Waza Daily

Waza Daily social media

 #ኢሬቻ  ሆራ አሶሳ የአብሮነት፤ የመቻቻልና የፍቅር ተምሳሌት  በሆነችው አሶሳ ከተማ የኢሬቻ በዓል በድምቀት ተከብሯል!!! እንኳን አደረሳችሁ! እንኳን ደስ አላችሁ!
22/10/2023

#ኢሬቻ ሆራ አሶሳ

የአብሮነት፤ የመቻቻልና የፍቅር ተምሳሌት በሆነችው አሶሳ ከተማ የኢሬቻ በዓል በድምቀት ተከብሯል!!! እንኳን አደረሳችሁ! እንኳን ደስ አላችሁ!

 ! #ኦሮሞ ለልጁ ስም ሲያወጣንኳ «ሌንሳ» ብሎ ነው። እርጥብ  #ሳር እንደማለት ነው። ባህሉ፣ አኗኗሩ ትውፊቱ በሙሉ ከተፈጥሮ ጋር የተሰናሰለ ነው። ውሃ ፣ ሳር ፣ ዛፍ እነዚህ ሶስት ነገሮ...
06/10/2023

!

#ኦሮሞ ለልጁ ስም ሲያወጣንኳ «ሌንሳ» ብሎ ነው። እርጥብ #ሳር እንደማለት ነው። ባህሉ፣ አኗኗሩ ትውፊቱ በሙሉ ከተፈጥሮ ጋር የተሰናሰለ ነው። ውሃ ፣ ሳር ፣ ዛፍ እነዚህ ሶስት ነገሮች ከኦሮሞ ጋር ጥብቅ ቁርኝት አላቸው። ዛፍ (ዋርካ) (ኦዳ) ምኩራቡ ማለት ነው። ከፀሃይ ይጠለልበታል። ለፍርድ ፣ ለእርቅ፣ ለሹመት ፣ ይሰየምበታል። ውሃ አዝእርቱን ያበቅበታል። ይጠጣዋል። ከብቶቹን ያረሰርስለታል። እርጥብ ሳር ዋቃ ጉራቻ ሲባርከው የሚሰጠው ምልክት ነው። የበረከቱ፣ የልምላሜው፣ የተፈጥሮ ፀጋው ምልክት! ልምላሜውን እየቀጠፈ የተባረከው ውሃ ውስጥ ነክሮ ውሃውንም፣ ፀሃዩንም። ልምላሜውንም። ማሩንም። ቅቤውንም። ወተቱንም። ጤናውንም ለሰጠው ፈጣሪ ምስጋና ያቀርባል። ኦሮሞና ምስጋና አይነጣጠሉም። በትንሹ የሚያመሰግን ህዝብ ነው። (እሱ አይመሰገንም እንጂ!)

ዋቄፈታ እምነት ነው። ሊያውም ኢትዮጵያ ውስጥ ካሉ እምነቶች በሙሉ ቀዳሚው! ክርስቲያን ብሆንም ፍልስፍናው ይደንቀኛል። ዋቃ ጉራቻ ማለት (ጥቁሩ አምላክ ማለት ነው) አለም ጥቁረትን እንደውርደት ተጠይፎ አምላኩንና መላእክቱን ሳይቀር ነጭ አድርጎ ሲስል ኦሮሞ ፈጣሪውን በራሱ መልክ ነው የቀረፀው። መፅሃፉም ሰው በፈጣሪ መልክ ተፈጠረ ይላል። ፈጣሪ እኔን ነው የሚመስለው። ከሚል በራስ ማንነት የመኩራት ፍልስፍና ውጤት ነው!

ኦሮሞ ባህሉን ማንፀባረቅ፣ ትውፊቱ፣ ቀኖናው፣ ዶግማው፣ ፍልስፍናው፣ ግር ላላቸው ሰዎች ማስረዳት፣ በቅንነት ለጠየቁት መልስ መስጠት ይገባዋል። ነገር ግን ከአመት እስካመት ኢሬቻን ከባእድ አምልኮ ጋር ለማገናኘት ለሚለፋ ሰው ራሱን በመግለፅ መድከም አይጠበቅበትም ። ለባህልና ለትውፊቱ የብቃት ማረጋገጫ የሚሰጠው
አንድም ምድራዊ ፍጡር የለም!

በሕገ-ወጥ የወርቅ አምራቾች ላይ የሚወሰደው እርምጃ ተጠናክሮ ይቀጥላል- አቶ አሻድሊ ሀሰን ************** በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በሕገ-ወጥ የወርቅ አምራቾች እና አዘዋዋሪዎችላይ ...
08/05/2023

በሕገ-ወጥ የወርቅ አምራቾች ላይ የሚወሰደው እርምጃ ተጠናክሮ ይቀጥላል- አቶ አሻድሊ ሀሰን
**************
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በሕገ-ወጥ የወርቅ አምራቾች እና አዘዋዋሪዎችላይ የሚወሰደው እርምጃ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አሻድሊ ሀሰን ገለጹ።

በክልሉ ሕገ-ወጥ የወርቅ አምራችና አዘዋዋሪዎችን ለመቆጣጠር የተቋቋመው ክልላዊ ኮማንድ ፖስት በሸርቆሌ ወረዳና አሶሳ ከተማ ከሚገኙ የወርቅ አምራችና አዘዋዋሪዎች ጋር ተወያይቷል።

በውይይቱም ርዕሰ መስተዳድር አሻድሊ ሀሰን፣ በመከላከያ ሠራዊት የ404 ኮር ዋና አዛዥ ብ/ጄነራል ሰይፈ ኢንጊን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች፣ ወርቅ አምራቾችና አዘዋዋሪዎች ተገኝተዋል።

አቶ አሻድሊ ሀሰን÷ መንግስት ሕጋዊ የሆኑ የወርቅ አምራቾችንና አዘዋዋሪዎችን ተጠቃሚ ለማድረግ የማበረታቻ እርምጃዎች መተግበር ጀምሯል ብለዋል።

በክልሉ የሚንቀሳቀሱ ወርቅ አምራቾችና አዘዋዋሪዎች የሚያመርቱትን ወርቅ ወደ ብሔራዊ ባንክ በማስገባት የማበረታቻው ተጠቃሚ እንዲሆኑ ጥሪ አቅርበዋል።

መንግስት ወርቅ የሚመረትበትን መንገድ ለማዘመን ለወርቅ አምራቾችና አዘዋዋሪዎች እያደረገ ያለው ድጋፍ ወደ ብሔራዊ ባንክ የሚገባውን የወርቅ ምርት ለማሣደግ መሆኑንም ጠቅሰዋል።

ከዚህ ውጪ የሚደረግን የወርቅ ግብይት የሀገርን ኢኮኖሚ የሚጎዳ በመሆኑ ኮማንድ ፖስቱ አይታገስም ነው ያሉት፡፡

በሕገ-ወጥ የወርቅ አምራቾች እና አዘዋዋሪዎች ላይ እየተወሠደ ያለው እርምጃ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ማረጋገጣቸውንም የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

ወርቃችንን ወደ አገራችን! ለአገራችን!በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የወርቅ ምርት ለወርቅ አምራቾችና አዘዋዋሪዎች ከስራ እድል ፈጠራ አልፎ ጠቀም ያለ ካፒታል እያስገኘ መሆኑ አይዘነጋም፡፡ ባለፈዉ...
07/05/2023

ወርቃችንን ወደ አገራችን! ለአገራችን!

