Silte Media House SMH

  • Home
  • Silte Media House SMH

Silte Media House SMH Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Silte Media House SMH, News & Media Website, .

29/09/2023
26/09/2023
22/09/2023
18/09/2023

WOW WOW NICE WORKE!!

14/09/2023

በስልጤ ዞን ቅበት ከተማ ከተከሰተው ግጭት ጋር ተያይዞ በተለያዩ አካላት እየተሰጡ ያሉ መግለጫዎች ሀላፊነት የጎደላቸው ናቸው ሲሉ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ሸይክ ሙሐመድ ኸሊል ተናገሩ!

መስከረም 2/2016 ወራቤ (ስልጤ ዞን ኮሙኒኬሽን)

ከሰሞኑ በስልጤ ዞን ቅበት ከተማ አስተዳደር በግለሰቦች መካከል የተከሰተውንና በሂደት ተስፋፍቶ ቁሳዊና ሰብዓዊ ጉዳት ያስከተለውን ግጭት አስመልክቶ አንዳንድ የክርስትና እምነት ተቋማትና ግለሰቦች እየሰጧቸው ያሉ መግለጫዎች ሀላፊነት የጎደላቸውና ችግሩን ለመፍታት እየተሰሩ ባሉ እንቅስቃሴዎች ላይ ጫና የሚፈጥሩ መሆናቸውን የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት የእስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ፕሬዚደንት ሸይክ ሙሐመድ ኸሊል ተናግረዋል።

ችግሩ የተከሰተው በሴት ልጆች ላይ ድግምት ተሰርቷል በሚለው ምክንያት ቁርዓን በሞንታርቦ በመከፈቱና በሂደት ቁርዓን የተከፈተባቸው ስፒከሮችና ሞንታርቦዎች ይነሱ አይነሱ በሚል በጸጥታ ሀይሎችና በተወሰኑ ግለሰቦች መካከል በተፈጠረ አለመግባባት መሆኑን ያነሱት ሸይክ ሙሐመድ ኸሊል የከተማውን ማህበረሰቡን አብሮነት ለማናጋት ያሰቡ ውስን አካላት ይህን ግጭት ወደ ሌላ አቅጣጫ በመውሰድ በከተማዋ ላይ ቁሳዊና ሰብዓዊ ኪሳራ እንዲደርስ አድርገዋል ብለዋል።

ችግሩ ከተፈጠረበት እለት ጀምሮ እንደ ሙስሊም ተቋም መሪና እንደ አከባቢው ተወላጅ የሀገር ሽማግሌ ከጸጥታ አካላትና ከመንግስት መዋቅሩ ጋር በመሆን ግጭቱን ለማስቆም ሰፊ ስራ እየሰሩ ከተማውን በማረጋጋት ውስጥ መቆየታቸውን ያነሱት ሸይክ መሐመድ ከዚህ በተቃራኒ በአንዳንድ የክርስትና አባቶችና ተቋማት በኩል ግጭቱን አስመልክቶ ከእውነት የራቀ፣ የአከባቢውን ተጨባጭ ያላገናዘበ፣ በፍረጃ የተሞላና፣ ሀላፊነት የጎደለው ሁከት ቀስቃሽ መግለጫ መውጣቱን አንስተዋል።

አለመግባባቱ የተፈጠረው በቅበት ከተማ ውስጥ በተወሰኑ የማህበረሰብ አካላት መካከል ከመሆኑም በላይ የግጭቱ ዋነኛ ተጎጂ የእስልምና እምነት ተከታይ የማህበረሰብ ክፍሎችና የሙስሊሙ ተቋም ሆኖ ሳለ ችግሩን በክርስትና እምነት ላይ የተከፈተ ዘመቻ አድርጎ ማቅረብ የእስልምና እምነት ተከታዮችንና የስልጤን ህዝብ በሙሉ የማይገለጽ በመሆኑ ሌላ ግብ ያለው የሚመስል ጭፍን ውንጀላ መሆኑን ሸይክ መሐመድ ገልጸዋል።

ተከስቶ በነበረው ችግር የአመራር ቤቶችን ጨምሮ የእስልምናና የክርስትና እምነት ተከታይ ወገኖች መኖሪያ ቤቶች ለይ ጉዳት መድረሱን ፕሬዚደንቱ ያነሱ ሲሆን በሌላ በኩል የእስልምና እምነት ተከታይ የሆኑ ከአምስት በላይ ወጣቶች ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባቸው ሆስፒታል በህክምና ክትትል ላይ መሆናቸውንና አንድ ሙስሊም ወጣት ለሞት መዳረጉን አብራርተዋል።

ችግሩ ሲከሰት በየተኛውም የክርስትና እምነት ተከታይ ቤተ እምነት ላይ ጉዳት አለመድረሱንና በአንጻሩ በከተማው መሃል በሚገኘው የሙስሊም መስጂድ ላይ ጉዳት መድረሱን ፕሬዚደንቱ ገልጸዋል።

