አንጎት ፕረስ ANGOT PRESS

  • Home
  • አንጎት ፕረስ ANGOT PRESS

አንጎት ፕረስ ANGOT PRESS ወቅታዊ የሀገር ውስጥና የውጭ ሀገር መረጃዎች በፍጥነት እንዲደርስዎ LIKE ...SHARE ....FOLLOW ያድርጉን።
@አንጎት ፕረስ ANGOT PRESS

ማርከህ ታጠቅ!እንዳታቃጥል! በዚህ ሰዓት ጎንደር ከተማ  የአማራ ፋኖ በጎንደር ቴድሮስ ብርጌድ  በመከላከያ ስም የሚንቀሳቀሰውን የአብይ ጦር እና መኪና ማርኮታል።
02/08/2023

ማርከህ ታጠቅ!
እንዳታቃጥል!

በዚህ ሰዓት ጎንደር ከተማ የአማራ ፋኖ በጎንደር ቴድሮስ ብርጌድ በመከላከያ ስም የሚንቀሳቀሰውን የአብይ ጦር እና መኪና ማርኮታል።

የላስታ አውራጃ አሳምነው ብርጌድ አማራ ፋኖ አስከተማን ተቆጣጠረ︎‼በዛሬው ዕለት አስከተማ እና መቄትን ሙሉ በሙሉ በፋኖ ላስታ አውራጃ አሳምነው ብርጌድ ፋኖዎች ቁጥጥር ስር መሆኑ ተሰምቷል።
29/07/2023

የላስታ አውራጃ አሳምነው ብርጌድ አማራ ፋኖ አስከተማን ተቆጣጠረ︎‼

በዛሬው ዕለት አስከተማ እና መቄትን ሙሉ በሙሉ በፋኖ ላስታ አውራጃ አሳምነው ብርጌድ ፋኖዎች ቁጥጥር ስር መሆኑ ተሰምቷል።

"በራሳችን አፈጉባኤ ታፍነናል። ወይ አፈጉባኤያችን ጭራሽኑ ከአድዋ፣ ወይ ከበሻሻ በሆነች። ከእኛ ባልሆነች።" - አቶ ዮሐንስ ቧያለውአለመታደል ሆኖ የአማራን ችግር እንዳንመክር፣ በአማራ ምክር...
22/07/2023

"በራሳችን አፈጉባኤ ታፍነናል። ወይ አፈጉባኤያችን ጭራሽኑ ከአድዋ፣ ወይ ከበሻሻ በሆነች። ከእኛ ባልሆነች።" - አቶ ዮሐንስ ቧያለው

አለመታደል ሆኖ የአማራን ችግር እንዳንመክር፣ በአማራ ምክር ቤት አፈጉባኤ ተከልክለናል። ወይ አፈጉባኤዋ ጭራሽኑ ከአድዋ፣ ወይ ከበሻሻ በሆነች። ከእኛ ባልሆነች። የጊዜ ጉዳይ ካልሆነ ሁላችንንም ይገድሉናል። ለስልጣናችን፣ ለህልውናችን የተዋደቀውን ልዩ ሀይል አፈረሳችሁት። ኢትዮጵያን እናፈርሳታለን፣ አማራን እናዋርዳለን ያሉት ጀነራሎች በነፃነት በሚንፈላሰሱባት ሀገር፣ እያነከሰ ያዋጋው ጀነራል ህክምና ተከለከለ። ለአማራ የቆሙ አመራሮች ተገደሉ፣ ተባረሩ። ምን ቀረን?

ጠላቶቻችን በአንድነት ዘምተውብናል። ክልሉን ልክ እናስገባዋለን በማለት ተነስተዋል። መከላከያ ያለ ክልሉ ፍቃድ፣ አማራን እያተራመሰ ነው። እኛስ?

አሁኑኑ መፍትሔ እናስቀምጥ። በዚህ ምክር ቤት በአማራ ክልል የተፈጠረውን ችግር እና መፍትሔ የሚያጠና ቡድን ይዋቀር።

29/06/2023

በዘንድሮው የማዳበሪያ እጦትና የዋጋ ውድነት ምክንያት በሚቀጥለው አመት አንድ ኩንታል ጤፍ ከ15,000 ብር በላይ ይሸጣል።

ታሪክ ራሱን እየደገመ ነው። በሊቪያ 2007 ዓ/ም  በኢትዮጵያ 2015 ዓ/ም
05/06/2023

ታሪክ ራሱን እየደገመ ነው።
በሊቪያ 2007 ዓ/ም
በኢትዮጵያ 2015 ዓ/ም

"ያሳደገችኝን ቤተ ክርስቲያንን  የከፈለ  አባቶችንና ምእመናንን ያሳዘነ ድርጊት በመሆኑ ይቅርታ እጠይቃለሁ "መጋቤ ሐዲስ ቆሞስ አባ ጸጋ ዘአብ አዱኛ በብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የተመራው "የኤጲስ...
25/01/2023

