ሰከላ ሚዲያ Sekela Media

  • Home
  • ሰከላ ሚዲያ Sekela Media

ሰከላ ሚዲያ Sekela Media Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from ሰከላ ሚዲያ Sekela Media, Broadcasting & media production company, .

የኔታ ያለቦታዎት እየተገኙ አይፎርሹ !/አይሳቱ !የአማራ ባንክ ስያሜ ተቃዋሚ ነኝ ይላሉ ?!🙆🙆መጋቢ አዲስ አዲስ እሸቱ አለማየሁ የሁሉም እምነት ተከታዮች በአንድ ድምፅ የሚወዷቸው ትልቅ መም...
20/06/2022

የኔታ ያለቦታዎት እየተገኙ አይፎርሹ !/አይሳቱ !

የአማራ ባንክ ስያሜ ተቃዋሚ ነኝ ይላሉ ?!🙆🙆

መጋቢ አዲስ አዲስ እሸቱ አለማየሁ የሁሉም እምነት ተከታዮች በአንድ ድምፅ የሚወዷቸው ትልቅ መምህር ናቸው። ነገር ግን ብልፅግና ፓርቲ ከመጣ ወዲህና የሆነ ሹመት ከሰጣቸው በኋላ የሃይማኖት ትምህርት ከመስበክ ይልቅ ባልተሰጣቸው መክሊት ፖለቲካውን በተለያዩ መድረኮች ሲያቦኩት እያየንና እየታዘብናቸው ነው።

ለብልፅግና መንግስት የንስሃ አባት ሆነው በተለያዩ ጊዜያት
ለብልፅግና ፓርቲ የነፍስ አድን ስራ ሲሰሩም እየተመለከትን ነው።

በቅርቡ ተመርቆ ስራውን የጀመረውን የምርቃት ስነ ስርዓቱ ላይ እኚህን አባት አክብሮ ድግሱ ላይ የክብር እንግዴ አድርጎ ቢጋብዛቸው በስንት ድካምና ጥረት ተለፍቶ እዚህ ደረጃ የደረሰውን >> ብለው ከእሳቸው የማይጠበቅ ንግግር ተናግረው በዕለቱ የነበረው ድግስ ላይ ቀዝቃዛ ውሃ ለመቸለስ ሲጥሩ ተመልክተናል።

የኔታ ያልገባቸው ነገር ቢኖር ፦ ይኼንን የአፍ ወለምታ ቴአትር ቤት ወይም ጦቢያ መድረክ መስሏቸው ይጨበጨብልኛል ብለው አስበው ነበር። ነገር ግን በርካታ ሕዝብ ያሳዘኑበትንና ታሪካዊ ስህተት የፈፀሙበትን ንግግር አድርገው ለትዝብት
ተዳርገዋል።

በሌላ ንግግርዎ ፦
< እንደ አማራ ፖለቲከኞች ኪሳራ እንዳይደርስባችሁ > ብለዋል። የኔታ የትኞቹ ፖለቲከኞች ?!
እውነት ይወራ ከተባለ እንደ ብልፅግና ( አዴፓ ) ኪሳራ የደረሰበት ፓርቲ አለ ?!

የኔታ ግዴለዎትም እባክሆ የብልፅግና ፓርቲ ፊርማዎትን ይቅደዱና በነፃ የፊርማ ዝውውር ሙሉ ጊዜዎትን ወደምትፈልገው ቤተክርስቲያን ይመለሱ።

እኛ የምንፈልገው የእርስዎን የማይጠገብ የመፅሐፍ ቅዱስ ሃይማኖታዊ ትምህርት እንጂ በየቴአትር ቤቱ እና ለእርስዎ በማይገባ ቦታ እየተገኙ ለብልፅግና ፓርቲ ጥብቅና እንዲቆሙና ስታንድ አፕ ኮሜዲ እንዲያቀርቡ አይደለም።

መጋቢ አዲስ እሸቱ አለማየሁ ቆም ብለው ያስቡበት።
አካሄድሆ አደገኛ ነው። ፖለቲካውን ለፖለቲከኞች ይተውላቸው።

በአንድ ወቅት ራስዎ እንዲህ ብለው ነበር ፦

ብለው ነበር።

ግልባጩን ፦ ለራስዎ !!!

ዘሪሁን ተዝናኑ
ከማይነበብ ፊርማ ጋር !!!

  ************** አቡነ ማትያስ "በማይወዷት ሀገርና በማይፈልጓት ቤተክርስቲያንን ላይ የተሾሙ ናቸው" ሲል ይናገራል ዲያቆን ዳንኤል ክብረት። ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ሆይ"   በሚዛን...
22/03/2022


**************
አቡነ ማትያስ "በማይወዷት ሀገርና በማይፈልጓት ቤተክርስቲያንን ላይ የተሾሙ ናቸው" ሲል ይናገራል ዲያቆን ዳንኤል ክብረት።
ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ሆይ" በሚዛን ተመዘንክ ቀህም ተገኘህ" እንልሀለን። ፓትርያርኩ ግድፈትና ስህተት ካለባቸው ሊጠይቃቸው የሚችል የቤተክርስቲያኒቱ መዋቅር አለ እሱም ቅዱስ ሲኖዶስ ብቻ ነው። ሰው አዋዋሉን ይመስላል የሚባለው እውነት በዲያቆን ዳንኤል ክብረት ላይ ደርሶ ለቤተክርስቲያን ክስረት ለመንግስት ደግሞ ውድቀት እያመጣ ነው።

የቤተክርስቲያንን አባት ለዛውም በመንፈስ ቅዱስ የሚመራውን የቅዱስ ሲኖዶሱን መሪ የሚሳደብ ለአለቃው ተገዥ በመሆን እንደ ኤሳው ክብሩን በምስር ወጥ የሚሸጥ፣ የቤተክርስቲያን ልጆችን እንባና ለቅሶ የማይሰማው፣ ለቤተመንግሥት ብፌ ብሎ ክብሩንና ሞገሱን ያጣ ሰው ፓትርያርኩን ለመናገር ሞራል የለውም። ምንም ነገር ከቤተክርስቲያን አይበልጥብንም። 60 እና 70 ሚሊዮን ኦርቶዶክስ አማኝ ባለበት ሀገር ጊዜና ወቅት እየጠበቃችሁ ለመንግስት የምታሸረግዱ የቤተክርስቲያን ልጆች ወይም በቤተክርስቲያን ስም የምትነግዱ ስግብግብ ነጋዴዎች እረፉ። አራት ኪሎ ቤተክህነትና አራት ኪሎ ቤተመንግሥት ምን እየተሰራ እና ምን እንደምትፈልጉ ስለምናውቅ ነው እረፉ የምንለው።

በተለይም የመነኩሴ ቆብ አድርጋችሁ፣ ዲያቆንና አባ የሚል ቅጥያ ከኋላ ይዛችሁ በድርጊት ግን ከውስጥ ሆናችሁ ቤተክርስቲያንን የምትወጉ እረፉ። ንግዳችሁን በልክ አድርጉት ብዙ ማትረፉ ስትፈልጉ ትከስራላችሁ ወይም ትወረሳላችሁ።

እግዚአብሔር ለሁላችንም ልቡና ይስጠን
ይፍቱኝ ይባርኩኝ

ሰበር ዜና ‼️ጁንታው ኢትዮጵያና ኤርትራን ለማጥፋት የቀበረው 2 ሙሉ ተሳቢ ከባድ መሳሪያ ፀረ ታንክ ባዙቃ የተለያዮ የረቀቁ መሳሪያዎቼ ጀግናው የኤርትራ ሰራዊት ከተቀበረበት በቁጥጥር ስር አ...
28/11/2021