ይሁንና የተፈጠረው ችግር የእስልምና እምነት ተከታዮችንና የህዝቡን የዘመናት የአብሮነት ታሪክ ለማጥፋትና የአከባቢውን ስም ለማጠልሸት ያለሙ የጥቂት ግለሰቦች ተግባር መሆኑን በመገንዘብ ህብረተሰቡን አረጋግቶ ወደ ሰላም የማምጣት ስራ ላይ ትኩረት መደረጉን ፕሬዚደንቱ ጨምረው ገልጸዋል።

የከተማዋን ሰላም ለመመለስና ህዝቡን በማረጋጋት በኩል የአከባቢው ህብረተሰብ በከፍተኛ ሁኔታ ትብብር እያደረገ እንደነበር ፕሬዚደንቱ አንስተው በሌሎች የእምነት ተቋማት በኩል ለመፍትሄው ከመተባበር ይልቅ ግጭቱን ሀይማኖታዊ ቅርጽ ለማስያዝና ከእምነት ተቋም የማይጠበቅ ሀላፊነት የጎደለው ተግባር ተፈጽሟል ሲሉ ሸይክ መሐመድ ሂደቱን ኮንነዋል።

በስልጤ ህዝብ ውስጥ የክርስትና እምነት ተከታይ ወገኖች በተለያዩ በማህበራዊና በመንግስታዊ መዋቅሮች ላይ ህዝቡን እያገለገሉ ከመቆየታቸው ባሻገር ከስልጤ ህዝብ ጋር ተዋልደውና ተጋምደው ለዘመናት የመኖራቸውን ታሪክ ወደ ጎን በመተው ህዝቡን በገፊነት መፈረጅ በምንም መልኩ ተቀባይነት የሌለው ለሰላምና እርቅም እንቅፋት የሚሆን መሰረተ ቢስ ውንጀላ ነው ሲሉም ፕሬዚደንቱ አንስተዋል።

ለሀገርም ይሁን ለቅበትና አከባቢው ማህበረሰብ ሰላምና ደህንነት የሚያስብ አካል እስከ ቦታው ዘልቆ እውነትን በመረዳት ለአብሮነት መስራት አለበት ያሉት ሸይክ መሐመድ መንግስት በበኩሉ በየተኛውም እምነት ውስጥ የተሸሸጉ አጥፊዎችን ለይቶ ለህግ በማቅረብ ህግ የማስከበር ሚናውን እንዲወጣ ጠይቀዋል።

ግጭቱን አስመልክተው አንዳንድ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክሪስቲያን አባቶችና የስልጤ፣ ሀዲያና ከምባታ እንዲሁም የደቡብና ምዕራብ አፍሪካ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ አቡነ ሕርያቆስ ያስተላለፏቸው መልዕክቶችና የሰጧቸው መግለጫዎች የአከባቢውን የእስልምና እምነት ተከታዮችንና ህዝቡን ፈጽሞ የማይገልጹና ዘመናትን ከስልጤ ህዝብ አብሮ ለኖረው የክርስትና እምነት ተከታይ ወገናችን ምንም የማይፈይድና እርስ በርስ ጥርጣሬ የሚፈጥር ተገቢነት የሌለው ውንጀላ መሆኑ ታውቆ በአስቸኳይ እንዲታረምም የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የእስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ፕሬዚደንቱ ሸይክ ሙሐመድ ኸሊል አንስተዋል።

ጠቃሚ መልዕክት ለስልጢ ቅበት ነዋሪዎች በሙሉ፦የቅበት ከተማ ነዋሪዎች በሁሉም ሀይማኖቶች መካከል በመከባበርና እርስ በርስ ካላቸው ቁርኝት የተነሳ ወንድም ሙስሊም እህት ኦርቶዶክስ አባት ክርስ...
04/09/2023

ጠቃሚ መልዕክት ለስልጢ ቅበት ነዋሪዎች በሙሉ፦

የቅበት ከተማ ነዋሪዎች በሁሉም ሀይማኖቶች መካከል በመከባበርና እርስ በርስ ካላቸው ቁርኝት የተነሳ ወንድም ሙስሊም እህት ኦርቶዶክስ አባት ክርስቲያን እናት ሙስሊም ሆነው ተከባብረው የሚኖሩባት ከተማ ናት ይህንን ስል እንደ እስልምናም ቢሆን ከየትኛውም ሀይማኖት ጋር አብራቹ በጋራ ተከባብራቹ ኑሩ እንጂ ተነቋቆሩ የሚል ነገር ስላሌለ።

አሁን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እየተስተዋለ ያለው ነገር የቅበት ከተማ ነዋሪዎችን የሚመጥን ተግባር ባለመሆኑ አሳፋሪ ክስተት ሆኖ አግኝቼዋለውና አንዳንድ ይህን አጋጣሚ ተጠቅማቹ ለመጣቃቃት የምትሞክሩ አካላት እጃችሁን ሰብሰብ አድርጉና ልክ እንደ ከዚህ ቀደሙ ተከባብራቹ ተፈቃቅራቺ ለመኖር ሞክሩ።

አንድ ጊዜ የመጣ አውሎ ንፋስ የከዚ ቀደም አብሮነታቹን ሊሸረሽረው አይገባም ደግሞ ማነክ እዚህ ቅበት እየኖርክ ለአማራ ነፍጠኞች ሪፖርት ከምታደርገው እኩይ ተግባርክ ተቆጠብና የከዚ ቀደሟን ቅበትን ለመመለስ አግዝ አግዢ።

