ዜና - Zena

  • Home
  • ዜና - Zena

ዜና - Zena Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from ዜና - Zena, News & Media Website, .

በህወሓት ጁንታ ታግተው የነበሩት ብርጋደል ጀነራል አዳምነህ መንገስቴን ጨምሮ 1 ሺህ ያክሉ የሰሜን እዝ የመስመራዊና ከፍተኛ መኮነኖች ተለቀቁአዲስ አበባ፤ ህዳር 30 ፤2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ...
09/12/2020

በህወሓት ጁንታ ታግተው የነበሩት ብርጋደል ጀነራል አዳምነህ መንገስቴን ጨምሮ 1 ሺህ ያክሉ የሰሜን እዝ የመስመራዊና ከፍተኛ መኮነኖች ተለቀቁ
አዲስ አበባ፤ ህዳር 30 ፤2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የህወሃት ጁንታ ለግብዣ በሚል ጠርቶ አግቷቸው ከነበሩት የሰሜን እዝ ምክትል አዛዥ ለኦፕሬሽን ብርጋደል ጀነራል አዳምነህ መንገስቴን ጨምሮ 1 ሺህ ያክሉ የሰሜን እዝ የመስመራዊና ከፍተኛ መኮነኖች ተለቀቁ።
የህወሃት ጁንታ ጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም ለግብዣ በሚል ጠርቶ አግቷቸው ከነበሩት የሰሜን እዝ ምክትል አዛዥ ለኦፕሬሽን ብርጋደል ጀነራል አዳምነህ መንገስቴን ጨምሮ 1 ሺህ ያህል የሰሜን እዝ መስመራዊና ከፍተኛ መኮነኖችን የአገር መከላከያ ሰራዊትና የፌዴራል ፖሊስ አባላት በሰሩት የጋራ አሰሳ አስለቀቁ።
የመከላከያ ኢንዶክትሪኔሽን ዋና ዳይሬክተር ሜጀር ጀነራል መሃመድ ተሰማ ለኢዜአ እንደገለጹት የህውሃት ጁንታ ጥቅምት 24 ቀን ምሽት ላይ የእራት ግብዣ ብሎ ከጠራ በኋላ አፍኖ በመውሰድ አግቷቸው ቆይቷል።
የጁንታው ሃይል መስመራዊና ከፍተኛ መኮንኖችን በሸሸበት ቦታ ሁሉ ይዟቸው ሲጓዝ ቆይቶ በቀድሞው የትጥቅ ትግል ወቅት የማዘዣ ቤዝ በነበረው አዴት በሚባል ቦታ አግቷቸው እንደነበርና የጁንታው ታጣቂ ሃይል መደበቁ በአሰሳና በጥናት ተደርሶበታል።
በዚሁ መሰረት የአገር መከላከያ ሰራዊትና የፌዴራል ፖሊስ ባደረጉት የጋራ አሰሳ እና እርምጃ መስመራዊና ከፍተኛ መኮነኖቹ ምንም ጉዳት ሳይደርስባቸው ከጁንታው አስለቅቀዋል።
ሰራዊቱ ያስለቀቃቸው 1 ሺህ ያክል የመስመራዊና ከፍተኛ መኮነኖች አሁን ላይ ሰራዊቱን መቀላቀላቸውን ሜጀር ጀነራል መሀመድ ገልጸዋል።
ሰራዊቱ ከጁንታው ካስለቀቃቸው መካከል የሰሜን እዝ ምክትል አዛዥ ለኦፕሬሽን ብርጋደል ጀነራል አዳምነህ መንገስቴም ይገኙበታል።
የጁንታውን አባላት የማደን ስራ ተጠናክሮ መቀጠሉን የገለጹት ሜጀር ጀነራል መሀመድ የመጨረሻ ምእራፍ በሆነው ወንጀለኞችን የማደንና የመልሶ ግንባታ ምእራፍ የተደበቀውን ጁንታ አስሶ የመያዙ ስራ በመከላከያ ሰራዊትና በፌዴራል ፖሊስ የጋራ ቅንጅት ተጠናክሮ ቀጥሏል ብለዋል።
ወደፊትም የጁንታውን ቡድንና ወንጀለኞቸን ለህግ የማቅረብና የማደን ስራ ውጤት በየጊዜው ለህዝብ እንደሚገለፅ ጨምረው ገልጸዋል።

ሌተናል ጄኔራል አበባው ታደሰ  ወንጀለኞችን  በቁጥጥር ስር ማዋልን በሚመለከት ከጦር አዛዦች ጋር ተወያዩአዲስ አበባ፣ ህዳር 30፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ምክትል ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ሌተናል...
09/12/2020

ሌተናል ጄኔራል አበባው ታደሰ ወንጀለኞችን በቁጥጥር ስር ማዋልን በሚመለከት ከጦር አዛዦች ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ፣ ህዳር 30፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ምክትል ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ሌተናል ጄኔራል አበባው በቀጣይ ወንጀለኞችን የማደንና በቁጥጥር ስር ማዋልን በሚመለከት በመቐለ ከግንባሩ የጦር አዛዦች ጋር ተወያይተዋል።
በትግራይ በተወሰነ አካባቢ ላይ የተደበቁ የህወሃት ቡድን አባላትን አድኖ በቁጥጥር ስር ለማዋል በሚያስችል ዝርዝር ሁኔታ ላይ መምከራቸውን ከሰራዊቱ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ኢትዮጵያን ከኬንያ የሚያስተሳስረውን የመንገድ ፕሮጀክት መረቁ************የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና የኬንያው ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ...
09/12/2020

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ኢትዮጵያን ከኬንያ የሚያስተሳስረውን የመንገድ ፕሮጀክት መረቁ
************
የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና የኬንያው ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ፣ የሐዋሳ-ቡሌ ሆራ-ያቤሎ-ሜጋ-ሞያሌ መንገድ እና የጋራ ፍተሻ ጣቢያ ፕሮጀክትን ዛሬ በይፋ መርቀዋል።
500 ኪ.ሜ ርዝመት ያለውና የሞምባሳ-ናይሮቢ-አዲስ አበባ ኮሪደር አካል የሆነው መንገዱ ኢትዮጵያን ከኬንያ የሚያስተሳስር መሆኑ ተገልጿል።
በመንገዱ ምረቃ መርሐ ግብር ላይ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች እንዲሁም የፌዴራል እና የክልል ባለሥልጣናት ታድመዋል።
ይኸው የሐዋሳ-ቡሌ ሆራ-ያቤሎ-ሜጋ-ሞያሌ የአስፓልት ኮንክሪት መንገድ 6 ነጥብ 3 ቢሊዮን ብር ወጪ እንደተደረገበት ተገልጿል።
የሐዋሳ-ቡሌ ሆራ መንገድ የመጀመሪያው ኮሪደር 199 ነጥብ 6 ኪ.ሜ የሚሸፍን ሲሆን፣ ግንባታው ከ3 ነጥብ 1 ቢሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ በሦስት ተቋራጮች ግንባታው ተከናውኗል።
ቡሌ ሆራ-ያቤሎ ያለው ሁለተኛው ኮሪደር 192 ነጥብ 3 ኪ.ሜ ርዝመት ያለው እና ከ1 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ የተደረገበት ነው።
በአጠቃላይ የአዲስ አበባ-ሐዋሳ-ቡሌ ሆራ-ያቤሎ-ሜጋ-ሞያሌ መንገድ ግንባታ አዲስ አበባን ከካይሮ፣ ጋቦሮኒ፣ ኬፕ ታውን እና ኬንያ-ሞምባሳ የሚያገናኝ ከመሆኑም ባሻገር ደቡብ ሱዳንን-ከኬንያ ላሙ ወደብ ጋር ለማገናኘት የሚያስችል መሆኑ ታውቋል።
በሌላ በኩል ሦስተኛው እና የኢትዮጵያን መሬት አቋርጦ የሚያልፈው የትራንስ-አፍሪካ አውራ ጎዳና የመጨረሻው ኮሪደር የሆነው 109 ኪ.ሜ ርዝመት ያለው የሜጋ-ሞያሌ መንገድ ግንባታ ከአንድ ቢሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ ተጠናቅቆ በይፋ ተመርቋል።
በኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት በቦረና ዞን ከምትገኘው ከሜጋ ከተማ ጀምሮ እስከ ሞያሌ የሚዘልቀው ይኸው የአስፓልት ኮንክሪት መንገድ በኢትዮጵያ እና ኬንያ መካከል የወጪ እና ገቢ ንግድን የሚያጠናክር ነው ተብሏል።
በአጠቃላይ ከሐዋሳ-ሞያሌ የሚዘልቀው 500 ኪ.ሜ መንገድ እና የጋራ ፍተሻ ኬላ የጉምሩክ፣ የኢሚግሬሽን፣ የጤና እና የደረጃ ድርብርብ ፍተሻ በማስቀረት የጉምሩክ ሥርዓቱን ግልጽ፣ ቀላል እና ቀልጣፋ እንደሚያደርግ ታውቋል።
ከዚህ ባለፈ በድርብርብ የፍተሻ አሠራር የሚባክነውን ጊዜ እና ወጪ በከፍተኛ ሁኔታ የሚያስቀር ነው ተብሏል።
መንገዱ የኢትዮጵያ እና ኬንያን የወጪ እና ገቢ ንግድ በማቀላጠፍ ረገድ ትልቅ ሚና የሚጫወት ሲሆን፣ ቀደም ሲል የተጎዳ ይዞታ እንደነበረው ተጠቁሟል።

ጌታቸው ረዳን ጨምሮ የጁንታው ቡድን መሪዎች የሚጠቀሙባቸውና በአሻራ የሚከፈቱትን ጨምሮ ከ40 በላይ ተሽከርካሪዎች ተያዙአዲስ አበባ ፣ ህዳር 28 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ጌታቸው ረዳን ጨምሮ...
07/12/2020

