Gondar today ጎንደር ዛሬ

  • Home
  • Gondar today ጎንደር ዛሬ

Gondar today ጎንደር ዛሬ Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Gondar today ጎንደር ዛሬ, News & Media Website, .

ጎንደሬነት ❤❤
06/06/2023

ጎንደሬነት ❤❤

ፋኖ ነጻ ያወጣውን መሬት መንግስት እውቅና እንዲሰጠው  እንፈልጋለን።-----------ሻለቃ መሳፍንት ተስፉ        ➢ እኛ የህዝብ ልጆች ነን፤ የህዝብ አደራ ጠባቂዎች ነን፤ ሌላ አላማ የ...
20/03/2022

ፋኖ ነጻ ያወጣውን መሬት መንግስት እውቅና እንዲሰጠው እንፈልጋለን።

-----------ሻለቃ መሳፍንት ተስፉ

➢ እኛ የህዝብ ልጆች ነን፤ የህዝብ አደራ ጠባቂዎች ነን፤ ሌላ አላማ የለንም።
➢ ፋኖም የአባቶቻችን ስም ነው።
✔ ጎንደር ለአማራ ምርኩዝ ቀኝ እጅ ነው
✔አማራ ክልል ለኢትዮጵያ የበኩር ልጅ ነው
➢ የአማራ ፋኖ አንድነት በጎንደር :-
✔ ጎጃምን በቀኛችን
✔ ወሎን በግራችን እንዲሁም
✔ ሸዋን በግንባራችን አድርጎ አንድ ሆኖ ይታገላል።የሌሎችም ፋኖ አንድነት ወደዚህ መምጣት አለበት።

መጋቢት 11/2014 አ.ም

ሰበር ራያ 💪💪ሼር ይደረግ !!የአማራ ልዩ ሀይል ድል በድል ሁኗልበዞብል ጉብታ ላይ አመሻሹ ላይ የጀመረ ከፍተኛ ውጊያ አሁንም እየተካሄደ ነው። ከ3 ሺህ በላይ የጁንታው ጦር እስካሁን እምሽክ...
22/07/2021

ሰበር ራያ 💪💪

ሼር ይደረግ !!

የአማራ ልዩ ሀይል ድል በድል ሁኗል
በዞብል ጉብታ ላይ አመሻሹ ላይ የጀመረ ከፍተኛ ውጊያ አሁንም እየተካሄደ ነው።

ከ3 ሺህ በላይ የጁንታው ጦር እስካሁን እምሽክ ብሏል።

የአማራ ልዩ ኃይል በመሬት ላይ ውጊያ እየቆላቸው ሲሆን መከላከያ ሠራዊቱ ደግሞ በሩቅ በከባድ መሳሪያ ጁንታው ያለበትን ተራራ እያደባየ ሽፋን እየሰጠ ነው። ጁንታው ግን አሁንም የህዝብ ማዕበል በመሰቦ ሲሚንቶ ፋብሪካ ተሳቢ መኪናዎች በገፍ እየጫነ ወደ ጦር ሜዳው አዳዲስ ማገዶ እያቀረበ ነው።

ፔጁን ላይክ ሼር ያድርጉ

   #ጎንደርየጥበብ ልክ ታይቶባታል፤ ፍቅርእንደዥረት ፈስሶባታል ጀግኖች እንደ አሸን ፈልተውባታል፡፡‹‹እምነት እንደዥረት የፈሰሰብሽ ዲያቆናት ቀሳውስቱ የተቀኙልሽ፤ ጎበዝ እና ገበዝ ደጎች ያ...
07/08/2020


#ጎንደር

የጥበብ ልክ ታይቶባታል፤ ፍቅር
እንደዥረት ፈስሶባታል ጀግኖች እንደ አሸን ፈልተውባታል፡፡

‹‹እምነት እንደዥረት የፈሰሰብሽ ዲያቆናት ቀሳውስቱ የተቀኙልሽ፤ ጎበዝ እና ገበዝ ደጎች ያሉብሽ፤ የነገሥታት ሀገር ጎንደር ›

እንዳለ ከያኒው ከጃን ተከል ዋርካ ስር ፍቅር፤ ከአርባ አራቱ አድባራት የቅኔ፣ የዜማ፣ የአቋቀም፣ የድጓና የትርጓሜ ሚስጥር፤ ከገነት፣አቡነአረጋዊና ገለዓድ ተራሮች ነብስ አዳሽ ንጹሕ አየር፣
ከእልፈኞቿ ወተት፣ ጠጅና ማር እየቀዳች ዘመንን አዘምና ከፍ ብላ ተቀምጣለች፡፡

ሙሽሪት ጎንደር በ1628ዓ.ም ዘመናዊ ከተማ ሆና ተመሠረተች፡፡
በዘመኑም በአፍሪካ አስደናቂ የሆነ የምህንድስና፣ የእመነት፣
የትምህርትና የፍልስፍና ማዕከል በመሆን የአፍሪካ መናገሻ ናት ተባለች፡፡ ጎንደር

ከቃል ኪዳኗ በተጨማሪ የንግድ ማዕከል በመሆኗ፣ የአየር ንብረቷ የተመቸ መሆን፣መልክአ ምድሯ የተመቸ መሆን እና ሌሎችም ተመራጭ አድርገዋታል፡፡
ጎንደር በኪነ ሕንጻና በተለያዩ ጥበቦች ያበበች ከተማ፡፡

➨ ጃናሞራ ገብስና ባቄላ፣ በደንቢያ ጤፍና የማር ወለላ፣ በበለሳ ሙሬና ሽንብራ፣ በመተማና ቋራ ሰሊጥ፣ ጥጥና ማሽላ፣ በፎገራና ከምከም ቃሮዳ ሩዝ፣ ቡሌና ዛንጋዳ፣ በወልቃይት ጠገዴና ሰቲት ሁመራ ወተት ቅቤና አሬራ ወደመናገሸዋ ይገባሉ፤ በመናገሻዋም ይሰባሰባሉ፡፡

ይህች የሁሉም መናገሻ ናት፤ የሃይማኖትና
የዘር እኩልነትን አስቀድማ አክብራለች፤ ለእንስሳት መብትም ተከራክራለች በአደባባይም ፍርድ ሰጥታለች፤ እምዬ ጎንደር፡፡

‹‹ጃን ተከል ዋርካው ስር እትብቴ ተቀብሮ፣
ልቤ ጎንደር ላይ ነው የትም ዞሮ ዞሮ››

እንዳለች ጠቢቧ በጃንተከል ዋርካ ስር አልፈው ወደታች
ሲጓዙ አራዳ እና ቅዳሜ ገበያን እየቃኙ በውበት ይገረማሉ፡፡

ከቤተ መንግሥት በስተሰሜን በኩል አድርገው ከሄዱም በቆብ አስጥል ድንቅዬ ድልድዮች ሾልከው በቀደምት አብያተ ክርስቲያናት ተማርከው በደስታ ይፈዝዛሉ፡፡