ለመተተኞች አላህ የእጃቸውን ይስጣቸውና የናንተም መቆራቆዝ የመተቸኞች ውጤት መሆኑን ተገንዝባቹ የሰው ህይወት ዋጋ መከፈል ስላሌለበት ነገሩን ሰከን ባለ መንፈስ ለማየት ሞክሩ።

ስልጤነት ያብብ ይለምልም ከፍ ይበል!!የስልጤ ቡና ምርት የጥራት ደረጃና ጣዕም ይፋ ሆነ!በል ማነክ የስልጤ አተካኖ በአፍሪካ ድንቃ ድንቅ ተመዘገበ የሚል ዜናን ስተሰማ የቅርብ ቤተሰበን በሞት...
02/08/2023

ስልጤነት ያብብ ይለምልም ከፍ ይበል!!

የስልጤ ቡና ምርት የጥራት ደረጃና ጣዕም ይፋ ሆነ!

በል ማነክ የስልጤ አተካኖ በአፍሪካ ድንቃ ድንቅ ተመዘገበ የሚል ዜናን ስተሰማ የቅርብ ቤተሰበን በሞት የተነጠቀ ሰው ይመስል ሙሾክን ያወረድክ የስልጤ ቡና በስልጤ ስም ለአለም አቀፍ ገበያ ቀረበ ሲባል መስማትክን እንዴት ትችለው ይሆን....!?

ለማንኛውም ተሞተም ተኖረ የኢፌድሪ ቡናና ሻይ ባለስልጣን የስልጤ ቡና ምርት የጥራት ደረጃና ጣዕም ውጤት ዛሬ ይፋ አድርጓል።

በዚሁ መነሻ ባለስልጣኑ በዛሬው ዕለት በአዲስ አበባ ከተማ ባካሄደው የውይይት መድረኩ ላይ የስልጤ ቡና የራሱ የሆነ ጣዕምና ብራንድ የክልልና ፌዴራል ቡናና ሻይ ባለስልጣን ዳይሬክተሮችና ሌሎች የዞንና የክልል ባለስልጣናት በተገኙበት ይፋ አድርጓል።

በአለም ገበያ በስሙ ተወዳዳሪ ለመሆን የስልጤ ቡና ጥራት ደረጃና ጣዕም ጣፋጭና ቸኮሌት ጣዕም እንዳለው ባለስልጣኑ በናሙና ውጤቱ ማረጋገጡን ተገልጿል።

መረጃወን ከስልጤ ዞን ኮምኒኬሽን አገኘነው!!

ልበ-ቀናውና ብርቱ፣ታታሪና ስራ ፈጣሪው ሬድዋን ከድር የፋሚሊ ጠቅላላ የብረታ ብረት፣ፈርኒቸር እና ቶርኖ ስራ ባለቤት በጎነት ለራስ የሚለው ብሂል በተግባር በማሳየትክ ከልብ እናመሰግናለን!!ፋ...
29/07/2023

ልበ-ቀናውና ብርቱ፣ታታሪና ስራ ፈጣሪው ሬድዋን ከድር የፋሚሊ ጠቅላላ የብረታ ብረት፣ፈርኒቸር እና ቶርኖ ስራ ባለቤት በጎነት ለራስ የሚለው ብሂል በተግባር በማሳየትክ ከልብ እናመሰግናለን!!

ፋሚሊ ጠቅላላ ብረታ ብረት እና ቶርኖ ስራ ወራቤ ከተማ ላይ ብቸኛው የቶርኖና ቅርጻ ቅርጽ ስራን የሚሰራ በብርቱውና በልበቀናው ሬድዋን ከድር ስራስኪያጅነት የሚመራ ለበርካታ ወጣቶች የስራ ዕድልን መፍጠር የቻለ ተቋም ነው።

ይህ ልበቀና ታታሪ ወጣት ሬድዋን ከድር በዛሬው ዕለት የስልጤ ዞን ስራ ዕድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዝ ልማት መምሪያ አስተባባሪነት "በጎነ ለኢትዮጵያ ከፍታ" በሚል መሪ ቃል በወራቤ ከተማ በክላስተር ማዕከል የችግኝ ተከላ እና የደም ልገሳ ፕሮግራም ላይ ወጣቱ የፋሚሊ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ባለቤትና ከሌሎች ልበቀናዎች ጋር በመሆን ከስጦታዎች ሁሉ ውድ ስጦታ የሆነውን ደም ሲለግስ ተመለከትኩኝ።

በወጣትነት ዕድሜ ለራሱ የስራ ፈጠራ ባለቤት ከመሆኑም ባለፈ ለሌሎች ለ12 ቋሚና ጊዜያዊ ወጣቶች የስራ ዕድልን መፍጠሩና ደስ የሚሉ የበጎ ስራዎችን ሲሰራ መመልከት በጎነት በወጣትነት ከማማርም በላይ እምር ያለ ነው አስብልኛልና ወንድም ሬድዋን በርታ ተበራታ እንላለን!!