"ያሳደገችኝን ቤተ ክርስቲያንን የከፈለ አባቶችንና ምእመናንን ያሳዘነ ድርጊት በመሆኑ ይቅርታ እጠይቃለሁ "
መጋቤ ሐዲስ ቆሞስ አባ ጸጋ ዘአብ አዱኛ
በብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የተመራው "የኤጲስ ቆጶሳት ሹመት" ሕገ ቤተ ክርስቲያን የጣሰ በመሆኑ ከሕገ ወጥ ቡድኑ መውጣታቸውን መጋቤ ሐዲስ ቆሞስ አባ ጸጋ ዘአብ አዱኛ ገለጹ።
አባ ጸጋ ዘአብ "አቡነ ኤጲፋንዮስ" በሚል በምሁር ኢየሱስ ገዳም "የበላይ ሓላፊ ጳጳስ" በሚል ተሹመው የነበረ ሲሆን በዛሬው ዕለት ምሽት ለመገናኛ ብዙኃን በሰጡት መግለጫ "ያሳደገችኝን ቤተ ክርስቲያንን የከፈለ አባቶችንና ምእመናንን ያሳዘነ ድርጊት በመሆኑ የይቅርታ ደብዳቤ ማስገባታቸውን አሳውቀዋል።
ለቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ በእንባ የይቅርታ ደብዳቤያቸውን አስገብተዋል።

አክሱምን ያነፁ እጆች ይሄን የምስጥ ኩይሶ ሳያዩ እንኳንም አረፉ!😭
21/01/2023

አክሱምን ያነፁ እጆች ይሄን የምስጥ ኩይሶ ሳያዩ እንኳንም አረፉ!😭

ዓለም የጉልበተኞች ናትፈሪዎችን አታስተናግድም።ፋኖ አርበኛ ዘመነ ካሴ ።መተማመኛችን ከላይ ፈጣሪ  ከዚህ መለስ ዋስትናችን ክንዳችን ነው ።ዘመነ-ነት ይፋፋም ፤ፋኖነት ይለምልም ‼️ዘመነ ካሴ ...
25/12/2022

ዓለም የጉልበተኞች ናት
ፈሪዎችን አታስተናግድም።
ፋኖ አርበኛ ዘመነ ካሴ ።

መተማመኛችን ከላይ ፈጣሪ ከዚህ መለስ ዋስትናችን ክንዳችን ነው ።ዘመነ-ነት ይፋፋም ፤ፋኖነት ይለምልም ‼️

ዘመነ ካሴ የአዲሱ አማራ ትውልድ የትግል ምልክት ነው ።
አዲስ ትውልድ ፣አዲስ አስተሳስብ
ክፋት ለማንም ፣በጎነት ለሁሉም ።

አማራነት ያሸንፋል ።

መምህርትና ጋዜጠኛ መስከረም አበራ በድጋሜ ታፈነች!ዛሬ 04/04/2015 መምህርት እና ጋዜጠኛ መስከረም አበራ በድጋሚ በአዲስ አበባ በተለምዶ መጠሪያው ሃያ ሁለት አከባቢ ከቀኑ 10:30 ላይ...
13/12/2022

መምህርትና ጋዜጠኛ መስከረም አበራ በድጋሜ ታፈነች!
ዛሬ 04/04/2015 መምህርት እና ጋዜጠኛ መስከረም አበራ በድጋሚ በአዲስ አበባ በተለምዶ መጠሪያው ሃያ ሁለት አከባቢ ከቀኑ 10:30 ላይ በፖሊስ ታፍና እንደተወሰደች ተገልጿል።
ፖሊሶቹም ወደ ፌደራል ወንጀል ምርመራ እንደሚወስዷት እንደነገሩት ባለቤቷ አቶ ፍፁም በፌስ ቡክ ገፁ ማጋራቱን ሮሃ ሚዲያ ዘግቧል።

10/12/2022

በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ከማሽ ዞን ሚዥጋ ወረዳ መንደር 42/ተንካራ ላይ ታህሳስ 1/2015 ከረፋዱ 4 ሰዓት ጀምሮ ከአርጆ ጉደቱ በመነሳት ወረራ የፈጸመው መንግስት መሩ የኦሮሚያ ልዩ ኃይል እና አሸባሪው ኦነግ ሸኔ ሰላማዊ አማራዎችን በጅምላ በማጥቃት መኖሪያ ቤቶችን እያቃጠለ እና እየዘረፈ ነው።
ዘር ማጥፋቱና ወረራው ቀጥሏል!