የጎንደርን ታሪክ መስካሪ የኢትዮጵያን ታሪክ ዘካሪ የሆኑት ደብረ ብርሃን ሥላሴ፣ መንበረ መንግሥት መድኃኒዓለም፣ ፊት አቦ፣ እልፍኝ ጊዮርጊስ፣ አበራ ጊዮርጊስ፣ አደበባይ ኢየሱስ፣ ፊት ሚካኤል፣ ጎንደር ባዕታ፣ ቁስቋምና ሌሎች በርካታ አድባራትም በዚችው ድንቅ ከተማ ይገኛሉ፡፡

የጎንደር ታላቁ መስጂድም ሌላኛው ድምቀትና ውበት ነው፡፡
ሀገር በሠላም እጦት ስትቸገር ጎን ለጎን ወደ ፈጣሪ
ስለሠላም የሚማልዱ ሙስሊሞችና ክርስቲያኖች የጋራ ከተማም ነች፤ ጎንደር፡፡

ጎንደር አዘዞ ድማዛ፣ ቀሃ፣ አራዳ፣ ፒያሳ፣ ብልኮ፣ አርበኞች አደባባይ፣ ቸቸላ፣ ማራኪ፣ እንኮዬ መስክ ቅዳሜ ገባያና ብዙ በሆኑ የሰፈር ስሞቿ ተውባ በተራራ ተከባ፣ በስልጣኔ አብባ የኖረች ከተማ ናት፡፡

ይቀጥላል ...............

መልካም ቀን !!
29/06/2020

መልካም ቀን !!

 #ጎንደርና የሰፈር ስሞቿ ! ጥንታዊ እና አዲሶቹ!!ስንቶቻችንን ይህንን እናውቅ ይሆን? 👉አደናግር በር 👉አዘዞ👉እርግብ በር👉ጠዳ👉ፋሲለደስ 👉ምንዝሮ👉እንኮየ በር(እንኮየ መስክ)👉ሞላጄእምነትና...
28/06/2020

#ጎንደርና የሰፈር ስሞቿ ! ጥንታዊ እና አዲሶቹ!!
ስንቶቻችንን ይህንን እናውቅ ይሆን?


👉አደናግር በር
👉አዘዞ
👉እርግብ በር
👉ጠዳ
👉ፋሲለደስ
👉ምንዝሮ
👉እንኮየ በር(እንኮየ መስክ)
👉ሞላጄ

እምነትና ሀይማኖትን መሰረት በማድረግ የተሰየሙ

👉 እስላም ቤት
👉ካይላ ሜዳ

ሹመትና ስምን መነሻ በማድረግ የተሰየሙ
👉እጨጌ ቤት
👉 ቀኝ ቤት
👉ግራ ወንበር
👉አቡን ቤት

ድርጊት እና ሁኔታን ለመግለፅ መነሻ በማድረግ የተየምሙ
👉 ድብ አንበሳ
👉 ፈረስ ቤት
👉 ሸዋ ሜዳ(አሸዋ)
👉ዲንጋፍ
👉 እርቅ ቤት
👉ኢድዩ ሰፈር

ጥንታዊ ናቸው ነገር ግን ተመዝግበው የማይገኙ ስሞች

👉 አርባቱእንስሳ ( አርባ ተንሳይ)
👉አዲሳለም
👉አልጋ ሜዳ።
👉አብየ እግዚህ
👉ገሰሰ ሰፈር
👉ሹምየ ሰፈር
👉ጎርጓዲት


👉ፒያሳ
👉አውቶ ፓርኮ
👉ብሪጋታ
👉አንባጅኔ
👉ቸቸላ
👉አራዳ
👉ማንዳ ሰፈር
👉ብልኮ
👉ዲጋዚቶ
👉ሳኔታ



👉ጉፋያ ማስጫ
👉 ቆብ አስጥል
👉ደጃች ጌታ
👉አባ ሸሪፍ
👉ጳውሎስ ሜዳ
👉ቆብ አስጥል
👉 ፈረስ ሜዳ
👉ልደታ
👉ቃዴ
👉ሳሙና በር
👉ባባ ሳሙኤል
👉ወድጅ

ከ1928-1933 ጀምሮ ከከተማዋ እድገት ጋር የወጡ ስሞች
👉 ጨዋ ሰፈር።
👉 ጡረታ ሰፈር
👉ደብረ ሰላም
👉መዳመጫ
👉ደሮ ማነያይ(ብቅ እንቅ)
👉ተቋም
👉ጭቃ ሰፈር
👉ሞኝ መቆሚያ
👉ኤል ሼፕ
👉 ግራር ሰፈር
የሚሉት ተጠቃሾች ናቸዉ !!!

👉ጎንደር ሁሉ በጄ ሁሉ በደጄ!👉 ጎንደር የብሉልኝ ጠጡልኝ ምድር! 👉ጎንደር የኃቀኞች ባድማ የኢትዮጵያዊነት ግርማ!👉 ጎንደር የዓለማዊም ሆነ የመንፈሳዊ ጥበብ የልኅቀት ማዕከል! 👉ጎንደር እን...
27/06/2020

👉ጎንደር ሁሉ በጄ ሁሉ በደጄ!
👉 ጎንደር የብሉልኝ ጠጡልኝ ምድር!
👉ጎንደር የኃቀኞች ባድማ የኢትዮጵያዊነት ግርማ!
👉 ጎንደር የዓለማዊም ሆነ የመንፈሳዊ ጥበብ የልኅቀት ማዕከል!
👉ጎንደር እንኳንስና እኛ ጥበብሽን ሞቀን ጥበብሽንም ተጎናፅፈን ለብሰን 👉ያደግነው ልጆችሽ ቀርቶ የጥበብ መዓዛሽ በሩቁ ያወዳቸው በዓዳን ወደ እልፍኝሽ ገብተው የኅሊና ርኃባቸውን
👉ከማስታገስ አልፈው በርካቶችም («ጎንደሬ» ሆነው) ቀርተዋል።

ጉንዳ ሃገር ወይም ትልቅ ሃገር ማለት ነው

?

