Info Daily

Info Daily thi page is posting information related to political, economic & social activities from trusted sou

የአዲስ አበባ ፖሊስ በጉለሌ ክ/ከተማ በአንድ ተማሪ ላይ የድብደባ ወንጀል የፈፀሙ የፖሊስ አባላትን በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ እያጣራ መሆኑን ገለፀ፡፡                *******የ...
17/06/2022

የአዲስ አበባ ፖሊስ በጉለሌ ክ/ከተማ በአንድ ተማሪ ላይ የድብደባ ወንጀል የፈፀሙ የፖሊስ አባላትን በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ እያጣራ መሆኑን ገለፀ፡፡
*******
የፓሊስ አባላት የህግ በላይነትን ለማስጠበቅ በሚያከናውኑት የትኛውም አይነት እንቅስቃሴ የሰው ልጆች ሰብዓዊ መብቶችን አክብሮ በማስከበር ህጋዊ አግባብ መሆን እንዳለበት የአ/አበባ ፖሊስ አስታወቀ፡፡

ጉለሌ ክ/ከተማ ወረዳ 7 ሰሜን ማዘጋጃ ጋበር ሆቴል በሚባል አካባቢ ሰኔ 8 ቀን 2014 ዓ/ም ከቀኑ 5 ሰዓት ላይ በክፍል ውስጥ ርንቺት ተኩሶ ከት/ቤት ውስጥ አምልጦ የሄደ አንድ ተማሪን አራት የፖሊስ አባላት ተከታትለው በመያዝ የድብደባ ወንጀል ፈጽመውበታል፡፡

ህገ- ወጥ ድርጊቱ እንደተፈፀመ ፖሊስ በደረሰው መረጃ እና ባደረገው ማጣራት ድል በር 2ኛ ደረጃ በሚባል ት/ቤት የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ነው በሚል ፕሮግራም ላይ በክፍል ውስጥ በተደረገ ዝግጅት አንድ ተማሪ ርችት እንደተኮስ እና በትምህርት ቤት ውስጥ ርችት መተኮሱ ሌሎች ተማሪዎችን እንደረበሻቸው ለፖሊስ መረጃ ይደርሰዋል፡፡ በእለቱ ድርጊቱን ፈፅሟልየተባለው ተማሪ ከት/ቤቱ ቅጥር ግቢ እንደወጣ የተነገራቸው 4 የጉለሌ ክ/ከተማ ፖሊስ መምሪያ አባላት ክትትል በማድረግ ሰሜን ማዘጋጃ ጋበር የሚባል ሆቴል አካባቢ ተማሪውን ይዘውት ተገቢ ያልሆነ ድብደባ ፈፅመውበታል፡፡

የአ/አበባ ፖሊስ እንዳስታወቀው ፖሊስ መረጃው ካደርሰው በኋላ ተጠርጣሪ የፖሊስ አባላቱን በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ እያጣራይገኛል ፡፡
በማነኛውም ሁኔታ ውስጥ የህግ አስከባሪነት መነሻው ህግን ማክበር መሆኑን ያስታወቀው ፖሊስ የዜጎችን ህጋዊ መብት በሚፃረሩ የፖሊስ አባላት ላይ የሚወሰደውን ዕርምጃ አጠናክሮ እንደሚቀጥልና በማንኛውም ሁኔታ ህገወጥ ተግባራት ሲፈፀሙ ህ/ሰቡ በያገባኛል ስሜት የሚሰጠውን መረጃ አጠናክሮ እንዲቀጥል ፖሊስ ጥሪውን አስተላልፏል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና ልዑካን ቡድናቸው በምርጫ ያሸነፉት የፕሬዚደንት ሀሰን ሼክ መሀሙድ በዓለ ሲመት ላይ ለመገኘት  ሞቃዲሹ ሲገቡ የተደረገላቸው አቀባበል።
09/06/2022

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና ልዑካን ቡድናቸው በምርጫ ያሸነፉት የፕሬዚደንት ሀሰን ሼክ መሀሙድ በዓለ ሲመት ላይ ለመገኘት ሞቃዲሹ ሲገቡ የተደረገላቸው አቀባበል።

በብርጋዴል ጀኔራል ተፈራ ማሞ ጉዳይ ፍ/ቤት የ10 ቀናት ተጨማሪ ጊዜ ፈቀደየአብክመ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዛሬ ግንቦት 22/2014 ዓ/ም በዋለው ችሎት የብርጋዴል ጀኔራል ተፈራ ማሞን ጉዳይ ያየ...
30/05/2022

በብርጋዴል ጀኔራል ተፈራ ማሞ ጉዳይ ፍ/ቤት የ10 ቀናት ተጨማሪ ጊዜ ፈቀደ

የአብክመ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዛሬ ግንቦት 22/2014 ዓ/ም በዋለው ችሎት የብርጋዴል ጀኔራል ተፈራ ማሞን ጉዳይ ያየ ሲሆን የመርማሪ ቡድኑ ምርመራየን ስላልጨረስኩ የተለያዩ ማስረጃዎችን ከባንክ፣ ከብሔራዊ መረጃና ደህንነት፣ ከኢሳት እና ከሌሎች ተቋማት የምንሰበስባቸው መረጃዎች ስላሉ የ14 ቀናት ተጨማሪ የጊዜ ቀጠሮ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል።

የተከሳሽ ጠበቃ በበኩላቸው አስፈላጊ ናቸው የተባሉ መረጃዎችን ለመሰብሰብ መረጃው የሚሰበሰብባቸው ተቋማት የመንግስት ስለሆኑ ያን ያህል ጊዜ ስለማይዎስዱ ተከሳሽ በውጭ ሆነው እንዲከራከሩ በዋስትና እንዲለቀቁ ጠይቀዋል።

የምርመራ ቡድኑ የጠበቃውን በዋስትና ይለቀቁልኝ ክርክር በመቃዎም ተከሳሹ ከእስር ቢለቀቁ የተለያዩ ማስረጃዎችን ያጠፉብናል በዚህ ምክኒያት በእስር ሊቆዩ እና የጠየቅነው የጊዜ ቀጠሮ እንዲፈቀድላቸው ጠይቀዋል።

ፍርድ ቤቱ የግራ ቀኙን ክርክር ሰምቶ የጊዜ ቀጠሮ መስጠቱን ስላመነበት የምርመራ ቡድኑ ከጠየቀው የ14 ቀን ውስጥ 10 ቀናት ብቻ ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ በመፍቀድ ለሰኔ 2/2014 ዓ/ም ቀጠሮ ሰጥቷል።

(አብክመ ጠቅላይ ፍርድ ቤት)

በሀናን መሐመድ ግድያ ወንጀል የተጠረጠረው ፍቅረኛዋ ከድር ሀሰን ፍርድ ቤት ቀረበ ======= #=======የአ/አ ፖሊስ መርማሪ ከ15 ቀን በፊት በአዲስ አበባ ከተማ በሞሴ ሆቴል ከ8ኛ ፎቅ...
30/05/2022

በሀናን መሐመድ ግድያ ወንጀል የተጠረጠረው ፍቅረኛዋ ከድር ሀሰን ፍርድ ቤት ቀረበ
======= #=======

የአ/አ ፖሊስ መርማሪ ከ15 ቀን በፊት በአዲስ አበባ ከተማ በሞሴ ሆቴል ከ8ኛ ፎቅ ህይወቷ አልፎ ስለተገኘችው በሀናን መሐመድ ግድያ ወንጀል ፍቅረኛዋ ተጠርጥሮ በቁጥጥር ሥር ውሎ ሰፊ የምርመራ ሥራ እያከናወነ መሆኑን ለችሎቱ አስታውቋል።

የሟች የአሟሟት ኹኔታን ለማጣራት ለአስከሬን ምርመራ እንዲደረግ ጠይቆ ውጤት እየተጠቃበቀ መሆኑን የገለጸው መርማራ ፖሊስ፤ ተጨማሪ ማስረጃዎችን ለማቅረብ እንዲያስችለው የ14 ቀን የጊዜ ቀጠሮ እንዲሰጠው ፍርድ ቤቱን ጠይቋል።

ተጠርጣሪ ከድር ሀሰን በበኩሉ፤ ከጅማ መተው በሆቴል እንደነበሩ ገልጾ፣ ሟች ሀናን መሐመድ የሚወዳት ፍቅረኛው መሆኗንና ህይወቷ እስካለፈበት ሰዓት በመካከላቸው ምንም አይነት ጸብም ሆነ ጭቅጭቅ እንደሌለ ለፍርድ ቤት አብራርቷል።

በማህበራዊ ሚዲያ የሚናፈሰውን ወሬ በተሰማ ቁጥር በየጊዜው እየተጠራሁ እጠየቃለው እውነቱ ግን ሀናን የማፈቅራት ሚስቴ ናት እሷ ነጋዴ ናት ዕቃ ገዝቼ እንድመጣ አዛኝ በሰላም ተነጋግረን ፊቴን ታጥቤ ከሆቴሉ በደረጃ በኩል ነው የወረድኩት፤ ስወጣ ባለቤቴ ደህና ነበረች ወጥቼ ሄጄ 2:00 ሰዓት ላይ በስልክ ደውላ በአስቸኳይ ተመለስ አለቺኝ ከዛ ስልኩን ዘጋች እኔም ለሆቴሉ ማናጀር ደውዬ ምን እንደሆነች እንዲጠይቅለኝ ነገርኩት በኋላ ላይ የሆቴሉ ማናጀር ደውሎ ለኔ መንገር ፈርቶ ደህናት ፈጥነህ ና አለኝ ከዛ እሷን ወደ ቤተዛታ ወስደዋት ነበር ቤተዛታ ስደርስ ህይወቷ አልፎ አገኘኋት ወዲያው ፖሊስ ጣቢያ ሄጄ እንዲያጣሩልኝ አመለከትኩ ሲል ለፍርድ ቤቱ አብራርቷል።

ከዚህ በፊትም በተደጋጋሚ እራሴን አጠፋለው እያለች ትናገር እንደነበር የገለጸው ተጠርጣሪ በማላታይን እራሷን ለማጥፋት በተደጋጋሚ ሞክራ እንደነበር ቤተሰቦቿ እንደሚያውቁ ለችሎቱ አስረድቷል።

በዕለቱ ሆቴል ውስጥ የተፈጠረውን ሁኔታ ከሆቴሉ ካሜራ ላይ የተቀሳቃሽ ምስል አይተው ማጣራት እየተቻለ እኔ ታስሬ የምወዳትን የሚስቴን አስከሬን ተቀብዬ መቅበር አልቻልኩም ሲል ለፍርድ ቤቱ አብራርቷል።

በፖሊስ በኩል የተቀሳቃሽ ካሜራ ማስረጃ እንደተቀበለና እንዳልተቀበለ ከፍርድ ቤቱ ለተነሳ ጥያቄ አለመቀበሉን የገለጸው መርማሪው ተንቀሳቃሽ ምስል እንደሚቀበል ገልጿል።

ጉዳዩን የተከታተለው የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ 1ኛ የጊዜ ቀጠሮ ችሎት የተጠርጣሪ የወንጀል ተሳትፎ ተለይቶ እንዲቀርብ ትዛዝ በመስጠት ለተጨማሪ ምርመራ ለፖሊስ የ 11 ቀን ጊዜ ፈቅዷል።