@ዓባይ ዘውዱ

07/12/2022

የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በኦሮሞ ልዩሃይ የሚያስፈጃቸው አንድም ለወትሮው "ነፍጠኛ"፣"ሰፋሪ" ወዘተ ሲል የሚጠራቸው በወለጋ የሚኖሩ ያልታጠቁ አማሮችን ነው፤ ሁለትም ራሱ ሚሊሽያ ሲል ያስታጠቃቸውን በኋላ ሲያስበው አማራ መሆናቸው ትዝ ያለው ንፁሃን አማሮች ናቸው! ይህ ሰላሳ ዘረኛ ካድሬ እግሩ እስኪቀጥን እየተመላለሰ በፌስቡክ ገፁ ስላወራ የሚቀየር ሃቅ አይደለም!

ለዜጎቹ ጥበቃ የማያደርግ መንግሥት ከገዳዮቹ እና ጨፍጫፊዎች የበለጠ ጥፋተኛ ነው። ወለጋ የአማራ መታረጃ ቄራ ከሆነ ዓመታት ተቆጥረዋል። ማፈናቀሉና ጭፍጨፋው የት፣እንዴት፣ መቼና በማን  እንደ...
05/12/2022

ለዜጎቹ ጥበቃ የማያደርግ መንግሥት ከገዳዮቹ እና ጨፍጫፊዎች የበለጠ ጥፋተኛ ነው። ወለጋ የአማራ መታረጃ ቄራ ከሆነ ዓመታት ተቆጥረዋል። ማፈናቀሉና ጭፍጨፋው የት፣እንዴት፣ መቼና በማን እንደሚፈጸም ይታወቃል።

እንዲህ ዓይነት የጭፍጨፋና የዘር ማጥፋት ድርጊት ነጋ ጠባ እየተፈጸመ፣ የፌደራል መንግሥት "ዝንብ የሞተበት" እንኳን አይመስልም።

እንዲህ ዓይነት ጨፍጫፊ ወንበደዎች የሚፈጽሙትን ጥቃት የመከላከያ ዘዴው የታወቀ ነው። ነገር ግን መንግሥት ሲሞክረው እንኳን አይታይም።

እንዲህ ዓይነት ጭፍጨፋ ሊከላከሉት የሚከብድ፣ ሊቀለብሱት የሚያዳግት የመተላለቅ መዘዝ እንደሚወልድ ልብ ሊባል ይገባል። ይሔ ተፈጥሯዊ ሒደት ነው። የመንግሥት በዝምታ የጭፍጨፋው ተባባሪነቱ፣ ተጨማሪ እና የባሰ ጥፋትና እልቂት እንደሚጠራ መታወቅ አለበት።


ዜጋውን ከጨፍጫፊ የማይጠብቅና የማይታደግ መንግሥት ከጨፍጫፊው የበለጠ ተጠያቂ ነው። ጥበቃ አለማድረግ ከጨፍጫፊው የባሰ ጨካኝነት ነው።

ነው ወይስ፥ ወለጋ የሚኖረው አማራ ሰው አይደለም እንዴ? ኢትዮጵያዊ አንደለም እንዴ? መንግሥት ከወለጋ የባሰ ምንም አጀንዳ ሊኖረው አይገባም። ለሌላ አጀንድ ቅድሚያ መስጠት ሲበዛ ጭፍጨፋውን መደገፍ ነው፤ በጣም ካነሰ እልቂቱና ጭፍጨፋውን በማረሳሳት መተባበር ነው።

04/12/2022

መቆጣት ያልቻለ ህዝብ ዕጣ ፈንታው መቀጣት ነው።

በኦሮሚያ በየቀኑ የሚገደሉ አማራዎች ገዳያቸው የአማራ መንግስትና የአማራ ህዝብ ነው።
03/12/2022

በኦሮሚያ በየቀኑ የሚገደሉ አማራዎች ገዳያቸው የአማራ መንግስትና የአማራ ህዝብ ነው።

01/12/2022

#ወለጋ!!

