KONSO News - Otota XONSO - ኮንሶ ዜና

  • Home
  • KONSO News - Otota XONSO - ኮንሶ ዜና

KONSO News - Otota XONSO - ኮንሶ ዜና Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from KONSO News - Otota XONSO - ኮንሶ ዜና, Media, .
(1)

KONSO News || ኮንሶ ዜና || Otota XONSO is a Konso Media Network established by the united Konso communities all over the globe, for the purpose sharing a balanced and fact supported news about/from Konso to the world.

የአርባ ምንጭ መካነ ኢየሱስ ቴክኒክ ኮሌጅ ከዚህ በታች በተዘረዘረው የትምህርት ዓይነት መምህራንን አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል፡፡
14/10/2024

የአርባ ምንጭ መካነ ኢየሱስ ቴክኒክ ኮሌጅ ከዚህ በታች በተዘረዘረው የትምህርት ዓይነት መምህራንን አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል፡፡

Posted inVacancy ክፍት የሥራ ቦታ ማስታወቂያ Posted by admin October 14, 2024No Comments የአርባ ምንጭ መካነ ኢየሱስ ቴክኒክ ኮሌጅ ከዚህ በታች በተዘረዘረው የትምህርት ዓይነት መምህራንን አወዳድሮ መቅጠር .....

11/10/2024
አዲሱ የፌስቡክ ደህንነት ማስጠበቂያ ስልት````````````````````````````````````````````````ሰሞኑን ፌስቡክ End-to-end encryption የተሰኘ አዲስ የደህንነ...
29/09/2024

