ በህግ ያልተገደበ መሆን አለበት፡፡

ማንኛውም መራጭ ድምፅ መስጠት የሚችለው:

• በመራጭነት በተመዘገበበት የምርጫ ጣቢያ ላይ፣

• የመራጮች መታወቂያ ካርድ ሲኖረው፣

• በመራጮች መዝገብ ላይ ሰፍሮ ሲገኝ፣

• እንዲሁም ድምፅ ያልሰጠ መሆኑ ሲረጋገጥ ብቻ ነው፡፡

• ማንኛውም መራጭ ድምፅ ለመስጠት በተገኘበት ምርጫ ጣቢያ ላይ ይዞ የተገኘውን የማንነት መግለጫ ሰነዶች በጣቢያው ላይ በሚገኙ የምርጫ አስፈጻሚዎች ድምፅ እንዲሰጥ መፍቀዳቸውን ማጣራት ይችላሉ፡፡

• አካል ጉዳተኞች፣ አረጋዊያን፣ ህጻናትን የያዙ ወላጆች እና ነፍሰ ጡሮች በምዝገባም ሆነ በድምፅ አሰጣጥ ሂደት ቅድሚያ ይሰጣቸዋል፡፡

ድምፅ የተሰጠባቸው ወረቀቶች ከሚከተሉት በአንዱ ምክንያት ዋጋ አልባ ሊሆኑ ይችላሉ:

• የመራጩ ማንነት በስም የተገለፀ ከሆነ፣

• ለምክር ቤቱ መምረጥ ከሚቻለው እጩዎች ቁጥር በላይ ምልክት የተደረገበት ከሆነ፣

• መራጩ ማንን እንደመረጠ መለየት የሚያስቸግር ከሆነ፣

• ሕጋዊ የድምፅ መስጫ ወረቀት ያልሆነ ወይም በምርጫ ጣቢያው ያልተሰራጨ የድምፅ መስጫ ወረቀት ሆኖ ከተገኘ፡፡

ምንጭ: የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ

     የ Ewnet Check የደቡብ ሱዳን አጋር 211 Check አዲስ ሪፖርት : "ደቡብ ሱዳን በምስራቅ አፍሪካ ቀጠና ውስጥ በጣም ውዱ የቤት ውስጥ የኤሌክትሪክ ክፍያ ያለባት ሀገር ናት፡...
16/05/2021


የ Ewnet Check የደቡብ ሱዳን አጋር 211 Check አዲስ ሪፖርት :
"ደቡብ ሱዳን በምስራቅ አፍሪካ ቀጠና ውስጥ በጣም ውዱ የቤት ውስጥ የኤሌክትሪክ ክፍያ ያለባት ሀገር ናት፡፡ ኢትዮጵያ ደሞ በጣም ዝቅትኛው፡፡"
https://211check.org/south-sudan-leads-the-east-african-region-in-electricity-charges/

Author: Emmanuel Bida – Associate Editor A new 211 Check report has revealed South Sudan in the East African region the country with most expensive domestic electricity charges. The statistics unveiled Juba Electricity Distribution Company (JEDCO) as the lead company with the highest electric fee ...

በማህበራዊ ሚዲያ ላይ መነጋገሪያ የሆነዉ የሰላም ሚኒስትር ተቋም ሰራተኞች ተነሱት የተባለዉ ፎቶ ምን ያህል እዉነት ነዉ...? በእዉነት ቼክ የቀረበበማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ እየተዘዋወረ የሚገ...
22/04/2021

በማህበራዊ ሚዲያ ላይ መነጋገሪያ የሆነዉ የሰላም ሚኒስትር ተቋም ሰራተኞች ተነሱት የተባለዉ ፎቶ ምን ያህል እዉነት ነዉ...?

