Ethiopia Today- ET

  • Home
  • Ethiopia Today- ET

Ethiopia Today- ET NEWS, political analysis, Human right activism, media monitoring

23/02/2024



አሜሪካ ከ ታጣቂዎች ጋር የሰላም ንግግር እንዲጀመር የኢትዮጵያ መንግሥትን እንደጠየቀች አሳውቃለች።

የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ሚኒስትር ሞሊ ፊ እንዲሁም የአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ አምባሳደር ማይክ ሃመር በኦንላይን መግለጫ ሰጥተው ነበር።

መግለጫቸው ባለፉት ቀናት በኢትዮጵያ የነበራቸውን የስራ ቆይታ የተመለከተ ነበር።

በዚህ ወቅት በኢትዮጵያ ቆይታቸው ከጠ/ ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ጋር ጨምሮ ከተለያዩ ባለስልጣናትና የተቋማት መሪዎች ጋር በኢትዮጵያ ያሉ ግጭቶች #በውይይት እንዲፈቱ መነጋገራቸውን አሳውቀዋል።

አሜሪካ በኦሮሚያ እየተካሄደ ያለው ግጭት እልባት እንዲያገኝ የበኩሏን ሚና እየተጫወተች መሆኑን ገልጸው በአማራ ክልልም ግጭቶች በሰላም እንዲቋጩ ከፋኖ ጋር ንግግር እንዲጀመር ጥሪ መቅርቡን ተናግረዋል።

አምባሳደር ማይክ ሃመር ምን አሉ ?

" ባለፈው ሕዳር ከኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ጋር በዳሬሰላም በተደረገው ውይይት ላይ በቀጥታ ተሳትፈናል። አሁን ይህን ለመቀጠል ዝግጁ ነን። ግጭቱ በሰላም እንዲፈታ እንዴት መመቻቸት እንደሚቻል ለሁለቱም አካላት ሃሳብ አቅርበናል።

ከፋኖ ጋር ንግግር እንዲደረግ አምባሳደር ማሲንጋ ለመንግሥት ጥያቄ ማቅረቡን እናውቃለን።

ሰላምን ለማረጋገጥ ያሉትን እድሎች በመጠቀም ጥረታችንን ለመቀጠል ዝግጁ ነን። በተደጋጋሚ እንዳልነው ለነዚህ ግጭቶች ወታደራዊ መፍትሄ አማራጭ አይሆንም አሁንም ትኩረት መደረግ ያለበት ውይይት ላይ ነው። " ብለዋል።

ሞሊ ፊ ምን አሉ ?

" ኢትዮጵያ በአሁን ወቅት በአማራ እና በኦሮሚያ ክልሎች ያጋጠሟትን ፈተናዎች በሰላም ለመፍታት ቁርጠኛ መሆናቸውን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተናግረዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዚህ ቁርጠንኝነታቸው እንዲቀጥሉ እናበረታታለን።

በታጣቂዎች ለሚፈፀሙት ጥቃቶች የመንግሥት የፀጥታ ኃይሎች ስለሚወስዱት እርምጃ አሳሳቢነት ገልጸናል። የጸጥታው ሁኔታን አሳሳቢነት ብንረዳም የሲቪሎችን መብት ለመጠበቅ ተጨማሪ ጥሪ ያስፈልጋል " ብለዋል።

አምባሳደር ማይክ ሃመር ፤ " ከተለያዩ ባለስልጣናት ጋር በተደረገው ስብሰባ ከኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ጋር ውይይት ለማመቻቸት እንዲሁም የቀጠሉትን ግጭቶች በሰላም ለመፍታት ከአማራ ፋኖ ጋር ሊደረግ የሚችል ንግግር ላይ ለመሳተፍ ፍላጎት እንዳለን ገልጸናል " ብለዋል።

ሃመር በኢትዮጵያ ላለው ግጭት ወታደራዊ መፍትሄ እንደሌለ ገልጸው የኢትዮጵያ መንግሥትም ለሰላማዊ መፍትሄ ዝግጁነት እንዳለው መግለፁን እናደንቃለን ሲሉ ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ መንግሥት ከዚህ ቀደም ግጭቶች በሰላም እንዲፈቱ ፅኑ አቋም እንዳለው መግለፁ ይታወቃል። ከኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ጋርም በይፋ ሁለት ጊዜ ድርድር ቢቀመጥም መጨረሻ ላይ መሳካት አልቻለም። በአማራ በኩል ከፋኖ ጋር ለድርድር ስለመቀመጥ እስካሁን በይፋ የተባለ ነገር የለም።

አሜሪካውያኑ ባለስልጣናት በሰጡት መግለጫ ከኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ጋር ሳይሳካ ቀርቶ የተቋረጠው ድርድር መቼ እንደሚቀጥል እንዲሁም መንግሥት ከፋኖ ጋር ለድርድር ይቀመጥ እንደሆነ በግልፅ ባይናገሩም የኢትዮጵያ መንግሥት ለሰላማዊ መፍትሄ ዝግጁ እንደሆነ እንዳሳወቃቸው ተናግረዋል።

ቪኦኤ

23/02/2024

በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን በተፈጸመ የድሮን ጥቃት ህፃናትን ጨምሮ በርካታ ንፁሐን ተገድለዋል ተባለ

ባለፈው ሰኞ በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ሰላ ድንጋይ ከተማ አቅራቢያ ሰላ መገንጠያ በተባለ ቦታ ላይ በተፈፀመ የድሮን ጥቃት ህፃናትን ጨምሮ በርካታ ንፁሐን መገደላቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ለዶይቼ ቬሌ ተናግረዋል፡፡ ህፃንን ክርስትና አስነስተው ሲመለሱ አደጋ ከደረሰባቸው መካከል የህፃኑ እናትም ህይወቷ ማለፉ ተነግሯል፣ በተመታው መኪና ውስጥ ከነበሩ ተሳፋሪዎች መካከል 2 ልጆቻቸው እንደተገደሉባቸው አንድ አባት ገልጠዋል፡፡

ባለፈው ሰኞ በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ሞጃና ወደራ ወረዳ ልዩ ስሙ “ሰላ መገንጠያ” በተባለ አካባቢ በተፈፀመ የድሮን ጥቃት በርካታ ሰዎች መገደላቸውን የዓይን እማኞች ተናግረዋል፡፡
ጥቃቱ በተፈፀመበት አካባቢ የነበሩና ለደህንነታቸው ሲባል ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ የሰላ ደንጋይ ነዋሪ በሰጡን አስተያት ሳሊት ከተባለ ከተማ የህፃን ልጅ የክርስትና ጥምቀት ፈፅመው በአይሲዙ የጭነት መኪና ተሳፍረው በመመለስ ላይ በነበሩ ሰዎች ላይ የድሮን ጥቃት ደርሶ እስከ 10 ዓመት አድሜ ያላቸው ህፃናትና ሌሎች ንፁሀን ሰዎች ተገድለዋል ብለዋል፡፡

“ክርስትና ነበር፣ የተሰበሰቡ እናት፣ እህት፣ ወንድም አክስት፣ የዘመድ ልጆች ነበሩ፡፡ የክርስትናውን ድግስ በልተውና ጠጥተው ወደ ቤታቸው በመመለስ ላይ ነበሩ፣ አይሱዙ መኪና ነበረች፣ በዚያች መኪና ወላዷና ሌሎችም ሰዎች ተጭነው ወደ ቤተሰቦቻቸው ሲመለሱ የድሮን ድምፅ ተሰማ፣ ከተማው ላይ ነበርን እኛም ሰማን፣ በመኪናው ውስጥ የነበሩ ንፁሀን ናቸው፣ ምንም የሚያውቁት ነገር አልነበረም፣ ከ10 ዓመት በታች ሁሉ ህፃናት ነበሩበት፡፡” ነው ያሉት፡፡

እንደ አስተያየት ሰጪው “በጥቃቱ ክርስትና አስነስታ ስትመለስ የነበረች እናት ህይወቷ ያለፈ ሲሆን ህጻኑ ደግሞ በተዓምር ከሞት አምልጧል” ብለዋል፡፡ ሌሎች 40 ያክል ሰዎች ደግሞ በጥቃቱ መገደላቸውን መስማታቸውን መልክተዋል፡፡

“የሞቱትን አንድ ሁለት ብለን ባንቆጥርም ባለው መረጃ ፣ 40 ነው የተባለው፣ እናት ሞታለች፣ አባት ቤት ይጠብቁ ስለነበር ወደ ቦታው ባለመሄዳቸው ተርፈዋል፣ በእለቱ ክርስትና የተነሳው ህፃኑ ሁለቱም አያቶች፣ አክስት አጎት፣ ሞተዋል፣ ህፃኑ አልሞተም ተርፏል፡፡” ብለዋል፡፡

ሌላ የሰላ ድንጋይ ከተማ አስተያት ሰጪ በበኩላቸው በጥቃቱ የሞቱትን ቁጥር በትክክል መናገር ባይችሉም ከአንድ ቤተሰብ እስከ 7 ሰዎች መገደላቸውን በስልክ ለዶቼ ቬሌ ተናግረዋል፡፡

“ጉዳት የደረሰው ከእኛ አካባቢ ከክርስትና ሲመለሱ ሰኞ እለት አይሱዙ ተሳፍረው በነበሩ ሰዎች ላይ ሰላ መገንጠያ ላይ ነው፡፡ ክርስትና ሲያስነሱ የነበሩ ቤተሰቦች እንዳለቁ ነው ያለው መረጃ፣ ምን ያክል ሰው እንደሞተ ባይታወቅም በጣም ብዙ ሰው እንደተጎዳ ነው መረጃ ያለው፣ ከአንድ ቤተሰብ እስከ ሰባት ሰዎች እንደሞቱ ከባለክርስትናው ቤተሰብ ተነግሯል፣ (በእለቱ)ጦርነት የነበረው ከእኛ ከሳሲት ከተማ ጋውና ወርዶ ፊላ ገነት ነው፣ ይህም ወደ 15 ኪሎሜትር ይርቃል፡፡”

የክርስትና ስነርዓቱ ተካፋይ ያልነበሩ ነገር ግን “ፊላ ገነት” በተባለው አካባቢ ጦርነት ስለነበረና ጦርነቱ ሊደርስባቸው ይችላል በሚል ከሳሲት ከተማ ልጆቻቸውን የትራንስፖርት ገንዘብ ከፍለው በክርስትና ስነስዓት ላይ የነበሩ ሰዎችን አሳፍሮ በነበረው የጭነት መኪና እንዲሳፈሩ ያደረጉ አንድ አርሶ አደር አባት ሁለት ህፃናት ልጆቻቸው በእለቱ በጥቃቱ እንደተገደሉባቸውና ቀብራቸው እንደተፈፀመ ገልጠዋል፡፡

“ ... ተማሪዎች ናቸው፣ ተኩስ ስለነበር (ፊላ ገነት) እነሱን አሸሻለሁ ብየ ነው፣ ንፁሀን ናቸው፣ ከጦርነቱ ጋር ምንም ግንኙነት የለውም (ጥቃቱ) የ10 ዓመትና የ8 ዓመት ተማሪዎች ናቸው፣ ሴትና ወንድ ናቸው፣ ቀብር ተከናውኗል፣ ብዙ ሰው ደግሞ ቆስሏል፡፡”

ጥቃቱ ከተፈፀመበት ሰላ መገንጠያ በግምት ከ15 እስከ 20 ኪሎሜትር ቦታ ላይ በእለቱ በፋኖና በመከላከያ ሰራዊት መካከል ጦርነት እንደነበርም አስተያየት ሰጪዎቹ ተናግረዋል፡፡

ጉዳዩን አስመልክተን ተጨማሪ አስተያት ለማካተት ለአማራ ክልል ሰላምና ፀጥታና ለክልሉ የኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊዎች ብንደውልም ስልካቸው አይነሳም፡፡ የኢትዮጵያ መንግስት በጉዳዩ ላይ እስካሁን ያለው ነገርም የለም ።

Via ዶቼቬሌ

No comment!
13/01/2024

No comment!