አዲሱ የፌስቡክ ደህንነት ማስጠበቂያ ስልት
````````````````````````````````````````````````
ሰሞኑን ፌስቡክ End-to-end encryption የተሰኘ አዲስ የደህንነት (Security) ማስጠበቂያ ዘዴን እያስተዋወቀ ነው። የዚህ ደህነነት ማስጠበቂያ ዘዴ ማንኛውም ሰው በ Messenger (ቻት) በኩልል ያስተላለፍናቸው ማናቸውንም መልእክቶች ከኛ ውጪ ማንም ማየት እንዳይችል የሚያደርግ ነው። የማኅበራዊ ሚዲያ ባለቤቶች (Meta) እንኳን ሳይቀር ከሰዎች ጋር የተቀያየርናቸውን መልእክቶች ማየት እንዳይችል የሚያደርግ ነው።
መረጃው ወደ ኔትዎርክ ሥርዓት ከመግባቱ በፊት በመልእክት ፈጣሪው ኮምፕዩተር ወይም ስልክ ላይ እንክሪፕት (አመሳጥሮ) ይደረጋል። መልእክቱ ወደ ተቀባዩ ሲደርስ የታተመው (የተቆለፈው ነገር ይፈታል) ወይም decrypt ይደረጋል።

ድንገት የምንጠቀመው ዕቃው (ስልክ ወይም ኮምፕዩተር) ከኛ እጅ ቢወጣ/ቢጠፋ ያገኘ ሰው የተቀያየርናቸውን መልእክቶች ማየት እንዳይችል ያደርገዋል። መልእክቱ ስላክ እኛ ብቻ በምናውቀው ምስጢራዊ ኮዶች ስለሚቆለፍ።

ከዚህ በፊት የነበረው ሁኔታ በቻት ወይም መልእክት መለዋወጫ በኲል የተቀያየርናቸው መልእክቶች ያልተቆለፉ በመሆናቸው ስልካችንን ወይም ኮምፕዩተራችንን ያገኘ ማንኛውም ሰው ማንበብ ይችላል (ምናልባት ሁልጊዜ ማኅበራዊ ሚዲያዎቻቸውን Log out ከሚያደርጉ ጥቂት ሰዎች በስተቀር)። ሌላው የፌስቡክ ድርጅት የኛን መልእክት በቀላሉ ማንበብ ይችላል። መልእክቱ በኔትዎርክ ሥርዓት ሲሄድ ድንገት መሃል-ጠላፊዎች እጅ ቢገባ እንኳን ማንበብ አይችልም። አሁን የተፈጠረው ዘዴ ግን ይኸንን ሁሉ ያስቀራል።

ውስንነቶች
• በውስጥ መስመር የተቀያየርናቸው የቪዲዮ ወይም የድምጽ መልእክቶች ለፌስቡክ ድርጅት ርፖርት ማድረግ አንችልም
• ከኛ ጋር ሲነጋገር የነበረ ሰው ድንገት መልእክቶቹን ለሌላ ሦስተኛ ሰው ቢያጋራ ሦስተኛው ሰው ማንበብ ይችላል።

እራሳችሁን ጠብቊ!!

አንድ ሰው በተከታታይነት የቲክቶክ ቪዲዮችን የሚያይ ከሆነ የትኲረት መጠኑ በከፍተኛ ሁኔታ እያሽቆለቆለ እንደሚሄድ ጥናቶች ያሳያሉ። በአሁን ጊዜ የሰው ልጅ የትኲረት መጠኑ ከ 8 ሴኮንዶች በታ...
23/09/2024

አንድ ሰው በተከታታይነት የቲክቶክ ቪዲዮችን የሚያይ ከሆነ የትኲረት መጠኑ በከፍተኛ ሁኔታ እያሽቆለቆለ እንደሚሄድ ጥናቶች ያሳያሉ። በአሁን ጊዜ የሰው ልጅ የትኲረት መጠኑ ከ 8 ሴኮንዶች በታች መውረዱ በዘርፉ የተደረጒ ጥናቶች አመልክተዋል።

ከዚህ በተጨማሪ የቲክቶክ ቪዲዮች በብዛት የሚያስቊ በመሆናቸው በአእምሮአችን ውስጥ ዶፓሚን የተሰኘ የደስታ ሆርሞን በከፍተኛ ደረጃ እንዲመረት ያደረጋል። የዶፓሚን በተደጋጋሚ ከፍ ብሎ መቆየት ሱስ ከማስያዙም በላይ ሌሎች ዶፓሚን የማያመነጩ (የማያስቊ) ጒዳዮች ላይ ያለን ፍላጎት በከፍተኛ ሁኔታ ይቀንሳል።

ሞት፡ በገነት በሮች ላይ (Death at the Gates of Paradise)ከማንበብዎ በፊት ፎቶውን ይዩ!ሁለት ጥንዶች (ተጋቢዎች ይኹን?) በስፔን ባህር ዳርቻ ሆነው መጠጣቸውን ፉት እያደረ...
22/08/2024

ሞት፡ በገነት በሮች ላይ (Death at the Gates of Paradise)

ከማንበብዎ በፊት ፎቶውን ይዩ!

ሁለት ጥንዶች (ተጋቢዎች ይኹን?) በስፔን ባህር ዳርቻ ሆነው መጠጣቸውን ፉት እያደረጉ ይዝናናሉ።
በቅርብ ርቀት ላይ ከአፍሪካ ወደ አውሮፓ ሊሻገር ያሰበ ስደተኛ በጀልባ ባህሩን አቋርጦ ከተሻገር በኋላ ሕይወቱ ወዲያ ትታው ስለሄደች ሥጋው ብቻ መሬት ላይ ወድቆ ይታያል። ሁለቱ ተዝናኚዎች ዓለማቸውን ይቀጫሉ። አሸዋው እንዳይቆረቊራቸው ምንጣፍ አንጥፈው፣ ጸሐይ እንዳይነካቸው በአበባ የተሽቆጠቆጠ ጃንጥላ ዘርግተው፣ ለጉሮሯቸው የሚጠጣ ነገር ጎናቸው አስቀምጠው፣ ሟቹን ሰውዬ በቀዝቃዛ ስሜት ይመለከታሉ። ሬሳው በምንም ዐይነት መልኲ ስሜታቸውን አልረበሸም። ክቡር የሆነው ሰው ሳይሆን ድንጋይ ወይም የዛፍ ጒቶ የሚያዩ ይመስላሉ። ወይም ሬሳው ጒዳያቸው አይደለም፣ እያዩት ተዝናኖታቸውን ቀጠሉ። ፎቶ በ2000 ዓ.ም Javier Bauluz በተባለ የፎቶ ጋዜጠኛ የተወሰደ ነው።