በእዉነት ቼክ የቀረበ

በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ እየተዘዋወረ የሚገኘዉ ፎቶ ሚኒስትሩን ብሎም የመግንስት ተቋማትን ስራ ለማጠልሸት የታሰበ ነዉ " የሰላም ሚኒስትር"

በትላንትናዉ ዕለት በቀን 13/2013 ዓ.ም በማህበራዊ ሚዲያ ሲዘዋወር የነበረዉ ፎቶ የሰላም ሚኒስትር ወ/ሮ ሙፈሪያት ካሚልን ጨምሮ በዉስጡ የሚሰሩ የተቋሙ ሰራተኞች በአንድ ላይ በሰልፍ መልክ በመያዝ አንዱ የአንዱን ትገሻ ሲያሽ እና እንቅስቃሴ ሲያደርጉ የሚያሳይ ነበር።

እጅግ ብዙ ተከታይ ያላቸዉ የፌስቡክ ገፆች አክቲቪስት ስዮም ተሾመ ሙክታሮቪችን ጨምሮ ሌሎችም የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች ፎቶዉን ሲቀባበሉት ዉለዋል።

በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ የተለቀቀዉ ፎቶ በተመለከተ የተሰራጨዉ ፅሁፍ

https://www.facebook.com/100001779897567/posts/3763782950357664/?app=fbl

https://www.facebook.com/1427051338/posts/10218596319845668/?app=fbl

የሰላም ማኒስትር ጉዳዮን ለማጥራት ትላንት ማምሻዉን ላይ በማህበራዊ ድረገፃቸዉ ባሰፈሩት ፅሁፋቸው በብዙዎች ዘንድ እየተዘዋወረ የሚገኘዉ ምስዕል በ 2012 ዓ.ም ሚኒስትር መስሪያ ቤቱ ባዘጋጀዉ የእቅድ ግምገማ መርሃግብር ላይ ከነበረዉ የስልጠና ፕሮግራም ላይ የተወሰደ እንጂ የትላንት ወይም የቅርብ ጊዜ አይደለም ሲል አስነብቧል።


ይህን ተከትሎ በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ እየተዘዋወረ የሚገኘዉ ፎቶ ሚኒስትሩን ብሎም የመግንስት ተቋማትን ስራ ሆን ተብሎ ለማጠልሸት የተሰራ እንደሆነ እና ሚኒስተሩ ከአዉድ ዉጪ የሆነን ምስዕል ማህበረሰብን ለማወናበድ በመጠቀማቸዉ የመረጃ ነፃነት አዋጅ ከቆመለት ዓላማ የሚፃረር በመሆኑ ግለሰቦቹን ተጠያቂ አደርጋለሁ ብሏል።

የሰላም ሚኒስተር ፅሁፍን ለመመልከት
https://www.facebook.com/178060545709281/posts/1738407563007897/?app=fbl

ምስዕሉ መቼ እና የት እንደተነሳ እዉነት ቼክ ለማጣራት የጎግል ሪቨርስን ተጠቅሞ ምልከታ ቢያደርግም ምስዕሉ መቼ እንደተነሳ በእዉን የሚታወቅ ነገር እንደሌለ መመልከት ችሏል።


ምንጭ አዉነት ቼክ

የ2013 ዓ.ም. አገር አቀፍ ምርጫ   #በምርጫብቻ     Join   on Telegram here:https://t.me/joinchat/Rng9EEVsRKO_xi-cData: National Electo...
17/04/2021

የ2013 ዓ.ም. አገር አቀፍ ምርጫ
#በምርጫብቻ
Join on Telegram here:
https://t.me/joinchat/Rng9EEVsRKO_xi-c

Data: National Electoral Board of Ethiopia- NEBE -የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ

በአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር የሚገኙ ምርጫ ጣቢያዎች በጎግል ካርታ ላይ ይህንን ይመስላሉ።ካርታውን በመጠቀም በአቅራቢያዎ ያለ ምርጫ ጣቢያ በመሄድ የመራጭነት ካርድዎን ይውሰዱ! ለሌሎችም መ...
13/04/2021

በአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር የሚገኙ ምርጫ ጣቢያዎች በጎግል ካርታ ላይ ይህንን ይመስላሉ።
ካርታውን በመጠቀም በአቅራቢያዎ ያለ ምርጫ ጣቢያ በመሄድ የመራጭነት ካርድዎን ይውሰዱ! ለሌሎችም መረጃውን ያጋሩ፡፡
#በምርጫብቻ https://www.google.com/maps/d/u/0/viewer?hl=en&ll=9.046108123489669%2C38.71187126984384&z=13&mid=1LtZfDcJ8XMQiI3y8P-WmmL8QdEAdUOkg

Via NEBE

https://t.me/joinchat/Rng9EEVsRKO_xi-c

የቴሌግራም መተግበሪያ  በ12ተኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውስጥ ሚናዉ ምን ነበር..?የፈተናዎች ኤጀንሲ የህዝብ ግንኙነት የሆኑት አቶ ረዲ ሺፋ ቃለ ምልልስ አድርገናል። ሊንኩን ተጭነው ያንብቡht...
11/04/2021

የቴሌግራም መተግበሪያ በ12ተኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውስጥ ሚናዉ ምን ነበር..?

የፈተናዎች ኤጀንሲ የህዝብ ግንኙነት የሆኑት አቶ ረዲ ሺፋ ቃለ ምልልስ አድርገናል።
ሊንኩን ተጭነው ያንብቡ
https://t.co/dipuz5Mwdd?amp=1

(በእዉነት ቼክ የቀረበ)

ፌስቡክ ግብጽን ጨምሮ በ11 ሀገራት ሀሰተኛ ዘመቻ የከፈቱ አካውንቶች ዘጋhttps://t.co/cQnwyn0kb1?amp=1
09/04/2021

ፌስቡክ ግብጽን ጨምሮ በ11 ሀገራት ሀሰተኛ ዘመቻ የከፈቱ አካውንቶች ዘጋ
https://t.co/cQnwyn0kb1?amp=1

በማህበራዊ ሚዲያ ላይ የሀሰተኛ መረጃዎችን ሲያሰራጩ የነበሩ ገፆች መታገዱ ተሰምቷል።

በአክሱም አቅራቢያ ማህበረ ዴጎ ኮረብታ ላይ የተፈጠረው ምን ነበር? Bellingcat የተሰኘ የመረጃ አጣሪ ተቋም ለBBC  የሰራው ማጣራት ይህን ይመስላል፡፡https://youtu.be/-fXB...
09/04/2021

በአክሱም አቅራቢያ ማህበረ ዴጎ ኮረብታ ላይ የተፈጠረው ምን ነበር? Bellingcat የተሰኘ የመረጃ አጣሪ ተቋም ለBBC የሰራው ማጣራት ይህን ይመስላል፡፡
https://youtu.be/-fXBuoJxZ5Y

For the first time, we've located the precise spot of a recent mass killing of civilians in Tigray based on videos that surfaced online this month.

   የፌስቡክ ተጠቃሚዎችን በማጭበርበር እና በማሳሳት አላማ ያደረጉ ማስታወቂያዎች ተበራክተዋል! በኢትዮ ቴሌኮም ስም ተመሳስሎ የፌስቡክ ማስታወቂያ ተጠቅሞ የተለቀቀው መረጃም በሽልማት መልክ ...
29/03/2021


የፌስቡክ ተጠቃሚዎችን በማጭበርበር እና በማሳሳት አላማ ያደረጉ ማስታወቂያዎች ተበራክተዋል!