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የወርቅ ምርት ለወርቅ አምራቾችና አዘዋዋሪዎች ከስራ እድል ፈጠራ አልፎ ጠቀም ያለ ካፒታል እያስገኘ መሆኑ አይዘነጋም፡፡ ባለፈዉ ዓመት ከ23 ኩንታል በላይ ወርቅ ከክልሉ ወደ ብሔራዊ ባንክ/ማዕከላዊ ገበያ የመቅረቡ ዜና ሲሰማ አንዳንዶች ማመን ተስኗቸው "ቦቆሎ ነዉ? ወይስ ወርቅ?" ብለዉ ነበር፡፡ ይህ ምርት ከ14 ቢሊየን ብር በላይ ገቢና 256 ሚሊየን የሚገመት ዶላር በማስገኘት በአገራዊ ወጪና ገቢ ንግድ ሚዛን ብሎም በዉጪ ምንዛሪ ግኝት ላይ ቀላል የማይባል ሚና ተጫዉቷል፡፡

በያዝነዉ አመት ከክልሉ ለማዕከላዊ ገበያ መቅረብ የቻለዉ የወርቅ ምርት ካለፈዉ አመት ተመሳሳይ ወቅት አንጻር በብዙ እጅ አንሶ ተገኝቷል፡፡ ምክንያቱ የምርት መቀነስ ስላጋጠመ አይመስልም፡፡ ይልቁንም በክልሉ ሰላማቸዉ እየተረጋገጠላቸዉ የሚገኙ ሌሎች ዞኖችም ካለፈዉ በተሻለ ሊያመርቱ እንደሚችሉ ይገመታል፡፡

ታዲያ ችግሩ ምነድን ነዉ?
ቁልፉ ችግር የግብይት ስለመሆኑ የክልሉ መንግስት ደርሶበታል፡፡ ሰላማችንን በማናጋት ወደ ትክክለኛ የልማት አቅጣጫ እንዳንገባ ሲገዳደሩን የከረሙት የዉጪ ኃይሎች አሁን ደግሞ በኢኮኖሚ ሻጥር ሊፈታተኑን ወርቅም ሆነ ሌሎች ምርቶቻችን በህገወጥ መንገድ በድንበር አካባቢ ከአገር እንዲወጡ በማድረግ በዉጪ ምንዛሪ እጥረት ሊያሽመደምዱን እንደሚሰሩ መገመት ከባድ አይደለም፡፡

የወርቅ ዝዉዉርን ሕጋዊ የማድረግና የድንበር አካባቢን የኢኮኖሚ ሻጥር የመቆጣጠር ስራ ደግሞ ለአንድ የክልል ርዕሰ መስተዳድር ወይም ደግሞ የማእድን ቢሮ ኃላፊ የሚተዉ እንዳልሆነም መገንዘብ ተገቢ ነዉ፡፡

ስለሆነም የወርቅ ዝውውርን ህጋዊነት በማረጋገጥ አገር ማግኘት የሚገባትን ጥቅም እንድታገኝ ወርቅ አምራቾች፣ ወርቅ አዘዋዋሪዎች፣ የፌደራልና የክልል ጸጥታ አካላት፣ በየደረጃዉ የሚገኝ አመራርና ማህበረሰቡ በጠቅላላ የሚጠበቅበትን አዉቆ በመስራት በአጪር ጊዜ ውስጥ ከፍተኛ ዉጤት ለማምጣት የክልሉ መንግስት ያስቀመጠው አቅጣጫ በአግባቡ ሊፈጸም ይገባል፡፡

እያንዳንዱ አመራርም ይህን ከኮትሮባንድ በላይ የሆነና በአገራዊ ኢኮኖሚ ላይ የተቃጣን ከፍተኛ ሻጥር በዉል በመገንዘብ፣ በተግባር በመረባረብና የሚፈለገዉንና የሚጠበቅበትን ዉጤት በማስመዝገብ በሚመዘንበት ሁኔታ የተሰጠዉ ስምሪት ተገቢና ወቅታዊ ነዉ፡፡

መሪነት በተግባር፤ መሪነት በዉጤት፤
ወርቃችንን ወደ አገራችን ለአገራችን!

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሀሰን ወደ መቀሌ ተጉዘዋል!የክልል ርዕሰ መስተዳድሮችና ሚኒስትሮች እንዲሁም የተለያዩ የስራ ሃላፊዎች መቀሌ ገብተዋል። የአማ...
27/04/2023

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሀሰን ወደ መቀሌ ተጉዘዋል!

የክልል ርዕሰ መስተዳድሮችና ሚኒስትሮች እንዲሁም የተለያዩ የስራ ሃላፊዎች መቀሌ ገብተዋል። የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ይልቃል ከፋለ፣ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ፣ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ፣ የድሬዳዋ ከተማ ከንቲባ ከድር ጁሀርና የተለያዩ ክልሎች ርዕሰ መስተዳድሮች ወደመቀሌ ተጉዘዋል። ዋናው የጉዞ አላማ ለትግራይ ማቋቋሚያ የሚሆን ገንዘብ ለመለገስ ነውም ተብሏል።

24/04/2023

ከሰላም የምታተርፈው ኢትዮጵያ ናት!
#ሰላም

1ሺህ 4 መቶ 44ኛው የኢድ አል ፈጥር በዓል በአሶሳ ከተማ ሀይማኖታዊ ስርዓቱን በጠበቀ መልኩ በደማቅ ሁኔታ ተከበረ ። በክልሉ የሚገኙ የዕምነቱ ተከታዬች ከዚህ ቀደም  የኢድ አል ፈጥር በዓ...
21/04/2023

1ሺህ 4 መቶ 44ኛው የኢድ አል ፈጥር በዓል በአሶሳ ከተማ ሀይማኖታዊ ስርዓቱን በጠበቀ መልኩ በደማቅ ሁኔታ ተከበረ ።

በክልሉ የሚገኙ የዕምነቱ ተከታዬች ከዚህ ቀደም የኢድ አል ፈጥር በዓልን በተለያየ ቦታ ሲያከብሩ እንደነበር አስታውሰው የዘንድሮው የኢድ በዓል ግን ሁሉም የእምነቱ ተከታዮች ተሰባስበው በአንድ ላይ በመስገድ ሀይማኖታዊ ስርዓቱን ባከበረ መልኩ በደማቅ ሁኔታ ማክበራቸውን የገለፁት የክልሉ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ም/ቤት ፕረዚደንት ሼህ ኢብራሂም የህዝበ ሙስሊሙ አንድነት አማራጭ የሌለው በመሆኑ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሀሰን ህዝበ ሙስሊሙ ባለፍት ጥቂት አመታት በጥቃቅን ልዩነቶች በተለያየ ሁኔታ ሲያከብር እንደነበር ገልጸው አሁን ላይ ችግሩን በንግግር በመፍታት በአንድነት ፈጣሪን በማመስገን በማክበራቸው መደሰታቸውገልጸዋል።

የእምነቱ ተከታዮች የዒድ አልፈጥር በዓልን ሲያከብሩ የተቸገሩ ወገኖች ካላቸው በማካፈልና በመደገፍ እንዲሆን ርዕሰ መስተዳድሩ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

የሀገራችን ሠላም በዘላቂነት ለማረጋገጥ ህዝበ ሙስሊሙ ስለ ሰላም አጥብቆ በመስበክ እያደረገ ያለውን ጥረት አጠናክሮ መቀጠል ይጠበቅበታልም ብለዋል።

ከሃና መንገሻ ዘገባ የተወሰደ!!

እንኳን ለ1 ሺህ 444ኛው የዒድ አል ፈጥር በዓል በሰላም አደረሰን አደረሳችሁ!ዒድ ሙባረክ! ርዕሰ መስተዳደር አሻድሊ ሀሰን ሀገራችንን የሚያጸኗት ሰላም፣ እዝነትና በረከት ናቸው። ሰላም ህል...
20/04/2023

እንኳን ለ1 ሺህ 444ኛው የዒድ አል ፈጥር በዓል በሰላም አደረሰን አደረሳችሁ!
ዒድ ሙባረክ!
ርዕሰ መስተዳደር አሻድሊ ሀሰን

ሀገራችንን የሚያጸኗት ሰላም፣ እዝነትና በረከት ናቸው። ሰላም ህልውናዋን ያጸናዋል። እዝነት ሕዝቦቿ ተከባብረው፣ ተፈቃቅደው፣ ተስማምተውና ተቻችለው እንዲኖሩ ያደርጋሉ። ለሰላም፣ ለእዝነትና ለበረከት ብቻ እጆቻችንን እንድንዘረጋና ልቦቻችንን እንድንከፍት አደራ እያልኩ በድጋሚ መልካም የዒድ አል ፈጥር በዓል እንዲሆን እመኛለሁ

ዒድ ሙባረክ!

