South Ethiopia

  • Home
  • South Ethiopia

South Ethiopia Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from South Ethiopia, Media/News Company, .

28/02/2024
28/02/2024

የደብብ ኢትዮጵያ ክልል መስተዳድር ምክር ቤት ዛሬ በበይነ መረብ ባደረገው ስብሰባ በተለያዩ ረቂቅ አዋጆችና ደንቦች ላይ በመወያየት ለክልሉ ምክር ቤት ቀርቦ እንዲፀድቅ ውሳኔ አስተላልፏል።

የመስትዳድር ምክር ቤት አባላቱ ዛሬ ባደረጉት ውይይት ክልሉ ህግን ተከትሎ ስራዎችን መስራት የሚያስችሉ 19 አዋጆችና አንድ ደንብ ላይ ውይይት በማድረግ ለሚመለከተው አካል ቀርቦ እንዲፀድቅ በሙሉ ድምፅ ወስኗል።

በተጨማሪ ምክር ቤቱ የክልሉን የ6 ወር አፈፃፀምም በመገምገም ስብሰባውን አጠናቋል።

28/02/2024

ስንተባበር ታሪክ ሰርተናል፤ እንሰራለንም!

ከውይይት ይልቅ ጦርነትን የማስቀደምን ኋላቀር አስተሳሰብ ብዙ አገራት ታሪክ አድርገውታል። አንዳንዶች ካሳለፉት ታሪክ ተምረው ሌሎቹ ደግሞ ከሌሎቹ ትምህርት ወስደው ላለመገዳደል ተማምለዋል።

የማሰብና የማሰላሰል ህሊና እያላቸው ከእንስሳት በታች ወርደው ወንድም ወንድሙን በመግደል የሚመፃደቁ፣ መግደል መሸነፍ መሆኑን የማይረዱ ቡድኖች ያሉባቸው አገራት ደግሞ ጦርነትን ታሪክ ማድረግ ባለመቻላቸው ፈራርሰው ታሪክ ሆነዋል።

በየአገሩ ያሉ አሸናፊ ሀሳብ የሌላቸው ጦር ሰባቂዎች ጭምር የሚረዱት እውነታ በንፁሀን መስዋዕትነት ሀብትን የማገባስ ጊዜአዊ የፖለቲካ ፍጆታ እንጅ ጦርነት ትናንትም ሆነ ዛሬ ነገም ወደፊትም የሚፈታው ችግር አለመኖሩን ነው።

ግጭቶችን በሰላማዊ መንገድ የመፍታት ቱባ ባህላዊና ሀይማኖታዊ እሴቶች ያሏት ኢትዮጵያ የውይይት ባህል ባለመዳበሩ እንጅ በንግግር የማይፈታ አንዳች ችግር አለመኖሩን በመገንዘብ ፓርቲያችን ለትብብርና ለፉክክር ፖለቲካ ይተጋል።

የውይይትን ባህልን ለማዳበር አገር በቀል እውቀቶችን ከዴሞክራሲያዊ መርሆች ጋር በማቀናጀት ለመጠቀም ከሚደረገው ጥረት ባሻገር መሰረቱን ለማፅናት ነፃ እና ገለልተኛ ተቋማትን መገንባት ልዩ ትኩረት ተሰጥቶታል።

የኛ ትውልድ የህዝባችንን ህይወት የመቀየር እና ኢትዮጵያን ወደተሻለ ደረጃ የማሻገር ሀላፊነት ያለበት የተንከባለለ ዕዳ ከፋይ ጭምር ነው።

ብርቱ ስንሆን ኢትዮጵያን ለወዳጅነትና ለሽርክና የሚፈልጋት ብዙ ነው። ስንደክም ግን ደካሞች ጭምር ውክልና ተሰጥቷቸው ይጎነትሏታል።

ዓለም አንድ መንደር በሆነችበትና የተለያዩ ዓለም አቀፍ ተቋማት ከሉዓላዊ አገራት የገዘፈ ፈርጣማ ጡንቻ በያዙበት በዚህ ዘመን የውጭ ተፅዕኖ ቀላል ባይሆንም የአገራት አስተማማኝ ሰላም፣ ዕድገትና ተፅዕኖ ፈጣሪነት የሚወሰነው በውስጥ አቅም ነው።

አገራችን በቅርቡ ገብታበት ከነበረው ውስጣዊ ፈተና እና ውጫዊ ጫና በድል ተሻግራ ብሪክስን ከመሰለ ተፅዕኖ ፈጣሪ ስብስብ አባል የሆነችው፣ በቅርቡም ከሶማሌላንድ ጋር በሰጥቶ መቀበል መርህ ወደብ ለማግኘት እየተደረገ ያለው ጠንካራ የዲፕሎማሲ ስራ ተጨባጭ ጥንካሬዋንና የወደፊት ተስፋዋን አመላካች ነው።