ጎንደር ከመመስረቷ በፊት በአካባቢው አራት ደብሮች ነበሩ፡፡
አንደኛው #አርባዕቱ እንስሣ ይባላል፡፡

በሌላ አቅጣጫ #ቅሀ ኢየሱስ የሚባል አለ፡፡
ጊዮርጊስ በሌላ አቅጣጫ አለ፤ #አበራጊዮርጊስ የሚባልም አለ።
ከዚያ በኋላ 👉 አፄ ፋሲል 7 ተከሉ፡፡
👉 ፃድቁ ዮሐንስ 2 ተከሉ፣👉 አድያም ሰገድ ኢያሱ #ደብረ ብርሃን ስላሴ ጨምሮ 2 ተከሉ፡፡

እንዲህ እንዲያ እያሉ ነገስታቱ በተፈራረቁ ቁጥር አዳዲስ ደብሮችን ሲተክሉ ኖሩ።
👉በዚህ ሂደት በእነዚህ ነገስታት 30 ተተከሉ።

👉 14 ያህሉ ደግሞ ቀድሞም የነበሩ ናቸው፡፡

እነዚህ ተደምረው ጎንደር የ44 ታቦት መገኛ ሃገር ተባለች፡፡
ኋላ ላይ በደርቡሽ ጦርነት 4 ያህሉ ተቃጥለው ነበር፡፡

ሃገሬው የተቃጠሉትን እንደገና ሰርቷቸዋል።
ከዚያ በኋላ ሌሎች ደብሮች በብዛት የተተከሉ ቢሆንም የጥንቱን የጎንደር ስልጣኔ ለማስታወስ 44ቱ ታቦታት የጎላ ቦታ አላቸው፡፡

?

ብዙ አፈታሪኮች አሉ፣ ነገር ግን ዋናው ማየት ያለብን የታሪክ ጥራዞችን ነው፡፡

የአፄ አምደፅዮን ዜና መዋዕል ላይ “ጎንደር” የሚለው ስም ሰፍሯል። ጎንደር ከመመስረቷ ከ300 ዓመት በፊት መሆኑ ነው፡፡ ወደ አፈታሪኩ ስንመለስ ጉንዳ ሃገር ወይም ትልቅ ሃገር ማለት ነው፡፡ አንዳንዶቹ ጓንግ እና ዳራ ከሚሉ ሁለት ቃላት የመጣ ሲሆን በአንገረብ እና ቅሃ ወንዝ መካከል ስላለች ነው ይህ ስም የተሰጣት ይላሉ፡፡

👉ነገስታቱ ይህን የቤተመንግስቱን ቦታ ከመያዛቸው በፊት ቦታው ላይ ምን ነበር? እንደ አፈታሪክ እዚህ ቦታ ላይ (አሁን ቤተመንግስቱ ያለበት) ውሃ ነበር ይባላል፡፡

👉ውሃውን አድርቀው ቤተ መንግስታቸውን ሰሩ፤ አንዳንድ ታሪክ ደግሞ ቦታው የባላባቶች/የእርሻ ቦታ ነበር ይላሉ።

👉ሌሎች አፈታሪኮች አፄ ፋሲል አደን ወጥተው አንዳንዶች ጎሽ ይላሉ ሌላው አንበሳ ይላል እያባረሩ መጥተው እዚህ ቦታ ሲደርሱ ተሰወረባቸው፤ ባህታዊ ተገልጦ ቤተ መንግስትህን የምትሰራበት ቦታ ይሄ ነው ብሎ ነገራቸው ይባላል፡፡

👉ከዚያ በፊት መላዕኩ ራጉኤል “ጎ” የሚባል ቦታ ላይ ትነግሳለህ ብሎ በራዕይ ይነግራቸው እንደነበር ይነገራል፡፡ “ጎ” ሲላቸው ቦታውን ፍለጋ ጎዛራ፣ ጎጃም፣ ጎርጎራ ሄደው በመጨረሻ ጎንደር ፀንቶላቸዋል ነው የሚባለው።

👉ነገር ግን በዚህ አካባቢ አድባራት በፊትም መኖራቸውን ስናይ ሰዎች ይኖሩበት እንደነበር ያመላክተናል፡፡

የኖህ መቃብር ነው የሚል ታሪክም ይነገራል? ሰዎች የራሳቸውን ታሪክ ይዘው ሊነሱ ይችላሉ።

እኔም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ይሄን ነገር ሰእየሰማሁ ነው፡፡

ይሁን እንጂ በ1960ዎቹ የተፃፈ አንድ ታሪክ የሚያሳየው፤ ፋሲል ቤተመንግስቱን እንደ ኖህ መርከብ አድርጎ እንደሰራው ነው።

👉ይህ ጉዳይ ሰፊና ጥልቀት ያለው ጥናት ይፈልጋል፡፡

 የመሀመድ አል አሩሲ አሳማኝ ሎጂክ ስለአባይ!ይናገራል አል አሩሲ! ይሄ ሞባይል የእኔ ነው። ለመደወል፣ ፎቶግራፍ ለማንሳት፣ ቪዲዮለመቅረጽ፣ማህበራዊ ሚዲያዎችን ለመጠቀም፣ ሰዓትና ቀን ለማወቅ...
26/06/2020



የመሀመድ አል አሩሲ አሳማኝ ሎጂክ ስለአባይ!
ይናገራል አል አሩሲ! ይሄ ሞባይል የእኔ ነው።

ለመደወል፣ ፎቶግራፍ ለማንሳት፣ ቪዲዮ
ለመቅረጽ፣ማህበራዊ ሚዲያዎችን ለመጠቀም፣ ሰዓትና ቀን ለማወቅ፣ ወዘተ ልጠቀምበት እችላለሁ።

ለምን እንደምጠቀም የምውስነው እኔ ነኝ። ይሄ መብት ሞባይሉን ከገዛሁበት ጊዜ ይጀምራል።
አላህ አባይን እንድንጠቀምበት ሰጥቶናል። የራሳችንን አባይ መጠቀም አትችሉም ማለት በገዛ ሞባይልህ ሰአት ማወቅ እንጂ ስልክ መደወል አትችልም፣ ኢንተርኔት መጠቀም አትችልም እንደማለት ነው።
ሞባይሉን ከገዛንበት ወቅት ጀምሮ ለፈለግነው አላማ እንደምንጠቀምበት ሁሉ፣ ፈጣሪም አባይን የሰጠን ለሚጠቅመን ነገር ሁሉ እንድንጠቀምበት ነው። የአረብ ሀገራት አላህ የሰጣቸውን ነዳጅ ለፈለጉት አላማ እንደሚጠቀሙበት እኛም በራሳችን አባይ ለፈለግነው አላማ መጠቀም አለብን።

አቻምየለሽ ጎንደር*****እምዬ ጎንደር የአኩሪ ታሪካችን ማኅደር! 👉ለእኔ ጎንደር ሰንደቅ ዓላማዬ ናት ፤👉በኢትዮጵያዊነቴ የምለይባት ድርብ ጌጤ!👉 ስለጎንደር ብዙ አልጽፍም፤ እጅጉንስለምሳሳላ...
26/06/2020