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የወደሙ የህዝብ መሠረተ ልማቶችን መልሶ ለማቋቋም ከ80 ቢሊዮን ብር በላይ በጀት ያስፈልጋል - የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ*********************************...
19/04/2023

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የወደሙ የህዝብ መሠረተ ልማቶችን መልሶ ለማቋቋም ከ80 ቢሊዮን ብር በላይ በጀት ያስፈልጋል - የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ
***************************************

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ባለፉት ሁለት ዓመታት በተከሰቱ የፀጥታ ችግሮች የወደሙ የህዝብ መሠረተ ልማቶችን መልሶ ለማቋቋም ከ80 ቢሊዮን ብር በላይ በጀት አንደሚያስፈልግ የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ባካሄደው ጥናት አረጋግጧል።

አሶሳ ዩኒቨርሲቲ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ከፀጥታ ችግር ጋር ተያይዞ በህዝብ አገልግሎት መስጫ ተቋማት ላይ የደረሰውን ጉዳት ለመለየትና እና መልሶ ለማቋቋም በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ጥናት አካሂዷል።

የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ያካሄደው የጥናት ውጤት የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶክተር ከማል አብዱረሂም እና የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሀሰን በተገኙበት ለክልሉ ካቢኔ አባላት ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል።

የጥናቱ ውጤት እንደሚያሳየው፣ በክልሉ ከጥቅምት 2014 ዓ.ም ጀምሮ ለተከታታይ ሁለት ዓመታት ውስጥ በደረሱ የጸጥታ ችግሮች 179 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች፣ 32 የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤቶች፣ 184 የተለያዩ የጤና ተቋማት ወድመዋል።

በግብርናው ዘርፍም የጸጥታ ችግሩ በፈጠረው ጫና መታረስ የነበረበት ከ450ሺህ በላይ ሄክታር ማሳ አለመታረሱን ጥናቱ አመልክቷል።

734ሺህ ኩንታልያልተሰበሰበ ምርት እንዲሁም አራት ቢሊዮን ኩንታል የተሰበሰበ ምርት በችግሩ ምክንያት መውደሙ በጥናቱ ተገልጿል።

እነዚህን የወደሙ መሠረተ ልማቶችን መልሶ በማቋቋም ዜጎችን ተጠቃሚ ለመድረግ ከ80 ቢሊዮን በላይ ብር እንዲሚያስፈልግ ጥናቱ አመላክቷል።

ጥናቱ በክልሉ ለሚከናወነው የመልሶ ማቋቋም ስራ በግብዓትነት የሚያገለግል መሆኑም ተገልጿል።

በጀማል አህመድ

18/04/2023
"የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ልዩ ሀይሎችን መልሶ የማደራጀት ተግባር ተጠናቋል!" ርዕሰ መስተዳደር አሻድሊ ሀሰን በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ልዩ ሀይሎችን መልሶ የማደራጀት ተግባር በተወሰነው ውሳ...
18/04/2023

"የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ልዩ ሀይሎችን መልሶ የማደራጀት ተግባር ተጠናቋል!" ርዕሰ መስተዳደር አሻድሊ ሀሰን

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ልዩ ሀይሎችን መልሶ የማደራጀት ተግባር በተወሰነው ውሳኔ መሠረት በሰላማዊ መንገድ ተሰርቶ መጠናቀቁን ርዕሰ መስተዳደር አሻድሊ ሀሰን ገለፁ፡፡

*የህግ የበላይነት ለኢትዮጵያ ህልውና!* 1. ለሰላምና ዴሞክራሲ በተከፈተው በር ማንም እየገባ እንደፈለገ ሲያንቦጫርቀው መንግሥት ዝም ብሎ መመልከት የለበትም። የዴሞክራሲ ምህዳሩ መስፋቱ ጥሩ...
13/04/2023

*የህግ የበላይነት ለኢትዮጵያ ህልውና!*

1. ለሰላምና ዴሞክራሲ በተከፈተው በር ማንም እየገባ እንደፈለገ ሲያንቦጫርቀው መንግሥት ዝም ብሎ መመልከት የለበትም። የዴሞክራሲ ምህዳሩ መስፋቱ ጥሩ ነበር። ነገር ግን ጽንፈኞችና የሥልጣን ጥመኖች የዴሞክራሲ ሜዳውን የፖለቲካ ንግድ ማጧጧፊያ ሜዳ አድርገውታል። የዛሬ አምስት አመት ለኢትዮጵያችን ሲባል የተከፈተው የይቅርታ፣ የምህረትና የሰላም በር የፖለቲካ አውሬዎች መጨፈሪያ ሆኗል።

2. ማንም እየተነሳ ሥልጣንና ገንዘብ ውልብ ባለበት ጊዜ ሁሉ ሁከትና ብጥብጥ አቅዶ፣ ስፖንሰር አድርጎ፣ ወጣቶችን በጭካኔና ጥላቻ ስሜት በሚዲያ ቀስቅሶ በየጎዳናው የፈለገውን ሰው በማንነት ለይቶ ገድሎ፣ የንጹሀንን ንብረት በማንነት ለይቶ አቃጥሎ፣ በማን አለብኝነት የመንግስትንና የህዝብን ንብረት ዘርፎ፣ የመንግሥትንና የህዝብን አስተዳደራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ እንቅስቃሴ በእብሪት አቁሞ አስተጓጉሎ፣ መንግሥትን በሀይል አፍርሼ ቤተ መንግሥት ልገባ ነው ብሎ በአደባባይ ፎክሮ፣ ህዝብንና መሪዎችን በስም እየጠራ ሙልጭ አድርጎ ሰድቦ፣ የዜጎችን ሰላምና ሰብዓዊ መብት አደጋ ላይ ጥሎ ሲያበቃ የወንጀል እጁን ታጥቦ እንደፈለገ በነጻነት የሚንቀሳቀስ ከሆነ ነገ ሁላችንም ዋስትና የለንም። እያንዳንዱ ወንጀለኛ ተለቅሞ ለህግ ይቅረብልን። ሀገሪቱ ህግ ያላትና ህግ ማስከበር የምትችል ሀገር መሆኗን በተግባር ማየት እንፈልጋለን።

3. የአማራን ህዝብ ፈጽሞ የማይወክሉና በሥልጣንና በገንዘብ ጥማት የሰከሩት የሰሞነኞቹ የሀሳብ ጭንጋፎች ዓላማችን በሀያ አራት ሰዓት ውስጥ አራት ኪሎ ቤተ መንግሥት መግባት ነው ብለው በግልጽ ተናግረዋል። ይህን የዘመናት ህልማቸውን ለማሳካት ንጹሃንን ገድለው ክብር ባለው አስክሬን ላይ ቆመው ጨፍረዋል፣ በህዝብና በመንግሥት ንብረት ላይ ከፍተኛ ውድመት አድርሰዋል፣ ከበዓላት በኋላ ዳግም የጎዳና ነውጡን እንቀሰቅሳለን ብለዋል። በዚህ አደገኛና ህገ መንግሥታዊ ሥርዓትን በጉልበት የማፍረስ ወንጀል ውስጥ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ እጃቸው ያለበት አካላት ተለቅመው ለህግ ሊቀርቡ ይገባል። ንጹሃንን የገደሉትም፣ ንብረት ያቃጠሉትም፣ የዘረፉትም፣ ህዝብን እንደ ህዝብ የሰደቡትም፣ መንግሥትን በሀይል እናፈርሳለን ያሉትም በአደባባይ ላይ በግልጽ ነው። የተለየ መረጃና ማስረጃ ማፈላለግ አይጠይቅም። ወንጀላቸውን ራሳቸው በቪዲዮ ቀርጸው ለአለም ህዝብ አሰራጭተው በራሳቸው ላይ መረጃና ማስረጃ አዘጋጅተዋል። በአስቸኳይ ለህግ መቅረብ አለባቸው። ካልሆነ ህዝብ በሰላምና በነጻነት የመኖር ዋስትናው አደጋ ላይ ይወድቃል። በመንግስትና በህዝብ መካከል ያለው መተማመንም ይሸረሸራል። መንግሥት ጠበቅ ያለ የማያዳግም እርምጃ ወስዶ ያሳየን። ነገም ከነገ ወዲያም የሥልጣንና ገንዘብ ፍቅር ነሸጥ ያደረገው ሁሉ በእብሪት ተነድቶ ለጥፋት ወደ ጎዳና ሲወጣ ክንደ ብርቱ ቅጣት እንደሚጠብቀው ይወቅ። መንግሥት ይህን ማድረግ እንደሚችል ያሳየን።

4. መንግሥት ጠበቅ ያለ ቆፍጣና እርምጃ ወስዶ የህግ የበላይነት ካላስከበረ ሌላ የግጭት አዙሪት ውስጥ መግባታችን ነው። እንደ ህዝብ ስሙ ተጠርቶ የተሰደበ፣ በአደባባይ መብቱ፣ ነጻነቱና ክብሩ የተገፈፈ፣ ሰብዓዊ መብቱ በእብሪተኛ ብሔርተኞች የተረገጠ ህዝብ የሰሞኑን ህልመኛ ግን ደግሞ ከሰላም አንጻር አደገኛ የሆነ እንቅስቃሴ በከፍተኛ ትዕግስትና በትኩረት እየታዘበ ይገኛል። መንግሥት ህግ ማስከበር አቅቶት ህዝቡ በራሴ መንገድ መብቴንና ክብሬን አስከብራለሁ ወደሚል ውሳኔ ከገባ ውጤቱ አደገኛ ነው። ስለሆነም መንግሥት አፋጣኝ፣ አስተማሪና ጠበቅ ያለ እርምጃ ወስዶ ህግ ያለባትና ህግ የሚከበርባት ሀገር መሆኗን ያሳየን።