ኦሮሚያ የአማራ እልቂት ቀጥሏል።
የአማራ ብልፅግና የአማራን ጀግኖች በማሳደድና በመግደል ተጠምዷል።
የኦሮሞ ብልፅግና አማራን ከምድር ያፀዳል።

የአማራ ህዝብ መድረሻው የት ይሆን?

አርበኛ ዘመነ ካሴ ያስተላለፈው የትግል ጥሪ:-                ለሚመለከተው ሁሉ:_"…ላለፉት አስራ አንድ ዓመታት ነፃ፣ ፋትሃዊትና ደስተኛ ምድር ማየትን በልጅነቴ አልሜ በአቅሜ ከጭቆ...
30/11/2022

አርበኛ ዘመነ ካሴ ያስተላለፈው የትግል ጥሪ:-

ለሚመለከተው ሁሉ:_

"…ላለፉት አስራ አንድ ዓመታት ነፃ፣ ፋትሃዊትና ደስተኛ ምድር ማየትን በልጅነቴ አልሜ በአቅሜ ከጭቆና ተራራ ጋር ግብግብ ገጥሜ ቆይቻለሁ። አሁንም ትንቅንቅ ላይ ነኝ። በሀገሩና በአድባሩ የተከበረ እና ነፃ ዐማራ፤ እንዲሁም በሁሉም ለሁሉም የሆነች ኢትዮጲያን እስካይ ድረስ ላፍታ እንኳን ረፍት ሳልሻ እቀጥላለሁ።

በዚህ የተነሳም ፀረ- ዐማራና ፀረ- ኢትዮጲያ ኃይሎች ላለፉት አስራ አንድ አመታት ስምና ጃኬት ብቻ እየቀየሩ ሲያሳድዱኝ ቆይተው መስከረም 11-01-2015፧ ዓ.ም እጃቸው ላይ መውደቄ ይታወቃል።

ከዚያ ዕለት ማግስት ጀምሮ ለስድስት (6) ጊዜ ፍ/ቤት ቀርቤያለሁ።

"…እውነት ለመነጋገር ከመጀመሪያው ቀን የፍ/ቤት ውሎ በኋላ ተመልሶ ችሎት ላይ የመቆም ጥፍር ታክል ፍላጎት አልነበረኝም። የመጀመሪያ ቀን የፍ/ቤት የተገኘሁትም ይህን አቋሜንና ፍላጎቴን ለመግለጽም ነበር። ይሁንና በወዳጆቼ ጉትጎታ እየተገፋሁ ሳዘግም ቆይቼ ዛሬ (16-03-2015) የመጨረሻውን የችሎት ውሎ አድርጌያለሁ።

በዕለቱም በጠበቆቼ ሕጋዊ እና እውነተኛ ጥያቄ መሰረት ክሱ ውድቅ ይደረጋል ተብሎ ሲጠበቅ ተሻሽሎ እንዲቀርብ ብቻ ተወስኗል። የኔ ዘመኗ ኢትዮጲያ፣ የነ አጅሬ ክልል ዐማራ ይህን ይመስላል።

ከጭቆና እና ግፍ ተራራ ጋር ግብግብ የገጠምኩት እውነተኛውን ነፃ አውጭ የናዝሬቱን እየሱስን የሰቀለች፣ ሶቅራጠስን መርዝ የጋተች፣ ጆርዳኖ ቡርኖን በሰም ለቁም ያቃጠለች እውነት የሚያቅራት ምድር ላይ መሆኑን ገና ድሮ ጠንቅቄ ስለማውቅ ቅንጣት ታህል አልገረመኝም።

"…የዐማራ ክልል መንግሥት በአጠቃላይ፣ የፍትሕ ሥርዓቱ በተለይ በጥቂት ግን በጥልቅ ተደራጅተው የፖለቲካ እና የመንግሥት መዋቅሩን በወረሩ ፍልፈል ኃይሎች የፊጥኝ ታስሮ ከወደቀ ቆይቷል። የክልሉ ዲፋክቶ (ውስጠ-ዘ) መሪዎችም እነዚሁ ኃይሎች ናቸው ማለት ይቻላል። ከዚህ ፍጥጥ ያለ እውነታ ላይ ተቋሙ ፍትህን መሻት ትልቅ ጅልነት ይሆናል።