30/08/2023

3 3 ቱ ᎓ የ ጦ ር ᎓ ስ ል ቶ ች

(በዓለማችን ዕውቅ ምሁር፣ በሮበርት ግሪን)

“ሰላምን አጥብቆ የሚወድ፥ ለጦርነት ይዘጋጅ!” — ፓብሊየስ ፍላቪየስ ሬናተስ፣ ‹‹ኤፒቶማ ሬ ሚሊታሪስ››፣ 395 ዓ.ም.

ስልት 1/ በቅድሚያ በውስጥ ጠላትህ ላይ ጦር አውጅ!

ለጦርነት ስትዘጋጅ በተኩላዎች የተከበብክ በግ እንዳትሆን አጥብቀህ ተጠንቀቅ፡፡ በቅድሚያ ጠላትህን ለይ፡፡ ግን ለራስህ በልብህ ያዘው፡፡ ካላወቅካቸው ጠላቶች እጅ ትድናለህ፡፡ ማንም ባልተናገርከው አይፈርድብህም፡፡ ዋናውን ጠላትህን ግን ምንም ያላወቅከው ምሰል፡፡ በሁሉ ቦታ ጠላት አትፈልግ፡፡ ከሁሉ ጋር ጠብን አትጫር፡፡ ጠላትህ ክንብንቡን ገፍፎ ይበልጥ ፊት ለፊት እንዲወጣ አድርገው፡፡ ጠላት እንደሆነ ሁሉም በግልጽ ካወቀው በኋላ ነው ‹‹ጠላቴ›› ብለህ መጥራት እና ጦርነትህን ማወጅ ያለብህ፡፡ እስከዚያ ተጣብቶ አላራምድ ያለህን፣ የገዛ ውስጥ እግርህን እሾህ በጥንቃቄ እየነቀልክ ራስህን አዘገጃጅ! በትክክለኛው ጊዜ ተነሣ!

ስልት 2/ የዘንድሮን ጦርነት በባለፈው ጦርነት አትዋጋ! አዲስ ስልት አምጣ!

ከዚህ በፊት የጦር በለስ ቀንቶህ ይሆናል፡፡ ደጋግመህ የተጠቀምክበት የውጊያ ሥልት ለድል አብቅቶህ ይሆናል፡፡ ግን ባለፈው ላይ ብቻ ችክ አትበል፡፡ ባለፈው ያዋጣህ ድልህ ለወደፊቱ ጦርነትህ ታላቁ ወጥመድ ሆኖ ሊጠብቅህ ይችላል፡፡ ጠላትህ የሚተነብይህ ተዋጊ አትሁን፡፡ ያምናውን ስልት ለከርሞው አትድገመው፡፡ ሁኔታውን እያየህ፣ የጠላትን አኳኋን እየለካህ፣ አዲስ የጦር ስትራቴጂ ፍጠር፡፡ ሁልጊዜ አዳዲስ ታክቲክ ቀይር፡፡ ጠላትህ አካሄዱን ሲለውጥ፣ አካሄድህን ለውጥ፡፡ ያለፈን እርሳው፡፡ ሁሌ አዲስ ኃይልና አሰላለፍ ያዝ!

ስልት 3/ አዕምሮህ ሁልጊዜም እንደተሳለ ሠይፍ ይሁን፣ በራስህ ተማመን፣ ፈጥነህ ተንቀሳቀስ!

ስለ ጠላትህ በድፍኑ አታስብ፡፡ ጫካውን ብቻ ሳይሆን፣ ጫካውን ስለፈጠሩት ስለ እያንዳንዶቹ ዛፎች በሚገባ ተረዳ፡፡ የጠላትን ጦር ስለፈጠሩት ስለያንዳንዳቸው ተሰላፊ አካሎች ጥልቅና ዝርዝር መረጃ ይኑርህ፡፡ ይህ በራስህ ያለህን እምነት ከፍ ያደርግልሃል፡፡ ልብ በል፡፡ በራሱ ያልተማመነ ጦር አያሸንፍም፡፡ በራስህ ተማመን፡፡ ሁልጊዜም ፈጣሪ ካንተ ጋር እንደቆመ አስብ፡፡ እውነትን ይዘሃል! ለሀቅ ቆመሃል! መላዕክታት በክብራቸው እንደሚጋርዱህ ደጋግመህ ተናገር፡፡ ጦርህ ከሰውም በላይ የፈጣሪን ጣልቃ ገብነት ይመን! ለሰው የማይቻል ለእግዚአብሔር ይቻላል፡፡ እና ፈጣሪህን እመን፡፡ ራስህንም እመን፡፡ በሌሎች አትመካ! እምነት፣ ጥልቅ መረጃ፣ እና በጥልቅ መረጃ ላይ የተመሠረተ ፈጣን እንቅስቃሴ - እነዚህ ናቸው የድል ቅመሞች!

ስልት 4/ ድላችሁም ሞታችሁም አሁን በዚህች ቅፅበት እንደሆነ እመን፣ ፋኖዎችህን አሳምን!

ብዙ የዓለማችን ስኬታማ ጄነራሎች የሚጠቀሙበት የጦር ስልት አለ፡፡ ድልድዩን ማፍራረስ! ወደ ጠላትህ እየገሰገስክ ወደ ጦርነት ስትወጣ የተሻገርክበትን ድልድይ - አፈራርሰው፡፡ ጀግና ወደ ኋላ መመለሻ የለውም! መመለሻ እንደሌለህ አውቀህ ውጣ፡፡ በፍፁም መመለሻ የለህም፡፡ ያለህ መሄጃ አንድ ነው፡፡ ያለህ ዕድል አንድ ነው፡፡ በቀጥታ ጠላትህን መግጠም፡፡ እና ማሸነፍ፡፡ ማመንታት የለም፡፡ ወደ ኋላ የለም! ወለም ዘለም የለም! ወይ ለመሞት! ወይ ለመትረፍ! ድል ለማድረግ!… (እና የመጨረሻው ክፉ ቢመጣ ለመሸነፍ!) እንጂ መዝረክረክ የለም! ወደፊት ብቻ! ፈረንሳዊው ጄነራል ታላቁ ናፖሊዮን ጦርሠራዊቱን ሲያዘምት፣ የተሳፈሩባቸውን መርከቦች ሁሉም እያየ በእሳት ያጋያቸዋል፡፡ መመለሻቸውን ያቃጥለዋል! መመለሻ የለህም! መሸሻ የለህም! ሽንጥህን ገትረህ ለነፍስህና ለሀቅህ መዋጋት ብቻ ነው የቀረህ ዕድል! ተሟሙተህ ተዋጋ! ተሟሙተህ አሸንፍ! ተሟሙተህ ትረፍ! ድልህም፣ ሞትህም፣ አሁን፣ በዚህች ቅፅበት ነች! ቅጽበቷን ተጠቀምባት! አትጠራጠር! አታወላውል! - ድል ካንተ ዓይነቱ ቆራጥ ጋር ነች!

ስልት 5/ የቡድን ምሪትን አስወግድ! የቡድን ፊት መሪ ሳይሆን - የማይነቀነቅ የጦር መሪ ሁን! ፍጠር!

ላንተ እና ለዓላማህ የገባልህ ሰው ሁሉ አንድ ዓላማና ምክንያት ብቻ ይኖረዋል ብለህ አታስብ፡፡ ሰዎች የጋራ ጠላትን ለመዋጋት የሚሹበት ሺህ ምክንያቶች ሊኖሯቸው ይችላሉ፡፡ እና ባንተ አንድ ዓላማ ብቻ አምነው እንዲሰለፉ የግድ ካልካቸው - ይጠሉሃል፡፡ እንዳሻቸው የየራሳቸውን ምክንያትና ዓላማ እንዲከተሉ ከለቀቅካቸው ደግሞ ዋናውን ትልቁን ግብ ትተው ሁሉም የየራሳቸውን አጀንዳ ለማስፈፀም ይሯሯጣሉ፡፡ ስለዚህ ሰዎች በምን ምክንያት አንተን አምነው መከተል እንዳለባቸው አትገድባቸው! የፈለጉትን ይመኑ! ግን አንድ ታላቅ ራዕይና መዳረሻ ግብ አስቀምጥላቸው፡፡ እና ተፈጥሯዊ ነብርነት ይኑርህ! መልካምና ጠቃሚ ሃሳቦችን ልብህን ከፍተህ ተቀበል! መጥፎዎቹን ሥር ሳይሰዱ ግራ! ፖለቲካ ለሚያነሆልላቸው የሚበቃ አጥጋቢ የፖለቲካ ቀለብ ይኑርህ! ሌሎች ምን ይሉኛል ብለህ ሃሳብህን አትከልክል! የልብህን እና መሸጫ መሸጫውን አውጥተህ ተናገር! ጦርህ ውስጥ አዘጥዛጭ የፖለቲካ ጆፌዎች እንዳይበዙ ተጠንቀቅ! ከበዙ ሠራዊትህን በአጀንዳዎቻቸው ይከፋፍሉብሃል! አክባሪህን አቅርበው! አዋጊ ከሆንክ የምትፈራ፣ የምትከበር፣ የማትሙለጨለጭ፣ ቀጥተኛና የማትነቀነቅ የጦር መሪ ሁን!

ስልት 6/ ጦርህን 40 ቦታ ለያየው ወይም በታትነዉ!

በጦርነት ዋናው የድል መተማመኛ ፍጥነት ነው፡፡ እንቅስቃሴ! ያለችውን ጦር ወደተፈለገበት ሥፍራ በፍጥነት ማንቀሳቀስና ቀድሞ መገኘት የቻለ ኃይል ሁሌም አሸናፊ ነው፡፡ ጠላትህ ማድረግ ከሚችልበት ፍጥነት በላይ በፍጥነት ቁርጠኛ ውሳኔዎችን በላይ በላዩ የመወሰን አቅሙ (ችሎታው) እና ወኔው ይኑርህ! ጠላትህ መድረስ ከሚችልበት ፍጥነት ቀድመህ የመድረስ፣ ከጠላትህ ከፍ ያለ የተነቃናቂነት አቅም ካለህ - ጠላትህ አለቀለት ማለት ነው! ግዙፍ ጦር ለጥቃት ይመቻል! ለማጥቃት እንዲመችህ፣ ጦርህን አርባ ቦታ ቆራርጠው፡፡ እያንዳንዱ በየራሱ ውሳኔ ወስዶ የሚንቀሳቀስ የውሳኔ ነፃነት ያለው ይሁን! ከጎበዝ አለቆች ውስጥ የቁርጥ ቀን ጀግኖች ይፈጠራሉ! ለአርባዎቹ ትናንሽ እዞችህ የጦር ዕውቀት ያላቸው፣ አሊያም በተፈጥሮ የጦር ስልት የተላበሱ የጎበዝ አለቆች ይኑራቸው! የአጠቃላዩን የዘመቻችሁን ዓላማና መንፈስ ስጣቸው! ግባችሁ ምን እንደሆነ በያንዳቸው ልብ አስርፅ! እና ያን ዓላማ ለማሳካት እንዳሻቸው የሚፈነጩበት የየራሳቸውን የማርያም መንገድ ስጣቸው! በእነዚህ ተርመስማሽ ጦሮች ጠላትህን ከጎን ከጎን ከተፍ እያልክ ብሽሽቱን ውጋው! ሳትታሰብ በቀኝ፣ በግራ፣ እየመጣህ ለጠላትህ - የማይላቀቀው የጎን ውጋት ሁንበት! ራሱን ችሎ ተበታትኖ በየራሱ የሚያጠቃ ህዝባዊ ሠራዊት - የሚያስመዘግበው የጎን ውጋት እየተጠራቀመ ሲሄድ - ድልህ እየቀረበ እንደመጣ እወቅ! ለጠላትህ አርባ የጎን ውጋት ሁንበት! ጠላትህ ግራ ይጋባል፡፡ በሁሉም አውደ ውጊያ ለመገዳደር ጦሩን ይበትናል፡፡ የመዘዋወር አቅሙን እየተከታተልክ ከነደፍከው - ብዙም ሳይቆይ - በውጋቶችህ ተቀስፎ ሲያለከልክ ታገኘዋለህ!