ጌታቸው ረዳን ጨምሮ የጁንታው ቡድን መሪዎች የሚጠቀሙባቸውና በአሻራ የሚከፈቱትን ጨምሮ ከ40 በላይ ተሽከርካሪዎች ተያዙ
አዲስ አበባ ፣ ህዳር 28 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ጌታቸው ረዳን ጨምሮ የጁንታው ቡድን መሪዎች በእግራቸው መሸሽ ከመጀመራቸው በፊት ሲጠቀሙባቸው የነበሩ ከ40 በላይ የመንግስት ተሽከርካሪዎች በመከላከያ ሰራዊቱ እጅ ገብተዋል።
ቡድኑ ሰራዊቱን መቋቋም ተስኖት ወደ ገጠራማ ስፍራ በእግር መጓዝ ሲጀምር በታጣቂዎቹ በኩል ለማጥቃት ቢሞክርም እንዳልተሳካለት የ32ኛ ክፍለ ጦር አዛዥ ኮሎኔል ደጀኔ ፀጋዬ ተናግረዋል።
ፅንፈኛው ቡድን የመንገድ መሰረተ ልማት በሌለበት ከማይጨው 60 ኪሎ ሜትር ርቃ በምትገኘው ዴላ ወረዳ ከ40 በላይ የመንግስት እና በርካታ የግል ተሽከርካሪዎችን ይዞ ለመደበቅ ያደረገው ሙከራም መክሸፉን ነው ኮሎኔል ደጀኔ የተናገሩት።
ተሽከርካሪዎቹን ከፅንፈኛው ቡድን ሀይሎች አስጥሎ በቁጥጥር ስር ያዋለው ሰራዊቱ ባደረገው ፍተሻ በተሽከርካሪዎቹ ውስጥ መታወቂያ እና ፓስፖርቶች ተገኝተዋል።
የተለያዩ ሰነዶቻቸውን ጥለው ከሸሹት መካከል የቀድሞው የመቐለ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ፕሮፌሰር ክንደያ ገብረህይወት፣ የማይጨው አስተዳዳሪ የነበረው ሀፍቱ ኪሮስ እና ሌሎች የወረዳ አመራር የነበሩ ሰዎች ሰነድ ይገኝበታል።
የአካባቢው ነዋሪዎች በሰጡት ጥቆማ መሰረት ጌታቸው ረዳ በዴላ በኩል ከሸሸው ቡድን ውስጥ እንደሚገኝበትም ነው ኮሎኔል ደጀኔ የገለጹት፡፡
በመከላከያ ሰራዊቱ ከተያዙት ተሽከርካሪዎች መካከል ስድስቱ በአሻራ የሚከፈቱ እጅግ ዘመናዊ ተሽከርካሪዎች ሲሆኑ አራቱ ለኮሮና ወረርሽኝ መከላከል ስራ ከፌደራል መንግስቱ ለትግራይ ክልል የተበረከቱ አምቡላንሶች ይገኙበታል።
ፅንፈኛው ቡድን ሲጠቀምባቸው የነበሩ የጭነት ተሽከርካሪዎች እና ቦቴዎችንም ሰራዊቱ ወደ ማይጨው ከተማ እንዲገቡ አድርጓል ብለዋል።
በአሻራ የሚከፈቱትን ተሽከርካሪዎችም ከሞኤንኮ ጋር በመነጋገር ከአካባቢው ለማንሳትና ፍተሻ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑንም አውስተዋል።
በፋሲካው ታደሰ

"በኢትዮጵያ ውስጥ ዘላቂ ሠላም እንዲሰፍን ከተፈለገ ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ “ድርድር” ከሚለው ሀሳብ ወጥቶ ህወሓት በሰራው ወንጀል ተጠያቂ እንዲሆን ጫና ማሳደር ይኖርበታል፡፡"በአለም አቀፍ ...
07/12/2020

"በኢትዮጵያ ውስጥ ዘላቂ ሠላም እንዲሰፍን ከተፈለገ ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ “ድርድር” ከሚለው ሀሳብ ወጥቶ ህወሓት በሰራው ወንጀል ተጠያቂ እንዲሆን ጫና ማሳደር ይኖርበታል፡፡"
በአለም አቀፍ ተግዳሮታዊ ጉዳዮች ላይ ትኩረቱን አድርጎ የሚሰራ እና መቀመጫውን በአሜሪካ ያደረገው የአትላንቲክ ካውንስል የአፍሪካ ማዕከል ዳይሬክተር ብሮንዊን ብሩተን

Get the app => https://bit.ly/36Mjge5ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ ሆስፒታል የሚገኙ የሀገር መከላከያ ሠራዊት አባላትን ጎበኙ አዲስ አበባ፣ ህዳር 27፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ጠቅ...
06/12/2020

Get the app => https://bit.ly/36Mjge5
ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ ሆስፒታል የሚገኙ የሀገር መከላከያ ሠራዊት አባላትን ጎበኙ
አዲስ አበባ፣ ህዳር 27፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ ሆስፒታል የሚገኙ የሀገር መከላከያ ሠራዊት አባላትን ጎበኙ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ኢትዮጵያን ከራሳቸው ያስቀደሙ ጀግኖች የመከላከያ ሠራዊት አባላት ሲሉ የገለጿቸውን ወታደሮች ዛሬ ማለዳ ላይ የገበኙ መሆኑን በትዊተር ገጻቸው አስታውቀዋል።

በጤና ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ የተመራ ከፍተኛ የአመራሮች ቡድን የጎንደር ዪኒቨርሲቲ ሪፈራል ሆስፒታልን ጉበኘአዲስ አበባ፣ ህዳር 27፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታ...
06/12/2020

በጤና ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ የተመራ ከፍተኛ የአመራሮች ቡድን የጎንደር ዪኒቨርሲቲ ሪፈራል ሆስፒታልን ጉበኘ
አዲስ አበባ፣ ህዳር 27፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ የተመራ ከፍተኛ የአመራሮች ቡድን የጎንደር ዪኒቨርሲቲ ሪፈራል ሆስፒታልን ጉበኘ።
በጉብኝቱ ላይ የሰላም ሚኒስትር ዴኤታ ወይዘሮ ፍሬዓለም ሽባባው፣ የጤና ሚኒስትር ዲኤታ ክቡር ዶክተር ደረጀ ዱጉማ ፣ ብርጋዴር ጀነራል ጥጋቡ እና ከፍተኛ የአመራሮች ተሳትፈዋል።
ጉብኝቱ የጎንደር ዪኒሸርስቲ ፕሬዚዳንት እና የሆስፒታሉ ሜዲካል ዳይሬክተር በተገኙበት የተደረገ ሲሆን፥ የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰና የሰላም ሚኒስትር ዴኤታ ወይዘሮ ፍሬዓለም ሽባባው በአካል በየህሙማን ክፍል በመገኘት ታማሚዎችን አነጋግረዋል።
በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል በህግ ማስከበር ሂደት የተጎዱ ጀግኖች የመከላከያ ሰራዊት አባላት ለሀገራቸው በመዋደቅ ላበረከቱት አኩሪ የጀግንነት ተጋድሎ አድናቆታቸውን ገልፀዋል።
“ሀገራችሁ ኢትዮጵያ እና ህዝባችሁ የኮራችባችሁ ጀግኖች ናችሁ፤ እዚህ ከፊታችሁ የቆምነው እናንተ ጀግኖች ለሀገራችሁና ለህዝባችሁ ላሳያችሁት የላቀ ጀግንነት በኢትዮጵያ ህዝብና መንግስት ስም ልናመሰግናችሁ ነው፤ ውለታችሁን ሀገራችሁ አትረሳም” ብለዋል።
ልዑካኑ ከጎንደር ሆስፒታል ማህበረሰብና አመራሮች ጋር በመወያየትም ሆስፒታሉ ስለሚጠናከርበት ሁኔታ የጋራ መግባባት ላይ መድረሳቸውን የሰላም ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል።

የህወሓት ጁንታን ጭካኔ የሚያወግዙ ሰልፎች ተካሄዱአዲስ አበባ፣ ህዳር 27፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የህወሓት ጁንታውን ጭካኔ የተሞላበት ድርጊት የሚያወግዙ ሰልፎች በማይካድራ፣ ቆቦ፣ አላማጣ ተ...
06/12/2020

የህወሓት ጁንታን ጭካኔ የሚያወግዙ ሰልፎች ተካሄዱ
አዲስ አበባ፣ ህዳር 27፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የህወሓት ጁንታውን ጭካኔ የተሞላበት ድርጊት የሚያወግዙ ሰልፎች በማይካድራ፣ ቆቦ፣ አላማጣ ተካሄዱ።
የሀገር መከላከያ ሰራዊት በትግራይ ክልል እያከናወነ ያለውን ህግ የማስከበር ዘመቻ እንደሚደግፉ አሳውቀዋል።
ሰልፈኞቹ የትግራይ ህዝብ መልካም ወንድም እና እህት መሆኑን ገልጸዋል።
ከሀዲው የህወሓት ቡድን ለመልካሙ የትግራይ ህዝብም ጠላት ነው ብለዋል ሰልፈኞቹ።
በሰሜን እዝ ላይ የተፈፀመው ጭካኔ የተሞላበት ድርጊት ታሪክ መቼም የማይዘነጋው ክህደት ነው ብለዋል፡፡
መንግስት ይህንን አረመኔያዊ ድርጊት የፈፀሙ አካላትን ተከታትሎ ተገቢውን ህጋዊ እርምጃ ሊወስድባቸው ይገባል ሲሉም ሀሳባቸውን ገልጸዋል፡፡

Get the app => https://bit.ly/36Mjge5ሩስያ የኮሮና ቫይረስ ክትባት መስጠት ጀመረችአዲስ አበባ፣ ህዳር 27፣ 2013 (ኤፍቢሲ) ሩስያ በወረርሽኙ ከፍተኛ ተጋላጭነት ውስጥ...
06/12/2020

Get the app => https://bit.ly/36Mjge5
ሩስያ የኮሮና ቫይረስ ክትባት መስጠት ጀመረች
አዲስ አበባ፣ ህዳር 27፣ 2013 (ኤፍቢሲ) ሩስያ በወረርሽኙ ከፍተኛ ተጋላጭነት ውስጥ ለሚገኙ ዜጎቿ የኮሮና ቫይረስ ክትባት መስጠት ጀመረች፡፡
ክትባቱ እየተሰጠ የሚገኘው ለዚሁ ተብለው በተከፈቱ አዳዲስ ክሊኒኮች ነው ተብሏል፡፡
ይህ ስፑትኒክ ቪ የተሰኘው ክትባት በ70 ክሊኒኮች ነው በትናትናው ዕለት መሰጠት የተጀመረው፡፡
ይህንን ተከትሎም ሩስያ በሰፊው የኮሮና ቫይረስ ክትባትን በመስጠት የመጀመሪያዋ ሀገር ሆናለች፡፡
ክትባቱ በመጀመሪያ እየተሰጠ የሚገኘው ከፍተኛ ተጋላጭነት ላለባቸው ለህክምና ባለሙያዎች፣ ለመምህራን እና ለማህበራዊ አገልግሎት ሰጪዎች ነው ተብሏል፡፡
ክትባቱ በ21 ቀናት ልዩነት ለሁለት ያህል ጊዜ እንደሚሰጥ ነው መረጃ የሚያሳየው፡፡
ሆኖም ተመራማሪዎች በክትባቱ ስራ ላይ መዋል ስጋታቸውን የገለጹ ሲሆን የመጨረሻውን የቤተሙከራ ደረጃ እንዳላጠናቀቀም ተሰምቷል፡፡
እስካሁን በሩስያ ከ2 ነጥብ 4 ሚሊየን በላይ ሰዎች በወረርሽኙ የተያዙ ሲሆን 42 ሺህ 684ቱ ደግሞ ህይወታቸውን አጥተዋል፡፡

ትግራይን መልሶ የመገንባቱ ሥራ የድኅረ ዘመቻ ዋናው ተግባራችን ነው- ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድአዲስ አበባ ፣ ህዳር 26 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ትግራይን መልሶ የመገንባቱ ሥራ የድኅረ ዘመቻ ዋና...
05/12/2020

ትግራይን መልሶ የመገንባቱ ሥራ የድኅረ ዘመቻ ዋናው ተግባራችን ነው- ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ
አዲስ አበባ ፣ ህዳር 26 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ትግራይን መልሶ የመገንባቱ ሥራ የድኅረ ዘመቻ ዋናው ተግባራችን ነው አሉ ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ።
ይህ ተግባር ሦስት መልኮች አሉትም ብለዋል ዶክተር ዐቢይ።
ሰብአዊና ማኅበራዊ ድጋፍ፣ የተጎዳውን መሠረተ ልማት መልሶ መገንባት እና መሠረታዊ አገልግሎቶችን መልሶ ማስጀመር መሆናቸውንም ገልጸዋል።
እነዚህ ሥራዎች በስፍራው በተገኙ ቡድኖች አማካኝነት ተጀምረዋልም ነው ያሉት።
የሰብአዊ ድጋፍ አገልግሎትም እጅግ ተጋላጭ የሆኑትን የማኅበረሰብ ክፍሎች በመደገፍ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።
አንድ ሆነን የተቋረጠውን እናስቀጥላለን፣ የፈረሰውን እንገነባለን፣ የነገውንም እናለማለን ሲሉ በማህበራዊ ገጻቸው ገልጸዋል።