በኢትዮ ቴሌኮም ስም ተመሳስሎ የፌስቡክ ማስታወቂያ ተጠቅሞ የተለቀቀው መረጃም በሽልማት መልክ የቀረበ ማታለያ ሆኖ አግኝተንዋል፡፡

እዉነት ቼክ ባደረገዉ ማጣራት የዚህ ድረገፅ አላማዉ ደግሞ የተጠቃሚውን አካውንት Hack/Phish ለማድረግ ሲሆን ፌስቡክ አመሳስሎ በመስራት እና እንዲጠቀሙ በማድረግ የይለፍ ቃል ለመዝረፍ ያለመ መሆኑን በዳሰሳችን ተመልክተናል።

 #የእዉነት እናት ፓርቲ የገንዘብ   #ድጎማ የገዢዉን ፓርቲ  #ጠይቋል...?(በእዉነት ቼክ የቀረበ)በትላንትናዉ ዕለት ማለትም በቀን 18/2013 ዓ.ም  ከአንድ ሚሊዮን አምስት መቶ ሺህ በ...
28/03/2021

#የእዉነት እናት ፓርቲ የገንዘብ #ድጎማ የገዢዉን ፓርቲ #ጠይቋል...?

(በእዉነት ቼክ የቀረበ)

በትላንትናዉ ዕለት ማለትም በቀን 18/2013 ዓ.ም ከአንድ ሚሊዮን አምስት መቶ ሺህ በላይ የፌስቡክ ተከታይ ያለዉ ጨምሮ የተለያዩ የማህበራዊ ድረገጽ ተጠቃሚዎች ሲቀባበሉት የነበረዉ እና በቀን 15/2013 ዓ.ም የእናት ፓርቲ ለቅስቀሳ የሚዉል #የአምስት ሚሊዮን ብር ድጎማ ከብልፅግና ፓርቲ መጠየቁን በማስመሰል የተፃፈ ደብዳቤ #የሀሰት እንደሆነ እዉነት ቼክ ባደረገዉ ማጣራት አረጋግጧል።

ዘ ሀበሻ ይህን ደብዳዴ ከድረገፁ ላይ ቢያጠፋም እኛ ግን Screenshot አድርገን አያይዘናል።

በዚህ ዙሪያ እራሳችን ካደረግነዉ ማጣራት ዉጪ የፓርቲውን አመራሮች አግኝተን ስለ ጉዳዮ ጠይቀናቸዋል።

በጉዳዩ ላይ ከእናት ፓርቲ ዋና ፀሐፊ ከአቶ #ጌትነት ጋር ባደረግነዉ አጠር ያለች የስልክ ቃለ ምልልስ ተከታዩን ብለዉናል።

" #ትላንት 18/2013 ዓ.ም የወጣዉ እና እናት ፓርቲ ፅፎታል የተባለዉ ደብዳቤ ፍፁም #ዉሸት ነዉ።

ይህን መረጃ በቀዳሚነት ያወጣዉ ዘ ሀበሻ የተባለዉ የፌስቡክ ፔጅ ሲሆን እኛም #በድረገፃችን መረጃዉ የሀሰት እንደሆነ ተናግረናል።

#የእናት የፓርቲን ስም ለማጠልሸት እየተጠቀሙበት ያሉት አንዳንድ #ሀላፊነት የማይሰማቸዉ ግለሰቦች እና ጦማሪያን ከድርጊታቸው እንዲቆጠብም ዋና ፀሐፊዉ ነግረውናል ።

አቶ ጌትነትም አክለዉ ዛሬም በድጋሚ የፓርቲውን ማህተም በማስመሰል እየወጣ ያለዉ መረጃ የዉሸት ሲሆን የእናት የፓርቲን አቋም የሚፃረር ተግባር ነዉ ብለዋል"።

ከገዢዉ ፓርቲ እና ከኢዜማ ቀጥሎ ብዙ እጩዎችን በማስመዝገብ በሶሶተኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠዉ ፓርቲዉ እንደሆነ በዳሰሳችን ተመልክተናል።