ይህ የዘመናዊው ዓለም ዓይነተኛ መገለጫ ነው። ሞትና ፈሽታ፣ እልልታና ለቅሶ፣ ልደትና ቀብር ተጎራብተው መኖራቸውን አሳይቶናል። በአጭሩ ሕይወትና ሞት ጎን ለጎን መሆናቸውን ያሳያል።

ከዚያ በላይ ግን፣

ይህ ፎቶ በጣም አጒልቶ ያሳየኝ አሁን ያለው የኢትዮጵያ መንግሥት ለዜጎች ያለውን እይታ ነው።
የዜጎች ሬሳ አደባባይ ላይ ሲበሰብስ መንግሥት የደስታ አታሞ ይደልቃል። የዜጎች ሞት የመንግሥትን ስሜት አይረብሽም፣ ሕጻናትና አዛውንቶች ሜዳ ላይ ቢበተኑ፣ በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለው አደባባይ ላይ ቢሰጡ፣ የታጠቊ ኀይሎች የመንግሥት መዋቅሮችን ተቆጣጥረው የሚዘርፉትን ዘርፈው፣ የሚያቃጥሉትን አቃጥለው የሚያፈርሱትን ሲያፈርሱ መንግሥት የሚሆነው በቀዝቃዛ ስሜት እየተመለከት የሰርክ ተግባሩን ያከናውናል። እንደ ዕድል ሆኖ ከብዙሃኑ መሃል ከሆነ በሚዲያ ጩኸት የተነሣ የኀዘን መግለጫ ሊያወጣ ይችላል። ወይም 'መግደል ጥሩ አይደለም' የሚል ምክር ይለገሳል።

ሰሞኑን በኮንሶ ዞን የሆነውን ባሰብኲ ቊጥር የመንግሥት የግድ-የለሽነት ጥግ ጎልቶ ይታየኛል። ምናልባትም እስከ ዕድሜ መጨረሻ ድረስ ከአእምሮዬም አይጠፋም ይሆናል። ከገዳዮች ጭካኔ በላይ የመንግሥት ንቀት ልቤን ሰብሮታል።

ፈጣሪ ለዜጎቹ የሚያስብ የተሻለ መንግሥት እንዲሰጠን ጸሎት ማድረስ እቀጥላለሁ! የተረፍነውም ለዚህ ቢሆንስ!!!

 !በጋርዱላ ዞን ሀይበና ቀበሌ መሽጎ  በሽብር ተግባር ላይ የተሰማራው የሽብር ቡድን ከቅዳሜ ነሐሴ 11/2016 ዓ.ም ጀምሮ ለተከታታይ አራት ቀናት የኮንሶ ዞን ሰገን ዙሪያ ወረዳ መቀመጫ የ...
22/08/2024

!
በጋርዱላ ዞን ሀይበና ቀበሌ መሽጎ በሽብር ተግባር ላይ የተሰማራው የሽብር ቡድን ከቅዳሜ ነሐሴ 11/2016 ዓ.ም ጀምሮ ለተከታታይ አራት ቀናት የኮንሶ ዞን ሰገን ዙሪያ ወረዳ መቀመጫ የሆነችውን ሠገን ከተማ በመክበብ በሥራ ላይ የነበሩ የፖሊስ አባላትን ጨምሮ ንጹሀን ሲቪል የኮንሶ ተወላጆችን እየመረጠ በአሰቃቂ ሁኔታ በመጨፍጨፍ፣ የህዝቡና የወረዳው መንግስት ንብረቶችን በመዝረፍና በማውደም በህዝባችን ላይ እጅግ አረመናዊና ጭካኔ የተሞላበት ከፍተኛ ግፍ ፈፅሟል።
በዚህም የሽብር ጥቃትም እስካሁን በተረጋገጠ መረጃ መሰረት የህዝባችን ሰላምና ደህንነት የመጠበቅ መደበኛ ስራቸው ላይ የተሰማሩ 8 የፖሊስ አባላትና 5 ሲቪል ወገኖቻችን በድምሩ 13 ወገኖቻችንን በአረመነያዊ ሁኔታ ተገድለው ከ600 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት የመንግስትና የህዝብ ሀብት መውደሙ ታውቋል፡፡
በጣም ልብ የሚሰብረው ነገር ይህ ከጋርዱላ ዞን ሀይበና ቀበሌ የተነሳው የሽብር ቡድን ለረጀም ግዜ ለእኩይ ተግባሩ ከፍተኛ ዝግጅት እያደረገ መሆኑ የሚመለከታቸው የክልሉ የጸጥታና የአስተዳደር አካላት በቂ መረጃ እያላቸው ጭፍጨፋውንና የንብረት ውድመቱን አስቀድመው ለመከላከል ምንም አይነት እርምጃ አለመውሰዳቸው ነው፡፡ ይባስ ብሎ ከቅዳሜ ነሐሴ 11 -15 ቀን 2016 ዓ.ም ባሉት አራት ተከታታይ ቀናት የሰገን ከተማ በሽብር ቡድኑ ተከባ በኮንሶ ዜጎች ላይ ከፍተኛ ዘር ተኮር አረመኔያዊ የጅምላ ጭፍጨፋ ስፈጸም እና የህዝብና የመንግስት ንብረት ስወድምና ስዘረፍ ቅዳሜ ነሐሴ 11/2016 ዓ.ም ከሌሊቱ 6፡00 ሰዓት አካባቢ ቁጥራቸው 50 የሚሆን የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል አድማ ብተና አባላት ከሰገን ከተማ 4 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ባለችው አድስገበሬ ቀበሌ የደረሱ ቢሆንም የሽብር ቡድኑ ከአቅማችን በላይ ነው በሚል ሰበብ ወደ ከተማው ሳይገቡ እዚያው ቀበሌ ላይ ለአራት ተከታታይ ቀናት አድረው እዚያው ተቀምጠዋል፡፡ እነዚህ የክልሉ አድማ ብተና አባላት ከከተማው አፍንጫ ስር ተቀምጠው የህዝቡን የሰቆቃ ጩሄት እየሰሙና የንበረት ውድመት እያዩ የበይ ተመልካች ሆነው ሰንብተዋል፡፡ እጅግ በሚያሳዝንና በሚዘገንን ሁኔታም የሽብር ቡድኑ ያለ ከልካይ ለአራት ቀናት ዜጎቻችንን ጨፍጭፎ የወረዳው ህዝብና መንግስት ንብረትን ዘርፎ የቀረውን አውድሟል፡፡