ምክትል ጠ/ሚና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ ከዴንማርክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጄፔ ኮፎድ ጋር ተወያዩአዲስ አበባ ፣ ህዳር 26 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ...
05/12/2020

ምክትል ጠ/ሚና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ ከዴንማርክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጄፔ ኮፎድ ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ ፣ ህዳር 26 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ከዴንማርክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጄፔ ኮፎድ ጋር ተወያዩ፡፡
በስልክ ባካሄዱት ውይይት አቶ ደመቀ መኮንን በትግራይ ክልል ስላለው የህግ ማስከበርና መልሶ ማቋቋም ስራ ላይ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡
የህግ ማስከበር ስራው መጠናቀቁን እና መንግስት በመልሶ ማቋቋም ስራ ላይ በትኩረት እየሰራ ስለመሆኑ አስረድተዋል፡፡
በመልሶ ማቋቋሙ ከህጋዊ የክልሉ መንግስት ጋር በምክክር እየተሰራ እንዳለ ገልፀል፡፡
በተጨማሪም ወንጀለኞችን በማደን ለህግ ለማቅረብ በትኩረት እየተሰራ ስለመሆኑ ተናግረዋል፡፡
ዓለም አማቀፍ የሰብዓዊ ድጋፍ ሰጪ ተቋማት ከፌደራል መንግስት ጋር በቅርበት እየሰሩ በመሆናቸውም አመስግነዋል፡፡
የዴንማርክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጄፔ ኮፎድ በበኩላቸው መንግስታቸው የኢትዮጵያ መንግስት መልሶ ማቋቋም እና ሰብዓዊ ድጋፍ ስራ ላይ የሚያካሂደውን ጥረት እንደሚደግፍ ገልፀዋል፡፡
ሀገራቸው ኢትዮጵያ በምታካሂደው ሀገር አቀፍ ምርጫ ለማገዝ ዝግጁ መሆኗን መናገራቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያሳያል፡፡

Get the app at => https://play.google.com/store/apps/details?id=com.chaosapps.zenaየወታደሯ የ3 ቀናት የመቃብር ውስጥ ቆይታ************...
05/12/2020

Get the app at => https://play.google.com/store/apps/details?id=com.chaosapps.zena
የወታደሯ የ3 ቀናት የመቃብር ውስጥ ቆይታ
******************
መ/ወ/ር ተስፋነሽ ጋቢሳ ትባላለች። የመከላከያ ሠራዊቱ ልዩ ኃይል አባል ናት፡፡ ጁንታው በከፈተው ውጊያ ለመፋለም በራያ ግንባር ከክፍሏ አባላት ጋር ተሰልፋ በርካታ ግዳጆችን በድል ተወጥታለች።
ጠላት ለዓመታት ያዋጋኛል ብሎ እንዳዘጋጀው በወታደራዊ ጠበብቶቹ በግንባሩ መሪ ሌ/ጄ ባጫ ደበሌ እና ሌሎች አመራሮች የተመሰከረለት ልዩ ቦታው አዲ ቀይህ የተባለው ቦታ ላይ ለ3 ቀናት በተደረገው ፍልሚያ በጀግንነት እየተዋጋች ሳለ ያልጠበቀችው ሁኔታ ገጠማት።
በዚህ ቦታ ላይ ጠላት ሙሉ ኃይሉን ተጠቅሞ መዋጋት በመጀመሩ እንደ ሌሎች ምሽጎች በቀላሉ መስበር ካለመቻሉም ባሻገር፣ ጠላትን ለመደምሰስ የገባውን የወገን ጦር ለመቁረጥ መልሶ ማጥቃት በማድረጉ ወገን የኃይል ሚዛኑን ለማመጣጠን እና ሌሎች ወታደራዊ ጥበቦችን ለመጠቀም ሲባል ከጠላት ከበባ ሰብረው እንዲወጡ ሲደረግ መ/ወ/ር ተስፋነሽ በጠላት ቀጣና ተቆርጣ ትቀራለች።
ወ/ር ተስፋነሽ ወገን አሸንፎ ሞሽጉን እንደሚሰብር ሙሉ እምነት ስለነበራት፣ የታጠቀችውን ስናይፐር ጨምሮ መሬቱን ቆፍራ ራሷን ጉድጓድ ውስጥ ትቀብራለች። አፈሩን በእጆቿ በላይዋ ላይ በመመለስ ከመሬቱ ጋር በሚገባ ትመሳሰላለች።
በዚህ ሁኔታ ላይ እያለች ብዙ የጁንታው ታጣቂዎች በላይዋ ላይ እየተረማመዱ ከወዲያ ወዲህ ይመላለሱባታል።
መማረክን ከሞት በላይ የምትፈራው እና ድሉን ሳታይ መሞት የማትፈልገው ጀግናዋ መ/ወ/ር ተስፋነሽ ያላት አማራጭ ሁሉንም ችላ ዝም ማለት ብቻ ነበር።
ነገር ግን ጁንታው ከአጠገቧ ላይ ዲሽቃውን ሲጠምደው፣ አንዱ የዲሽቃው መቋሚያ እግር ከተቀበረችበት አቅራቢያ ላይ አረፈ። ዲሽቃውም ቦታውን ሳይለቅ ከአቅራቢያዋ እየተኮሰ 3 ቀናት ተቆጠሩ።
በእነዚህ ቀናት ራሷን እንደ ሙት ያለ ምንም እንቅስቃሴ ትንፋሿን አምቃ ምድር ውስጥ ሳለች ከፍተኛ ውጊያ ከተካሄደ በኋላ ሠራዊቱ ምሽጉን ሰብሮ ድል ማድረጉን የዲሽቃው መቋሚያ እግርም እሷ ካለችበት ጉድጓድ አካባቢ መነሣቱን አወቀች፡፡
ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ ራሷን ከቀበረችበት በማስነሣት አካባቢውን ስትመለከት ጀግኖች ጓዶቿ ጁንታውን አባርረው ቦታውን ሙሉ በሙሉ ተቆጣጥረውታል።
እሷ ብታውቃቸውም እነሱ ግን ሙሉ ሰውነቷ ከአፈር ስለተመሳሰለ አላወቋትም ነበርና 'እጅ ወደ ላይ' የሚል ድምፅ ሰማች።
እሷም እጆቿን አንሥታ 'ወገን ነኝ ' የሚል ድምፅ በደስታ ብዛት ተውጣ አሰማች። እነሱም ወደ ኋላ በመውሰድ ከ3 ቀናት በኋላ እህል እና ውኃ እንድትቀምስ አድርገዋታል።
መ/ወ/ር ተስፋነሽ ጋቢሳ በአሁኑ ወቅት በሙሉ ጤንነት ወደ መደበኛ ተግባሯ ተመልሳ ጁንታውን ለደምሰስ እየተፋለመች ትገኛለች ሲል ከመከላከያ ሠራዊት የፌስ ቡክ ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

በትግራይ ክልል ከቀዬአቸው ሸሽተው የነበሩ ዜጎች መመለስ ጀመሩ**************************በትግራይ ክልል በተለያዩ አካባቢዎች ከቀዬአቸው ሸሽተው የነበሩ ዜጎች መመለስ መጀመራቸው...
01/12/2020

በትግራይ ክልል ከቀዬአቸው ሸሽተው የነበሩ ዜጎች መመለስ ጀመሩ
**************************
በትግራይ ክልል በተለያዩ አካባቢዎች ከቀዬአቸው ሸሽተው የነበሩ ዜጎች መመለስ መጀመራቸውን ነዋሪዎቹ ገልጸዋል።
ቤታቸውን ጥለው ሊሸሹ የቻሉት የትህነግ ታጣቂ ቡድን መከላከያ ሊያጠፋችሁ ነው የሚል የሀሰት ፕሮፓጋንዳ በመንዛቱ ነው ተብሏል።
ወ/ሮ ናፍታሃ ገ/ስላሴ በትግራይ ክልል፣ ህንጣሎ ዋጅራት ወረዳ፣ ጸሀፍት ቀበሌ ነዋሪ ሲሆኑ በቅርቡ ቤታቸውን ጥለው በመሸሽ ለአንድ ሳምንት ያህል በዱር መቆየታቸውን ይናገራሉ። አሁን ግን በአካባቢው የሀገር መከላከያ ሠራዊት ተሰማርቶ ሰላም በመስፈኑ ወደቀዬአቸው መመለስ ችለዋል።
በህንጣሎ ዋጅራት ወረዳ ከተማ በንግድ ስራ የሚተዳደሩት አቶ ካህሳይ ሰመሮም በተመሳሳይ ከአካባቢያቸው ሸሽተው በዱር በመቆየታቸው የተለያዩ ችግሮች እንደገጠሟቸው ገልጸው አሁን ግን በከተማዋ የእለት እለት እንቅስቃሴ መጀመሩን ተከትሎ ወደከተማዋ ተመልሰው የንግድ ስራቸውን መጀመራቸውን ተናግረዋል።
የጽንፈኛው ትህነግ ታጣቂዎች የሀገር መከላከያ ሠራዊት ሊያጠፋችሁ ነው ብለው ሀሰተኛ መረጃ ስለሰጡን ቤታችንን በመተው ወደ ዱር እንድንሰደድ ተገደን ነበር ያሉት ነዋሪዎቹ ስለ መከላከያ ሠራዊቱ የተነገረን ፈጽሞ ሀሰት መሆኑን በተግባር አረጋግጠናል ብለዋል።
አሁንም ከቀዬአቸው ርቀው ያሉ ሌሎች ዜጎች እንዲመለሱ ከሀገር መከላከያ ሠራዊት ጋር በመሆን እየሰሩ መሆናቸውን ነዋሪዎቹ ገልጸዋል።

አይቅርብኝ ያሉት እናት የዶሮ “ሰንጋ” ለመከላከያ ሠራዊቱ *********በኦሮሚያ ክልል በምስራቅ ወለጋ ዞን ሌቃ ዱላቻ ወረዳ ነዋሪዎች የመከላከያ ሠራዊቱ ህግ የማስከበር ተልዕኮውን በድል ማ...
01/12/2020

አይቅርብኝ ያሉት እናት የዶሮ “ሰንጋ” ለመከላከያ ሠራዊቱ
*********
በኦሮሚያ ክልል በምስራቅ ወለጋ ዞን ሌቃ ዱላቻ ወረዳ ነዋሪዎች የመከላከያ ሠራዊቱ ህግ የማስከበር ተልዕኮውን በድል ማጠናቀቅን ተከትሎ ያዋጡትን 23 ሰንጋ ይዘው ለሠራዊቱ ለማበርከት አደበባይ በተገኙበት ቦታ የአንዲት እናት ድርጊት የብዙዎችን እናቶች የሚወክል ድርጊት ፈፅመዋል፡፡
ይህች እናት ግን ለሠራዊቱ ያላቸውን አክብሮት የገለጹት ደግሞ በጓዳቸው ያሳደጉትን የዶሮ “ሰንጋ” ይዘው አደባባይ በመውጣት ነው፡፡
ከ23ቱ ሰንጋዎች በተጨማሪ የሳቸውም የዶሮ "ሰንጋ" 24ኛ ሆኖ በስጦታ መልክ የዱላቻ ወረዳ ለሠራዊቱ ማስረከቡን ከመከላከያ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
የምስራቅ ወለጋ ዞን ምክትል አስተዳዳሪ አቶ ደረጄ አበራ በስነ ስርዓቱ ላይ እንዳሉት ሠራዊታችን የተቃጣበትን ጥቃት እና ክህደት ቀልብሶ ድል ማድረጉ አስደሳች መሆኑን ገልጸው፣ የዱላቻ ወረዳን ጨምሮ በዞኑ የሚገኙ 4 ወረዳዎች ብቻ 83 ሰንጋ ድጋፍ ማድረጋቸውን ተናግረዋል፡፡