እናት ፓርቲን በማህበራዊ ሚዲያዎች ለማግኘት :-

በፌስቡክ ፡
http://www.facebook.com/EnatParty

እዉነት ቼክን ለማግኘት 👇

https://facebook.com/EwnetCheck

https://twitter.com/EwnetCheck

T.me/EwnetCheck

  ከስር በምስዕሉ የምትመለከቱት እና በማህበራዊ ድረገፅ /ፌስቡክ / ላይ በኢትዮጵያ የተከሰተ ተደርጎ ሲዟዟር የነበረዉ ፎቶ የሀሰት እንደሆነ እዉነት ቼክ ጎግል ሪቨርስን ተጠቅሞ አረጋግጧል።...
26/03/2021



ከስር በምስዕሉ የምትመለከቱት እና በማህበራዊ ድረገፅ /ፌስቡክ / ላይ በኢትዮጵያ የተከሰተ ተደርጎ ሲዟዟር የነበረዉ ፎቶ የሀሰት እንደሆነ እዉነት ቼክ ጎግል ሪቨርስን ተጠቅሞ አረጋግጧል።

ምስዕሉ ወደ በደቡብ ሱዳን የሚያመራ ሲሆን 3.6 ሚሊዮን ህፃናት እና ታዳጊዎች በ August 4,2011 በተከተሰተዉ ጦርነት እና ድርቅ ለርሃብ የተጋለጡ እና ከቤት ንብረታቸዉን የተፈናቀሉ ናቸዉ ይህ ማለት ከ ዛሬ አስር ዓመት በፊት መሆኑ ነዉ።

ሌላኛዉ ፎቶ ደግሞ በየመን በተከሰተው ጦርነት ለርሃብ እና ለችግሮች የተጋለጡ ህፃናት ልክ እንደ ሱማሊያ ተመሳሳይ ሁኔታ የተፈጠረበት ነዉ።

ነገር ግን በሀገራችን ኢትዮጵያ በተለይ በአማራ ክልሎች በተከተሰቱ ጦርነት ዜጎቻችን በእንዲህ አይነት መልኩ ለርሃብ ተጋልጠዋል ተብሎ የተሰራጨው ፎቶ የሃሰት እንደሆነ እዉነት ቼክ አረጋግጧል።

ምንጭ

     በባራክ ኦባማ ፋዉንዴሽን ስም ተመሳስሎ የተከፈተዉ ሀሰተኛ የፌስብክ አካዉንት አላማዉ ምንድነዉ..?(በእዉነት ቼክ የቀረበ)በማህበራዊ ሚዲያ  በተለይ በፌስቡክ መተግበሪያ ላይ መልኩን ...
20/03/2021



በባራክ ኦባማ ፋዉንዴሽን ስም ተመሳስሎ የተከፈተዉ ሀሰተኛ የፌስብክ አካዉንት አላማዉ ምንድነዉ..?

(በእዉነት ቼክ የቀረበ)

በማህበራዊ ሚዲያ በተለይ በፌስቡክ መተግበሪያ ላይ መልኩን እየቀያየረ ተጠቃሚዉን ማወናበዳቸዉን ቀጥለዋል።

በዚህ ሁለት ቀን ዉስጥ ደግሞ ልክ እንደሌሎቹ በተመሳሳይ የፌስብክን ስፖንሰር (ማስታወቂያ) ተከፍሎ የተለያዩ #አሳሳች የሆኑ እና ከእዉነት የራቁ መልዕክቶች አሁን ላይ እየተስተዋወቁ ይገኛሉ።

"በባራክ ኦባማ ፋዉንዴሽን" ስም የተከፈተዉ እና ነፃ የትምህርት እድሎችን ( Scholarship) እንደሚሰጡ በመግለፅ በእዚህም አብዛኛው የፌስቡክ ተጠቃሚ በማወናበድ ላይ እንዳሉ እዉነት ቼክ ባደረገዉ ቅኝት ታዝቧል።