ሰበር ዜና ‼️

ጁንታው ኢትዮጵያና ኤርትራን ለማጥፋት የቀበረው 2 ሙሉ ተሳቢ ከባድ መሳሪያ ፀረ ታንክ ባዙቃ የተለያዮ የረቀቁ መሳሪያዎቼ ጀግናው የኤርትራ ሰራዊት ከተቀበረበት በቁጥጥር ስር አውሎታል

የአሸባሪው ሀይል ከኢትዮጵያ ለአመታት ዘርፎ የቀበረው ከ2 ሙሉ ጭነት ተሳቢ በላይ እጅግ ብዛት ያለው መሳሪያ በጀግኖቹ የኤርትራ ሰራዊት ደህንነት አባላት አነፍናፊነት በቁጥጥር ስር ውሏል

ጀግኖቹ የኤርትራ ሰራዊት አባላት አሸባሪው ሀይል እጅግ ብዛት ያለውን መሳሪያ ጥልቀት ባለው ጉድጓድ ቆፍሮ ቢቀብርም ተከታትለው ጎልጉለው አውተውታል

የተገኘውን መሳሪያም ለጀግናው መከላከያ ሰራዊት አስረክበዋል

ጀግናው የኤርትራ ሰራዊት ክብር ይገባዋል ኢትዮጵያን ከጥፋት ታድጓል

ድል ለኢትዮጵያ ! ሞት ለጠላቶቿ ‼️

13/10/2021

ጋሼ ስብሃት ወጎቹ ደስ ይላሉ

አንድ ግዜ ስለ አማርኛ ቋንቋ
እንዲህ ብሎ ነበር…

እንግሊዝኛ ምን በአለም ቢነገር ፡ ምን ቢሊዮኖች ቢመኙት እዛው ከቻይና ብር ይበደሩበት እንጂ ፡ ፊልም ይሰሩበት እንጂ እንደኔው ላለው መች እንደ አማርኛ ከልብ ያደርሳል ? እስቲ አሁን "አይዞህ ን" ልበልህ ብለው እንዴት ይገለጻል ?
እንግሊዘኛ እንደ ቋንቋ መተሳሰብን መች ይደግፋል ? እስቲ አሁን "እኔን " ብሎ ነገር የት አባቱ ያውቃል? እሱን ተዉት "የት አባቱ" ማለትንስ የት አባቱ አውቆት?! ሰው እንቅፋት ሲመታው "እኔን " በሚለው መተሳሰብ ፋንታ ''ዋች አውት" ! " አር ዩ ኦኬ ?" የት ያደርሳል? "ዋች አውት " አጠጋግተን ስንተረጉመው እንግዲህ "ምን አባሽ ያደናብርሻል ? " አይደለም?

ሳንፈራ እውነትን እንመስክዘመኑ የሰማአታት እንደመሆኑ እውነቱን ተናግሮ ሰማዕትነትም ቢሆን ክብር ነው እና ተጋፍጦ ሴጣንን አጋልጦ የመጣብንን የክብር መከራ መቀል አለብን ።እኛ ዛሬላይ ዝም እ...
02/10/2021

ሳንፈራ እውነትን እንመስክ

ዘመኑ የሰማአታት እንደመሆኑ እውነቱን ተናግሮ ሰማዕትነትም ቢሆን ክብር ነው እና ተጋፍጦ ሴጣንን አጋልጦ የመጣብንን የክብር መከራ መቀል አለብን ።
እኛ ዛሬላይ ዝም እንዳልን ትላንት ላይ ሰማዓታት አባቶቻችን ዝምቢሉ ጣዖታትን ባይቃወሙ ኖሮ ይህን ዛሬ እኛ የምንተርከውን ተጋድሎ መከራ ባልተቀበሉ ነበር።

ዛሬ ላይ እንደምናየው በአንድ እጅ መስቀል በአንድ እጅ ጣዖት ይዞ ሊያውም የሁለት ተቃራኒ ሃይማኖቶች መሪ እና የክብር እንግዳ ሆኖ እየቀረቡ የማይቀራረቡትን ለማቀራረብ የማይመሳሰሉትን ለማመሳሰል መሞከር ከንቱ ድካም ከንቱ ማደናገር መሆኑን ሁሉም የክርስቴን እምነት ተከታዮች የሚረዱት ሀቅ ነው።

እኛም መምህራኖች ትላንት እነ ሐዋርያው ጴጥሮስ፣ቶማስ፣ማርቆስ....ወዘተ የከፈሉትን መስዋእትነት ለመክፈል ፈርተን ተመሳስለን ዝም ብለን ይልቁንም ጣዖትን አጅበን ለጣዖት የተሰዋውን በልተን ብንገኝ ነገ በፍርድ ቀን ከተጠያቂነት የሚያስጥለን እንደሌለ ልናውቅ ይገባል።

የሚከተለውን ትምህርት ጣዖትን እንድንቃወመው ስል አቀርብላችኋለው። እግዚአብሔር ይርዳን።

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።
🥀 በረከታቸው ይደርብንና አቡነ ተክለሃይማኖትና አቡነ ቀውስጦስ በዛፍ ላይ አድሮ ይመለክ የነበረውን ሰይጣን ከዛፉ ላይ እንዳስወጡትና እንዳጠፉት የሚናገር ተአምር ይህ ነው፦ ‹‹… አቡነ ተክለሃይማኖት ወደ ከተታ አውራጃ በደረሰ ጊዜ የዚያች አገር ሰዎች እንደ እንስሳ ሆነው አገኛቸው። እርሱም "ምን ታመልካላችሁ?" አላቸው። ሰዎቹም የምናመልከው የምንሰግድለት ታላቅ ዛፍ አለ" አሉት። አባታችንም "በሰገዳችሁለት ጊዜ ምን ይመስላችኋል?" አላቸው። እነርሱም "እኔ ፈጠርኳችሁ ፈጣሪያችሁ እኔ ነኝ" ብሎ ከዛፉ ላይ ቃል ይናገረናል፣ ስለዚህ ነገር እኛም እንሰግድለታለን፣ የወደደውን እንሠዋለታለን" አሉት። አቡነ ተክለሃይማኖትም "እሰግድለት ዘንድ እኔንም ከእናንተ ጋራ ውሰዱኝ" አላቸው። እነርሱም "እሺ ነገ እንወስድሃለን" ብለው በነጋታው ለጣዖቶታቸው የሚሰግድ መስሏቸው አቡነ ተክለሃይማኖትን ከእነርሱ ጋራ ወሰዱት። ከዛፉ ዘንድ በደረሱ "እናንተ የዚህች ሀገር ሰዎች ከእኔ ሥራ ልዩ የሆነ ሰው ለምን አመጣችሁብኝ? ይኸውም በመካከችሁ የሚሄድ ተክለ ሃይማኖት ነው..." እያለ በዛፏ ላይ ያደረ ሰይጣን ጮኸ። አባታችንም ፊቱን ወደ ምሥራቅ መልሶ ወደፈጣሪው ጸለየ። "...አቤቱ በፍጥረትህ ላይ ሰይጣን የሚሠራውን ተንኮል ተመልከት! ሥነ ፍጥረትህን ያጠፋ ዘንድ ይህን ጠላት እንዲሰለጥን አትተወው፣ ይህን ትዕቢተኛ ሰይጣን በእኔ እጅ በሕዝቡ ፊት ታዋርደው ዘንድ አቤቱ እለምንሃለሁ..." እያለ ጸለየ።