አቻምየለሽ ጎንደር
*****
እምዬ ጎንደር የአኩሪ ታሪካችን ማኅደር!
👉ለእኔ ጎንደር ሰንደቅ ዓላማዬ ናት ፤
👉በኢትዮጵያዊነቴ የምለይባት ድርብ ጌጤ!
👉 ስለጎንደር ብዙ አልጽፍም፤ እጅጉን
ስለምሳሳላት እና ረቂቅነቷን አሳንሼ እንዳልገልፀው ስለምፈራ!
👉ከአንዲት የውበት ገንቦ ከሆነች ቀዘባ ልጃገረድ ኃይለኛ ፎንቃ የያዘው ወጣት ማፍቀሩን በምን ቋንቋ
ማስረዳት እንዳለበት የሚቸገረውን ያህል እኔም ለእምዬ ጎንደር ያለኝን ፍቅር እንዴት መግለፅ እንዳለብኝ እንኳን አላውቅም
👉 ጎንደር የአያት ቅድመአያቶቼ
፤የእኔም፤የልጅ ልጅ ልጆቼም ጭምር የኩራታቸው ምንጭ፤ የኢትዬጲያ ደማቅ
ክብር የሚቀዳብሽ የክብር የወርቅ ጋን ነሽ!
👉ጎንደር ሁሉ በጄ ሁሉ በደጄ!
👉 ጎንደር
የብሉልኝ ጠጡልኝ ምድር!
ጎንደር የኃቀኞች ባድማ የአማራነታችን ግርማ!
👉 ጎንደር
የዓለማዊም ሆነ የመንፈሳዊ ጥበብ የልኅቀት ማዕከል!
👉 ጎንደር እንኳንስና እኛ ጥበብሽን ሞቀን ጥበብሽንም ተጎናፅፈን ለብሰን ያደግነው ልጆችሽ ቀርቶ የጥበብ
መዓዛሽ በሩቁ ያወዳቸው በዓዳን ወደ እልፍኝሽ ገብተው የኅሊና ርኃባቸውን ከማስታገስ አልፈው በርካቶችም ጎንድረው («ጎንደሬ» ሆነው) ቀርተዋል።
👉ፍቅርሽ ከሩቁ ማንንም ያንበረክካል።
👉«የተኛውን ፍቅሬን ቀስቅሱት ይነሳ፣
👉ዓለሙን ያስደምም ጥቁረቴ ድል ይንሳ»
እያልሽ ለዘመናት ስትጣሪ ኖረሻል ።
👉ዕድለኛው ይኸ የኔ ትውልድ ጆሮዎቹ ጥሪሽን
አድምጧል።
👉 እናም ወደ ቀደመ ክብራችን፤ ወደ ገናናው ሥልጣኔያችን መናገሻችን
በምናደርገው ትግል ውስጥ ጎንደር በልባችን የታተምሽ ከአፋችን የማንነጥልሽ
መሪ ኮከባችን ነሽ።
👉እምዬ ጎንደር እንኳንም የኢትዮጵያዊነት አርማ የሆንሽ! ስላንቺ ብዙ
ብልም መግለጫ የለኝም፤ ከማንም ከምንም አላወዳድርሽም ።
ጎንደር ላንቺ
አቻየለሽም!

መይሳዉየወንዶቹ ባል መይሳዉ ካሳእንኳን ለጠላቱ ለራሱ ማይሳሳተኩሶ ማይሰት ጥሎ ፎካሪለሀገሩ አለኝታ ለወገኑ አኩሪጠላት አባሮ ወንዝ አሻጋሪማን ይፈታታል የቴዲን ሱሪአንድ ለእናቱ ሺ ለጠላቱአሞ...
26/06/2020

መይሳዉ

የወንዶቹ ባል መይሳዉ ካሳ
እንኳን ለጠላቱ ለራሱ ማይሳሳ
ተኩሶ ማይሰት ጥሎ ፎካሪ
ለሀገሩ አለኝታ ለወገኑ አኩሪ
ጠላት አባሮ ወንዝ አሻጋሪ
ማን ይፈታታል የቴዲን ሱሪ
አንድ ለእናቱ ሺ ለጠላቱ
አሞተ ኩሩ ጠንካራ በርቱ
ጀግናዉ ጎንደሪ ወንዱ ተባቱ
እጁን አይሰጥም ሳለች ጥይቱ
ቃሉን አካባሪ ሀገር ወዳዱ
የቋራዉ ጀግና ቆራጡ ወንዱ
ሺ ቢወለድ ሺ ነዉ ጉዱ
እንደ ቴዎድሮስ ይበቃል አንዱ

 👉የኢትዮጵያ ጥንታዊ ከተሞች ስም ሲነሳ ለረዥም ዘመናት የመንግሰት መቀመጫ በመሆን ካገለገሉት ቀድማ የምትነሳው ጎንደር ከተማ ነች፡፡በ17ኛው ክፍለ ዘመን የመጀመሪያ አጋማሽ ላይ በ1620ዎቹ...
26/06/2020



👉የኢትዮጵያ ጥንታዊ ከተሞች ስም ሲነሳ ለረዥም ዘመናት የመንግሰት መቀመጫ በመሆን ካገለገሉት ቀድማ የምትነሳው ጎንደር ከተማ ነች፡፡

በ17ኛው ክፍለ ዘመን የመጀመሪያ አጋማሽ ላይ በ1620ዎቹ በአጼ ፋሲለደስ ዘመነ መንግስት የተቆረቆረችው ጎንደር ከተማ ለ250 ዓመታት ገዳማ የኢትዮጵያ ዋና ከተማ በመሆን መዲናነቷን አስመስክራለች፡፡

የጎንደር ከተማ ከአዲስ አበባ 740 ኪሎሜትር እንዲሁም 175 ኪሎሜትር ከክልሉ መዲና ባህር ዳር ከተማ ትርቃለች፡፡
ጎንደር 2200 ሜትር ከባህር ወለል በላይ ከፍታ ትገኛለች፡፡
ከተማዋ በመካከለኛው ዘመን ኢትዮጵያን ያስተዳድሩ የነበሩ ነገስታትን አሻራዎች በውስጧ ይዛለች፡፡በጊዜው ነገስታቶች ከቦታ ቦታ እየተዟዟሩ ሀገራቸውን የማስተዳደር ልምድ ነበራቸው ሆኖም ጎንደር ላይ ግን ስድስት ነገስታቶች እየተፈራረቁ በዋና ከተማነት ተጠቅመዉባታል፡፡

👉የራሳቸውንም አብያተክርስትያናትና ገዳማት ያሰሩ ነበር፡፡
👉ጎንደር ከተማም ጥንታዊ የህንጻ ጥበቦች እጅጉን የሚስተዋሉባት ከተማ ነች፡፡
👉ወደር ከማይገኝላቸው ህንጻዎች ውስጥም የጎንደር አብያተ መንግስታት ወይም ፋሲል ግቢ ይገኝበታል፡፡ የፋሲል ግቢ እኤአ በ1978 በዩኔስኮ የዓለም ቅርስ ሆኖ ተመዘግቧል፡፡70 ሺህ ካሬ መሬት ላይም አርፏል፡፡አብያተ መንግስታቱ የተገነቡትም ከእንጨትና ከኖራ ሲሆን ለግንበታ የዋሉት ቁሳቁሶች ከቁስቋምና ከጅብ ዋሻ እንደመጡም ድርሳናት ይመሰክራሉ፡፡