ከላይ የተዘረዘሩትንና ሌሎች አገልግሎቶችን ማግኘት ሲፈልጉ፦
አድራሻ፦
ማምረቻ ቦታ፦ወራቤ ከተማ ክላስተር ማዕከል
መሸጫ ቦታ፦የሆሌ ሎጅን ተሻግሮ ኒማዛ ወንዝ ድልድይ አካባቢ በሚገኘው የማህበራት ምርት መሸጫ ህንጻ ያገኙታል
ሞባይል➠0912485666
➠➠➠➠0916839512
ወራቤ

08/07/2023

200ሺ ገብተናል🙌 አልሃምዱሊላህ

ውድ የወራቤ ቲዩብ ቤተሰቦች🧡
በእናንተ ጥረት እዚህ ደርሰናል እናመሰግናለን (ያሾክርናን)
ጉዞ ወደ Worabe Tv - ወራቤ ቲቪ
#ሽልማት👇
አስተያየታቹን፣ መልካም ምኞታቹን ኮሜንት ላይ አስቀምጡልን
ብዙ ላይክ ላገኙ 3 ኮሜንቶች "ሐረመይን ዲዛይን" የተጠበበት ሙሉ የስልጤ ባህላዊ ልብስ እንሸልማለን።

የወራቤ ቲዩብ ቤተሰብ ይሁኑ🧡
#ወራቤቲዩብ
YouTube: https://youtube.com/
Tiktok: tiktok.com/
Telegram: https://t.me/worabetube
Instagram: https://instagram.com/worabetube
Twitter: https://twitter.com/WorabeTube
Facebook: https://www.facebook.com/Worabetube/

03/07/2023

የስልማ ሪፎርም ጉዳይ በስልጤ ህዝብ ዘንድ ለብዙ ጊዜ ጥያቄው ሲነሳ የቆየ ጉዳይ በመሆኑ መስመር መያዙ ለብዙ የልማት ጥያቄዎቻችንን በየደረጃው ለመፍታት ያለው ፋይዳ ከፍ ያለ ነው!!

ቅን አሳቢው የሞሮኮ ብሄራዊ ቡድን ተጨዋች "ሃኪም ዚያች"የሞሮኮ ብሔራዊ ቡድን የፊት መስመር ተጫዋች ሀኪም ዚያሽ ከ 2015 የውድድር ዘመን ጀምሮ ለሀገሩ ግልጋሎት በሚሰጥበት ወቅት የሚያገኘ...
11/12/2022

ቅን አሳቢው የሞሮኮ ብሄራዊ ቡድን ተጨዋች "ሃኪም ዚያች"

የሞሮኮ ብሔራዊ ቡድን የፊት መስመር ተጫዋች ሀኪም ዚያሽ ከ 2015 የውድድር ዘመን ጀምሮ ለሀገሩ ግልጋሎት በሚሰጥበት ወቅት የሚያገኘውን የጥቅማ ጥቅም ክፍያ እንደማይቀበል ተገልጿል።

ሀኪም ዚያሽ ከ 2015 ጀምሮ ለሞሮኮ ብሔራዊ ቡድን ግልጋሎት በሰጥበት ወቅት ያገኘውን የጉርሽ ክፍያ በድምሩ 325,000 ዶላር አቅም ለሌላቸው ሞሮካዊያን እንደሚሰጥ ተዘግቧል።

09/12/2022
09/12/2022
ያረብ በስልጤዋ መዲና ወራቤ ከተማ ላይ ለሚገነባው ሂክማ ኢስላማዊ ዩኒቨርሲቲ ያልተገደበ ብር ለመስጠት ለመስጠት ኡኮ ነው ብር ሳይሆን ዶላር ዶላሩን በሀላሉ መንገድ ያ......ረብብብብብ!!!
09/12/2022

ያረብ በስልጤዋ መዲና ወራቤ ከተማ ላይ ለሚገነባው ሂክማ ኢስላማዊ ዩኒቨርሲቲ ያልተገደበ ብር ለመስጠት ለመስጠት ኡኮ ነው ብር ሳይሆን ዶላር ዶላሩን በሀላሉ መንገድ ያ......ረብብብብብ!!!

09/12/2022

ስልቶጲያ!ደስ ደስ እያለኝ ነው!

በስልጥኛ ምን ይባላል?
29/11/2022

በስልጥኛ ምን ይባላል?

"X-England star John Terry wearing Silte cultural scarff On Quatar"ኢትዮጵያዊው የስልጤ የባህል ስከርቭ ኳታር ደርሶ የቀድሞው የአለማችን ኮከብ የኢንግላ...
19/11/2022

"X-England star John Terry wearing Silte cultural scarff On Quatar"

ኢትዮጵያዊው የስልጤ የባህል ስከርቭ ኳታር ደርሶ የቀድሞው የአለማችን ኮከብ የኢንግላንድ እና የቼልሲ ተጨዋች ጆን ቴሪ እጅ ገብቷል

በተጨማሪም የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት አቶ ኢሳያስ ጂራን ጨምሮ የተለያዩ ታዋቂ ሰዎች በባህል ልብሳችን ደምቀዋል።

ዶክተር ኢንጂነር ተውፊቅ ጀማልና በአለም አቀፍ መድረክ የስልጤ ባህልን ከማስተዋወቃቸውም ባለፈ ስልጤ ከዞኑና ከሀገሩ አልፎ በውጪው አለምም ኩሩና በሀገራችን ውስጥ ከሚገኙ ህዝቦች መካከል የታላላቅ ሀገራዊ ታሪኮች ባለቤት መሆኑንም እንደሚያስተዋውቁ እሙን ነው።

ዶክር ያሾክርናን!ሹክረን ዶክተር ተውፊቂያ!!