5. መንግሥት ውስጡንም ፈትሾ ያጽዳ። የመንግሥት አመራሮች፣ የጸጥታ አካላትና ሌሎች መዋቅሮች በተከሰተው ነውጥ ውስጥ የነበራቸው ሚና በጥልቀት ይገምገም። ይለያል ዘንድሮ የማስመሰል ኑሮ። በአቋም የጸኑ፣ ዥዋዥዌ የሠሩ እና በንፋሱ የተወሰዱ አመራሮች ከሀይማኖት ችግር ጊዜው ይልቅ አሁን ቁልጭ ብሎ ታይተዋል። ወይ ቆፍጣና መንግስት ሆኖ ኢትዮጵያን ማዳን፣ ወይ በጽንፈኛ ብሔርተኝነት ማዕበል ውስጥ እየዋኙ ትውልድ ማስበላት። ከመሀል ሀገርም ከክልሉም የነውጥ ዕቅዱን ሲያስፈጽሙ፣ በለው ሲሉ የነበሩ፣ ሀላፊነት መወጣት ትተው ስልካቸውን አጥፍተው የጠፉ፣ ሸሽተው አዲስ አበባ ያሉ፣ የክልሉን ከተሞች ለአውሬ ሰጥተው ህዝቡን አውላላ ሜዳ ላይ ጥለው የተሸሸጉ፣ በአንድ እግራቸው መንግስት ጋር በሌላኛው እግራቸው ነውጠኛ የብሔር አክቲቪስት ጋር ያሉ ሁሉ አስተዳደራዊም ፖለቲካዊም ተጠያቂነት ሊረጋገጥባቸው ይገባል።

6. ተጠያቂነትና የህግ የበላይነት ለኢትዮጵያ ህልውና እጅግ ወሳኝ ስለሆነ ህዝቡ በወንጀሉ የተሳተፉ አካላት ተለቅመው ለህግ ሲቀርቡና እንደየወንጀላቸው ክብደት ህጋዊ ቅጣት ሲጣልባቸው ማየት ይፈልጋል። ይህ ከሆነ ብቻ ነው መንግሥትና ህዝብ ተማምነው ለጋራ ዓላማ በጋራ የሚቆሙት።

የባምባሲው የልማት አርበኛ : አባ አብደራሂም!!ሚያዝያ 03/2015  በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል ርዕሰ መስተዳዳር በክቡር አቶ አሻዲል ሀሰን የተመራው ከፍተኛ የክልል አመራሮች   ቡድን በባምባ...
13/04/2023

የባምባሲው የልማት አርበኛ :
አባ አብደራሂም!!

ሚያዝያ 03/2015 በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል ርዕሰ መስተዳዳር በክቡር አቶ አሻዲል ሀሰን የተመራው ከፍተኛ የክልል አመራሮች ቡድን በባምባሲ ወረዳ ጃማፃ ቀበሌ በሰብል ምርት፣ በአትክልትና ፍራፍሬ እና በእንስሳት እርባታ አስደናቂ ስራ እያከናወኑ የሚገኙትን የልማት አርበኛው የአባ አብደራሂምን እርሻ ልማት ሥራዎች ጎብኝቷል።
የልማት አርበኛው ስራ በተለይ ለክልሉ ብሄር ብሄረሰቦች አርአያነቱ ከፍ ያለ ነው።

በርዕሰ-መስተዳድሩ ቤተ-መንግስት የጋራ የኢፍጣር መርሃ-ግብር ተካሄደ*****************የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ-መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሀሰን በቤተ-መንግስት የጋራ የኢፍጣር ዝ...
02/04/2023

በርዕሰ-መስተዳድሩ ቤተ-መንግስት የጋራ የኢፍጣር መርሃ-ግብር ተካሄደ
*****************

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ-መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሀሰን በቤተ-መንግስት የጋራ የኢፍጣር ዝግጅት አድርገዋል።

የክልሉ እስልምና ጉዳዮች ምክርቤት ፕሬዚዳንት ሼህ ኢብራሂም ሲራጅ፣ በክልሉ በጋራ አብሮ መብላት እና በጾም ወቅትም ያለውን ተካፍሎ ማፍጠር የቆዬ ባህላዊ እሴት መኖሩን ጠቅሰዋል።

በረመዳን ወቅት የተቸገሩትን መደገፍ፣ በአንድነት ሆነን ለሀገራችን እና ለክልላችን ሠላም መጸለይና ዱኣ ማድረግ ይጠበቅብናል ብለዋል።

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የተከናወነው የበጋ ስንዴ ልማት ሥራ አበረታች መሆኑ ተገለጸበቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የተከናወኑ የበጋ ስንዴ ልማት ሥራዎች የሚበረታቱ መሆናቸውን የግብርና ሚኒስትር ግ...
02/04/2023

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የተከናወነው የበጋ ስንዴ ልማት ሥራ አበረታች መሆኑ ተገለጸ

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የተከናወኑ የበጋ ስንዴ ልማት ሥራዎች የሚበረታቱ መሆናቸውን የግብርና ሚኒስትር ግርማ አመንቴ (ዶ/ር) ገለጹ።

የግብርና ሚኒስትሩ፣ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ አሻድሊ ሀሰን እና ሌሎች ከፍተኛ አመራሮች በክልሉ የተከናወኑ የበጋ ስንዴ ልማት ሥራዎችን ጎብኝተዋል።

ግርማ አመንቴ (ዶ/ር) ÷ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልልምአርሶ አደሩን በማሳተፍ የተከናወኑ የበጋ ስንዴ ልማት ሥራዎች የሚበረታቱ ናቸው ብለዋል።

ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ በቀጣይ የክልሉን የስንዴ ልማት ሥራ ለማጠናከር አስፈላጊ ግብዓቶችን እንደሚያቀርብም ገልጸዋል።

አቶ አሻድሊ ሀሰን በበኩላቸው÷ የክልሉ መንግሥት ለአርሶ አደሩ ግንዛቤ ከመፍጠር ጀምሮ አመራሩን በማሰማራትድጋፍ እና ክትትል በመደረጉ አሁን ላይ የተሻለ ተሞክሮ የተያበት የስንዴ ልማት መከናወኑን ገልጸዋል።

በመስክ ጉብኝቱ የተገኙት በዓለም ባንክ የኢትዮጵያ ዳይሬክተር ኦስማኔ ዲዎን÷ በክልሉ በተመለከቱት የስንዴ ልማት ሥራ መደሰታቸውን ገልጸዋል።

ባንኩ የማሽነሪ እና የግብዓት አቅርቦት ላይ ትኩረት በመስጠት ለክልሉ የግብርና ዘርፍ ዕድገት አስፈላጊውን እገዛ ያደርጋል ማለታቸውን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት መረጃ ያመላክታል ።

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ወርቅን ከብሔራዊ ባንክ ዋጋ በላይ ግብይት በሚፈጽሙ አካላት ላይ ህጋዊ እርምጃ ይወሠዳል፦ አቶ አሻድሊ ሀሰን***************በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ወርቅን ...
02/04/2023

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ወርቅን ከብሔራዊ ባንክ ዋጋ በላይ ግብይት በሚፈጽሙ አካላት ላይ ህጋዊ እርምጃ ይወሠዳል፦ አቶ አሻድሊ ሀሰን
***************
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ወርቅን ከብሔራዊ ባንክ ዋጋ በላይ ግብይት በሚፈጽሙ አካላት ላይ ህጋዊ እርምጃ እንደሚወሰድ የክልሉ ርዕሰ-መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሀሰን ገለጹ።

በርዕሰ-መስተዳድሩ አቶ አሻድሊ ሀሰን የተመራ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ልዑክ በመንጌ ወረዳ ተገኝቶ ወርቅ የሚመረትባቸውን አካባቢዎች የጎበኘ ሲሆን የቀጣይ አቅጣጫዎችን አስቀምጧል።

አቶ አሻድሊ ሀሰን በዚሁ ወቅት እንደገለጹት፣ በክልሉ ከዚህ ቀደም የተሻለ የወርቅ ምርት ወደ ብሔራዊ ባንክ ይገባ እንደነበር አስታውሰው፣ አሁን ህገ-ወጥ የወርቅ አዘዋዋሪዎች በመበራከታቸው ወደ ብሔራዊ ባንክ የሚገባው ምርት ቀንሷል ብለዋል።

መንግስት ወርቅን በህገ-ወጥ መንገድ ከብሔራዊ ባንክ ዋጋ በላይ በሚገዙ ግለሰቦች፣ ማኅበራት፣ ምርት በሚደብቁ አምራቾች እና ሌሎች ህገ-ወጥ አካላት ላይ የተጠናከረ ህጋዊ እርምጃ እንደሚወሰድ አቶ አሻድሊ ገልጸዋል።