ከወራት በፊት የተከፈተዉ እና ሙሉዉን የገንዘብ ወጪ በፋዉንዴሽኑ ይሸፈናል በሚል እየተስተዋወቀ የሚገኘዉ እና በተለይ ደግሞ ከፅሁፍ ስር ለመታመን የተለያዩ ሊንኮችን አስቀምጠዋል ። ይህ የሀሰተኛዉ የፌስብክ ገፅ በስፖንሰር መልክ ቀርቦ ብዙ ላይክ እና ሼሮችን እንዲሁም ኮሜንቶች(አስተያየቶች) እንዳለዉ ተመልክተናል።

ሀሰተኛዉ ገፅ (Fake account)

https://www.facebook.com/103761141786951/posts/106962081466857/?app=fbl

"ባራክ ኦባማ ፋዉንዴሽን የተቋቋመዉ በደቡብ ቺጋጎ ከተማ ሲሆን 7 የት የአሜሪካ ዜግነት ያላቸዉ ግለሰቦች ተቋቁሟል አላማዉ ደግሞ እንዲህ ቀርቧል።

" The Obama Foundation is a living, working start-up for citizenship — an ongoing project for us to shape, together, what it means to be a good citizen in the 21st century. The Foundation is based on the South Side of Chicago, and we will have projects all over the city, the country, and the world. To help us get started, we would love to hear from you. Send us your ideas, your hopes, your dreams about what we can achieve together. Tell us about the people who inspire you and the organizations whose work you admire." ይህ መሆኑን አረጋግጠናል ትክክለኛዉ የፌስቡክ ፔጅ ደግሞ ከስር አስቀምጠናል።

Real Account
http://www.facebook.com/567101470157212/posts/1566005513600131/?app=fbl

ምንጭ:

   የፌስቡክ ተጠቃሚዎችን በማጭበርበር እና በማሳሳት አላማ ያደረገዉ ማስታወቂያ..?በኢትዮ ቴሌኮም ስም ተመሳስሎ የፌስቡክ ማስታወቂያ ተጠቅሞ የተለቀቀው መረጃም በሽልማት መልክ የቀረበ ማታለ...
16/03/2021



የፌስቡክ ተጠቃሚዎችን በማጭበርበር እና በማሳሳት አላማ ያደረገዉ ማስታወቂያ..?

በኢትዮ ቴሌኮም ስም ተመሳስሎ የፌስቡክ ማስታወቂያ ተጠቅሞ የተለቀቀው መረጃም በሽልማት መልክ የቀረበ ማታለያ ሆኖ አግኝተንዋል፡፡

በተመሳሳይም በኢትዮ ቴሌኮም ስም ተመሳስሎ የተከፈተዉ እና ተጠቃሚዉን በማጭበርበር ልክ እንደ ሚሰንጀር app የፌስቡክ ማስታወቂያን በመጠቀም የተለያዩ #ሽልማቶችን ከተጨማሪ ስጦታዎች ጋር እንሸልማለን በማለት የማጭበርበር ስራዎችን ተክነዉበት ይገኛሉ።

እዉነት ቼክ ባደረገዉ ማጣራት በግብፅ ሀገር ወደ ተመዘገቡ ድረገፅ የሚያመሩ ሊንኮች መመልከት ችለናል። የዚህ ድረገፅ አላማዉ ደግሞ የተጠቃሚውን አካውንት Hack/Phish ለማድረግ ሲሆን የፌስቡክ ሜሴንጀርን አመሳስሎ በመስራት እና እንዲጠቀሙ በማድረግ የተጠቃሚዉን የይለፍ ቃል (Password and username) በመዝረፍ ሙሉ ለሙሉ ለመቆጣጠር ያለመ መሆኑን በዳሰሳችን ተመልክተናል።

https://t.me/joinchat/Rng9EEVsRKO_xi-c

የፌስቡክ ተጠቃሚዎችን በማጭበርበር እና በማሳሳት አላማ ያደረገዉ ማስታወቂያ..?(በእዉነት ቼክ የቀረበ)በፌስቡክ ላይ በርከት ያሉ ተጠቃሚዎችን በማታለል  የተሰረዙ መልዕክቶችን እና የተለያዩ ...
13/03/2021

የፌስቡክ ተጠቃሚዎችን በማጭበርበር እና በማሳሳት አላማ ያደረገዉ ማስታወቂያ..?