የሽብር ቡድኑ ሰገን ከተማ ተቆጣጥሮ ዜጎቻችንን እየጨፈጨፈና የወረዳውን ንብረት እየዘረፈ ተቋማትን በእሳት ሲያጋይ ከቆየ ከ 2 ቀናት በኋላ ማለትም ከነሐሴ 11 እና 12 ቀን 2016 ዓ.ም በኋላ ሰኞ ነሐሴ 13/2016 ዓ.ም ቁጥራቸው ወደ 300 የሚሆኑ የሀገር መከላከያ ሠራዊትና የፌዴራል ፖሊስ አባላት ከተጨማሪ የክልሉ አድማ ብተና አባላት ጋር በመሆን ወደ ከተማዋ አቅራቢያ ያላቸው አድስገበሬ ቀበሌ ቢደርሱም አንዴ ትዕዛዝ አልተሰጠንም ሌላ ጊዜም ከአቅማችን በላይ ነው በማለት ምንም እርምጃ አለመውሰዳቸው ለላው ልብ ሰባሪ ክስተት ሆኗል፡፡ በዚህም ምክንያት ከተማ ውስጥ ከሽብር ቡድኑ ጭፍጨፋ በተለያዩ ስፍራዎች የተሸሸጉ ዜጎቻችን በድጋሜ የመዳን ዕድል ተነፍገው ማክሰኞ ነሀሴ 14 ቀን 2016 ዓ.ም ሌሊት የሽብር ቡድኑ አስቀድሞ ባዘጋጀው ቼክ ሊስት መሰረት ቤት ለቤት እየዞሬ በርካታ ዜጎቻችንን ረሽኗል፡፡ የሽብር ቡድኑ ያለ ማንም ከልካይ የፈለገውን አላማ ካሳካ በኋላ ባላው የግንኙነት መረብ ተነግሮት ከተማውን ለቆ ከወጣ በኋላ ረቡዕ ነሐሴ 15/2016 ዓ.ም በጠዋት የመከላከያ ሰራዊቱ ወደ ከተማው ሲገባ አንድም የታጠቀ አካል ሳያገኝ በብሔራቸው ማንነት ብቻ ተመርጠው በግፍ የተገደሉ የኮንሶ ዜጎች አስከረን ለአራት ቀናት በየሜዳው ተበትኖ በክብር ሳይቀበር ከቀረበት ህዝቡ እንዲያነሳ ተደርጓል፡፡
ይህ ከ2011 ዓ.ም ጀምሮ የተለያዩ አካላት ከሽብር ቡዱኑ ጋር ተቀናጅተው በጥንቃቄ እየታቀደና እየተደገፈ ያለው የሽብር ተግባርና ግፍ በህዝባችን ላይ ያለ ከልካይ እየተፈጸመ ይገኛል፡፡ ይህ የሽብር ተግባር መንግስት ባለበት አገር ያለ ከልካይ በጠራራ ፀሐይ በህዝባችን ላይ ያለ ማቋረጥ ለስድሰት ተከታታይ አመታት መፈጸሙ ልብ ሰባሪና እጅግ በጣም አሳዛኝ ክስተት ሆኖ ተመዝግቧል፡፡ በመሆኑ መንግሥት የህግ የበላይነትን የማስፈንና የሁሉንም ዜጎች የመኖር መብትና ደህንነት በእኩልነትና ፍትሓዊ በሆነ መንገድ የመጠበቅ ኃላፊነቱ በአግባቡ መወጣት ካልቻለ ዜጎች በመንግስት ላይ አመነታ እንዲያጡና መንግስትን በጥርጣረ እንዲመለከቱ የሚያደርግ በመሆኑ ድርጊቱ ፈፅሞ ተቀባይነት የለሌው መሆኑን በፅኑ እናምናለን፡፡
ስለሆነም ከነሐሴ 11 -15 ቀን 2016 ዓ.ም በዚህ ዘር ተኮር ጭፍጨፋ፣ ንብረት ዘረፋና ውድሜት በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የተሳተፉ የመንግሰት አካላት፣ የሽብር ቡድኑና ግብረአበሮቹ ላይ የሚመለከተው የመንግሰት አካል የማጣራት ስራ ሰርቶ ለህግ እንድያቀርባቸውና የህግ የበላይነትን እንዲያሰፍ በአፅንኦት እንጠይቃለን። በተጨማሪም ከ2011 እስከ 2016 ዓ.ም ድረስ ተመሳሳይ ወንጀል በህዝባችን ላይ ፈጽመው ተፈርዶባቸው ያለ አግባብ የተለቀቁና በፍትህ ስርአቱ ውስጥ ሆነው ወንጀለኞችን ያለ አግባብ የለቀቁና ያስለቀቁ ግለሰቦችና አካለት በገለልተኛ አካል ጉዳያቸው ተጣርቶ ለህግ እንድቀርቡ እንጠይቃለን፡፡
በተጨማሪም የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽንን ጨምሮ በሀገር ውስጥም ሆነ አላም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ተቋማት በኮንሶ ህዝብ ላይ በተፈፀመው የሽብር ጥቃት በሰውና በንብረት ላይ የደረሰውን ጉዳት በማጣራት ህዝባችን ፍትህ እንዲያገኝ የበኩላቸውን እንዲወጡ ማህበራችን ጥሪውን ያቀርባል፡፡
በመጨረሻም በሰላማዊ ዜጎቻችን ላይ በተፈፀመው በዚህ የሽብር ጥቃት ህይወታቸውን ላጡ ወገኖቻችንን የተሰማንን ጥልቅ ሐዘን እየገለጽን፤ ለተጎጂ በተሰቦችና ለመላው የኮንሶ ህዝብ መጽናናትን እንመኛለን!
የኮንሶ ምሁራን ማህበር
ነሐሴ 16 ቀን 2016 ዓ.ም

ምቀኝነትና ኢትዮጵያውያን``````````````````````````ብዙውን ጊዜ ከኢትዮጵያውያን ጋር ተያይዘው የሚነገሩ የምቀኝነት ተረኮች አሉ። ከነዚህ ውስጥ አንዱ እንደሚከተለው ነው፦'እግዚአ...
07/08/2024

ምቀኝነትና ኢትዮጵያውያን
``````````````````````````
ብዙውን ጊዜ ከኢትዮጵያውያን ጋር ተያይዘው የሚነገሩ የምቀኝነት ተረኮች አሉ።
ከነዚህ ውስጥ አንዱ እንደሚከተለው ነው፦

