06/01/2024
የብሔራዊነት ወርቃማ ትርክት ምሳሌ የሆነችው የሁላችንም ከተማ!!
ከተማችን በአዲስ መንፈስ ታድሳ፣ ብሩህ ተስፋ ሰንቃ የአፍሪካ መዲና የሆነች ሁሉ ሚናፍቃት የብዝሀነት ማዕከል ናት። እንደ ስሟ እያበበች ያለችው አዲስ አበባ የጀመረችውን የተስፋ ጉዞ አጠናክራ በመቀጠል የኗሪዎችን ሁለንተናዊ ችግሮቿን ፈታ ውጥን ትልሞቿን አሳክታ ያቀደችዉን ብልፅግና አሳክታ በፈጣን እድገት ላይ የምትገኝ ውብ ከተማ ናት።
ፓርቲያችን ሊገነባው ለሚፈልገው የብሔራዊነት ትርክት ቀደምት ምሳሌ የሆነች የብሔር የሀይማኖት፣ የሀሳብ ብዝሀነትን በውስጧ አቅፋ በፍቅር በሰላም እና በአንድነት የምታኖር መሰባሰቢያ አውዳችን ናት!!
በከተማችን በብልፅግና ፓርቲ የሚመራው መንግስት የተለያዩ ሰው ተኮር ተግባራትን እየተገበረ ፣ የተለያዩ የገበያ ማእከላት፣ ትምህርት ቤቶች፣ ሆስፒታሎች፣ የመመገቢያ ማእከሎች፣ የወጣቶችን ጥያቄ ለመመለስ የተለያዩ የወጣቶች ማእከሎች እና የተለያዩ ስታዲየሞች እየገነባ ይገኛል።
የከተማችን አስተዳደር የኑሮ ውድነትን ለመቀነስ የክ/ከተሞች የእሁድ ገበያን በማቋቋም ህብረተሰቡ በቀላል ዋጋ የግብርና እና የኢንዱስትሪ ምርቶችን እንዲሸምቱ እየተደረገ ያለው ተግባር የሚበረታታ ነው።
ይህ ተግባር ፓርቲያችን በምርጫ ወቅት ለዜጎች ቃል የገባውን ሁሉንም አንድ በአንድ እየመለሰ መሆኑን የሚሳይ ነው።
የለውጡ አመራር በከተማችን ባስመዘገበው ዘርፈ ብዙ ተግባራት በአለም መድረክ የተለያዩ እውቅናዎችን እና ሽልማቶችን እየተቸሩን ይገኛሉ።
ከተማችን ሁለንተናዊ ብልፅግናን አረጋግጣ ለሁሉም ነዋሪዎቿ ምቹ እና ሁሉም ዜጎች በእኩልነት የሚኖሩባት ህብረ-ብሔራዊ አንድነት የሰፈነባት ከተማ ሆኗ ትቀጥላለች።