"…ባለፉት አስራ አንድ ዓመታት በጎ ምኞት እውን ሆኖ ባይ ብዬ የአቅሜን ስሞክር እንኳን ወንጀል የጸጉር ስንጣቂ የምታክል ስህተት ሠርቼ አላቅውቅም። የተለየሁ ፍጥረት ሆኜ አይደለም፤ የድንግል ማርያም ልጅ ሁሌም አብሮኝ ስላለ እና ስለሚጠብቀኝ እንጂ። የሆነው ሆኖ ወንጀለኞች "ወንጀለኛ" ብለው ከሰውኝ እየተናነቀኝም ቢሆን እስከዛሬዋ ቀን ፍ/ቤት ተመላልሻለሁ። ዛሬ ግን ጨርሻለሁ። በቃኝ። ከዛሬ በኋላ ፍ/ቤት፣ ችሎት፣ ቀጠሮ ጂኒጃንካ እያልሁ የምሄድ የምመጣበት ቦታ አይኖርም።

በሁለት ዋና ዋና ምክንያቶች ምክንያት:-

(1) ዲሽቃ እና ስናይፐር ወድረው ፍ/ቤት አድርሰው የሚመልሱኝ ኃይሎች የሚታዘዙት እንድጠፋ ሌት ተቀን በሚሠሩ ግለሰቦች እና ከላይ የክልሉን ሁለንተና ተቆጣጥረዋል ባልኳቸው ቡድኖች ነው።

ከነስጋቴም ቢሆን ፍ/ቤት ደርሼ የምመለሰው ከጠላት ጋር በሚዶልቱ አምስት ከማይበልጡ አባሎቻቸው ውጪ በማረሚያ ቤቱ ፖሊሶች እና አስተዳደሩ ላይ እምነት ስላለኝ ብቻ ነው።

ጠላቶቼ የሚያዙት ሃይል መቼ፣ የት፣ እና በምን ደቂቃ የሚያጅቡበትን ዲሽቃና ስናይፐር አፈሙዝ ወደኔ እንደሚያዞሩት እንኳን አላውቅም። ፍ/ቤት ደርሼ የምመለሰው በሞት ባቡር ተሳፍሬ ነው። ይህን የሚመለከት አቤቱታ ለከፍተኛ ፍርድ ቤቱ ማቅረቤም ይታወቃል። ስጋቱ ግን እያየለ መጣ እንጂ አልቀነሰም።

በዚህ ሁኔታ ውስጥ የማይገኝ ፍትህ ፍለጋ "ቀጠሮ" እያሉ መመላለስ የጠላት የመግደያ ወረዳ ውስጥ በገዛ ፈቃድ ሰተት እያሉ እንደመግባት በመሆኑ ከዚህ በኋላ ፍ/ ቤት አልቀርብም።

(2) የጥቂት ፍልፈል ኃይሎችና ማጅራት መቺዎች መጫወቻ እና ሸቀጥ በሆነ የፍትህ ሥርዓት ውስጥ "ፍትህ ይገኛል" ማለት የሞተ ፈረስ እየጋለቡ ሰባተኛው ሰማይ ድረስ ለመውጣት የመሞከር ያክል ቂልነት ወይንም እብደት ይሆናል።

የማልክደው እና በፍ/ቤት ምልልሴ የታዘብሁት ነገር ችሎት ላይ ስቆም የዳኞችን ጭንቀት በግልጽ አይ ነበር።

ሌላው ቀርቶ ከሳሽ ሆነው የሚቆሙት ዐቃቤ ሕጎች እንኳን ሲጨነቁ እና ግራ ሲጋቡ በዓይኔም በስሜቴም ታዝቤያለሁ። ግን ምን ዋጋ አለው? ዋናው ችሎት ያለው የአንዱ ካድሬ ቢሮ ውስጥ ነው። ዋናው ዳኛም ካድሬው እና የካድሬው ስልክ ነው። የታሰረው ዘመነ ብቻ አይደለም፤ በእሳት ሰንሰለት የታሰረው ዳኛውም ዐቃቤ ሕጉም ነው።

ይህን ሰንሰለት መቼ? እንዴትና በምን አኳኋን እንስበረው? ይህ ዘመነ ብቻ ሳይሆን ዳኛውም ዐቃቤ ሕጉም እኩል መመለስ ያለባቸው ጥያቄ ነው። የፍትህ ሞት የህዝብና የሀገር ሞት ነውና። በኔ በኩል ሰንሰለቱ መሰበር ብቻ ሳይሆን መቅለጥ ያለበት ዛሬ ነው፤ እደግመዋለሁ ዛሬ!