ይበል የሚያሰኝ ተግባር ነው።የስልጤ ዞን ግብርና መምሪያ በዞኑ ገሚገኙ በግብርናው ኢንቨስትመንት ከተሰማሩ ኢንቬስተሮች ጋር በመሆን ባለ 120 cc የፈረስ ጉልበትና 75 cc የፈረስ ጉልበት ...
07/11/2022

ይበል የሚያሰኝ ተግባር ነው።

የስልጤ ዞን ግብርና መምሪያ በዞኑ ገሚገኙ በግብርናው ኢንቨስትመንት ከተሰማሩ ኢንቬስተሮች ጋር በመሆን ባለ 120 cc የፈረስ ጉልበትና 75 cc የፈረስ ጉልበት የሆኑ New Juhn Deree የሚባሉ 16 ትራክተሮችን ገዝቶ አስገብቷል።

እነዚህ ትራክተሮች ወደ ስራ ሲገቡ የዞኑን የግብርናውን ዘርፍ አንድ ደረጃ ከፍ ያደርጋሉ ተብሎም ይታመናል።

እነዚህ 16 ትራክተሮች ከ71 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ የተደረገባቸው እንደሆነም ከውስጥ አዋቂዎች መረጃውን ማግኘት ችለናል በርቱ ተበራቱ ለማለት ወደድን!!

"ሙዚቃ የአለም ቋንቋ" የሚለውን አባባል ትክክለኛነት እንድንመሰክር ያደረገው ታላቁ የጥበብ ሰው አሊ መሀመድ ቢራ ከዚህ አለም በሞት ተለየ።የኦሮምኛ ሙዚቃ ንጉሱ ዶ/ር አርቲስት አሊ መሀመድ ...
07/11/2022

"ሙዚቃ የአለም ቋንቋ" የሚለውን አባባል ትክክለኛነት እንድንመሰክር ያደረገው ታላቁ የጥበብ ሰው አሊ መሀመድ ቢራ ከዚህ አለም በሞት ተለየ።

የኦሮምኛ ሙዚቃ ንጉሱ ዶ/ር አርቲስት አሊ መሀመድ ቢራ በትላንትናው ዕለት ወደማይረው አኼራ ሄዷል።

አላህ ጀነተል ፊርደውስን ይወፍቀው!!

የኢትዮጵያ መንግሥት በአፍሪካ ኅብረት አማካይነት ደቡብ አፍሪካ ውስጥ ለሚካሄደው የሰላም ድርድር የቀረበለትን ግብዣ መቀበሉን አስታወቀ።በሰሜን ኢትዮጵያ የሚካሄደውን ጦርነት ለማብቃት እንዲቻል...
05/10/2022

የኢትዮጵያ መንግሥት በአፍሪካ ኅብረት አማካይነት ደቡብ አፍሪካ ውስጥ ለሚካሄደው የሰላም ድርድር የቀረበለትን ግብዣ መቀበሉን አስታወቀ።

በሰሜን ኢትዮጵያ የሚካሄደውን ጦርነት ለማብቃት እንዲቻል የአፍሪካ ኅብረት የኢትዮጵያ መንግሥትን እና የትግራይ ኃይሎችን ድርድር እንዲጀምሩ ባለፈው ሳምንት ማብቂያ ላይ ነበር ጥሪ ያቀረበው።

መንግሥት በኮሙኒኬሽን አገልግሎት በኩል የአፍሪካ ኅብረት የሰላም ንግግሩን የሚመሩ አካላትን፣ቀንና ስፍራን አሳውቆ የሰላም ውይይቱ እንዲጀመር ይፋዊ ጥሪ ማቅረቡን አረጋግጧል።

የአፍሪካ ኅብረት ግብዣ የኢትዮጵያ መንግሥት ከዚህ በፊት ያቀረባቸውን አቋሞች የጠበቁ ናቸው በማለት፤ንግግሩ በአፍሪካ ኅብረት አደራዳሪነት ብቻ እንዲሆን እና ያለ ቅድመ ሁኔታ እንዲደረግ መንግሥት አቋሙን ሲገልጽ መቆየቱን አመልክቷል።ስለዚህም መንግሥት ግጭቱን ለመፍታት ሲወስዳቸው የቆዩትን ሁሉንም ዓይነት የመፍትሔ እርምጃዎች አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቋል።

በተመሳሳይ የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የብሔራዊ ደኅንነት አማካሪ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን በትዊተር ገጻቸው ላይ እንዳሰፈሩት የኢትዮጵያ መንግሥት የሰላም ንግግር ጥሪውን መቀበሉን ገልጸዋል።
Via@bbc amharic