በጉብኝቱ ላይ የተገኙት የ22ኛ ክፍለ-ጦር ዋና አዛዥ ሌ/ጀኔራል ሠይፈ አንጌ በበኩላቸው፣ በህገ-ወጥ የወርቅ አዘዋዋሪዎች ላይ ጠንካራ ክትትልና ቁጥጥር እንደሚደረግ ተናግረዋል።

ህገ-ወጥ የወርቅ ዝውውርን ለመቆጣጠር በቀጣይ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት በማድረግ ኦፕሬሽን ይካሄዳል ማለታቸውን ከክልሉ ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

 #ዜና ሹመትየቀድሞው የአሶሳ ከተማ አስ/ር ከንቲባ አቶ አብዱልሙኒየም አብዱልዋሂድ ለአዲሱ የአሶሳ ከተማ አስ/ር ከንቲባ ለአቶ አብዱልከሪም አብዱረሂም የስራ ርክክብ አደረጉ፡፡አቶ አብደልከሪ...
24/03/2023

#ዜና ሹመት

የቀድሞው የአሶሳ ከተማ አስ/ር ከንቲባ አቶ አብዱልሙኒየም አብዱልዋሂድ ለአዲሱ የአሶሳ ከተማ አስ/ር ከንቲባ ለአቶ አብዱልከሪም አብዱረሂም የስራ ርክክብ አደረጉ፡፡

አቶ አብደልከሪም አብደረሂም
ከዚህ ቀደም በአሶሳ ወረዳ በተለያዩ የመንግስት ኃላፊነት በአመራርነት አገልግለዋል። በአሶሳ ከተማ አስተዳደርም የን/ኢ/ትራንስፖርት መምሪያ ኃላፊ እንድሁም በከተማ አስተዳደሩ የአገልግሎት መምሪያ ኃላፊ በመሆን በከተማው የተሰሩትንና በመሰራት ላይ ያሉ ኘሮጀክቶችን ውጤታማ በሆነ መልኩ መርተዋል፤ በመምራት ላይም ናቸው።

እንኳን ለታላቁ የረመዳን ፆም አደረሳችሁ። ይህ ታላቅ የፆም እና የፀሎት ወር ባልተገባ መንገድ የተዘራው የቂም እና የጥላቻ ዘር ከሥሩ ተነቅሎ ፣ የህዝባችን የአብሮነትና የወንድማማችነት ግንኙ...
22/03/2023

እንኳን ለታላቁ የረመዳን ፆም አደረሳችሁ። ይህ ታላቅ የፆም እና የፀሎት ወር ባልተገባ መንገድ የተዘራው የቂም እና የጥላቻ ዘር ከሥሩ ተነቅሎ ፣ የህዝባችን የአብሮነትና የወንድማማችነት ግንኙነት በይቅርታና በፍቅር ታድሶ ለሀገራችንን የብልፅግናና የከፍታ ጉዞ ስኬት በአንድ ስሜት በጋራ የምንተጋበት እንዲሆን እመኛለሁ!!
ክቡር አቶ አሻደሊ ሀሰን

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ከፍተኛ አመራሮች በሀገራዊና ክልላዊ ወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ያተኮረ ውይይት በተሳካ ሁኔታ ተጠናቀቀበብልጽግና ፓርቲ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት " ...
22/03/2023

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ከፍተኛ አመራሮች በሀገራዊና ክልላዊ ወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ያተኮረ ውይይት በተሳካ ሁኔታ ተጠናቀቀ

በብልጽግና ፓርቲ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት " ድሎችን የማጽናትና ፈተናዎችን የመሻገር ወቅታዊና ታሪካዊ አመራሮች ተልዕኮ " በሚል ርዕስ ለከፍተኛ አመራሮች የተዘጋጀ የውይይት መድረክ በተሳካ ሁኔታ ተጠናቅቋል።

በመድረኩም የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ ሙህመድ፣ የኦሮሚያ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አወሉ አብዲ፣ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ-መስተዳድር ተወካይ አቶ ባበክር ኻሊፋ፣ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የብልጽግና ፓርቲ ቅርጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ኢስሃቅ አብዱልቃድር፣ የክልሉ ምክር ቤት ምክትል አፈ-ጉባኤ ወ/ሮ አለምነሽ ይባስ፣ በሲዳማ ክልል የብልጽግና ፓርቲ ቅርጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አብርሃም ማርሻሎን ጨምሮ የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

የብልጽግና ፓርቲ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ሠሞኑን ባካሄደው ውይይት ያሣለፋቸውን ውሣኔዎች፣ በወቅታዊ በሀገራዊና በክልላዊ ጉዳዮች ዙሪያ ትኩረት አድርጎ በሚካሄደው የውይይት መድረክ ላይ የክልል፣ የዞንና የወረዳ አመራሮች ተሳትፈዋል።

የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ ሙህመድ መድረኩን ባጠቃለሉበት ወቅት የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አመራሮች ለገጠማቸው ፈተና እጅ ሳይሰጡ በድል በመወጣት ለሁለንተናዊ ብልጽግና እያደረጉት ያለውን ርብርብ አድንቀዋል።

አቶ ሙስጠፌ ሙሀመድ በክልል አመራሮች በፌዴራል ደረጃ መፈታት ያለባቸው ብለው የጠየቁትን የመሰረተ-ልማት፣ የሰላምና የልማት ጥያቄዎች ለፌደራል ለማቅረብ ለይተው መያዛቸውን ገልጸዋል።

የኦሮሚያ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አወሉ አብዲ በበኩላቸው ህብረ-ብሔራዊነትን በመላበስ ለህዝቦች ሰላምና ልማት በጋራ መስራት ያስፈልጋል ብለዋል።የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ከፍተኛ አመራሮች በሀገራዊና ክልላዊ ወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ያተኮረ ውይይት በተሳካ ሁኔታ ተጠናቀቀ

በብልጽግና ፓርቲ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት " ድሎችን የማጽናትና ፈተናዎችን የመሻገር ወቅታዊና ታሪካዊ አመራሮች ተልዕኮ " በሚል ርዕስ ለከፍተኛ አመራሮች የተዘጋጀ የውይይት መድረክ በተሳካ ሁኔታ ተጠናቅቋል።

በመድረኩም የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ ሙህመድ፣ የኦሮሚያ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አወሉ አብዲ፣ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ-መስተዳድር ተወካይ አቶ ባበክር ኻሊፋ፣ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የብልጽግና ፓርቲ ቅርጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ኢስሃቅ አብዱልቃድር፣ የክልሉ ምክር ቤት ምክትል አፈ-ጉባኤ ወ/ሮ አለምነሽ ይባስ፣ በሲዳማ ክልል የብልጽግና ፓርቲ ቅርጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አብርሃም ማርሻሎን ጨምሮ የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

የብልጽግና ፓርቲ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ሠሞኑን ባካሄደው ውይይት ያሣለፋቸውን ውሣኔዎች፣ በወቅታዊ በሀገራዊና በክልላዊ ጉዳዮች ዙሪያ ትኩረት አድርጎ በሚካሄደው የውይይት መድረክ ላይ የክልል፣ የዞንና የወረዳ አመራሮች ተሳትፈዋል።

የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ ሙህመድ መድረኩን ባጠቃለሉበት ወቅት የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አመራሮች ለገጠማቸው ፈተና እጅ ሳይሰጡ በድል በመወጣት ለሁለንተናዊ ብልጽግና እያደረጉት ያለውን ርብርብ አድንቀዋል።

አቶ ሙስጠፌ ሙሀመድ በክልል አመራሮች በፌዴራል ደረጃ መፈታት ያለባቸው ብለው የጠየቁትን የመሰረተ-ልማት፣ የሰላምና የልማት ጥያቄዎች ለፌደራል ለማቅረብ ለይተው መያዛቸውን ገልጸዋል።

የኦሮሚያ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አወሉ አብዲ በበኩላቸው ህብረ-ብሔራዊነትን በመላበስ ለህዝቦች ሰላምና ልማት በጋራ መስራት ያስፈልጋል ብለዋል።

ኢትዮጵያ በሰላም ጎዳና*************** የኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች  ም/ቤት ሕወሓት ላይ አሳልፎ የነበረው የሽብርተኝነት ውሳኔን በዛሬው ዕለት አንስቷል፡፡ ታድያ ዛሬ ላይ ለተደረሰው ...
22/03/2023

ኢትዮጵያ በሰላም ጎዳና
***************

የኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት ሕወሓት ላይ አሳልፎ የነበረው የሽብርተኝነት ውሳኔን በዛሬው ዕለት አንስቷል፡፡