🥀‹‹…ጸሎቱንም ከጨረሰ በኋላ (ሰይጣን አድሮባት በሰዎች ዘንድ ትመለክ ወደነበረችው) ዛፍ ተመልሶ ‹ሰይጣን በአንቺ አድሮ እየተናገረ ሕዝቡን የሚያስትብሽ አንቺ ዛፍ እኔ በምሰግድለት በኢየሱስ ክርስቶስ ስም አዝሻለሁ ሰዎቹ ሁሉ የፈጣሪዬን ኃይል ያዩ ዘንድ ከሥርሽ ተነቅለሽ ወደኔ ነይ› አላት፡፡ በውስጧ አድሮ የነበረውንም ሰይጣን ‹አንተ ቀድሞ እንዳሳትካቸው ዛሬም ጉስቁልናህን ያዩ ዘንድ የዚህችን ሀገር ሰዎች ‹እኔ ቀድሞ በሐሰት አስቻችኋለሁና እንግዲህስ ከባሕርይ አባቱ ከአብ፣ ከባሕይር ሕይወቱ ከመንፈስ ቅዱስ ጋራ ለኢየሱስ ክርስቶስ ስገዱ› በላቸው አለው፡፡ ሰይጣንም ‹እነዚህን ሦስቱን ስም መጥራት አይቻለኝም› አለ፡፡ ተክለ ሃይማኖትም ‹የሦስቱን ስም መጥራት የማይቻልህ ከሆነ እናንተንም እኔንም ለፈጠረ ለሰማይና ለምድር ፈጣሪ ስገዱ ተገዙ› በላቸው አለው፡፡ ሰይጣኑም በዚያ እርሱን ሊያመልኩት ለተሰበሰቡት ሰዎች ‹ቀድሞ እኔን በመሰላችሁኝ ጊዜ በሐሰት ሳስታችሁ ኖርኩ፣ እንግዲህስ ሀገራችሁን ትቼላችሁ ሔድኩ፣ ሰማይንና ምድርን፣ እኔንና እናንተን ለፈጠረ ስገዱ ተገዙ፤ የእኔን ሥራ የሚሠራ ግን ከእኔ ጋራ በገሃነም ይኖራል› ብሎ ወጥቶ ወደ ምድረ በዳ ሔደ፡፡ ሰዎቹም እንደአንድ ልብ ሆነው ‹በተክለ ሃይማኖት አምላክ አምነናል› አሉ፡፡ እርሱም በሦስቱ ስም አጠመቃቸው፡፡››

🥀(ምንጭ፦ ገድለ አቡነ ተክለሃይማኖት፣ የደብረ ሊባኖስ እትም ገጽ 110፣ የትንሣኤ እትም ገጽ 84፣ የተስፋ ገብረሥላሴ እትም ገጽ 86)

🥀ዳግመኛም የመሐግሉ የአቡነ ቀውስጦስ በዛፍ ላይ አድሮ ይመለክ የነበረውን ሰይጣን ከዛፉ ላይ እንዳስወጡትና ተፈጽመው እንዳጠፉት የሚናገር ተኣምር ይኽ ነው፦

🥀(እርሳቸውም አርሲ ፈንታሌ ተራራ ላይ ሠሪቲ ለምትባል ጠንቋይ እየተላላኩ ሕዝቡን የሚያስቱና የሚያሰቃዩ 470,300 (አራት መቶ ሰባ ሺህ ሦስት መቶ) አጋንንትን በጸሎታቸው እሳት ከሰማይ አውርደው ያቃጠሏቸው ታላቅ ጻድቅ ናቸው። የታናሽ ወንድማቸው የዐፄ ይኩኖ አምላክ ልጅ ዐፄ አምደ ጽዮን በክፉዎች ምክር የአባቱን እቁባት በማግባቱ አቡነ ቀውስጦስ እንደ መጥምቁ ዮሐንስ ሄደው ንጉሡን ስለገሠፁት ንጉሡ በግዞት ወስዶ ጎናቸው በጦር ወግቶ በሰማዕትነት የገደላቸው ሰማዕት ናቸው።)

🥀 ‹‹አቡነ ቀውስጦስ በወግዳ ተቀምጠው ከሚጸልዩበት ከማጢ ዋሻ ወጥተው ወደ የይ ሔዱ፤ በዚያም የአካባቢውን ሰዎች በእሸ ዛፍ ሥር ተቀምጠው እየበሉና እየጠጡ የአሕዛብን ዘፈን እየዘፈኑ ሰይጣናትን ሲያመልኳቸው አገኟቸው፡፡ እነርሱም እሳትን በእጃቸው እየዘገኑ በአፋቸው ይጎርሳሉ፣ ‹‹እሳቱ ያላቃጠለን በአምላካችን በቆርኬ ኀይል ነው›› እያሉ እየዘፈኑ ለጣዖቱ ሲሰግዱና ብዙ በግና ፍየል እያረዱ የጣዖቱን አገልጋዮች ሲመግቡ አባታችን አይተው አዘኑ፡፡ አባታችንም እነዚያን ሰዎች የጣዖት አምልኮን ትተው እግዚአብሔርን እንዲያመልኩ ከነገሯቸው በኋላ ከዛፉ ላይ ወጥተው ጣዖቱን ቆርኬን አውርደው ሰባበሩት፣ የጣዖቱ መንበር ትልቁ ዛፍ ነበርና፡፡ ጣዖቱም በጣዖታውያኑና በጠንቋዮቹ ፊት እንደትቢያ ሲሆን ከዛፉ ሥር 140 ታላላቅ እባቦች ወጡ፣ አባታችንም በበትረ መስቀላቸው ራስ ራሳቸውን ቀጥቅጠው ገደሏቸው፡፡ አጋንንትም የአካባቢው ሰዎች መሥዋዕት ካላቀረቡላቸው በእነዚኽ እባቦች ላይ እያደሩ ወደየቤታቸው እየሔዱ ያስፈራሯቸው ነበር፡፡

🥀ጣዖታውያኑና ጠንቋዮቹም በድንጋጤ ተቀምጠው ቆይተው ተነሡና አባታችን ቀውስጦስን እሾህ ባለው የቀጋ በትር ደበደቧቸው፤ የአባታችንም ጀርባቸው ቆሰለ፣ ደማቸውም እንደውኃ በምድር ላይ ፈሰሰ፡፡ አባታችንንም የገደሉ መስሏቸው በዛፉ ሥር ጥለዋቸው ሔዱ፡፡ የአካባቢው ሰዎች ሸሽተው ወደየቤታቸው ሔደው በራፋቸው ዘግተው በፍርሃት ሳይተኙ አደሩ፣ በነጋም ጊዜ እነዚያን እባቦች አላገኟቸውም፤ ወደ ዛፉ ቢሔዱ አባታችን ቀውስጦስን ቆመው ሲጸልዩ የእባቦቹንም በድኖች የሰማይ ወፎች ሲበሉት አገኟቸው፡፡ የአካባቢውም ገዥ የሞቱ መስሎት አብሮ ከሕዝቡ ጋር መጥቶ ነበርና አባታችንን ‹‹እነዚኽን እባቦች በፍርሃት ስናመልካቸው ኖረናል፣ የማይሞቱ ይመስለን ነበር ነገር ግን አንተ ራስ ራሶቻቸውን ቀጥቅጠህ ገደልካቸው፣ እኔም ከሠራዊቴ ጋር በአምላክህ አምኛለሁ›› አላቸው፡፡ አባታችንም ወደ ጌታችን በጸለዩ ጊዜ ሕዝቡ ሁሉ እያዩ ቅዱስ ገብርኤል ከሰማይ ወርዶ በጣዖቱ ቆርኬ ላይ አድሮ የነበረውን ሰይጣን አንቆ ይዞ አስለፈለፈው፡፡ ሰይጣኑም ‹‹የመላእክት አለቃ ገብርኤል ሆይ! በይቅር ባዩ አምላክ እማጸንሃለሁ ጊዜዬ ሳይደርስ አታጥፋኝ፣ ወደ ጥለቁ እንጦርጦስ ልሒድ ተወኝ፣ ይኽ ሰው ባለበት ሥፍራ ከእንግዲህ አልደርስም፣ እርሱ እስኪሞትልኝ ወደዚህ ዓለም አልመጣም…›› በማለት ምሎ ተገዘተ፡፡ አባታችንም ዛፉን እንዲወድቅ አዘዘውና ወዲያው ወደቀና አምስት ጣዖታውያንንና አራት ጠንቋዮችን ገደላቸው፡፡