"…ለማንኛውም የኔ ዘመን በድን የፍትሕ ጉዞ እና ድራማ ላይ ከዚህ በላይ ለመተወን ዝግጁ አይደለሁም። ኃጢአትም ነው። ስለዚህ ከዛሬ በኋላ የፍርድ ቤት ቀጠሮ አይመለከተኝም፤ ችሎት ላይም አልቆምም። አንድ ቀን እልቂት የታወጀበት የዐማራ ህዝብ እና ረፍት ያጣችው ሀገራችን ነፃ ሲወጡ እኔም ነፃ እወጣለሁ። ስለዚህ አሁን ሁሉም ትግሉ ላይ ብቻ ትኩረት ያድርግ።

"…ቀና አባቶቻችን እና ወንድሞቻችን ጉዳዩ ፖለቲካ ወለድ ክስ በመሆኑ በሽምግልና እንዲያልቅ ያደረጉት ጥረትም ውጤት እያመጣ አይደለም። እንዲያውም ጠላቶቼ የሽምግልናውን እና የፍርድ ቤት ሂደቱን የጊዜ መግዣ እና ማዘናጊያ ሲያደርጉት ታዝቤያለሁ።

ከፊሉ ሕዝብ የፍርድ ቤት ውሎ፣ ላይ ከፊሉ ደግሞ ሽምግልናው ላይ አጉል ተስፋ እንዲጥል ጆሮ ጠቢዎቻቸውን አሰማርተው በየጊዜው አዲስ ኢንፎርሜሽን ካምፔን በመክፈት አደገኛ ጊዜ እየገዙ ነው።

ስለዚህ ከሊቅ እስከ ደቂቅ፣ የምር የትግል ፍላጎትና ወኔ ያለው በሙሉ ትግሉ እና ትግሉ ላይ ብቻ ትኩረት ያድርግ። ወትሮም ቢሆን ከሞት ጋር ትከሻ ለትከሻ ስንጋፋ፣ አልፎም የሞትን አፍንጫ ለመያዝ ሳንደፍር ነፃ አንወጣም።

"…እነዚህ ሰዎች በማወቅም ይሁን ባለማወቅ ሀገሩን እሳት ጎርሶ እሳት ለሚተፋ አብዮት እያመቻቹት ነው። ይህ በእርጥብ የጭቆናና የግፍ ቆዳ የታፈነ ምድር የፈነዳ እለት የሚነሳው እሳት ፍጥረትን በሙሉ ይጠርጋል። ያገኘውን ይበላል። ያኔ እንኳን ህዝቡን የበደሉ ካድሬ መሆን፤ የካድሬ ዘመድ ሆኖ መገኘት ብቻ የተፈጠሩበትን ቀን ያስረግማል። ለማንኛውም ሁሉም ትኩረቱን ትግሉ ላይ ብቻ ያድርግ። እግሮች ሁሉ ወደ ትግሉ ሜዳ ይጓዙ። ወደ ትግሉ ሜዳ ይሩጡ።

የዛሬ ህመማችን እና የውስጥ ለውስጥ እንጉርጉሯችን ነገ ህፃናት ሳይቀሩ በደስታ የሚዘምሩት የአደባባይ ብሔራዊ መዝሙር ይሆናል። እንበርታ ብቻ!!

"…በዚህ ትግል ውስጥ አስራ አንድ ዓመት ቆይቻለሁ። ለአስራ አንድ ሰከንድ እንኳን ተጠራጥሬ የማላቀው ነገር ቢኖር በመጨረሻ አሸናፊዎች እኛ መሆናችንን ነው። መንገዳችን የፍትሕ፣ የእኩልነትና የእውነት መንገድ ነው። ከእውነት ጋር እግዚአብሔር አለ። ከእግዚአብሔር ጋር ያለ ደግሞ ማሸነፉ አይቀርም። ጽናት፣ ብርታት እና ትእግስት ብቻ!!። እንበርታ! እንሰባሰብ፣ እንደብረት እንጠንክር።

• (ክፋት ለማንም በጎነት ለሁሉም)
• (አዲስ ትውልድ፣ አዲስ አስተሳሰብ፣ አዲስ ተስፋ)
• ድል ለዐማራ ሕዝብ…!
ድል ለኢትዮጲያ ሕዝብ…!

አርበኛ ዘመነ ካሴ
ከባህርዳር ወኅኒ ቤት

26/11/2022

ይድረስ ለፋኖ ወንድሞቻችን!