ታድያ ዛሬ ላይ ለተደረሰው ውሳኔ ከፕሪቶሪያ - ናይሮቢ - መቐለ- ሀላላ ኬላ ድረስ የዘለቀውና ለሰላም የተሄደው መንገድ ከፍተኛ ሚናን ተጫውቷል።

በመጀመሪያ የፌደራል መንግስት እና ህወሃት በደቡብ አፍሪካ ፕሪቶሪያ በተደረገው የሰላም ንግግር ህገ መንግስታዊ ስርዓቱን እና የኢትዮጵያን ጥቅም ባከበረ መልኩ ሃገሪቱን ወደ ቀደመ ሰላሟ ለመመለስ የሚያስችለውን የሰላም ስምምነት `የአፍሪካን ችግር በአፍሪካዊ መፍትሄ` መፍታት መርህ በማድረግ የሰላም ስምምነቱ ሂደት ተጀመረ።

ከተለያዩ አካላት የደረሱባት ጫናዎች ያልበገሯት ኢትዮጵያ የአፍሪካ ህብረት ከመሳሰሉ አህጉር በቀል ተቋማት ጋር በመሆን የውጭ ጣልቃ ገብነትን አስወግዳ የጀመረችውን የሰላም መንገድን ቀጠለች።

የፌደራል መንግስት እና የህወሓት ወታደራዊ አዛዦች በጎረቤት ሀገር ኬንያ ናይሮቢ መክረው መግባባት ላይ በመድረስ የሰላሙን ጉዞ ፍጥነት እና ደህንነቱ እንደተጠበቀ እንዲቀጥል አድርገዋል።

በተለያዩ የአፍሪካ ሃገራት የተጀመረው ሰላም የማስፈን ስምምነት ሂደት በሀገር ውስጥም በማስቀጠል ከ2 ዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ በህዝብ ተወካዮች ም/ቤት አፈ ጉባኤ ታገሰ ጫፎ የተመራ ልዑክ ወደ መቐለ አቅንቶ የሰላም ስምምነቱን አተገባበር ቃኝቶ እና በታቀደው መሰረት እንዲፈጸም በሚያስፈልጉ ጉዳዮች ዙሪያ መከረ።

ቀጥሎም የገበታ ለሀገር ፕሮጀክት አካል በሆነው ሃላላ ኬላ የሠላም ስምምነቱ ኮሚቴ አባላት ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ጋር ውይይት በማድረግ በሰላም ስምምነቱ አፈፃፀም ዙሪያ የተከናወኑ ተግባራት ግምገማ ተደርጎ በቀጣይ ትኩረት በሚያስፈልጋቸው ጉዳዮች ላይ አቅጣጫ ተቀምጧል።

ዛሬ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሕወሓት ላይ አሳልፎ የነበረው የሽብርተኝነት ውሳኔን ማንሳቱ ደግሞ ከዚህ በፊት የሄደበትን የሰላም መንገድ የሚያጠናክር እና ሀገሪቱም በቀጣይ የፈነጠቀውን የሰላም ፋና ተከትላ ፊቷን ወደ ልማት እንድትመልስ የሚያደርግ መሆኑን ኢብኮ ዘግቧል።

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ከፍተኛ አመራሮች በሀገራዊና ክልላዊ ወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ የተኮረ ውይይት ማካሄድ ጀመሩ************** የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ከፍተኛ አመራሮች በሀገራዊና ...
21/03/2023

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ከፍተኛ አመራሮች በሀገራዊና ክልላዊ ወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ የተኮረ ውይይት ማካሄድ ጀመሩ
**************

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ከፍተኛ አመራሮች በሀገራዊና ክልላዊ ወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ የተኮረ ውይይት ማካሄድ ጀመሩ።

በመድረኩም የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ ሙህመድ፣ የኦሮሚያ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አወሉ አብዲ፣ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ-መስተዳድር ተወካይ አቶ ባበክር ኻሊፋ፣ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅርጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ኢስሃቅ አብዱልቃድር፣ የክልሉ ምክር ቤት ምክትል አፈ-ጉባኤ ወ/ሮ አለምነሽ ይባስ፣ የሲዳማ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅርጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አብርሃም ማርሻሎን ጨምሮ የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

የብልጽግና ፓርቲ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ሠሞኑን ባካሄደው ውይይት ያሣለፋቸውን ውሣኔዎች፣ በወቅታዊ በሀገራዊና ክልላዊ ጉዳዮች ዙሪያ ትኩረት አድርጎ በሚካሄደው የውይይት መጅረክ የክልል፣ የዞንና የወረዳ አመራሮች አየተሣተፉ ይገኛል።

የኦሮሚያ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አወሉ አብዲ፣ የብልጽግና ፓርቲ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ሠሞኑን ባካሄደው ውይይት ያሣለፋቸውን ውሣኔዎችን የያዘ የውይይት ሠነድ እያቀረቡ ይገኛል።

የሱማሌ ክልል ፕሬዘዳንት አቶ ሙስጠፌ ሙሃመድ ፣ የኦሮሚያ ክልል ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ አወሉ አብዲ እና የስዳማ ክልል ብልፅግና ፖርቲ ቅርጫፍ   ጽ/ቤት ኃላፍ አቶ አብርሃም ማርሻሎ በትላን...
21/03/2023

የሱማሌ ክልል ፕሬዘዳንት አቶ ሙስጠፌ ሙሃመድ ፣ የኦሮሚያ ክልል ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ አወሉ አብዲ እና የስዳማ ክልል ብልፅግና ፖርቲ ቅርጫፍ ጽ/ቤት ኃላፍ አቶ አብርሃም ማርሻሎ በትላንትናው አሶሳ ከተማ ገብተዋል።

የተለያዩ የስራ ኃላፊዎች አሶሳ ህዳሴ ኤር ፖርት ማረፊያ ሲደርሱም የክልሉ ብልፅግና ፖርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ኢሳሃቅ አብዱልቃድር ጨምሮ የክልሉ ክፈተኛ አመራሮች አቀባበል አድርጎላቸዋል ።

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ም/ቤት 15ኛ መደበኛ ጉባዔውን እያካሄደ ነው የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምክር ቤት 15ኛ መደበኛ ጉባዔውን ማካሄድ ጀምሯል፡፡ምክር ቤቱ ለሁለት ቀናት በሚያካሂደው ጉባ...
06/03/2023

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ም/ቤት 15ኛ መደበኛ ጉባዔውን እያካሄደ ነው

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምክር ቤት 15ኛ መደበኛ ጉባዔውን ማካሄድ ጀምሯል፡፡

ምክር ቤቱ ለሁለት ቀናት በሚያካሂደው ጉባዔ በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ እንደሚያሳልፍ ይጠበቃል፡፡

ጉባዔው የክልል ምክር ቤት አባላት አሠራርና ሥነ-ምግባር ማሻሻያ ደንብን፣ የአስተዳደር ሥነ-ሥርዓት ረቂቅ አዋጅን እንዲሁም የጠበቆች አስተዳደር ማሻሻያ ረቂቅ አዋጅን መርምሮ እንደሚያፀድቅ ይጠበቃል፡፡

የተጓደሉ የምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴ አባላትን ማሟላትና የዳኞችን ሹመት መርምሮ ማጽደቅም የጉባዔው አጀንዳዎች መሆናቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

 #ሰበር ዜና በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን አባቶች መካከል ተፈጥሮ የነበረው አለመግባባት በንግግርና ውይይት ተፈታ።
15/02/2023

#ሰበር ዜና

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን አባቶች መካከል ተፈጥሮ የነበረው አለመግባባት በንግግርና ውይይት ተፈታ።

ሰበር ዜና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ያጋጠማትን አስተዳደራዊ ችግር ለመፍታት ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በተገኙበት ውይይት ተካሂዷል፡፡ በውይይቱም አባቶች ችግሩን በሕግ  እና ...
10/02/2023

ሰበር ዜና

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ያጋጠማትን አስተዳደራዊ ችግር ለመፍታት ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በተገኙበት ውይይት ተካሂዷል፡፡ በውይይቱም አባቶች ችግሩን በሕግ እና ስርዓት በውይይት እንዲፈቱ ከስምምነት ላይ ተደርሷል፡፡

በክልሉ ለመጀመሪያ ጊዜ በተከናወነው የስንዴ ልማት የተገኘው ውጤት በቀጣይ በስፋት ለመሥራት የሚያነሣሣ ነው፦ ርዕሰ-መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሀሰን******************በቤኒሻንጉል ገገጉ...
10/02/2023

በክልሉ ለመጀመሪያ ጊዜ በተከናወነው የስንዴ ልማት የተገኘው ውጤት በቀጣይ በስፋት ለመሥራት የሚያነሣሣ ነው፦ ርዕሰ-መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሀሰን
******************
በቤኒሻንጉል ገገጉሙዝ ክልል ለመጀመሪያ ጊዜ በተከናወነው የስንዴ ልማት የተገኘው ውጤት በቀጣይ በስፋት ለመሥራት የሚያነሣሣ መሆኑን ርዕሰ-መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሀሰን ተናገሩ።