የምርመራ ውጤት ለመጠባበቅ ለሰኔ 3 ቀን 2014 ተለዋጭ ቀጠሮ መስጠቱን ጋዜጠኛ ታሪክ አዱኛ ዘግባለች።

በኢትዮጵያ ባንኮች ላይ ባነጣጠረ የማጭበርበር ወንጀል 1ነጥብ 9 ቢሊየን ብር የሚጠጋ ገንዘብ መመዝበሩ ተገለጸበኢትዮጵያ የሚገኙ ባንኮችን ባነጣጠረ የማጭበርበር ወንጀል ከ1 ቢሊየን 896 ሚሊ...
30/05/2022

በኢትዮጵያ ባንኮች ላይ ባነጣጠረ የማጭበርበር ወንጀል 1ነጥብ 9 ቢሊየን ብር የሚጠጋ ገንዘብ መመዝበሩ ተገለጸ

በኢትዮጵያ የሚገኙ ባንኮችን ባነጣጠረ የማጭበርበር ወንጀል ከ1 ቢሊየን 896 ሚሊየን ብር በላይ መመዝበሩን በፍትህ ሚኒስቴር የተደረገ ጥናት አመላከተ።

ከ2009 ዓ.ም ጀምሮ በተካሄደው በዚህ ጥናት ከ370 ሚሊየን ብር በላይ በባንኮች ላይ ለማጭበርበር ተሞክሮ ማትረፍ መቻሉ ተመላክቷል።

ጥናቱን ተከትሎ የፍትህ ሚኒስቴር የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ገዥ ዶክተር ይናገር ደሴ እና የተለያዩ ባንኮች ፕሬዚዳንቶች፣ የኢትዮ ቴሌኮምና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት እያደረገ ነው።

ጥናቱ በባንኮች ላይ የሚፈጸሙ የማጭበርበር ወንጀሎች መንስኤዎቻቸው እና የአፈጻጸም ዘዴያቸውን በመለየት የመፍትሔ ሃሳቦችን ለማቅረብ በፍትህ ሚኒስቴር የተደረገ መሆኑ ተገልጿል፡፡

በውይይቱም በኢትዮጵያ የሚገኙ ባንኮችን ባነጣጠረ የማጭበርበር ወንጀል ከ1 ቢሊየን 896 ሚሊየን ብር በላይ መመዝበሩን የተደረገው ጥናት አመላክቷል።

የባንክ ማጭበርበር ከተፈፀመባቸው 16 ባንኮች 50 በመቶው ወይም 961 ሚሊየን ብሩ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ላይ የተፈፀመ መሆኑ በጥናቱ ተጠቁሟል፡፡

በተጨማሪም 17 በመቶው ወይም 329 ሚሊየን ብር የሚጠጋው በአቢሲኒያ ባንክ እንዲሁም 8 ነጥብ 5 በመቶ ወይም 162 ሚሊየን ብር የሚሆነው በኦሮሚያ ባንክ ላይ የተፈፀመ ነው ተብሏል።

በባንኮች ላይ የሚፈፀሙ የማጭበርበር መንስኤዎች እና ወንጀሎች መንስኤያቸውን በመለየት የመፍትሄ ሀሳቦችን ለማቅረብ የተዘጋጀው ጥናት የሚፈፀሙት ወንጀሎች ለህዝብ ይፋ የሆኑ፣ በባንክ ብቻ የሚታወቀው እና የማይታወቁ የማጭበርበር ወንጀሎች መፈፀማቸውን አመላክቷል።

የማጭበርበር ወንጀሎቹ በባንኮች አስተዳደር አካላት የባንክ ሰራተኞች በሶስተኛ ወገን የሚፈፀሙ መሆናቸው ነው የተገለጸው፡፡

በሚፈፀሙት ወንጀሎችም የኢትዮ-ቴሌኮም ሰራተኞች ጭሞር እንደሚሳተፉ የተደረገው ጥናት አመላክቷል፡፡
FBC

የ“ፊንፊኔ ኢንተግሬትድ ብሮድካስቲንግ” የቴሌቪዥን ጣቢያ ጋዜጠኛ ሰቦንቱ አህመድ ዛሬ ረፋዱን ከእስር መለቀቋን የጣቢያው ዋና ዳይሬክተር ለሚ ታዬ ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናገሩ። ጋዜጠኛ ሶ...
30/05/2022

የ“ፊንፊኔ ኢንተግሬትድ ብሮድካስቲንግ” የቴሌቪዥን ጣቢያ ጋዜጠኛ ሰቦንቱ አህመድ ዛሬ ረፋዱን ከእስር መለቀቋን የጣቢያው ዋና ዳይሬክተር ለሚ ታዬ ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናገሩ። ጋዜጠኛ ሶቦንቱ የተለቀቀችው በቢሾፍቱ ከተማ ከሚገኝ ፖሊስ ጣቢያ መሆኑን ዋና ዳይሬክተር ገልጸዋል።

ጋዜጠኛ ሶቦንቱ በፖሊስ ቁጥጥር የዋለችው ባለፈው ሳምንት ሐሙስ ግንቦት 18፤ 2014 አመሻሽ ላይ ከስራ ቦታዋ ስትወጣ መሆኑን በወቅቱ ተገልጾ ነበር። በ“ፊንፊኔ ኢንተግሬትድ ብሮድካስቲንግ” ቴሌቪዥን ጣቢያ ዜና አንባቢ እና የመዝናኝ ፕሮግራም አዘጋጅ የሆነችው ሰቦንቱ በማግስቱ ወደ ቢሾፍቱ ከተማ መወሰዷን የጣቢያው ዋና ዳይሬክተር ተናግረው ነበር።

ያለፉትን ሶስት ቀናት በእስር ያሳለፈችው ሰቦንቱ፤ ዛሬ ሰኞ ግንቦት 22 ከጠዋቱ አራት ሰዓት ተኩል ገደማ በዋስ መለቀቋን አቶ ለሚ ገልጸዋል። (ኢትዮጵያ ኢንሳይደር)

ባለፈው ሰኔ ወር ላይ የትግራይ አማፂያን መቀለ ከተማን እና አብዛኛውን የትግራይ አካባቢ ከተቆጣጠሩ በኋላ በትግራይ ላለፉት 11 ወራት ያህል የባንክ፣ የስልክና ሌሎች መሠረታዊ አግልግሎቶች እ...
30/05/2022

ባለፈው ሰኔ ወር ላይ የትግራይ አማፂያን መቀለ ከተማን እና አብዛኛውን የትግራይ አካባቢ ከተቆጣጠሩ በኋላ በትግራይ ላለፉት 11 ወራት ያህል የባንክ፣ የስልክና ሌሎች መሠረታዊ አግልግሎቶች እንደተቋረጡ ናቸው።

በዚህም ምክንያት በችግር ውስጥ ላሉ ለቤተሰቦቻቸው ገንበዘብ መላክ የሚፈልጉ ሰዎች፣ ከሚልኩት ብር ወደ ግማሽ የሚጠጋውን ገንዘቡን ለሚያደርሱ ሰዎች ለመክፈል ተገደዋል።

ባለፈው ሰኔ ወር ላይ የትግራይ አማፂያን የመቀለ ከተማን እና አብዛኛውን የትግራይ አካባቢ ከተቆጣጠሩ በኋላ ትግራይ ላለፉት 11 ወራት ያህል የባንክ፣ የስልክና ሌሎች መሠረታዊ አግልግሎ.....

ህንዳዊው ባለሀብት ስሙን "ለሚ ኦዳ" ብሎ  ቀየረ   | ትላንት ናሁ ቴሌቪዥን  ላይ ከፒተር ሾው ጋር ቆይታ የነበረው ህንዳዊው ባለሃብት አግራሞትን የሚያጭር ነጥቦችን አንስቷል። በጉዲፈቻ ስ...
30/05/2022

ህንዳዊው ባለሀብት ስሙን "ለሚ ኦዳ" ብሎ ቀየረ

| ትላንት ናሁ ቴሌቪዥን ላይ ከፒተር ሾው ጋር ቆይታ የነበረው ህንዳዊው ባለሃብት አግራሞትን የሚያጭር ነጥቦችን አንስቷል።

በጉዲፈቻ ስርዓት "ኢትዮጵያዊ ሆኛለሁ" ያለ ሲሆን ከዚህም የተነሳ "ስሜ ለሚ ኦዳ ሆኗል" ብሏል።

የሐበሻ ስቲል ብረታ ብረት ድርጅት ማኔጅንግ ዳይሬክተር ኪቨን ራቫን ወይም "ለሚ ኦዳ" በድርጅታቸው በኩል ብዙ ህፃናትን እያስተማሩ እንደሆነ አብራርተዋል።

የሐበሻ ስቲል ብረታ ብረት ድርጅት በዱከም አካባቢ ለበርካታዎች የስራ እድል ከመፍጠሩ ባሻገር በርካታ ማኀበራዊ ኃላፊነቶችን እየተወጣ ይገኛል።

TVቴሌግራም :- https://t.me/NahooTelevisionፌስቡክ፦https://www.facebook.com/Nahooethiopiaዩትዩብ፦https://www.youtube.com/c/NahooTVEthiopia

የሩሲያ ጦር ሴቪየርዶኔትስክ የተባለች ቁልፍ ከተማ እየተቆጣጠሩ መሆኑን ዩክሬን አስታወቀችዩክሬኗ ሉሃንስክ ግዛት አስተዳዳሪ፤ የሩሲያ ጦር ወደ ሴቪየርዶኔትስክ ከተማ ዘልቆ እየገባ ነው ብለዋል...
30/05/2022

የሩሲያ ጦር ሴቪየርዶኔትስክ የተባለች ቁልፍ ከተማ እየተቆጣጠሩ መሆኑን ዩክሬን አስታወቀች

ዩክሬኗ ሉሃንስክ ግዛት አስተዳዳሪ፤ የሩሲያ ጦር ወደ ሴቪየርዶኔትስክ ከተማ ዘልቆ እየገባ ነው ብለዋል። የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ዘለንስኪ በከተማዋ የሚገኙ መሰረተ ልማቶችና ህንጻዎች 90 በመቶ ወድመዋል ብለዋል።

የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ዘለንስኪ በከተማዋ የሚገኙ መሰረተ ልማቶችና ህንጻዎች 90 በመቶ ወድመዋል ብለዋል

"በአጠቃላይ አሁን ያለንበትን ዘመን የሚመስል ክፉ ዘመን አለ ብዬ አላስብም። ቅስም የሚሰብር፣ ወንድም በወንድሙ ላይ የሚጨክንበት እና ዘረኝነት የነገሰበት ዘመን ነው። ውሉ የጠፋበት ዘመን ነ...
28/05/2022

"በአጠቃላይ አሁን ያለንበትን ዘመን የሚመስል ክፉ ዘመን አለ ብዬ አላስብም። ቅስም የሚሰብር፣ ወንድም በወንድሙ ላይ የሚጨክንበት እና ዘረኝነት የነገሰበት ዘመን ነው። ውሉ የጠፋበት ዘመን ነው። በዚህ የፖለቲካ መስተጋብር ውስጥ ለውጥ ለማምጣት የሚተጋ ፓርቲ ምን ያህል ችግር ውስጥ እንደሚገባ መገመት አያስቸግርም። እንደ ማኅበረሰብ የታመምን እና ነገ ምን እንደሚፈጠር ባለማወቅ ስሜታዊነት ውስጥ የገባንበት ሁኔታ ውስጥ ነው ያለነው።" አቶ አንዱዓለም አራጌ

አቶ አንዱዓለም አራጌ የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅህበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) ምክትል መሪ ናቸው። አንዱዓለም በኢትዮጵያ የተቃውሞ ፖለቲካ ውስጥ ጉምቱ ከሚባሉ ፖለቲካኞች መካከል ይጠቀሳሉ። አሁ....