ስልት 7/ በጦርነት ወቅት የግል-ድል፣ እና የግል-ሽንፈት የለም! ድሉም ሽንፈቱም የጋራ ነው!

አንተ ከኋላ ሆነህ፣ ጦርህን አስቀድመህ፣ እውነተኛ ድል አይገኝም! ከኋላ ሆነህ አትግፋ! ከፊት ቀድመህ ተገኝ፣ ከፊት ቀድመህ ምራ! አስር ሰው እንደ ግለሰብ ሲቆጠር አስር ብቻ ይመስላል፡፡ እንደ ጦር ግን ሲነቃነቅ የሺህ ያህል ነው፡፡ ህይወታችሁም፣ ሞታችሁም፣ ቁስላችሁም፣ ደስታችሁም የጋራ ሲሆን - ያን ጊዜ ‹‹የኛ›› የሚባለው ታላቅና ለድል እጅግ አስፈላጊ ነገር በመካከላችሁ ይፈጠራል! በአስር የቆረጡ ፋኖዎች መሐል አስራ አንደኛው የስሜት ህዋስ ይፈጠራል፡፡ ያንን አስራ አንደኛውን የጋራ ስሜት ፍጠረው! በጦርነት ወቅት የግል ድል፣ እና የግል ሽንፈት የለም! አስራአንደኛው የጋራ ስሜት ካለ፣ ድል አለ! ድልም ባይኖር ሁሉም የጋራ ይሆናል!

ስልት 8/ የምትዋጋቸውንና የማትዋጋቸውን አውደ ውጊያዎች ለይተህ ምረጥ!

ጦርነት እጅግ ውድ ነገር ነው፡፡ የሰው ህይወት ይከፈልበታል፡፡ ቆጥበህ ተጠቀመው! ወጪው የሚተካበት ቢዝነስ አድርገህ አትቁጠረው ጦርነትን፡፡ ገንዘብም ከሆነ፣ በጦርነት የምታውለው ገንዘብ እሳት ውስጥ እንደምትወረውረው ያህል ነው፡፡ ከገባ አይመለስም፡፡ ውድ ነው ጦርነት፡፡ በዋጋ የማይተካው የሰው ሕይወትም አንዴ ከጠፋ ዳግመኛ አይመለስም፡፡ ደግሞም መቆረጥ አለ፡፡ መቁሰል አለ፡፡ መድማት አለ፡፡ የሚፈስ እንባ እና የሚንቆረቆር ላብ አለ፡፡ ጦርነት ልትገጥም ስታስብ - እነዚህን ሁሉ የጦርነት ወጪዎች ቀድመህ አስላቸው፡፡ እያንዳንዱን ውጊያ አሸንፈህ ዋናውን ጦርነት ብትሸነፍ ምን ያደርግልሃል? ጦርነት ውስጥ የምትገባው የመጨረሻውን ሣቅ ልትስቀው ከሆነ ብቻ ይሁን! ዝም ብሎ ተዋጋ ለመባል፣ ድል ለማስቆጠር ብቻ፣ አትዋጋ፡፡ መርጠህ፣ አስበህ፣ ተጠንቅቀህ፣ አድብተህ፣ አቅደህ፣ ዋናውን ጠላትህን አንድያውን ለማሸነፍ የሚጠቅም ከሆነ ብቻ ተዋጋ! ለመተላለቅ አትዋጋ! ያለህን ሁሉ ለክፉው ቀን ቆጥበህ ተጠቀመው! ግን - አንዴ ወስነህ ልትገጥም ከገባህ - በፍፁም የማትሸነፈውን ዓይነት ክብር ያለህ ተዋጊ ሁን! በሚረባውም በማይረባውም ውጊያ አትልከስከስ! ጠብቅ! አጥና! ታገስ! ተዘጋጅ! አድባ! እና ለማሸነፍ ግባ!

ስልት 9/ ምርጡ ጡጫ - ሲመጣብህ የምታየው ጡጫ ነው!

ይሄን የጦርነት ህግ ሁልጊዜም አስታውስ! በፍፁም! በፍፁም! በፍፁም! ቀድመህ ጦርነትን አትጀምር! የመጀመሪያዋን የጦርነት እርምጃ የምትራመደው አንተ እንዳትሆን - በመላ ነፍስህ እና በመላ ስጋህ ተገዝተህ፣ ተጠንቅቀህ፣ ተንቀሳቀስ! ጠላትህ አንተን አሳንሶ ገምቶ ይምጣ! ጠላህት የፈለገውን አጀብ ያሳይ! ያሰለፈብህን ጦር እንደ ትርዒት አሰልፎ ያቅርበው! ያጠመደብህን መሣሪያ እያሳየ ይፎክር! በሠልፉ ወደ አንተ ይጠጋጋ! ኃያልነቱን ለማሳየትና ያንተን የውጊያ ሞራል ለማዳከም የፈለገውን ያህል ይቦርቅ! በሰማይ በምድር ይደንፋ! ይዛት! ይፈንጭ! - አንተ ግን ዝም! ጭጭ! ብለህ አድፍጥ! ጠላትህ ፈርቶኛል ብሎ ያስብ፡፡ ጠላትህን የመቶ ሺህ ሳተና ትንፋሽ ባለበት፣ ያንድ ሰውም ድምጽ እንዳይሰማው አድርገው! አይቋቋመኝም ብሎ እንዲያስብ አንድ ሺህ ምክንያቶችን ስጠው፡፡ እና ጥቃቱን በሙሉ ልቡ ተማምኖ እስኪከፍትብህ አድባ!

አንድ ሺህ ጊዜ ቢተነኩስህ፣ አንድ መቶ ሺህ ጊዜ አድብተህ ጠብቀው! ሲመጣ ግን ከላይ የመከርኩህን ሁን! ለማሸነፍ ግባ! ቀድመህ ተጠቃ! መልሰህ አጥቃ! መልሶ ማጥቃትህ እንደ ሠማያት እሣት ይሁን! ፍጠን! ተንቀሳቀስ! ፈጥነህ እንቅስቃሴዎቹን ተቆጣጠር! እና ብሽሽቱን እየመርጥክ ከጎን ከጎን እየተከታተልክ ውጋው! ከጀመርከው ደግሞ ሳትወቃው፣ ሳታበራየው እንዳትለቀው! ሳታሸንፈው እንዳትመለስ! የቆሰለ ነብር ለማንም አይበጅ! ደግሞ ምርጡ ጡጫ - ሲመጣብህ የምታየው ጡጫ እንደሆነ ሁልጊዜም እወቅ፡፡ ጡጫን ቀድመህ ሰንዛሪው አንተ ከሆንክ - ያንተን ጡጫ የሚያይብህ ጠላትህ ይሆናል፡፡ እና ለክቶ፣ ሰፍሮ ያወራርድሃል! እና እደግምልሃለሁ፡፡ ምርጡ ጡጫ - ሲመጣብህ የምታየው ጡጫ ነው! አንበሣ ሚዳቆን ተመስጦ በዝምታ እንደሚያያት፣ ጠላትህን አድብተህ ተመስጠህ እየው! እና አድብተህ ውጋው!

ስልት 10/ ለጠላትህ ጥቃት የማትመች ሁን!

ባገራችን ጀግና ካልደረስክበት ካልደረስክበት አይደርስብህም፡፡ ከነካኸው ግን አይምርህም፡፡ የማትነካ መሆንህን አሳየው፡፡ ከጀመርክ ሳትተላለቅ የማትመለስ መሆንህን ጠላትህ ይወቅ፡፡ እስከ መጨረሻው መራር መስዋዕትነት ድረስ፣ እስከመጨረሻዋ እስትንፋስ ድረስ የመዋጋት ታሪክ እንዳለህ አስረግጠህ ንገረው ለጠላት፡፡ ስትሞት ብቻህን እንደማትወድቅ፣ ተያይዘህ የጠላትህን ጉሮሮ አንቀህ እንደምትሞት በማያወላዳ ቋንቋ አስረዳው፡፡ ከጠላትህ አንፃር ስትታይ ከነኩህ የማትለቅ ግሥላ ሆነህ ከተገኘህ፣ ጠላትህ ሁለቴ ያስባል! ‹‹ምን ላገኝ ነው ከእነዚህ በደማቸው ተዋጊነት ከተዋሃደ ህዝቦች ጋር የምተላለቀው?›› ብሎ ደጋግሞ ማሰቡ አይቀርም፡፡ ለድል አስፈላጊ የሆነው ወኔው ይሰለባል!

ደመ መራር ሆነህ ተገኝ፡፡ እንደ ሚጥሚጣ አቃጣይ መሆንህን ጠላትህ እንዲገባው ይሁን፡፡ ከዚህም በባሰ ደግሞ አሻሚ ሁን፡፡ በጦርነት አሻሚ መሆን፣ ከላይ ሲልህ ከታች፣ ከታች ሲልህ ደሞ ከላይ መገኘት ነው፡፡ ዘጠኝ የጀግና ልብ ይዘህ ጠብቀው፡፡ በእርግጠኝነት አካሄድህን መገመት እንዳይችል አድርገው፡፡ ጠላትህ ይወዛገብ፡፡ ስላንተ ያለው መረጃ ሃምሳ ሺህ ዓይነት ይሁን፡፡ ስትያዝ ሙልጭልጭ፣ ስትበላ እሾህ ሁንበት፡፡ ካንተ ጋር ቢዋጋ ምን ወጪ እንደሚጠብቀው፣ ምን መስዋዕትነት እንደሚከተለው፣ ምን የከፋ አደጋ አፉን ደቅኖ እንደሚጠብቀው ያላወቀ ጠላት - ሊዋጋ አይወጣም፡፡ እጁን ሰብስቦ ነው የሚቀመጠው፡፡ ደፍሮ ከመጣብህ ግን ከተባልከውምና ከሆንከውም በላይ ከፍተህና መርረህ ጠብቀው፡፡

ስልት 11/ ጊዜን ግዛ፣ ቦታን በጊዜ ለውጥ!