'እግዚአብሔር ለሰዎች የሚፈልጒትን እንዲጠይቊ ዕድል ሰጣቸው አሉ፣ የሚሰጣቸው ነገር ለጓደኛቸው እጥፍ ተደርጎ ይሰጣቸዋል ተባል። የሁሉም አገር ዜጋ የሚጠቅመውን መሻቱን ጠየቅ፣ ቤት፣ መኪና፣ ቆንጆ ሚስት/ባል፣ ዕውቀት. . . ወዘት። እንደተባለውም ለጓደኛቸው የነሱ እጥፍ ተሰጣቸው፣ ኢትዮጵያዊ መጣና ፈጠሪን ምን ቢጠይቅ ጥሩ ነው፣ "የኔን አንድ ዓይን አጥፋ'። የሱ አንድ ዓይኑ ከጠፋ የጓደኛው ሁለት ዓይኖች ይጠፋሉ የሚለውን ስሌት አስልቶ መሆኑ ነው እንግዲህ'። ምቀኛ ሰው ከራሱ ስኬት ይልቅ የጓደኛው ውድቀት ያስደስተዋል ይባላል። እንደዚህ የመሰሉ ብዙ ተረቶች አሉን።

ምንም እንኳን ይኸ ነገር እንዲሁ የሚነገር ተረት ቢሆንም፣ ይኸንን ተረት በሳይንሳዊ መንገድ የሚያረጋግጥ አንድ ጽሑፍ አንብቤ በጣም ተገረምኹ። ለካስ የሚነገርብን ተረት ብቻ ሳይሆን በገቢር የምንኖረው ሕይወት ኖሯል።