ርዕሰ-መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሀሰን፣ በክልሉ በ2015/16 ለሚከናወነው የመኸር ስንዴ ልማት በተዘጋጀው ንቅናቄ ዙሪያ ከክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ጋር ምክክር አካሂደዋል።

በንቅናቄ ሰነድ ግምገማው ላይ ምክትል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ጌታሁን አብዲሣ፣ የክልሉ ብልፅግና ፖርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ኢስሃቅ አብዱልቃድርን የክልሉ ከፍተኛ አመራሮችና ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በ2015/16 የመኸር እርሻ 50 ሄክታር መሬት በስንዴ በዘር ለመሸፈን መታቀዱ ተገልጿል።

ከመኸር የምርት ዘመኑ በዘር ለመሸፈን የታቀደውን የስንዴ ሠብል በማሣካት 2 ሚሊዮን ኩንታል የስንዴ ምርት ለመሰብሰብ መታቀዱም ተመልክቷል።

የክልሉ ርዕሰ-መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሀሰን፣ መንግስት የአርሶ አደሩን በስንዴ ልማት እና በሌማት ትሩፋት በማሣተፍ የምግብ ዋስትናን በዘላቂነት ለማረጋገጥ ትኩረት አድርጎ እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል።

በክልሉ በዘንድሮው የመኸር ወቅት በአብዛኛዎቹ ወረዳዎች ለመጀመሪያ ጊዜ በተከናወነው የስንዴ ልማት ተስፋ ሠጪ ብቻ ሣይሆን አበረታች ውጤት መገኘቱን ጠቁመው፣ በቀጣዩ የምርት ዘመን ስንዴን በስፋት ለማልማት ዕቅድ መያዙን አስረድተዋል።

ለውጤታማነቱም ከአመራሩ ጀምሮ ሁሉም በቁርጠኝነት እንዲሰራ አሣስበዋል።

የክልሉ ግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ባበክር ኻሊፋ፣ በክልል ደረጃ ለመጀመሪያ ጊዜ በ2014/15 የመኸር እርሻ በ7 ሺህ 833 ሄክታር መሬት ወ 249 ሺህ 393 ኩንታል ስንዴ ምርት ለመሠብሠብ ጥረት መደረጉን ተናግረዋል።

የ2014/15 የመኸር እርሻ ስንዴ ልማት ጥሩ ልምድ የተወሰደበት መሆኑን የተናገሩት አቶ ባበክር፣ በቀጣዩ የ2015/16 የመኸር ወቅት ስንዴን በሁሉም ዞኖችና ወረዳዎች በሰፊው ለማልማት መታቀዱን ገልጸዋል።

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በ2015/16 የመኸር እርሻ 50 ሄክታር መሬት በስንዴ በዘር በመሸፈን 2 ሚሊዮን ኩንታል ምርት ለመሰብሰብ ታቅዷል ብለዋል።

ዕቅዱን ለማሣካት የዘር፣ የማዳበሪያ፣ የፀረ-ተባይ ኬሚካል አቅርቦትን ጨምሮ በንቅናቄና ላይ ትኩረት ተደርጎ እንደሚሠራም ጠቁመዋል።

በክልሉ በ2015 ዓ.ም ባለፉት ስድስት ወራት ከ1 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ መሠብሠቡ ተገለጸ****************(አሶሳ፣ ጥር 30/2015 ዓ.ም) በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በ2015 ዓ.ም...
07/02/2023

በክልሉ በ2015 ዓ.ም ባለፉት ስድስት ወራት ከ1 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ መሠብሠቡ ተገለጸ
****************

(አሶሳ፣ ጥር 30/2015 ዓ.ም) በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በ2015 ዓ.ም ያለፉት ስድስት ወራት ከ1 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ መሠብሠቡ ተገለጸ።

በበጀት አመቱ ግማሽ ዓመት ለመሰብሰብ ከታቀደው ውስጥ 1 ቢሊዮን 273 ሚሊዮን 197 ሺህ 387 ብር ውስጥ የዕቅዱ 85 በመቶ መሰብሰብ መቻሉ ተገልጿል፡፡

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የ2015 ዓ.ም የ6 ወራት አፈጻጻም በተገመገመበት ወቅት ባለፉት ስድስት ወራት ብቻ 1 ቢሊዮን 077 ሚሊዮን 330 ሺህ 361 ብር ገቢ መሠብሠቡን አስታውቋል።

ይህም ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ372 ሚሊዮን 504 ሺህ 850 ብር ወይም የ53 በመቶ ብልጫ እንዳለው ያሳያል ተብሏል፡፡

ገቢው ከቀጥታ ታክስ፣ቀጥታ ካልሆነ ታክስ፣ታክስ ካልሆኑ ገቢዎች፣ ከወረዳዎችና ከከተሞች የተሠበሠበ መሆኑ መገለጹን የክልሉ ኮሚኒኬሽን መረጃ ያሳያል፡፡

01/02/2023

የሃይማኖት ተቋማት ከ3 ነገሮች እራሳቸውን ቢጠብቁ ከብዙ ችግር ነፃ ይሆናሉ።

"የሀገራችንን ብልጽግና ለማረጋገጥ መነጋገር እና በጋራ መቆም ይጠበቅብናል"፦ ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሀሰን*******************(አሶሳ፣ ጥር 20/2015 ዓ.ም) ሀገራችን የጀ...
28/01/2023

"የሀገራችንን ብልጽግና ለማረጋገጥ መነጋገር እና በጋራ መቆም ይጠበቅብናል"፦ ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሀሰን
*******************

(አሶሳ፣ ጥር 20/2015 ዓ.ም) ሀገራችን የጀመረችውን የብልጽግና ጉዞ ለማረጋገጥ መነጋገር እና በጋራ መቆምን ያስቀደመ ሥራ መሥራት እንደሚገባ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሀሰን ተናገሩ።

በሀገራዊና ክልላዊ የሠላምና የልማት ጉዳዮች ላይ ያተኮረ የምክክር መድረክ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አሶሳ ከተማ እየተካሄደ ነው።

በምክክር መድረኩም የሀገር ሽማግሌዎች፣ ታዋቂ ግለሰቦች እና የተለያዩ ባለድርሻ አካላት ተሣትፈዋል።

በመድረኩም የክልሉ ርዕሰ-መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሀሰን፣ የውኃ እና ኢነርጂ ሚኒስትር ዶ/ር ኢ/ር ሀብታሙ ኢተፋ፣ የመከላከያ ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ማርታ ሊዊጂን ጨምሮ የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል።

የኢፌዴሪ ውኃ እና ኢነርጂ ሚኒስትር ዶ/ር ኢ/ር ሀብታሙ ኢተፋ፣ ኢትዮጵያ የጀመረችው የብልጽግና ጉዞ በተለያዩ ፈተናዎች ውስጥ እያለፈ የመጣ መሆኑን ተናግረዋል።

በዚህ የለውጥ ጉዞ እንድንከፋፈል በሚፈልጉ ኃይሎች የመጡብንን ፈተናዎችን በመሻገር አስደናቂ ስኬቶችን ማስመዝገብ ችለናል ብለዋል።

ጠላቶቻችን አሁንም ከጀመርነው የብልጽግና ጉዞ ወደኋላ እንድመለስ ለማድረግ የሚዘረጉትን መልከ-ብዙ ፈተና በጋራ መሻገር እንደሚያስፈልግ አስረድተዋል።

ህዝቡ ከመቼውም ጊዜ በላይ በሀገሩ ሠላም እና ልማት ላይ በጋራ ሊቆም እንደሚገባ ሚኒስትሩ ተናግረዋል።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ማርታ ሊዊጅም፣ ባለፉት ዓመታት እንዳንግባባ ሠፊ ሥራ ሲሠራብን መቆየቱን አስታውሰው፣ አሁንም የጽንፈኝነት ፈተና አለብን መቀጠሉን ገልጸዋል።

እነዚህን ፈተናዎች ቀጋራ ማረጋጋት ከቻልን በፖለቲካው፣ በኢኮኖሚው፣ በግብርናው እና በሌሎችም ዘርፎች የጀመርናቸው ሪፎርሞች የበለጠ ውጤታማ ይሆናሉ ብለዋል።

የሚያጋጥሙንን ተደጋጋሚ ፈተናዎች በጋራ በመሻገር ከፍታችንን ማረጋገጥ ይጠበቅብናል ያሉት ወ/ሮ ማርታ፣ የችግሩን መጠን በአግባቡ መገንዘብ እና ለመፍትሔው ርብርብ ማድረግ ከሁሉም እንደሚጠበቅ ተናግረዋል።