"ኢትዮጵያ የሰብዓዊ እርዳታ ለሚሹ ዜጎች ድጋፍ እንዲደርስ ቁርጠኛ ናት" -ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ  ኢትዮጵያ በተፈጥሮ እና ሰው ሰራሽ አደጋዎች ለተጎዱ ዜጎች የሰብዓዊ እርዳታ ድጋፍ ...
28/05/2022

"ኢትዮጵያ የሰብዓዊ እርዳታ ለሚሹ ዜጎች ድጋፍ እንዲደርስ ቁርጠኛ ናት" -ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ

ኢትዮጵያ በተፈጥሮ እና ሰው ሰራሽ አደጋዎች ለተጎዱ ዜጎች የሰብዓዊ እርዳታ ድጋፍ እንዲደርስ ቁርጠኛ ናት ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ ተናገሩ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በትዊተር ገጻቸው እንዳስታወቁት ኢትዮጵያ በተፈጥሮ እና ሰው ሰራሽ አደጋዎች ለተጎዱ ዜጎች የሰብዓዊ እርዳታ ድጋፍ እንዲደርስ ቁርጠኛ መሆኗን ገልጸው፤ አጋሮች በመላው አህጉሪቱ የሚያደርጉትን የሰብዓዊ ድጋፍ ማሳደግ እንደሚገባቸው ገልጸዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና ልዑካን ቡድናቸው በኢኳቶሪያል ጊኒ ማላቦ ከተማ እየተካሄደ በሚገኘው በ15ኛው የአፍሪካ ኅብረት የሰብዓዊ ዕርዳታ እና ቃል ኪዳን ጉባዔ ላይ እየተሳተፉ ይገኛሉ።

በዚሁ መድረክ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትሩ የአፍሪካ ቀንድ በዓለም በአየር ንብረት ለውጥ እና በድርቅ ሳቢያ የከፋ ሰብዓዊ ቀውስ ከተከሰተባቸው ቀጠናዎች አንዱ መሆኑን ጠቅሰው ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ለአፍሪካ የሚያደርገውን ሰብዓዊ ድጋፍ እንዲያጠናክር ጥሪ ማቅረባቸው ይታወሳል።
ኢዜአ

ስንታየሁ ቸኮል በባሕር ዳር ከተማ በቁጥጥር ስር ውሏል። በብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የትብብር ደብዳቤ ባልድራስን ሃገር አቀፍ ለማድረግ የተጀመረውን እንቅስቃሴ ለመምራት ባህርዳር ከተማ  የገባው የ...
27/05/2022

ስንታየሁ ቸኮል በባሕር ዳር ከተማ በቁጥጥር ስር ውሏል።

በብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የትብብር ደብዳቤ ባልድራስን ሃገር አቀፍ ለማድረግ የተጀመረውን እንቅስቃሴ ለመምራት ባህርዳር ከተማ የገባው የባልደራስ ከፍተኛ አመራር ስንታየሁ ቸኮል በባሕር ዳር ከተማ በቁጥጥር ስር ውሏል።
ምንጭ - መረጃ ዶት ኮም

በሃሰተኛ ገንዘብ ነዳጅ ቀድቶ ለማምለጥ የሞከረው አሽከርካሪ ከቆመ ተሽከርካሪ ጋር በመጋጨቱ ህይወቱ ማለፉን የአዲስ አበባ ፖሊስ ገለፀ፡፡                    የትራፊክ አደጋው የደረ...
27/05/2022

በሃሰተኛ ገንዘብ ነዳጅ ቀድቶ ለማምለጥ የሞከረው አሽከርካሪ ከቆመ ተሽከርካሪ ጋር በመጋጨቱ ህይወቱ ማለፉን የአዲስ አበባ ፖሊስ ገለፀ፡፡

የትራፊክ አደጋው የደረሰው ግንቦት 18 ቀን 2014 ዓ/ም ከሌሊቱ 6፡30 ሰዓት ገደማ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 2 ልዩ ቦታው ሚካኤል አደባባይ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ነው ፡፡

የሰሌዳ ቁጥር ኮድ 1- 30262 አ.አ የሆነ ተሽከርካሪ ከጀሞ 1 አቅጣጫ ወደ ሚካኤል አደባባይ እየተጓዘ 67 ማዞሪያ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በሚገኝ ነዳጅ ማደያ ውስጥ ነዳጅ ሊቀዳ መግባቱን በአዲስ አበባ ፖሊስ የትራፊክ አደጋ ምርመራ ቲም ሃላፊ ምክትል ኢንስፔክተር ስጦታው ወልዴ ገልፀዋል፡፡
አሽከርካሪው ነዳጅ ከቀዳ በኋላ አምስት ባለ 100 መቶ ሀሰተኛ የብር ኖቶችን ለነዳጅ ማደያው ሰራተኛ ሰጥቶ በሚሄድበት ወቅት ነዳጅ ቀጂው የብሮቹን ትክክለኛነት በመጠራጠሩ ሊያስቆመው መሞከሩን የጠቀሱት ምክትል ኢንስፔክተር ስጦታው አሽከርካሪው ግን በፍጥነት በማሽከርከር ለማምለጥ ጥረት ሲያደርግ መንገድ ዳር ቆሞ ከነበረ የሰሌዳ ቁጥር ኮድ 3A- 60203 አ.አ ከሆነ አይሱዙ ተሽከርካሪ ጋር በመጋጨቱ ህይወቱ ማለፉን ተናግረዋል፡፡ በወቅቱ አብረውት ተሳፍረው የነበሩ 2 ግለሰቦች ላይም ከባድ የአካል ጉዳት በመድረሱ ተጎጂዎቹ በህክምና ላይ እንደሚገኙ ምክትል ኢንስፔክተር ስጦታው ወልዴ አስረድተዋል፡፡

ሩሲያን ለመነጠል እየሞከሩ ያሉ ሃገራት እራሳቸውን እያዳከሙ ነው - ፕሬዚዳንት ፑቲን ሩሲያን ለመነጠል እየሞከሩ ያሉ ሃገራት የራሳቸውን ኢኮኖሚ እያዳከሙ ነው ሲሉ ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ...
27/05/2022

ሩሲያን ለመነጠል እየሞከሩ ያሉ ሃገራት እራሳቸውን እያዳከሙ ነው - ፕሬዚዳንት ፑቲን

ሩሲያን ለመነጠል እየሞከሩ ያሉ ሃገራት የራሳቸውን ኢኮኖሚ እያዳከሙ ነው ሲሉ ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ተናገሩ።

ፑቲን በእስያ አውሮፓ የኢኮኖሚ ፎረም ላይ ባደረጉት ንግግር፥ ሩሲያን ማግለልና መነጠል የማይቻል መሆኑን አስረድተዋል።

አያይዘውም ይህን ለማድረግ የሚሞክሩና በሩሲያ ላይ የሚያሴሩ ሃገራት እራሳቸውን ይጎዳሉም ነው ያሉት።

“ዓለም ላይ ጠንካራ ኢኮኖሚ ያላቸው ሃገራት አሁን ላይ ከባድ የዋጋ ግሽበትና ከፍተኛ የሆነ የስራ አጥ ዜጎች ቁጥር እያስተናገዱ” መሆኑንም አመላክተዋል።

ከዚህ ጋር ተያይዞም ዓለም አቀፉ ቀውስ እጅግ ተባብሷል ማለታቸውን ሺንዋ በዘገባው አመላክቷል።

“ይህም መላው የኢኮኖሚ ስርአትና ፖለቲካዊ ግንኙነቶች ላይ ተፅዕኖ የሚያሳርፍ ጉዳይ” መሆኑንም አጽንኦት ሰጥተዋል።

ሃገራትን ለማዳከም በማሰብ የሚጣሉ ማዕቀቦችና ገደቦችም እርባና ቢስና ጠቀሜታ የሌላቸው ናቸው ብለዋል ፑቲን በንግግራቸው።
FBC

መሀመድ ኡመር ጋዳፊ ስለ መንግስቱ ሀይለማሪያም የተናገረው።ኮረኔል መንግስቱን እወደው ነበር። ብዙም እንደሚባለው አምባገነን አልነበረም። ከኮረኔል መንግስቱ ጋር በፈረጆቹ 1988  አዲስ አበባ...
27/05/2022

መሀመድ ኡመር ጋዳፊ ስለ መንግስቱ ሀይለማሪያም የተናገረው።
ኮረኔል መንግስቱን እወደው ነበር። ብዙም እንደሚባለው አምባገነን አልነበረም። ከኮረኔል መንግስቱ ጋር በፈረጆቹ 1988 አዲስ አበባ ላይ በዝግ መክረን ነበር። የአፍሪካ ጥምር ጦር ለማቋቋምና በቀይ ባህር ዳርቻ ያሉ አገሮችን ለመቆጣጠር አስበን ነበር። መንግስቱም እሽ ብሎ ተስማምተን ነበር። ወዲያው ግን ለመንግስቱ የቤት ስራ ተሰጠው።

በኢትዮጵያ የመሰነጣጠቅ ፖለቲካ ተጀምሯል። መንግስቱ ጥምር ጦር ለማቋቋም ያሰበው አገሪቱ ላይ ያሉትን ታጣቂዎች ከደመሰሰ በኋላ ነው። ሱዳንና ግብፅ ኬኒያ ጅቡቲ ግን ለጥምር ጦር ማቋቋም እሽ ብለውን በኋላ ከድተውናል። ለአሜሪካና ለእስራኤል ሚስጥሩን ሸጡት። በዚህ የተናደደው መንግስቱ የጅቡቲውን መሪ አሰፈራራው። አንዲት የምዕራባውያን ጅቡቲ ከሰፈረ፣ አለቅህም የሚል ነበር ማስፈራሪያው። በወቅቱ መንግስቱ ከምዕራባውያን ጋር ጥል ነበር። ያጣላቸው እነሱ ጅቡቲን ላይ መተው ለመስፈር ፈልገው እሱ አይቻልም ብሎ ጅቡቲን ማስፈራራቱ ነው።። ፈረንሳይ ከጁቡቲ አልፋ ማሊ፣ ጊኒን፣ ኒጀርን በቅኝ ግዛት እየገዛች ነበር።
መንግስቱ ባንድ ግዜ ከሁሉም ጋር ተጣላ። ሱዳንና ግብፅ ጁቡቲ ኬኒያ ሲአይኤ ሞሳድ
ሆነው መከሩበት። ያነየ እነ ሱዳን እነ ግብፅ እነ ኬኒያ እነ ጅቢቲ ኢትዮጵያ ውስጥ መንግስቱን ለሚዋጉ ሀይሎች ድጋፍ ያደርጉ ነበር። እኔ ሱዳንን ተይ ብያት ነበር። መጨረሻ ላይ ግን ሳናሰበው መንግስቱን አሶረዱት። በተቻለኝ አቅም ግን ከነበሩን አውሮፕላኖች በተጨማሪ ያሉንን የጀት ቦንቦች ለመንግስቱ ሰተነው ነበር። እስራኤል አሜሪካ ኬኒያ ጅቡቲ ግብፅ ሱዳን ምዕራባውያን ሆነው ነው መንግስቱን የወገት። ሩሲያ ግን ያነየ ከኢትዮጵያ ጎን ብትሆንም እንዳሁ አቅም የላም ነበር።