የሀዲያ ህዝብ የዘመን መለወጫ የ"ያሆዴ" ዋዜሜ አከባበር ላይ የስልጤ ዞን ባህል ቡድን ፈርጦች ውስጥ አንዱ የሆነው አብዱ ከድር (አብዱ ሌሌን) በፎቶ
23/09/2022

የሀዲያ ህዝብ የዘመን መለወጫ የ"ያሆዴ" ዋዜሜ አከባበር ላይ የስልጤ ዞን ባህል ቡድን ፈርጦች ውስጥ አንዱ የሆነው አብዱ ከድር (አብዱ ሌሌን) በፎቶ

በየትኛውም መንገድ ህዝባችንን ይጠቅማሉ ብለን የምናስባቸውን አስተያየቶች መሰንዘር የሰጠነው አስተያየት በተለያየ መልኩ ተቀባይነት ባይኖረውም እጅግ ጠቃሚ መሆኑ ይሰማኛል።ለዚህች ሀሳቤ መነሻ ...
23/09/2022

በየትኛውም መንገድ ህዝባችንን ይጠቅማሉ ብለን የምናስባቸውን አስተያየቶች መሰንዘር የሰጠነው አስተያየት በተለያየ መልኩ ተቀባይነት ባይኖረውም እጅግ ጠቃሚ መሆኑ ይሰማኛል።

ለዚህች ሀሳቤ መነሻ የሆነኝ ቁምነገር ቢኖር ወንድማችን አ/ማሊክ ጀማል የወራቤ ከተማ አስተዳደር የህንፃ ግንባታ ቦታን መነሻ አድርጎ ከህንጻው ደረጃ አንጻር በየትኛውም መልኩ ህንጻውን ሊመጥን በሚችል ቦታ ቢሰራ ብሎ ያቀረበው አስተያየት ነውና ወንድሜ ክበርልኝ!!

አረ ይሄ ሰውዬ ዳዒ ነበርኩኝ ለማለት ትንሽ ነው ኡኮ የቀረው፦ጁዝ የሚለውን ጁስ ብሎ እየተናገረ 30 ጁዙን ጨርሼ አሰጋጅም ነበርኩኝ ብሎን አረፈው ኡኮ።አረ ወገን የዚህን ነቢይ አብድልቃድር ...
18/09/2022

አረ ይሄ ሰውዬ ዳዒ ነበርኩኝ ለማለት ትንሽ ነው ኡኮ የቀረው፦ጁዝ የሚለውን ጁስ ብሎ እየተናገረ 30 ጁዙን ጨርሼ አሰጋጅም ነበርኩኝ ብሎን አረፈው ኡኮ።

አረ ወገን የዚህን ነቢይ አብድልቃድር ነኝ ባዮችና መሰሎቻቸው የሚዘባርቁትን ነገር አንድ የሚል አካልም ይሁን መዋቅር የለምን?
የኻላ ኃላ ግን ውጤቱ አስደሳች አይመስለኝምና ከመተቸት ይልቅ ምንም ይሁን ምን የየራሳችንን መንገድ ብንከተል መልካም ነው ባይ ነኝ!

በወረዳችን SNV Horti life project ከግብርና ጽ/ቤት ጋር ተቀናጅቶ በእ/ጉጣንቾና በገ/ዚኮ ቀበሌ የመኸር ዝናብን በመጠቀም እየለሙ የሚገኙ የተለያዩ የጓሮ አትክልቶች ማሳ በከፊል....
16/09/2022

በወረዳችን SNV Horti life project ከግብርና ጽ/ቤት ጋር ተቀናጅቶ በእ/ጉጣንቾና በገ/ዚኮ ቀበሌ የመኸር ዝናብን በመጠቀም እየለሙ የሚገኙ የተለያዩ የጓሮ አትክልቶች ማሳ በከፊል...!

ገራሚ የግብርና ልማት ስራ ነውና በርቱ ተበራቱልን!!

እና እኛስ መች ጦር-ሜዳ ነው ኣልን...!?እናነተ ላይ ሁሉም በረታ እንበል..?
10/09/2022

እና እኛስ መች ጦር-ሜዳ ነው ኣልን...!?እናነተ ላይ ሁሉም በረታ እንበል..?

28/08/2022

ገረድ በቀናት...!?

ስልጤ ጠልና አሸዶች ያለ የሌለ ዘመቻቸውን ቢቀጥሉም የማይንበረከክ እና ንቁ የሆነ ትውልድን ለመፍጠር ምክንያት እየሆኑ ስለመሆኑ አልጠራጠርም!!
26/08/2022

ስልጤ ጠልና አሸዶች ያለ የሌለ ዘመቻቸውን ቢቀጥሉም የማይንበረከክ እና ንቁ የሆነ ትውልድን ለመፍጠር ምክንያት እየሆኑ ስለመሆኑ አልጠራጠርም!!

የፌዴሬሽን ምክር ቤት፤በደቡብ ክልል አደረጃጀት ጉዳይ አስቸኳይ ስብሰባ ጠራ!መደበኛው ጉባኤውን ከአንድ ወር በፊት ያደረገው የፌዴሬሽን ምክር ቤት፤በደቡብ ክልል አደረጃጀት ጉዳይ ላይ አስቸኳይ...
15/08/2022

የፌዴሬሽን ምክር ቤት፤በደቡብ ክልል አደረጃጀት ጉዳይ አስቸኳይ ስብሰባ ጠራ!