"የአማራ ፋኖ አንድነት ምስረታ!" የሚል መረጃ በተለያዩ መንገዶች በስፋት ሲስተጋባ እያየሁ ነው፡፡ እርግጥ ነው! እንቅስቃሴው የማያስደስተው ቢኖር እርሱ በተቃራኒዉ ምድብ ያለ ሀይል ነው፡፡ ነገርግን ከእስካሁኑ ብዙ ልምዶቻችን ተነስቼ እንደታናሽ ወንድማችሁ > በማለት የተሰማኝን ልገልፅላችሁ እወዳለሁ!

በእኛ ሀገር ብልሹ የፖለቲካ ምህዳር ውስጥ ፥ ድምፅን አጥፍቶ በወጀቡ የማይናወጥ ፥ መነሻና መድረሻ ግቡን በቅጡ የተረዳ ህዝባዊ አደረጃጀት መፍጠር ብልሀት እንጂ ፍርሀት አይደለም!

@ዘሪሁን ገሰሰ!

የወልድያ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት የከተማ አስተዳደር አመራሮችን ሹመት አፅድቋል።በዚህም መሰረት፦ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ --አቶ ዱባለ አብራሬምክትል ከንቲባ --- ዶ/ ር ዳዊት መለሰከንቲ...
25/11/2022

የወልድያ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት የከተማ አስተዳደር አመራሮችን ሹመት አፅድቋል።

በዚህም መሰረት፦

ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ --አቶ ዱባለ አብራሬ

ምክትል ከንቲባ --- ዶ/ ር ዳዊት መለሰ

ከንቲባ ጽ/ቤት ኃላፊ ------አቶ ኢትዮጵስ አያሌው

ህዝብ ቅሬታ ሰሚ ጽ/ቤት ኃላፊ -----ወ/ሮ ሳባ ሀብተማርያም

መንግስት ኮሚኒኬሽን ጽ/ቤት ኃላፊ --ወ/ሮ አስናቀች ሀይሌ

ትምህርት መምሪያ ኃላፊ -- አቶ ደምስ አለባቸው

ጤና መምሪያ ኃላፊ -------አቶ መንገሻ ይመር

ገንዘብ መምሪያ ኃላፊ ----አቶ ብርሃኑ መክብብ

ገቢዎች መምሪያ ኃላፊ-- አቶ አለማየሁ ካሳሁን

ፍትህ መምሪያ ኃላፊ ------አቶ ሰማዬ ፈለቀ

ኢንደስትሪና ኢንቨስትመንትን መምሪያ ኃላፊ -- አቶ ዳዊት ብርሃኑ

ንግድና ገበያ ልማት መምሪያ ኃላፊ --አቶ አንተነህ ሲሳይ

ባህልና ቱሪዝም ተጠሪ ጽ/ቤት ኃላፊ ---ወ/ሮ አበባ አያሌው

ግብርና መምሪያ ኃላፊ ------ወ/ሮ ደስታ ሞላ

ወጣቶችና ስፖርት መምሪያ ኃላፊ -- አቶ ዝናቡ ሰጠ

ስራና ስልጠና መምሪያ ኃላፊ -አቶ አለምነህ ጌጡ

መሬት መምሪያ ኃላፊ ---- አቶ ፈንታው ባዬ

ሲ/ሰርቪስ የሰው ሀብት ልማት መምሪያ ኃላፊ-- ወ/ሪት ወይነጥበብ ተ/ማርያም

ሴ/ህ/ማ/ራዊ ጉዲይ መምሪያ ኃላፊ -----ወ/ሮ ሸዋዬ ሙሉ

ትራንስፖርት ተጠሪ ጽ/ቤት ኃላፊ --አቶ ንጉስ ዝናቡ ያሲን

እንስሳትና አሳ ሀብት ልማት ተጠሪ ጽ/ቤት ኃላፊ--- አቶ በላይ ገሰሰ

ህ/ስራ ማህበራት ተጠሪ ጽ/ቤት ኃላፊ ---ወ/ሮ መላክነሽ ሀይሌ

ከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ ኃላፊ ---አቶ ሀብታሙ አሊጋዝ

ህንፃ ሹም ተጠሪ ጽ/ቤት ኃላፊ---- አቶ አቡበክር ሰይድ

ህገወጥ ድርጊት መከላከልና ደምብ ማስከበር ተጠሪ ጽ/ቤት ኃላፊ -----አቶ ጌታቸው ካሳው

የአካባቢ ጥበቃ ፅዲትና ውበት ተጠሪ ጽ/ቤት ኃላፊ---- ወ/ሮ ካንቺወዲያ ግዴ

ከተማ ልማት ዘርፍ ምክትል ስራ አስኪያጅ ኃላፊ ----- አቶ አለምነው ወርቅዬ

ከተማ ልማት ኮንስትራክሽን ዘርፍ ም/ስራ አስኪያጅ ----- አቶ ሙሃመድ ሷልህ

ተጨማሪም፦

በወልድያ ከተማ የብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት

በወልድያ ከተማ የብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ ----- አቶ መለሰ ተሻለ