ጉዳዩ እንደዚህ ነው፦
በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የድኅረ-ምረቃ ፕሮግራም ተመራቂ ተማሪዎች ላይ ጥናት ተደረገ። የጥናቱ ዓላማ "የድኅረ-ምረቃ ተማሪዎች በብዛት የሚፈጽሙት የሥነ-ምግባር ችግሮች ምንድን ናቸው?" (What do you think are the most common problems observed among student researchers?) የሚለውን ጥያቄ ለመመለስ ነው።

እኔ ብዙ ነገር ገምቼ ነበር፣
ግምቶቼም፦
፥- የሰውን ሀሳብ ዕውቅና ሳይሰጡ መገልበጥ (plagarism)፣ የሌላ ሰው ሪሰርች የራስ አድርጎ ማቅረብ፣ ዳታ ሳይሰበስቡ እንደሰበሰቡ አድርጎ ማቅረብ. . . ወዘተ ግምቶቼ ነበር።
በጥናቱ መሠረት ግምቶቼም የተወሰነ ዋጋ አላቸው።
ዋናው ግኝት ግን እሱ አልነበረም።

ትልቊን ድርሻ የሚይዘው ችግር እንደሚከተለው ይነበባል፦
'Hide materials that can be useful to others'። ለሌሎች ሊጠቅሙ የሚችሉ ነግሮችን መደበቅ። 59.8% የዚህ ችግር መጠን ነው። በጥናት የተዘረዘሩ ሌሎች ችግሮች በሙሉ ከዚህ በታች ናቸው። አያሳፍርም?