እስራኤል በፍልስጥኤማውያን ላይ የምታደርሰውን ግፍ መንግስቱ መቃወሙ ነው ያስጠመደው። ሁለተኛ የቀይ ባህር በር ከኢትዮጵያ በላይ አለቃ የለውም የሚል ህልም ነበረው። አሜሪካና አጋሯቿ ግን ጁቡቲና ኬኒያን መጀመሪያ ይዘዋል። ሱዳን በግብፅ ተሸውዳ ለሽምቅ ተዋጊዎቹ ማሰልጠኛ ማዕከል ተደርጋ ነበር። ሁለት ጊዜ የኛ ጀቶች ከሊቢያ በረው ድብደባ አድርገው ነበር። ግን የተባለው ውጤት አልመጣም። ጓድ መንግስቱም እንዲህ በቀላሉ የሚበገር አልነበረም። በኋላ ላይ ጀነራሎቹ ለዶላር ፍቅር ሲወድቁ እሱም ተሸነፈ።
ከዛ በኋላ ኤርትራም አገር ሆነች። ኢትዮጵያም አገር ሆነች። ሁለቱን አገሮች የመሰረቷቸው ምዕራባውያን እና አሜሪካ እስራኤል ናቸው ። ኢሳያስ እንደገና ከዳቸው። ኢትዮጵያን የሚመራው ቡድን ሁሉም ነገሩ አሜሪካ ሁሉም ስረአቱ ምዕራባውያን ሆኖ መጣ። የአፍሪካ ነፃነት አቀንቃኝ የሆነችው አገር ኢትዮጵያ፣ የምዕራባውያን ተላላኪ ስትሆን የአፍሪካ ህብረት ከአዲስ አበባ ወደ ሊቢያ እንዲዛወር ተከራኬሪያለሁ።

ሆኖም መንግስቱ ወደር የለለው ጥቁር የአፍሪካን አንድነትን ወዳጅና አፍቃሪ መሪ ነበር። መንግስቱ ባይሴርበት ኖሮ፣ ሱዳንና ግብፅ፣ ኬኒያና ጅቡቲ፣ ባይከዱን የአፍሪካ ጥምር ጦርና ፣የጥምር ጦሩ አመታዊ ሀብት በአፍሪካ ወርቅ ብቻ እንዲሸፈን ተስማምተን ነበር። ግን አልሆነም።

ፕሬዚዳንት መሀመድ ኡመር ጋዳፊ በዘመነ ስልጣኑ የሚለው የታሪክ መፅሀፉ ላይ ካሰፈራቸው በልጁ የታተመው አዲሱ የአባቱ ሂዎተ መፀሀፍ ላይ የተወሰደ።

አሁን ፕሬዝዳንት መሀመድ ኡመር ጋዳፊ ሞቷል። ፕሬዝዳንት ኮረኔል መንግስቱም ዝንባቡዌ ሆነው የተወለዱበትን 81ኛ አመታቸውን እያከበሩ ነው።

ሱሌማን አብደላ

ጀነራል ቡረሀን ለውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አቶ ደመቀ መኮነን ንግግር መልስ የሚሆንጉብኝት አድርጓል። ከኢትዮጵያ ወሮ በያዟቸው የገላባትና፣ የሀምዳይት፣  የአልፋሽጋ፣ መሬቶች ላይ እየተዟዟረ ጉብኝ...
26/05/2022

ጀነራል ቡረሀን ለውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አቶ ደመቀ መኮነን ንግግር መልስ የሚሆን
ጉብኝት አድርጓል።

ከኢትዮጵያ ወሮ በያዟቸው የገላባትና፣ የሀምዳይት፣ የአልፋሽጋ፣ መሬቶች ላይ እየተዟዟረ ጉብኝት ያደረገው ጀነራል ቡረሀን፣ ከመሬታችን የምንለየው ጠቅላላ ሞተን ስናልቅ ብቻና ብቻ ነው ብሏል። የምስራቅ ዕዝ አዛዥ የሆኑት ጀነራል መሀመድ ረሻድ በበኩላቸው ከጎረቤት አገር እየተቃጣ ያለውን የወረራ ሙከራ ጦሩ ለሚያደርገው አጥጋቢ የመልስ ምት ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
ጀነራል ቡረሀን በበከሉ መሬታችንን እና እናቶቻችንን የመጠበቅ አቅም ያለን ወንድ ልጆች ነን፣ የሱዳን ድንበር የሚጠበቀው የሱዳን እናቶች በወለዷቸው ወንድ ልጆቻቸው ነው ብሏል። ጀነራሉ በዕብሪት
የታጠረ ንግግር ከማድረጋቸው ባለፈም ከኢትዮጵያ በወረራ የያዟቸው መሬቶች ላይ የትምህርት ቤት፣ የወጣቶች መዝናኛ እንደሚገነቡ አሳውቀው፣ ከዚህ በተጨማሪም ለሴቶችና ህፃናት የገንዝብና የቁስ ድጋፍ እንደሚያደርጉ ቃል የገቡ ሲሆን፣ ከኢትዮጵያ በኩል የሚመጡ ታጣቂዎች ተጨማሪ ጉዳት እንዳያደርሱ
ወታደራዊ ጥቆችንና የሰው ሀይሎችን ማስፈር እንደሚጀመሩ ነው የገለፁት።
ሱሌማን አብደላ

ጋዜጠኛ ያየሰው ሽመልስ መታሰሩ ተሰማጋዜጠኛ ያየሰው ዛሬ ሀሙስ በፀጥታ ኃይሎች ወደ ሶስተኛ ፖሊስ ጣቢያ መወሰዱን ጠበቃው ገልፀዋል።ጠበቃው አቶ ታደለ ገ/መድህን የካ አባዶ አካባቢ ከሚገኘው ...
26/05/2022

ጋዜጠኛ ያየሰው ሽመልስ መታሰሩ ተሰማ

ጋዜጠኛ ያየሰው ዛሬ ሀሙስ በፀጥታ ኃይሎች ወደ ሶስተኛ ፖሊስ ጣቢያ መወሰዱን ጠበቃው ገልፀዋል።

ጠበቃው አቶ ታደለ ገ/መድህን የካ አባዶ አካባቢ ከሚገኘው መኖሪያ ቤቱ ከአዲስ አበባ ፖሊስ መምጣታቸውን በተናገሩ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ውሏል ብለዋል።

ጠበቃው አቶ ታደለ ፤ ያየሰው ላለፉት 2 ዓመታት ትምህርት ላይ ማሳለፉን አስታውሰው፤ በአሁኑ ሰዓት በጋዜጠኝነት ሥራ ላይ አይገኝም ብለዋል፤ በተያዘበት ወቅትም ለመያዙ ምንም አይነት ምክንያት እንዳልተሰጠው አስረድተዋል።

ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ በቁጥጥር ስር ዋለ!!  : የፍትህ መጽሔት ማኔጂንግ ዳይሬክተር የሆነው ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ በቁጥጥር ስር መዋሉን የሥራ ባልደረቦቹ ለቢቢሲ አረጋገጡ። ተመስገን ...
26/05/2022

ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ በቁጥጥር ስር ዋለ!!

: የፍትህ መጽሔት ማኔጂንግ ዳይሬክተር የሆነው ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ በቁጥጥር ስር መዋሉን የሥራ ባልደረቦቹ ለቢቢሲ አረጋገጡ። ተመስገን ዛሬ ሐሙስ ግንቦት 18/2014 ዓ.ም. ረፋድ ላይ ከሥራ ቦታው በሁለት መኪና በመጡ የፀጥታ ኃይሎች ተይዞ መወሰዱን ስማቸውን መግለጽ ያልፈለጉ ባልደረቦቹ ተናግረዋል።

በቁጥጥር ስር ያዋሉት ኃይሎች መሳሪያ የታጠቁ ይሁኑ እንጂ የሲቪል ልብስ የለበሱ መሆናቸውንም አክለዋል።

"አሸባሪው ሕወሓት ኤርትራን ምድር ከረገጠ የቡድኑን ኣባላት ጠራርገን አርቀን የምንቀብርበት ጊዜ ሩቅ አይሆንም!" ፕሬዚደንት ኢሳያስ አፈወርቂ«አሸባሪው ሕወሓት የጋላቢዎቹን ተልእኮ ተቀብሎ ለ...
25/05/2022

"አሸባሪው ሕወሓት ኤርትራን ምድር ከረገጠ የቡድኑን ኣባላት ጠራርገን አርቀን የምንቀብርበት ጊዜ ሩቅ አይሆንም!" ፕሬዚደንት ኢሳያስ አፈወርቂ

«አሸባሪው ሕወሓት የጋላቢዎቹን ተልእኮ ተቀብሎ ለማስፈፀም እና የኤርትራን ሕዝብ አንገት በማስደፋት የባሕር በር ለመያዝ ከፍተኛ ወታደራዊ ዝግጅት እያደረገ እንደሆነ እናውቃለን።

በመንደፈራ፣ ፆሮና እና ባድመ ከተሞች ኣቅጣጫ ከኤርትራ የድንበር ጠባቂዎች ጋር ተደጋጋሚ ትንኮሳዎችን ሞክሮ እየተመታ ተመልሷል። በተለይም በመንደፈራ ኣቅጣጫ በወታደሮቻችን ላይ አለማቀፍ የምርኮኛ ሕግን በመጣስ የጦር ወንጀል ፈጽሟል።

እኛ የወንበዴው ቡድን የሆነውን የሕወሓትን ሰይጣናዊ ድርጊት ይዘን የምንከስበት እና የምንወቅስበት ኣካሔድ ኣይኖረንም። የሽብር ቡድኑ ዝግጅቱን ኣጠናቅቆ ወደ ኤርትራ ምድር ከረገጠ ግን የቡዱኑን ኣባላት ጠራርገን አርቀን የምንቀብርበት ጊዜ ሩቅ አይሆንም።

ኤርትራ ሉኣላዊነቷን ለመዳፈር ለሚሞክሩ ተላላኪዎች ከበቂ በላይ ምላሽ መስጠት የሚችል ኣስተማማኝ የጦር ሓይል እና ሕዝብ ኣላት።»

ግንቦት 24/2022 አቶ ኢሳያስ ለሰነኣ ጋዜጣ የሰጡትን ቃል መጠይቅ ዋቢ አድርጎ ኤርትራ ፕሬስ የዘገበው

መስከረም አበራና ሰለሞን ሹምዬ ፍርድ ቤት ቀረቡ======= #=======ዕረቡ ግንቦት 17 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) የፌደራል የመጀመሪያ ፍርድ ቤት ትናንት ረፋዱ ላይ ባዋለው ችሎት የዩት...
25/05/2022

መስከረም አበራና ሰለሞን ሹምዬ ፍርድ ቤት ቀረቡ
======= #=======

ዕረቡ ግንቦት 17 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) የፌደራል የመጀመሪያ ፍርድ ቤት ትናንት ረፋዱ ላይ ባዋለው ችሎት የዩትዩብ መገናኛ ብዙኀን ዝግጅት አቅራቢዋን መስከረም አበራን ጉዳይ ተመልክቷል።

