ለድሽታ ግና በዓል አስተዋጽኦ ያበረከቱ ምስጋና የጂንካ ከተማ አስተዳደር ክቡር ከንቲባ አቶ ሲሳይ ጋልሺ አቀረቡ።
''ታላቁ ሩጫ ለድሽታ ግና ለሠላምና ለአንድነት እሮጣለሁ''
በሚል መሪ ቃል ፋን ኢትዮጵያ ከኣሪ ዞን አስተዳደር ጋር በጋራ በመተባበር የድሽታ ግና በዓልን ምክንያት በማድረግ የተዘጋጀ የ8 ኪ.ሜ የጎዳና ላይ ሩጫ ልጀምር ነው።
በፎቶ በጂንካ ከተማ መንግስት ኮሙኒኬሽን
ህዳር 28/2017
ጂንካ
ሚስ ድሽታ ግና የቁንጅናና ዲዛይን ውድድር ጀመረ
ዲሸታ ግና በዓል ምክንያት በማድረግ የቲክቶክ ውድድር መዘጋጀቱን የኣሪ ዞን መንግስት ኮሚኒኬሽን መምሪያ አሳወቁ።
ህዳር 14/2017 ዓ,ም
ጂንካ
ውድድሩ የድሽታ ግና በዓል እሴት የሚገልጽ ከ1ደቂቃ በላይ መሰራት እንዳለበት ተገልጿል ።
በውድድሩ 1ኛ የወጣ 20,000
2ኛ የወጣ 15,000
3ኛ የወጣ 10,000
[email protected] የኣሪ
ዞን የቲክቶክ አካውንትን ታግ መደረግ አለበት።
ውድድሩ ህዳር 29/04/2017 ከቀኑ 8:00 ይጠናቀቃል።
ህዳር 30/2017 በኣሪ ዞን ምክርቤት አዳራሽ ከ1-3 ለወጡ ሽልማት ይሰጣል።
የኤሶል ልዩ ሁለተኛ ደረጃ (አዳሪ) ትምህርት ቤት ተማሪዎችን ለመቀበል አስፈላጊውን ቅድመ_ዝግጅት ማጠናቀቁን የኣሪ ዞን ትምህርት መምሪያ ገለፀ ።
ህዳር 10/2017 ዓ.ም -ጂንካ
በኣሪ ዞን በጂንካ ከተማ አስተዳደር በጤናዳም 01 ከተማ ቀበሌ የፅዳት ዘመቻ በንቅናቄ ተካሄደ።
ህዳር 9/ 2017 ዓ.ም
ጂንካ
የዲሽታ ግና ዕሴት የሆነው አንዱ የፅዳትና ውቤት ፣ Bars's'i በቀለም የማስዋብ ፣ አካባቢን የማፅዳት ዘመቻ በወጣቶች በሴቶች ልማት ቡድን አደረጃጀት በነቅስ እየተከናወነ ይገኛል ።
የጂንካ ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ ዋና የመንግስት ተጠሪ አቶ ግርማ ገብሬ በቦታው ተገኝተው መልዕክት አስተላልፈዋል።
ከፊታችን ሎንጋ(ታህሳስ) 1 የሚከበረው የኣሪ ብሔረሰብ ዘመን መለወጫ አድስ ዓመት ዲሽታ ግና ዕሴቶች መሀከል አንዱ አከባቢ የማጽዳትና የማስዋብ Bars's'i ቀለም የመቀባት ስሆን በሁሉም አከባቢዎች መልካም የሆኑ እሴቶች ተጠናክረው ልቀጥሉ እንደምገባ አሳስበዋል።
በኣሪ ዞን የጂንካ ከተማ ከተማዋን ውብ ሳቢ እና ምቹ የማድረግ ሥራዎች አጠናክሮ ቀጥሏል ።
************
ህዳር 2/2017 ዓ.ም
ጂንካ ከተማ