ድሮ ተማሪ እያለው ተፈላጊ መጽሐፍትን ከላይብራሪ የሚደብቊ ተማሪዎች ትዝ አሉኝ።
ታዲያ ኢትዮጵያውያን ምቀኞች ናቸው ቢባል እውነትነ የለውም ትላላችሁ?

ምንጭ፡ Belay Tefera and Abdinasir Ahmed: Research Methods (Mega printing press) Addis Ababa. p.43

29/07/2024

የማክሮ-ኢኮኖሚ ማሻሻያውን ምዕራባውያን እያዳነቊት ይገኛሉ፣
ይኸ ነገራቸው ፍርሃት ጭሮብኛል። ጠቅላይ ሚኒስተሩ እጅ እየሰጡ ይኹን?

ዶ/ር እንግዳ ኦርካይዶ በአስቸኳይ ይፈታ!የህዝብን ጥያቄ ማስተጋባት ወንጀል አይደለም! /ር_እንግዳ_ኦርካይዶ
22/07/2024

ዶ/ር እንግዳ ኦርካይዶ በአስቸኳይ ይፈታ!

የህዝብን ጥያቄ ማስተጋባት ወንጀል አይደለም!

/ር_እንግዳ_ኦርካይዶ

21/07/2024

መግደልና ማሰር መፍትሂ እንደማያመጣ ከደርግና ከኢሕአዴግ መማር ካልቻልን ታሪክ ለመደጋገም የተፈረደብን ድኲማን ነን ማለት ነው።

ነፃ ሥልጠና፣ ከሰፊ የሥራ ዕድል ጋር!```````````````````````````````````````````የአርባምንጭ መካነ ኢየሱስ ቴክኒክ ኮሌጅ ከመካነ ኢየሱስ ልማትና ማኅበራዊ አገልግሎት...
09/07/2024

ነፃ ሥልጠና፣ ከሰፊ የሥራ ዕድል ጋር!
```````````````````````````````````````````
የአርባምንጭ መካነ ኢየሱስ ቴክኒክ ኮሌጅ ከመካነ ኢየሱስ ልማትና ማኅበራዊ አገልግሎት ኮሚሽን (DASSC) እንዲሁም ዓለም ዐቀፍ የአድቨንቲስት ልማትና ተራድዖ ድርጅት (ADRA) ጋር በመተባበር ከጀርመን መንግሥት በተገኘ ድጋፍ ባለፉት 3 ወራት ካሠለጠንናቸው 38 ተማሪዎች መካከል 18 ሥልጠናቸውን እንደጨረሱ ከመንግሥታዊና መንግሥታዊ ካልሆኑ ተቋማት ጋር አስተሳስረን በቀጥታ ሥራ አስጀምረናል። መቀጠር ያልፈለጒ ደግሞ በራሳቸው ሥራ እየተንቀሳቀሱ ይገኛሉ።

ለሁለተኛ ዙር ሥልጠና ምዝገባ ጀምረናል።

መስፈርት፡ ፍላጎት ያላቸው ዜጎች ሁሉ
የሥልጠናው ዓይነት፡ የሶላር ቴክኖሎጂ ዲዛይን፣ ተከላና ጥገናና እንዲሁም የኢንተርፕርንየር ሥልጠና
የሚፈጀው ጊዜ፡ 3 ወር
ክፊያ፡ በፕሮጀክቱ ለሚታቀፉት ሥልጠና በነፃ፣ በራሳቸው መማር ለሚፈልጒት መጠነኛ ክፊያ
የሥራ ዕድል፡ መንግሥታዊና መንግሥታዊ ካልሆኑ ተቋማት ጋር እናገናኛለን፣ በራሳቸው መንገድ ቢዝነስ መክፈት ለሚፈልጒ ሁኔታዎችን እናመቻቻለን።

እናመሰግናለን!```````````````የሕዝብን ድምጽ አክብራችሁ ብልህ ውሳኔ ስለወሰናችሁ እናመሰግናችኋለን። ከዚህ ጋር አያይዤ!በቀጠናው ላይ ለተፈጠረው ሰላምና መረጋጋት ዳዊት የተጫወተው ሚ...
15/06/2024

እናመሰግናለን!
```````````````
የሕዝብን ድምጽ አክብራችሁ ብልህ ውሳኔ ስለወሰናችሁ እናመሰግናችኋለን።

ከዚህ ጋር አያይዤ!
በቀጠናው ላይ ለተፈጠረው ሰላምና መረጋጋት ዳዊት የተጫወተው ሚና ቀላል አልነበረም። ሁሉንም ወገኖች ለማቀራረብ የሄደበት ርቀት እጅግ በጣም የሚደንቅ ነው። የ Leadership qualityና ብስለትን በደንብ ያሳየ ነበር። የጋርዱላ ዞን አስተዳደር የሆኑት አቶ ብርሃኑም የሚደነቅ ነው፣ የሁለቱም ትብብር ሰላም ፈጥሯል። ምናልባትም የደቡብ ኢትዮጵያ ክልልም ለዚህ ዕውቅና ይሰጣል ብለን እንጠብቃለን። ለሰላም የሚተጒትን ስናበረታታ ችግርን በጦርነት ለመፍታት የሚያስቡትን discourage እናደርጋለን። መተቻቸት ብቻ ሳይሆን መሞጋገስም ይለመድ። መልካም የሠሩትን እናበረታታ፣ ያጠፉትን እንገስጽ። ይኽ ሥልጣኔ ነውና!
እናመሰግናለን!!