🥀ሕዝቡም ይኽን ተኣምር አይተው ‹‹በአቡነ ቀውስጦስ አምላክ አምነናል›› ብለው በመመስከር የእግዚብሔርን ሕግ እንዲያስተምሯቸው ለመኗቸው፡፡ ገዥውም ወደቤቱ እንዲሔዱና አብረው እንዲያድሩ አባታችንን ሲለምናቸው እርሳቸውም ‹‹ሔደህ መካን የሆነችውን ሚስትህንና ሆድ ሕማም የታመመውን አባትህ ይዘህ ና›› ሲሉት ደንግጦ ‹‹አባቴ ሆይ! ይኽንን ማን ነገረህ? የዞረሬ ሰው የጸጋ ዘአብ ልጅ ተክለ ሃይማኖት ለፈጠጋር ሰዎች የሚሰብክላቸው ኢየሱስ አንተ ነህን?›› አላቸው፡፡ አባታችንም ‹‹እኔስ በስሙ የማስተምርለት የኢየሱስ ባሪያ ነኝ›› በማለት ተገርፈው ለጅቦች ተጥለው ሳለ ስለእርሱ መልአኩ እንደነገራቸው ነገሩት፡፡በነጋታውም በሀገሩ የታመሙ 900 ሕሙማንንና ደዌ የጠናባቸውን ሁሉ ሰብስበው አመጡላቸውና አባታችን የኪዳን መጽሐፍ ደግመው በጠበሉ ፈወሷቸው፡፡ የሀገሩ ገዥ አባትም መጥቶ ለአባታችን ታላቅ ምሥጢርን ነገራቸው፡፡ ከዚኽም በኋላ አቡነ ቀውስጦስ የሀገሩን ሰው ሁሉ ሰብስበው በሥላሴ ማመንን ሲያስተምሯቸው የሀገሩ ገዥ ‹‹አባቴ ሆይ! ያስተማርከንን ሁሉ አምናለሁ ነገር ግን የሙታን መነሣት ውሸት ይመስለኛል›› ሲላቸው አባታችንም ወደ ጌታችን ከጸለዩ በኋላ የመኰንኑ እናትና እነዚያ ዛፉ ወድቆባቸው የገላደቸው አምስት ጣዖታውያንና አራት ጠንቋዮች እንዲሁም ከተንባላት ወገን የሆኑ ብዙ ሙታን ተነሡ፤ የተንባላት ወገንም ነቢያቸውን እየረገሙ ‹‹በአቡነ ቀውስጦስ አምላክ አምነናል›› ብለው መሰከሩ፡፡ ከሙታን መካከል የተነሡትም ለገዥውና ለሕዝቡ ሁሉ በሲኦል ስላለው እጅግ ጽኑ መከራ ከነገሯቸው በኋላ አባታችንን ድጋሚ ወደዚያ የሥቃይ ቦታ እንዳይሔዱ ለመኗቸው፤ አባታችንም በስመ ሥላሴ አጠመቋቸውና ‹‹አምላኬ በይቅርታው ብዛት ምሯችኋልና ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ሒዱ›› አሏቸው፤ እነርሱም ተመልሰው አንቀላፉ፣ ነፍሶቻቸውም በአባታችን ጸሎት ድኅነትን አገኘች፡፡››

🥀(ምንጭ፦ገድለ አቡነ ቀውስጦስ ዘመሐግል (ኢቲሳ ደብረ ጽላልሽ አቡነ ተክለሃይማኖት
ገዳም፣ 2007ዓ.ም)

🥀የአቡነ ተክለሃይማኖትና የአቡነ ቀውስጦስ ረድኤት በረከታቸው ይደርብን፣ በጸሎታቸው ይማረን።
✞ ✞ ✞

🥀የዛሬ ዓመት ላይ ይኽን ጽፈን ነበር፦ ድንጋይም ያምልክ ዕንጨት፣ ዛፍም ያምልክ ወንዝ...ማንም ሰው የፈለገውን ማመን፣ እምነቱንም በተግባር መግለጽ መብቱ ነው። ባመነበት እምነቱ ግን ጽድቅ ወይም ኩነኔ እንዳለበት ማወቅ አለበት። "...ኢሬቻ የምስጋና በዓል ነው...." ምናምን እያሉ ሰውን ማጃጃል ግን አይቻልም። ምንም መቀባባትና መሸፋፈን አያስፈልገውም-ኢሬቻ ለኢትዮጵያ መርገምን የሚያመጣ ምድሪቷንም የሚያረክስ ለአውሬው መሥዋዕት የሚቀርብበት የባዕድ አምልኮ ነው። ኢሬቻ ማለት በአጭሩ ዋቃ ጉራቻ (ጥቁሩ አምላክ) ማለት ነው። በዛፍ ሥር ቅቤ የሚቀመጥለት፣ የእምነቱ ተከታዮች እንደየአቅማቸው እንስሳትን አርደው በሐይቅ ውስጥ የሚጥሉለት፤ አረቄ፣ ጠላ፣ የሚደፉለት አምላክ ዋቃ ጉራቻ (ጥቁሩ አምላክ) ነው እንጂ እግዚአብሔር አይደለም።

🥀ፕሮቴስታንቶቹ እነ ዐብይ አህመድና ጀሎዎቹም ይኽንን ዋቃ ጉራቻ (ጥቁሩ አምላክ) የሚመለክበትን አምልኮተ ጣዖት ዘመናዊ መልክ እንዲኖረው ለማድረግና በሕዝቡ ዘንድ ተቀባይነት እንዲኖረው ለማድረግ "ባሕል ነው" እያሉ ራሳቸው ተጃጅለው ሰውንም ሊያጃጅሉ ይሞክራሉ።

🥀ኢሬቻ ራሱን የቻለ እምነት ነው-እነርሱ ማመን መብታቸው ነው ነገር ግን ኢሬቻን ከክርስትና ጋር ማገናኘት እጅግ አጸያፊ ነው፣ እግዚአብሔርንም ማስቆጣት ነው። "ለቤዛም ቀን የታተማችሁበትን ቅዱሱን የእግዚአብሔርን መንፈስ አታሳዝኑ።" (ኤፌ 4፡30) እንዲል ቅዱሱ መጽሐፍ እግዚአብሔር በኃጢአት ከሆነ ይታገሳል፣ በክህደት ወይም ለእርሱ ብቻ የሚገባውን ክብር ለሌላ ለባዕድ ነገር ሲሰጥበት ግን ትዕግሥት የለውም፣ የቁጣ በትሩን ይመዛል።