መደበኛው ጉባኤውን ከአንድ ወር በፊት ያደረገው የፌዴሬሽን ምክር ቤት፤በደቡብ ክልል አደረጃጀት ጉዳይ ላይ አስቸኳይ ስብሰባ ሊያካሄድ ነው።ሁለት የፌዴሬሽን ምክር ቤት አባላት በሚቀጥለው ሳምንት ረቡዕ ነሐሴ 11 ቀን 2014 ለሚደረገው ለዚሁ አስቸኳይ ስብሰባ ጥሪ እንደተደረገላቸው ታውቋል።

የፌዴሬሽን ምክር ቤት የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ ተረፈ በዳዳ፤ ምክር ቤቱ አስቸኳይ ስብሰባውን በመጪው ረቡዕ እንደሚያካሂድ ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” አረጋግጠዋል።አቶ ተረፈ ምክር ቤቱ “በደቡብ ክልል ጋር ተያይዞ የሚወስናቸው ውሳኔዎች ይኖራሉ” ሲሉ ስብሰባው የተጠራበትን ምክንያት ገልጸዋል።

በደቡብ ክልል የሚገኙ አስር ዞኖች እና ስድስት ልዩ ወረዳዎች፤ በሁለት የተለያዩ ክልሎች የመደራጀት ጥያቄያቸውን ባለፈው ሳምንት ሐሙስ ሐምሌ 28 ቀን 2014 ለፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ጽህፈት ቤት አስገብተዋል።ጥያቄዎቹን የያዙ ሰነዶች ርክክብ ስነ ስርዓት ላይ ንግግር ያደረጉት የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ አገኘሁ ተሻገር፤“የፌዴሬሽን ምክር ቤት በጥያቄው ላይ ውይይት አካሄዶ፤በአጭር ጊዜ ውስጥ ውሳኔ ወስኖ የሚያሳውቅ ይሆናል” ብለው ነበር።

dire tube

13/08/2022

መዥርጤና ዠልጤ ከዚህ ዘመን ትውልድ ጋር አብረው ሊጓዙ አይችሉም!!

30/07/2022

ገኘቴ ያድራርቃው ባተ....!?

ወርቅ ያመጡ አትሌቶች በአዲስ አበባ 500 ካሬ ሜትር የመሬት ስጦታ ተበረከተላቸው።ሶጣታው የተበረከተው በከተማው አስተዳደር ካቢኔ ውሳኔ ነው።🇪🇹 አትሌት ለተሰንበት ግደይ 500 ካሬ ሜትር መ...
28/07/2022

ወርቅ ያመጡ አትሌቶች በአዲስ አበባ 500 ካሬ ሜትር የመሬት ስጦታ ተበረከተላቸው።ሶጣታው የተበረከተው በከተማው አስተዳደር ካቢኔ ውሳኔ ነው።

🇪🇹 አትሌት ለተሰንበት ግደይ 500 ካሬ ሜትር መሬት

🇪🇹 አትሌት ጎተይቶም ገ/ስላሰ 500 ካሬ ሜትር መሬት

🇪🇹 አትሌት ታምራት ቶላ 500 ካሬ ሜትር መሬት

🇪🇹 አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ (ልዩ ተሸላሚ) 500 ካሬ ሜትር መሬት እና ወርቅ ቅብ " እናመሰግናለን "የሚል ስጦታ ተበርክቶላታል።

🇪🇹 ለመላው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ልዑክ ቡድን 10 ሚሊዮን ብር

🇪🇹 የወርቅ ቅብ ሰሃን " እናመሰግናለን " የሚል ለኮማንደር አትሌት ደራርቱ ቱሉ!!

🇪🇹 አትሌት ወርቅውሃ ጌታቸው 350 ካሬሜትር መሬት

🇪🇹 አትሌት ለሜቻ ግርማ 350 ካሬሜትር መሬት

🇪🇹 አትሌት ሞስነት ገረመው 350 ካሬሜትር መሬት

🇪🇹አትሌት ዳዊት ስዩም 250 ካሬሜትር መሬት

🇪🇹 አትሌት መቅደስ አበበ 250 ካሬሜትር መሬት ተበርክቶላቸዋል።

😍😍አረ ስንት አይነት ከንቱ ወንድ ኣለ😍😍ለፍቅረኛው ብሎ 3 ጊዜ ራሱን ሊያጠፋ የነበረው ወጣትሴቷ ፦እኔ ወንድ ልጅ አንቺን ካጣው እምታለው የሚለውን በእሱ ነው ያየውት፦በኔ ምክንያት ከ3 ጊዜ...
21/07/2022