የሮቤ እና የጎባ ከተማ ነዋሪዎች የመከላከያ ሰራዊት የተቀዳጀውን አንፀባራቂ ድል  አስመልክቶ የተሰማቸውን ደስታ እየገለፁ ነውአዲስ አበባ ፣ ህዳር 20 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦሮሚያ ክል...
29/11/2020

የሮቤ እና የጎባ ከተማ ነዋሪዎች የመከላከያ ሰራዊት የተቀዳጀውን አንፀባራቂ ድል አስመልክቶ የተሰማቸውን ደስታ እየገለፁ ነው
አዲስ አበባ ፣ ህዳር 20 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦሮሚያ ክልል የሮቤ እና የጎባ ከተማ ነዋሪዎች በትናንትናው እለት የመከላከያ ሰራዊት የጁንታውን የመጨረሻ ምሽግ መቐለን መቆጣጠሩን ተከትሎ ደስታቸውን እየገለፁ ይገኛሉ፡፡

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ልዩ ስብሰባውን ነገ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በተገኙበት ያካሄዳል**********************የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ልዩ ስብሰባውን ጠቅላይ ሚኒ...
29/11/2020

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ልዩ ስብሰባውን ነገ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በተገኙበት ያካሄዳል
**********************
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ልዩ ስብሰባውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በተገኙበት በነገው ዕለት እንደሚያካሄድ አስታወቀ፡፡
ምክር ቤቱ 2ኛ ልዩ ስብሰባውን በጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት በሚገኘው መሰብሰቢያ አዳራሽ ከጠዋቱ 3:00 ጀምሮ ማካሄድ እንደሚጀምር ገልጿል፡፡
በስብሰባውም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በወቅታዊ አገራዊ ጉዳዮች ላይ ከምክር ቤት አባላት ለሚቀርቡላቸው ጥያቄዎች ምላሽ እንደሚሰጡም ይጠበቃል፡፡
የምክር ቤቱ 6ኛ አመት የስራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ስብሰባ ቃለ ጉባኤ መርምሮ ማጽደቅ የስብሰባው ሌላኛው አጀንዳ እንደሆነ ከሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

የወልቃይት፣ ጠገዴ እና ዳንሻ ከተማ ነዋሪዎች ከሃዲው የትህነግ ቡድን መደምሰሱን ተከትሎ ደስታቸውን እየገለፁ ነውአዲስ አበባ ፣ ህዳር 20 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የወልቃይት፣ ጠገዴ እና ዳ...
29/11/2020

የወልቃይት፣ ጠገዴ እና ዳንሻ ከተማ ነዋሪዎች ከሃዲው የትህነግ ቡድን መደምሰሱን ተከትሎ ደስታቸውን እየገለፁ ነው
አዲስ አበባ ፣ ህዳር 20 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የወልቃይት፣ ጠገዴ እና ዳንሻ ከተማ ነዋሪዎች ከሃዲው የትህነግ ቡድን መደምሰሱን ተከትሎ ደስታቸውን እየገለፁ ይገኛሉ፡፡
ነዋሪዎቹ ለጀግናው የመከላከያ ሰራዊት፣ ለአማራ ልዩ ኃይል እና ሚሊሻ የድጋፍ ሰልፍ እያካሄዱ ነው፡፡
በዚህ ወቅት የከተማው ነዋሪዎች አማራ በመሆናችን ብቻ ለ30 ዓመታት ሲደርስብን የነበረው ግፍ በማብቃቱ ነፃነታችንን በአደባባይ ለመግለፅ በቅተናል ብለዋል፡፡
ህዝቡ ለሰሜን እዝ አምስተኛ ሜካናይዝድ ክፍለ ጦር ያለውን ፍቅርም እየገለፀ እንደሚገኝ አብመድ ዘግቧል፡፡

የትግራይ ሕዝብ ከስግብግቡ ጁንታ ጋር እንዳልሆነ በተግባር አስመስክሯል- ጠ/ሚ ዐቢይ  አዲስ አበባ፣ ህዳር 19፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የትግራይ ሕዝብ ከስግብግቡ ጁንታ ጋር እንዳልሆነ በተግ...
28/11/2020

የትግራይ ሕዝብ ከስግብግቡ ጁንታ ጋር እንዳልሆነ በተግባር አስመስክሯል- ጠ/ሚ ዐቢይ
አዲስ አበባ፣ ህዳር 19፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የትግራይ ሕዝብ ከስግብግቡ ጁንታ ጋር እንዳልሆነ በተግባር ማስመስከሩን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ገለፁ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በፌስቡክ ገፃቸው ባስተላለፉት መልእክት፥ የመከላከያ ሠራዊት በድል በገሠገሠባቸው የትግራይ አካባቢዎች ሁሉ የትግራይ ሕዝብ ለሀገሩ ያለውን ፍቅርና ለመከላከያ ሠራዊቱ ያለውን ክብር አሳይቷል ብለዋል።
ጁንታው ካስታጠቃቸው ጥቂት የክፋት ኃይሎች ውጭ ያለው የትግራይ ሕዝብ መቀሌ እስኪገባ ድረስ ለመከላከያ ሠራዊቱ የሚጠበቅበትን ድጋፍ ሁሉ አድርጓል፤ ይህም የሠራዊቱን ድልና የጁንታውን ሽንፈት አፋጥኖታል ሲሉም ገልፀዋል።
ስግብግቡ ጁንታ በየትኛውም መመዘኛ ለትግራይ ሕዝብ አይመጥነውም፤ የትግራይ ሕዝብ ከእውነት ጋር በመቆምና የጁንታውን እኩይ ዓላማ በመፃረር ከቀበሌ ቀበሌ፣ ከዞን ዞን መቀሌ እስኪገባ ድረስ ተመሳሳይ ድጋፍ ለሠራዊቱ ሰጥቷል።
“ለዚህም ከፍ ያለ ምስጋናዬን አቀርባለሁ” ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ፥ ጁንታው በሸሸበት ከተማና አካባቢ ሁሉ የጤና ተቋማትን፣ ትምህርት ቤቶችን፣ ድልድዮችን፣ መንገዶችን፣ መሥሪያ ቤቶችን እያወደመ ሄዷል፤ በዚህም የገዛ ወገኑ ጠላት መሆኑን አሳይቷል ብለዋል።
“ጁንታው እኔ ከሞትኩ ብሎ ያፈረሳቸውን መሠረተ ልማቶች በፍጥነት በመገንባት የትግራይ ሕዝብ ወደ ሰላማዊ ኑሮው እንዲመለስ ለማድረግ የቻልነውን ሁሉ እንደምናደርግ ቃል እገባለሁ” ሲሉም ገልፀዋል።
“በዚህ ዘመቻችን ንጹሐን ዜጎች ዒላማ ሳይሆኑ፣ ከተሞቻችንና ቅርሶቻችን ሳይጎዱ መቀሌ ለመግባት ተችሏል” ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ።

የአገር ክህደት ወንጀል በፈፀሙ ወታደራዊ ሹማምንትና በሚዲያዎች ሀገር አፍራሽ መረጃ በሚያሰራጩ ግለሰቦች ላይ የመያዣ ትዕዘዝ ወጣአዲስ አበባ፣ ህዳር 19፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ)  የአገር ክህ...
28/11/2020