በተቻለህ መጠን ጠላትህ በየተሰለፈበት አቅጣጫ ጠላትህን የማትዋጋ ዓይነት ባላጋራ ሆነህ ትዕግስቱን አስጨርሰው፡፡ ጠላትህ ያንተን የተወሰነ ርስት ወርሮ ከቦታ ቦታ ይንዘራወጥ፡፡ ተወው! ጦሩን ይዞ ባንተ ግዛት ከቦታ ቦታ ይንቀሳቀስ፡፡ ባለመዋጋትህ አስጨንቀው፡፡ ጦርነት አጥቶ በምድረበዳ እንዲቅበዘበዝ ተወው፡፡ አንተ ግን ጊዜን ግዛ፡፡ ጊዜ በጦርነት ትልቅ ሀብት ነው፡፡ ጊዜን ግዛና ራስህን አደራጅ፡፡ ጦርህን አጠንክር፡፡ የጀግንነትን ስሜት ከትውልድህ ልብ ውስጥ እንደ ቅቤ ንጠህ አውጣው፡፡ ባተረፍከው ጊዜ ውስጥ ቅፅሮችህን የበለጠ አጠናክር፡፡ ጦርህን በየፊናው በአዳዲስ መልክ አደራጅ፡፡ ጠላትህን በዓይነቁራኛ እየተከታተልክ ልቡ እንዲያብጥ ተወው! መስፋፋቱን እንዲቀጥል ልቀቀው፡፡
በዓለም የሚሊቴሪ ሳይንስ ከፍተኛ ተቀባይነትን ያገኘ ‹‹የመርፊ የመሳ ለመሳ ውጊያ ህግ›› (The Murphy’s Laws of Combat) የሚባል የጦርነት መርህ አለ፡፡ ከጠላትህ ጋር መሳ ለመሳ እየተያየህ ባለህበት ወቅት - በፍፁም በጠላትህ የጦር አዛዥ የሜዳ መነፅር እይታ ውስጥ አትግባለት፡፡ ለጠላትህ አዛዥ አትታየው፡፡ ለጠላትህ ሠራዊትም አትታየው፡፡ የትኛውም ጠላትህ በመነፅሩ እንዳይመለከትህ ባለ ርቀትና ሥፍራ ሁንበት፡፡ ብትቆም ለጠላትህ የምትታየው ከሆነ፣ አጎንብሰህ ጠብቀው፡፡ አጎንብሰህ የምትታየው ከሆነ፣ በደረትህ እየተሳብክ ጠብቀው፡፡ በደረትህ ስትሳብ የምትታየው ከሆነ፣ ሰጥ-ለጥ ብለህ ተኝተህ ጠብቀው፡፡ አሊያ ግን የሀገሩን ካርታና መነጽር ይዞ የመጣ ጠላት ከታየኸው የፈሪ ዱላውን ያወርድብሃል! The most dangerous thing in the world is a Second Lieutenant with a map and a compass.
ጊዜ ስትገዛ - በመካከል ጠላትህ የሆነ እንከን ይገጥመዋል፡፡ ስንቅ ያልቅበታል፡፡ ስህተት ይሰራል፡፡ ስስ ብልቱን ያጋልጣል፡፡ የጦር አቅዱን ያጋልጣል፡፡ የግንኙነት መስመሩ ይታወቃል፡፡ የሆነ ነገር ይፈጠራል! እና ጊዜ ግዛ፡፡ ጊዜ ገዝተህ ጠላትህ የሚሰራውን ስህተት በዓይነቁራኛ ተከታተል፡፡ ጠላትህ ስስ ብልቱን የሚከፍትበትን አመቺ ጊዜ ጠብቅ፡፡ ጠላትህ የሚዘናጋበትን ምክንያትና አጋጣሚ ሁሉ ጠንቅቀህ አስተውል፡፡ ጠላትህ ቀን እስኪጎድልበት አድፍጠህ ተጠባበቀው፡፡ በእርግጥ - ጊዜ ስትገዛ - ጊዜ ፊቷን የምትከዳው በጠላትህ ላይ ብቻ ነው ብለህ ግን አትገምት፡፡ አንተንም ጊዜ በገፋ ቁጥር ቀን ሊያጋድልብህ፣ ጊዜ ፊቷን ልታጨልምብህ እንደምትችልም ደጋግመህ አስበው! ከምንም በላይ በጊዜ ሂደት ጠላትህን አትዘንጋው፡፡ በፍጹም! ለአፍታም! ጊዜ አለፈ ብለህ አትዘናጋ፡፡ አመቺ ጊዜ ብቻ ጠብቅ፡፡

ስልት 12/ ለአውደ ውጊያዎች ተበገር፣ ለጦርነቱ ግን ፈጽሞ እንዳትበገር!

እውነተኛው ጦርነት ከመካሄዱ በፊት ብዙ አውደ ውጊያዎች እንደሚኖሩ አትርሳ፡፡ በየአውደውጊያዎቹ ተረታህ ማለት ጦርነቱን ተሸነፍክ ማለት አይደለም፡፡ አስር ጊዜ በአስር አውደ ውጊያዎች ተሸነፍ፡፡ ግን አሁንም አለህ፡፡ አልጠፋህም፡፡ ገና ጦርነቱን ልታሸንፍ ነው የተረፍከው! እና የቀረህን ትልቁን የፍጻሜ ጦርነት ተዋጋና አሸንፈው ጠላትክን፡፡ ትንንሽ ሽንፈቶችህ ላይ አቀርቅረህ አትቅር፡፡ ከሽንፈቶችህ ዋሻ ውጣ፡፡ እና ትልቁን ጦርነቴን እንዴት ነው የማሸንፈው ብለህ በረዥሙ ሰንቀህ ተነሳ፡፡ ደግመህ አቅድ! በተሸነፍክበት አውደ ውጊያ የጠላትህን አቋምና አሰላለፍ በሚገባ አይተኸዋል! ድክመትህን አርመህ፣ ድክመቱን ተመርኩዘህ ድጋሚ ግጠመው! በዓለም ላይ በጭንቅላቱ የተመሰከረለት የቼስ ተጫዋች አለ፡፡ ጋስፓሮቭ! በቅድሚያ ያሉትን ጠጠሮች በትንሽ በትንሹ እያንቀሳቀሰ ለባላጋራው እያስበላ ይቆይና፣ በስተመጨረሻ ሳይታሰብ የባላጋራውን ንግሥት ይማርካታል! እንደሱ ሁን!

ጊዜያዊ ሽንፈቶችን ተሸነፍ፡፡ ዋናውን ጦርነት ግን እንዳትሸነፍ፡፡ ጦርነትን ለመሸነፍ አትጀምር፡፡ ከተዋጋህ ማሸነፍ አለብህ፡፡ ብትሸነፍም ከጠላትህ ጋር ተላልቀህ ነው፡፡ እንዲሁ መሸነፍ የለም፡፡ ትልቁን ዓላማህን አስበው፡፡ የተነሳህበትን ትልቁን ራዕይህን አስበው፡፡ ማሸነፍ ለምን ለአንተ የህይወት ጉዳይ እንደሆነ በቀን ሺህ ጊዜ በአዕምሮህ አውጠንጥነው፡፡ ለልብህ ለነፍስህ ለሠማያትና ለአምላክህ ሁሉ ለምን ማሸነፍ ብቻ አማራጭህ እንደሆነ ደጋግመህ ንገራቸው፡፡ እነዚህ የምትናገራቸው ነገሮች ናቸው እንደ ድል የማያልቁ ውስጣዊ ነዳጅ ሆነው ወደ ፊት የሚያስቀጥሉህ፡፡ ለሽንፈት ፊት አትስጥ! ትልቁን ስዕልህን እያየህ ቀጥል ለድል ወደፊት፡፡ እና ትልቁን ጦርነት በድል ተወጣ! ግድየለህም! በህይወት እስካለህ፣ ጊዜ አለህ!

ስልት 13/ ጠላትህን እና የጠላትህን ፊት መሪዎች ጠንቅቀህ እወቅ!

የሰውን ፊት አንብብ፡፡ የጠላትህ መሪዎችና አዋጊዎች መግለጫ ሲሰጡ ልብ ብለህ ተመልከታቸው! ሰዎች ከሚናገሩበት መንገድ ተነስተህ በውስጥ አዕምሯቸው የሚመላለሰውን ሃሳብ ድረስበት፡፡ የጠላትህን ሰዎች ከአኳኋናቸው እወቃቸው፡፡ ሰዎችን አንብብ፡፡ ሰዎችን ማንበብ ከቻልክ የአሸናፊነትን ግማሹን መንገድ ተጓዝክ ማለት ነው፡፡ ጠላትህ ምን እንደሚያስብ፣ በምን ሂሳብ እንደሚንቀሳቀስ፣ ምን እያሰላ እንደሚራመድ፣ ምን እንደተማመነ፣ ምን እንደሚፈራ፣ ማንን እንሚጠረጥር፣ ከማን ጋር ምን ህብረት ሊፈጥር እንደሚያስብ፣ የከፋው ቀን ምን ቢመጣበት ምን ለማድረግ እንደሚፈልግ፣ ምን ለማድረግ እንደሚገደድ፣ ምን ከማድረግ ወደ ኋላ እንደማይል… የጠላትህን ሁሉን አስተሳሰቡንና ነገሩን ሁሉ ጠንቅቀህና አበጥረህ እወቀው፡፡ በጠላትህ ጭንቅላት ውስጥ ሰርገህ ግባ፡፡

በዓለም አሉ የተባሉ ክንደ ብርቱ ጦርሠራዊቶች የተመቱት፣ የመሪዎቻቸውን አዕምሮ ለጠላታቸው አስጣጥተው ሲያበቁ መሆኑን ልብ ብለህ አስተውል፡፡ ስለላ ለጦርነት ዋናው ቁልፍ መሆኑን አስታውስ፡፡ የጠላትህን መናጆ ቀርበህ ስትሰልለው ደርሶ ብዙ ጥያቄ አታብዛበት፡፡ ሰው ጥያቄ ባበዛህበት ቁጥር ወደመከላከልና ነገሩን ወደመሸሸግ ያመራል፡፡ ወደምትፈልገው የመረጃ ነጥብ ለመድረስ ብለህም ንትርክ አትፍጠር፡፡ መረጃ ስታነፈንስ የቀድሞ ጓደኝነትህንና ቀረቤታህን ጨምርበት፡፡ በቻልከው ውለታን አብዛ፡፡ ለዒላማህ ዝቅ ዝቅ በልለት፡፡ ዝቅ እያልክ ግን ከእግር ጥፍሩ እስከ ራስ ፀጉሩ ተጠግተህ አጥናው የጠላትን ነገረሥራ፡፡ ራሱ በፍላጎቱ ምስጢሩን አንድ ሁለት እያለ እስኪዘከዝክልህ ጠብቅ! አትወትውት፡፡ ደካማ ጎኑን፣ ስስ ብልቱን፣ የማይወጣቸውን ዳገቶች፣ የማይደፍራቸውን ቁልቁለቶች፣ ልብ ብለህ ያዝ፡፡ ልትዋጋው ያሰብከውን ጠላት ራሱ ራሱን ከሚያውቀው በላይ፣ ከነድክመቱ፣ ከነተጋላጭነቱ አንጠርጥረህ እወቀው፡፡ ጠላትህን ማንበቡ ሲበቃህ፣ የጠላትህን ፊትመሪዎች አንብበህ ስትጨርስ፣ ማንና ማን ምን አስበው አልመው በየት በኩል ሊመጡብህ እንደተገኙ ሲገባህ፣ ያነበብከውን በተግባር የምትፈትንበት ወቅት ደረሰ ማለት ነው፡፡ ፈተናውን እለፈው!

ስልት 14/ ፍጥነት! ፍጥነት! አሁንም ፍጥነት!

የናዚ ጀርመኑ መሪ አዶልፍ ሂትለር ድፍን አውሮፓን በወራት ጊዜ ውስጥ ያንበረከከበት አንድ የሚታወቅበት ስልት አለ፡፡ ‹‹ብሊትዝክሪዬግ›› ይባላል፡፡ ብሊትዝክሪዬግ ደረቅ ቃሉ መብረቅ ማለት ነው፡፡ የመብረቅ እሳት እንደማለት ነው፡፡ ሂትለር ለአውሮፓውያኑ ባላንጣዎቹ የሆነባቸው እንደዚያ ነበረ፡፡ ያልታሰበ ነጎድጓዳማ የመብረቅ እሳት፡፡ እና ጦርነት አንዴ ከተለኮሰ፣ ድል እንዲቀናህ ፍጥነትን በመላ አካልህ ተላበስ፡፡ ሠራዊትህ መብረቃዊ ይሁን፡፡ በጠላትህ ላይ እንደ ድንገተኛ መብረቅ እሣትህን ሳይታሰብ አውርድበት! ጓዙንና ካዝናውን ለመሰብሰብ እንኳ ጊዜ እንዳይኖረው አድርገህ ጠላትህን በክንፎቹ አቅጣጫ ቀርበህ አዋክበው! ጠላትህ የበጋ መብረቅ እንደወረደበት ሁሉ በድንጋጤ እንዲበረግግ ይሁን፡፡ ከፍጥነትህ የተነሳ በምትፈጥረው ድንገተኛነትህ ጠላትህ ለቅጽበቶች በፍርሃት የሚይዝ የሚጨብጠውን እንዲያጣ አድርገው፡፡ በእውር ድንብሩ ሲውተረተር ለብዙ ስህተቶች እንዲጋለጥ አድርገው፡፡ ድንገት ጥይት የተተኮሰባት ሚዳቆ በፍርሃት ደንብራ ወዳላሰበችበት እንደምትዘለው፣ ጠላትህን በስሜት ተንጦ በነሲብ እንዲዘልል በድንገተኛ መብረቃዊ ውርጅብኝ አናውጠው! ሰው የተፈጠረው ከፍርሃት ጋር ነው፡፡ ያንን ፍርሃት ናጠውና አውጣው፡፡ ጠላትህ በድንጋጤ ሲውሸለሸል እንደ መብረቅ ትኩስ እሳት ጎርሰህ፣ ነጎድጓዳማ እሳት ለብሰህ እንደተዋከበ ምታው!