በነገራችን ላይ በፋሲል ግቢ ውስጥ 6 ነገስታቶች ተፈራርቀዋል፡፤
1ኛ/አጼ ፋሲለደስ-1624-1659
2ኛ/አጼ አዕላፍ ሰገድ ዮሀንስ -1660-1674
3ኛ/አጼ አድያም ሰገድ እያሱ-1674-1698
4ኛ/አጼ ዳዊት ሳልሳዊ-1708-1713
5ኛ/አጼ በካፋ-1713-1723
6ኛ/አጼ ብርሃን ሰገድ እያሱ1723-1747 እንዲሁም እቴጌ ምንትዋብ መቀመጫቸውን በግቢው ውስጥ አድርገው እንዳስተዳደሩ መረጃዎች ያሳያሉ፡፡

ፋሲል ግቢ 12 በሮች እንደነበሩት ይነገራል፡፡

👉እንኮየ በር፣ዕቃ ግምጃ ቤት በር፣ፊት በር/ጃንተከል በር/ወንበር በር፣ተስካር በር፣አዘዝ ጥቁሬ በር፣አደናግር በር፣ኳሊ በር፣እምቢልታ በር፣ፈረስ ባልደራስ በር፣እርግብ በር እና ቀጭን አሽዋ በር ተብለው ይጠራሉ፡፡

👉ከግቢው ውጭም በተመሳሳይ ዘመን የተገነቡ ኪነህንጻዎች ይገኛሉ፡፡ለአብነትም የራስ ሚካኤል ስሁል/ራስ ግንብ/ እና የደብረብርሃን ስላሴ ቤተክርስትያን አንዱ እና በርካቶች ለጉብኝት የሚመርጡት ቤተክርስትያን ነው፡፡

👉በውስጡም ጥንታዊ ስዕሎች ያረፉበት የጎንደር የአሳሳል ዘዴ ያረፈበት ግሩም የህንጻና የስዕል ጥበብ አሻራ ነው፡፡

ግድግዳውና ጣሪያው በስዕል ያሸበረቀ ቤተክርስትያን ነው፡፡ምንም አይነት ጉዳት ያልደረሰበት የዘመኑ ጥበብን ፍንትው አድርጎ የሚያሳይ ኪነ-ህንጻ ነው፡፡

ቁስቋም፡ከከተማዋ 3 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የሚገኝ የእቴጌ ምንትዋብ ግቢ ሲሆን ጉዳት ደርሶበት አብዛኞቹ የኪነ-ህንጻው ክፍል ፈርሷል፡፡ሆኖም ቆመው በሚገኙት ግድግዳዎች ላይ ያሉት የአንበሳና የዝሆን ምስሎች አሁንም ዘመኑን ለመመልከት ሁነኛ መስታወት ናቸው፡፡

ቁስቋም እጅጉን እድሜ ጠገብ የጽድና ሀገር በቀል ዛፎችን የያዘች ቤተክርስትያን ነች፡፡
በውስቷም በርካታ ቅርሶችን አቅፋ የያዘች የከተማዋ የመስህብ መዳረሻ ነች፡፡

የአጼ ፋሲል መዋኛ ገንዳ ለጎንደር ከተማ ጎብኝዎችን ከሚስቡ መስህቦች ይመደባል፡፡

ምክንያቱም በጎንደር ከተማ የሚከበረው የጥምቀት በዓል የታቦታት መዳረሻ ስለሆነ ነው፡፡

ነብስ ይማር  😭😭😭
25/06/2020

ነብስ ይማር 😭😭😭

 የኢትዮጵያ ፌዴራሊስት ኃይሎች ጥምረት ህወሓትን ከጥምረቱ አባልነት መሰረዙን አስታወቀ*******************************የኢትዮጵያ ፌዴራሊስት ኃይሎች ጥምረት ህወሓት ከአባልነት...
25/06/2020



የኢትዮጵያ ፌዴራሊስት ኃይሎች ጥምረት ህወሓትን ከጥምረቱ አባልነት መሰረዙን አስታወቀ
*******************************
የኢትዮጵያ ፌዴራሊስት ኃይሎች ጥምረት ህወሓት ከአባልነት መሰረዙን
አስታውቋል።

ጥምረቱ ይህንን ውሳኔ ያስተላለፈው በ4ኛው መደበኛ ጠቅላላ መደበኛ ጉባዔው ላይ ነበር፡፡

የኢትዮጵያ ፌዴራሊስት ኃይሎች ጥምረት ህወሃትን ከጥምረቱ የሰረዘበት ምክንያት ህወሃት የጥምረቱን መተዳደሪያ ደንብን ባለመክበሩ መሆኑን ገልጿል።

ጥምረቱ የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን አስመልክቶ ምርጫ እንደማይኖር ወይም ደግሞ የምርጫው መካሄድ ተገቢ እንዳልሆና መክሯል፡፡
በሀገሪቱ ላይ ሰላምና ጸጥታ ሊሰፍን በሚችልባቸው ሀሳቦችም ላይ ውይይት መደረጉ ተገልጿል፡፡

የኢትዮጵያ ፌዴራሊስት ኃይሎች ጥምረት ሊቀመንበር አቶ ደረጀ በቀለ እንደገለጹት፣ ህወሃት ከአንድም ሁለት ጊዜ በተጠረው ስብሰባ ላይም አልተገኘም ብለዋል፡፡

ሕህወሃት ለሀገር መግባባት በማይጠቅምና አፍራሽ በሆነ አካሄድ አዲስ አበባ ላይ የሚካሄዱ ስብሰባዎች ህገ ወጥ ናቸው የሚል ግፊት ሲያደርግባቸው እንደነበር ሊቀመንበሩ ተናግረዋል፡፡
በተቃራኒው ደግሞ ስብሰባዎቹ በመቐለ ከተማ ይደረጉ የሚል ግፊት በህወሃት በኩል ሲደረግብን ነበር ብለዋል አቶ ደረጀ፡፡

ሪፖርተር :- እስሌማን አባይ

ጎንደር አራዳ !!
25/06/2020

ጎንደር አራዳ !!