የአገር ክህደት ወንጀል በፈፀሙ ወታደራዊ ሹማምንትና በሚዲያዎች ሀገር አፍራሽ መረጃ በሚያሰራጩ ግለሰቦች ላይ የመያዣ ትዕዘዝ ወጣ
አዲስ አበባ፣ ህዳር 19፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአገር ክህደት ወንጀል በፈፀሙና በተለያዩ እርከን በሚገኙ ወታደራዊ ሹማምን ትበፈፀሙት የዘረፋ ወንጀል ንብረታቸው የሚፈለግ የጁንታው ህወሃት ቡድን አባላትና በአሃገር ውስጥና ባህርማ ዶሆነው የተለያዩ ሚዲያዎችን በመጠቀም አገር አፍራሽ መረጃ በሚያሰራጩ ግለሰቦች ላይ የመያዣ ትዕዘዝ መውጣቱ ተገለፀ።
የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በላከው በመግለጫ፥ ቀደም ሲል በፈፀሙት የአገርክህደት ወንጀል የመያዣ ትዕዛዝ ከወጣባቸው 117 ጄኔራል መኮንኖች፣ ከፍተኛ መኮንኖችና የበታች ሹማምንቶች በተጨማሪ ስማቸው ቀጥሎ የተገለፀው 7 በተለያየ የእርከን ላይ የሚገኙ ወታደራዊ ሹማምንት ላይ የመያዣ ትዕዛዝ እንዲወጣ ተደርጓል።
በዚህምመሠረት፡-
1. ሜጀር ጄነራል ዘውዱ ኪሮስ ገብረኪዳን
2. ኮሎኔል ተወልደ ገብረትንሣይ
3. ኮሎኔልገብረእግዚአብሔር ዓለምሰገድ
4. ኮሎኔል የማነ ገብረሚካኤል
5. ሻምበል ተወልደ ገብረመድህን
6. ኰሎኔል ጌትነት ግደያ
7. ኮሚሽነር ረታ ተስፋዬ ናቸው።
በተያያዘም ቀደም ሲል የነበራቸው ወታደራዊ ኃላፊነት እና ከጁንታው የህወሃት ቡድን ጋር ያላቸውን ጥብቅ ትስስር ተጠቅመው ከፍተኛ የዘረፋ ወንጀል በመንግሥት ላይ በመፈፀም ከፍተኛ ንብረት ማካበታቸው የተደረሰባቸው 20 ግለሰቦች ስማው ቀጥሎ ተገልጿል።
በዚህም መሰረት፦
1. ሌተናል ጄነራል ታደሰ ወረደ- ሥልጠና ዋና መምሪያ ጡረተኛ
2. ሜጀር ጄነራል ገብረገአድሃና ገብረዲላ- መረጃ ዋና መምሪያ ጡረተኛ
3. ሜጀር ጄነራል ተክለበርሃን ወልደአረጋይ /ሳንቲም/ - የኢንሳዳይሬክተር ጡረተኛ
4. ሜጀር ጄነራል ብርሃነ ነጋሽ /ወዲመድን/ - ሚንስትር ዴኤታ ጡረተኛ
5. ሜጀር ጄነራል ማዕሾ በየነ- ምሥራቅ ዕዝ አዛዥ ጡረተኛ
6. ሜጀር ጄነራል ኢብራሂም አብዱልጀሊል- ሎጀስቲክ ዋና መምሪያ ጡረተኛ
7. ሜጀር ጄነራል ዮሃንስ ወልደጊዮርጊስ - ማዕከላዊ ዕዝአዛዥ የነበረ ጡረተኛ
8. ሜጀር ጄነራል ነጋሲትዕኩ- በሰላም ማስከበር ግዳጅ የከዳ
9. ብርጋዴር ጄነራል አባዲፍላንሳ- ምስራቅ ዕዝ መረጃኃላፊ ጡረተኛ
10. ብርጋዴር ጄነራል ፀጋየ ተሰማ /ፓትሪስ/- ኢንስፔክሽን ዋና መምሪያ የነበረ ጡረተኛ
11 ብርጋዴር ጄነራል ምግበ ኃይለ- ሥልጠና ዋናመምሪያ ጡረተኛ
12. ብርጋዴር ጄነራል ተክላይ አሸብር /ወዲአሸብር/- የንዑስ ዕዝ አዛዥ የነበረ ጡረተኛ
13. ብርጋዴር ጄነራል ኃይለሥላሴግርማይ /ወዲዕበይተ/- ዘመቻ ዋና መምሪያ ጡረተኛ
14. ብርጋዴር ጄነራል ሙሉጌታ በርሔ- የአጋዚ ክፍለ ጦአዛዥ የነበረ ጡረተኛ
15. ኮሎኔል ተወልደ ገብረተንሳይ- መከላከያ መረጃ ጡረተኛ
16. ኮሎኔል ገብረእግዚአብሔር ዓለምሰገድ - መከላከያ መረጃ የነበረ ጡረተኛ
17. ኮሎኔል ደጀን ግርማይ- የዕዝ ስምሪት ኃላፊ ጡረተኛ
18. ኮሎኔል የማነ ገብረሚካኤል- የአጋዚ ክፍለ ጦር አዛዥ ጡረተኛ
19 ኮሎኔል ገብረሀንስ አባተ /ወዲአባተ/- ምዕራብ ዕዝ 43ኛ ክፍለ ጦር አዛዥ ጡረተኛ
20 ሻምበል ተወልደ ገብረመድህን /ወዲአድዋ/- ድሬዳዋ ያለ ቀደም ብሎ የወጣ
ከሕዝብ የዘረፉትን ንብረቶች ማስመለስ ይቻል ዘንድ ንብረቶቹ የሚገኙበትን ትክክለኛ አድራሻ በፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ወንጀል መከላከል ቢሮ ስልክ ቁጥሮች፥ 011 1 55 12 00 ወይም የነፃ የጥሪ መስመር 861 ወይም በአካል ወንጀል ምርመራ ቢሮ በመገኘት እንድታሳውቁን የተለመደ ትብብራችሁን እንጠይቃለን ብሏል የፌደራል በመግለጫው።
እንዲሁም በአገር ውስጥና በውጪ አገር ተቀምጠው የተለያዩ የሚዲያ አውታሮችን በመጠቀም አገር በማፍረስ ተግባር ላይ የተሰማሩ፦
1. ዶክተር እዝቅኤል ገቢሳ
2. ዶክተር አወልአሎ ቃሲም
3. ዶክተር ኢታና ሀብቴ
4. ዶክተር ፀጋዬ አራርሳ
5. አቶ ዳንኤል ብርሃኔ
6. አቶ ፍፁም ብርሃኔ
7. አቶ አሉላ ሰለሞን
8. ሠናይት መብርሃቱ በፈፀሙት የአገር ማፍረስ ወንጀል በሕግ የሚፈለጉ መሆኑን የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን በመግለጫው አስታውቋል።

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አፈጻጸም መርማሪ ቦርድ የመጀመሪያውን ዙር የመስክ ምልከታ በማካሄድ ላይ ነው****************ሕገ-መንግስቱንና ሕገ-መንግስታዊ ሥርዓቱን ከአደጋ ለመከላከል ሲባል...
28/11/2020

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አፈጻጸም መርማሪ ቦርድ የመጀመሪያውን ዙር የመስክ ምልከታ በማካሄድ ላይ ነው
****************
ሕገ-መንግስቱንና ሕገ-መንግስታዊ ሥርዓቱን ከአደጋ ለመከላከል ሲባል በቅርቡ የጸደቀው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አፈጻጸም መርማሪ ቦርድ የመጀመሪያውን ዙር የመስክ ምልከታ በማካሄድ ላይ መሆኑን የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አስታውቋል።
ቦርዱ ህዳር 14 ቀን 2013 ዓ.ም የጀመረው የመስክ ምልከታ እስካሁን በባህርዳር፣ በጎንደርና በዳንሻ አከባቢዎች ተዘዋውሮ የምርመራ ስራውን አከናውኗል።
በከሃዲው የሕውሓት ቡድን ጥቃት የደረሰባቸውን የባህርዳር እና የጎንደር አየር መንገዶችን በመመልከት ነው መርማሪ ቦርዱ ስራውን የጀመረው።
የመርማሪ ቦርዱ አባላት በሲቪል አየር ማረፍያ የተደረገው የጥቃት ሙከራ ኢሰብዓዊ መሆኑን ገልጸው፤ ምናልባት ተመሳሳይ ጥቃት ሊፈጸም ስለሚችል ጥንቃቄ እንደሚያስፈልግ ለሁለቱም አየር መንገድ የስራ ኃላፊዎች ምክረ ሃሳብ አቅርበዋል።
የመርማሪ ቦርዱ አባላት የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ሆስፒታልን በጎበኙበት ወቅት በከሃዲው የሕውሓት ቡድን አስገዳጅነት በተሰማሩበት ግጭት የተጎዱ ታካሚዎችን ተመልክተዋል።
አባላቱ በሆስፒታሉ የህክምና እርዳታ ሲደረግላቸው የነበሩ የትግራይ ልዩ ሃይልና ሚሊሻ አባላትን ባነጋገሩበት ወቅት ታካሚዎቹ ተገቢ የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው መሆኑን አስረድተዋል።
የኢትዮጵያ መንግስት እያካሄደ ባለው ህግ የማስከበር ዘመቻ እጃቸውን ለመከላከያ ሠራዊት የሰጡት እንዲሁም ቆስለው የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው የሚገኙት የሕውሓት ልዩ ኃይልና ሚሊሻ አባላት እንደሚሉት ቀደም ሲል በሕወሓት አመራሮች ከተነገራቸው ማስፈራሪያ በእጅጉ የሚቃረን እርዳታና እንክብካቤ እየተደረገላቸው መሆኑን ለመርማሪ ቦርዱ አባላት ገልጸዋል።
የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ሆስፒታል ሜዲካል ዳይሬክተር ዶ/ር አሸናፊ ታዘብ እና የዞኑ ጤና ቢሮ ኃላፊ አቶ ገብያው አሻግሬ ለመርማሪ ቦርዱ አባላት በነበረው የህግ ማስከበር ተጎድተው የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው የሚገኙትን ወገኖች ባስጎበኙበት ወቅት ሆስፒታሉ ባለው አቅም በግጭቱ የተጎዱ ታካሚዎች ላይ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን ጠቁመዋል።
አያይዘውም ሆስፒታሉ የህክምና ቁሳቁስና የበጀት እጥረት ያለበት መሆኑን ለሚመለከታቸው የበላይ አካላት በመግለጽ ምላሽ እየተጠባበቁ መሆኑን ለመርማሪ ቦርዱ አስረድተዋል።
የመርማሪ ቦርዱ አባላት በበኩላቸው በሆስፒታሉ ለታካሚዎቹ እየተደረገ ያለው የህክምና እርዳታ በጣም ጥሩ መሆኑን ገልጸው፤ ባጠቃላይ የሆስፒታሉን ባለሙያዎችና ሰራተኞች ከመደበኛ ስራቸው በላይ ድጋፍ እያደረጉ በመሆኑ፤ እንዲሁም የጎንደር ከተማ ወጣቶችና ባለሀብቶች ደግሞ ሀገራዊ በሆነ ስሜት ድጋፍ እየሰጡ በመሆኑ አመስግነዋል።
በቀጣይም የሆስፒታሉን አቅም ለመገንባትና ለገጠመው የበጀትና የህክምና ቁሳቁስ ጉድለት መፍትሄ ለማፈላለግ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመነጋገር እንደሚሰሩ የመርማሪ ቦርዱ ሰብሳቢ የተከበሩ አቶ ለማ ተሰማ ጠቁመዋል።
መርማሪ ቦርዱ ወደ ዳንሻ ባመራበት ወቅት በጽንፈኛው ቡድን የመጀመሪያው የጥቃት ሰለባ የሆነውን የሰሜን እዝ 5ኛ ሜካናይዝድ ክፍለ ጦር ጎብኝቷል።
ከብርጋዴር ጄነራል ሙሉአለም ጋር በመገናኘታቸው ክብር እንደሚሰማቸው የገለጹት የመርማሪ ቦርዱ አባላት በጥቃቱ ክፉኛ ማዘናቸውን ገልጸው፤ ለህይወታቸው ሳይሳሱ በከፍተኛ የሀገር ፍቅር ስሜትና ተጋድሎ ሀገራችንን ከመበታተን አደጋ በማዳናቸው ጀነራሉንና የክፍለ ጦሩን አባላት በጠቅላላ አመስግነዋል።
የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ መርማሪ ቦርድ የመስክ ምልከታውን የቀጠለ ሲሆን፤ በቀጣዮቹ ቀናት ወደሌሎች አከባቢዎች ተንቀሳቅሶ መረጃዎቹን እንደሚሰበስብ ይጠበቃል።
የቪዲዮ መረጃዎቻችንን ለማግኘት ትክክለኛውን የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ

በመተከል የሕግ የበላይነትን ለማስፈን እየተወሰደ ያለው እርምጃ ተጠናክሮ መቀጠሉን የዞኑ ኮማንድ ፖስት አስታወቀ****************በመተከል ዞን በተደጋጋሚ የሚስተዋለውን የሰዎች ግድያ ...
27/11/2020

በመተከል የሕግ የበላይነትን ለማስፈን እየተወሰደ ያለው እርምጃ ተጠናክሮ መቀጠሉን የዞኑ ኮማንድ ፖስት አስታወቀ
****************
በመተከል ዞን በተደጋጋሚ የሚስተዋለውን የሰዎች ግድያ ለማስቆም እየተወሰደ ያለው ሕግን የማስከበር እርምጃ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የመተከል ዞን ኮማንድ ፖስት ሰብሳቢ ኮሎኔል አያሌው በየነ ገልጸዋል።
በመቐለ የመሸገውን ጁንታ ተልዕኮ በማስፈጸም በዞኑ ውስጥ ዜጎችን በመግደል፣ በማፈናቀልና ንብረት በማውደም የተሰማሩ ቡድኖችን ለማጽዳትም እርምጃው ይቀጥላል ብለዋል ኮሎኔል አያሌው።
ቀጠናው የአጎራባች ሀገሮች አዋሳኝ መሆኑ እና ጸረ ሰላም ኃይሎችን ከህብረተሰቡ ነጥሎ ለማውጣት የአንዳንድ አመራሮች ቁርጠኝነት ማነስ ሁከቱን በአጭር ጊዜ ለማረጋጋት አዳጋች እንዳደረገው ተናግረዋል።
በቀጠናው የሚንቀሳቀሱ ጸረ ሰላም ኃይሎችን ለመደምሰስ የሀገር መከላከያ ሰራዊት፣ የፌደራል ፖሊስና የክልሉ ልዩ ኃይል በቅንጅት የኦፕሬሽን ስራዎችን እያከናወኑ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡
ህብረተሰቡ አጥፊዎችን አጋልጦ እንዲሰጥ የፖለቲካ አመራሩ እየሰራ እንደሚገኝ የጠቆሙት ኃላፊው እነዚህን አካላት ወደ ሕግ በማቅረብ የሕግ የበላይነትን ለማረጋገጥ እየተሰራ እንደሆነ አክለው ገልጸዋል።
ባለፉት ሁለት ቀናት ሕግን ለማስከበር በተደረገው የተቀናጀ ኦፕሬሽን በማንዱራ 17፣ በዳንጉር 4 እና በጉባ 2 በአጠቃላይ 23 ጸረ ሰላም ኃይሎች መደምሰሳቸውን ከመተከል ዞን ኮሙኒኬሽን መምሪያ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