(በእዉነት ቼክ የቀረበ)

በፌስቡክ ላይ በርከት ያሉ ተጠቃሚዎችን በማታለል የተሰረዙ መልዕክቶችን እና የተለያዩ ዘርፈ ብዙ ጥቅሞችን ለማግኘት አሁን እየተጠቀሙ የሚገኙትን ሚሴንጀር ወደ "Golden Messenger " ይቀይሩ በማለት የተዛባ ሊንክ በማስቀመጥ ወደ ሌላ የሃሰት የሆነ የፌስቡክ ድረገፅ ላይ እንዲዛወሩ ያደርጋል።

እዉነት ቼክ ባደረገዉ ማጣራት በግብፅ ሀገር ወደ ተመዘገቡ ድረገፅ የሚያመሩ ሊንኮች መመልከት ችለናል። የዚህ ድረገፅ አላማዉ ደግሞ የተጠቃሚውን አካውንት Hack ለማድረግ ሲሆን የፌስቡክ ሜሴንጀርን አመሳስሎ በመስራት እና እንዲጠቀሙ በማድረግ የተጠቃሚዉን የይለፍ ቃል (Password and username) በመዝረፍ ሙሉ ለሙሉ ለመቆጣጠር ያለመ መሆኑን በዳሰሳችን ተመልክተናል።

ይሄው ድረገጽ በኢትዮጵያ እና በፊሊፒንስ የፌስቡክ ተጠቃሚዎች ላይ ትኩረት በማድረግ እና በሁለቱም ቋንቋዎች ተመሳሳይ ቃላቶችን በመጠቀም እንዲሁም የፌስቡክ ማስታወቂያዎችን ( Sponsor) በመጠቀም አሳሳች መልዕክቶችን በማስተዋወቅ ላይ ይገኛል።

በአጠቃላይ በፈረንጆቹ ፌብራሪ 2021 ላይ በኢትዮጵያ የፌስቡክ ተጠቃሚ ቀጥር 928,000 (6%) ሲሆን በፊሊፒንስ ደግሞ 74 ሚሊዮን (93%) ነዉ። በአለም አቀፍ ደረጃ ደግሞ 2.7 ቢሊዮን የፌስብክ ተጠቃሚ እንዳለ በቅርቡ የወጡ መረጃዎች ያመላክታሉ።

Via T.me/EwnetCheck

ሁለቱ መሪዎች በደቡብ ሱዳን የአንድ ቀን ጉብኝት አድርገዋል? By Eyasu Zekariyasሁለቱ መሪዎች በደቡብ ሱዳን የአንድ ቀን ጉብኝት አድርገዋል ተብሎ የተሰራጨዉ መረጃ የሀሰት እንደሆነ...
13/03/2021

ሁለቱ መሪዎች በደቡብ ሱዳን የአንድ ቀን ጉብኝት አድርገዋል?

By Eyasu Zekariyas

ሁለቱ መሪዎች በደቡብ ሱዳን የአንድ ቀን ጉብኝት አድርገዋል ተብሎ የተሰራጨዉ መረጃ የሀሰት እንደሆነ ለእዉነት ቼክ በደረሱት መልዕክቶች ማረጋገጥ ችለናል

ሙሉዉን ያንቡብ 👇

http://bit.ly/3ewHLjG

Address


Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ewnet Check posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

  • Address
  • Alerts
  • Contact The Business
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share