በዕለቱ መርማሪ ፖሊስ ተጠርጣሪዋ ኹከትና ብጥብጥ በማስነሳት እና አማራ ክልልን ከፌደራል መንግሥቱ ለመነጠል ገንዘብ ተከፍሏት ትሰራለች ብሎ እንደጠረጠራት ለችሎት አስረድቷል። የተጠርጣሪዋ ጠበቆች ከመርማሪ ፖሊስ ጋር ክርክር ያደረጉ ሲሆን፣ መርማሪ ፖሊስም 14 ተጨማሪ የምርመራ ቀናት ይሰጠኝ ሲል ችሎቱን መጠየቃቸውን የዋዜማ ሪፖርተር ዘገባ አመላክቷል።

መርማሪ ፖሊስ ተጨማሪ የምርመራ ቀናት የጠየቀው፣ በተጠርጣሪዋ ላይ የሰነድ ማስረጃዎችን እያሰባሰበ እንደሆነ እና ግብረ አበሮቿን ለመያዝ እንደሆነ ለችሎቱ አብራርቷል።

የተጠርጣሪዋ ጠበቆች በበኩላቸው፣ ደንበኛቸው ሥራዋን በግልጽ በመገናኛ ብዙኀን እንደምትሰራ ለችሎት እና የፖሊስ ውንጀላ ከመገናኛ ብዙኀን አዋጁ ጋር የሚጣረስ እንደሆነ በመግለጽ፣ ለፖሊስ ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ እንዳይሰጠው ጠይቀዋል።

ተጠርጣሪዋ የ7 ወር ሕጻን ልጅ ያላት፣ ጡት የምታጠባ እና ቋሚ አድራሻ ያላት መሆኑን በመጥቀስም፣ በውጭ ሆና ጉዳዩዋን እንድትከታተል ጠበቆቿ ጨምረው አቤት ብለዋል።

የኹለቱን ወገኖች ክርክር ያዳመጠው ችሎቱ፣ መዝገቡን መርምሮ ውሳኔ ለመስጠት ለዛሬ ቀጠሮ ሰጥቶ ነበር። ችሎቱ በዛሬው ውሎው የተጠርጣሪዋ ጠበቆች ያቀረቡትን መቃወሚያ ውድቅ በማድረግ፣ ለመርማሪ ፖሊስ የ13 ቀናት የምርመራ ቀናትን ፈቅዷል። በችሎቱ ውሳኔ መሠረት ቀጣዩ የችሎቱ ተለዋጭ ቀጠሮ ግንቦት 29 ሆኗል።

መስከረም አዲስ አበባ ላይ በጸጥታ ኃይሎች ቁጥጥር ሥር የዋለችው ቅዳሜ ቀትር ላይ ከባሕርዳር ወደ አዲስ አበባ በኢትዮጵያ አየር መንገድ በተመለሰችበት ወቅት ነበር።

በተያያዘ ዓርብ ረፋዱ ላይ በፖሊስ ቁጥጥር ስር የዋለው የቴሌቪዥን ዝግጅት አዘጋጅ እና አቅራቢው ሰለሞን ሹምዬ ቅዳሜ ጧት ላይ ከፌደራሉ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት መቅረቡ ታውቋል።

መርማሪ ፖሊስ በተጠርጣሪው ሰለሞን ላይ 14 የምርመራ ቀናት የጠየቀ ቢሆንም፣ ችሎቱ ግን ለፖሊስ ዘጠኝ የምርመራ ቀናት በመፍቀድ ለግንቦት 22 ተለዋጭ ቀጠሮ መስጠቱን ዋዜማ ራዲዮ ዘግቧል።

19 ህጻናት የቀጠፈዉ የ 18 ዓመቱ ወጣት አሜሪካዊ ዓለምን እያነጋገረ ነዉአንድ የአስራ ስምንት  ዓመት አሜሪካዊ በደቡብ ቴክሳስ ግዛት ኡቫልዴ በምትባል ትንሽ  ከተማ ዉስጥ በሚገኝ አንደኛ ...
25/05/2022

19 ህጻናት የቀጠፈዉ የ 18 ዓመቱ ወጣት አሜሪካዊ ዓለምን እያነጋገረ ነዉ

አንድ የአስራ ስምንት ዓመት አሜሪካዊ በደቡብ ቴክሳስ ግዛት ኡቫልዴ በምትባል ትንሽ ከተማ ዉስጥ በሚገኝ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ትናንት ማክሰኞ 19 ህፃናትን በመትረየስ ሩምታ መግደሉ ዓለምን አሳዝኖአል እያነጋገረም ነዉ። ከቦታዉ በሚወጣ መረጃ መሰረት በአዉቶማቲክ መሳርያ አንድ አስተማሪና አንድ ሌላ ለአካለመጠን የደረሰ ሰዉን ጨምሮ 19 ህጻናትን በትምህርት ቤታቸዉ ረፍርፎ የገደለዉ ወጣት በዝያዉ በከተማ ዉስጥ ባለ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ዉስጥ ተማሪ ነዉ። ገዳዩ የ 18 ዓመት ወጣት ወደ ትምህርት ቤት ሄዶ ህጻናቱን ከመግደሉ በፊት አያቱን ተኩሶ ገድሎአል ተብሎአል። ወንጀል በተፈፀመበት ትምህርት ቤት ዉስጥ የሚማሩት ተማሪዎች አብዛኞቹ ከደቡብ አሜሪካ ሃገራት የመጡ ስፓኒሽ አሜሪካዉያን ናቸዉ። ከዚህ ጥቃት በህይወት የተረፉ ነገርግን በህወት ለመቆየት አሳሳቢ በሆነ ሁኔታ ላይ የሚገኙ አንዲት የ 66 ዓመት ሴት እና አንድ የ 10 ዓመት ታዳጊ ህፃን ፤ ሆስፒታል የቅርብ ክትትል እየተደረገላቸዉ ነዉ ተብሎአል። እራሱን አዘጋጅቶ የጥይት መከላከያ ሰድርያ ለብሶ ህጻናትን የቀጠፈዉ ወጣት አሜሪካዊ የፀጥታ ፖሊስ ደርሶ ተኩሶ ባይገድለዉ ኖሮ ብዙ ህይወት ሊቀጥፍ ይችል እንደነበር ተዘግቦአል። ጠመንጃ የመያዝ ጉዳይን መቼ ነዉ የምንቃወመዉ ሲሉ የጠየቁት የዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዚዳንት ጆ ቢደን በሃገሪቱ ጥብቅ የመሳርያ ህግ እንዲፀድቁ ጠይቀዋል።

በታንዛኒያ አንድ የፓርላማ አባል በአካባቢያችን መንገድ ሊሰራልን አልቻለም የሚለዉን ቅሬታ ለማሰማት በእጃቸዉ መቆማቸዉ መነጋገሪያ ሆኗልአንድ የታንዛኒያ የፓርላማ አባል በምርጫ ክልላቸው ባለው...
25/05/2022

በታንዛኒያ አንድ የፓርላማ አባል በአካባቢያችን መንገድ ሊሰራልን አልቻለም የሚለዉን ቅሬታ ለማሰማት በእጃቸዉ መቆማቸዉ መነጋገሪያ ሆኗል

አንድ የታንዛኒያ የፓርላማ አባል በምርጫ ክልላቸው ባለው የመንገድ ችግር በመበሳጨት በፓርላማው ቅሬታቸውን ያቀረቡበት መንገድ ትኩረት ስቧል፡፡የምቡሉ ሰሜናዊ ምርጫ ክልል የፓርላማ አባል የሆኑት ፍላቲ ማሳይ ሰኞ ዕለት በበጀት ግምት ላይ አስተያየት ሲሰጡ መንግስት በምርጫ ክልላቸው 100 ኪ.ሜ ያለው የአስፋልት መንገድ ለመገንባት የገባውን ቃል እንዲፈጽም ጠይቀዋል።

የተገባው ቃል ባለፉት ሶስት በጀት ዓመት ችላ መባሉን ተናግረው እጃቸዉን በጠረጴዛ ላይ አድርገዉ በእጃቸዉ ቆመዋል፡፡ አንዳንዶች የሰርከስ ትርኢት የምንመለከት ነበር የመሰለን ሲሉ ሌሎች ደግሞ ጉዳዩ ትኩረት እንዲሰጠው ያደርጋል ሲሉ ተስፋ እንዳላቸዉ ገልጸዋል፡፡

"ይህን ሁሉ የማደርገው ህዝቤ በመንግስት ቅር እንደተሰኘ ለመግለጽ ነው። መንግስት የገባዉን ቃል መተግበር አለበት ብለዋል፤ ሌሎች አካባቢዎች ቃል የተገባላቸዉን እያገኙ እኛ የምቡሉ ሰዎች ለምን ምንም አናገኝም?" ሲሉ ጠይቀዋል፡፡

Via ዳጉ ጆርናል

በቆቦ ከተማ ለህወሀት ቡድን ሊደርስ የነበረ 3 ሚሊየን ብር በቁጥጥር ሥር መዋሉ ተገለፀ በቆቦ ከተማ በጋሪ ብረቶች ውስጥ ተደብቆ ለህወሃት ቡድን ሊደርስ የነበረ 3 ሚሊየን ብር በቆቦ ከተማ ...
24/05/2022

በቆቦ ከተማ ለህወሀት ቡድን ሊደርስ የነበረ 3 ሚሊየን ብር በቁጥጥር ሥር መዋሉ ተገለፀ
በቆቦ ከተማ በጋሪ ብረቶች ውስጥ ተደብቆ ለህወሃት ቡድን ሊደርስ የነበረ 3 ሚሊየን ብር በቆቦ ከተማ ህዝብ፣ በከተማው ፓሊስና በሕዝባዊ ሚኒሻ ሠራዊቱ አማካኝነት በቁጥጥር ሥር መዋሉ ተገልጿል።
የቆቦ ከተማ አስተዳደር ሠላም እና ፀጥታ ሀላፊ ሀምሳ አለቃ አበበ ደርሶ እንደተናገሩት፤ "ብዙው ነገር ሲደረስበት ባልተነቃ መልኩ ለጁንታው እናደርሳለን ያሉት የውስጥ ባንዳዎችን በመጠቀም ወገናቸውን አሳልፎ እንዲሰጡ ቢደረግም በኹሉም የፀጥታ ሃይላችን አማካኝነት በቁጥጥር ሥር ውለዋል።"
የቆቦ ከተማ አስተዳደር ፓሊስ ፅ /ቤት ሀላፊ ኮማንደር ታደሰ ተሰሜ በበኩላቸው፤ ጋሪው የተሰራው ሙሉ በሙሉ ውስጡ ክፍት በመሆኑ፤ ሥም የተፃፈበት ብር በእያንዳንዱ ብረት በማድረጋቸው ላለመያዝ የተጠቀሙበት መንገድ ያልተጠበቀ ቢሆንም የቆቦ ከተማ ህዝብም ይሁን የፀጥታ አካሉ በመግባባቱ በቁጥጥር ሥር ውለዋል ብለዋል።
ኮማንደር ታደሰ እና ሀምሳ አለቃ አበበ በጋራ ባስተላለፉት መልዕክትም፤ ኹላችንም በጋራ ከሰራን ከዚህ የበለጠ ችግር ቢገጥመንም በጋራ የማንወጣው አስከፊ ችግር ስለማይኖር አገር የማዳን ሥራችን ተጠናክሮ መቀጠል አለበት ሲሉ ገልፀው፤ የቆቦ ከተማ ህዝብ ካጠገባችን በመሆኑ ኹሌም ኩራት ይሰማናል ማለታቸውን ከቆቦ ኮሚኒኬሽን የተገኘው መረጃ ያመላክታል።
አዲስ ማለዳ