🥀ትናንት በሀገረ አሜሪካ እያሉ "ታቦት አያስፈልግም፣ አማላጃችን ኢየሱስ ነው፣ ቅዱሳን አያስፈልጉም ..." በማለት በግልጽ ምንፍቅናን ሲያቀረሹ የኖሩት አባ ወልደትንሳኤ (የአሁኑ "አቡነ" በርናባስ) እኽ....ባለፈው ዓመትስለ ኢሬቻ በዓል ሲናገሩ "ኢሬቻ የምስጋና በዓል ነው...." ሲሉ ተደምጠዋል። ባለጊዜ ነን የሚሉ ሥልጣን ላይ ያሉ ደናቁርት መሪዎችም "የኢሬቻ በዓል የሁላችንም ነው" ብለዋል። ኢሬቻ ይመለከተኛል የሚል ሁሉ በዓሉን ማክበር እምነቱንም መከተል መብቱ ነው ነገር ግን "የእኛ እምነት የእናንተም እምነት ነው፣ ኑ ከኛ ጋር ለዛፍ ለወንዝ ለሜዳ ለተራራ ስገዱ..." ማለት ግን እግዚአብሔርን አስክዶ ለጣዖት ካሰገደው ከናቡከደነፆር አዋጅ ተለይቶ የማይታይ ነው። የኢሬቻን እምነት በበላይነት የሚያስተባብሩት መምለኬ ጣዖታትም "በዓሉ የሁሉም በዓል ስለሆነ ሁሉም ኢትዮጵያዊ አብሮን ያክብር" ብለዋል።

🥀እኛ ኦርቶዶክሳውያንስ ከላይ በተኣምራታቸው እንዳየነው በዛፍ ላይ አድሮ ይመለክ የነበረውን ጣዖት ከምድረ ገጽ ያጠፉት የእነ አቡነ ተክለሃይማኖት ልጆች ነን እንጂ እንደዚህ ዓይነቱ መርገምን ከሚያመጣ ምድሪቷንም ከሚያረክስ ለአውሬው መሥዋዕት ከሚቀርብበት የባዕድ አምልኮ ጋር አንተባበርም። "አሕዛብ የሚሠዉት ለአጋንንት እንዲሆን እንጂ ለእግዚአብሔር እንዳይሠዉ እላለሁ፤ ከአጋንንትም ጋር ማኅበረተኞች እንድትሆኑ አልወድም" (1ኛ ወደ ቆሮ 10፡20) የሚለው የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ለሁላችንም የተሰጠን የማስጠንቀቂያና የአደራ መልእክት ነዉ።

🥀የቅዱሳን አምላክ በምድር ላይ ከሚፈጸመው እርኩሰት ሁሉ ይጠብቀን።

በመምህር ምህረተአብ አሰፋ

The Best Airlines in Africa 1)-Ethiopian Airlines🇪🇹2)-Rwandair  🇷🇼3)-Air Mauritius 🇲🇺4)-Air Seychelles🇸🇨5)-Kenya Airways...
01/10/2021

The Best Airlines in Africa

1)-Ethiopian Airlines🇪🇹

2)-Rwandair 🇷🇼

3)-Air Mauritius 🇲🇺

4)-Air Seychelles🇸🇨

5)-Kenya Airways🇰🇪

6)-Royal Air Maroc 🇲🇦

7)-Fastjet

8)-Mango airlines 🇿🇦

9)-Egyptair 🇪🇬

10)-Kulula air🇿🇦

500,000 ብር ከሌለህ ጎንደርን ትተህ ተሰደድ!!!------------------------------------------------------------ማጋነን እንዳይመስልህ!!!ከደቡብ ጎንደር በ...
01/10/2021

500,000 ብር ከሌለህ ጎንደርን ትተህ ተሰደድ!!!
------------------------------------------------------------
ማጋነን እንዳይመስልህ!!!
ከደቡብ ጎንደር በስተቀር ያሉት ሶስቱ የጎንደር ዞኖች ላይ እየሆነ ያለ ሀቅ ነው::
ጎንደር ከተማ ላይ ከ12:30 በኃላ በነፃነት አትንቀሳቀስም:: ባጃጅ ይዣለሁ ብለህ (የራስህ ቢሆን እንኳን) አትተማመንም:: ጨለማ ለብሶ መንገድ ዳር የቆመ አንድ ሰው ሽጉጥ ወይም ጩቤ ያወጣና "ውረድ" ይልሃል:: የዕቅድ ዝርዝርህ ውስጥ የሞት እቅድ ጨምረህ ስላልፃፍክ ወደህ ሳይሆን በግድህ ትወርዳለህ:: ይነዳሃል:: ማለቴ እጅህን የኃሊት አስሮ ይነዳሃል:: ከዚያ የቤተሰብህን ስልክ ይቀበልህና ደውሎ "500,000 ብር" ይጠይቃል:: ቤተሰቦችህ "ከየት አመጣለሁ?" አይሉም:: ምክንያቱም አስከሬንህን መንገድ ላይ ማንሳት አይፈልጉም:: (በነገራችን ላይ አስከሬንህ መንገድ ላይ የሚገኘው ሽፍታው "አዛኝ" ከሆነ ነው:: ሽው ባለ ገደል የተጣሉ ብዙ ናቸው::) ስለዚህ ገንዘቡ ካለ ተከፍሎልህ ትለቀቃለህ:: ከሌለ ደግሞ ሚስኪን እናትህ ወይም ሽማግሌ አባትህ ፌስታል አንጠልጥለው ልመና ይዞራሉ:: በተባሉት ቀን ውስጥ ገንዘቡ ከሞላላቸው እድለኛ ነህ:: ተርፈሃል:: Congrates!! ካልሞላላቸው ግን ግንባርህ በጥይት ይነደላል:: RIP!!!
መንግስት ደንቁሯል ዞር ብሎ አያይህም ፖለቲካውን እስካልረበሸበት ድረስ አይመለከተውም:: እንዲያውም ከፖሊስ እስከ ካድሬ ድረስ ተቀናጅተው እገታውን ይመሩታል ትልቅ የገቢ ምንጭ አድርገውታል አራስ ጨቅላ ሳይቀር እያገቱ ትርፍ በትርፍ ሆነዋል:: ከአንዱ ቦታ ሲጠረጠሩ ሌላ ቦታ ላይ ተወስደው ይሾማሉ:: ይኸው ነው::
ሌላው የዚህ እገታ አጋዥ ቴሌ ነው ያ ሁሉ ቴክኖሎጅ 4G 5G ከሚሉን ቀላሉ ነገር በGPS የእያንዳንዱን ስልክ አድራሻ እና ቦታ ለይቶ ለህግ ማቅረብ እየቻለ ህግ እንኳን ባይከታተለው ለታጋች ቤተሰብ አድራሻ ቦታዎችን በመጠቆም የታገቱ ወገኖቹን ራሱ የታጋች ቤተሰብ እንዳያስፈታ እንዳያስለቅቅ ትልቁን ሚና መጫወት እየቻለ ለምን ሎኬሽን መጠቆም እንዳልተፈለገ አለገባንም የፖለቲካ ጉዳይ ሲሆን በቴሌ ስንት ሚስጥራት እንደሚወጡ የሚታወቅ ነው።
ታድያ 500,000 ብር ከሌለህ ጎንደር ላይ ምን ትሰራለህ???