😍😍አረ ስንት አይነት ከንቱ ወንድ ኣለ😍😍

ለፍቅረኛው ብሎ 3 ጊዜ ራሱን ሊያጠፋ የነበረው ወጣት

ሴቷ ፦

እኔ ወንድ ልጅ አንቺን ካጣው እምታለው የሚለውን በእሱ ነው ያየውት፦

በኔ ምክንያት ከ3 ጊዜ በላይ እልል ብሎ እራሱን ሊያጠፉ ሞክሯል።

የመጀመሪያ፦እኔ የምስራበት ፀጉር ቤት መጣና እልል ብሎ ምላጩን በሙሉ አኝኮ በላው ከዛ በስንት መከራ ተረፈ 🥹

ለሁለተኛ ጊዜ ደሞ፦ እልል ብሎ የኤክትሪክ ገመድ ታንቆ ፊንት ነቀለብኝ እኔም እሱን ይዤ ሀኪም ቤት በለሊት ሄድኩኝ በስንት መከራ ተረፈ🥹

3ኛ ደሞ፦አንቺን ካጣው ብሎ ወደ ገደል እራሱን ወረወረ እኔም እታች ገደል ስር ገብቼ ፈልጌ አግኝቼው ሀኪም ቤት ይዤ ሄጄ በስንት መከራ ተረፈ🥹

ስንት ወጣቶች ለእናት ሀገራቸው በሚሰዎባት እማማ ኢትዮጵያ ለፍቅርም እንዲህ እልል ብሎ 3ቴ ሊሰዋ የነበረ ወጣት አለ

😀እስኪ ይህንን ሰው እስኪ እናንተ ግለጹት😀
Via@ጉርሻ

08/07/2022

የስልጤ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት እንኳን ለ1443ኛው የኢድ አል አድሃ (አረፋ) በዓል በሰላም አደረሳቹ ይላል፤

የፓርቲ ጽ/ቤቱ ኃላፊው አቶ ቀድሩ አብደላ ባስተላለፉት መልዕክት የዘንድሮውን 1443ኛውን የአረፋ በዓል ስናከብር የእምነቱን አስተምሮ መሰረት በማድረግ በመተጋገዝ፣በመደጋገፍና አቅም የሌላቸውን በመርዳት ሊሆን ይገባል ብለዋል።

ኃላፊው በእንኳን አደረሳቹ መልዕክታቸው አያይዘው እንደገለጹት የእስልምና እምነት መቻቻል፣መደጋገፍና አብሮነትን የሚያጠናክር ነውና እኛም ይህንን በተግባር በማሳየት ሰውኛ ግዴታችንን ልንወጣ ይገባል ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

አቶ ቀድሩ በተጨማሪም በዓሉን ለማክበር ወደ ዞናችን ከተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የሚመጡት እንግዶች በአሉን በሰላም አሳልፈው እንዲመለሱ የአካባቢያችንን ሰላምና ደህንነት በማረጋገጥና በማጠናከር አርሂቡ ብለን ልንቀበላቸው ይገባል ብለዋል።

በድጋሚ እንኳን ለ1443 የኢድ-አል አድሃ አረፋ በዓል በሰላም አደረሳቹ!!

በዛሬው ዕለት በለገሪቱ የተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች የተመረቃቹ እንኳን ደስ ኣላቹ!!Congratulations!!!
02/07/2022

በዛሬው ዕለት በለገሪቱ የተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች የተመረቃቹ እንኳን ደስ ኣላቹ!!Congratulations!!!

የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ወደ ስልጤ ዞን ጎራ ብለዋል።ወደ ስልጤ መዲናዋ ወራቤ ከገቡ ወዲህ በስልጤ አርቆ አሳቢዎች ተወጥኖ በስልጤ ልማት ወዳድ ማህበረሰብ ወጪ የተ...
27/06/2022

የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ወደ ስልጤ ዞን ጎራ ብለዋል።ወደ ስልጤ መዲናዋ ወራቤ ከገቡ ወዲህ በስልጤ አርቆ አሳቢዎች ተወጥኖ በስልጤ ልማት ወዳድ ማህበረሰብ ወጪ የተሰራውን የሀይረንዚ ልዩ 2ኛ ደረጃን ጎብኝተዋል።

እኔ በግሌ ኸይአንዚን መጎብኘታቸው ብዙም አላስደሰተኝም ለምን ብትሉኝ እንደ ሀገራቀፍ ሊሰሩ ከታቀዱ 50 ልዩ አዳሪ ት/ቤቶች ውስጥ በቀጣይ ማለትም 2015 የበጀት አመት 12 ት/ቤቶች ሊገነቡ ተወጥኗል።

ከነዚህ ከ12 ውስጥም ቡዒ ከተማ ላይ ለመገንባት ተወጥኗል የሚል ጭምጭምታ ሰምቻለሁኝና የፕሮፌሰሩ የኸይረንዚ ጉብኝት ምናልባት ስልጤ ዞን ልዩ አዳሪ ት/ቤት እንዳለው የአይን ምስክርነታቸውን ለመስጠትና በታቀዱት 50 ልዩ አዳሪ ት/ቤቶች ውስጥ እንዳንካተት እንዳያደርግ ስጋት ኣለኝ።

ብቻ ፕሮፌስር እንኳን ደና መጡ!!

Address


Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Silte Media House SMH posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Videos

Shortcuts

  • Address
  • Alerts
  • Videos
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share