የአውሮፓ ህብረት አዲሱ አጀንዳ አውሮፓ ሕብረት በጦር ወንጀል የተሳተፉ ሀይሎችን ለህግ እንዲያቀርብ መንግስትን ጠይቋል። ለመንግሥት ማንኛውን ወገን ለፍርድ አቅርብ እንዳለው ምናልባትም ሊያውቀ...
24/05/2022

የአውሮፓ ህብረት አዲሱ አጀንዳ
አውሮፓ ሕብረት በጦር ወንጀል የተሳተፉ ሀይሎችን ለህግ እንዲያቀርብ መንግስትን ጠይቋል። ለመንግሥት ማንኛውን ወገን ለፍርድ አቅርብ እንዳለው ምናልባትም ሊያውቀው ወይም ልክ እንደኔ ቢጤዎቻችን ግራ ሊያጋባው ይችላል።
አውሮፓ ሕብረት ለፍርድ ይቅረቡ የሚለው የመንግስት ወታደሮች ነው። አንድም የአማራ ሀይል የሚባሉትን ሁለትም መከላከያ ስራዊት ውስጥ ያሉ ህወሓት ጥላቶቸ ናቸው ብሎ ፅፎ የሰጣቸውን ሰዎች ነው። መንግስት ነገሩን እንደወረደ ተቀብሎ በሚዲያ ዜና ሰራው እንጅ፣ ይህ መርዛማ ድርጅት እንዴት ይሄንን አለ. ለምንስ ይችን አጀንዳ መዞ ሰጠን አላለም። ይሄንን ያልኩበት መንግስት ለጉዳዩ እስካሁን ማብራሪያ ስላልሰጠበት ነው። ቢሰጥበት ኖሮ የመንግስትን አቋምና የምዕራባውያንን ፍላጎት ለመለየት አንቸገርም ነበር፣ (ከፖለቲካ አንፃር )
አውሮፓ ህብረት ዕስካሁን ድረስ ከህወሓት ጎን እንደተሰለፈ ነው። ምንም እንኳን የሀይል ሚዛኑን እያየ ቢራመድና የዩክሬን ጉዳዩ ለህወሓት ያለውን ትኩረት ቢነፍገውም ህብረቱ እስካህን ድረስ አቋም አንድ ነው።
በወልቃይት በኩል የተጨፈጨፉት አማሮች መሉ በመሉ የትግራይ ተወላጆች ብቻ ናቸው ብሎ ነው የሚያምነው። ይህ ከህወሓት ያገኘው ጥቅም ወይም የገባችለት ቃል ስላለ የሟቾችን አስክሬን ረግጥ ለህወሓት ያዳላውን አቋሙን እንደያዘ ነው። ህወሓት ኤርትራን ለመውረር ሞክራ በክፉኛው ከተደቀሶች በኋላ ነገሮች የመቀያየር ባህሪ አምጥተዋል።

የትግራይ ቴሌቪዥን በዚህ ሦስት ቀን ውስጥ የኢትዮጵያ አንድነት እንዲጠበቅ ከተፈለገ ሁሉንም ያሳተፈ ወይይት መረደግ አለበት የሚል ሀሽታግ ጀምሯል። ከእንገነጠላለን፣ ወደ ወይይት መር የተመለሱት በኤርትራ ድብደባ ልባቸው ድንጋጤ ላይ ስላለ፣ አማራጭ መንገድ እየፈለጉ ነው። ይህ የህወሓት አቋም ለአፍሪካ ህብረትና ለአረብ ሊግ በደብዳቤ መልክ ተልኳል።
አውሮፓ ህብረት ከላይ ወደታች የወረደባቸውን እያንዳዱ ንግግሮቹ ህወሓትን እንዴት እንታደግ ከሚል የሚመነጭ ሀሳብ ነው። የጨመረው ድብቆ የያዘውን፣ ሴራ በቅርብ ቀን ለአለም ህዝብ ይፋ ያደርጋል። እሱም በወልቃይት በኩል የሰላም አስከባሪ ይግባ የሚል ነው። ሂዊ ይሄንን ማሳከት ከቻለች ትልቅ ነጥብ ጥላ ጦርነቱን በበላይነት አጠናቀቀች ማለት ነው። አሁን ሂዊይ የሰላም ሰበካ ላይ ናት። ማረኳቸው የምትላቸውን የመከላከያ ስራዊት አባሎችን መልሳለች። ሁሉንም አካታች ድርድር ይከፈትልኝ እያለች ነው።

ከዚህ ቀጥላ በሰላም ፈላጊ ስም ወልቃኢትን ለምዕራባውያን አስረክባ
የሱዳኑን ቦርደር ለመጠቀም ያስችላታል። ይህ ሂዊይም የአውሮፓ ህብረትም የጋራ አጀንዳቸው ነው። በቀጣይ ቀናቶች የአውሮፓ ህብረት በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ ይመክራል። ሂዊይም ይሄንን እድል ለመጠቀም ፍፁም ስሙን ጠራውታ የማታውቀውን ፈጣሪዋን እየለመነች ማስቸገር ይዘዋለች። መቸም (ዋቃ) ለህወሓት የሚያዝን የምህረት ምዕራፍ ይኖረዋል ብየ አልገምትም። ያው እሱ ያቃል እንጅ !

ሱሌማን አብደላ

" የMokeypox በሽታ መስፋፋት ለኢትዮጵያም ስጋት ነው " በኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የቅድመ ማስጠንቀቂያ እና መረጃ ስርዓት አስተዳደር ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ዘውዱ አሰፋ ለ...
23/05/2022

" የMokeypox በሽታ መስፋፋት ለኢትዮጵያም ስጋት ነው "

በኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የቅድመ ማስጠንቀቂያ እና መረጃ ስርዓት አስተዳደር ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ዘውዱ አሰፋ ለአል ዓይን ኒውስ በሰጡት ቃል የተናገሩት ፦

" ቫይረሱ ከዚህ በፊት ፈንጣጣ መሰሉ በሽታ ተጠቂ የሌለባቸው ሀገራት ሳይቀር እየተስፋፋ ነው፡፡

እንደማንኛውም ሀገር እኛም በቫይረሱ ስርጭት ስጋት አለን። በኢትዮጵያ የመግቢያ እና መውጫ በሮች ላይ የተለመደው ክትትል እየተደረገ ይገኛል።

በሀገሪቱ የየብስ እና የአየር ትራንስፖርት መግቢያ እና መውጫ ላይ ወደ ሀገር ውስጥ እንዳይገባ እና ወደ ሌሎች ሀገራት እንዳይሄድ የተላላፊ በሽታዎች ክትትል እየተደረገ ነው።

የበሽታው ተጠቂ በኢትዮጵያ ቢገኝ ማድረግ ስለሚገባን ስራዎች፣ ለህብረተሰቡ መሰጠት ስለሚገባው የግንዛቤ ፈጠራ መልዕክት እና የህክምና ክትትል ስራዎችን ለመለየት የቅድመ ዝግጅት ስራዎች በመሰራት ላይ ነው "

TIME መጽሔት በ2022 የዓመቱ 100 ተፅእኖ ፈጣሪ ሰዎች መካከል የኢትዮጵያ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐብይ አህመድን አካቷቸዋል።
23/05/2022

TIME መጽሔት በ2022 የዓመቱ 100 ተፅእኖ ፈጣሪ ሰዎች መካከል የኢትዮጵያ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐብይ አህመድን አካቷቸዋል።

አንድ የኡጋንዳ ሚኒስትር “ደሆች ገነት አይገቡም” ማለታቸው እያነጋገረ ነውድሆች ገነት የማይገቡት ሁሌም ፈጣሪን በድህነታቸው ስለሚያማርሩ ነው የሚሉት ሚኒስትሩባለጸጋ መሆን ክብር ነው ሲሉ ስ...
23/05/2022

አንድ የኡጋንዳ ሚኒስትር “ደሆች ገነት አይገቡም” ማለታቸው እያነጋገረ ነው

ድሆች ገነት የማይገቡት ሁሌም ፈጣሪን በድህነታቸው ስለሚያማርሩ ነው የሚሉት ሚኒስትሩባለጸጋ መሆን ክብር ነው ሲሉ ስለመናገራቸውም ተዘግቧል፡፡

ሚኒስትሩ “ድሆች ገነት የማይገቡት ሁሌም ፈጣሪን ስለሚያማርሩ ነው” ብለዋል

ሩሲያ በሰመጠችው “ሞስክቫ” ምትክ አዲስ የጦር መርከብ ጥቁር ባህር ላይ አሰማራችአዲሷ የሩሲያ መርከብ “ማካሮቭ” የሚል መጠሪያ ያላት መሆኑ ተነግሯል። “ማካሮቭ” የጦር መርከብ ስምሪት የሩሲ...
23/05/2022

ሩሲያ በሰመጠችው “ሞስክቫ” ምትክ አዲስ የጦር መርከብ ጥቁር ባህር ላይ አሰማራች

አዲሷ የሩሲያ መርከብ “ማካሮቭ” የሚል መጠሪያ ያላት መሆኑ ተነግሯል። “ማካሮቭ” የጦር መርከብ ስምሪት የሩሲያን የሚሳዔል ጥቃቶች ከፍ ሊያደርገው እንደሚችል የዩክሬን ጦር ሰግቷል።

“ማካሮቭ” የጦር መርከብ ስምሪት የሩሲያን የሚሳዔል ጥቃቶች ከፍ ሊያደርገው እንደሚችል የዩክሬን ጦር ሰግቷል

ቻይና ታይዋንን  በኃይል ለመያዝ ከሞከረች አሜሪካ ወታደራዊ ኃይሏን ትጠቀማለች -ፕሬዚዳንት  ባይደንቻይና የታይዋን ደሴትን በኃይል ለመያዝ ከሞከረች አሜሪካ  በቀጥታ  ከቻይና ጋር ግጭት ውስ...
23/05/2022

ቻይና ታይዋንን በኃይል ለመያዝ ከሞከረች አሜሪካ ወታደራዊ ኃይሏን ትጠቀማለች -ፕሬዚዳንት ባይደን

ቻይና የታይዋን ደሴትን በኃይል ለመያዝ ከሞከረች አሜሪካ በቀጥታ ከቻይና ጋር ግጭት ውስጥ ለመግባት ዝግጁ መሆኗን የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን አስታወቁ፡፡

ጆ ባይደን ከጃፓኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ፉሚዮ ኪሺዳ ጋር በቶኪዮ ተገናኝተው በጋራ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ እንደተናገሩት÷ ዋሽንግተን አስፈላጊ ሆኖ ካከኘቸው በቻይና እና በታይዋን መካከል በሚፈጠር ግጭት ውስጥ ታይዋንን ለመከላከል በቀጥታ ወታደራዊ ኃይሏን ልታሰማራ ትችላለች፡፡

"እኛ የቻይናን ሉዓላዊነት እናከብራለን ፤ ነገር ግን ቻይና ታይዋንን በኃይል የመያዝ ስልጣን የላትም ይህንን አንታገስም " ነው ያሉት ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን፡፡

በእስያ ምድር የመጀመሪያውን ይፋዊ የሥራ ጉብኝት በማድረግ ላይ የሚገሹት ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ፥ ጉብኝቱ በክፍለ ዘመኑ የመጀመሪያው ቻይናን ያላካተተ ጉብኝት ነው ተብሏል፡፡

የጃፓኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ፉሚዮ ኪሺዳ እና የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ባይደን ቻይናን እንዴት እንከላከል በሚል ርዕሰ ጉዳይ ዙርያም ሳይመክሩ እንዳለቀሩ ኒኬ ኤዥያ የተባለን የዜና ምንጭ ጠቅሶ አርቲ ዘግቧል፡፡

በውይይቱ ላይ ከሁለቱ መሪዎች በተጨማሪ የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን፣ የንግድ ሚኒስትር ጂና ሬይሞንዶ፣ የንግድ ተወካይ ካትሪን ታይ፣ በጃፓን የአሜሪካ አምባሳደር ራህም አማኑኤል እና የብሄራዊ ደህንነት አማካሪ ጃክ ሱሊቫን መገኘታቸው በዘገባው ተጠቅሷል፡፡

ቻይና በአሁኑ ጊዜ ሰራዊቷን ወደ ታይዋን እያስጠጋች በማስፈር ላይ መሆንዋ “ ቻይና ሰራዊቷን በማስገባት ታይዋንን ልትወር ነው” የሚል ከፍ ያለ ስጋት እንዳለባትም ነው ባይደን በንግግራቸው የጠቆሙት።

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ከዚህ ቀደም ባደረጉት ንግግር፥ ዋሽንግተን የቻይናን “የአንድ ቻይና” ፖሊሲን እንደሚያከብር ነበር የገለጹት - ይህም ቤጂንግ በሚገኘው ማዕከላዊ መንግስት ለምትመራ ለአንድ ቻይና እውቅና የሚሰጥ ንግግር ተደርጎ ነበር የተወሰደው።

ዛሬ ደግሞ ታይዋንን ለመከላከል ስንል ከቻይና ጋር ለመዋጋት ዝግጁ ነን ሲሉ ተደምጠዋል ባይደን።

ቻይና በበኩሏ÷ ከጥቂት ሳምንታት በፊት በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴሯ በኩል እንዳስታወቀችው ፥ የአሜሪካው የቅርብ ጊዜ ድርጊት የአንድ ቻይና መርህን ለማጥፋት ያለመ ነው፡፡

"ታይዋንን በተመለከተ በሚፈፀም እንዲህ ዓይነት የፖለቲካ ሸፍጥ ውስጥ የሚሳተፉ እና በእሳት የሚጫወቱ አካላት ይቃጠላሉ" ስትል ማስጠንቀቋም የሚታወስ ነው ፡፡

ከአንድ ግብር ከፋይ ላይ 80 ሺህ ብር ጉቦ የተቀበለ የገቢዎች ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ባለሙያ እጅ ከፈንጅ ተያዘ   አዲስ አበባ፣ ግንቦት 15፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ሃሰተኛ ደረሰኝ አቅርበሃ...
23/05/2022

ከአንድ ግብር ከፋይ ላይ 80 ሺህ ብር ጉቦ የተቀበለ የገቢዎች ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ባለሙያ እጅ ከፈንጅ ተያዘ


አዲስ አበባ፣ ግንቦት 15፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ሃሰተኛ ደረሰኝ አቅርበሃል በሚል ምክንያት ከአንድ ግብር ከፋይ ላይ 80 ሺህ ብር ጉቦ የተቀበለ የገቢዎች ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት የታክስ ኢንተለጀንስ ባለሙያ እጅ ከፈንጅ ተይዞ ምርመራ እየተደረገበት እንደሚገኝ የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ፡፡


ተጠርጣሪው የጉለሌ ክፍለ ከተማ ገቢዎች አነስተኛ ግብር ከፋይ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት የታክስ ኢንተለጀንስ እና የኦፕሬሽን ባለሙያ ሲሆን÷ በየካቲት ወር ውስጥ የግል ተበዳይን ፋይል አውጥቶ ስልክ በመደወል ሃሰተኛ ደረሰኝ ለመስሪያ ቤታችን አቅርበዋል በወንጀል ይጠየቃሉ ብሎ ወደ ቢሮ እንዲመጡ መጥራቱን ከአዲስ አበባ ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ክፍል የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡


የግል ተበዳይ ወደ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤቱ ቢሮ ሄደው ከግለሰቡ ጋር ከተገናኙ በኋላ÷ ሃሰተኛ ደረሰኝ እንዳላስገቡ እና ይህንንም ማረጋገጥ እንደሚቻል ለባለሙያው ቢገልፁለትም ባለሙያው ግን ሊከሰሱ ስለሆነ ጉዳዩን ከእኔ ጋር ተደራድረው ቢፈቱ ይሻላል ብሎ 140 ሺህ ብር ጉቦ ይጠይቃቸዋል፡፡

የግል ተበዳይም ከቤተሰብ ጋር ልማከር ብለው ከተለያዩ በኋላ ለ1 ወር ከ15 ቀናት ያህል ሳይገናኙ ይቆያሉ፡፡

ተጠርጣሪው ግን በድጋሚ ወደግል ተበዳይ ስልክ በመደወሉ ጭቅጭቁ የበዛባቸው የግል ተበዳይ ሁኔታውን ለገቢዎች የስራ ኃላፊዎች በማሳወቅ እና በጋራ በመሆን ጉዳዩን ለፖሊስ አመልክተዋል፡፡

ፖሊስም የቀረበለትን ጥቆማ ተቀብሎ ባደረገው ክትትል ተጠርጣሪው ከግል ተበዳይ ላይ 80 ሺህ ብር ለመቀበል ተስማምቶ ግንቦት 11 ቀን 2014 ዓ.ም ጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 ፊናንስ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በሚገኝ አንድ ባንክ ውስጥ ቀጥሯቸው ከተገናኙ በኋላ ገንዘብ ገቢ ማድረጊያ ፎርም በመሙላት 80 ሺህ ብሩን ተቀብሎ ወደራሱ አካውንት ሊያስገባ ሲል እጅ ከፈንጅ ተይዞ ምርመራ እየተረገበት እንደሚገኝ የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡

ግንቦት 15፣ 2014ኮሎኔል ሳያድ ኮዳይ የተባሉ የኢራን የጦር መኮንን በመዲናዋ ቴሕራን በሁለት ታጣቂዎች በተከፈተባቸው ተኩስ መገደላቸው ተሰማ፡፡ኮሎኔሉ አብዮታዊ ዘብ የተሰኘው የኢራን የጦር...
23/05/2022

ግንቦት 15፣ 2014

ኮሎኔል ሳያድ ኮዳይ የተባሉ የኢራን የጦር መኮንን በመዲናዋ ቴሕራን በሁለት ታጣቂዎች በተከፈተባቸው ተኩስ መገደላቸው ተሰማ፡፡

ኮሎኔሉ አብዮታዊ ዘብ የተሰኘው የኢራን የጦር ክፍል ባልደረባ እንደሆኑ ዲፌንስ ፖስት ፅፏል፡፡

አብዮታዊ ዘብ በተለይም የውጭ አገራት የጦር ተልዕኮዎችን የሚወጣ የጦር ክፍል እንደሆነ በመረጃው ተጠቅሷል፡፡

ኮሎኔል ሳያድ ኮዳይ የተገደሉት መኪና እየነዱ በማምራት ላይ ሳሉ በሞተር ብስክሌቶች በቀረቧቸው ማንነታቸው ባልተለየ ታጣቂዎች ነው ተብሏል፡፡

ማፈኛ በተገጠመላቸው የጦር መሳሪያዎች ቢያንስ አምስት ጊዜ ተኩሰውባቸው ከስፍራው እልም ማለታቸው ታውቋል፡፡

የኢራን መንግስት የሽብር አንጋሾች አለም አቀፍ ጀብደኞች ድርጊት ነው ለማለት አላረፈደም፡፡

አባባሉ ብዙው ጊዜ ከአሜሪካ ጋር እንደሚያያዝ በመረጃው ተጠቅሷል፡፡

ከሁለት ዓመታት በፊትም የኢራን አብዮታዊ ዘብ ከፍተኛ የጦር መኮንን የነበሩት ጄኔራል ቃሲም ሶሌማኒ በአሜሪካ ሰው አልባ በራሪ አካል (ድሮን) በኢራቋ ርዕሠ ከተማ ባግዳድ እንደተገደሉ ዘገባው አስታውሷል፡፡

የኔነህ ከበደ

በታሊባን ትእዛዝ መሰረት የአፍጋኒስታን ሴት የቴሌቪዥን ዜና አቅራቢዎች ፊታቸውን መሸፈን ጀመሩትዕዛዙ ሃሙስ እልት ከተገለጸ በኋላ፣ ጥቂት የዜና ማሰራጫዎች ብቻ ተግባራዊ ቢያደርጉትም፤ የታሊባ...
23/05/2022

በታሊባን ትእዛዝ መሰረት የአፍጋኒስታን ሴት የቴሌቪዥን ዜና አቅራቢዎች ፊታቸውን መሸፈን ጀመሩ

ትዕዛዙ ሃሙስ እልት ከተገለጸ በኋላ፣ ጥቂት የዜና ማሰራጫዎች ብቻ ተግባራዊ ቢያደርጉትም፤ የታሊባን ምክትል እና በጎነት ሚኒስቴር አዋጁን ማስፈፀም ከጀመረ በኋላ አብዛኞቹ የሀገሪቱ ሴት የቴሌቭዥን ዜና አቅራቢዎች ፊታቸው ተሸፍኖ ታይቷል።

ባለፈው ዓመት ስልጣን መልሶ የተቆጣጠረው ታሊባን ሴቶችን የሚመለከቱ ክልከላዎችን በብዛት በማውጣት ላይ ሲሆን፤ ከተላለፉ ትእዛዞች አንዱ ሴት የቴሌቪዥን አቅራቢዎች ሂጃብ እንዲለብሱ እና ፊታቸውን እንዲሸፍኑ የሚለው መሆኑ ይታወቃል።

የኔቶ ዋና ጸኃፊ ፊንላንድ እና ስዊድን የእንቀላቀል ጥያቄያቸውን ያቀረቡት “አስጨናቂ ወቅት ላይ ነው”ብለዋልከብዙ ፖለቲካዊ ውጣ ውረድ በኋላ የኖርዝ አትላንቲክ ትሪቲ ኦርጋናይዜሽ(ኔቶ)ን ለመ...
23/05/2022

የኔቶ ዋና ጸኃፊ ፊንላንድ እና ስዊድን የእንቀላቀል ጥያቄያቸውን ያቀረቡት “አስጨናቂ ወቅት ላይ ነው”ብለዋል

ከብዙ ፖለቲካዊ ውጣ ውረድ በኋላ የኖርዝ አትላንቲክ ትሪቲ ኦርጋናይዜሽ(ኔቶ)ን ለመቀላቀል ጥያቄ ቢያቀርቡም የኔቶ አባል የሆነችው ቱርክ ሁለቱ ሀገራት እንዳይቀላቀሉ እንቅፋት ሆናባቸዋለች፡፡

የሁለቱ ሀገራት የመቀላቀል ጥያቄ በኔቶ ዋና ጸኃፊ ጄንስ ስቶልተንበርግ ዘንድ በበጎ ተቀባይነት ማግኘቱን ሲጂቲኤን ዘግቧል፡፡

ቀደም ሲል የኖርዌይ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ሲያገለግሉ የነበሩት ስቶልተንበርግ የኖርዲክ ጎረቤቶቻቸው ኔቶ ለመቀላቀል ያሳለፉት ውሳኔ“አስጨናቂ ወቅት ላይ ነው”ብለዋል።

