ETHO news

ETHO news Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from ETHO news, Media/News Company, .

ህፃን ልጁ ላይ የግብረሰዶም ወንጀል የፈፀመው ግለሰብ በፅኑ እስራት እንዲቀጣ ተወሰነበት፡፡ተከሳሽ (ለተጎጂው ሲባል ስሙ ያልተጠቀሰ) የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የወንጀል ሕግ አንቀፅ 631/1/ለ ስር የተ...
22/09/2021

ህፃን ልጁ ላይ የግብረሰዶም ወንጀል የፈፀመው ግለሰብ በፅኑ እስራት እንዲቀጣ ተወሰነበት፡፡

ተከሳሽ (ለተጎጂው ሲባል ስሙ ያልተጠቀሰ) የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የወንጀል ሕግ አንቀፅ 631/1/ለ ስር የተመለከተውን ድንጋጌ በመተላለፍ በጥቅምት እና ህዳር ወር 2011 ዓ.ም በተለያዩ ቀናት በአቃ/ቃ/ክ/ከተማ ወረዳ 09 ልዩ ቦታዉ ኮዬ ፈጬ ኮንዶሚኒየም ዉስጥ ዕድሜዉ 7 ዓመት የሆነዉን የራሱን ልጅ የግብረሰዶም ጥቃት ወንጀል የፈፀመበት በመሆኑ በፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት አቃቂ ቃሊቲ ምድብ ወንጀል ችሎት በአቃቤ ህግ ክስ ቀርቦባታል፡፡

ተከሳሽ በችሎት ቀርቦ የእምነት ክህደት ቃሉን ሲጠየቅ ድርጊቱን አልፈፀምኩም በማለት ክዶ በመከራከሩ የዓቃቤ ህግ የሰው እና የሰነድ ማስረጃ ቀርበው ተከሳሽ ወንጀሉን ስለመፈፀሙ እንደክስ አመሰራረቱ ያስረዱ በመሆኑ እንዲከላከል ችሎቱ ብይን ቢሰጥም ተከሳሽ ባቀረባቸዉ የሰነድና የሰዉ መከላከያ ማስረጃዎች መከላከል ባለመቻሉ ፍ/ቤቱ መዝገቡን መርምሮ የጥፋተኝነት ፍርድ ሰጥቶ ነበር ለመስከረም 14 ቀን 2013 ዓ.ም ቀጠሮ ይዞ መዝገቡ ያደረው፡፡

በዚህም መሰረት ፍርድ ቤቱ ከላይ በተገለጸው እለት በዋለው ችሎት ተከሳሽ በአስራ ስድስት (16) ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ወስኗል፡፡

ምንጭ፦ የኢፌዴሪ ጠቅላይ አቃቤ ህግ

https://t.me/ETHOfast
https://t.me/ETHOfast

news Yh channel Tamgn ena arif arif merja emnakerbebt channel nw

218 ኩንታል የህወሓት ቡድን አደንዛዥ ዕጽ ተያዘ !የህወሓት ቡድን ሊጠቀምበት የነበረ 218 ኩንታል አደንዛዥ ዕጽ በሁመራ ግንባር ተይዞ እንዲቃጠል መደረጉን የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ሰሜን ...
22/09/2021

218 ኩንታል የህወሓት ቡድን አደንዛዥ ዕጽ ተያዘ !

የህወሓት ቡድን ሊጠቀምበት የነበረ 218 ኩንታል አደንዛዥ ዕጽ በሁመራ ግንባር ተይዞ እንዲቃጠል መደረጉን የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ሰሜን ዳይሬክቶሬት ዲቪዥን 3 ኃላፊ ኮማንደር እንየው አለባቸው ገለጹ፡፡

አደንዛዥ ዕጹ የተያዘው ከሁመራ ወደ ሱዳን ሊሻገርና ተቀምሞ በዱቄት መልክ ለሽብር ቡድኑ አባላት መልሶ ለማሰራጨት ታስቦ እንደነበር ኃላፊው ተናግረዋል፡፡

አደንዛዥ ዕጽ የተያዘው በተለያዩ ጊዜያት በኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስና በሌሎች የጸጥታ አካላት እንዲሁም በአካባቢው ማህበረሰብ ጥብቅ ቁጥጥርና ክትትል ነው ተብሏል።

የአሸባሪው የህወሓት ቡድን በኢትዮጵያ ላይ የቃጣውን ክህደትና የዘር ጭፍጨፋ ለማባባስ እንደትልቅ መሳሪያ እንደሚጠቀምበት ኃላፊው ጠቅሰው በዕጽ ዝውውር ተግባር ላይ በተሳተፉ አካላት ላይ እርምጃ እየተወሰደባቸው እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡

ከሱዳን ወደ ሁመራ በተናጠል አደዛዥ ዕጽ ይዘው ሰርገው ለመግባት እየሞከሩ ያሉ አካላትም በቁጥጥር ስር እየዋሉም ነው ብለዋል፡፡

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ፣ የሀገር መከላከያ ሰራዊትና ከአማራ ክልል ልዩ ሃይል ጋር በጋራ የድንበር አካባቢውን በንቃት በመጠበቅ ላይ እንዳሉም ብስራት ሬድዮ ከኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ያገኘው መረጃ ያመላክታል።

https://t.me/ETHOfast
https://t.me/ETHOfast

news Yh channel Tamgn ena arif arif merja emnakerbebt channel nw

Address


Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ETHO news posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

  • Address
  • Alerts
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share