ይሄ ሰውየ'' የአለማችን ትልቁን ድርጅት ተመድን ከመሩ ሰዎች ውስጥ አሳፋሪ ሰው ነው። ኢትዮጵያ የተመድን ሰራተኞች ለማባረር በመወሰኗ ደንግጫለሁ አለ። ለምን ክው ብለህ አቀርም እኛ ስላንተ ...
01/10/2021

ይሄ ሰውየ'' የአለማችን ትልቁን ድርጅት ተመድን ከመሩ ሰዎች ውስጥ አሳፋሪ ሰው ነው። ኢትዮጵያ የተመድን ሰራተኞች ለማባረር በመወሰኗ ደንግጫለሁ አለ። ለምን ክው ብለህ አቀርም እኛ ስላንተ መደንገጥ አለመደንገጥ አይደለም የምንጨነቀው። እኛ የምንጨነቀው ስለ ሀገራችን ኢትዮጵያ ነው። ሰራተኞቹ ከሙያቸው ውጭ ለህወሓት ሲሰሩ ተይዘዋል። በእርዳታ ስም የሚገቡ መኪኖች 6 ወር የሚያስኬዳቸው ነዳጅ ጭነው የሚገቡት
ለምን እንደሆነ መንግስት ያውቀዋል። ከዚህ በላይ መታገስ የኢትዮጵያን ህዝብ መከራ መቀጠል ነው። በዚህ የማይረባ ሰው ድንጋጤ ምክኒያት የመንግስት ውሳኔ መቀልበስ የለበትም። የተሰጣቸውን ሰአት አክብረው ከአገራችን ለቀው ይውጠልን !

ሱሌማን አብደላ

የኔዋ ኢትዮጵያ 👉በማማ  ጎንደር👈አንች ህብረት ቀለም የአፍሪካ ተምሳሌትልጆችሽ ሳይሳሱ የሚሰጡሽ ሕይዎት አዎ አንች ልበልሽ እማዬ እናት ዓለምአንችን የመሰለሽ በዓለም ላይ የለምእምዬ የኔ እና...
29/09/2021

የኔዋ ኢትዮጵያ 👉በማማ ጎንደር👈
አንች ህብረት ቀለም የአፍሪካ ተምሳሌት
ልጆችሽ ሳይሳሱ የሚሰጡሽ ሕይዎት
አዎ አንች ልበልሽ እማዬ እናት ዓለም
አንችን የመሰለሽ በዓለም ላይ የለም
እምዬ የኔ እናት ኩራት እና ክብሬ
የትም የትም ብኖር ያው ባንች ነው ክብሬ
ገና ያምርብሻል ትሞሸርያለሽ
የማያስደፍርሽ ቆራጥ ልጅ ሞልቶሽ
ታጋዩ የሞተው የፈሰሰው ደሙ
ላንች ነው ኢትዮጵያ ላረንጓዴ ቢጫ ለቀይ ቀለሙ።
የሀገርህ የወገንህ ነገር ሲያሳስብህ በውስጥህ በአዕምሮህ ሌላ ሃሳብ አይመላለስብህም. እወድሻለሁ የኔ ኢትዮጵያ 🟢🟡🔴

ሹመትና ሽረት ከእግዚአብሔር የሚሰጥ ስጦታ ነው ብዩ አምናለሁ ።     ከሰው ልጅ የሚመጣን ስልጣንም ይሁን ሌላ ጥቅም ጊዚያዊ እንጅ ወንዝ የሚያሻግር አይደለም ።     ክብርና ሞገስም እንዲ...
22/09/2021

ሹመትና ሽረት ከእግዚአብሔር የሚሰጥ ስጦታ ነው ብዩ አምናለሁ ።
ከሰው ልጅ የሚመጣን ስልጣንም ይሁን ሌላ ጥቅም ጊዚያዊ እንጅ ወንዝ የሚያሻግር አይደለም ።
ክብርና ሞገስም እንዲሁ ።
ቀደም ብሎ ብዙ መልካም ነገር በመፈፀምህ በርካታው የኢትዮጵያ ሕዝብ ሹመቱንና ሞገሱን ሳይሰስት ችሮህ ቆይቷል ።
አሁን ግን ክብርና ሞገስክን ወርውረህ ለመጣል የፈጠንክ ትመስላለህ ።
ይኸ የሆነው ከምንም ሳይሆን ሕዝብ በበጎነት የሰጠህን ክብርና ሞገስ ጠብቀህ ለማቆዩት ባለመቻልህ ይመስለኛል ።
ውድቀትም ሆነ ሹመት ያለው ከባለቤቱ ነው ። ምርጫው የገለሰቡ ነው ።
አንተም በምርጫው የተወዛገብክ ይመስላል ። ሕዝብ ደግሞ ፍርዱ ሚዛናዊ ነውና ውጤቱን በሔደት የምታየው ይሆናል ።
ያለአግባብ ስልጣን እና ጥቅም ፈላጊዎች የፈተና ወጤት የሚለካው ይህንኑ ያለአግባብ በሚያድሉ ባለጊዜዎች አይደለም ።
ይልቁንም በሰፊው ሕዝብ እንጅ !!!

16/09/2021

ቅዱስ - አስገራሚ ትንታኔ
ፊደላችንን ተነተነው
>
< ቅዱስ ዕንቁባህሪ > እግዚአብሔር መጨረሻህን ያሳምረው

31/08/2021

(ፋኖ) የአሸባሪውን የትግራይ ወራሪ ሀይል ከፍተኛ ቁጥር ያለው የጠላት ታጣቂዎችን ዛሬ አይቀጡ ቅጣት ቀጥተው በሚገባው ቋንቋ አናግረው ደምስሰው በርካቶችም ማርከው ደስታችሁን በዚህ መልኩ ከቦታው እየገለፁ ይገኛሉ ነገም ሌላ የጀግንነት ስራ ይጠብቀናል ነገም ሌላ የደስታ የድል ዜና ጠብቁ።

30/08/2021

ዜና ዓወት!

ናይ ጭፍራ ወያነ ወራሪ ኣምበጣ ሰራዊት ብወራር ሒዝዎ ካብዝነበረ ካብ ደብረ ዘቢጥ ብጀጋኑ ሓይልታት መከላኸሊ ኢትዮጵያ፣ ብፍሉይ ሓይልታት ኣምሓራን ሚሊሻን ተደምሲሱ ኣሎ።

ይትረፍ ሎሚ ክሳድ ሒዘ ኣብ ዓደይ፣
ዘሚተንዶ ዘምበርክኽ ፀላእተይ፤
***
ገረብ ገረብ ኣምሓራይ፣
መቓብር ፋሽስት ወያናይ!

ዓወት ንህዝቢ ኢትዮጵያ!
ኢትዮጵያ ትስዕር!

የትግራይ ወራሪ ሀይል  የሽንፈት  ፅዋን በየግንባሩ  እየቀመሰ ነው ******* በዛሬው  ዕለት ደብረ ዘቢጥ ላይ መሽጎ የነበረው የአሸባሪው ህውሓት ቡድን  በመደምሰሱ የተነሳ  ቦታው  በመከ...
30/08/2021

የትግራይ ወራሪ ሀይል የሽንፈት ፅዋን በየግንባሩ እየቀመሰ ነው
*******
በዛሬው ዕለት ደብረ ዘቢጥ ላይ መሽጎ የነበረው የአሸባሪው ህውሓት ቡድን በመደምሰሱ የተነሳ ቦታው በመከላከያ ሰራዊት፣ በአማራ ልዩ ኀይል እና በአማራ ሚሊሻ ቁጥጥር ስር መሆኑን ሰምተን ደስታችን አጣጥመን ሳንጨረስ የትግራይ ወራሪ ሀይል የገባበት የአማራ መሬት ሁሉ እሾህ ሆኑበት ።

በሰሜን ጎንደር በዳባት አዋሳኝ አጅሬ አረፈዳ ከተማ ዙሪያና ከዳባርቅ እርቀት ላይ ቧሂት በሚባል ቦታ በሃገር መከላከያና የአማራ ልዩ ሃይልና ፋኖ የጋራ ጥምር እርምጃ ተደምስሷል ።

የአካባቢው አርሶ አደሮች ጀግነት ልዩ ነበር በርካታ መሳሪያዎችን እጃቸው ገብቱዋል

የአሸባሪው ህውሓት ቡድን መቀበሪያው ጊዜ ቅርብ ነው‼️ ክብርና ምስጋና በጀግንነት ለሚዋደቁት ሁሉ!