ስቶልተንበርግ እንዳሉት አባል ሀገራት በመስፋፋት አስፈላጊነት ላይ ይስማማሉ፤ ህብረቱ በባልቲክ ክልል ጠንካራ ቢሆንም አጠቃላይ የጸጥታ ሁኔታን ለማሳደግ እንደሚረዳም አሳስበዋል።

የኔቶ ዋና ጸኃፊ ሁለቱ ሀገራት የእንቀላቀል ጥያቄያቸውን ያቀረቡት አስጨናቂ ወቅት ላይ ነው”ብለዋል

በርካታ ሰዎች መታሰራቸው ተገለፀ ❗ኢሰመኮ የፌዴራል መንግሥት እና የክልል የፀጥታ ኃይሎች "በተቀናጀ መንገድ የሕግ በላይነትን ማስከበር" በሚል ባለፉት ጥቂት ቀናት መውሰድ በጀመሩት እርምጃ፣...
22/05/2022

በርካታ ሰዎች መታሰራቸው ተገለፀ ❗

ኢሰመኮ የፌዴራል መንግሥት እና የክልል የፀጥታ ኃይሎች "በተቀናጀ መንገድ የሕግ በላይነትን ማስከበር" በሚል ባለፉት ጥቂት ቀናት መውሰድ በጀመሩት እርምጃ፣ ጋዜጠኞችና የማኅበረሰብ አንቂዎችን ጨምሮ በርካታ ሰዎች መታሰራቸውን ገልጿል።

ኢሰመኮ ሁኔታዎችን በቅርበት እየተከታተለ መሆኑን ገልጾ፤ የተወሰኑት ተጠርጣሪ ታሳሪዎች በቤተሰቦቻቸው የተጎበኙና በተለያየ የጊዜ መጠን ወደ ፍ/ቤት የቀረቡ ቢሆንም በርካታ ታሳሪዎች ከፍ/ቤት ትዕዛዝ ውጭ መታሰራቸውን፣ ፍ/ቤት ያለመቅረባቸውን፣ በቤተሰብ አለመጎብኘታቸውን አመልክቷል።

በተለይ በአማራ ክልል በርካታ ታሳሪዎች ከመደበኛ መኖሪያ አካባቢያቸውና ከመደበኛ እስር ቦታዎች ውጭ ጭምር በመታሰራቸው ቤተሰቦቻቸው ያሉበትን እንኳን ለማወቅ መቸገራቸውን አስረድቷል።

በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ሕግና ሥርዓትን ለማስከበር መንግሥት በሕጋዊ መንገድ ሊወስድ የሚችላቸውን እርምጃዎች እገበዘባለሁ ያለው ኮሚሽኑ " የዚህ አይነት የሰብአዊ መብቶች መርሆዎችን ያልተከተለና የተስፋፋ እስር ተገቢ አለመሆኑን " ዶ/ር ዳንኤል በቀለ ገልጸዋል።

" በተለይ የፌደራል ሆነ የክልል የፀጥታ ኃይሎች ተጠርጣሪዎችን ከወንጀል ምርመራ በፊት ከማሰር፣ ጋዜጠኞችን በስራቸው ምክንያት ከማሰር እና ከፍ/ቤት ትዕዛዝ ውጭ ሰዎችን ከማሰር ሊታቀቡ ይገባል። በማናቸውም አይነት ሁኔታ የታሰሩ ሰዎች ሁሉ ቤተሰቦቻቸው ወዲያውኑ እንዲያውቁ እንዲደረግና ወደ ፍ/ቤትም ሊቀርቡ ይገባል” ብለዋል፡፡

አክለውም ኮሚሽኑ በማናቸውም ስፍራ በእስር ላይ የሚገኙ ሰዎችን ሁኔታ በድንገተኛ ጉብኝት ለመከታተል በተሰጠው ስልጣንና ኃላፊነት መሰረት፣ ክትትል በማድረግ ላይ መሆኑን ገልፀው ሁሉም የፌደራልና የክልል መንግሥታት አካላት ለኮሚሽኑ ሥራ የመተባበር ግዴታቸውን በአግባቡ እንዲወጡ አሳስበዋል፡፡

የቀድሞው የጊኒ ፕሬዝዳንት ሀገራቸውን ለቀው እንዲወጡ ተፈቀደላቸውየቀድሞው የጊኒ ፕሬዝዳንት አልፋ ኮንዴ ለህክምና ወደ ቱርክ እንደሚሄዱ ተገልጿል፡፡ አልፋ ኮንዴ ባሳለፍነው መስከረም ወር ላይ...
22/05/2022

የቀድሞው የጊኒ ፕሬዝዳንት ሀገራቸውን ለቀው እንዲወጡ ተፈቀደላቸው

የቀድሞው የጊኒ ፕሬዝዳንት አልፋ ኮንዴ ለህክምና ወደ ቱርክ እንደሚሄዱ ተገልጿል፡፡
አልፋ ኮንዴ ባሳለፍነው መስከረም ወር ላይ ነበር በሀገሪቱ ልየ ሀይል አዛዥ ኮለኔል ማማዲ ዶምቢያ በተፈጸመባቸው መፈንቅለ መንግስት ከስልጣናቸው የተነሱት፡፡
ሀገሪቱን እየመራ ያለው ወታደራዊ መንግስትም የ81 ዓመቱ የቀድሞው ፕሬዝዳንት አልፋ ኮንዴ ለህክምና ወደ አንካራ እንዲያቀኑ ፈቅዶላቸዋል ተብሏል፡፡
የቀድሞው የጊኒ ፕሬዝዳንት ኮንዴ እና ሌሎች የቀድሞ ባለስልጣናት በሙስና፣ በአስገድዶ ደፈራ፣ሰዎችን በማሰቃየት እና ሌሎች ወንጀሎችን ፈጽመዋል በሚል ከአንድ ወር በፊት ክስ ተመስርቶባቸዋል፡፡

ተወዳጁ የእንግሊዝ ፕሪሚየርሊግ ዛሬ አጓጊነቱን ይዞ ፍፃሜውን ያገኛል። ጋርዲዮላ የጨበጠውን ዋንጫ ከፍ አድርጎ ያነሳል ወይስ ለክሎፕ አሳልፎ ይሰጣል የሚለው በጉጉት ይጠበቃል።ሌሎች ተጠባቂ ጨ...
22/05/2022

ተወዳጁ የእንግሊዝ ፕሪሚየርሊግ ዛሬ አጓጊነቱን ይዞ ፍፃሜውን ያገኛል። ጋርዲዮላ የጨበጠውን ዋንጫ ከፍ አድርጎ ያነሳል ወይስ ለክሎፕ አሳልፎ ይሰጣል የሚለው በጉጉት ይጠበቃል።
ሌሎች ተጠባቂ ጨዋታዎች አርሰናል ከኤቨርተን፣ ኖርዊች ከቶተነሃም፣ ሁሉም በተመሳሳይ ሰዓት ይደረጋሉ።
.et

የኦሮሚያ ክልል በሀገራችን የመጀመሪያ የሆነዉን በገጠር ዘመናዊ የመኖሪያ ቤት ግንባታ ልማትን አስጀመረ።የኦሮሚያ ክልል የመኖሪያ ቤት ችግር ለመቅረፍ በከተሞች ብቻ ተወስኖ ሲሰራ የነበረን የቤ...
22/05/2022

የኦሮሚያ ክልል በሀገራችን የመጀመሪያ የሆነዉን በገጠር ዘመናዊ የመኖሪያ ቤት ግንባታ ልማትን አስጀመረ።

የኦሮሚያ ክልል የመኖሪያ ቤት ችግር ለመቅረፍ በከተሞች ብቻ ተወስኖ ሲሰራ የነበረን የቤት ልማት ስራን በገጠርም ለማስፋት የሚያስችል ፕሮግራም በዛሬዉ እለት በክቡር አቶ ሽመልስ አብዲሳ የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት በይፋ አስጀምረዉታል። በእለቱ ለግንባታ የሚዉለዉን የጡብ ማምረቻ ማሽኖችም ለጥቃቅን እና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች የማስተላለፍ ስራ ተከናዉኗል።

22/05/2022
ሩሲያ ሞርጋን ፍሪማንን ጨምሮ 963 አሜሪካዊያን ወደ ሀገሯ እንዳይገቡ አገደችዩክሬን የሰሜን አትላንቲክ ቃልኪዳን ጦር ወይም ኔቶን እቀላቀላለሁ ማለቷን ተከትሎ ከሩሲያ ጋር ወደ ይፋዊ ጦርነት...
22/05/2022

ሩሲያ ሞርጋን ፍሪማንን ጨምሮ 963 አሜሪካዊያን ወደ ሀገሯ እንዳይገቡ አገደች

ዩክሬን የሰሜን አትላንቲክ ቃልኪዳን ጦር ወይም ኔቶን እቀላቀላለሁ ማለቷን ተከትሎ ከሩሲያ ጋር ወደ ይፋዊ ጦርነት ካመራች ሶስት ወር ሊሞላው ጥቂት ቀናት ብቻ ቀርተውታል፡፡አሜሪካን ጨምሮ ምእራባውያን ሀገራት ለዩክሬን ወታደራዊ ድጋፍ እያደረጉ ይገኛሉ፡፡https://am.al-ain.com/article/russia-bans-entry-of-963-us-citizens-including-morgan-freeman

አዲሱ የሩሲያ ውሳኔ በአሜሪካ ተደጋጋሚ ለተጣሉ ማዕቀቦች ምላሽ ነው ተብሏል

በመዲናዋ ለሐረሪ ክልል ባህል ማዕከል መገንቢያ ቦታ ተዘጋጅቷል - ከንቲባ አዳነች አቤቤአዲስ አበባ፣ ግንቦት 14፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ለሐረሪ ክልል ባህል ማዕከል መገንቢያ ...
22/05/2022

በመዲናዋ ለሐረሪ ክልል ባህል ማዕከል መገንቢያ ቦታ ተዘጋጅቷል - ከንቲባ አዳነች አቤቤ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 14፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ለሐረሪ ክልል ባህል ማዕከል መገንቢያ ቦታ መዘጋጀቱን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ፡፡

“የሸዋል ኢድ” በአዲስ አበባ ሃይማኖታዊና ባሕላዊ ትውፊቱን በጠበቀ መልኩ የተከበረ ሲሆን ፥ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በፕሮግራሙ ላይ ተገኝተው ለሐረሪ ባህል ማእከል መገንቢያ ቦታ መዘጋጀቱንም አብስረዋል፡፡

ከንቲባዋ አክለውም ፥አዲስ አበባ የሁላችንም ከተማ ነች፤ ይህን ውብ የሸዋል ባህል ከሌሎች ባህሎቻችን ጋር አዋህደን የአብሮነት መድመቂያ እንዲሆን ከተማ አስተዳድሩ ይደግፋል፤ አብሮም ይሰራል ብለዋል፡፡

እኛ ኢትጵያውያን የብዙ ደማቅና ውብ ባህሎችና ወጎች ባለቤት ብንሆንም፥ የሌሎችን ባህልና ማንነት በፍቅር ይዘን ስንከባከብ አንድነታችን የበለጠ ይጎለብታል ብለዋል፡፡

የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ኦርዲን በድሪ በበኩላቸው ፥ የዘንድሮው የሸዋል ኢድን ከሌሎች የወንድም ብሔር ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ጋር በጋራ ለማክበር የተደረገው ጥረት ውጤታማ እንደሆነ መናገራቸውን ከመዲናዋ ከንቲባ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

Address


Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Info Daily posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

  • Address
  • Alerts
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share