17/07/2023
ከ 73 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡ ተገለፀ፣
በምዕ/ጐጃም ዞን ወምበርማ ወረዳ ከ 73 ሚሊየን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡን የወረዳው ገቢዎች ጽህፈት ቤት ገለፀ፡፡ በጽ/ቤቱ የግብር ትምህርትና ኮምንኬሽን ቡድን መሪ አቶ ገነት ሙሉጌታ እንደገለፁት ከበጀት አመቱ ከሀምሌ 1/2014 እስከ ሰኔ 30/2015 በጀት አመት 76,000,853 ብር ለመሰብሰብ ታቅዶ እስከ ሰኔ 30/2015 ዓ.ም 73,802,930.78ብር 97.1% መሰብሰብ መቻሉን አሳውቀዋል፡፡ ገቢው የተሰበሰበውም ከእርሻ፣ከንግድ ዘርፍ ገቢና ከልዩ ልዩ ዘርፎች ሲሆን ግብር ከፋዩ ግብር የመክፈልግዴታውን መወጣት አለበት። በቀጣይ የተሻለ ገቢ ለመሰብሰብ የትምህርት መግለጫ ዘዴዎችን ተጠቅሞ ተከታታይ የግንዛቤ ትምህርት በመስጠት ውጤታማና ዘመናዊ የሆነ ግብር ከፋይ ለመፍጠር በትኩረት እየተሰራ መሆኑን አቶ ገነት ሙሉጌታ ገልፀዋል፡፡
ሮያሊቲ ክፍያ መክፈል የሚገባችሁ በተቆቋመው ኬላ መሰረት አንድትከፍሉ እናሳስባለን።
የአመቱን ግብር በውጤታማ ለመፈጸም አጋር አካላት፣የወረዳና የቀበሌ አመራሩ እና የገቢ ሰብሳቢ ባለሙያ ተቀናጅተው በመስራታቸው የዓመቱ ተግባር በውጤታማነት ተጠናቋል ።
የአመቱ ተግባሮች በውጤታማነት ሊጠናቀቅ የቻሉበት የአስተዳድር ም/ቤት የኬላ ሰራተኛ እንዲቀጠር በማድረግ፣በማቴሪያልና በገንዘብ እገዛ በማድረግ፣በእየ ወሩ ተግባሮችን እየገመገሙ ያልተሰራውን ስራ በመለየት እገዛ በማድረግ ውጤት እንዲመጣ እገዛ አድርገዋል፡፡
ግብር መክፈል ለሃገር ልማት የሚውል በመሆኑ ሁሉም ግብር ከፋይ በወቅቱ በመክፈል የዜግነት ግዴታውን ይወጣ።
ማሣሰቢያ፣
በአመቱ የእርሻ ግብር አሰባስብ ወምበርማ ወረዳ ገቢዎች ጽ/ቤት ከያዘው ዕቅድ 120,864 ብር ሽንዲ ከተማ አስተዳድር ገቢዎች ጽ/ቤት ሰብስቦብናል እና ክልል ገቢዎች ቢሮ የእርሻ ግብር አዋጅ ይቀየራል ብሎ የጨመረብን የእርሻ ግብር = 2,781,339 ብር ሲሆን ይህ ተቀንሶ የአመቱ እቅድ =72,977,786 ክንውን=73,802,930.78 አፈጻጽም =101.13% መሆኑን እንገልጻለን::