ስልት 15/ የጦር አውድማውን ሂደት ተቆጣጠር! ጠላትህ ሜዳውን የተቆጣጠረ እንዲመስለው አድርገው! በምንም ተዓምር ጠላትህ እንዳይመቸው ተጠንቀቅ!!

በመጀመሪያ ጠላትህን በንዴት የሚታንጨረጭረዋን አንዲቷን ምልኪውን እወቃት፡፡ እና ያቺን ጠላትህን ኤሌትሪክ የምታስጨብጠዋን ነገር አድርግበት! አቅሉን እንዲስት የሆነ የሚያንጨረጭረውን ነገር ፈልገህ አደባይበት! አንጀቱ በማይጨክንበት ጎኑ ተንኩሰው! ጠላትህ ንዴት ለብሶ፣ እሳት ጎርሶ በቁጣ እንዲገሰግስ፣ ቁልፉን ነገር ፈልገህ በዚያ ቆስቁሰው! እና ያን ንዴቱን ተላብሶ ገንፍሎ ሲወጣ፣ ወደምትፈልግበት አቅጣጫ፣ ወዳሻኸው መንገድ ምራው፡፡

ለምሳሌ እጅግ የተናደደን ሠራዊት በመንገዱ ላይ ጠብቀህ ለደቂቃዎች ብታቆመው፣ ባለ በሌለ ኃይሉ ይመጣብሃል፡፡ ይሄ ተገልብጦ ሲነበብ ምን ማለት ነው? ይህ ማለት - ያ ሠራዊት ወደየት አቅጣጫ፣ እና ምን ቦታ ላይ፣ በምን ሰዓት ላይ፣ ወደሆነ አቅጣጫ እንዲመጣ የምትመራው አንተ ሆንክ ማለት ነው! እና በጠላትህ የንዴት ስነልቡና ላይ ጢባጢቤ ተጫወትበት፡፡ እና በንዴት የጨሰውን ትልቁን ጦር - እንደ ህጻን ልጅ እጁን ይዘህ ወደምትፈልግበት አቅጣጫ ምራው፡፡

የጠላትህ ጦር ለዘብተኛ ከሆነም - በትንሽ በትልቁ ቆስቁሰህ ቆስቁሰህ አቅሉን እንዴት እንደምታስተው አሳምረህ እወቅበት፡፡ የተናደደን ጦር መምራት ሳታውቅበት፣ የራስህን ጦር ልትመራ አትችልም! በጦር አውድማ ጠላትህ ሜዳውን ሁሉ የተቆጣጠረ ሆኖ እንዲሰማው የቻልከውን ሁሉ እንክብካቤም ደግሞ አድርግለት፡፡ ዕቅዱ የሰመረ እንዲመስለው፣ ያሰበውን አውቀህ፣ ያሰበህን የሆንክ መስለህ ተገኝለት፡፡ ታላቁ የጦር አውድማን የመቆጣጠር ሚስጥር ምን መሠለህ? - ጠላትህ የጦር አውድማውን ሳይቆጣጠረው፣ ግን ልክ እንደተቆጣጠረው እንዲሰማው ማድረግ መቻል ነው!

እንዲያ ማድረግ ከቻልክ ዕዳው ገብስ ነው! ጠላትህ የተስተካከለለት በመሰለው የውጊያ መስመሩ ሰተት ብሎ ሲገባ - ድንገት አሰላለፉን አፋልስበት! በግራ በቀኝ በድንገተኛ ተወርዋሪ ፋኖዎች በሚገባው ቋንቋ አናግረው! ከቀኝ ከግራ፣ ከሸለቆው ከቁጥቋጦው፣ ከጉድባው ከዛፉ፣ ከዚህም ከዚያም ሳይል... ጨርሰህ አዋክበው! ወዳላሰበው አቅጣጫ እንዲዋጋ አስገድደው! ፋታ ሳትሰጥ ለመሸሸግም፣ ለመዋጋትም እንዳይመቸው አድርገው! ውጊያውን አንተ ወደሚመችህ መንገድ ቀይርበት!

ጠላት ሩቅ አልሞ ተኳሽ መሳሪያዎችንና ሠራዊቶችን ይዞብህ ከመጣ፣ የማይመቸውን ሥፍራ ጠብቀህ አፍንጫው ስር ሆነህ ተዋጋው፡፡ ጠላት በተሽከርካሪ ከባድ መሣሪያ ጭኖ ሲመጣ፣ ተሽከርካሪው በማያመቸው መልክዓ ምድር ላይ ጠብቀው! ጠላት ግዙፍ አፈሙዝ ደግኖ ሲመጣ፣ ከእግሩ፣ ከጎማው ሥር ደርሰህ አደባየው! ጠላት በዕቅድ እየተመራ ሲራመድ፣ ወደየት እንደሚራመድ እወቅና መንገዱን አፋልስበት፣ እንቅፋቱን አብዛበት፣ ሊሸሸግበት ያሰበውን ሥፍራ ቀድመህ አስበህ፣ ረመጥ አድርገህ ጠብቀው፣ ጦሩን በታትነው፣ ሰልፉን ቆራርጠው፣ ያቀደውን ትቶ፣ እዚያው በዚያው የእውር ድንብር ውሳኔ እንዲወስን አስገድደው!

ደግሞ በተቻለህ መጠን፣ በፍጹም፣ ለጠላትህ ጥቃት የምትመች የተኩስ መለማመጃ ቁና ሆነህለት አትጠብቀው! ነጻ ዒላማ አትተውለት! ላንተ ሲያልም በራሱ ወገን ላይም ጭምር እንዲያልም አድርገው! በቁንጫ መደብ ላይ እንደተኛ እንግዳ - የጦር አውድማው ለጠላትህ ለአፍታ እንኳ እንዳይመቸው አድርገው! ለጠላትህ ፊት ለፊት የምትገጥም ጅል አትሁንለት! እንደ ቁርበት ቁንጫ የለም ሲልህ ብቅ ብለህ የምትመዘልግ፣ እንደ ወገብ ቅማል እፎይ ሲል ብሽሽቱን የምታነደው፣ አለሁ ሲል ድንገት የጎን ውጋት የምትለቅ ቀሳፊ ጃዊሳ ሁንበት!

ጃዊሳ ማለት የባህር ላይ ወንበዴ ማለት ነው! ፓይሬትስ! ተናቃናቂ ነው! ለማንም ዕረፍት አይሰጥም! ባህሩን ጠንቅቆ ያውቀዋል! ተኩሶ አይስትም! በጀግንነቱ ታላላቅ መርከቦችን ይማርካል! የምድር ፓይሬት ሁንበት! ፀጥ ያለ የውሃ መንገድ ስጠውና፣ መሐሉ ላይ ሲደርስ፣ መመለሻው ሲርቅ፣ እንደ ጃዊሳ ደርሰህ መብረቅህን አቅምሰው! በምንም ተዓምር ጦርሜዳው ለጠላትህ እንዳይመቸው ተጠንቀቅ! ጠላትህ እንኳን በውጊያው ወቅት፣ አውደ ውጊያው ካለፈም በኋላ፣ ተንደርድሮ አንተን ሊገጥም የገባበትን ቀን ሲረግም እንዲኖር አድርገህ ልቀቀው! ይሄም ለነጋሪ ከተረፈ ነው!

ስልት 16/ ሴንተር ኦፍ ግራቪቲን (የስበት ማዕከልን) ለይተህ ዕወቅ!

ቡጢን በቡጢ አትመልስ፡፡ በጦርነት የታወቀው የደደብነት መለኪያ ይሄ ነውና፡፡ ይልቁን የጠላትህን ትልቁን ጎተራ ተመልከት፡፡ ግን ጎተራውን ብቻ ሳይሆን፣ ጎተራው እንዲቆም የደገፈችውን ትንሽዬ ዐለትም አስተውለህ ተመልከታት፡፡ እና ከጎተራው ጋር ከመታገል፣ ያቺን ዐለት ነጥለህ ምታት፡፡ ጠላትህ ጎተራው ይዘረገፋል!

በጦርነት ጠላትህ ትልቁን ኃይሉን የገነባው ጥቂት ወሳኝ ነገሮችን ተጠቅሞ ነው፡፡ እነዚያ ወሳኝ ነገሮቹ ምን እንደሆኑ በደንብ አስተውል፡፡ ለጠላት ኃይል የደም ዝውውር መስመሩ የትኛው እንደሆነ ፈጥነህ እወቅ፡፡ የጠላት ኃይል እንደልቡ እንዲንቀሳቀስ የሚያስችለው የጉልበት ምንጩ እምን ላይ እንዳለ ድረስበት፡፡ ጠላት ስንቁን የሚያገኘው ከየት ነው፣ በየት መስመር ነው፣ መሣሪያና ጥይቱን የሚጭነው በየት በኩል ነው? ዕወቃቸው! እና በጉሮሮው ላይ ቁምበት! ከመላ አካሉ ጋር ስትታገል አትገኝ!

እና ሁልጊዜም የጦርነትህ ዓላማ ያንን ዋናው ነገሩን (የስበት ማዕከሉን) መትተህ የውጊያ አቅሙን ባጭሩ ማኮላሸት ላይ ያነጣጠረ ይሁን! ጠላትህ ሲዋጋ በጣም የሚጠብቀውና የሚከላከለው አካሉ የትኛው እንደሆነ አስተውለሃል? ከአሰላለፉና ከአካሄዱ አይተህ ጠላትህ አጥብቆ የከለለውን ስስ ብልቱን እወቅ፡፡ መረጃዎችን በጥልቅ አንቀርቅበህ ፈትሽ፡፡ እና የጠላትህ የኃይል ማዕከል ምን እና የቱ ላይ እንደሆነ ድረስበት፡፡

በኢንጂነሪንግ የግንባታ ሣይንስ ትልልቅ ያረጁ ግንባታዎችን ለማፍረስ የሚጠቀሙበት አንድ የታወቀ ፊዚክስ የወለደው ህግ አለ፡፡ የሴንተር ኦፍ ግራቪቲ - የስበት ማዕከል - ቀመር፡፡ መሃንዲሶች በዚያ ቀመር ተመርተው - አንድን ተራራ ለማፍረስ ሲፈልጉ ተራራውን ሙሉ አያፈነዱም! የጊዜ፣ የወጪ ብክነት ነው! ደማሚታቸውን የቱና የቱ ቦታ ላይ መጥመድና ማፈንዳት እንዳለባቸው ያውቃሉ፡፡ ወይ ድልድይ አፍርሰው ለመስራት - ድልድዩ የቱ ቦታ ላይ ቢመታ፣ የቱ ቦታ ላይ ቢሰበር፣ ድልድዩ ከነመላ አካሉ እንክትክቱ እንደሚወጣ ጠንቅቀው ያውቃሉ፡፡

አንድን ህንፃ ከነክብደቱ ያቆመው ዋነኛው የምርኩዙ ስፍራ የቱ ቦታ ላይ እንዳለ መሃንዲሶቹ እንደሚያውቁት ሁሉ፡፡ ህንጻን ሲያፈርሱም ያንን ቦታ መርጠው እንደሚያፈርሱት ሁሉ፡፡ ሲገነቡም ደግሞ ሙሉ ህንጻውን እንዲሸከምላቸው የቱን ቦታ ከሌሎቹ በላይ አጠንክረው ማቆም እንዳለባቸው ከፍተኛ ትኩረት ሰጥተው እንደሚሠሩት ሁሉ፡፡ አንተም የጠላትህን ወሳኝ የልብ ትርታ፣ ወሳኝ የደም መሯሯጫውን፣ የስበት ማዕከሉን አስልተህ ፈትነህ ድረስበት፡፡

ጠላትህ ብዙውን ጊዜውን የፈጀው፣ ብዙውን ትኩረቱን የሰጠው የቱን ኃይሉን ለመገንባት ነው? ከጠላትህ ጫካ የመሠለ ሠራዊት ውስጥ የትኞቹ ዛፎች ናቸው ለጠላትህ የልብ ሞተር ሆነው እያገለገሉት ያሉት? የትኛው የጠላትህ አፍንጫ ቢመታ ነው፣ የትኛው ዓይኑ የሚያለቅሰው? ፈልግና አግኘው! እና ያንን የስበት ሥፍራ ነጥለህ፣ መርጠህ፣ አነጣጥረህ ምታው! ድል ካንተ ጋር ነች!