"የመከላከያ ሠራዊት እንዲፈፅም በተሰጠው የመጨረሻው ምዕራፍ ዘመቻ ለንፁሃን ሰዎች ከፍተኛ ጥንቃቄ ይደረጋል፡፡ በሕዝብ ላብ የተሠራችው የመቐለ ከተማ የከፋ ጉዳት እንዳያገኛት እንዲሁም ቅርሶች...
27/11/2020

"የመከላከያ ሠራዊት እንዲፈፅም በተሰጠው የመጨረሻው ምዕራፍ ዘመቻ ለንፁሃን ሰዎች ከፍተኛ ጥንቃቄ ይደረጋል፡፡ በሕዝብ ላብ የተሠራችው የመቐለ ከተማ የከፋ ጉዳት እንዳያገኛት እንዲሁም ቅርሶች፣ ቤተ-እምነቶች፣ የሕዝብ መገልገያዎች፣ የልማት ተቋማት እና የሕዝብ መኖሪያዎች የጥቃት ዒላማ እንዳይሆኑ ሁሉም ዓይነት ጥንቃቄ ይደረጋል።"
ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አህመድ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሁለት A-350 ኤርባስ አዳዲስ አውሮፕላኖች ተረከበ**************የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአፍሪካ እና በተቀረው ዓለም በአቪየሺን ቴክኖሎጂ ያለውን ቀዳሚነት...
07/11/2020

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሁለት A-350 ኤርባስ አዳዲስ አውሮፕላኖች ተረከበ
**************
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአፍሪካ እና በተቀረው ዓለም በአቪየሺን ቴክኖሎጂ ያለውን ቀዳሚነት የሚያስቀጥሉ የኤርባስ ኩባንያ ምርት የሆኑ ሁለት አዳዲስ A-350 አውሮፕላኖች መረከቡን አስታውቋል።

በኢትዮጵያ ካርጎ እና ሎጂስቲክስ አገልግሎቶች ክፍል ዛሬ በተከናወነው ርክክብ ሥነ ሥርዓት ላይ አውሮፕላኖቹ ጤና ሚኒስቴር ለሚከውናቸው ሰብአዊ ድጋፍ የሚውሉ የሕክምና መሣሪያዎች ይዘው መምጣታቸውን የኢትዮጵያ አየር መንገድ ገልጿል።

በሀገሪቱ ያለውን ወቅታዊ ሁኔታ ምክንያት በማድረግ በመሰረታዊ የፍጆታ ዕቃዎች ላይ የዋጋ ጭማሪ ማድረግ በሕግ እንደሚያስቀጣ የንድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አስታወቀ************* በሀገሪቱ...
06/11/2020

በሀገሪቱ ያለውን ወቅታዊ ሁኔታ ምክንያት በማድረግ በመሰረታዊ የፍጆታ ዕቃዎች ላይ የዋጋ ጭማሪ ማድረግ በሕግ እንደሚያስቀጣ የንድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አስታወቀ
*************

በሀገሪቱ ያለውን ወቅታዊ ሁኔታ ምክንያት በማድረግ በመሰረታዊ የፍጆታ ዕቃዎች ላይ የዋጋ ጭማሪ ማድረግ በሕግ እንደሚያስቀጣ የንድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አስታውቋል።

ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ዛሬ በሰጠው መግለጫ በመሰረታዊ የፍጆታ ዕቃዎች ላይ የዋጋ ጭማሪ እንዳይደረግ እየሰራ መሆኑንም አስታውቋል።

በዚህ ወቅት ሊፈጠር በሚችሉ ስጋቶች ምክንያት ባለፈው ዓመት የተመዘገበው ከፍተኛ የወጭ ንግድ ስኬትም እንዳይቀንስ ከላኪዎች ጋር በቅንጅት እንደሚሰራ ተገልጿል።

የነዳጅ ግብይቱ ላይም ችግር እንዳይፈጠር እየሰራ መሆኑን የገለጹት የንግድና ኢንዳስትሪ ሚኒስቴር የኮመኒኬሽን ዳይሬክተሩ አቶ ወንድሙ ፍላቴ በአዲስ አበባ የነዳጅ ማደያዎች ከጧቱ 12፡00 ሰዓት አስከ ምሽት 2፡00 ሰዓት ብቻ አገልግሎት መስጠት የሚችሉ ሲሆን በክልሎች ደግሞ ከጧቱ 12፡00 ሰዓት እስከ ምሽት 1፡0 ሰዓት ብቻ አገልግሎት መስጠት የሚችሉ ይሆናል ብለዋል።

ምርትን ያለአግባብ የሚያከማቹ ነጋዴዎችንና ሸማቾችን ለመከላከል በኮሮናው ወቅት የተዘረጋ አሰራር ስላለ በዚያው ግብረ ኃይል ቁጥጥር እንደሚደረግም አቶ ወንድሙ ፍላቴ ገልጸዋል።

በሀገር መከላከያ ሰራዊት ላይ ህወሃት ውስጥ ያለ ቡድን የከፈተውን ዘመቻ ለመመከት በተከፈተው ጦርነት ንጹሃን ዜጎች እንዳይጎዱ ከፍተኛ ጥንቃቄ ተደርጓል- የሃገር መከላከያ ሰራዊት  አዲስ አበ...
05/11/2020

በሀገር መከላከያ ሰራዊት ላይ ህወሃት ውስጥ ያለ ቡድን የከፈተውን ዘመቻ ለመመከት በተከፈተው ጦርነት ንጹሃን ዜጎች እንዳይጎዱ ከፍተኛ ጥንቃቄ ተደርጓል- የሃገር መከላከያ ሰራዊት

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 26፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በሀገር መከላከያ ሰራዊት ላይ ህወሃት ውስጥ ያለ ቡድን የከፈተውን ዘመቻ ለመመከት በተከፈተው ጦርነት ንጹሃን ዜጎች እንዳይጎዱ ከፍተኛ ጥንቃቄ መደረጉን የኢፌዴሪ ሃገር መከላከያ ሰራዊት አስታወቀ።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት ምክትል ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጀኔራል ብርሃኑ ጁላ ዛሬ በጉዳዩ ላይ መግለጫ ሰጥተዋል።

በመግለጫቸውም፥ ህገ መንግስታዊ ስርዓቱን ለመጠበቅ እና ሀገርን ከውጭ ወራሪ ለመከላከል በተቀመጠው የሃገር መከላከያ ሰራዊት ላይ የተከፈተው ጥቃት የሃገር ክህደት መሆኑን ገልጸዋል፡፡

የትኛውም አይነት የፖለቲካ ልዩነት በፖለቲካዊ መንገድ ሊፈታ ሲገባ የሰሜን እዝ በራሱ ወገን ጥቃት ተከፍቶበታል ብለዋል።

መከላከያ ሰራዊቱ ጥቃቱ ከተፈጸመ በኋላ በተሟላ ብቃት እየመከተ መሆኑን በመግለፅም የተከፈተው ጦርነት በአጭር ጊዜ ውስጥ እንደሚቋጭም አስታውቀዋል።

በሰሜን ያለውን ሰራዊት ለማገዝ ከተለያየ የሀገሪቱ አቅጣጫ የሃገር መከላከያ ሰራዊት እየተንቀሳቀሰ መሆኑንም አስረድተዋል።

ጦርነቱን በመቋጨት ሰላምን ለማስፈን በሚደረገው ሂደት የትግራይ ክልል ህዝብ ከሃገር መከላከያ ሰራዊት ጋር መሆኑን በተግባር አሷይቷልም ነው ያሉት።

ተገዶ ወደ ጦርነት የገባው ልዩ ሃይልም በግልጽ ተቃውሞውን መግለጹን ያነሱት ጀኔራል ብርሃኑ ጁላ፥ የሀገር መከላከያ ሰራዊት በጦርነቱ የቆሰሉ የትግራይ ልዩ ሃይል አባላትን ለህክምና እያመጣ መሆኑንም አውስተዋል።

በህወሃት ውስጥ ያለው ቡድን ግን ለህዝቡ ደንታ እንደሌለው በከፈተው ጦርነት አረጋግጧል ብለዋል በመግለጫቸው።

አርሶ አደሩ ምርት በሚሰበስብበት ወቅት የተከፈተው ጦርነት የአርሶ አደሩ ልፋት በጥይት እንዲቃጠል የጥፋት ሃይሉ ሆን ብሎ ያቀነባበረው ጥቃት ነውም ብለዋል።

ይህ ቡድን ትግራይን የጦር ቀጠና ሌሎች የሃገሪቱን አካባቢዎች ደግሞ የሽብር ግንባር ለማድረግ ቆርጦ በመነሳቱ ሁሉም ዜጋ ከመከላከያ ሰራዊቱ ጎን እንዲቆም ጠይቀዋል።

በአላዛር ታደለ

በትግራይ ክልል የሲቪል ሰዎችን ደኅንነት እና የሰብዓዊ እርዳታ አገልግሎት አቅርቦት ማረጋገጥ ያስፈልጋል- ኢሰመኮአዲስ አበባ፣ ጥቅምት 26፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በትግራይ ክልል የሲቪል ሰዎ...
05/11/2020

በትግራይ ክልል የሲቪል ሰዎችን ደኅንነት እና የሰብዓዊ እርዳታ አገልግሎት አቅርቦት ማረጋገጥ ያስፈልጋል- ኢሰመኮ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 26፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በትግራይ ክልል የሲቪል ሰዎችን ደኅንነት እና የሰብዓዊ እርዳታ አገልግሎት አቅርቦት ማረጋገጥ እንደሚያስፈልግ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) አስታወቀ።

ኮሚሽኑ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በላከው መግለጫ፥ በፍጥነት እየተባባሰ የቆየውን የትግራይ ክልል የፀጥታ ሁኔታ የሚያሳስበው መሆኑንና ክስተቱን በቅርበት እየተከታተለው እንደሚገኝ አስታውቋል።

የኮሚሽኑ ዋና ኮሚሽነር ዶክተር ዳንኤል በቀለ፥ ለፌዴራል እና ለክልሉ የፀጥታ ኃይሎች የሲቪል ሰዎችን ደኅንነት እና የሰብዓዊ መብቶችን በማንኛውም ሁኔታ ውስጥ እንዲጠብቁና እንዲያከብሩም ጥሪ አቅርበዋል።

ዋና ኮሚሽነሩ አክለውም፥ በተለይ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በትግራይ ክልል ተፈጻሚ እንዲሆን የቀረበውን የአስቸኳይ ጊዜ ሁኔታ ረቂቅ አዋጅ መጽደቅ ላይ ለመምከር በሚሰበሰብበት በዛሬው እለት፣ ምግብና መድኃኒት የመሳሰሉ የሰብዓዊ እርዳታ አቅርቦቶችን ማረጋገጥ እንደሚያስፈልግ ገልፀዋል።