ኢትዮጵያ ታሸንፋለች

የታማኝ በየነ መልዕክትሰላም ለሁላችሁም ይሁንልኝ።ሰሞኑን በቤተሰቤ ላይ ትህነግ የፈጸመውን ወንጀል ሰምታችሁ በተለያዬ መንገድ ድጋፋችሁን ያሳያችሁኝ ወገኖቼ በሙሉ ምስጋናዬ ይድረሳችሁ።ትህነግ ...
30/08/2021

የታማኝ በየነ መልዕክት
ሰላም ለሁላችሁም ይሁንልኝ።
ሰሞኑን በቤተሰቤ ላይ ትህነግ የፈጸመውን ወንጀል ሰምታችሁ በተለያዬ መንገድ ድጋፋችሁን ያሳያችሁኝ ወገኖቼ በሙሉ ምስጋናዬ ይድረሳችሁ።
ትህነግ ለኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ለሰው ልጆች ሁሉ ጸር መሆኑን ተገንዝቤ ወንጄላቸውን ሳጋልጥ ኖሪያለሁ ለዚህ ደግሞ በእነሱ በኩል የመሰላቸውን አጸፋ በእኔ ላይ ቢወስዱ የምጠብቀው ነው። ነገር ግን በኢትዮጵያዊ ሞራል ይሆናል ብዬ የማልጠብቀው መለኩሴ ላይ ጠበንጃ ደግኖ መፎከር ። ላምና በሬን የአማራ ነው ብሎ መግደል እስከ ዛሬ በነበረው ታሪካችን አይቼ አላውቅም።
ነገሮች ሁሉ ግልጽ ሆነዋል። "ሂሳብ ማወራረድ" ምን እንደሆነ በግልጽ አሳይተውናል። ስለዚህ የእያንዳንዳችን ምላሽ ምንድን ነው?
እኔን በተመለከተ ግን በቤተሰቤ ላይ ያደረሱት ነገር ሞራሌን የሚነካ ከትግሉ እንዳፈገፍግ አስበው ከሆነ ተሳስተዋል። ትህነግን ለመታገል እስከ ህይዎት መስዋእትነት ለመክፈል ዝግጁ መሆኔን አረጋግጥላቸውላሁ። እናንተስ???

29/08/2021

በጎንደር ከተማ ከፍተኛ የተኩስ ልውውጥ ተጀምሯል

የጎንደር ህዝብ በተጠንቀቅ ቁም ተዘጋጅ : መረጃ ተለዋወጥ !!!!

አሁን የጠላት ተላላኪ ሆኖ አፋርና አማራ ክልልን የሚጨፈጭፈው  ትህነግ  ባለፉት 27 አመታት ዘግናኝ የሰብአዊ መብት ፈፅሞ፣ ዘርፎ፣ ሀገር ያዋረደ ቡድን ነው። ያኔ 100 አመት ለመግዛት ተነ...
27/08/2021

አሁን የጠላት ተላላኪ ሆኖ አፋርና አማራ ክልልን የሚጨፈጭፈው ትህነግ ባለፉት 27 አመታት ዘግናኝ የሰብአዊ መብት ፈፅሞ፣ ዘርፎ፣ ሀገር ያዋረደ ቡድን ነው። ያኔ 100 አመት ለመግዛት ተነስቶ በደል ፈፅሟል። አሁን ደግሞ የስልጣን እጦት በቀሉን ለመወጣት ነው። አገር ሊበትን ነው። ዘርፎ አውድሞ በድህነት ለማማቀቅ ነው! ይህን አሸባሪ ከመታገል ውጭ ያለው አማራጭ ውድመትና መጨፍጨፍ ነው!

ተዘጋጅ!
ሰልጥን!
መክት!

👉 ዝምተኛው እና ቁማርተኛው መንግሥት አማራን መግደል ወንጀል መሆኑን አውቆ የመኖር መብታችንን እስኪያረጋግጥ ድረስ እንቢተኛ ሆነን በምንችለው ሁሉ ልንታገለው የገባል  !!          የአ...
27/08/2021

👉 ዝምተኛው እና ቁማርተኛው መንግሥት አማራን መግደል ወንጀል መሆኑን አውቆ የመኖር መብታችንን እስኪያረጋግጥ ድረስ እንቢተኛ ሆነን በምንችለው ሁሉ ልንታገለው የገባል !!

የአማራም ህዝብ ከተሰለፉበት ጠላቶች ጋር ለአይቀሬው የሞት ሽረት የህልውና ተጋድሎ በመዘጋጀት፣ የበቀል በትሩን አንስቶ፣ ደምን በደም ለማጥራት ሊከት የተገባበት ፅንፍ ላይ እንደ ደረሰ መገንዘብ ይገባዋል።

※ በቃ ምርጫው አንድ ብቻ ነው ፡፡ ሟች ከሞት ለመዳን ራሱን መከላከል፤ ራሱን ማደራጀት፣ ገዳይን ሞት ምን ያህል መራራ መሆኑን ማቅመስ ብቻ ፣ ✔ አለቀ ❗❗

😭😭😭 😭😭😭

26/08/2021

ባንዳው በዋለበት ተራራ ፊት ለፊት ውለን መቀበሪያውን እየጫርንለት ነው‼️

የአጅሬ ጃኖራ ጥቁር አንበሳ አባ ድፈን መሳፍንት ተስፉ አርበኛ አራጋውና የእንቃሹ ጀግና ባየ ጋር አጠር ያለ ውይይት አድርገናል። ዝርዝሩን በተግባር።

ምድራችን ላይ የገባ አይወጣም‼️ መቃብሩ ላይ ቆመን የአማራንና የኢትዩጵያን ትንሳኤ ዳግም እናያለን ✊🏽

25/08/2021

ጃሎ መገን

24/08/2021

ፈፅመን አንዘናጋ!

በደቡብ ጎንደር ትልቅ ሽንፈት የገጠመው ይህ ጠላት በሰሜን ወሎና ሰሜን ጎንደር ያለ የሌለ ኃይሉን እየተጠቀመ ነው። ትኩረት የሚሹ ጉዳዮች፤

1) በጠለምትና በአበርገሌ የገባው ኃይል ተሽሎክሉኮ ወደ ማዕከላዊና ምራብ ጎንደር ተቆራርጦ በመግባት ከቅማንት ኮሚቴ ጋር በመደባለቅ ቢችል ጎንደርን ለመያዝ ዓላማ ይዞ ከፍተኛ ጥረት እያደረገ ይገኛል። ይህ ኃይል ተከዜን በቶሎ ካልተሻገረ አደጋ አለው።

2) በሰሜን ወሎ በኩል ወደ ግሸን ተራራማ ስትራተጂክ ቦታዎችና በአፋር በኩል አድርጎ ወደ ከምሴና ባቲ ለመሄድ የሚንቀሳቀስ ኃይልም አለ። ይህ ኃይል ዋና ዓላማ የኦነግ ኃይል ወደ ቦታው በማስመጣት ጥምረቱን መሬት ላይ ማሳዬት ነው።

ስለሆነም ሳንዘናጋ አሁንም እንታገል፤ ዝመት ክተት። ወያኔ ሳይቀበር ሰላም የለም።
Muluken Tesfaw

23/08/2021

#የተረጋገጠ

!!