ስልት 17/ በጠላትህ መካከል ጠብንና አለመተማመንን ዝራ! ምሬትን ቀስቅስ! ጠላትህን ከፋፍለው! እና ሲነጣጠል ምታው!

ፀሐይን ቀና ብለህ እያት፡፡ ከተፈጠረች ሚሊየን ዓመታት ሆኗታል፡፡ ግለቷ ግን በዘመን ብዛት እየጨመረ እንጂ እየቀነሰ አልመጣም፡፡ የከፋፍለህ ግዛው ስልትም እንደዚያ ነው፡፡ ጥንትም ይተገበር ነበረ፡፡ አሁንም ከነጉልበቱ አለ፡፡ ጠላትህ ባንድ ላይ ኃይሉን አሰባስቦ ከመጣብህ የሚጠብቅህ አደጋ ከባድ ነው፡፡ ስለዚህ ጠላትህን እርስ በእርሱ እንዳይስማማ፣ የተለያየ አጀንዳ ስጠው፡፡

ጠላትህን ሰሜንና ደቡብ፣ ምስራቅና ምዕራብ እያልክ ነጣጥለው፡፡ በቋንቋው እየከፋፈልክ ነጣጥለው፡፡ በጎሳው እየከፋፈልክ እርስ በእርሱ ነጣጥለው፡፡ በባህሉ በትውልዱ በሀብቱ በሥልጣኑ እየመተርክ የጠብንና የቅሬታን መንፈስ በጠላትህ መካከል ቀን ከሌት ተግተህ ዝራ፡፡ አንዱ ለአንዱ መስዋዕት እንዳይሆን ጥርጣሬንና ቁርሾን መዝዘህ በመካከሉ ነስንስበት፡፡ ከብዙው መካከል ለአንዱ የላቀ ወዳጅነት ያለህ መስለህ ቅረብ፡፡

በዓለማችን የታወቁ የሂሳብ ሊቆች የሚጠቀሙበት የማቃለል አልጎሪዝም አለ፡፡ ያ አልጎሪዝም ትልቁን ፕሮብሌም ለመፍታት ያን ፕሮብሌም ወደ ብዙ ትንንሽ ፕሮብሌሞች የመሸንሸን ስልት ነው፡፡ ከትልቁ ውስብስብ ችግር ጋር ከምትታገል ይልቅ፣ የዳጎሰውን ውስብስብ ወደ ትናንሽ ቀላላል ተግዳሮቶች አውርደህ፣ እያንዳንዳቸውን ትናንሾቹን ነጣጥለህ ብትፈታታቸው ነው የሚቀልህ ትልቁን ችግር ለመፍታት፡፡ ጠላትህንም እንደ አንድ ትልቅ ችግር ቁጠረው፡፡ ችግሩን ለመፍታት ጠላትህ ወደ ትናንሽ ችግሮች ተለይቶ፣ ተሸንሽኖ፣ ተነጣጥሎ መቀመጥ አለበት፡፡

ጠላትህን በተለያየ መለኪያ እየሠፈርክ ሸንሽነው! በወረዳ፣ በአውራጃ፣ በጎጥ፣ በቀዬ ከፋፍለው! በቻልከው ነገር ሁሉ ከፋፍለው! እና ሲነጣጠል እየጠበቅህ በየተራ ምታው! ሁሉም የጠላትህ ኃይል ባንድ ላይ ተባብሮ ታላቅ የባላጋራ ማዕበል ፈጥሮ ከሚመጣብህ ይልቅ፣ የተወሰነውን ነጣጥለህ፣ ግማሹን ወዳጅ፣ ግማሹን ጠላት አድርገህ፣ አጠቃላዩን ጠላት ገባርህ የምታደርግበትን መላ አስልተህ፣ አጥንተህ፣ ተውነህ፣ አስመስለህ፣ ተነጥፈህ ፍጠር!

የከረመ ብሶትን በጠላትህ መንደር አቀጣጥል! አንድ የማያደርጋቸውን ነገሮች መንጥረህ አሳያቸው! ሐይማኖታቸው ምን ያህል እርስ በእርስ እንደሚጋጭ አስረዳቸው! አንዱ ከሌላው የበለጠ ምን ያህል የሰለጠነ እንደሆነ አሳያቸው! አንዱ በሌላው ዓይን ምን ያህል ዝቅ ተደርጎ እንደሚታይ አስጣጣላቸው! ጠላት እንዳለመው ድል ቢቀናው ማን በማን ኪሣራ እንደሚበለጽግ ቀመሩን በግልጽ አሳያቸው!

ላበሩብህ ጠላቶች ቀን ከሌት እርስ በእርስ የሚነጣጠቁበትን ዳቦ አቀብላቸው! አንድነታቸውን በሺህ አቅጣጫዎች ሸርሽር! እና መነጣጠላቸውን እርግጠኛ ስትሆን፣ ነጣጥለህ ምታቸው! ግድየለህም ስለውጤታማነቱ አታስብ! ይህ ለሺህ ዓመታት በተግባር የተፈተነ የጦር ስልት ነው! የተነጣጠለ ጠላት በቀላሉ በእጅህ መዳፍ ላይ ይወድቃል! ነጣጥለህ በለው!

(በነገራችን ላይ በዚህ ስልት ጠላትህም በአንተ ላይ ሊጠቀምብህ ይሞክራል! ጠላትህ የቀበሮ ባህታዊ ሆኖ አንዱን ወዳጁ፣ አንተን ጠላቱ አድርጎ ካንተ ጋር የሚተባበሩትን ሁሉ እያባበለ፣ እያሰባ ይይዛል! ያንተ ህዝባዊ ኃይል በጋራ ጠንክሮ ከፊቱ እንዳይቆም በተለያዩ ከፋፋይ አጀንዳዎች በህዝብህ መሀል መቃቃርና ልዩነት እንዲፈጠር ተግቶ ይሠራል! ጠላትህ ነጣጥሎ ሊመታህ እንደሚያስብ እወቅ! ነጣጥሎ ሊመታህ ሲያስብ፣ እንዳይሞክር ቀድመህ ነቅተህ ጠብቅ! ቢሞክርም ‹አካሄዱን አይተህ፣ ቀድመህ ጭብጦውን ቀማው›! የቀደሙትን ስልቶችም አስባቸው! አንዳንዴም ለጠላትህ በምኞቱ መሠረት የተከፋፈልክ መስለህ ጠብቀው! ካንተ ነጥለህ አጋር ስጠው! አጋርህን አምኖ አንተን ሊወጋ ሲንቀሳቀስ፣ ከውስጥና ከውጭ አርበኞች፣ በሁለት በኩል ብሽሽቱን ወግተህ ቀስፈው!)

ውድ አንባቢ፦ ደራሲው ሮበርት ግሪን በዘመናት የሰው ልጅ ጦርነቶች ውስጥ ይዞህ እየነጎደ ነው፡፡ ይህን የሰው ልጅ ለዘመናት የተከማቸ ዝክር እያነበብክ የሆነ ትልቅ የሰው ልጆች አውደ ፍልሚያ ልክ አሁን እንደተገኘህበት እውነት ሆኖ በሁለመናህ መጣብህ? ደራሲው ስለ አንድ ጦርነት ውሎ እያወራልህ - በአዕምሮህ ሺህ ዓይነት ውሎዎች በቅፅበታት ፍጥነት ሥጋ ለብሰው ተመላለሱብህ? በጀግንነት የተመላለሱት የአያት የቅድመ-አያቶችህ መንፈስ ልብህን እያሞቀ ከምናብህ ይቀሰቅስሃል?

ልብ በል! ጦርነት የሚመለክ ነገር የለውም፡፡ የምድሪቱ የውጊያ ሜዳዎች ሁሉ ስንቱን የጀግንነት ስቃይ የሚናገሩ ህያው የጀግኖች ኃውልቶች መናቸውንም አትርሳ! ነገር ግን ሳይወዱ በግድ ለነፃነታቸው ጦርነት የገቡ ዘሮችህ የጀግና ትንፋሽ ያሙቅህ! ሁሌም እጅህን ወደ ኋላ አጣጥፈህ፣ ከጉልበትህ ዝቅ ብለህ፣ ከወገብህ ሸብረክ ብለህ… በክብር ሀገርህን ከነነጻነቷ ለሰጡህ ባለውለታ፣ ቀደምት አርበኛ አባቶችህ በክብር እጅ ንሣ! እና የጀግና አባቶችህ ስሜት ስለተጋባብህ ደስ ይበልህ!

ይሄ የሮብርት ግሪን ‹‹33ቱ የጦርነት ስትራቴጂዎች›› መጽሐፍ ይዞህ የማይነጉድበት ቦታ የለም! የመጨረሻዎቹን የጦር ስልቶች ይዘን ዳግመኛ መገናኘታችን አይቀርም! ባንገናኝም፣ ባናወራቸውም ኢትዮጵያዊ ነህ! የአርበኞችን ልብ የታጠቅክ! ባልግርህም ታውቃቸዋለህ! ስለሆነም ፍፁም በሆነ ኢትዮጵያዊ የጀግኖች ዜማ… በፍቅር፣ እሰናበትሃለሁ! እንዲህ እያልኩ፡-

“ወዘት በይ ልቤ፣ እንደ ጀበና
አልወጣልሽም፣ የጦር ባፈና
የጦር ባፈና…፣ የጦር ባፈና…
የጦር ባፈና… !”
(— ፋኖ ፋኖ፣ ካሣ ተሰማ)

በመውጣታችን በመግባታችን ጀግንነት አይለየን!

አማራነት ጀግንነት ነው!

ሕዝብ ያሸንፋል!
©Bezabih Mekonen
ፈጣሪ ነገደ አማራን ይባርክ!!

No comment,©Zemdkun Bekele.
12/04/2023

No comment,
©Zemdkun Bekele.