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ሕዝብ፣ በድንበር በኩል ያለውን ፈተና በመመከት ሀገር እንድትጠበቅ የበኩሉን ድርሻ አየተወጣ እንደሚገኝ ጠቅሰው፣ ይህንኑ አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አቅርበዋል።

የክልሉ ርዕሰ-መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሀሰን፣ ሀገራችን የጀመረችውን የብልጽግና ጉዞ ለማረጋገጥ መነጋገር እና በጋራ መቆም እጅግ አስፈላጊ መሆኑን ተናግረዋል።

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በሀገራዊ ለውጡ እኩል የመወሠን ህገ-መንግስታዊ መብቱ መረጋገጡን ጠቅሰዋል።

ከለውጡ ጎን ለጎን የተስተዋለው አደገኛ የጽንፈኝነት አስተሣሰብ በተለያዩ አካባቢዎች ግጭቶች እንዲከሠቱ እና ከፍተኛ ጉዳት እንዲደርስ ማድረጉን ገልጸዋል።

አስቸጋሪ የነበረውን የጸጥታ ችግር ሕዝቡን ያሣተፈ ሥራ በመሥራት ጥበብ በተሞላበት መንገድ በመፍታት ሠላማዊ ሁኔታ ተፈጥሯል ብለዋል።

ርዕሰ-መስተዳድሩ፣ ሠላም በማምጣት ሂደት ለተሣተፉ የተለያዩ ባለድርሻ አካላት ምስጋና አቅርበዋል ሲል የክልሉ ኮሚኒኬሽን ዘግቧል።

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል እየተከናወነ ያለው የበጋ መስኖ ስንዴ ልማት አበረታች መሆኑን ነው - አቶ አሻድሊ ሀሰን******************የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አሻድሊ...
25/01/2023

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል እየተከናወነ ያለው የበጋ መስኖ ስንዴ ልማት አበረታች መሆኑን ነው - አቶ አሻድሊ ሀሰን
******************

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አሻድሊ ሀሰን በመተከል ዞን እየለማ ያለውን የበጋ መስኖ ስንዴ ተዟዙረው ጎብኝተዋል።

አቶ አሻድሊ በመተከል ዞን፣ ፓዊ ወረዳ የተደራጁ ወጣቶች እያለሙት ያለውን የበጋ መስኖ ስንዴ የጎበኙ ሲሆን፤ ስራው ለሌሎች ተሞክሮ እንደሚሆን በዚሁ ወቅት ገልጸዋል።

የአርሶ አደሮችን ዘላቂ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እየተከናወነ ያለውን የልማት እንቅስቃሴ አጠናክሮ ለማስቀጠል አስፈላጊው ድጋፍና ክትትል እንደሚደረግ አክለው ገልጸዋል።

በመተከል ዞን፣ ፓዊ ወረዳ የስራ አጥ ወጣቶችን ቁጥር ለመቀነስ 90 የሚደርሱ ወጣቶችን በማደራጀት በበጋ መስኖ ስንዴ ስራ ተሰማርተው ዘጠኝ ሄክታር መሬት እያለሙ ነው።

የሌሎች አርሶ አደሮችን ያለውን ጨምሮ በወረዳው 60 ሄክታር መሬት በበጋ መስኖ ስንዴ እየለማ መሆኑ በጉብኝቱ ወቅት ተገልጿል።

በክልሉ በመጀመሪያ ዙር ለማልማት ከታቀደው ውስጥ 2 ሺህ 700 ሄክታር መሬት መከናወኑን የሚበረታታ ነው ተብሏል።

በሌሎች አካባቢዎች ያልለሙ መሬቶችን ለማልማት ስራ አጥ ወጣቶችን በማደራጀት ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ ይገባል ብለዋል አቶ አሻድሊ።

አርሶ አደሩ በዓመት ሶስት ጊዜ በማምረት የምግብ ዋስትናውን ከማረጋገጥ ባለፈ የኢኮኖሚ አቅምን ለማሳደግ ርብርብ እያደረገ እንደሆነ ተገልጿል።

አርሶ አደሮቹ ላነሱት የውሃ ፓምፕ ጄነሬተር እና የነዳጅ አቅርቦት ጥያቄም ርዕሰ መስተዳድሩ ክልሉ በተቻለ መጠን ምላሽ ይሰጣል ማለታቸውን ከመተከል ዞን ኮሙኒኬሽን መምሪያ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

አቶ አሻድሊ ሀሰን በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመልሶ-ማቋቋም ፕሮጀክትን በይፋ አስጀመሩ ********************በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በጸጥታ ችግር የተጎዱ መሠረተ-ልማቶችን መልሶ ...
25/01/2023

አቶ አሻድሊ ሀሰን በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመልሶ-ማቋቋም ፕሮጀክትን በይፋ አስጀመሩ
********************

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በጸጥታ ችግር የተጎዱ መሠረተ-ልማቶችን መልሶ ለማማቋቋም የሚያስችል ፕሮጀክት በርዕሰ-መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሀሰን ይፋ ሆነ።

የመጀመሪያ ምዕራፍ የመልሶ-ማቋቋም ፕሮጀክቱ የክልሉ ርዕሰ-መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሀሰንን ጨምሮ ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት በመተከል ዞን፣ ማንዱራ ወረዳ፣ ፎቶማንጀሪ ቀበሌ ነው ይፋ የተደረገው።

ርዕሰ መስተዳድር አሻድሊ ሀሰን ፕሮጀክቱን በይፋ ባስጀመሩበት ወቅት፥ የክልለ መንግስት ወደቀዬአቸው የተመለሱ ዜጎችን በዘላቂነት ለማቋቋም እና የተጎዱ መሠረተ-ልማቶችን መልሶ-ለማቋቋም በጥናት ላይ የመሠረተ ሥራ አየሠራ መሆኑን ተናግረዋል።

ፕሮጀክቱ በተያዘለት ጊዜ እንዲጠናቀቅ ሁሉም የበኩሉን ሊወጣ ይገባል ያሉት አቶ አሻድሊ፤ በቀጣይ በሌሎች አካባቢዎች መሠል ሥራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገልጸዋል።

የክልሉ ፋይናንስ ቢሮ ምክትል ሃላፊ ወይዘሮ ትዕግስት ዲቢሳ፥ በክልሉ የወደሙ ተቋማትንና ዜጎችን በዘላቂነት ለማቋቋም 155 ሚሊዮን ብር መነሻ በጀት መያዙን ገልጸዋል።

በመጀመሪያው ዙር የፕሮጀክቱ ትግበራ ማንዱራ፣ ቡለንና ሰዳል ወረዳዎች ተደራሽ የሚደረጉ ሲሆን፤ መሰረታዊ አገልግሎት የሚሰጡ ተቋማትን ለማደስና በአዲስ መልክ ለመገንባት እንደሚሠራ ሃላፊዋ ጨምረው ተናግረዋል።

በተጨማሪም ፕሮጀክቱ ህብረተሰቡን በስነ-ልቦና የማጠናከር እና በኑሮ በዘላቂነት የማቋቋም ዓላማ እንዳለው ጠቅሰዋል።

የአምስት ዓመት ቆይታ የሚኖረው ፕሮጀክቱ ከዓለም ባንክ በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ እንደሚተገበር ተገልጿል።

በርዕሰ መስተዳድር አሻድሊ ሀሰን የተመራው የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ልዑክ በጸጥታ ችግሩ ጉዳት ደርሶባቸው መልሰው የተገነቡ ተቋማትን ተዘዋውሮ መጎብኘቱን ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

አቶ በረከት ስምኦን ከእስር ተፈቱ ላለፉት አራት ዓመታት በእስር ላይ የቆዩት አቶ በረከት ስምኦን “የአመክሮ ጊዜያቸውን ጨርሰው” ዛሬ ረቡዕ ጥር 17፤ 2015 ጠዋት ከባህር ዳር ማረሚያ ቤት...
25/01/2023

አቶ በረከት ስምኦን ከእስር ተፈቱ

ላለፉት አራት ዓመታት በእስር ላይ የቆዩት አቶ በረከት ስምኦን “የአመክሮ ጊዜያቸውን ጨርሰው” ዛሬ ረቡዕ ጥር 17፤ 2015 ጠዋት ከባህር ዳር ማረሚያ ቤት መፈታታቸውን ጠበቃቸው ህይወት ሊላይ ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናገሩ። (ኢትዮጵያ ኢንሳይደር)

Address


Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Waza Daily posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

  • Address
  • Alerts
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share