ዲፕሎማሲያችን ወይም አጠቃላይ የውጭ ግንኙነታችን ውስጣችን ሲደክም የሚዳከም ስንጠነክር ደግሞ የሚጠነክር በመሆኑ ቁልፉ በእጃችን ነው።

ያለችን አንዲት አገር ናት፤ አንድ አይን ያለው በአፈር አይጫወትም እንዲሉ አበው መቼም ይሁን የትም ማንም ኢትዮጵያን ለድርድር ማቅረብ አይገባም። ሲመቸን የምንወዳት ሳይመቸን የምንረግማት ሳይሆን የከፍታዋም የዝቅታዋም ምክንያት እራሳችን መሆናችንን ተረድተን ድህነቷን ቀርፈን ብልፅግናዋን ለማረጋገጥ ታሪካዊ አሻራችንን እናሳርፍ!

27/02/2024

ሰላም የፖለቲካ መረጋጋት ከማረጋገጡም በላይ ለአዎንታዊ የህዝብ ለህዝብ ትስስር ከፍተኛ ሚና አለው፦

ኢትዮጵያ የተለያዩ ብሄሮች፣ ብሄረሰቦች ፣ ህዝቦች እና ሀይማኖቶች ተዋድደውና ተከባብረው የሚኖሩባት ሀገር ናት።

ሠላም የፖለቲካ መረጋጋትን በማስፈን ውጤታማ አስተዳደር እንዲኖር እና የዴሞክራሲ ተቋማትን መመስረት ያስችላል። ለኢኮኖሚ ዕድገት ምቹ ሁኔታን ይፈጥራል፣ ኢንቨስትመንቶችን ይስባል፣ ለህዝቡ የስራ እድል ይፈጥራል።

በተጨማሪም ሰላም ለሰብአዊ መብቶች መከበር እና መሰረታዊ አገልግሎቶችን እንደ ትምህርት፣ ጤና አጠባበቅ እና የመሰረተ ልማት ዝርጋታ አቅርቦት ወሳኝ ነው።

ኢትዮጵያ ሰላምን በማስቀደም የውስጥ ግጭቶችን በሰላማዊ መንገዶች ብቻ በመፍታት በሀገር ግንባታ ላይ በማተኮር ለዜጎቿ ብሩህ ተስፋን ለማስፈን ተግታ እየሰራች ትገኛለች።

የኢትዮጵያ ሰላም ከውስጥ ተጠቃሚነት በተጨማሪ አህጉራዊና ዓለም አቀፋዊ ጠቀሜታ አለው። ኢትዮጵያ በአፍሪካ ቀንድ ስትራተጂካዊ ቦታ ላይ ስለመትገኝ የኢትዮጵያ ሰላም ለቀጣናችን መረጋጋት ወሳኝ ሚና አለው።

ኢትዮጵያ የድንበሯን ሰላም በማስጠበቅ ለአካባቢው ሰላምና መረጋጋት የበኩሏን አስተዋጽኦ ማድረግ ትችላለች ለዛም እየሰራች ትገኛለች።

ከዚህም በላይ ኢትዮጵያ ለሰላም የሰጠችው ቁርጠኝነት ለሌሎች ተመሳሳይ ፈተናዎች ለሚጋፈጡ ሀገሮች መነሳሳት ሆኖ የሚያገለግል ሲሆን ይህም በውይይት፣ በዕርቅና በሰብዓዊ መብቶች መከበር ግጭቶችን መፍታት እንደሚቻልና ማህበረሰቦችም ሊያድጉ እንደሚችሉ ያሳያል።

በኢትዮጵያ ያለው ሰላም የራሱን ህዝቦች ብቻ ሳይሆን የበለጠ ሰላም የሰፈነበት እና የበለፀገ አለም እንዲሰፍን አስተዋፅዖ ያደርጋል።

27/02/2024

ኢትዮጵያ ወደ ብልፅግና...

⚫ የሁሉንም ብሔሮች ብሔረሰቦች እና ህዝቦች የጋራ ተሳትፎ እኩልነት እና ተጠቃሚነትን ባረጋገጠ መልኩ፤

⚫ ህብረ ብሔራዊ ማንነታችንን እና ሀገራዊ አንድነታችን ባስከበረ አውድ፤

⚫ በአሰባሳቢ ትርክቶች፤በጋራ ደማቅ ታሪኮች፤በአንድነታችን ገድሎች ደምቀን ወደ ብልፅግና እንጓዛለን!

25/02/2024

Address


Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when South Ethiopia posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Videos

Shortcuts

  • Address
  • Alerts
  • Videos
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share