09/02/2023

ቅዱስ ሲኖዶስ ዛሬ መግለጫ ሰጥቷል።

ቅዱስ ሲኖዶስ ዛሬ በሰጠው መግለጫ ትላንት ምሽት የመንግሥት ደኅንነት የጋራ ግብረ-ኃይል " ወቅታዊ የፀጥታ ጉዳይ " ን አስመልክቶ የተሰጠው የሰልፍ ክልከላ መግለጫ እንደማይቀበል አሳውቋል።

" መንግሥት አሁንም ችግሩን ለመፍታት ሳይሆን ቤተክርስቲያኒቱን ለአንዴና ለመጨረሻ ለማውደምና ቤተ ክርስቲያኒቱን ለማጥፋት የታወጀ አዋጅ መሆኑን በጽኑ እንድናምን አድርጎናል " ብሏል።

ቅዱስ ሲኖዶስ መንግስት ከአጉል እልከኝነቱ ወጥቶ ፦

- ከሕገ ወጦቹ ግለሰቦች ጋር በመተባበር በአደባባይ እየፈጸመ ያለውን የሕግ ጥሰት ዛሬን ጨምሮ በቀጣዮቹ ፪/ሁለት/ ቀናት ውስጥ እንዲያቆም እና ሕግ እና ሥርዓትን እንዲያስከብር

- በኃይል የወረራቸውን መንበረ ጵጵስና እና አጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት ለቆ ለቤተክርስቲያኒቱ ሕጋዊ መዋቅር እንዲያስረክብ፣

- ያለአግባብ ያሠራቸውን ካህናት እና ምእመናን ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲለቅ፣

- ቤተ ክርስቲያኒቱ ላይ ለፈፀመው በደል በአደባባይ ይቅርታ እንዲጠይቅ፤

- በካህናት እና ምእመናን ላይ ለደረሰው ሞት እና የአካል ጉዳት ተገቢውን ካሳ እንዲክስ እና የወደሙ ንብረቶቿን እንዲጠግን በጥብቅ ጠይቋል።

ቅዱስ ሲኖዶስ ፤ መንግሥት ሕግ እየጣሰ እና የቤተ ክርስቲያኒቱን ክብር እና ልእልና እያዋረደ የሚቀጥል ከሆነ ቤተ ክርስቲያን መብቷን ለማስከበር እስከአሁን ድረስ ፍጹም ሰላማዊ የሆነውን እንቅስቃሴዋን አድማሱን በማስፋት በየካቲት 5/2015 ዓ/ም ለማድረግ ያቀደችውንና ያሳወቀችውን ሀገር አቀፍ እና ዓለም አቀፍ ሰላማዊ ሰልፍ ያለማንም ከልካይነት በራሷ አደባባይ የምታከናውን መሆኑን አሳውቋል።

መንግሥት ድርሻው ሰልፉ ሰላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ መንግሥታዊ ኃላፊነቱን በአግባቡ መወጣት ብቻ መሆኑን ያሳሰበው ቅዱስ ሲኖዶስ " ዛሬም ቢሆን መንግሥት ቆም ብሎ በማሰብ ከእኛ ከአባቶች ጋር ሃይማኖታዊ ፣ ቀኖናዊ እና መንፈሳዊ የአስተዳደር ሥርዓታችንን ባልጣሰ መልኩ ለመነጋገር እና ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታት ጥረት ካደረገ በውይይት ለመፍታት መንፈሳዊ በራችን ክፍት መሆኑን እናሳውቃለን " ብሏል።

ከዚህ ውጭ ግን በሁለቱ አባቶች መካከል የተፈጠረ ችግር እየተባለ የሚነገረው ፖለቲካዊ ጨዋታ የመንግሥት እንጂ በሀገሪቱ ሕጋዊ ሰውነት የሌላቸውና ከቤተ ክርስቲያን የተለዩ ግለሰቦች ጋር ማነጻጸር ሕገ መንግሥታዊም ሆነ ሞራላዊ የሕግ መሠረት የለውም ሲል አስገንዝቧል።

ቅዱስ ሲኖዶስ ሰላማዊ ሰልፍ ማድረግ በህገመንግስቱ የተደነገገ መሰረታዊ መብት መሆኑን ገልጾ ቤተክርስቲያን የጠራችውን ሰላማዊ እና ሕጋዊ የሆነ የመብት ጥያቄ የማፈን ሂደትን በጥብቅ እንቃወማለን ብሏል።

08/02/2023

የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ቄሶች በኦሮሚያ ፖሊስ ሲደበደቡ የሚያሳይ ተንቀሳቃሽ ምስል..
©ዘመድኩን በቀለ

05/02/2023

ሽምግልና ቀልድ ነው!
©Getachew Shiferaw

1) "መንግስት" የተወገዘ ቡድን ብቻ አይደለም የደገፈው። የቤተ ክርስቲያንን ክብር ያወርዳሉ ያላቸውን ሰዎች ሰብስቦ ነው ፕሮጀክቱን እያስኬደ ያለው። የቤተ ክርስቲያንን ህግና ስርዓት መናድ ብቻ አይደለም። የመጨረሻውን ንቀት፣ ጥላቻ ያሳየበት ነው።

2) ሲኖዶሱ ለምኗል። በመንግስት ደረጃ ጥቃት ታውጆበት እንኳን የማሰቢያ ጊዜ ሰጥቷል። መንግስት የተወገዘውን ቡድን ደግፎ የቤተ ክርስቲያን በር ሰብሮ ሲገባ ነው ሰልፍ የጠራው።

3) ቤተ ክርስቲያን የቀራት ነገር የለም። ህጓ ተጥሷል። ተንቃለች። ተጠቅታለች። ልጆቿ ተገድለዋል። ለሽምግልና የሚሆን ክፍተት አልቀራትም። እያንዳንዱን እየሄደችበት ያለው በህጓ መሰረት ነው።

4) መንግስት የተወገዘውን ቡድን የማስቆም ሙሉ አቅም እያለው ሽምግልና ሊጠይቅ አይችልም። መሆን ካለበት የተወገዘው ቡድን በሰራው ወንጀል ተጠይቆ፣ መንግስት ለፈፀመው ወንጀል ተጠያቂ ሆኖ፣ ቤተ ክርስቲያንንና የህዝብን ቁስል የሚያሽሩ እርምጃዎች ቢወሰዱ ነበር። አያደርጉትም! ማዘናጊያ ብቻ ነው። የትግሉን ርቀት መለኪያ ነው!

ሽምግልና ቀልድ ነው። የቤተ ክርስቲያን በርን እየሰበረ ለሚገባ የተወገዘ ቡድን ድጋፍ የሚሰጥ ኃይል ስለ ሽምግልና ለመጠየቅ ሞራል የለውም። አያምንበትምም። ቤተ ክርስቲያንን ያዋርዱልኛል ያላቸውን ሰዎች ከየትም ለቃቅሞ የማፍረስ ስራ እየመራ ያለ ኃይል ስለ ሽምግልና የሚያወራው ስለጨነቀውና ስላላዋጣው ብቻ እንጅ ሊያምንበት አይችልም።

ቤተ ክርስቲያንንና ህዝብን እናዋርድበታለን ያሉበትን የመጨረሻውን ርቀት ሄደዋል። የቤተ ክርስቲያንንና ህዝብን ክብርና ህልውና የሚያስጠብቀውን የመጨረሻው ርቀት ድረስ መሄድ ያስፈልጋል። በአንድ በኩል የቤተ ክርስቲያን በር እየሰበረ በሌላ በኩል ሽምግልና እየላከ የሚያወናብድ አካል ማወናበጃው እንደማይሰራ ማሳየት የሚቻለው ጥቃቱን ለማስቆም የሚቻለውን የመጨረሻ ርቀት መሄድ ሲቻል ነው።

ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስትያን የማህበራዊ ሚዲያ መለያዎቿን ከስር ባለው ምስል ቀይራለች።
03/02/2023

ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስትያን የማህበራዊ ሚዲያ መለያዎቿን ከስር ባለው ምስል ቀይራለች።

06/12/2022

ብዙ አለም አቀፍ ሚዲያዎች በኦሮሚያ የተፈፀመዉን የአማራ ጭፍጨፋ በግልፅ ዘግበዉታል።

ሰበር!ዛሬ ናይሮቢ ላይ በትህነግ እና በአብይ መንግስት መካከል በተፈረመ ስምምነት መሰረት  #ወልቃይት እና ራያን ወደ ትግራይ የመመለስ ሂደት በይፋ ተጀምሯል! በስምምነቱ መሰረት የአማራ ሀይ...
12/11/2022

ሰበር!
ዛሬ ናይሮቢ ላይ በትህነግ እና በአብይ መንግስት መካከል በተፈረመ ስምምነት መሰረት #ወልቃይት እና ራያን ወደ ትግራይ የመመለስ ሂደት በይፋ ተጀምሯል! በስምምነቱ መሰረት የአማራ ሀይሎች ከወልቃይት እና ራያ እንዲወጡ የሚያስገድድ ስምምነት ተፈፅሟል። አንቀፅ (2) D ይመልከቱ!!

28/08/2022

ስለ አሁናዊ ሁኔታ ለምትጠይቁኝ…!!
በዘመድኩን በቀለ

"…በራያ፣ በቆቦ ኔትወርክ ስለሌለ ምንም መረጃ የማገኝበት መንገድ የለም። ስለዚህ ፈጥሬ አላወራላችሁም። እንደነ ጋሽ ደርቤ ኔትወርክ በሌለበት በመንፈስ ፈጥሬ አልነግራችሁም። እናም በራያ፣ በቆቦ፣ በሮቢት፣ በዞብል ተራራ ላይ ምን እየተካሄደ እንደሆነ የሚያውቁት በሥፍራው ያሉት ዜጎችና በውጊያ ላይ ያሉ ወንዶች ብቻ ናቸው። አከተመ።

"…መብራት ሲለቀቅ፣ ኔትወርክ ሲሠራ ግን በቦታው ምን እንደተካሄደ ሁላ ጭምር ነጭ ነጯን እነግራችኋለሁ። በመከላከያ፣ በፋኖና በዐማራ ልዩ ኃይል ውስጥ የነበሩ የእኔ የመረጃ ምንጮች ትናንት ይህን ከነገሩኝ በኋላ አልተገናኘንም።

"…ዘመዴ ኔትዎርክ እስከሚጠፋ ድረስ አለን። ኮድ 0021 ባለበት ግንባር (ኮዱ የግላችን ነው) እነሱ ወያኔዎቹ ካላኮርማ ሮቢትን ለመያዝ ርብርብ እያደረጉ ነው። እዚህ በእኔ ግንባር እየተዋደቀ ያለው ፋኖም ሆነ ሚኒሻ ተተኳሽ የለውም። ያለችው ጥቂት ተተኳሽ እንዳለቀች ካላኮርማ ሮቢትን ያለምንም ከልካይ ይይዟታል። አሁን ውጊያው የኛዎቹ ፋኖዎች ማደሬበር ከሮቢት ከተማ ወደ አራዱም መስመር ካለው ተራራ ማደሬ በር ሕወሓት፣ ከማደሬ በር ፊት ለፊት ካለው ለጋይሶራ ከሚባል ሰንሰለታማ ተራራ ላይ ናቸው። ብዙ የተቆረጠ ፋኖ እና የዐማራ ልዩ ኃይል በቆቦ በአራዱም አለ። ፋኖውም የዐማራ ልዩ ኃይሉም እንደ ወታደሩ ከምንሸሽ ሞታችንን እንመርጣለን ብለው ነው ጥይታቸው እስኪያልቅ እየተዋጉ ያሉት። ካልተገናኘን ሰላም ሁን። ወደ ወልድያ ስላለፈ ለኮድ 0027 ደውልለት። ሰላም ሁን ዘመዴ። ተባብለን ነው የተለያየነው።

"…የመጣው ኃይል ዐማራን የሚያሸንፍ ሆኖም አልነበረም። የሆነው ሆኖ አሁን ምን ላይ እንዳሉ የማውቀው ነገር የለም።

"…ድል ለኢትዮጵያ ሃገሬ…!! ውድቀትና ሞት ለሁሉም ጠላቶቿ…!!

27/08/2022

የባለፈው ስህተት እንዳይደገም!