ከነፋስ መውጫ ተመቶ የተረፈው የጁንታ ሃይል ከከተማዋ ሸሽቶ ጨጨሆ አካባቢ ምሽግ ውስጥ መግባቱን ከትናንት በፊት ምሽት ላይ ነግሬአችሁ ነበር።

አሁን ጁንታው ከዚህ ምሽግ ምሽጉ ተሰብሮበታል። ከዚህ ያመለጠው ኃይልም ተበትኗል። መስመሩን ይዞ እግሬ አውጭኝ ብሎ የሸሸውም #ደብረዘቢጥ ላይ ምሽግ እንደያዘ መረጃው ደርሶናል። እናማ የለመደውን ድብደባ ይቀምስና ከዚህ ምሽግም አስከሬኖቹን ከምሮ ይወጣል። በነገራችን ላይ በዚህና በተለያዩ ግንባሮች እየተደቆሰ መሆኑ ያስደነገጠው አረመኔ የጁንታ ከትግራይ #እናቶችን ሳይቀር እያፈሰ ወደጦር እያዘመተ ነው።

በዚህ ግንባር የጁንታው ጦር የተረፈረፈበት በርካታ የአስክሬን ፎቶዎችም አሉን። ለሚፈልግ በውስጥ መስመር እልካለሁ። እኔ መለጠፍ ስለማይፈቀድልኝ!!



#ወንዳጥር መኮነን ከጨጨሆ

ሳማንታ ፓወር ፋሽስት ወያኔ ከደቡብ ጎንደር አከርካሪው ተሰብሮ መባረሩን ተከትሎ “እኛ ውጡ ብለናቸው ወጡ” ለማለት እግሬ አውጪኝ ብሎ እየፈረጠጠ ላለው ለፋሽስት ወያኔ “ከአማራና አፋር ክልሎ...
22/08/2021

ሳማንታ ፓወር ፋሽስት ወያኔ ከደቡብ ጎንደር አከርካሪው ተሰብሮ መባረሩን ተከትሎ “እኛ ውጡ ብለናቸው ወጡ” ለማለት እግሬ አውጪኝ ብሎ እየፈረጠጠ ላለው ለፋሽስት ወያኔ “ከአማራና አፋር ክልሎች እንዲወጣ” ጥሪ አስተላልፋለች። ሳማንታ ፓወር በየመግለጫዋ አማራን ከርስቱ ከወልቃይት ይውጣ እያለች ስትጣራ እንዳልከረመች ሁሉ ዛሬ ያንን ሳታነሳ ፋሽስት ወያኔ አከርካሪው ተሰብሮ ከደቡብ ጎንደር መባረሩንና እየፈረጠጠ መሆኑን ስታውቅ ለፋሽስት ወያኔ ብቻ “ሕወሓት ከአማራና ከአፋር ክልሎች በአስቸኳይ ይውጣ” የሚል ጥሪ ማቅረቧ “እኛ ውጡ ብለናቸው ወጡ” ለማለት ከመፈለጓ ባሻገር ፋሽስት ወያኔም “አሜሪካ ውጡ ስላለችን ወጣን” በሚል ሰበብ ሽንፈቱን እንዲሻፍን ለማደረግ ታስቦ ነው። ነቄ ብለናል! አቻምየለህ ታምሩ

የጁንታው ኮሎኔል ተማረከ!! ሌ/ኮሎኔል ገ/ህይወት ገ/አላፍ ይባላል። ከጋሳይ ግንባር የወገን ጦር መድረሻ ሲያሳጣው እጅ የሰጠ ጁንታ ኮሎኔል ነው። 4 የተለያዩ መታወቂያዎችን ይዟል። በአሽሽ ...
21/08/2021

የጁንታው ኮሎኔል ተማረከ!!

ሌ/ኮሎኔል ገ/ህይወት ገ/አላፍ ይባላል። ከጋሳይ ግንባር የወገን ጦር መድረሻ ሲያሳጣው እጅ የሰጠ ጁንታ ኮሎኔል ነው። 4 የተለያዩ መታወቂያዎችን ይዟል። በአሽሽ ተለውሶ የተጋገረ ብስኩቶችንም ይዞ ተገኝተዋል። በርከት ያሉ የባንክ አካውንቶችም ተይዘዋል። ኮሎኔሉ ጦራቸው እንደተበተነ፤ ተስፋ እንደቆረጡ፣ ስርዓት የማፍረስ ተልዕኮ እንደያዙ ይናገራሉ።

20/08/2021

እንደኔ ማምለክ የምትወዱ
በዚህ አምልኮ ከፍ ካላሉቹ መንፈስ ካልነካቹ እኔ ልጠየቅ
ክብር ለመንፈስ ቅዱስ የጌታ ስም ይባረክ አሜን

19/08/2021

ስሜት ቀስቃሽ ሽለላ

መጠርጠር የሌለበት አንድ ሀቅኢትዮጵያ እኛ አማራዎች  እያለን እግዚአብሔር በመንበሩ እያለ  አትፈርስም! ኢትዮጵያ
18/08/2021

መጠርጠር የሌለበት አንድ ሀቅ
ኢትዮጵያ እኛ አማራዎች እያለን እግዚአብሔር በመንበሩ እያለ አትፈርስም! ኢትዮጵያ

ነሀሴ 7 ቀን 2013በከሃዲው የቀድሞው የ31ኛ ክ/ጦር አዛዥ ብ/ጄ ከበደ ፍቃዱ የሚመራው የጠላት ጦር በወልድያ መግቢያ ጥቁር ውሃ አካባቢ ተደምስሷል ፡፡በዚህ ውጊያ ከ70 በላይ የጠላት ሃይ...
13/08/2021

ነሀሴ 7 ቀን 2013

በከሃዲው የቀድሞው የ31ኛ ክ/ጦር አዛዥ ብ/ጄ ከበደ ፍቃዱ የሚመራው የጠላት ጦር በወልድያ መግቢያ ጥቁር ውሃ አካባቢ ተደምስሷል ፡፡

በዚህ ውጊያ ከ70 በላይ የጠላት ሃይል ሊደመሰስ ችሏል ፡፡

ጀግኖቹ የ21ኛ ክ/ጦር የሰራዊት አባላት የድል ችቦዋቸውን ከፍ አድረገው እያውለበለቡ በጥቁር ውሃ ላይ ሌላ አዲስ ታሪክ መስራታቸውን ቀጥለዋል።

ክፍለ ጦሩ በጥቁር ውሃ አካባቢ በወገን ጦር ላይ ጥቃት ለማድረስ በእንቅስቃሴ ላይ የነበረውንና በከሃዲው ጀነራል ከበደ ፍቃዱ የሚመራውን የጠላት ጦር በአስደናቂ የወታደራዊ ስልት መደምሰስ መቻሉን የ211ኛ ብርጌድ ዋና አዛዥ እና ም/አዛዥ ለኦፕሬሽናል አስታውቀዋል።

አዛዦቹ እንዳስታወቁት ፣ በሰራዊቱ እልህና ቁጭት አስደናቂ የጀግንነት ተግባር ፈፅመናል ብለዋል።

ክ/ጦሩ በጥቁር ውሃ አካባቢ ለይ በፈፀመው የጀግንነት ውሎው ከ70 በላይ የጠላት ሃይል ሲደመሰስ ፣ 19 ክላሽን ኮቭ መሣሪያ ፣ 5 ስናይፐር እና በርካታ ቁጥር ያላቸው ከከባድ እስከ ቀላል የጦር መሳሪያዎች ተማርከዋል ።

ሠራዊቱ አሁንም የህልውና ዘመቻውን በአስተማማኝ የጀግንነት መንፈስ ለመወጣት ከመቸውም ግዜ በላይ ዝግጁ መሆኑንም አረጋግጠዋል።

Address


Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ሰከላ ሚዲያ Sekela Media posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Videos

Shortcuts

  • Address
  • Alerts
  • Videos
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share