አባይ ግድብ ግድብ ብቻ አይደለም ህልውናም ጭምር ነው።ከዚህ በኃላ የመኖር እና ያለመኖር ጉዳይም ጭምር ነው።አባይ የደሞዝ ጭማሪያችን ጉዳይ ነው።አባይ የንሮ ውድነትን የመቀነሻ መሳሪያዎችን ነ...
24/06/2020

አባይ ግድብ ግድብ ብቻ አይደለም ህልውናም ጭምር ነው።
ከዚህ በኃላ የመኖር እና ያለመኖር ጉዳይም ጭምር ነው።
አባይ የደሞዝ ጭማሪያችን ጉዳይ ነው።
አባይ የንሮ ውድነትን የመቀነሻ መሳሪያዎችን ነው።
አባይ የሴቶችን ጫና ከጫንቃቸው ላይ የመቀነሻ ጉዳያችን ነው።
አባይ የጎዳና ተዳዳሪዎችን ወደ ትምህርት እና ስራ የምናሰማራበት የስራ አድል
መፍጠሪያ አጀንዳችን ነው።
አባይ ማህበራዊ እረፍት ማግኛችንም ነው ።

ፔጁን ላይክ ሸር በማድረግ ይቀላቀሉን !!
24/06/2020

ፔጁን ላይክ ሸር በማድረግ ይቀላቀሉን !!

  ..ስለህዳሴው ሙሌት...ፕሬዝዳንት ኢሳያስ ስለግብጽና 13ቀናት ብቻ ስለቀሩት የህዳሴው ሙሌትአጋርነቱን አረጋገጠ ...!"…እኛ ኢትዮጵያ ሁለተኛ ሀገራችን ናትና፤ ኢትዮጵያ በሉዓላዊ ግዛቷ ...
24/06/2020

..ስለህዳሴው ሙሌት...

ፕሬዝዳንት ኢሳያስ ስለግብጽና 13ቀናት ብቻ ስለቀሩት የህዳሴው ሙሌት
አጋርነቱን አረጋገጠ ...!

"…እኛ ኢትዮጵያ ሁለተኛ ሀገራችን ናትና፤ ኢትዮጵያ በሉዓላዊ ግዛቷ በራሷ ወንዝ ግድብ እየገነባች መገኘቷን እንመሰክራለን፣ እናምናለን። ግብፅ ይህ እንዳይሳካ
ብዙ ጥራለች።

እኛንም መጠቀሚያ ለማድረግ ከብዙ ማማለያዎች ጋር ረብጣ
ዶላሮችን አቅርባለች።

ምስጋና ለክቡር ዳክተር አብይ ይሁንና የዚህ ክፋት ፀሐይ ጠልቃለች። ድሮም ጠላታችን የወያኔ ስርዓት እንጂ የኢትዮጵያ ህዝብ አልነበረም። የኢትዮጵያ ዕድገት ለኛም ይተርፋል፣ ደስ ይለናል።

እንኳን ከግብፅ መሻረክ ኢትዮጵያ ስትነካ እኛንም ያመናል።
አሁን ግብፅ የተለያዩ ጫና እንድትፈጥር ዕቅዶችን የሚያቀርቡ የክህደት ባለቤት የሆኑ የወያኔ ሰዎች እንዳሉ መረጃ አለን።

ኢትዮጵያ አይደለም አንድ፣ ሰላሳ ግድብ ብትሰራ እንደግፋለን። የፈለገው ነገር ቢመጣ ከኢትዮጵያ ጎን ነን።

ግብፅ የቅኝ ግዛት ህጎች ይከበሩ ካለች እንግሊዝ ከኢትዮጵያ መደራደር
አለባት።ሕልም አለኝ። ኢትዮጵያ በግድቡ ታድጋለች።
ድህነትን ታጠፋለች። ከከፋፋይ የብሔር ሴረኞች ተላቃ ሁሉም ሀገሬ ይላታል።

ታላቅም ነበረች፣ ታላቅ ትሆናለች። ብዙ አባይ ግድቦችን ትሰራለች።
ኢትዮጵያውያን አሸናፊ ይሆናሉ፣ ሀቅን ይዘዋልና።
ይህ የእያንዳንዱ ኤርትራዊ ፅኑ እምነት ነው። ለዘላለም የማንፍቀው ወንድም
ኤርትራውያን።
...

24/06/2020
 #ሰበር ዜና ግብፅ ከታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ጋር በተያያዘ ለአረብ ሊግ ያቀረበችውን የውሳኔ ሀሳብ ጅቡቲ፣ ሶማሊያና ኳታር ተቃውመውታል።የአረብ ሊግ አባል ሀገራት በዛሬው እለት ስብሰባ...
23/06/2020

#ሰበር ዜና

ግብፅ ከታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ጋር በተያያዘ ለአረብ ሊግ ያቀረበችውን የውሳኔ ሀሳብ ጅቡቲ፣ ሶማሊያና ኳታር ተቃውመውታል።
የአረብ ሊግ አባል ሀገራት በዛሬው እለት ስብሰባቸውን በማካሄድ ላይ ይገኛሉ።
የአረብ ሊግ በስብሰባው ግብፅ ከታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ጋር በተያያዘ ለአረብ ሊግ ያቀረበችውን የውሳኔ ሀሳብን ጨምሮ የሊቢያ ጉዳይንም በመመልከት ላይ ይገኛል።

በዚህ ስብሰባ ላይም የሊጉ አባል ሀገራት የሆኑት ጅቡቲ፣ ሶማሊያና ኳታር የግብፅን
ከታላቁ የውሳኔ ሀሳብን እንደማይቀበሉት አስታውቅዋል።

  ...  .."ፀሐይ በእሳታማ ቀለበት ተሞሽራ በማየት በሕይወቴ ካስደሰቱኝ ዕለታት ውስጥ አንደኛው ዛሬ ነበር። "ዶ/ር ሮዳስእውነት ለመናገር ዛሬ አንተና ጨረቃ የተጋባችሁበት የሰርጋችሁ እለ...
21/06/2020

...

..

"ፀሐይ በእሳታማ ቀለበት ተሞሽራ በማየት በሕይወቴ ካስደሰቱኝ ዕለታት ውስጥ አንደኛው ዛሬ ነበር።
"ዶ/ር ሮዳስ
እውነት ለመናገር ዛሬ አንተና ጨረቃ የተጋባችሁበት የሰርጋችሁ እለት፣ ጸሀይ እና ከዋክብቶቹ ሚዜዎቻችሁ ሆነው የደመቃችሁበት ታሪካዊ ቀን ነው.....፡፡

እግዚአብሔር የአባቶቻችንን ጥበብ የገለጸልህ ያልተዘመረልህ የዘመናችን ዕንቁና መንፈሳዊ ሳይንቲስት።
እኛ እንደሆን ነጭ "ያልባረከው" እውነት ስለማይመስለን ለማበረታታት የዘገየን ለመተቸት ግን የፈጠንን ነን።