ትህነግ በራያ ግንባር እንደለመደው በሕዝብ መአበል መጥቷል። ዘራፊውንም ተዋጊውንም አግተልትሎ በኢትዮጵያ መከላከያ ላይ ጥ*ቃት ከፍቷል። ከእርዳታ ድርጅቶች ነዳጅ ሰርቆ ወደ ማ*ጥ* ቃ**ት የገባው ትህነግ ለእርዳታ ድርጅቶች ከአማራ ክልል ዘርፌ እመልስላቸዋለሁ ብሎ አስቧል። ከፍተኛ የተተኳሽ እጥረት ያለበትም በመሆኑ ሰራዊቱን ከብቤ ተተኳሽና መሳርያ አገኛለሁ የሚል እቅድ አለው። ከፊት የሚያሰልፈውን መንጋ ዘርፈህ ትመጣለህ እያለ አባብሎታል። ትግራይ ውስጥ በትህነግ ታፍኖ የከረመው ወጣት ከባለፈው አመት በበለጠ እድል ሲያገኝ ለኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት እጅ እየሰጠ ቢሆንም ትህነግ የገፋ ሲመስለው ግን ባለፈው ከፈፀመው ግፍ በላይ ለመፈፀም ወደኋላ የማይል ጨ*ካ*ኝ መሆኑ መረሳት የለበትም።

ትህነግ እስካሁን ባለው ከፍተኛ ኃይል እየረገፈበት ቢሆንም ለእሱ የሚያልቀው የትግራይ ወጣት ነፍስ ከጥይት ዋጋ አይበልጥበትም። የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት፣ የአማራ ልዩ ኃይልና ፋኖ ከፍተኛ ተጋድሎ በማድረግ የትህነግን መንጋ እየመከተ ይገኛል። ይሁንና ትህነግ ካለው እቅድ አንፃር በዚህ ግንባር የመጣውን የትህነግ መንጋ ኃይል አሰባስቦ መመከት ግዴታ ነው።

ትህነግ እድል ካገኘ ባለፈው ከፈፀመው በላይ ውድመት እንደሚያደርስ የሚገመት ነው። ስለሆነም የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት፣ ባለፈው አመት መከራውን ያየው ሕዝባችን ላይ የተከፈተውን ጥ**ቃ*ት ከየትኛውም ጉዳይ አስበልጦ ኃይልን አሰባስቦ መመከት ያስፈልጋል።

የባለፈው ስህተት እንዳይደገም፣ ከአሁኑ መረባረብ ግዴታ ነው። ሁሉም በሚችለው ተረባርቦ ሕዝብ ከስቃይ ማዳን ግድ የሚልበት ሌላ ዙር የትህነግ ጥ*ቃ**ት ላይ ነን።
©ጌታቸዉ ሽፈራዉ

27/08/2022

ጦርነቱ መሬት ላይ ያለው ሃቅ…!!
በዘመድኩን በቀለ

"…ያለ ተለዋጭ፣ ያለ ተተኪ፣ ያለ አዛዥ፣ ያለበቂ ቅንጅት ለጦርነት የተላከው የመከላከያ ሠራዊት አሁን ሙሉበሙሉ ከግንባር ተበትኗል። በእግሩም በመኪናም ወደ ወልድያ እየቀደደው ነው። ባለ ቀይ ቦኔቶቹ የመከላከያ ወታደሮች ዞብል ተራራ አካባቢ ተቆርጠዋል። ጋቲራ በወያኔ ቁጥጥር ስር ነው። ወታደሮቹ ከከበባ ለመውጣት ብቻ ነው የሚዋጉት።

"…ህወሓት ባላት የሰው ኃይል እና በሚደርሳት የተሟላ መረጃ በመታገዝ አሁን ቆቦን ሙሉ በሙሉ መያዟ ተነግሯል። በአረፋ ጊዮርጊስ ወርደው፣ ቀጭን ቦይ ጎዲናን ዘግተዋል። ለሮቢት 7 ኪሎ ሜትር ርቀት ነው የቀራቸው። አራዶም ተይዟል። የቀጭን ቦይ ጎዲና ድልድይ በህወሓት ስለተያዘ አሁን ትልቁ ወደቆቦ የሚወስደው የፌደራል መንገድ ተዘግቷል። አከተመ።

"…መከላከያው የምሥራቅ ዐማራ ፋኖን አስከብቦ እሱ በእግሩ እንዲሸሽ ነው የተደረገው። ፋኖ ከበባውን ሰብሮ ለመውጣት ትንቅንቅ ላይ ነው። የፋኖው መሪ ምሬ ወዳጆ ግን ሮቢት ከተማ ላይ ታይቷል። ውጊያው ላይ የለም።

"…የሚገርመውና የሚደንቀው ነገር ማለት ነው ሮቢት ሃይስኩል ውስጥ 5 መኪና ኦራል ሙሉ ተተኳሽ ጥይት ተከዝኖ ተቀምጧል። የምሥራቅ ፋኖ አባላትም፣ የመከላከያ ወታደሮችም ተተኳሽ ስጡን ብለው ቢሄዱም ኦሮሚኛ ተናጋሪዎቹ አመራሮች ከበላይ ስላልታዘዝን አንሰጥም በማለት ከልክለዋል። ከብዙ ንትርክ በኋላ 2 ጆንያ ብቻ ጥይት ለፋኖዎች እንዲሰጥ ተወስኖ ፋኖዎች ወስደዋል። ተተኳሹ ህወሓት ወደ ወልድያ ለምታደርገው ጉዞ ተዘጋጅቶላት እየጠበቃት ነው።

"…አዳሜ ህወሓት በሰረቀችው ነዳጅ እንግሊዝ፣ ጀርመን፣ ሳማንታ ፓወር፣ ብሊንከን፣ እያልክ አዝግ። ጨዋታው ሌላ ነው። ዐቢይ አህመድ ወሎን ሽጦታል። ጎንደር ይቀረዋል።

• ለማስታወስ ያህል መከላከያ ሚንስትሩ ትግሬ ነው። አይ ዐማራ…!!

24/06/2022

ናዕት
(እያመመው ቁጥር ፪)
➖➖➖➖➖➖

ዶፍ (x2) …….

ግርም ያለ ጊዜ ሆነ ሰአቱ
በዳንኪራው ደምቆ በምቱ
ለደቂቃም አይቆይ በስልቱ
ቦግ እልም እያለ መብራቱ (x2)

ኡኡ …… ሬጌ ናዕት
ሬጌ ናዕት

� ብልጭልጭ ቢሆን ዳሱ

ኡኡ …… ሬጌ ራት
ሬጌ ናዕት

ማን ሊታደም ከድግሱ

ኡኡ …… ሬጌ ናዕት
ሬጌ ናዕት

ብልጭልጭ ቢሆን ድንኳን

ኡኡ …… ሬጌ ራት
ሬጌ ናዕት

አይለውጥ ጎግ የእውነት መልኳን

ቢጋርድ ሀሳብ አርጎ ሜዳን ገደል
እም አእላፍ ስቃይ ጭንቀት ቢደረደር
የነፍስ ሕላዊ መሻት ዋዌ ሳይገባቸው
ስንቶች በዘር ተዘፍቀው ታዘብናቸው

ዘውግ ያወረው ድንበር ማላውን የረሳ
ሳር ያለመልማል ዛሬም በእልፍ አእላፍ ሬሳ
እያረረ ሆዴ ብስቅ በማሽላ ዘዴ
ና ታደም ይለኛል ደግሞ በነ ኡኡ ሬጌ

ኡኡ …… ሬጌ ናዕት
ሬጌ ናዕት

ብልጭልጥ ቢሆን ዳሱ

ኡኡ …… ሬጌ ራት
ሬጌ ናዕት

ማን ሊታደም ከድግሱ

ተላላ ዝንጉ ሰብ የሙታን ሸማ ደዋሪ
ምን አለ አይል ከፊት ሆኖ ቅርብ አዳሪ
ተናገር አፌ ደፍረህ ሳትናወጥ ከቶ
ዝም አይሆንም ሜዳ ተራራ ሞት መጥቶ

ከበሮ ግም ሲል በእምቢ ነጎድጓድ ምቱ
ይናዳል የዘር ድንዛዜ ያ ድውይ ቤቱ
ገለል በል ኤሳው ነፍሴን አንቀህ አታሳሳት
ብታገስ ባሰ ባንተ የልቤ እሳት

እያመመው መጣ (x2)

ያዳፈነው እሳት ከሆዱ ሳይወጣ
ልቤ እንደካቻምናው እያመመው መጣ
የሚያዜም ይመስላል ሲያጣጥር ተጨንቆ
ውስጡን ሲሰብቅለት ኡ….እያለ ማሲንቆ
ኡ….ኡ…..

እያመመው መጣ (x2)

የተረገጠ እውነት በጊዜ ውስጥ እግር
ታፍኖ የቆየ በሆታ ግርግር
ትንሽ ጋብ እንዳለ የጭብጨባው ጩኸት
እረጭ ሲል ውሸት ይናገራል እውነት

እያመመው መጣ (x2)

ቂምን ሻረውና ወይ ፍቅርን አንግሰው
ሁለት ሆኖ አያውቅም አንድ ነው አንድ ሰው
ከሀገርም ይሰፋል ያ የፍቅር ገዳም
መጠሪያው ሰው እንጂ ዘር አይደለም አዳም

ዶፍ ዶፍ ቢዘንብ እሳት
ሀገሬን ላልረሳት
ቃል አለኝ ኖሬ ሞቼም ልክሳት (x2)

ዳር አለው እንዴ ድንበር …….. ዳር አለው እንዴ
ዳር አለው እንዴ ፍቅር …….. ዳር አለው እንዴ
የዘር ሐይማኖት ድንበር …….. ዳር አለው እንዴ
ዳር አለው እንዴ ፍቅር …….. ዳር አለው እንዴ
በዚህ ለፀና እውነት …….. ዳር አለው እንዴ
የፍቅር ሀገር ከጥንት …….. ዳር አለው እንዴ
ዘብ ያድራል ሁሉም እስከሞት …….. ዳር አለው እንዴ
ዶፍ ቢዘንብ እቶን እሳት …….. ዳር አለው እንዴ

ዶፍ ዶፍ ብዘንብ እሳት
አገሬን ላልረሳት
ቃል አለኝ ኖሬ ሞቼም ልክሳት (x4)

-----------------------------//----------------------

የቃላት ፍቺ

ናዕት…. ሮሚጦ ቂጣ
ዋዌ….የልብ (የውስጥ) ሀሳብ ድምፀት (INTENTION)
ድውይ….ደዌ(በሽታ)
ዘውግ…..ዘር(ጎሳ)

---------------------------------------------------

ግጥም — ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ)
ዜማ — ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) እና ቆየት ያለ የሀገረሰብ ባህላዊ ዜማ
ሙዚቃ ቅንብር ፥ ኪቦርድ እና ሚክሲንግ — በረከት ተስፋዝጊ (ቤኪ)
ጊታር — በረከት ተስፋዝጊ(ቤኪ)
መሰንቆ — ማንደፍሮ ካሳ (ቤቢ)
ድምፅ ቀረፃ እና ማስተሪንግ — ማሩ ዓለማየሁ

ምስጋና — ይህ ሥራ የተሳካ እንዲሆን በተለያየ መንገድ አስተዋፅዖ ላደረጋችሁ በሙሉ ::

መታሰቢያነቱ — ላለፉት አራት አመታት በተለያዩ የሀገራችን ክፍሎች አላግባብ በግፍ ለተገደሉ ፥ አካላቸው ለጎደለ እና ከመኖሪያ ቀያቸው ለተፈናቀሉ ንፁሀን ዜጎች በሙሉ ይሁን።

Address


Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethiopia Today- ET posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Videos

Shortcuts

  • Address
  • Alerts
  • Videos
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share