እንዲሁም የግንኙነትና የትራንስፖርት አገልግሎቶችን ሙሉ በሙሉ እንዳይቋረጥ ጥንቃቄ እንዲደረግ በማሳሰብ፥ የትግራይ ክልል በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ስደተኞች እንደሚያስጠልልም አስታውሰዋል።

Get the app at :> https://play.google.com/store/apps/details?id=com.chaosapps.zenaበሶሮቃ እና ቅርቃር በተደረገ  ውጊያ በርካታ ያለፍላጎቱ እን...
05/11/2020

Get the app at :> https://play.google.com/store/apps/details?id=com.chaosapps.zena
በሶሮቃ እና ቅርቃር በተደረገ ውጊያ በርካታ ያለፍላጎቱ እንዲዋጋ የተገደደ የፀጥታ ኃይል በሰላም እጁን መስጠቱን የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ገለፁ
*******************
በአማራ ክልል አዋሳ በሆኑት በሶሮቃ እና ቅርቃር በተደረገ ውጊያ በርካታ ያለፍላጎቱ እንዲዋጋ የተገደደ የፀጥታ ኃይል በሰላም እጁን መስጠቱን የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ገለፁ፡፡

ርዕሰ መስተዳድሩ የክልሉ ልዩ ኃይል፣ ሚሊሻ እና የመከላከያ ሰራዊት በየደረጃው ያሉ ዓመራሮች እና አባላት በተቀናጀ መልኩ ያደረጉት ተጋድሎ ስኬታማ ነበር ብለዋል::

በተለይም በትናንትናው ዕለት በሶሮቃ እና ቅራቅር ከዕኩለ ሌሊት እስከ ረፋድ ተደጋጋሚ ማጥቃት ተሰንዝሮብን ነበር ያሉት አቶ ተመስገን፣ ከረፋድ በኋላ በተደረገ ማጥቃት በርካታ ቦታዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ተናግረዋል::

“በተቆጣጠርናቸው ቦታዎች ያለው የህዝብ ድጋፍ ድንቅ ነበር:: በርካታ ያለፍላጎቱ እንዲዋጋ የተገደደ የፀጥታ ኃይል በሰላም እጁን ሰጥቷል: “ብለዋል፡፡

ርዕሰ መስተዳድሩ አቶ ተመስገን አክለውም“ እዋጋለሁ ብሎ የመረጠም ፊቱን አዙሮ እኛን ሲያግዝ ውሏል:: ጦርነት አንፈልግም ስንል ጠላታችን ድህነት ነው ከሚል እንጅ ጦርነት ካለማወቅ አይደለም:: ዛሬም በሌላ ድል ታጅቦ ያልፋል”ብለዋል፡፡

ሰበር! "ገዳ ዮቹ ራሳቸው ናቸው" አማራ ክልል እነታውን አፈረጠው! የታፈኑት ኦቦ ዳውድ ምን አሉ? Dawuid Ibsa | Amhara | Ethiopia
14/10/2020

ሰበር! "ገዳ ዮቹ ራሳቸው ናቸው" አማራ ክልል እነታውን አፈረጠው! የታፈኑት ኦቦ ዳውድ ምን አሉ? Dawuid Ibsa | Amhara | Ethiopia

ሰበር! "ገዳ ዮቹ ራሳቸው ናቸው" አማራ ክልል እነታውን አፈረጠው! የታፈኑት ኦቦ ዳውድ ምን አሉ? Dawuid Ibsa | Amhara | Ethiopia The best destination for...

ኢትዮጵያ እና የዓለም ባንክ የ400 ሚሊየን ዶላር የድጋፍ ስምምነት ተፈራረሙ! ስምምነቱን የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሽዴ እና በኢትዮጵያ፣ ኤርትራ፣ ደቡብ ሱዳን እና ሱዳን የዓለም ባንክ...
14/10/2020

ኢትዮጵያ እና የዓለም ባንክ የ400 ሚሊየን ዶላር የድጋፍ ስምምነት ተፈራረሙ!

ስምምነቱን የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሽዴ እና በኢትዮጵያ፣ ኤርትራ፣ ደቡብ ሱዳን እና ሱዳን የዓለም ባንክ ዳይሬክተር ኦስማን ዲዮን ተፈራርመውታል፡፡ ድጋፉ በመላ ሃገሪቱ በሚገኙ 83 ከተሞች ለከተማ ሴፍቲኔት እና ለወጣቶች የስራ እድል ፈጠራ ይውላል ተብሏል፡፡

በከተሞች በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ ነዋሪዎችን ህይዎት ለማሻሻል የሚውል ሲሆን 816 ሺህ ሰዎችም ተጠቃሚ ይሆናሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

Via FBC

Ethiopia: 3 መረጃዎች - የኢሳያስ ጉብኝት ትሩፋቱ ምንድነው? | በባሌ ሮቤ የተገደለው ወጣት እንዴት? በገርበ ጉራቻ ጥቃት ያደረሰው ማን ነው?
14/10/2020

Ethiopia: 3 መረጃዎች - የኢሳያስ ጉብኝት ትሩፋቱ ምንድነው? | በባሌ ሮቤ የተገደለው ወጣት እንዴት? በገርበ ጉራቻ ጥቃት ያደረሰው ማን ነው?

Zehabesha News - Isaias Afwerki | Dr Abiy Ahmed | We’re here for one reason to provide fair and unbiased information to the community and is committed to sep...

ባለፈው ሳምንት ኢትዮጵያን የጎበኙ ሁለት የአውሮፓ ህብረት ከፍተኛ ባለሥልጣናት በኮሮና ስጋት ራሳቸውን አገለሉ!ባለፈው ሳምንት ከፕሬዝዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ እና ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አህመ...
14/10/2020

ባለፈው ሳምንት ኢትዮጵያን የጎበኙ ሁለት የአውሮፓ ህብረት ከፍተኛ ባለሥልጣናት በኮሮና ስጋት ራሳቸውን አገለሉ!

ባለፈው ሳምንት ከፕሬዝዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ እና ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አህመድ ጋር የተገናኙ ሁለት የአውሮፓ ህብረት ከፍተኛ ባለሥልጣናት በኮሮና ስጋት ራሳቸውን አገለሉ። ሁለቱ ባለስልጣናት ራሳቸውን ያገለሉት አብረዋቸው ወደ ኢትዮጵያ ከተጓዙ የልዑካን ቡድን አባላት መካከል አንዱ በኮሮና መያዛቸው በምርመራ ከተረጋገጠ በኋላ ነው።

ከትናንት ጀምሮ ራሳቸውን ማግለላቸውን የገለጹት የአውሮፓ ህብረት የውጭ ጉዳይ እና የጸጥታ ፖሊሲ ከፍተኛ ተወካይ ጆሴፕ ቦሬል እና የህብረቱ የቀውስ አስተዳደር ኮሚሽነር ያኔዝ ሌናርቺች ናቸው። ባለፈው ሳምንት ሐሙስ መስከረም 28፤ ከጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አህመድ ጋር የተገናኙት ባለስልጣናቱ፤ በማግስቱ ከፕሬዝዳንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ ጋርም ተወያይተዋል።

የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በሚድሮክ ወርቅ ላይ የባለቤትነት ድርሻ እንደጠየቀ ሪፖርተር ጋዜጣ ዘግቧል!
14/10/2020

የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በሚድሮክ ወርቅ ላይ የባለቤትነት ድርሻ እንደጠየቀ ሪፖርተር ጋዜጣ ዘግቧል!

የጀርመንዋ ላይፕዚሽ ከተማ የአዲስ አበባ ፍቅርዋን ለመግለፅ አንዱን ጎዳናዋን አዲስ አበባ ብላ ሰይማለች!ከጎርጎረሳዉያኑ 2004 ጀምሮ በእህትማማችነት ዝምድናን የመሰረቱት የጀርመንዋ ላይፕዚሽ...
13/10/2020

የጀርመንዋ ላይፕዚሽ ከተማ የአዲስ አበባ ፍቅርዋን ለመግለፅ አንዱን ጎዳናዋን አዲስ አበባ ብላ ሰይማለች!

ከጎርጎረሳዉያኑ 2004 ጀምሮ በእህትማማችነት ዝምድናን የመሰረቱት የጀርመንዋ ላይፕዚሽ ከተማ እና አዲስ አበባ ወዳጅነታቸዉ ጥልቅ ነዉ ። በላፕዚሽ ከተማ ዩንቨርስቲ የአማርኛ እና ግዕዝ ቋንቋ ትምህርት እና ጥናት ከጀመረ ዘመናት ተቆጥረዋል።

በነገራችን ላይ ላይፕዚሽ ከተማ አንዱን የከተማዋን አደባባይ አዲስ አበባ ብላ የሰመችዉ ዛሬ ሳይሆን የዛሬ 5 ዓመት በጎርጎረሳዉያኑ 2015 መስከረም 29 ነዉ። ከዝያ ስያሜዉን ረዘም በማድረግ በያዝነዉ የጎርጎረሳዉያን 2019 ዓመት ግንቦት ወር መጨረሻ ከአነስተኛ አደባባይ ተነስቶ ወደ ጎዳና የሚወስድን 50 ሜትር መንገድን አዲስ አበባ ፕላትዝ ብላ ሰይማለች። እንዲህ ነዉ እህትማማችነት

Via Azeb Tadesse/ Photo: Elias Yimer

የኤርትራው ፕሬዝደንት ኢሳያስ አፈወርቂ ወደ ኢትዮጵያ እያመሩ ነው!የኤርትራ መንግስት ቃል አቀባይ አቶ የማነ ገ/መስቀል ከደቂቃዎች በፊት የትዊተር ገፃቸው ላይ እንዳሰፈሩት ፕሬዝደንት ኢሳያስ...
12/10/2020

የኤርትራው ፕሬዝደንት ኢሳያስ አፈወርቂ ወደ ኢትዮጵያ እያመሩ ነው!