ይኼኔ ዛሬ ይሄ ግርዶሽ እውን ባይሆን ኑሮ ስንት አጥንት ሰባሪ ጹሁፎች ይፃፍ ነበር።

እንኳን በአንተ በቤተክርስቲያን ላይ እንዴት ይዘመትባት ነበር
ዶ/ር መጋቤ ሐዲስ ሮዳስን ማድነቅም ማክበርም ግድ ይለናል።

መንፈሳውያን በዓለምም የእውቀትና የጥበብ ባልደራሴ መሆናቸው ጥንታዊቷ ቅድስት ቤተክርስቲያን ልምድ ውስጥ ጎልቶ የወጣ ሀቅ ነው። ቅዱስ ሉቃስ ከወንጌል አገልግሎቱ በተጨማሪ በህክምና ሙያ አንቱ የተባለለት እንደነበረ ዜና ድርሳኑ ያሳያል።

የስነ ከዋክብት ሚስጥራትን የገለፀው ኢትዮጵያዊው ቅዱስ ሄኖክ እንደሆነ መጽሐፈ ሄኖክን መግለጥ ብቻ በቂ ነው።

ቅዱስ ያሬድ ዛሬም ድረስ በመቅደስ እና በዓለም ሰዎች የሚጠቀሙትን ዜማ ሰርቷል።

ጠቢቡ ሰለሞን በዳኞታ ዝናው የናረ ነበር ። ዕዝራ የእውቀትና የጥበብን
ጥግ ተመልክቷል።
ዛሬ ይህን ልምድ በመጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ ተመልክተነዋል። መጽሐፍ ዘርግቶ፤ አውድ ነቅሶ፤ ርዕስ መርጦ የሀዲስ ኪዳን ወንጌልን ሲያመሳጥር የቅዱስ ዮሐንስ የአባ ህርያቆስ ፀጋ እንዳልተለየው ያሳብቃል።
በዓለማዊ እውቀቱ እስከ ዶክትሬት ዲግሪ [ PhD in astronomy (degree of philosophy in astronomical science )] የደረሰ በሁለት ጎኑ የተሳለ ታላቅ ሰው ነው።

እንኳን የፀሐይ ግርዶሽን ይቅርና የክረምት ዝናብን በትክክል መተንበይ በማይቻልበት ሀገር ስለ ፀሐይ ግርዶሽ ትዕይንት የቀን ቀመሩን እየገለጠልን ንቃተ ህሊናችንን ከፍ አድርጎልን የዛሬን ክስተት መመልከታችን የእዚህ እውነት አማናዊ ምስክር ነው

 # እንቢ_አለኝ_እንቢ_አለኝለአባቱ ብናገር እንቢ አለኝ እንቢ አለኝለእናቱ ብንገር እንቢ አለኝ እንቢ አለኝለወንድሙ ብናገር እንቢ አለኝ እንቢ አለኝለእህቱ ብናገር እንቢ አለኝ እንቢ አለኝእ...
17/06/2020

# እንቢ_አለኝ_እንቢ_አለኝ
ለአባቱ ብናገር እንቢ አለኝ እንቢ አለኝ
ለእናቱ ብንገር እንቢ አለኝ እንቢ አለኝ
ለወንድሙ ብናገር እንቢ አለኝ እንቢ አለኝ
ለእህቱ ብናገር እንቢ አለኝ እንቢ አለኝ
እምዬ በመንካት እጅግ አስቸገረኝ
እንግዲህ ምን ላድርግ ለጥይቴ ልንገር ለሚገላግለኝ
# ዘራፍ_ያባቱ_ልጅ

አምባዬ!ገዳይ የማውቃችሁ ደሜን አታፍስሱትከልቤ ይቀዳል ወንድማለም ማለትፍቅርእንዲያስተምር አዳራሹን እርጩት
11/06/2020

አምባዬ!

ገዳይ የማውቃችሁ ደሜን አታፍስሱት
ከልቤ ይቀዳል ወንድማለም ማለት
ፍቅርእንዲያስተምር አዳራሹን እርጩት

 # እማማ_ወልቃይት---------የአርባ አመት ተጋድሎ የማንነት ቋቱወልቃይት ጠገዴ ዳገት ቁልቁለቱየፋኖ ነጭ ለባሽ ከፋኝ የጠለምቱየአውራ የአቀወርቁ የቃፍታ ሰቲቱውሳኔ ዳኝነት የሚሰጥበቱፋይሉ...
11/06/2020

# እማማ_ወልቃይት
---------
የአርባ አመት ተጋድሎ የማንነት ቋቱ
ወልቃይት ጠገዴ ዳገት ቁልቁለቱ
የፋኖ ነጭ ለባሽ ከፋኝ የጠለምቱ
የአውራ የአቀወርቁ የቃፍታ ሰቲቱ
ውሳኔ ዳኝነት የሚሰጥበቱ
ፋይሉን በደም ፅፈው የፈረሙበቱ
ታሪካዊ ዳራው ይህ ነው መስሪያ ቤቱ
እማማ ወልቃይት መልካም ወላዲቱ
ሀምሌ አምስት ይመስክር ዛሬም እንደጥንቱ
አርማጭሆ ክንዷ ዳባት ነው ትራሷ
ጎንደር በጌምድር አማራ ነው ልብሷ
ተከዜን ተሻግራ አትዳርም እሷ
ካለ ፍላጎቷ ቀን ጥሏት እማማ
አግብታለች አሉኝ ጊዚያዊ ውሽማ
//አንድቀን ግን...
የውሽሜ ነገር እንደምናውቀው ነው
ሲወጣ አካሔዱ ፌስታል ጠቅሎ ነው
የተፅኖው ሸክም ሲላቀቅ ከጫንቃ
የእነ ውሸት ዘመን ጊዚያቸው ሲያበቃ
እሷም ታገባለች ማንነት ጠይቃ
ያች ወልቃይቴ የአማራዎች ልጅ
አትጋባም ከዛ ተገዳ ነው እንጅ
እማማ ወልቃይት ውባለም ውቢቱ
ክብርሽ እንዲመለስ ዛሬም እንደ ጥንቱ
ይሉሻል ልጆችሽ ጎንደሬ አማራይቱ
እውነት ያሸንፋል!