14/06/2024

የድሮ መምህሬ!
ሐመር ሐንሻና
እህታችን የውብዳር ኦላታ፣ ለዚህ ታላቅ ኀላፊነት ስለበቃችሁ እኳን ደስ አላችሁ።
ደስ ብሎኛል!

የቀድሞ መምህሬ!ኢንጂነር ፍሬዘር ኮርባይዶ፣ ይኸንን በማየቴ በጣም ደስ ብሎኛል!መልካም የሥራ ዘመን!
14/06/2024

የቀድሞ መምህሬ!
ኢንጂነር ፍሬዘር ኮርባይዶ፣
ይኸንን በማየቴ በጣም ደስ ብሎኛል!
መልካም የሥራ ዘመን!

የፌስቡክ ገጻችንን እንዴት ከኢሉሚናቲዎች መጠበቅ ይቻላል?```````````````````````````````````````````````````````````````````````ብዙውን ጊዜ እኛ ሳና...
02/06/2024

የፌስቡክ ገጻችንን እንዴት ከኢሉሚናቲዎች መጠበቅ ይቻላል?
```````````````````````````````````````````````````````````````````````
ብዙውን ጊዜ እኛ ሳናውቅ በፌስቡክ ገጻችን ላይ የሚለጠፉ ማናቸውም ጽሑፎች፣ ሥዕሎችና ቪዲዮች ለመቆጣጠር ማድረግ ያሉብን እጅግ በጣም ወሳኝ የሆኑ የ Security Settings. በዚህ ቪዲዮ ቀጥሎ ያሉ ሐሳቦች ላይ እንነጋገራለን።
1. የፌስቡክ አካንታችንን እንዴት Secure ማድረግ እንችላለን?
2. የወሲብ ቪዲዮች የኛ ገጽ ላይ ብቻ ነው የሚለጠፉት?
3. እነዚህ አስጸያፊ ቪድዮችን የሚለጥፈው ማን ነው?
4. ወደ ገጻችን የሚመጡ የተለያዩ ሐሳቦች እንዴት እኛ ጋ ሊደርሱ ቻሉ?
፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠
መልእክቱ ጠቃሚ ሆኖ ካገኛችሁት ለሌሎችም ያጋሩ።

ብዙውን ጊዜ እኛ ሳናውቅ በፌስቡክ ገጻችን ላይ የሚለጠፉ ማናቸውም ጽሑፎች፣ ሥዕሎችና ቪዲዮች ለመቆጣጠር ማድረግ ያሉብን እጅግ በጣም ወሳኝ የሆኑ የ Security Settings. በዚህ ቪዲዮ ቀጥሎ ያሉ .....

Fate of Sisyphus: የኮንሶ ፖለቲካበግሪክ አፈ-ታሪክ ውስጥ ሲሲፈስ የሚባል የቆሮንቶስ ንጉሥ አለ። ንጉሡ በጣም አታላይ በመሆኑ ሞትንም ጭምር ሳይቀር አታሏል፣ አንዴ ሳይሆን ሁለቴ። ...
17/05/2024

Fate of Sisyphus: የኮንሶ ፖለቲካ

በግሪክ አፈ-ታሪክ ውስጥ ሲሲፈስ የሚባል የቆሮንቶስ ንጉሥ አለ። ንጉሡ በጣም አታላይ በመሆኑ ሞትንም ጭምር ሳይቀር አታሏል፣ አንዴ ሳይሆን ሁለቴ። ሲሲፈስ የሚበቃውን ያህል ከኖረና የምድር ሕይወቱ ማብቂያ በደረሰ ጊዜ የሞት አለቃ የሆነው ታናቶስ ሊወስደው መጣ። አለቃው በእጁ ሟቾች ታስረው የሚወሰዱበትን ገመድ (ማሰሪያ ይዟል)። አታላዩ ሲሲፈስ ግን ከሞት አለቃ ጋር ንግግር ይጀምራል። የያዘው ማሰሪያ (ገመድ) እንዴት እንደሚሠራ፣ ሟቾች እንዴት ታስረው እንደሚወሰዱ እንዲያስረዳለት ይጠይቀዋል። ታናቶስም ሳይጠራጠር አሠራሩን በራሱ ላይ እየሞከረ ለሲሲፈስ ያስረዳል። በዚያን ጊዜ ሲሲፈስ ታናቶስ (የሞት አለቃ) በራሱ ላይ ለሙከራ በጠመጠመው ገመድ ያስራል። በዚህ ምክንያት ሟች የሆነ ማንኛውም ሕይወት ያለ ነገር እንዳይሞት ሆነ። የሚሞት ሰው ባለመኖሩ የጦርነት አምላክ የሆነውና በግድያና በጭፍጨፋ የሚታወቀው አሬስ ለአምላኲ ዘዩስ ክስ አቀረበ። ዘዩስ ሲያይ ማንም እየሞተ አይደለም። መጨረሻ ላይ በተደረገው ግምገማ ችግሩ የታናቶስ (የሞት አምላክ) መታሰር መሆኑ ተደረሰበት።

ታናቶስ ተፈታ። ሲሲፈስም እንደገና ሞተ። ድጋሜ ሲሞት ቀጥታ ወደ ሐዴስ (የሲኦል ንጒስ) ይሄድና አቤቱታ ያቀርባል፣ ምንም የቀብር ሥርዓት አልተደረገልኝም ብሎ። ሐዴስም ሄዶ ሚስቱን ቀጥቶ ቶሎ እንዲመለስ ፈቃድ ይሰጠዋል። ሲሲፈስ እስኪመለስ ድረስ በቦታው ሐዴ ታሰረ። ሆኖም ግን ሲሲፈስ በቃሉ መሠረት ቶሎ ወደ ሲኦል አልተመለሰም፣ ይልቊን ከሚስቱ ጋር ከሞት መልስ ሁለተኛ ዙር ኑሮውን ያጣጥም ጀመር። አሁንም ሰው መሞት አቆመ።

በዚህ የተቆጣው ዘዩስ ሲሲፈስይን ይይዝና ቀጥሎ ያለውን ፍርድ ይበይንበታል።
ከተራራ ግር ወደ ተራራ ጫፍ አንድ ግዙፍ ድቡልቡል ድንጋይ እንዲገፋ፣ ገፍቶ ገፍቶ ተራራ ጫፍ ላይ ሲያደርስ ድንጋዩ እንደገና ተንከባልሎ ወደ ተራራው ግርጌ እንዲወርድ ይደረጋል። ይህ ሂደት ዘላለማዊ ይኾናል። በዚህ ምክንያት ሲሲፈስ ያታለለውን ሞት እንዲናፍቅ ሆነ። ማብቂያ የለሌው ዘላለማዊ ልፋት ከመልፋት ሞቶ መገላገል ይሻላል ዓይነት ነገር። የሰው ልጅ በራሱ መንገድ ዘላለማዊ ሕይወት ፍለጋ ለዘላለማዊ ሥቃይ እንደሚዳርጒ አንዱ ማስተማሪያ ነው።

ይኸንን አፈ ታሪክ በመጠቀም አልበርት ካሙ የተሰኘ የፈረንሳይ (ትውልደ አልጀሪያዊ) ፈላስፋ የሲሲፈስ አፈ-ታሪክ (Myth of Sisyphus) የሚል አንድ ጽሑፍ አቅርቦ ነበር። ፈላስፋው የሕይወት ትርጒም አልባነትን (Absurdity of life) ለማስተዋወቅ ተጠቅሞበታል።

የኮንሶ ፖለቲካ ይህንን ግዙፍ ድቡልቡል ድንጋይ ከተራራ ግርጌ ወደ ተራራው አናት እንደ መግፋት ሆኖ ይታየኛል። ተገፍቶ ተገፍቶ አናት ላይ አድርሰን ትንሽ እናርፋለን ስንል ተንከባልሎ ከተራራ ግርጌ ያርፋል። ሰሞኑን ፖለቲካችን ወደ ግርጌ ተንከባልሎ እያየን ነው። እንዴ ሲሲፈስ የበደልነው ነገር ምን ቢሆን ነው?

Book Review By Abyot S. GashuteI've been immersed in a book titled “How to Read a Book,” a title that perfectly aligns w...
06/05/2024

Book Review
By Abyot S. Gashute
I've been immersed in a book titled “How to Read a Book,” a title that perfectly aligns with my fervent desire to refine my reading habits and skills. Despite being authored five decades ago; its content remains as pertinent today as it was upon its initial release in 1940. Following a reprint in 1967, twenty-seven years later, it underwent revisions and expansion in 1972, culminating in the final edition I had the pleasure of reading.

You can get the Full Review by clicking the following link:

How to Read a Book: The Classic Guide to Intelligent Reading Introduction I've been immersed in a book titled “How to Read a Book,” a title that perfectly aligns with my fervent desire to refine my reading habits and skills. Despite being authored five decades ago; its content remains as pertine...

Address


Alerts

Be the first to know and let us send you an email when KONSO News - Otota XONSO - ኮንሶ ዜና posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to KONSO News - Otota XONSO - ኮንሶ ዜና:

Videos

Shortcuts

  • Address
  • Alerts
  • Contact The Business
  • Videos
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share