የኤርትራ መንግስት ቃል አቀባይ አቶ የማነ ገ/መስቀል ከደቂቃዎች በፊት የትዊተር ገፃቸው ላይ እንዳሰፈሩት ፕሬዝደንት ኢሳያስ በኢትዮጵያ የሶስት ቀን ይፋዊ ጉብኝት ለማድረግ ለአስመራ አየር ማረፊያ ተነስተዋል።

በጉብኝቱ ላይ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ኦስማን ሳሌህ እና የፕሬዝደንቱ አማካሪ የማነ ገብረአብ ተካተዋል ተብሏል።

"በትግራይ ክልል ለሚገኙ ተማሪዎች 2.8 ሚሊዮን ማስክ ይከፋፈላል"  - ትምህርት ሚኒስቴር ለቲክቫህ ኢትዮጵያየትምህርት ሚኒስቴር የተማሪዎች የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል (Face Mask)...
11/10/2020

"በትግራይ ክልል ለሚገኙ ተማሪዎች 2.8 ሚሊዮን ማስክ ይከፋፈላል" - ትምህርት ሚኒስቴር ለቲክቫህ ኢትዮጵያ

የትምህርት ሚኒስቴር የተማሪዎች የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል (Face Mask) ስርጭትን በተመለከተ ክልሎች ለተማሪዎቻቸው ተረክበው እንዲያሰራጩ የሚገልጽ እና ድልድሉንም አስመልክቶ የጊዜ እና የመጠን ዝርዝር ያለው ደብዳቤ ለክልል ትምህርት ቢሮዎች ጽፏል፡፡

በዚህ ደብዳቤ ውስጥ የትግራይ ክልል ትምህርት ቢሮ አልተካተተም፡፡ ይህም በበርካቶች ዘንድ ጥያቄ ፈጥሯል፡፡

ጉዳዩን በተመለከተ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱን ጠይቀን ተከታዩ መረጃ ተሰጥቶናል ፦

- የተደረገው ድልድል የትግራይ ክልል ተማሪዎችን ጭምር የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ እንዲያገኙ ተደርጎ የተሰራ ነው፡፡

- በደብዳቤው ላይ ማካተት ያልተቻለው የፌዴሬሽን ምክር ቤት በቅርቡ ባሳለፈው ውሳኔ ምክንያት ነው፡፡

- አሁን ላይ በመላ ሀገሪቱ ላሉ 26 ሚሊዮን ተማሪዎች የማስክ አቅርቦት እንዲሟላ እየተሰራ ይገኛል፡፡

- ለትግራይ ክልል ለሚገኙ ተማሪዎችም ይህንን ሥርጭት ለማድረስ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከወረዳዎች እና ከዞኖች ጋር ግንኙነት ጀምሯል፡፡ ሥርጭቱም በዚያው በኩል የሚካሄድ ይሆናል፡፡

- አጠቃላይ ወደ 50 ሚሊዮን ማስክ በዝግጅት ላይ ነው፡፡ ከዚህም ውስጥ 2.8 ሚሊዮን የሚሆነው በትግራይ ክልል ለሚገኙ ተማሪዎች የሚከፋፈል ይሆናል፡፡

ወደ ትግራይ እንዳይገባ የታገደው ድሮን ጉዳይ ምንድን ነው?በርካታ ሰዎች ለአንበጣ መከላከል እንዲውል ከእስራኤል የተላከ ድሮን በቦሌ ጉምሩክ እንደተያዘ እና ስራ ላይ እንዳይውል እንደተደረገ ...
11/10/2020

ወደ ትግራይ እንዳይገባ የታገደው ድሮን ጉዳይ ምንድን ነው?

በርካታ ሰዎች ለአንበጣ መከላከል እንዲውል ከእስራኤል የተላከ ድሮን በቦሌ ጉምሩክ እንደተያዘ እና ስራ ላይ እንዳይውል እንደተደረገ ለኢትዮጵያ ቼክ መረጃ አድርሰዋል፣ ለምን እንደሆነ እንድናጣራም በርካታ ጥያቄዎች ደርሰውናል።

ኢትዮጵያ ቼክ በመጀመርያ ያናገራቸው በቦሌ ጉምሩክ የሚገኙ ሀላፊዎችን ሲሆን "የተያዘ ድሮን ካለ ፍቃድ የሚሰጠው አካል የሆነውን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲን ብታናግሩ ጥሩ ነው፣ ፈቃድ ኖሮት የተያዘ ካለ ግን የተያዘበት አካል መጥቶ ሊያናግረን ይችላል" የሚል መልስ አግኝተናል።

በመቀጠል ኢትዮጵያ ቼክ ከኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲን ምክትል ዳይሬክተር አቶ ከፍያለው ተፈራ ተጨማሪ መረጃ ጠይቋል። መረጃው እንዲህ ይቀርባል:

- በመጀመርያ በጉምሩክ የተያዘ ድሮን አለ? ብዛቱ ስንት ነው? መቼስ ወደ ሀገር ቤት ገባ፣ ከየት ሀገር?

አቶ ከፍያለው>> ድሮኑ በቁጥር አንድ ነው፣ ወደ ኢትዮጵያ የመጣው የዛሬ አምስት ወር ገደማ ነበር፣ በወቅቱ የተባለው አረም ለማስወገድ ይውላል ነበር። የመጣው ከእስራኤል ሀገር ሲሆን ስሪቱ ደግሞ የቻይና ነው።

- ለምን እንዲያዝ ተደረገ?

አቶ ከፍያለው>> አሁን ባለው መመርያ መሰረት ወደ ሀገር እንዲገባ የሚፈቀደው ድሮን የመጫን አቅሙ ከአምስት ኪሎ ያልበለጠ ነው፣ ይህ ድሮን ደግሞ ከሀያ አምስት ኪሎ በላይ መጫን ይችላል፣ ረጅም ርቀትም መጓዝ ይችላል። ስለዚህ ለሌላ አላማ ሊውል ስለሚችል እንዲጣራ እንዲቆይ ተደርጓል፣ ይህ የፀጥታ ስጋት ሊሆን የሚችል ድሮን ነው። በተጨማሪም ድሮኑ ምንም አይነት ገላጭ መረጃ (description) አብሮት አልመጣም።

- አሁን ካለው የአንበጣ ችግር አንፃር ስራ ላይ እንዲውል ማረግ አይቻልም?

አቶ ከፍያለው>> የአንበጣ ችግር እንዳለ ይታወቃል፣ ነገር ግን ለሌላ አላማ እንዳይውል እንደ ግብርና ሚኒስቴር አይነት አካል ሀላፊነቱን ሊወስድ ይገባል።

ፎቶ: 25 ኪሎ መሸከም የሚችል ድሮን ምስል (ከኢንተርኔት)

☆ ይህ መረጃ የቀረበላችሁ የኢንተርኒውስ ፕሮጀክት በሆነው ኢትዮጵያ ቼክ ነው። የኢትዮጵያ ቼክን ስራዎች ለመከታተል:

10/10/2020
በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 01 በተለምዶ አየር አምባ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ባሉ መኖሪያ ቤቶች ከምሽቱ 1:30 አካባቢ በተከሰተ እሳት አደጋ እስካሁን የ4 ሰዎች ህይወት አልፏል። አንድ ሰው ...
10/10/2020

በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 01 በተለምዶ አየር አምባ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ባሉ መኖሪያ ቤቶች ከምሽቱ 1:30 አካባቢ በተከሰተ እሳት አደጋ እስካሁን የ4 ሰዎች ህይወት አልፏል። አንድ ሰው ላይ ከባድ ቃጠሎ ደርሷል።

የእሳት አደጋው በአሁን ሰዓት በቁጥጥር ስር የዋለ ሲሆን የአደጋው መነሻ በመጣራት ላይ እንደሚገኝ የቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር አስታውቋል፡፡

 የኢትዮጵያውያን ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኢዴፓ) ፕሬዝደንት አቶ አዳነ ታደስ ለኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 ሬድዮ ጣቢያ የተናገሩት፦"አቶ ልደቱ አያሌው በድንገት ከቢሾፍቱ ፖሊስ ጣቢያ ወደ አዳማ ከ...
09/10/2020



የኢትዮጵያውያን ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኢዴፓ) ፕሬዝደንት አቶ አዳነ ታደስ ለኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 ሬድዮ ጣቢያ የተናገሩት፦

"አቶ ልደቱ አያሌው በድንገት ከቢሾፍቱ ፖሊስ ጣቢያ ወደ አዳማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ተወስደዋል። ፖሊስ አቶ ልደቱን ለምን ፖሊስ ወደ ፍርድ ቤት እንደወሰዳቸው እስካሁን ምንም መረጃ የለንም።

የዋስትና መብታቸውን ፖሊስ እንዲያከብር ለመነጋገር ፍርድ ቤት ቀጠሮ ሰጥቶን እየጠበቅን ባለንበት ሁኔታ ነው ዛሬ ከፖሊስ ጣቢያ ወደ አዳማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት መወሰዳቸውን የሰማነው።

አቶ ልደቱ ምንም አይነት መጥሪያ እንዳልደረዳቸውም ፤ በአንድ ሚዲያ ግን አቶ ልደቱ አያሌው በሌላ ጉዳይ ክስ እንደተመሰረተባቸው የሚያሳይ ዘገባ ወጥቶ ተመልክተናል። በእጅጉ በፍትህ ስርአቱ ላይ ተስፋ እንድንቆርጥ አድርጎናል።

አቶ ልደቱ ፖሊስ ወደ አዳማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ከወሰዳቸው በኃላ ስለተፈጠረው ነገር ለማጣራት ከአዲስ አበባ ከተማ ወደ አዳማ እየተጓዝኩ ነው።"

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከጥቅምት 20 - 30 /2013ዓ.ም ድረስ ተማሪዎችን ለመቀበል ዕቅድ መያዙን የዩኒቨርሲቲው ፕሬዜዳንት ተናግረዋል፡፡የAAU ፕሬዚዳንት ፕሮፌሰር ጣሰው ወልደሃና ለአዲ...
09/10/2020

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከጥቅምት 20 - 30 /2013ዓ.ም ድረስ ተማሪዎችን ለመቀበል ዕቅድ መያዙን የዩኒቨርሲቲው ፕሬዜዳንት ተናግረዋል፡፡

የAAU ፕሬዚዳንት ፕሮፌሰር ጣሰው ወልደሃና ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከተገሩት ፦

- ዩኒቨርሲቲው ተማሪዎችን በ2 ዙር እንዲገቡ ለማድረግ ዕቅድ ይዞ ዝግጅት ቢያደርግም በኮቪድ 19 የሚያዘው ሰው ቁጥር በመጨመሩ ተማሪዎችን በ3 ዙር ለመቀበል ዝግጅቱን አጠናቋል፡፡

- በአንድ ክፍል ከ25 በላይ ተማሪዎች እንደማይማሩ እና መምህሩ ደግሞ ከ35 ደቂቃ በላይ ማስተማር እንደሌለበት ተወስኗል።

- ከዚህ ቀደም አንድ የተማሪዎች ማደሪያ ክፍል (ዶርሚተሪ) ከስምንት እስከ 18 ተማሪዎች ይይዝ ነበር የኮሮና ቫይረስ ስርጭት ለመግታት ሲባል በአንድ ዶርሚተሪ ለ2 ተማሪዎች ቢበዛ 3 ተማሪዎችን እንዲይዝ ይደረጋል።

- ባለፈው ዓመት ተመራቂ የነበሩ አራት ሺህ የሚሆኑ የቀን ተማሪዎች በመጀመሪያው ዙር ከገቡ በኋላ በ45 ቀን ውስጥ ትምርታቸውን አጠናቀው እንዲመረቁ ይደረጋል።

- የማታ መርሀ ግብር ተማሪዎች ትምህርታቸውን ይቀጥላሉ።

- የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ 7 ካምፓሶች በተለይ ከውጭ አገር ለሚመለሱ ዜጎች ለለይቶ ማቆያነት ይጠቀሙባቸው ነበር ከዛሬ ጀምሮ ወደ እነዚህ ካምፓሶች ለለይቶ ማቆያ የሚገባ ሰው እንደማይኖር ስምምነት ላይ ተደርሷል።

- በዩኒቨርሲቲው በኩል የሚደረገው ዝግጅት ተጠናቋል። በትራንስፖርት እና በሌሎች ጉዳዮች ዙሪያ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ውይይት ይደረጋል።

- ከጥቅምት 20 እስከ 30 /2013 ዓ.ም ድረስ ተማሪዎችን ለመቀበል ዕቅድ ተይዟል።

Address


Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ዜና - Zena posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Videos

Shortcuts

  • Address
  • Alerts
  • Videos
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share