ዘመቻ ምዕራብ ጎንደር ፤ እኔም ከገበሬው ጎን እቆማለሁየደ/ታቦር በጎፈቃደኛ ወጣቶችና የአገልግል የተፈጥሮ ጥበቃ በጎ አድራጎት ማህበራት 👉እኔም ከገበሬው ጎን እቆማለሁ በሚል መሪ ቃል መነሻቸ...
10/06/2020

ዘመቻ ምዕራብ ጎንደር ፤ እኔም ከገበሬው ጎን እቆማለሁ
የደ/ታቦር በጎፈቃደኛ ወጣቶችና የአገልግል የተፈጥሮ ጥበቃ በጎ አድራጎት ማህበራት

👉እኔም ከገበሬው ጎን እቆማለሁ በሚል መሪ ቃል መነሻቸውን
በጥንታዊቷ የመይሳው ከተማ ደብታቦር አድርገው ከጉና፣ ርብ ተፋሰስን አካለው እስከ ጣና ድረስ በገበሬው ቀየ ዘልቀው ስለኮሮና መከላከያና የተፈጥሮ ጥበቃ ዘዴዎች የግንዛቤ ገለጣ ሲያደርጉ ከራርመው ዛሬ ደግሞ ወደ ምዕራቡ የጎንደር (ቆላማው) ሰሊጥ አመራች ገበሬ በአረንጓዴ መለያቸው ብቅ ብለዋል፡፡

👉አዳራቸውን በመናገሻ ጎንደር አድርገው በጠዋቱም ወደ ቆላው አምራችና ድንበር ጠባቂው ገበሬ ወገናቸው ቀየ ዘልቀዋል፡፡

👉በጉዟቸውም የተለመደውን ግንዛቤ
ትምህርት እየሰጡ የወጣቶችን የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ባህል ለማሻሻል የሚያነሳሳ መልዕክት ያስተላልፋሉ፤ወጣቶች በእንደዚህ ያሉ የበጎ ፈቃድ ስራዎች ተሳተፉ ፤ሀገርና ህዝብ የሚለማውና የሚለወጠው በበጎፈቃደኛ ወጣቶችና በቁርጠኛ መሪዎች ነውና፡፡

👉የጉዞ ወጫቸውንና የመጓጓዣ መኪና የቴወድሮስን ራዕይ የማሳካት ሃላፊነት የተጣለበት የደ/ታቦር ዩኒቨርሲቲ በመስጠት ትብብር አደርጓልና ምስጋና ይገባዋል አገልግንና የዲቲ በጎ ፈቃድ ወጣት ማህበራትን በርቱ በሉልን!
#በሪሁን አሰፋ

ወ/ሮ ኬርያ ኢብራሂም ከፌዴሬሽን ም/ቤት አፈ ጉባኤነታቸው መልቀቃቸው ለራያእና ለወልቃይት ህዝብ ትልቅ እፎይታን ያስገኛል!"(ዶክተር ሲሳይ መንግስቴ)ሸር በማድረግ ለሌሎች ያጋሩ !!
09/06/2020

ወ/ሮ ኬርያ ኢብራሂም ከፌዴሬሽን ም/ቤት አፈ ጉባኤነታቸው መልቀቃቸው ለራያ

እና ለወልቃይት ህዝብ ትልቅ እፎይታን ያስገኛል!"
(ዶክተር ሲሳይ መንግስቴ)

ሸር በማድረግ ለሌሎች ያጋሩ !!

  👉ባህልን፤ 👉እምነትን፤ 👉ሃይማኖትን፤ 👉የተፈጥሮ ሃብትን እና ህልውናን መታደግ ነው እና በጋራ እንረባረብ!ሸር በማድረግ ለሌሎች ያጋሩ !!
06/06/2020


👉ባህልን፤ 👉እምነትን፤ 👉ሃይማኖትን፤ 👉የተፈጥሮ ሃብትን እና ህልውናን መታደግ ነው እና በጋራ እንረባረብ!

ሸር በማድረግ ለሌሎች ያጋሩ !!

ብርሀን ለሆነ ህዝብ ብርሀን መከልከል የአባይን ሀገር ከአባይ አትጠቀሙ ብሎእንደመከልከል ይቆጠራል።በኢትዮጵያ የስልጣኔ ጉዞ ፊተኞች የኋለኞች እንዲሆኑ አንሻም ኋለኞቹን ወደ ፊትማምጣት እንጅ ...
06/06/2020

ብርሀን ለሆነ ህዝብ ብርሀን መከልከል የአባይን ሀገር ከአባይ አትጠቀሙ ብሎ
እንደመከልከል ይቆጠራል።
በኢትዮጵያ የስልጣኔ ጉዞ ፊተኞች የኋለኞች እንዲሆኑ አንሻም ኋለኞቹን ወደ ፊት
ማምጣት እንጅ በብልፅግና ዘመን የኋለኛው ማየት ለወደፊት ከተጠቀመ ብቻ
እንጅ ለመቆዘም አንጠቀምበትም።
ከዘመናት በፊት የኢትዮጵያ ዘመናዊ ኢንዱስትሪ የተተከሉበት ከተማ መብራት ይዛ
እራት ስታበላ መኖሯ ሌላ ማረጋገጫ አያስፈልግም።
ታሪክ ጥበብና ትምህርት የተገመደባት ከተማ ናት ደብረታቦር
በኢትዮጵያ ህዝቦች የአንድነት ታሪክ የኦሮሞ እና የአማራ እንዲሁም የትግራይ
የጋራ ታሪክ የምታሳይ ታሪካዊ ከተማ ናት የኢትዮጵያ እና የእንግሊዝን ታሪክ
የምታሳይም ከተማ ናት ደብረታቦር።
የቅኔ ዜማ መፍሰሻ ከተማ ናት ደብረታቦር የተክሌ ዩኒቨርስቲ መገኛ ከተማ ናት
የአፄ ቴወድሮስ ራዕይ የተገለጠባት ከተማ ናት ደብረታቦር ።
በዝች ከተማ መብራት ገባ ብሎ ማድነቅ አይገባም ነበር ታሪክ ግን በአስገራሚ
እና በተቃርኖ የተሞላ ነውና የመብራት ማከፋፈያ መሆን በነበረባት ከተማ መብራት
በመግባቱ እየተደሰትን እንገኛለን ቁጭቱ ጥሩ ነው ወደ ሀዘን ሳይሆን ወደ ስራም
ይወስደናል።
ደብረታቦር ከተማ ወደ ሚገባት ብልፅግና መሄድ አለባት በከፍታ ላይ ያለችው
ከተማ ከዚህ የሚልቅ ከፍታ ይገባታል።
ኑ ቆርጠን እንነሳ
ኑ ተባብረን እንስራ
ኑ ወደ ፊት እንሂድ
ኑ ወደ ኢንዱስትሪ ከተማነቷ እንመልሳት ።
አመሰግናለሁ
ተመስገን ጥሩነህ
ሸር

አዲስአበባ ኢትዮጵያ 💚💛❤አራት ኪሎ ሃዉልት በተመረቀበት ወቅት !!ላይክ ሸር
06/06/2020

አዲስአበባ ኢትዮጵያ 💚💛❤

አራት ኪሎ ሃዉልት በተመረቀበት ወቅት !!

ላይክ ሸር

የአፍሪካ ትልቁ የገበያ ማዕከል መርካቶ ቀደምት ገፅታፔጁን ላይክ ሸር
06/06/2020

የአፍሪካ ትልቁ የገበያ ማዕከል መርካቶ ቀደምት ገፅታ

ፔጁን ላይክ ሸር

Address


Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Gondar today ጎንደር ዛሬ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

  • Address
  • Alerts
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share