በወልድያ ከተማ የብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ -----ወ/ሮ ሀድያ ፈንታው

በወልድያ ከተማ የብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ ---- አቶ ተገኘ ፈንታው

በወልድያ ከተማ የብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት የፖለቲካ ዘርፍ ምክትል ኃላፊ----ወ/ሪት ራሄል ገዳሙ ሴት

በወልድያ ከተማ የብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ምክትል ሀላፊ--ወ/ሮበላይነሽ ጌታነህ

የወጣት ሊግ ኃላፊ-------- አቶ ኤፍሬም አያሌው ሰጠ

የወጣት ሊግ ምክትል ኃላፊ-- አቶ ተመስጌን አያሌው

የሴቶች ሊግ ኃላፊ----- ወ/ሮ አበቡ ቸኮል

የሴቶች ሊግ ምክትል ኃላፊ ---ወ/ሪት ሉባባ ሰይድ በመሆን ተሹመዋል።

20/11/2022

ጠሚው ተወላገደ የሚለውን የወልቃይትን አማርኛ እንካ🤔

የቂሊንጦ ማረሚያ ቤት የግል እስረኛ ሆኛለሁ የፍርድ ቤት ትዕዛዝ በመጣስ የቂሊንጦ ማረሚያ ቤት በራሱ ፍቃድ የማረሚያ ቤቱ እስረኛ አድርጎኛል ፤ እኔ ላይ ለሚፈጠረው ማናቸውም ነገር ኃላፊነቱ ...
15/11/2022

የቂሊንጦ ማረሚያ ቤት የግል እስረኛ ሆኛለሁ
የፍርድ ቤት ትዕዛዝ በመጣስ የቂሊንጦ ማረሚያ ቤት በራሱ ፍቃድ የማረሚያ ቤቱ እስረኛ አድርጎኛል ፤ እኔ ላይ ለሚፈጠረው ማናቸውም ነገር ኃላፊነቱ የማረሚያ ቤት ነው።
ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ

15/11/2022

አትዘናጋ....
ህወሓት ተበታትኖ የነበረውን ተዋጊውን አሰባስቦ ጦርነት ሊከፍት ስለሆነ ወገብህን ጠበቅ በማድረግ ግብአተ መሬቱን መፈፀም ይበጃል።

ጋዜጠኛ ጎበዜ ሲሳይ በአንድ መቶ ሺህ ብር ዋስ  ከእስር ተፈቷልእንኳን ለቤትህ አበቃህ
11/11/2022

ጋዜጠኛ ጎበዜ ሲሳይ በአንድ መቶ ሺህ ብር ዋስ ከእስር ተፈቷል
እንኳን ለቤትህ አበቃህ

ሰበር ዜና…!!"…ኦነጎቹ በአሁን ሰዓት ከነቀምቴ ከተማ የዓመት ቀለባቸውን ከባንኮችና ከመንግሥታዊ ተቋማት የሚዘረፈውን ሁሉ ዘርፈው ወደ ጫካቸው እየተመለሱ መሆኑ ተነግሯል።
06/11/2022

ሰበር ዜና…!!

"…ኦነጎቹ በአሁን ሰዓት ከነቀምቴ ከተማ የዓመት ቀለባቸውን ከባንኮችና ከመንግሥታዊ ተቋማት የሚዘረፈውን ሁሉ ዘርፈው ወደ ጫካቸው እየተመለሱ መሆኑ ተነግሯል።

ቆቦ ሮቢጥ የት አካባቢ ናት?ጎግል ላይ ብፈልጋት አጣኋት!
03/11/2022

ቆቦ ሮቢጥ የት አካባቢ ናት?
ጎግል ላይ ብፈልጋት አጣኋት!

Address

Adis Abeba Bole

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when አንጎት ፕረስ ANGOT PRESS posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Videos

Shortcuts

  • Address
  • Alerts
  • Videos
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share